Monday, April 15, 2013

እነ ማን ነበሩ? አሁንስ ማን ናቸው?


ገብረመድህን አርአያ

ፐርዝ፤ አውስትራሊያ
ይህ ጽሑፍ ትኩረት የሚሰጠው በትግል በረሃ በነበርንበት ወቅት ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት.) በክርስትና እና በእስልምና ሃይማኖቶች ላይ ሲከተል የነበረውን አቋሙን
Gebremedhin Araya former TPLF
አቶ ገብረመድህን እርአያ
ተቀብሮ ከነበረበት ጉድጓድ አውጥቼ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እነማን ናቸው የሚለውን ታሪካቸውን እና የተፈጸመውን ጸረ-እምነት ግፍ በአጭሩ ለማሳወቅ ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. ገና ሲፈጠርና ተ.ሓ.ህ.ት. ተብሎ እንደተመሰረተ ሙልጭ ያለ ጸረ-ዲሞክራሲ ድርጅት ነው። በጸረ-ኢትዮጵያነትና በጸረ- ሕዝብነት የተሰማራ ቅጥረኛ ድርጅት መሆኑን ብዙ ጊዜ በጽሑፍና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናግሬአለሁ። የአሁኑ ጽሑፌ ህ.ወ.ሓ.ት. በሃይማኖት ላይ ሲከተለው የነበረውን ፖሊሲ ገና ከመጀመሪያ ትግሉ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የነበረውን ጸረ- ሃይማኖት ተግባራቱን የኢትዮጵያ ሕዝብ በግልጽ አውቆታል። እኔ ደግሞ የራሴን ልበል።
በ1969 መጀመሪያ ጀምሮ “ወይን” በሚለው የድርጅቱ ልሳን መጽሔት ላይ በተደጋጋሚ “የክርስትና ሃይማኖትና አማራው” በሚል ርእስ ተጽፎ የሚወጣው ጽሑፍ፣ “የክርስትና ሃይማኖት የአማራው ዋና መሳሪያና የግዛቱን ህልውና ማስጠበቂያ ነው፣ በመሆኑም የትግላችን ጠላት አማራውና መሳሪያው የተዋህዶ ክርስትና ስለሆኑ አብረው እንዲጠፉ ማድረግ አለብን” እያለ ያትት ነበር።
ይህንን መጽሔት በሰፊው ለታጋዩና ለአባላቱ በማሰራጨት ሰፊ ቅስቀሳ አካሂዶበታል። በነሐሴ 1969 “ወይን” መጽሔት አማርኛ ቋንቋም አብሮ መጥፋት እንዳለበት ሃተታ ይዞ ወጥቷል።
“ወይን” የምትለውን መጽሔት የሚያዘጋጁት ከፍተኛ የአመራር አባላት በፕሮፓጋንዳ ቢሮ ሆነው ለዚሁ ተግባር የተዘጋጁ ጽሑፎችን በስፋት የሚያሰራጩት፣ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ ነበሩ። እነዚህ ሶስቱ የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር አባላት እብዶችና በጸረ- ሃይማኖት፣ ጸረ-አማራ ባህሪያቸውና አቋማቸው በሰላማዊው ህብረተሰብና ታግዩም ጭምር በግልጽ የሚታወቁ ናቸው።
የሕዝብ ግንኙነት ቢሮ የሚመራውም በነዚህ ሶስት እብድ አመራሮች ነበር። ከዚህ በመነሳት መስከረም 1970 በጸረ-ሃይማኖት፣ በተለይም በተዋህዶ ኦርቶዶክስ ላይ ቅስቀሳውን በስፋት ለማካሄድ በማሰብ፣ ሕዝብ ያሳምናሉ ተብለው የሚታመንባቸውን ታጋዮች መርጠው እገላ ወረዳ መሬቶ ተብላ በምትጠራ ቁሽት ውስጥ ተሰብስበው ቦታ ተዘጋጅቶ ከላይ በተጠቀሱት ሶስቱ አመራር ሴሚናር ተዘጋጀ። በሴሚናሩ ላይ የሚከተሉት ታጋዮች ተካፍለው ነበር፤
1. መርሳ ረዳ 9. ጉእሽ ጓእዳን
2. ሃለቃ ፀጋይ በርሄ 10. ቢተው በላይ
3. ቴዎድሮስ ሃጎስ 11. ሃድሽ ገዛኸኝ
4. አባይ ወልዱ 12. ሮማን ገ/ሥላሴ
5. ሃዳስ ዓለሙ 13. አፈራ ተክለሃይማኖት
6. ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን 14. ወልደገብርኤል ሞደርን
7. ሃሪያ ሰባጋድስ 15. አዲስዓለም ባሌማ
8. ቅዱሳን ነጋ
ከላይ የተጠቀሱት ታጋዮች በተካሄደው ሴሚናር በጸረ-ክርስትና እና በጸረ-እስልምና አስተሳሰብ በሶስት ቀን ውስጥ ተጠምቀው ጨረሱ። እንደጨርሱም በሶስት ሪጅን ተመደቡ፤ አመዳደባቸውም፤ ሪጅን 1 መርሳ ረዳ፤ ሪጅን 2 ሃለቃ ጸጋይ በርሄ፤ ሪጅን 3 አዲስዓለም ባሌማ በሃላፊነት እንዲመሩት ተመረጡ። ቀሪዎቹም በእነዚህ የበላይ ተጠሪዎች ስር ተደለደሉ።
ሪጅን 1 ሪጅን 2 ሪጅን 3
መርሳ ረዳ ተጠሪ ጸጋይ በርሄ ተጠሪ አዲስዓለም ባሌማ ተጠሪ
1-ጉእሽ ጓእዳድ 1-ቅዱሳን ነጋ 1-ቴዎድሮስ ሃጎስ
2-አባይ ወልዱ 2-ሃዳስ ዓለሙ 2-ወ/ገብርኤል ሞደርን
3-ኃ/ሥላሴ ገ/ኪዳን 3-ቢተው በላይ 3-አፈራ ተ/ሃይማኖት
4-ሃርያ ሰባገድል 4-ሃድሽ ገዛኸኝ
5-ሮማን ገብረሥላሴ
