Thursday, March 7, 2013

በኬንያ ምርጫው እየተጭበረበረ ነው ሲሉ ራይላ ኦዲንጋ ቅሬታ አቀረቡ


የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንትቀን ፳፻፭ / 

ኢሳት ዜና:-በምርጫው ከተሸነፉ ዳግም ምርጫ እንዲደረግ አለያም የጥምር መንግስት እንዲቋቋም እንደሚጠይቁ የኬንያውጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ አስጠነቀቁ።

እስካሁን የተደረጉት የድምጽ ቆጠራዎች በምርጫው የጆሞ ኬንያታ ልጅ ኡሁሩ ኬንያታ እየመራ እና  ኦሬንጅ ዲሞክራቲክሙቭመንቱ ራይላ ኦዲንጋ በሁለተኝነት እየተከተሉ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ይህንኑ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ለመጭበርበሩ እና በድምጽ ቆጠራው ሂደት ስርቆት ለመፈጸሙበቂ ማስረጃዎች አሉን ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በአሁኑ ጊዜ  እየተካሄደ ያለውና በዲሞክራሲያዊነቱ በጎ አስተያየቶች እየጎረፉለት ያለው የዘንድሮ የኬንያ ምርጫ ወደመጨረሻው ላይ ችግር እንዳይፈጠር ስጋቶች ብቅ እያሉ ቢሆንም፤ እንደባለፈው ምርጫ ጊዜ ደም አፋሳሽ ችግርየሚከሰትበት መንገድ ግን እጅጉን የጠበበ እንደሆነ ነው ዘገባዎች የሚያመለክቱት።

ኦዲንጋ አቤቱታ ቢያቀርቡም ለደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ጥሪ እንደማያደርጉ አረጋግጠዋል። የአገሪቱ ዋነኛ የምርጫአስፈፃሚ አካል ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ኦዲንጋን ቅሬታ ውድቅ አድርጎታል። የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር አህመድይስሀቅ ሀሰን፤ የምርጫ ውጤቱ እንዲጭበረበር የሚያደርግ ምንም ዓይነት ክፍተት የለም ነው ያሉት።

ቀደም ሲልም የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች በጽሁፍ የቀረበ ምንም አይነት አቤቱታእንዳልነበር የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊ ሊሊያኔ ማሂሪ ዛጃ  መናገራቸው ይታወሳል።

ይሁንና የኤክትሮኒክ ድምጽ መቁጠሪያው ከተበላሸ በሁዋላ የድምጽ ቆጠራ ሂደቱ እጅጉን መዘግዬቱን ቢቢሲ ጠቁሟል። በአሁኑ ጊዜ የምርጫ ኮሞሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ ከዲፕሎማቶች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል።

እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር  2007-2008 በተካሄደው የኬንያ ምርጫ ሚስተር ራይላ ኦዲንጋ የድምጽ ቆጠራ ሂደቱበፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ ደጋፊዎች እንደተጭበረበረ መናገራቸውን ተከትሎ በተነሳው አመጽ  1000 በላይ ኬንያውያንመሞታቸው ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment