Sunday, March 31, 2013

“የአዲሱ የናይል ሸለቆ ፕሮጀክት” በግብፅ


አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የግብፅ መሪ ሆስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ በ1997 “New Nile Valley Project” “የአዲሱ የናይል ሸለቆ ፕሮጀክት” በሚል ግዙፍ የሆነውን የሰሐራ በረሃን የማልማት ዕቅድ ነድፈው ያም ዕቅድ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በተያዘለት ዕቅድ ከተከናወነ ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል የማጠናቀቂያ ጊዜው እስከ 2020 ድረስ መሆኑን በቅርብ ጊዜ ከወደ ግብፅ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዋናነት ሁለት ምዕራፎች ሲኖሩት አንደኛው በሰሜን ምሥራቅ ግብፅ የሚገኘው የአል-ሰላም ቦይ (canal) ፕሮጀክት ነው፡፡ እሱም ውኃ ከዓባይ ግርጌ በመጥለፍ ወደ ሲና በረሃ ማሻገር ነው፡፡
ይህን በማድረግ ብዙ መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት በማልማት 750 ሺሕ ግብፃውያንን ለማስፈር ያለመ ነው፡፡ ዋናውና ትልቁ ፕሮጀክት ግን የቶሽካ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ይህም የደቡብ ምዕራብ ግብፅ በረሃን ለማልማት ያቀደ ፕሮጀከት ነው፡፡ በግብፃውያኑ ዘንድ ይህ ፕሮጀክት አሁን ባለው ሁኔታ እ.ኤ.አ 2020 ያልቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት አዲስ ግብፅን በበረሃው ለመፍጠር ያቀደ ሲሆን፣ የተለያዩ በርካታ የውኃ ቦዮችንና የውኃ መምጠጫ ፓምፖዎችን በመገንባት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህን በማደረግ በረሃውን በማልማት ወደ ሦስት ሚሊዮን ግብፃውያንን የማስፈር ዕቅድ አላቸው፡፡ እንደ ግብፃውያኑ ከሆነ ይህ ፕሮጀክት ውኃውን የሚያገኘው በናይል ላይ ከተሠራው የአስዋን ግድብ ጀርባ ከሚገኘው የናስር ሐይቅ ነው፡፡ ግብፃውያኑ ይህን ሥራ የትኞቹንም የላይኛውን የተፋሰስ አገሮች ሳያናግሩ ሲሠሩት ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት ያሰቡ አልመሰሉም፡፡ እነሱ እ.ኤ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር የተፈራረሙት በሌሎቹ አገሮች ውድቅ የተደረገው “ስምምነት” ለራሳቸው በሰጡትና በመደቡት 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ራሽን/ኮታ መሠረት “ያላቸውን” ውኃ ለመጠቀም በማሰብ ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህ ኮታ በሌሎቹ የላይኛው ተፋሰስ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ግብፃውያኑ ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት አሁንም ግልጽ አይደለም፡፡
እንግዲህ የሳዑዲ ዓረቢያ ሚና በዚህ ፕሮጀክት ላይ ምንድን ነው? ስንል ታላቅ ኢንቨስትመንትን እናገኛለን፡፡ የሳዑዲው ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ቢን አብዱላዚዝ አልሳዑድ “ዘ ኪንግደም አግሪካልቸራል ዴቨሎፕመንት” የተሰኘ ኩባንያ ባለቤት ሲሆኑ፣ ግብፅ ውስጥ በጥቅሉ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያንቀሳቅሳሉ፡፡ በቶሽካ ፕሮጀክት ደግሞ ከ10 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ተረክበው የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለማምረት ከግብፅ የውኃና የመስኖ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል፡፡ በየዓመቱም በሚሊዮኖች ለዚሁ የቶሽካ ፕሮጀክት አካል ለሆነው መሬት እንደሚያፈሱ ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ግብፅ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ያሉት የሳዑዲ ቤተሰብ የሆኑት የንጉሡ ዘመድና ልዑሉ እንጂ ከኢትዮጵያዊ እናት የተገኙት ሼክ አል አሙዲ አይደሉም፡፡ ይህም ማለት ለሳዑዲ ዓረቢያ ቤተ መንግሥትም ሆነ ለምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ የሚቀርቡት ሼክ አል አሙዲ ሳይሆኑ ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ናቸው፡፡ ስለዚህ የምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ ንግግር ከዚህ አንፃርም ሊታይ ይችላል፡፡
ዓባይ ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ከሚለው ፅሁፍ የተወሰደ
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው zerihun.yigzaw@graduateinstitute.ch ማግኘት ይቻላል፡፡