በዚህ መልክ ተደራጅተው በየሪጅኑ ተሰማሩ። ድጋፍ ሰጪ የሕዝብ ግንኙነት ካድሬዎችም በየድርጅቱ በስፋት ተሰማሩ። እነዚህም በተጠናከረ ሃይል ጸረ-ክርስትና፣ ጸረ-አማራ፣ ጸረ-እስልምና ቅስቀሳቸውን ቀጠሉበት። በተዋህዶ ክርስትና ላይ ሙሉ ሃይላቸውን በመጠቀም በስፋት ጸረ-ክርስትና ቅስቀሳውን በተከታታይ እሁድና ሌሎች በዓላት እንዳይከበሩና የሥራ ቀን መሆናቸውን በማወጅ በህብረተሰቡ ላይ ካባድ ተጽእኖ አሳደሩበት። ቀሳውስትና ዲያቆናት በማንኛውም በዓላት ቤተ ክርስቲያን ከፍተው ሲቀድሱ ቢገኙ ከባድ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስጠነቀቁ። አልፎ አልፎ ተቃውሞ ይገጥማቸው ስለነበር በበላይ አመራሩ ለእነ ስብሃት ነጋ ምን እናድርግ እያሉ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። ከአመራሩ የተሰጠው ምላሽ፣ ማንም ያንገራገረ ቄስ፣ ባህታዊ፣ ዲያቆን ወይም ሌላ እዛው ባለበት በሕዝቡ ፊት ግደሉት የሚል መመሪያ ተሰጣቸው። በዚህ መሰረት አድዋ አውራጃ እንዳባጻህማ ወረዳ የሚገኘው እንዳሥላሴ ተብሎ የሚታወቀው ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን መሪ አባ ሃይለሥላሴ የሚባሉ ቄስ፣ “ሃይማኖታችንን አታርክሱት፣ የተቀደሰ ሃይማኖት ነው” ብለው ስላሉ በቦታው የነበረ ጸጋይ በርሄ የሚባል ታጋይ በያዘው አጭር ጓንዴ ተኩሶ ጭንቅላታቸው ላይ በመምታት በሕዝብ ፊት ገደላቸው። ቀሪው ምእመናን ተደናግጦና በርግጎ ተበታተነ። ሃለቃ ጸጋይ በርሄ በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የነበረውን ንብረትና ሃብት ጠራርጎ ወሰደው። በተመሳሳይ፣ ዛና ወረዳ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን መሪ የነበሩት አባ ቄስ አርአያ ከአንድ የ90 ዓመት አዛውንት ባህታዊ ጋር ሆነው፣ “እባካችሁ ሃይማኖታችንን አታርክሱብን” በማለታቸው ከቢተው በላይ ጋር ተደራቢ ሆኖ የሄድው አርከበ እቁባይ ሁለቱን ንጹሃን ዜጎች በሕዝቡ ፊት ገደላቸው። በስብሃት ነጋ፤ አባይ ፀሃየና መለስ ዜናዊ የሚመራው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ከላይ የተጠቀሱትን 15 ታጋዮች የተግባሩ ፋጻሚዎች በማድረግ በርካታ ቤተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል። ከአድዋ፣ አክሱምና ተምቤን አውራጃዎች ብዙ ቀሳውስትና ባህታውያን እንዲሁም ዲያቆናት ሌሊትና ቀን እየታፈኑ ተውስደው የውሃ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።
የእስልምና ሃይማኖትን በተመለከተ፤ እስልምና ተከታይ ኢትዮጵያውያን ጸሎት ለመድረግ በሚሰበሰቡበት ጊዜ እየጠበቁ ጸረ-እስልምና ሰበካዎችን ለማራመድ በየመንገዱ ቅዱሱን ነብዩ መሃመድን እና ቅዱስ ቁርአንን ማብጠልጠልና ማራከስ በጀመሩበት ወቅት፤ ከሪጅን 1-3 በሚገኘው የእስልምና ተከታይ ሰፊ ተቃውሞ ገጠማቸው። በተለይ በሪጅን 3 አፋሮች የእስልምና ተከታዮች ስለሆኑ ጸረ-ወያኔ ተቃውሞ በማሰማት ለእምነታችን እንሞታለን፤ እንዋደቃለን በማለት ከፍተኛ ተቃውሞ አሰሙ። በሪጅኑ የተመደቡትን የህ.ወ.ሓ.ት. አባላት ተከታትለው በማደን ገደሏቸው። ከተገደሉት መካከል፣ ትእግስት አሰፋ፣ የኋላሸት ገ/መድህን (አላሚን)፣ ፀሃየ አብርሃ ወዘተ ይገኙበታል። የዚህ አይነቱን ተመሳሳይ እጣ በታጋዮች ላይ በተደጋጋሚ አድርሰዋል። የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ስለሁኔታው ሲጠየቅ እስከ አሁን ድረስ ድርጊቱን በመካድ በጦርነት ሞቱ እያለ ይዋሻል። በጦርነት ሳይሆን ነቢዩ መሃመድን በማንቋሸሻቸውና ቅዱስ ቁርአንን በማቃጠላቸው በአፋር ሕዝብ የተገደሉ ናቸው። ቀሪዎቹ ማለትም አዲስዓለም ባሌማ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስና አፈራ ተክለሃይማኖት ጨለማን ተገን በማደግ ሸሽተው በዱር በገደል ሲያመልጡ ተሰባብረውና ገርጥተው ባንድ ወር ጊዜ አጋሜ አውራጃ ሶቦያ ደርሰው ሕይወታቸውን አዳኑ። በዚህ ምክንያት ህ.ወ.ሓ.ት. እስከ 1976 ድረስ አፋር ውስጥ መግባት ስለፈራ እንቅስቃሴውን አቆመ።
በዚህ ወቅት በርካታ ቅዱስ ቁርአን እና መጽሐፍ ቅዱስ በህ.ወ.ሓ.ት. የተዘረፈ ንብረት ማጠራቀሚያ ውስጥ ታጉረው ለእሳት ማቀጣጠያ ይደረጉ እንደነበር በርካታ በጊዜው የነበሩ ታጋዮች የሚናገሩት የነበረ ሃቅ ነው።
