Thursday, February 28, 2013

በከፍተኛ ጉጉት ሲተበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቋ ፡፡


በከፍተኛ ጉጉት ሲተበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ በአሁኑ ሰዓት ተጠናቋ ፡፡ ከተመዘገቡት 870 መራጮች መካከል ከ800 በላይ ያህሎቹ  ድምጻቸውን መስጠታቸው ታውቋል ፡፡  ከአሁን በኋላ የሚቀረው ሂደት የካርዱን ብዛትና የመራቹን ቁጥር ማነጻጸር ፤ ድምጹን ቆጥሮ ቃለ ጉባኤ መፈራረም ፤ የመገናኛ ብዙሃንን በመጥራት ማን ምን ያህል እንዳገኝ መግለጽ እና ቀጣይ ፓትርያርኩን የማወጅ ስራ ብቻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አባላትና የምርጫው ታዛቢዎች በጋራ÷ በምርጫው ላይ የተገኙና ያልተገኙ መራጮች ቁጥር እኩል መኾኑን፣ እንዲሁም መራጮች የተቀበሉት የድምፅ መስጫ ወረቀትና በሣጥን ውስጥ የተገኘው የድምፅ መስጫ ወረቀት እኩል መኾኑን አረጋግጠዋል፤ በቃለ ጉባኤም ተመዝግቧል፡፡በአሁኑ ወቅት የአስመራጭ ኮሚቴ አባላትና ታዛቢዎች በጋራ÷ እያንዳንዱ ድምፅ ሰጪ የሰጠው ድምፅ ዋጋ ያለው (የሚቆጠር) መኾኑን አለመኾኑን የመለየትና የመወሰን ሥራ በመሥራት ላይ ናቸው፡፡
ስድስተኛው ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ…………… ሆነዋል የሚለውን ድምጽ እንጠብቃለን፡፡
የድምፅ ቆጠራው ውጤት ታውቋል፡፡
ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በ500 ድምፅ አሸናፊ ! ! !
ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – በ98 ድምፅ
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – በ39 ድምፅ
በዚህም መሠረት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካቲት 24 ቀን 2005 ዓ.ም በመንበረ ተክለ ሃይማኖት የሚሾሙ ስድስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ይኾናሉ፡፡

No comments:

Post a Comment