ኢህአዴግ የሠላማዊ ሰልፍ መብታችንን ማረሳሳቱ ነው እንዴ?

eprdf 9th meeting 

እኔ የምላችሁ…ኢህአዴግ 9ኛውን የፓርቲውን ጉባኤ ያካሄደበትን እጅግ የተንቆጠቆጠ “ባለ 7 ኮከብ” (ኮከብ የመስጠት ኮፒራይቱ የራሴ ነው!)
የስብሰባ አዳራሽ አይታችሁልኛል? (በኢቴቪ ማለቴ ነው!) በአካልማ ማን አስደርሷችሁ! (አዳራሹ ከ2ሺ ሰው በላይ አይችልማ!) ለነገሩ አዳራሹም ቢበቃ ሌላም የመግቢያ መስፈርት እንደነበረው ሰምቻለሁ።
ምንጮቼ እንደነገሩኝ — “ተራማጅ” ወይም “አብዮተኛ” ያልሆነ ግለሰብም ሆነ ፓርቲ —- እንኳንስ በጉባኤው ሊሳተፍ ቀርቶ በአካባቢው ዝር ማለትም አይፈቀድለትም ነበር! (አሉ ነው እንግዲህ) በነገራችሁ ላይ አሁን ባልኩት ጉዳይ ዙርያ ማስረጃም ሆነ መረጃ እንደሌለኝ ከወዲሁ ለመግለፅ እወዳለሁ (እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር አሉ!) እናላችሁ —- ኢህአዴግ ከውጭ አገር 13 “እህት ፓርቲዎች”ን ጋብዞ ከአገር ውስጥ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ ያልጋበዘው አንዳንዶች እንደሚያስወሩት በ“ንቀት” ወይም “በአገር ውስጥ ምርት ስለማይኮራ” አይደለም ! (የሥጋ ዘመድ እንደሌለው በባዕድ ፓርቲዎች መታጀብ ምኑ ደስ ይላል?) በነገራችሁ ላይ ተጋባዥ የውጭ አገር ፓርቲዎቹ “እህት ፓርቲዎች” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አገር ውስጥ ከገቡ በኋላ እንደሆነ ከሁነኛ የገዢው ፓርቲ ምንጮች “ሁነኛ መረጃ” ማግኘቴን ስነግራችሁ በኩራት ነው፡፡

