Friday, March 15, 2013

አንድ ምሬትአንድ ምሬት ! አቤ ቶኪቻው


ሰሞኑን ኮምፒውሬ ወሰድ መለስ ሲያደርጋት ነበር እና በቅጡ መገናኘት አልቻልንም፡፡ ይባስ ብላም የመረጃ ማጠራቀሚያ መሳሪያዋ (ሀርድ ዲስኳ) ከጥቅም ውጭ ሆኖ የነበሩኝ በሙሉ እንዳልነበሩኝ ሆነዋል፡፡ እኔም ብያለው፤ “ሁሉም አላፊ ሁሉም ጠፊ ነው… ገዢው ፓርቲም ጭምር” እዚህ ጋ እንኳን ገዢው ፓርቲ መግባት አይገባውም ነበር፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ወዳጆች በተለያየ ጊዜ ጽንፈኛ ሆንክ ሲሉ አስተያየት እየሰጡኝ በመሆኑ እነሱን ለማስደሰት ይሁነኝ ብዬ ያደረግሁት ነው!
አረ እኔ የምለው ወዳጄ ቀልዱ ቀልድ ነው፤ የኮምፒውተሬስ እሺ በራሴው ጦስ ያመጣውት ነው፡፡ ድረ ገጼ ላይ ደግሞ በዚህ ሰሞን በርካታ አስተያየቶች እንዳሉኝ ምልክት ተመልክቼ ማን  ምን አለ ይሆን… ብዬ ወደ አስተያየቱ ጓዳ ስገባ ምንም እርባና የሌላቸው ጹሁፎች እየተመለከትኩ ነው፡፡
የነዚህ መልዕክቶች ባለቤት  ማን እንደሆነ እርሱ ባለቤቱ ይወቀው አብዛኛዎቹ፤ “እንዲህ ነው እንጂ ድረ ገጽ” በሚል ማበረታቻ የሚመስል አማላይ ቃል የተሞሉ ናቸው፡፡ አስተያየቶቹ እጅግ የበዙ ከመሆናቸው የተነሳ ከመንግስታችን ፈርጀ ብዙ ችግር ሁላ ይብሳላ፡፡
ምን ጠረጠርክ ይበሉኝ… ምናልባት እነ አጅሬ ይሆኑ እንዴ… እንዲህ በአስተያየት ብዛት የሚያማርሩን…! ሀገር ቤት እያለን የአይነ ቁራኛ አስተያየታቸው ቢቀፈን ሀገር ለቀን ወጣንላቸው! አሁን ደግሞ የት ሂዱ ብለው ነው እንዲህ የሚያደርጉን…! ብለን እንቀውጠው እንዴ! (አንድ ወዳጅ መሆን የተሳነው ግለሰብ፤ “እነ ቐሽ ገብሩ በተሰዉት እኮ ነው አንተ ዛሬ ማንችስተር ለመኖር የበቃኸው እናም ማመስገን ይገባሃል” ብሎኛል፡፡ እውነቱን ነው… ለዚህ የስደት ኖሮ የበቃነው… በታጋዮቻችን የተነሳ ነው እናም ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡ እግዜር የስራችሁን ይስጣችሁ ብለን እንመርቃቸዋለን! ከዛ ቁጭ ብለን ምርቃቱ ሲደርስ መመልከት ነው…!)
የምር ግን አረ መላውን የምታውቁ አንድ በሉኝ…! እንዴ… የወዳጆቼን አስተያየት እኮ ማየት አልቻልኩም! እስቲ ማነው ጎበዝ እኒህን አስተማሪ የበደላቸው ሴረኞች ሃይ የሚልልኝ! የምር ምርር ነው ያደረጉኝ! ነውር አይደለም እንዴ…

No comments:

Post a Comment