የእስልምና ታከታዩ ኢትዮጵያዊ በወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የተጀመረውን ጸረ-እስልምና እንቅስቃሴ በሶስቱ ሪጅን የሚኖረው አማኝ ከፍተኛ ተቃውሞ በማስነሳት በአንድነት ቆመ። ወይ ወያኔ ይጨርሰን አለበለዚያ እኛ እንጨርሳችኋለን እንጂ በሃይማኖታችን አትገቡብንም በማለት የህ.ወ.ሓ.ትን አመራር ጉሮሮ ያዙት። የወያኔ አመራር በሁኔታው ተደናገጠ። በገጠርም ሆነ በከተማ የሚኖረው ሕዝብ ይህንን ድርጊት የሚፈጽሙት የአመራር አባላት የሆኑት ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊና አባይ ፀሃየ መሆናቸውን በማወቁ እነዚህ ግለሰቦች በፍርሃቻ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አቆሙ፣ ከተንቀሳቀሱም በታጋይ እየታጀቡ ሆነ። በዚህ ጊዜ ወያኔ በኢ.ዲ.ዩና በኢ.ህ.አ.ፓ. የተወረረበት ወቅት ስለነበረ የአመራሩ የትግል ስሜት መሬት የወረደበት ጊዜ ነበር። ከዚህ በመነሳት ለጸረ-ሃይማኖት ተግባር ለተመደቡት ታጋዮች አስቸኳይ ትእዛዝ በማስተላለፍ ጸረ-እስልምና እንቀቃሴአቸውን እንዲያቆሙ፣ ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት ሥራቸውን ግን እንዲቀጥሉበት ታዘዙ። ጸረ- ክርስትናው ቀጠለ። በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚኖሩት የእስልምና ሃይማኖት እህቶቻን እና ወንድሞቻችን ከዛች ቀን ጀምሮ ለወያኔ መታዘዛቸውን አቆሙ። ክርስቲያኑ ወገን የህ.ወ.ሓ.ት. ንብረት አመላላሽ እየሆነ ሲያገለግል የእስልምና ተከታዮች ኢትዮጵያውያን ግን ሳይደፈሩ ተፈርተው ለዓመታት ቆዩ።
የካቲት 1971 የህ.ወ.ሓ.ት. 1ኛው ጉባኤ በተካሄደበት ጊዜ የተመረጠው አመራር ማለትም፤ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ስብሃት ነጋ፣ የፕሮፓጋንዳው ሃላፊዎች መለስ ዜናዊን እና አባይ ፀሃየን መረጠ። እነዚህ ሶስቱ ጸረ-ሕዝብ አመራሮች ሃይላቸውን እና ጉልበታቸውን በማጠናከር ድርጅቱ ያወጣውን በርካታ አዳዲስ ፖሊሲ ግንባር ቀደም በማድረግ በሥራ ላይ ማዋል ጀመሩ። እነሱም፣ የተዋቅህዶ ክርስትና ሃይማኖት የአማራው መሳሪያና መገልገያ ስለሆነ፣ እግዚአብሄር የሚባል ነገርም ስለሌለ፣ ከአሁን ጀምረን ከነፃ መሬታችን ጠራርገን ማጥፋት አለብን። ለወደፊትም የሃገራችን የትግራይ መንግሥት ሲቋቋም ሕዝባችን ከማንኛውም አጉል እምነቶች ነፃ የሆነ ሃገር እንመሰርታለን በማለት የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ወሰነ።
ከላይ የተጠቀሰው እንዳለ ሆኖ፣ በአዲስ ጉልበትና አዲስ ጸረ-ተዋህዶ ክርስትናን ማዳከሚያ ፖሊሲ ተጠናክሮ ወጣ። በተግባር ከተፈጸሙት መካከል፣
1. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚገኙት አብያተክርስትያናት ያላቸውን ሃብትና ንብረት በሙሉ ለህ.ወ.ሓ.ት. እንዲያስረክቡ ታዘዘ፣
2. ቄሶች ቆባቸውን እና ጥምጥማቸውን አውልቀው በመጣል የህ.ወ.ሓ.ት. “ወየንቲ” (ሚሊሻ ማለት ነው) እንዲሆኑ ተወሰነ፤ በተግባርም ታየ። ቄሶች የህ.ወ.ሓ.ት. ምንሽር፤ ጓንዴ፤ አልቤን እየተሸከሙ የህ.ወ.ሓ.ትን ነፃ መሬት ጠባቂ ሆኑ።
3. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚገኙ ዲያቆናት ትዳር የመሰረተ ትዳሩን አፍርሶ ከነሚስቱ ወደ ትግል ሜዳ እንዲቀላቀሉ፣ ትዳር የሌለው ደግሞ በቀጥታ ወደ ትግሉ እንዲገባ ተብሎ ተወሰነ። ብዙ ትዳር ፈርሶ በውዴታም በግዴታም የህ.ወ.ሓ.ት. ታጋይ ተደረጉ።
ወላጆች ጧሪ አልባ ሆነው ቀሩ። አብያተ ክርስቲያናት ካለ ቀዳሽና አገልጋይ ክፍት ሆነው ቀሩ። አብያተ ክርስቲያናት በዘራፊው የህ.ወ.ሓ.ት. ማፊያ ቡድን ተዘረፉ። በወያኔ አመራር የተዘረፈው ጥንታዊና ታሪካዊ መጽሐፍት፤ ውድና ብርቅ ጥንታዊ ታሪካዊ ንብርቶች ሲዘረፉ፣ በርካታ የግእዝ የብራና መጽሐፍትና ቅዱሳን መጽሀፍት ተቃጠሉ።
ይህንን ጸረ-ሃይማኖት ድርጊትና የማውደም ሥራ እንዲከናወን በተለያዩ ጊዜያት ትእዛዝና አመራር የሰጡት፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊና አባይ ፀሃየ ነበሩ። በተባባሪነት ተጨማሪ እርዳታ የሚያደርጉት ደግሞ፣ አርከበ እቁባይ፣ ኤርትራዊው ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ አውአሎም ወልዱ፣ ዘርአይ አስገዶም፤ ስየ አብርሃ፣ ስዩም መስፍን ሳይጠቀሱ የማይታለፉ ናቸው። እነዚህ የአመራር አባላት የነመለስ፣ አባይና ስብሃት ታማኝና አገልጋይ አሽከሮች በመሆን ሕዝበ እስላሙን እና ክርስቲያኑን ሲያቃጥሉ የታዩ ናቸው። ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንም በማቃጠል አውድመዋል፡
ይህ በዚህ አይነት እየቀጠለ ባለበት ጉዞ፣ ከየአብያተ ክርስቲያናቱ በውድም በግድም የለቀቁ ቄሶችና ዲያቆናት የካድሬ ሴሚናር ለሳምንታት ለመስጠት የሚከተሉት “መሪሕ ባእታ” ካድሬዎች ተመረጡ፤
1. ሙሉጌታ ጫልቱ 6. ጎበዛይ ወ/አረጋይ
2. ዘርአይ አስገዶም 7. አባይ ወልዱ
