ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዞኑ ያለው ችግር እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ ፣ የችግሮች ምንጭ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች እየተያዙ ሲሆን፣ መምህር ጸጋየ ገብረመስቀል የተባሉት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሎች ሶስት ተፈላጊ መምህራን ለመሸሸግ የተገደዱ ሲሆን፣ ፖሊስ እያሳደዳቸው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም አሉ።
ከትናንት በስቲያ በእስር ላይ ከሚገኙት ከአቶ ዱባለ ገበየሁ እና ከሁለት ጠበቆች የእስር ቦታ ማዛወር ጋር በተያያዘ የታዘዙትን ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆኑ ኮንስታብል ዘነበ ዶዮ እና ኮንስታብል ሚስታ ናቸው።
የታሳሪዎቹንና የታሰሩበትን እስር ቤት የሚያሳይ ፎቶግራፍ በፌስ ቡክ ላይ መለጠፉ ያስደነገጠው የዳውሮ ፖለቲካ ክፍል ሃላፊዎች በእስር ቤት እስረኞቹ ኮምፒተር ሳይጠቀሙ አይቀርም በሚል ሥጋት የሌሊት ጥበቃ ፖሊሶች በተጠናከረ ጥበቃ ሌሊቱን እንዲያሳልፉ ልዩ መመሪያ እንደተሰጣቸው ታውቋል።
ኢሳት እስር ቤት እያሉ ቃለመጠይቅ ያደረገላቸውን አቶ ዱባለ ገበየሁን በልዩ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸው የወረዳው ፖሊስ ትእዛዝ ደርሶታል። ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንዳይታሰሩና ለብቻ ተለይተው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
ሕዝቡን ቀስቅሰዋል በሚል ግምት የታሰሩትን ዐቃብያን ህጎች በግንቦት 7 አባልነት ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል።
የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አሰፋ በመሩት የደህዴግ ካድሬዎች ስብሰባ ላይ አባሎቹ ችግሮችን ለማስታገስ ተብሎ የሚወሰደው የእሥራት እርምጃ ሕዝቡን ወደ ከፋ ሁኔታ ሊመራው ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
የኔሰው ገብሬ ራሱን አቃጥሎ ባጠፋበት የዳውሮ ዞን የሚነሱ የመብት አሁንም እንደቀጠሉ ነው።
No comments:
Post a Comment