(የተርብ ካድሬ የፈጠራ ውጤት ነው ተብሏል!) በአሁኑ የኢህአዴግ ጉባኤ ምን እንዳስደሰተኝ ታውቃላችሁ? አንደኛ እንዳለፈው የአዳማ ጉባኤ “ጓድ! ጓድ!” የሚል ነገር ብዙም አልሰማሁም (ጥሎብኝ ሶሻሊዝም አይመቸኝም!) ሁለተኛው ያስደሰተኝ ነገር ደግሞ የኢህአዴግ ግንባሮች በነፍስወከፍ (በፉክክር አልወጣኝም!) ያስገነቧቸውን ቄንጠኛ የጉባኤ አዳራሾች መመልከቴ ነው፡፡ (የአዳራሽን ችግር እነ “አንድነት”ፓርቲ ይንገሯችሁ!) አንዱ አሽሟጣጭ ወዳጄ ስለኢህአዴግ 9ኛው ጉባኤ ምን እንዳለኝ ልንገራችሁ አይደል—(አደራችሁን ኢህአዴግ እንዳይሰማ!) የዘንድሮ ጉባኤ የተካሄደው “አዳራሽ ከእኔ፤ ጉባኤ ከእናንተ” በሚል መርህ ነው ብሎኝ ቁጭ አለ፡፡ እኔ እንኳን በዚህ አልስማማም፡፡
ለምን መሠላችሁ? የአመራሩን የ“አድርባይነት” ችግር ያጋለጠውን “ታላቅ ጉባኤ” እኮ ነው አፈር ድሜ ያስበላው! እኔ የምለው ግን — ጉባኤው በእንግሊዝኛም ሲካሄድ ነበር ልበል — (የአማርኛው ሳያንስ እንግሊዝኛውንም?) ከሁሉም በላይ ቅር ያሰኘኝን ደግሞ ልንገራችሁ። በጉባኤው ላይ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አባላት መጋበዛቸው አልተመቸኝም፡፡ (ጠንቋይ ቤት ሄጄ ወይም አዋቂ ነግሮኝ ግን አይደለም) ቆይ እስቲ — የቻይና ፖለቲከኞች ምን ሊፈይዱልን ነው የተጠሩት? የቀድሞው የአገራችን መሪ ጓድ (ኮሎኔል) መንግስቱ ኀይለማርያም ምን እንዳሉ ሰምታችኋል? የአገራችን የረዥም ጊዜ ወዳጅ የነበረችው የሶቭየት ህብረት የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሚኻኤል ጎርባቾቭ፤ በ11ኛው ሰዓት ክህደት እንደፈፀሙባቸው በምሬት ተናግረዋል፡፡

(ፖለቲከኛ ወዳጅ የለውም ለማለት ነው!) አንዳንድ እውቅ የፖለቲካ ተንታኞች ስለቻይና ምን ይላሉ መሰላችሁ? “ቻይና የሚያምርባት ቀለበት መንገድ ስትሰራ ብቻ ነው!” በዚህ እንኳን እኔም ራሴ እስማማለሁ፡፡ ለዘመናት ከአንድ ኮሙኒስት ፓርቲ ውጭ የማታውቅ አገር፤ ለኢህአዴግ ምን ልታስተምርብን እንደምትችል መገመት አያቅተንም! (እሱ ለራሱ በቋፍ እኮ ነው!) የእኔን ዋነኛ ስጋት ብነግራችሁ ግን ደስ ይለኛል። ምን አለ በሉኝ — የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ አባላት እንዲህ እግር ካበዙ ስንት ታጋዮች የህይወት መስዋዕትነት የከፈሉበትን የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት ግንባታ ከንቱ ያደርጉብናል፡፡

