Sunday, March 17, 2013

ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያም እና ሌሎች ታዋቂ ሰዎች ዛሬ ታሰሩ!


(EMF) በዛሬው እለት መጋቢት ስምንት ቀን 2005 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ የግራዚያኒን ሃውልት መሰራት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል።  ከታሰሩት መካከል ታዋቂው  የህግ ሰው ዶ/ር ኃያዕቆብ ኃይለማርያም ይገኙበታል። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ይህን በተመለከተ ከአዲስ አበባ ያስተላለፉት መል ዕክት እንዲህ የሚል ነበር። ” የዛሬው ጉድ ነው፤ በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እየተሠራ መሆኑን ለመቃወም የተለያዩ አገር ወዳድ ወጣቶች ከስድስት ኪሎ ወደኢጣልያ ኤምባሲ ሰልፍ ለማድረግ ጠርተው ነበር፤ ግራዚያኒ በየካቲት አሥራ ሁለት በቦምብ ከቆሰለ በኋላ የኢትዮጵያን ሕዝብ ያስጨፈጨፈ አረመኔ ፋሺስት ነበር፤ ለዚህ ሰው ኢጣልያኖች ሐውልት መሥራታቸው የዛሬውን የኢትዮጵያ ትውልድ መናቅ ብቻ ሳይሆን ከኢጣልያ ጋር የተዋደቁትን ኢትዮጵያውያን ማዋረድ ነው፤ ስለዚህ ዛሬ መጋቢት 8/2005 ተቃውሞ ለማሳየት ታቅዶ ነበር፤ ፖሊሶች ሰልፉ እንዳይደረግ መከልከል ይችሉ ነበር፤ የተሰበሰቡትን በሰላማዊ መንገድ በበተን ይቻል ነበር፤ ፖሊሶች የመረጡት እየያዙ ማሰርን ሆነ፤ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ወጣቶች ሴቶችና ወንዶች በየፖሊስ ጣቢያዎች ታስረዋል፤ ዶር. ያዕቆብ ኃይለ ማርያምንም ይዘውታል፤ በዓይኔ ባላየው ለማመን ትንሽ ያስቸግረኝ ነበር፤ እንዲያውም የተያዙትን ለመጠየቅ ሄጄ የፖሊስ ጣቢያው በር ላይ ያገኘሁትን ነጭ ለባሽ ዛሬ የታሰሩ ሰዎች እዚህ መጥተዋል ወይ ብዬ ብጠይቀው ‹‹ምናባክ አውቅልሃለሁ፣ ግባና ጠይቅ፤›› አለኝ፤ በሩ ላይ የነበሩ ሴት ፖሊሶች ‹‹አለቆቹ ስለሌሉ በኋላ ተመለስ›› ለማናቸውም እስረኞቹ በረንዳ ላይ ታጉረው አየኋቸው፤ እኔ ይህ የጤንነት አይመስለኝም!” ብለዋል።
ሰላማዊ ሰልፉ የተጠራው ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ የግል ተነሳሽነት ማህበር፤ ሰማያዊ ፓርቲ እና ባለራዕ ወጣቶች ማህበር በጋራ በመሆን “ለፋሽስቱ የጦር ወንጀለኛ ለማርሻል ግራዚያኒ ክብር መስጠት የአባቶቻችን መስዋዕትነት ማራከስ ነው” በሚል የተጠራውን ሰልፍ አምባገኑ የኢህአዴግ መንግስት በርካታ የፌደራል ፖሊስ፣ የደህንነት አባላትን እና የአዲስ አበባ ፖሊሶችን በማሰማራት ሲበትን፤ የተቋማቱን ከፍተኛ አመራሮች፤ ታዋቂ ግለሰቦች እና በርካታ ወጣቶች ጨምሮ ቢያንስ 34 ሰዎች አስሯል የታሳሪዎች ቁጥር አሁንም በመጨመር ላይ ነው፡፡
እንዲሁም በትላንትናው እለት ለተቃውሞ ሰልፉ የቅስቀሳ ስራ ሲሰሩ ከነበሩት ውስጥ 2 የሰማያዊ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ አባላትን እንዲሁም የባለራዕይ ወጣቶች የስራ አስፈጻሚ አባላትን ጨምሮ 8 ሰዎችን አስረዋል፡፡
በአሁኑ ሰአት በእስር ላይ የሚገኙት እና ስማቸው የተገኙት የሚከተሉት ናቸው።
1. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
2. አቶ ታዲዎስ ታንቱ
3. አቶ ይልቃል ጌትነት (የሰማያዊ ሊቀመንበር)
4. ስለሺ ፈይሳ (የሰማያዊ ም/ሊቀመንበር)
5. ይድነቃቸው ከበደ (የሰማያዊ የህግ ጉዳይ ሀላፊ)
6. ሀና ዋለልኝ (የሰማያዊ የሴቶች ጉዳይ ሀላፊ)
7. ጌታነህ ባልቻ (የሰማያዊ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ)
8. ብርሀኑ ተክለያሬድ (የባለራዕይ ወጣቶች ተ/ምክትል ሊቀመንበር)
9. ያሬድ አማረ (የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ጸሀፊ)
10. ኤልሳቤጥ ወሰኔ
11. ሰለሞን ወዳጅ
12. ወይንሸት ንጉሴ
13. እየሩሳሌም ተስፋው
14. ለገሰ ማሞ
15. ትዕግስት ተገኝ
16. አማኑኤል ጊዲና
17. አለማየሁ ዘለቀ
18. አገኘሁ አሰገድ
19. ሻሚል ከድር
20. አሸብር ኪያር
21. ጌታቸው ሽፈራው
22. ግሩም አበራ
23. አቤል ሙሉ
24. ዩሀንስ ጌታቸው
25. ስማቸው ተበጀ
26. ፍቃዱ ወንዳፍራው
27. ባህረን እሸቱ
28. ሄኖክ መሀመድ
29. እንቢበል ሰርጓለም
30. አለማየሁ በቀለ
31. ዩናስ
32. የመኪናው ሹፌር
33. ዮዲት አገዘ
34. ጥላዬ ታረቀኝ እና ሌሎችም ስማቸው ያልተዘረዘሩ ኢትዮጵያውያን በእስር ቤት ውስጥ ይገኛሉ። በርግጥ የኢህአዴግ አፋኝ አስተዳደር የአፓርታይድ ቅርጽ እየያዘ ነው!
http://ethioforum.org/

No comments:

Post a Comment