Monday, February 4, 2013

በገንዘብዎ ሳይሆን በጊዜዎ የሚገዙት ሎተሪ በኢሳት !


የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን / ኢሳት / በሬዲዮ፣በቴሌቪዥን፣ በድህረ ገጽ፣ በፌስ ቡክና በትዊተር የሚዲያ ዘርፎቹ  በወር ከ7.6 ሚሊዮን በላይ ጎብኚ ያለው ነው። ይህ ከፍተኛ አድማጭና ተመልካች ያለው የሚዲያ ተቋም በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ያለውን ተቀባይነት ጠብቆ ለመቆየት፤  ስራውን እያሳደገና ወደ ኢትዮጵያ የሚያድርገውንም የቴሌቪዥንና ሬዲዮ ስርጭት አስተማማኝ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል። በሚያስተላልፈው ፕሮግራምም የተለያየ የህብረተሰብ ክፍልን ፍላጎት ለማሟላት በየጊዜው ያልተቋረጠ ፕሮግራሞችን የማስፋፋት ስራም እያከናወነ ነው። ከዚህም ውስጥ አንዱ ለንግዱ ማህበረሰብ የገበያ ምንጭ የሆነው ሸማች ተሰባስቦ የሚገኝበት ብቸኛ የጋራ ቦታ በሆነው የኢሳት ሚዲያ የማስታወቂያ አገልግሎት ለመስጠት አቅዷል። የመጀመሪያውን የማስታወቂያ አገልግሎትም ኢሳትን ከገንዘብ ድጋፍ አንስቶ ገንቢም ሆነ ነቃፊ አስተያየት በመስጠት የአንድ ወገን ሚዲያ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መድረክ አንዲሆን ላደረገው ህዝብ  ጊዜን አንጂ ገንዘብን የማይጠይቅ የሎተሪ እጣ በማዘጋጀት  የንግዱ ማህበረሰብ ምርትና አገልግሎቱን በማስተዋወቅ ከሸማቹ ጋር እንዲገናኝ ጋብዟል።
ከማስታወቂያው የሚገኘውም ገቢ  ኢሳት ለኢትዮጵያ ህዝብ እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት ለማስፋፋትና  በአገር ቤትም ስርጭቱን በአስተማማኝነት ለማስቀጠል ለሚያስችለው ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚውል ነው።
ስለዚህ ገንዘብዎን ሳይሆን የሁለት ደቂቃ ጊዜዎትን በመክፈል የሎተሪ ቅጹን ይሙሉና የሎተሪው ተሳታፊ ይሁኑ። በሎተሪው የሚያገኙት እጣ ለ15 ቀናት የሚቆይ፣ በሳምንት ለ3 ቀናት፣ በቀን ለ30 ሰከንድ የንግድ ድርጅትዎን ምርትም ሆን አገልግሎት ለማስተዋወቅ የሚያስችል እጣ አሸናፊ የሚያደርግዎት ይሆናል። የእጣውም ብዛት 5 ሲሆን ፤ ከዚህ ውስጥ የአንዱ እጣ ባለ እድል  በመሆን ምርትዎንም ሆነ አገልግሎትዎን በኢሳት ሬዲዮን አማካኝነት በሚሊዮኖች  ጆሮ እንዲገባ ለማድረግ እጣውን ሞልተው  advert@ethsat.com በሚለው የኢሜል አድራሻ ለኢሳት የአየር ሰዓት ሽያጭና ማስታወቂያ ክፍል  ይላኩ።
ሎተሪው የሚወጣበት ቀን ማርች 03/2013 ነው።
ምርትዎንም ሆነ አገልግሎትዎን የኢትዮጵያውያን አይንና ጆሮ በሆነው ኢሳት ያስተዋውቁ !
Lottery Form
Business Name………………………………………………………..        Country………………………………………………………
Email address………………………………………………………………      City……………………………………….
Business phone No…………………………………………
Cell phone No…………………………………………..

    No comments:

    Post a Comment