እዚህ አገር ተቃዋሚ ፓርቲዎች መኖራቸውን ሲሰሙ በድንጋጤ አፋቸውን መያዛቸው አይቀርም ብዬ እገምታለሁ፤ ከዚያም “ተራማጅ ፓርቲ በሚመራው ልማታዊ መንግሥት ውስጥ ተቃዋሚዎች ምን ይሰራሉ? ይሄ የተራማጅ ፓርቲ ተፈጥሮም ሆነ መርህ አይደለም” በማለት ኢህአዴግን ይሞልጩታል (የአቋም መግለጫ ሁሉ ሊያወጡ እንደሚችሉ ጠርጥሩ!) እኔ የምላችሁ ግን … ቻይና ውስጥ የምርጫ ቦርድ ኮሚሽን የሚባል ነገር አለ እንዴ? አረ አይመስለኝም! ፓርቲዎችና የምርጫ ፉክክር በሌሉበት አገር ምርጫ ቦርድ ምን ይሠራል? (የሥራ እድል ይፈጥራል ካልተባለ በቀር!) የፓኪስታን ጠ/ሚኒስትር አንድ ወዳጅ አገር ይሄዱና ባቡር ሳይኖር የሃዲድ መስመር ተዘርግቶ ያያሉ፡፡ በዚህ ተገርመውም የአገሪቱን ፕሬዚዳንት “ባቡር በሌለበት ሃዲድ ምን ይሰራላችኋል?” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ፕሬዚዳንቱም የዋዛ አልነበሩም “እናንተ አገር የፍትህ ሚኒስቴር አለ አይደለም እንዴ!” በማለት ዝም አሰኟቸው (ፍትህ ሳይኖር ፍትህ ሚ/ር— ማለታቸው እኮ ነው!) ኢህአዴግ ሁልጊዜ በምን እንደሚያስገርመኝ ታውቃላችሁ? ራሱን ሲወቅስ ለነገ አይልም፡፡

የእሱ ችግር ምን መሰላችሁ? ወቀሳና ቅጣትን አይለይም። ወቅሶ ዝም ነው! (እንኳን ፓርቲ ህፃንም ቅጣት ያስፈልገዋል!) እናም— “ችግሩን ሸፋፍነን ልናልፍ አይገባም!” ማለት ብቻውን ውጤት አያመጣም ለማለት ያህል ነው ! እኔ የምላችሁ… ኢህአዴግ “የአመራሩ ችግር አድርባይነት ነው” ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? (አንዳንዴ እኮ በወፍ ቋንቋ የሚያወራ ነው የሚመስለው!) በነገራችሁ ላይ አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ በአሉ ግርማ በአንድ የሥነፅሁፍ ሥራው ላይ “ከአድርባይ ብዕር ባዶ ወረቀት ይሻላል” በማለት ፅፏል፡፡ የዘመኑ ደራሲ ደግሞ “ከአድርባይ አመራር ባዶ ፓርቲ ይሻላል” እንደሚል እገምታለሁ (ከሰሞኑ የኢህአዴግ ግምገማ በመነሳት) እናንተ አንባቢዎቼ እንደምታውቁት እስከዛሬ ድረስ በገዢው ፓርቲ የአመራር ጉዳይ ውስጥ ገብቼ “ፈትፍቼ” አላውቅም (ህገመንግሥታዊ መብቴ እንደሆነ ባውቅም!) አሁን ግን የአመራሩ ችግር አድርባይነትና ኪራይ ሰብሳቢነት መሆኑን ከራሱ ከኢህአዴግ ስለሰማሁ መፍትሄ ለመሰንዘር እፈልጋለሁ፡፡ በዚህ ፈታኝ ወቅት እኮ ዝምታ ከ“ጠላት” እንጂ ከ”ወዳጅ” አይጠበቅም፡፡ (“ወዳጅ” እንጂ “አባል ነኝ” አልወጣኝም!) እናላችሁ… ኢህአዴግ የፓርቲውን አመራር ለውጭ ማኔጅመንት በኮንትራት ቢሰጠው ጥሩ ይመስለኛል፡፡

