Tuesday, March 5, 2013

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አርቲስት ታማኝ በየነ የመራው የኢሳት የአውሮፓ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ተጠናቀቀ


የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት ሳምንታት በአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር ስለ ሰብአዊ መብቶች ቀላል፣ ግልጽ እና አስተማሪ በሆነ መንገድ እያቀረበ ለኢሳትም የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ የሰራው እውቁ አርቲስት ታማኝ በየነ የአውሮፓ ጉዞውን ቅዳሜ ማርች 2፣ 2013 በጀርመንዋ የፍራንክፈርት ከተማ በደመቀ ዝግጅትና ስነስርአት አጠናቋል።
አርቲስት ታማኝ ጉዞውን በጄኔቫ ስዊዝርላንድ ጀምሮ በ ስዊድን  ስቶክሆልም፣ በ ኖርዌይ  ኦስሎ ፣በ ጀርመን  ሚዩኒክ ፣    በኔዘርላንድስ አምስተርዳም ፣ በ እንግሊዝ  ለንደን  ፣ በ ቤልጂየም  ብራሰልስ  ቆይታ ካደረገ በሁዋላ በ ጀርመን ፍራንክፈርት  አጠናቋል።
አርቲስት ታማኝ በአውሮፓ ቆይታው ከኢትዮጵያውያን ባሻገር ከአውሮፓ  የፓርላማ አባል ከተከበሩ ሚስ አና ማሪያ ጎሜዝ ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ውይይት አድርጓል። እንዲሁም በኖርዌይ አገር ለሚታተም ጋዜጣ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ቃለምልልስ ሰጥቷል።
በፍራንክፈርቱ ዝግጅት በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የመዝጊያ ስነስርአቱ በደመቀ ሁኔታ ተጠናቋል።
በፍራንክፈርት የነበረውን  ዝግጅት  በተመለከተ ከዜናው በሁዋላ ተጨማሪ ዘገባ ይቀርባል።

No comments:

Post a Comment