Wednesday, April 3, 2013

ብአዴን የት ናት…? Abe Tokichaw


DSCN1103
ባለፈው ሰሞን ከደቡብ ክልል ጉራ ፈርዳ “አማሮች ስለሆናችሁ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ” ተብለው ሲፈናቀሉ የነበሩ ዜጎች ጉዳይ ምን እንደደረሰ ምንም የረባ ነገር ሳንሰማ ይሄው ዛሬ ደግሞ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል “አማሮች ውጡ” ተባሉ ሲባል እየሰማን ነው፡፡ የአሁኑ ይባስ እንዲሉ፤ የአሁኑ ደግሞ ጭራሽ ተፈናቃዮቹ ሲጓዙበት የነበረው መኪና አደጋ ደርሶበት ስደተኞቹ በሙሉ ህይወታቸው ተቀጥፏል፡፡
በየአመቱ ህዳር አስራ አንድ ልደቷት የምታከብር አማራውን እወክላለሁ የምትል ብአዴን የተባለች ፓርቲ አለች፡፡
ብአዴንን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርች አንዱ የሆኑት አቶ ደመቀ መኮንን ይመሯታል፡፡ በስራቸውም በርካታ አንጋፋ ታጋዮች ይገኛሉ፡፡ አቶ አያሌው ጎበዜም አቶ አዲሱ ለገሰም አንዱ እና ሁለቱ ናቸው፡፡ ሌሎችም ብዙ አበል የሚበሉ አባሎች አሏት… ብአደዴን!
እንግዲህ በተደጋጋሚ የክልሉ ተወላጆች በዘራቸው የተነሳ ወደ ሀገራችሁ ሂዱ እየተባሉ ከተለያዩ ክልሎች ሲባረሩ ብአዴን ምን እያደረገች ነው… መቼም ወግ ነውና ልጠይቅ ብዬ ነው አንጂ… ብአዴንም ሆነች መላዋ የትዳር አቻዎቿ በጥቅሉ እነ ኢህአዴግ ጥያቄ ለመመለስ ጊዜ ያላቸው አይመስሉም፡፡ አነርሱቴ፤ ርስ በርስ ተቃቅፈው የሞቀ ፍቅር እየሰሩ ነው፡፡
ሳስባት ብአዴን የኢህአዴግ ፍቅር አለቅጥ አስክሯታል፡፡ “በልጆቿ” ላይ የሚያደርሰው መከራም ከነጭርሹ ሊታያት አልቻለችም፡፡ ፍቅር እውር ነው ብቻ ሳሆን እውርም ያደርጋልና እነሆ ብአዴን ልጆቿን ረስታለች፡፡ የት እንደሆኑ ምን እንደሆኑም አልሰማችም፤ አላየችምም፡፡
ብትሰማም ጆሮ ዳባ ብላለች፡፡ ብታም አይኔን ግንባር ያድርገው ብላለች፡፡
ጥያቄዬ አጭር ናት፤ ብአዴን የት ናት…!? ብኤዴን የማናት…!?  ለመሆኑ ደህና ናት…!? ስራዋስ ምን ይሆን…!?
ብአዴን ሆይ ልደት ማክበር፤ መጨፈር እና ከጎረምሳው ኢህአዴግ ጋር ሲቃበጡ ማደር… በቃ ይሄው ነው ያንቺ ሞያ…!? እባክሽ ተንፍሺ…!
እንበል ይሆን… !?

No comments:

Post a Comment