አሃ… የኢህአዴግ አመራር ችግሮች ያለቅጥ በዙ እኮ! ይሄውላችሁ… በግልፅ እንነጋገር ከተባለ በዘንድሮው የኢህአዴግ ጉባኤ ፓርቲው የሰራው በጐ ነገር አለ ከተባለ፤ ቅድም እንዳልኩት ያስገነባቸው ቄንጠኛ የጉባኤ አዳራሾች ብቻ ናቸው፡፡ ችግሩ ግን ምን መሠላችሁ? የጉባኤ አዳራሾች የመልካም አስተዳደር ችግርን ሊፈቱ አይችሉም፡፡ እንኳን የጉባኤ አዳራሾች የመንገድ እና የኮንዶሚኒዬም ግንባታዎችም ለመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍትሄ አይሆኑም፡፡ በጉባኤው ላይ የህወሃት ሊ/መንበር “ልማቱ ሲቀላጠፍ የመልካም አስተዳደር ችግሮችም ይፈታሉ ” በማለት የሰጡት ሃሳብ የተሳሳተ መሆኑን የቀድሞው ምክትል ጠ/ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ መናገራቸው አስደስቶኛል! (አንጋፋ የብአዴን ታጋይና በመተካካት ሥልጣን ያስረከቡ ግንባር ቀደም ባለሥልጣን መሆናቸው እንዳይዘነጋ!) ኢህአዴግ ራሱን “አድርባይ” ብሎ ሲገመግም ምን ሊል እንደፈለገ አልገባኝም ብያችሁ አልነበር —- ስለዚህ ምን አደረግሁ መሰላችሁ — “የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል” ያዘጋጀውን መዝገበ ቃላት አንስቼ ፍቺውን ማፈላለግ ጀመርኩላችሁ (ነገርዬው የአገር ጉዳይ ነዋ!) እናላችሁ እንዲህ ይላል- “አድርባይ አደራ ከሚለው ግስ የመጣ ሲሆን አድርባይ ሆነ ማለት ተስማምቶና መስሎ ኖረ ማለት ነው” ቆይ ግን — የኢህአዴግ አመራር ከማን ጋር ነው ተስማምቶና መስሎ የኖረው? (እንወቀዋ!) ከተቃዋሚዎች? ከህዝብ? ከኪራይ ሰብሳቢዎች? ወይስ ከ”ሽብርተኛ”? (ይሄኔ ነው መሸሽ!) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ህላዌ ዮሴፍ ደግሞ “የአመራራችን ቁንጮ የሚጠየቅበት አሰራር አለ ወይ?” ሲሉ መጠየቃቸው የመገረምና የመደነቅ ስሜት ነው የፈጠረብኝ፡፡ ኢህአዴግ ከ20 ዓመት በላይ ሲገዛን የተጠያቂነት ሥርዓት እንኳን አልዘረጋም ማለት ነው? (እንዲያ ከሆነ በመጪው ወር ምርጫ ያገናኘን!) ይቺን “አድርባይ” የምትል የፈረደባት ቃል ፍቺ ስፈልግ አዲስ ሃሳብ ብልጭ አይልልኝ መሰላችሁ … ለኢህአዴግ የአማርኛ ቋንቋ መፍቺያ መዝገበ ቃላት ማዘጋጀት!! እውነቴን ነው… የኑሮ ውድነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሳያንሰን ኑሮአችንን የአማርኛ ቋንቋ ፈተና አደረገብን እኮ! ቆይ እስቲ–“የቀለም አብዮት” ማለት ምን ማለት ነው? “ተቸካይ” ማለትስ? “ጥገኝነትስ?” “ኪራይ ሰብሳቢስ?” የሰሞኑ “ተራማጅ” የሚል ቃልስ? (ደርግም ተራማጅ መሆኑን ያውጅ ነበር ብዬ እኮ ነው!) አሁን ለምሳሌ ተቃዋሚዎች ፈፅሞ ሊገባቸው ያልቻለ ኢህአዴግ የሚያዘወትረው አንድ አባባል አለው – “ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት አስመዝግቤአለሁ” የሚል፡፡ እናላችሁ — እነዚህንና ሌሎችንም አስቸጋሪ የኢህአዴግ ቃላት ያካተተ መዝገበ ቃላት ለማሰናዳት ስፖንሰር እያፈላለግሁ ነው፡፡