3. መርሳ ረዳ 8. ቅዱሳን ነጋ
4. አክሊሉ ደንበአርቃይ 9. ግደይ በርሄ
5. ገብረኪዳን ደስታ 10. ቢተው በላይ
እነዚህ ካድሬዎች በሪጅን 1 እና 2 በመመደብ በተለያዩ ቦታዎች በመሰማራት ቀሳውስትና ዲያቆናትን ከ1973 መጀመሪያ አንስቶ ለስድስት ወራት በመዘዋወር የማርክሲስም ሌኒኒዝም ትምህርት በማስተማር በክለው ጸረ-ክርስትና ሃይማኖት አደረጓቸው። በሚመረቁበት ጊዜ በእነ ኢያሱ በርሄ የሚመራው የባህል ቡድን በበዓሉ ላይ በመገኘት ቀሳውስቱ እስክስታውን (ስእሲኢት) አወረዱት፣ አምላክን አወገዙት፣ “ክርስትና ሃይማኖት ከአማራው ጋር አብረው ይደመሰሳሉ” እያሉ በየስብሰባው መክፈቻ መፈክራቸው አደረጉት።
4. በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚከተሉት በአዋጅ ታግደው ነበር። በሕዝብ ግንኙነት በኩል ተፈጻሚ እንዲሆኑም ትእዛዝ ተሰጥቶባቸው ነበር፣ እነሱም
4.1 በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት ሠርግ ታገደ
4.2 ተስካር (ተዝካር) እና የሞት ፍትሃት ታገደ
4.3 አዲስ ለሚወለዱ ሕፃናት ክርስትና እና ጥምቀት ታገደ
4.4 በየወሩ በመሰባሰብ ጸበል ፀዲቅ ማድረግ ታገደ
4.5 በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት በየትኛውም ቦታ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በየዓመቱ የሚያካሂዱት በዓላት ታገዱ።
ከላይ የተጠቀሱትን የህ.ወ.ሓ.ት ትእዛዝ የጣሰ እንደ ጸረ-ህ.ወ.ሓ.ት ተቆጥሮ ሃለዋ ወያነ 06 ገብቶ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድበታል። ሃብት ንበርቱ ለህ.ወ.ሓ.ት ገቢ ይደረጋል። የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ታጋዮችም ይህንን ተግባራዊ አደርገውታል። ስለሆነም ሕዝብ በሃሰት እየተከሰሰ ሃለዋ ወያነ በመግባት የስንቱ ሕይወት በከንቱ ጠፍቷል። ንብረታቸው ተወርሶ እናትና ልጆቿ ለክፉ መከራ ተጋልጠዋል። አብያተ ክርስቲያናት ገንዘባቸውና ሃብት ንብረታቸው ተዘርፏል። ይህ በ1969 የተጀመረው ድርጊት ህ.ወ.ሓ.ት እስከ መጨረሻው ቀጥሎበት ፖሊሲውን በተግባር አውሎታል።
ከዚህ ጎን ለጎን ደግሞ በ1969 መጀመሪያ ህ.ወ.ሓ.ት እንደ ግንባር ቀደም ፖሊሲው ያደረገው አማራ የትግራይ ሕዝብ ጠላት ነው የሚለውን ነበር። ለዚህ ዓለማ ብለው የህ.ወ.ሓ.ት አመራር በፕሮግራሙ (ሕገ ደንቡ) የተጻፈውን ቀዳሚውን ፖሊሲውን በአጭሩ እንመልከት፤
አማራው በትግራይ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ተጽእኖ በማጠናከር በትግራይ ሕዝብ ላይ በሚያካሂደው የኢኮኖሚ ብዝበዛ ሕዝባችንን ለድህነት፤ ለረሃብ፤ ለውርደትና መንከራተት ዳርጎታል።
ይህንን ግፍና በደል ጨቋኙ የአማራ ብሄር ሆን ብሎ ፈጽሞታል። በዚህም የተነሳ የትግራይ ሕዝብ በኑሮው እንዲጎሳቆል፤ ለሥራ አጥነት፤ ለሽርሙጥና፤ ለስደት፤ ለለማኝነትና መንከራተት ዳርጎታል። በተጨማሪም የትግራይን ሕዝብ ታሪኩን፣ ቋንቋውን እና ባህሉን እንዲጠፋ አድርጓል። የሶስት ሺህ ዓመታት ታሪካችንን ተነጥቀን የአማራው መመኪያና የግል ታሪኩ አድርጎታል። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ያላት ታሪክ ከንጉሥ ምኒልክ የሚጀምርና እንደሃገር የኖረችውም ከ100 ዓመት አይዘልም። ኢትዮጵያ እንደ ሃገር የተፈጠረችው በአማራው ተስፋፊነት የተነሳ ስለሆነ ከምኒልክ ንግሥና በኋላ ነው።
የአማራው ብሄር የትግራይን ሕዝብ ከአቅሙ በላይ ግብር እንዲከፍል በማድረግና በማስገደድና ጭቆናውን በማራዘም የትግራይን ሕዝብ ከሰብአዊ ፍጡር ውጭ አድርጎታል። የትግራይን ሕዝብ እንደ እንሰሳ በመቁጠር በሚደርስበት ጭካኔ የተሞላ አገዛዝ (ኢሰብአዊነት) ድህነት፣ ረሃብ፣ ውርደትና ስደት እንዲደርስበት አድርጓል። በተጨማሪም የትግራይ ሕዝብ ለረጅም ዘመን ሰብአዊና ፖለቲካዊ መብቱ ተንፍጎ ሲጠላና ሲናቅ እንዲሁም አድልዎ ሲፈጸምበት ቆይቷል። ይህንን በደል ጨቋኟ የአማራ ብሄር ሆን ብላ እንደመንግሥት መመሪያዋ አድርጋ ስትሠራበት ነበር። ከላይ በጥቂቱ የዘረዘርኩት በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ግጽ 8-14፣ 15-16፤ 18 ላይ ተመልክቷል። በአጠቃላይ ፕሮግራሙ ከመነሻው እስከ መጨረሻው አማራን ይወነጅላል። አሁን ደግሞ ደርግ ቀጥሎበታልም ይላል። የትግራይን ሕዝብ ቂሙን እና ጥላቻውን እያለ ይገልጻል። ጨቋኟ አማራም ሕብረተሰባዊ እርፍትና ስላም አታገኝም ብሎ ይደመድማል። ገጽ 16 ላይ ይመልከቱ። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው በኢትዮጵያ ውስጥ የአማራ መንግሥት የሚባል የለም፣ አልነበረምም። ኢትዮጵያ ብዙ ነገሥታትን አፍርታለች። ነገሥታቱም የሚነግሡት በዘር ሃረጋቸው ነበር። ይህም የቤተ መንግሥቱን መቀመጫ በሃይል ሳይሆን በቅብብሎሽ የሚደረግ ነበር። የአክሱም ቤተ መንግሥት ወደ ላስታ ተዘዋወረ፣ ከዚያም ወደ ሸዋና ጎንደር ሲዘዋወር በነገሥታቱም በሕዝቡም ተቀባይነት እያገኘ ነበር። በመጨረሻም ወንበሩ ሸዋ፣ አዲስ አበባ ላይ ሆነ። አፄ ኃ/ሥላሴም በዚሁ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት ውስጥ ነገሡ። የአፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥትም ከኦሮሞ፣ ከትግራይ፣ ከኤርትራ፣ ከአማራ፣ አፋር፣ ጉራጌ ወዘተ ኢትዮጵያውያንን ማእከል ያደረገ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ነበራቸው። ከሚኒስቴር ዲኤታ እስከ መምሪያ ሃላፊዎች ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያቀፈ መንግሥት ነበር።
እንዲያውም ቁልፍ የሆኑትን የሚንስቴር ቦታ ይዘው የነብሩት ትግሬዎች ነበሩ። በሥልጣን ክፍፍሉ አድልዎ አይታይም ነበር። በጤና እና በትምህርት ዋን ተጠቅሚ ትግራይ ነበረች። በዚህም አድልዎ አልታየም። አርመኔያዊ አገዛዝ፣ ኢሰብአዊነት (Dehumanisation) እያለ የህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም የሚለፍፈው እንደዚህ አይነት ተግባር በትግራይ አልታየም። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ የአፄ ኃ/ሥላሴ መንግሥት ምርጥ ምርጡን ለትግራይ ይሰጥ የሚል ስርዓት ነበረው። የትግራይ ሕዝብም ንጉሠ ነገሥቱን ከልብ ይወዳል፤ ንጉሡም የትግራይን ሕዝብ ይወዱ ነበር። ደርግ አፄ ኃ/ሥላሴን እንደገደላቸው ባወቀ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ ከትንሽ እስከ ትልቁ ደርግን ክፉኛ አውግዞት ነበር። የትግራይ ሕዝብ ከአፄ ኃ/ሥላሴ ሞት በኋላ በኑሮው የተጎሳቆለና ለችግር የተጋለጠ ሕዝብ ሆነ። በደርግ ስርዓትም ቢሆን የትግራይ ሕዝብ ለችግርም ሆነ ለረሃብ ብዙ የተጋለጠ አልነበረም። ደርግ የመሬት አዋጁን በትግራይ ውስጥ ተግባራዊ አላደረገውም። ምክንያቱም የእርሻ መሬቱ አነስተኛ በመሆኑ ነበር። ደርግ በሥልጣን ላይ በነበረበት ጊዜ በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ወንጀል የለም። በኑሮም አልተጎሳቆለም። በቀይ ሽብርም ቢሆን የተጠቃው አማራው ነበር። የትግራይን ሕዝብ ያጠቃ፣ ለድህነት የዳረገ፣ ለስደት፣ ለሸርሙጥና እና ለመንከራተት ያበቃውና ችግርና መከራ ይዞለት የመጣው ህ.ወ.ሓ.ት. ብቻ ነው። የህ.ወ.ሓ.ትን ፕሮግርራምና አፈጻፀሙን ካየን፣ ተግባራዊንቱን ደግሞ እንመልከት።
ወደዚህ ከመግባታችን በፊት ግን መመልከት ያለብን ነጥብ አለ። የአፄ ኃ/ሥለሴ መንግሥት ሃገር አቀፍ የሆነ ስርዓት እንጂ በአማሮች ብቻ የሚመራ መንግሥት አልነበረም። አማራው እንደቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የተለየ ጥቅም ተቀባይ አልነበረም። እውነታው ይህ ሆኖ እያለ ህ.ወ.ሓ.ት. ለምን አማራውን ብቻ በጨቋኝነት፣ በዝባዥነትና በጸረ-ሰውነት ፈረጀው? ህ.ወ.ሓ.ት. በ48 ገጾች ሆን ብሎ አማራውን ለማጥቃት ያሰናዳው ፕሮግራም ወንጀል ነው። ከትግሉ መነሻ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት 48 ገጽ ፕሮግራም ያወጣው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው። አሁንም በሥልጣን ላይ ሆኖ በአማራው ላይ የዘር ማጥፋት ድርጊት የሚፈጽመው ህ.ወ.ሓ.ት. ነው። ፕሮግራሙን አርቅቀው እንዲተገበር ያደርጉት እነማን ናቸው? ዝርዝር ስማቸውን እንመልከት፤
1. አረጋዊ በርሄ 8. ተወልደ ወ/ማርያም
2. ስብሃት ነጋ 9. ገብሩ አስራት
3. መለስ ዜናዊ 10. አርከበ እቁባይ
4. አባይ ፀሃየ 11. ጻድቃን ገብረተንሳይ
5. ሥዩም መስፍን 12. ዘርአይ አስገዶም
6. አውአሎም ወልዱ 13. ግደይ ዘርአጽዮን
7. ስየ አብርሃ
ከነዚህ በተጨማሪ ከዚህ አለም በሞት የተለየው አታክለት ቀጸላ፣ በስብሃት ነጋ የተገደለ፤ አስፍሃ ሃገኦስ፣ ታሞ የሞተ፤ ግደይ ዘርአጽዮን ከ1969 ጀምሮ ህ.ወ.ሓ.ትን በጸረ- ዲሞክራሲነቱና በሽብርተኝነቱ ያወገዘ፤ ራሱን ከማንኛውም አስከፊ ተግባር ያገለለ፣ በታጋዩ ተከብሮና ታቅፎ የቆየና በ1977 ከህ.ወ.ሓ.ት. በመለስና በስብሃት ተባሮ የወጣው ኢትዮጵያዊ ይገኝበታል።
በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም በገጽ 16 ተጽፋ የምትገኘው ደርግንም የአማራ መንግሥት በማለት በመፈረጅ ታወግዛለች። ደርግ ግን የአማራ አልነበረም። ከዘረኝነት የጸዳ ነበር። የደርግ ስርዓት ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ ነበር። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህን ሁሉ ውሸት የሚደረደረው ዋናው ምክንያት አማራውን ለማጥቃት የተቀነባበረ “ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ” ነው። በገጽ 16 መጨረሻ ላይ ጽሑፉ እንዲህ በማለት ያጠቃልላል፣ “ጨቋኟ አማራም ህብረተሰብአዊ እረፍትና ሰላም አታገኝም” ይላል።
“ወይን” የሚባለው የህ.ወ.ሓ.ት. ልሳን መጽሔት ከ1969 መጀመሪያ በአማራው ላይ እንዲፈጸሙ በመሬት ላይ ተግባራዊ መሆን አለባቸው ተብለው በአጭርና በረጅም የትግል ጉዞ የተግባር ዝርዝር ሃታታ በስፋት በመዘርዘር አውጥተዋል። ከተዘረዘሩትም አንዱ የአማራው ሕዝብ እረፍትና ሰላም አያገኝም ለመኖርም አይችልም የምትለው የህ.ወ.ሓ.ት. አቋምና ፖሊሲ ይዛለች። ህ.ወ.ሓ.ት. በአማራው ላይ አጸፋዊ እርምጃ ይወስዳል። እርምጃውም አማራው ከመኖር ወደ አለመኖር ይለወጣል። በዚህ መሰረት በወይን መጽሔት የተዘረዘረው በጥር 1969 ወደ ተግባር ተለውጦ አማራው በተገኘበት መግደል ተጀምሮ ከዛም ወደ ወልቃይት ፀገዴ ተሸጋግሮ የዘር ማጥፋት ተካሂዷል።
1. ማንኛውም በህ.ወ.ሓ.ት. ነፃ መሬት የሚኖር አማራ ከትግራይ ለቆ በአስቸኳይ ይውጣ። በሕዝብ ግንኙነት ከያሉበት እየተለቀሙ በርካታ በጡረታ የተገለሉ ጦር ሰራዊት፣ ፖሊስ፣ ፊናንስ ፖሊስ፣ በሌላ የመንግሥት ሥራ ሲሰሩ የነበሩ በተለያዩ ቦታ ይኖሩ የነበሩ፤ ከትግራይ ሚስት አግብተው፤ ልጆች ወልደው ብዙዎቹም ልጆቻቸው ለትዳር የበቁ የልጅ ልጅ ያዩ ናቸው። ይህ ድንገተኛ ዘረኛ የህ.ወ.ሓ.ት. ፖሊሲ እንደተላለፈ አማራውም ከየቦታው እየተያዘ ሃለዋ ወያነ 06 ገብቶ ይጠፋል፣ ንብረቱም ይወረሳል። የትግራይ መሬት ለትግራይ ሰዎች ብቻ በማለት ከሃገራችን ልቀቁልን ይላል። በትግራይ በ1969 የተጀመረው አሁን አማራው ከተለያየ ቦታ እየተጠረገ ተገፍቶ፣ ተፈናቅሎ በረሃ ላይ ወድቆ ይገኛል። ስለዚህ ከመሬታችን ውጡልን የተጀመረው በ1969 በህ.ወ.ሓ.ት. ሲሆን አሁንም ይህንን ክልል ተብለው የሚጠሩ የረጅም ጊዜ ውጥን ህ.ወ.ሓ.ት. በተግባር እፈጸመው ይገኛል። ከህ.ወ.ሓ.ት. ትግል መነሻ ጀምሮ እስከ ዛሬ አማራ ዘሩ እየጠፋ ነው።
2. ኢ.ህ.አ.ፓ. አባይ ኢትዮጵያ ከትግራይ ውጣ ሲባል፣ ትግራይ ኢትዮጵያ እኛም ኢትዮጵያውያን ነን ብለው አንወጣም በማለታቸው ለጥቃት ተዳረጉ።
“ወይን” መጽሔት ከ1969 ጀምሮ በተከታታይ የሚያወጣው ጽሑፍ በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራም ላይ የተቀመጡ የረጅም ጊዜ እቅድ በመተንተን እና በማብራራት ለታጋዩ ለውይይት በማቅራብ ሲያብራራ፣ ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብሎ የሚናገረውን አማራ ማጥፋት ከሱም ጋር አብሮ የሚቀበረው አማርኛ ቋንቋ ይሆናል ይላል።
በህ.ወ.ሓ.ት. ፕሮግራምና በወይን መጽሔት እንደተዘገበው፣ አማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንደመሆኑ በግንባር ቀደምትነት ህ.ወ.ሓ.ት. አማራውን ማጥፋት ግዴታው ነው ይላል። ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ከዓለም ካርታ ፍቆ ለማስወጣት አማራው ሲጠፋ ብቻ ነው በማለት ወይን መጽሔት ይዘረዝራል። ከጎንደር ጠ/ግዛት ከወሎ ለምና ሰፊ መሬት የነጠቀው ወያኔ በፕሮግርራሙ መቅድም V ላይ እንደዘረዘረው እውን ሆኖለታል። በሰፊና ለም መሬት የተከበበች ትግራይ “የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ” ነፃ ሃገር ማቋቋም ግብ አማራው ከጠፋ ተቀናቃኝ አይገጥመኝም በማለት የታቀደ የረጅም ጊዜ የስትራተጂ እቅድ ቀስ በቀስ ወደ ተግባር የሚለወጥ ነው።
የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር ኢትዮጵያን እገዛለሁ የሚል ተስፋም ህልምም አልነበረውም። ደርግ ተዳክሞ በራሱ ጉዞ እንደጠፋ ህ.ወ.ሓ.ት. በለስ ቀንቶት ግንቦት 1983 ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ እንደ ዋናው የፖሊሲ ፕሮጀክትና እቅድ በ1984 መጀመሪያ በተግባር ላይ ዋለ። አማራውን ለብዙ ዓመታት ከኖረበት ቦታ ያፈራውን ሃብትና ንብረቱን፤ በትዳር ከኦሮሞው፣ ከሲዳማው፤ ከወላይታው ጋር ከተሳሰረበት ለአማራው “ነፍጠኛ፣ ተስፋፊ” የሚል ተለጣፊ ስም በመስጠት የአማራው ዘር እየተፈለገ በሁሉም እድሜ የሚገኙትን እየሰበሰበ በጥይት በመደብደብ፤ በገደል በመወርወር ፈጅቷል። ይህንን ተግባሩን እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በመቀጠል በቤንች ማጂና ጉራ ፈርዳ ተመሳሳይ ድርጊት ፈጽሟል። ሊገድላቸው ያልቻለውን ደግሞ የማንገላታት ተባሩን ቀጥሎ የአማራውን ብሄረሰብ እየነጠለ ከጉራ ፈርዳ፤ ከቤኒሻንጉል እንዲባረሩ በማድረግ ለክፉ ሰቆቃ ተዳርገዋል። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ከመመስረቱ ጀምሮ የወጠነውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።
ይህንን ለመተግበር ወያኔ አስቀድሞ ያዘጋጀው እቅድ የአማራውን ቦታ ማጥበብ ነው። ትግራይ ከበጌምድርና ከወሎ ሰፊና ለም መሬት ወስዳለች። ከወሎ ሰፊ መረት ወደ አፋር ተከልሏል፤ የጎጃም መሬት ለአፋርና ለሌሎች ተሰጥቷል፤ ሸዋ እንዳለ የኦሮሞ ሆኗል። በዚህ አይነት የአማራው መሬት ተከፋፍሎ የቀረችው መሬት የበሬ ግንባርም አታክልም። አንድ ነገር ካልተደረገ በስተቀር ነገ ደግሞ ከዚችው ከቀረችው መሬት ውጣ ሊባል ይችላል። ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን አማራውን የማጥፋት “Systematic elimination and genocide” ዋናው ፖሊሲ አድርጎ የተነሳው ገና ትግራይ በረሃ እዳለ ነው። አማራውን መግደል፤ ካልተቻለም በዘዴ ማጥፋት ብሎ ያቀደውን አሁን በግልጽ እያስፈጸመው ነው። አማራው ከሌላው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር በመሆን እኩል መስዋእትነት ከፍሎ ሃገራችንን ዳር ድንበሯን በማስከበር ለብዙ ሺህ አመታት በነጻነት ያቆየን የሕዝብ አካል ነው።
ህ.ወ.ሓ.ት. አማራውን ለምን በጠላትነ ፈርጆ ያጠቃዋል? ለዚህ ብዙ ምክንያቶች መስጠት ቢቻልም ዋና ዋንዎቹን አንድ ሁለት ልበል፤
1. አማራውም ሆነ ቀሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ነው። ኢትዮጵያዊነቱን አምርሮ የሚወድና የሚያፈቅር አማራ ነው ብሎ ስለሚያስብ አማራ ካልጠፋ ኢትዮጵያን ማጣፋትም ሆነ ማፍረስ ቀላ አይሆንም የሚል ግምት አለው። ስለዚህ አስቀድሞ የአማራውን አከርካሬ መስበር ከተቻለ ኢትዮጵያዊነትም አብሮ ይሰበራል የሚል ሕልም ስለአለው ነው።
2. ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ሃገሪቱን በቋንቋና በሃይማኖት ከፋፍሎ እርስ በርሱ በማፋጨት ቂም በቀል እንዲይዝና አዳክሞ አገዛዙን ማቅለል ከበረሃ ይዞት የመጣው ውስጣዊና ድብቅ ፖሊሲው ነው።
3. በዚች ዓለም ብዙ የተለያዩ ቋንቋዎች ይነገራሉ። ቢሆንም ብሄራዊ ቋንቋ የሌላቸው ሃገሮች የሉም ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ ሃገራችንም ከ85 በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገርባት ሃገር ናት። ይሁን እና ለብዙ ዘመናት እንደብሄራዊ ቋንቋ ሲያገለግል የቆየው ግን በአማርኛ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ የትኛውም ቦታ ቢኬድ አማርኛ ተናጋሪ አይጠፋም። የአማርኛ ቋንቋ መግባቢያ፣ መወያያና ሃሳብ ለሃሳብ መለዋወጫ ከሆነ በሺህ የሞቆጥር ዘመን አልፏል።
ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የአማርኛ ቋንቋ የጠላት ቋንቋ ስለሆነ መጥፋት አለበት ብሎ በፖሊሲ ደርጃ ይዞ የተነሳው ከ1967 ጀምሮ ነው። ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ስርዓቱ ስር እንደወደቀች፤ ክልል ብሎ ከፋፍሎ እንዲያመቸው በከፋፈላቸው ግዛቶቹ በት/ቤቶች፤ በፍርድ ቤቶች፣ በመንግሥት መስሪያ ቤቶች አማርኛ ጥቅም ላይ እንዳይውል አገደ። ወያኔ ሥልጣኑን ከያዘ ወዲህ የተወለዱ ሕፃናት በትግራይ፣ ኦሮም፣ አፋር፣ ሲዳሞ፣ ጋምቤላ ወዘተ አማርኛ የማይናገረውና የማይሰማው በርክቷል። ይዞት በመጠው የጫካው ፖሊሲ አማካኝነት አማርኛን እያዳከመ በመቅበር ላይ ይገኛል። ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. የአማርኛ ቋንቋን በማዳከሙ ምን ትርፍ ያገኛል? የሚሉ አይጠፉም። በጥቂቱ ላስረዳ፤
