Monday, February 4, 2013

መድረክ የአሰራር ችግር የለበትም ሲሉ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ


ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር እና የመድረክ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ይህን የተናገሩት ኢሳት የግንባሩን ማንፌስቶ መጽደቅን አስመልክቶ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ ነው።
ዶ/ር ነጋሶ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ ግንባሩ ያካሄደው ጉባኤ የተሳካ ነበር። በቅርቡ አቶ ቡልቻ ሚዴቅሳና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክን አስመልክቶ የተናገሩት ችግር በአሁኑ ጉበኤ ተነስቶ ተነጋግራችሁበታልን? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ዶ/ር ነጋሶ ችግሩ ተነስቶ እንዳልተወያዩበት ግለሰቦቹ በግላቸው የሰጡት አስተያየት ትክክል እንዳልነበር ገልጸዋል።
ኢሳት ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የነበረው የመድረክ ህገደንብ ጸደቀ በሚል የሰራው ዘገባ ትክክል እንዳልነበር የገለጡት ዶ/ር ነጋሶ፣ ህገ ደንቡ ከስድስት ወራት በፊት የጸደቀና አሁን ማሻሻያ እንደተደረገበት ተናግረዋል።

በስዊዘርላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሳካ የኢሳት የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት አደረጉ

ጥር 27 ቀን 2005 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው አርቲስት ታማኝ በየነ እንዲሁም ጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን በክብር እንግድነት በተገኙበት ጀኔቫ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ለኢሳት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።
የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ የሆነው ወጣት ጴጥሮስ አሸናፊ እንደገለጠው ዝግጅቱ ከታሰበው በላይ በስኬት መካሄዱን ገልጿል ( )
አርቲስት ታማኝ በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ለኢሳት የሚያደርገውን ድጋፍ በስዊዘርላንድ ጀምሯል። ከአውሮፓ አገራት መካከል በስዊድን ፣ በኖርዌይ ፣ በጀርመን ፣ በቤልጂየም፣ በሆላንድና በለንደን የኢሳት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት እንደሚደርግ የኢሳት የድጋፍ አሰባሰባቢ ኮሚቴ ያወጣው መርሀ ግብር ያሳያል።

      No comments:

      Post a Comment