(ምርጥ የቢዝነስ አይዲያ አይመስላችሁም?) አንድ ወዳጅ አለኝ – ተቃዋሚዎችን “ያሳዝኑኛልም ያናድዱኛልም” የሚል (ፈረንጆቹ love – hate relationship የሚሉት ዓይነት መሆኑ መሠለኝ) ይሄ ወዳጄ የኢህአዴግን 9ኛ ጉባኤ እንደ ልብ ሰቃይ ፊልም ቤቱን ቆልፎ በኢቴቪ ሲኮመኩምልኝ ሰነበተና በቀደም ዕለት ስልክ መታልኝ – “ሃሎ” አልኩት፡፡ “እቺ አገር እኮ ዜጐቿን በሁለት ሚዛን ነው የምትሰፍረው!” አለኝ – ተስፋ በቆረጠ የአነጋገር ቃና፡፡ “ምነው… ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ?” አልኩት “የኢህአዴግ አድርባይ አመራሮች በተንቆጠቆጠ አዳራሽ ሲሰበሰቡ — ተቃዋሚዎች አዳራሽ አጥተው በየቤታቸው ይሰበሰባሉ!” (ምህዳሩ ጠቧል ሲባል የት ነበረ?) “ግን እኮ ኢህአዴግም አምኗል!” አልኩት – ዝም ከማለት ይሻላል ብዬ “ምኑን?” ተገርሞና ተቆጥቶ ጠየቀኝ “የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለበት!” የሚገርም ሳቅ በጆሮዬ እያንቆረቆረልኝ ሳለ ስልኩ ተቋረጠ (እድሜ ለቴሌኮም!) ወዳጄ ዝም ብሎ በሸቀ እንጂ ኢህአዴጐችም ቢሆኑ እኮ በአንዴ “ባለ 7 ኮከብ” አዳራሽ ውስጥ አልተንፈላሰሱም፡፡

እስቲ አስቡት 17 አመት ሙሉ በትግል ላይ ሳሉ የት ነበር ጉባኤያቸውን የሚያካሂዱት? ዛፍ ስር እኮ ነበር (ታሪክ ነው እንዳትሉኝ ብቻ!) ለነገሩ ተቃዋሚዎችም ዛፍ ስር ይሰብሰቡ ቢባል እኮ አያስኬድም (ኢህአዴግ “የትጥቅ ትግል” በኔ ይብቃ ብሏላ!) እስቲ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ … በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱ ይመስላችኋል? (የስልጣን ዘመኑ ስንት ነው ካላችሁኝ ግን እንኳን እኔ ባለቤቱም አያውቀውም) እናንተ ግርም ይላል እኮ —- መልካም አስተዳደር እንደናፈቀን የ22 ዓመት ጐረምሳ አደረስንም አይደል! እግረ መንገዴን አንድ ነገር ጣል ላድርግ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ህገመንግስታዊ መብታችንን ኢህአዴግ ሊያረሳሳን የፈለገ ይመስላልና እንደነቃንበት ለምን አንነግረውም? (በእልህ ሳይሆን በፒስ!) ወይ ይፈቀድ ወይ ይከልከል? (እዚህና እዚያ ማጣቀስ አይቻልም!) እርግጠኛ ነኝ— ኢህአዴግ ህገመንግስቱ ያጎናፀፈንን መብታችንን መልሶ ይሰጠናል (“አድርባይነት” ቢያስቸግረውም 2 ሚ. ብር እየመዥረጠ ለተቃዋሚዎች የሚለግስ “ቸር ፓርቲ” እኮ ነው!)

addisadmas.com

የአረብ አገር ተጓዦች ፅንስ በማቋረጥ ለጉዳት እየተጋለጡ ነው!