1. የኢትዮጵያዊነት ብሄራዊ እምነትን ያዳክማል፤ ቀስ በቀስም ኢትዮጵያዊነትን ይደመሰስላል፤ ሃገር አልባና ባይተዋር ያደርጋል። የግል መገለጫና ማንነትን ያጠፋል።
2. ብሄራዊ ቋንቋ ስለማይኖር ከተወለድክበት ክልል መውጣት አትችልም። በማንኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተዘዋውሮ መሥራት አይቻልም። ይህ ሁሉንም የኢትዮጵያ ዜጋ የሚመለከት ነው። ይህ የወያኔ ፖሊሲ ወጣቱን ኢትዮጵያዊ አይኑን እና አእምሮውን ሸፍኖ ዜግነቱን እንዲረሳ የታቀደ ተንኮል ነው።
3. ብሄራዊ ቋንቋ እንዳይኖር እየተገበረ ስለሆነ፤ አመለካከትና አስተሳሰብ ከመንደር የዘለለ አይሆንም። ኢትዮጵያዊ ታሪክ፣ ባህልና ማንነት አብሮ ይጠፋሉ።
4. ብሄራዊ ቋንቋ ካልኖረ እድገትና ልማት በምንም ተአምር በሃገሪቱ አይታይም። ይህም አንዱ የህ.ወ.ሓ.ት. ጸረ-ልማት ፖሊሲ ነው።
ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ክልል ብሎ ያስቀመጣቅቸው የኢትዮጵያ ሕዝብና ብሄራዊ የሆነውን የአማርኛ ቋንቋ በማዳከምና በማጥፋት ነው። አንዱን ክልል በሌላው ላይ መጠራጠርና ጥላቻ እንዲፈጥር ቢጥርም የፈለጉትን ያህል አልተሳካላቸውም። በሕዝቡ ብርታትና አልበገር ባይነት በተቻለው ሁሉ ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ የሚኖር ኩሩ ሕዝብ እንደሆነ ይገኛል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የህ.ወ.ሓ.ትን ማንነት አውቆ ድርጊቱን በተለያየ መንገድ መግለጽ ከጀመረ ከራርሟል።
ስለዚህ ህ.ወ.ሓ.ት. ይህንን የአማራውን የዘር ማጥፋት (Genocide)የረጅም ጊዜ እቅድና ፖሊሲ በማውጣትና በመተግበር በዋናነት የሚጠየቁት፤ ከነዘር ሃረጋቸው፤ እነማን ናቸው የሚለውን እንመልከት፤
1. መለስ ዜናዊ፣ በአባቱም በእናቱም ሕዝብና ሃገር ያጠፋ የባንዳ ዘር ኤርትራዊ
2. ስብሃት ነጋ፣ በእናቱ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በናቱ በኩል)
3. አባይ ፀሃየ፣ የባንድ ልጅ አክሱም
4. ሥዩም መስፍን የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
5. አርከበ እቁባይ፣ የባንዳ ልጅ አድዋ
6. ዶ/ር ሰሎሞን እንቋይ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በአባቱ በኩል)
7. ጸጋይ በርሄ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
8. ጻድቃን ገብረተንሳይ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
9. ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
10. አባይ ወልዱ፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ (በአባቱ በኩል)
11. ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የባንዳ ልጅ ኤርትራዊ
12. ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ የባንዳ ልጅ (የሻእቢያ ፈዳያን የነበረ) ኤርትራዊ
13. አዜብ መስፍን፣ እድገቷ ኤርትራና ሱዳን ፀገዴ (ጸረ-አማራ)
ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ወላጆቻቸው የጣልያን ወራሪን በባንዳነት አሽከር ሆነው እያገለገሉ፣ ኢትዮጵያን የወጉና ሕዝቧን ያስፈጁ የጠላት ልጆች ናቸው። የወላጆቻቸውን ፈለግ በመከተል ወላጆቻቸው የሰጧቸውን አደራ በመከተል አሁንም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ጥቃትና በደል እየፈጸሙ ነው። ኢትዮጵያን በማፍረስ፣ ሃብትና ንብረቷን በመመዝበርና በዘር ማጥፋት ወንጀል በመሰማራት በሕግ የሚያስጠይቃቸውን ድርጊት እየፈጸሙ ናቸው። ብ.አ.ዴ.ን. እና ኦ.ህ.ዴ.ድ. እንዲሁም የደቡብ ህዝቦች ንቅናቄም በዘር ማጥፋት አስፈጻሚነታቸው በወንጀል ተጠያዊ ናቸው።
ይህንን የወያኔ ህ.ወ.ሓ.ትን እና የግብረአበሮቹን ሃገርና ሕዝብን የማጥፋት ተግባራቸው የመግቻው መፍትሄ ምንድን ነው? ለሚለው፤ እከሌ ከእከሌ፤ ፓርቲ ከፓርቲ፤ ግንባር ከግንባር፣ ወገን ከወገን ሳይለያይ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ አሻፋረኝ፣ አልገዛም፣ በቃኝ ብሎ በአጠቃላይ አንድ ሆኖ የሕዝብ አመጽ ማስነሳት ብቻ መፍትሄ ያመጣል እላለሁ።
ኢትዮጵያና ሕዝቧን እናድን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር

No comments:

Post a Comment