(EMF) የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ፕሬዘዳንት የነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም እንደሞቱ ተደርጎ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ብእሚገኙ ሚዲያዎች ሲወራ ሰንብቷል። ኢ.ኤም.ኤፍ. ከኮ/ል መንግስቱ የቅርብ ቤተሰብ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ ወሬው ከወሬ ያላለፈ የውሸት ዜና ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ከኮሎኔል መንግስቱ ጋር ባደረግነው ቃለ ምልልስ፤ “ወያኔ እንኳንስ በህይወት እያለሁ፤ ሞቼ አስከረኔንም አያገኘውም።” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። እስካሁን የዜና ምንጭ ተብሎ የሚጠቀሰው የዙምባብዌ ቴሌቪዥን ነው። ሆኖም ቴሌቪዥኑ ይን በተመለከተ ምንም ነገር አላለም። ነገር ግን ቴሌቪዥኑን ጠቅሶ ሌላ ድረ ገፅ ባለፈው ኤፕሪል ፉል April Fool እለት ህዝቡን ለማሞኘት ይህን ዜና ሰርቶት ነበር። የሚገርመው ነገር April fool ካለፈ 3 ሳምንታት ተቆጥረዋል።
ጊዜው ቢዘገይም ይህንን ዜና ይዘው ወሬውን የሚያባዙት ሰዎች በራሳቸው ተሞኝተዋል ማለት ነው። 3 ሳምንታት ቢቆጠሩም… እነዚህን የሞኝ ወሬ ሳያረጋግጡ የሚነዙትን ሰዎች April Fool እንበላቸው (ከፈገግታ ጋር)።
ማጠቃለያችን የሚሆነው… “ኮሎኔል መንግስቱ አልሞቱም።” የሚለው ርእሳችን ነው።
No comments:
Post a Comment