 የአረብ አገር ተጓዦች ፅንስ በማቋረጥ ለጉዳት እየተጋለጡ ነው!
ፒያሳ በሚገኘው ሜሪስቶፕስ ኢንተርናሽናል ክሊኒክ አካባቢ በቋሚነት የሚያንዣብቡት ደላሎች ወደክሊኒኩ የሚያመሩ የመሰሏቸውን ወጣት እንስቶች አያሳልፉም “ክሊኒኩ ተዘግቷል፤ ወዴት ናችሁ?” በማለት በጥያቄ ያጣድፋሉ፡፡ ከቀናቸውና የሚያነጋግራቸው ካገኙ “የክሊኒኩ ዋና ዶክተር የግሉን ክሊኒክ ስለከፈተ እዛ ልውሠድሽ” በማለት ማግባባት ይጀምራሉ፡፡ አሁንም ከተሳካላቸው (በአብዛኛው ይሳካላቸዋል) አገልግሎት ፈላጊዋን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ቦታ (መንደር ውስጥ) ይወስዳሉ፡፡ በዚህ ሰዓት ደላሎቹ የሚያሳዩት ትህትናና ሽቁጥቁጥነት ማንኛዋም ሴት ለክፉ አደጋ ወደሚዳርጋት ሥፍራ ይወስዱኛል ብላ እንዳታስብ ያደርጋታል፡፡ ፅንስ ማቋረጥ የሚፈፀምበት ቦታ ከወሰዳት በኋላም ምናልባት በክፍያ ላትስማማ ትችላለች፡፡ ይኼኔ ደላላው መሀል በመግባት ያደራድራል፡፡
ይሄ ደግሞ የደላላውን የኮሚሽን ክፍያ ይጨምርለታል፡፡ ደላላው ሁሉን ደማምሮ ኮሚሽኑን ከተቀበለ በኋላ እብስ ይላል፡፡ ከዚህ በኋላ የሚመጣውን ክፉና ደግ የምትቀበለው እንስቷ ብቻ ናት፡፡ በዚህ ዓይነቱ የድለላ ስራ ላይ የተሠማራው የ16 አመቱ ታዳጊ ወንዱ (ጩቤ በሚል ቅፅል ስሙ ይበልጥ ይታወቃል) በቀን ከ8-10 የሚደርሱ ወጣት እንስቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ ወደሚፈፀምባቸው ሥፍራዎች እንደሚወስድ ይናገራል፡፡ ወንዱ እንደሌሎች ደላሎች “ክሊኒኩ ተዘግቷል” አይልም፡፡ በክሊኒኩ ሲሰሩ የነበሩ ዕውቅ ዶክተሮች የራሳቸውን ክሊኒክ ከፍተው መውጣታቸውንና አሁን ያሉት ተማሪዎች (ተለማማጅ ሃኪሞች) ስለሆኑ “እንዳያበላሿችሁ” በሚል እያስፈራራ ጭምር ነው ሴቶችን ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ አገልግሎት ወደሚሰጡባቸው ሥፍራዎች አግባብቶ የሚወስደው፡፡
ይሄ ደላላ አንደበቱን አምነው የተከተሉትን ተላላ ሴቶች፤ እሪ በከንቱ አካባቢ ወደሚገኝ ባህላዊ የፅንስ ማቋረጥ የሚካሄድበት ሥፍራ ይወስዳቸዋል፡፡ እኔ ወደዚህ ሥፍራ ልሄድ የቻልኩት ሜሪስቶፕስ አካባቢ ወንዱን አግኝቼው የአራት ወር ነፍሠጡር መሆኔን ከነገርኩት በኋላ ነው፡፡ እሪበከንቱ አካባቢ ስደርስ ግን አንድም ክሊኒክ የሚመስል ነገር አላገኘሁም፡፡ ሆኖም ደላላው ይሄ ዓይነቱ ጥያቄ ከእንስቶቹ ከመምጣቱ በፊት እያዋከበ በጭቃ የተሠራ ቤት ውስጥ ይዟቸው ዘው ይላል፡፡ ቤቱ ለእንስቶቹ እንጂ ወንዱን ለመሰሉ ደላሎች አዲስ አይደለም፡፡ በዚህ ቤት ውስጥ አንዲት ካርድ የምትሰጥ ሴት፣ አንድ ሃኪምና የፅንስ ማቋረጡን የሚሰራ “ባለሙያ” መኖራቸውን አይቼአለሁ፡፡ ቤቷ አንዲት ክፍል ብትሆንም በአቡጀዲ ጨርቅ ሦስት ቦታ ተከፋፍላለች – ሦስት ክፍሎች ለመፍጠር፡፡ ወደዚህች ቤት እንደገባን በወንዱ መሪነት ለካርድ ሀያ ብር ከፍዬ ከተደረደሩት ወንበሮች በአንደኛው ላይ ተቀመጥን፡፡
