Monday, April 1, 2013

በፌስ ቡክ አስተያየት የፃፈ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ታሰሩ !


በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሙስና ይፈፀማል ብሎ የማኅበራዊ መገናኛ መድረክ በመሆነዉ ፌስ ቡክ የፃፈ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ መታሰሩ ተሰምቷል።
በአዲሱ የአዲስ አበባ ቴክኒዎሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነዉ ወጣት በዚሁ ምክንያት ታስሮ ወደአርባምንጭ መወሰዱን ወኪላችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል። የአርባ ምንጭ ፖሊስ የሰዎች ስም የሚያጎድፍ በማዉጣቱ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከአዲስ አበባ ወስደን ለፍርድ ለማቅረብ ጉዳዩን እያጣራሁ ነዉ ማለቱንም ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር በዘገባዉ ጠቅሷል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር  audio here http://www.dw.de/popups/mediaplayer/mediaId_16712823
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ
dw.de

No comments:

Post a Comment