ከጎኔ ሁለት የምኒሊክ ት/ቤት ዩኒፎርም የለበሱ ወጣት እንስቶች ተቀምጠው ነበር፡፡ ጠጋ ብዬ ለምን እንደመጡ ጠየቅኋቸው፡፡ ጓደኛቸው አርግዛ ለማስወረድ ይዘዋት እንደመጡና ሃኪሙን ልታነጋግር ወደውስጥ እንደገባች ነገሩኝ፡፡ “አያስፈራም?” ስል ጠየቅኋቸው፡፡ እንደማያስፈራ ከነገሩኝ በኋላ የተለያዩ አማራጮች እንዳሉና አንዱን መምረጥ እንዳለብኝ ምክር ቢጤ ለገሱኝ፡፡ ወዲያው ጓደኛቸው ሃኪሙን አናግራ በመውጣቷ በተራዬ እኔ ደግሞ ገባሁ፡፡ ደላላውም ተከትሎኝ ገባ፡፡ የሃኪሙ ነጭ ቀለም የተቀባ የሚመስል ጠረጴዛ ለዓይን እንኳን ይዘገንናል፡፡ መሀሉ የተቦረቸፈ ስትሬቸር ግድግዳው ጥግ ይታየኛል፡፡ የእርግዝና ማዳመጫ መሳሪያ ጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል፡፡ በቃ እኒሁ ናቸው የህክምና ቁሳቁሶቹ – ሌላ ነገር የለም፡፡ “ስንት ወርሽ ነው?” ሃኪሙ ጠየቀኝ “አራት ወር ገደማ ይሆነኛል” አልኩት- የውሸቴን መሆኑ እንዳይታወቅብኝ በመጠንቀቅ “ችግር የለም እስከ ሠባት ወር እንሠራለን —- ትንሽ ግን ክፍያው ይወደድብሻል” አለኝ ሃኪሙ “እኔ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ—- ጓደኛዬ ነው የሚከፍልልኝ፤ዋጋውን ንገረኝና ገንዘቡን ተቀብዬው እመጣለሁ” “እሺ አራት ወር ከሆነሽ ሠባት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤በመድሃኒት ወይም በማሽን ይሰራልሻል፤ ብሩ ተወደደብኝ ካልሽ ደግሞ በግሉኮስ ላስቲክ ሊሰራልሽ ይችላል” ሲለኝ የእያንዳንዱን ዋጋ እንዲነግረኝ ጠየቅሁት፡፡ እሱም ማብራራቱን ቀጠለ “በመድሃኒት ለሚሠራው ነው ሠባት መቶ ብር ያልኩሽ፤ በማሽን ከሆነ ስድስት መቶ ብር ትከፍያለሽ፤ በግሉኮስ ሶስት መቶ ብር” ከጓደኛዬ ጋር ልምከርበት አልኩትና ሃኪሙን አመሥግኜው ወጣሁ፡፡ ከቤቱ እንደወጣን “ቤቱ ደስ አላለኝም” በሚል ሰበብ ወንዱ ሌላ ቦታ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት፡፡ “ችግር የለም” አለኝና መንገዳችንን ቀጠልን – ወደ ሁለተኛው አማራጭ፡፡
ብዙም ሳንደክም ነው የደረስነው፡፡ “በርጌስ ክሊኒክ” የሚል ማስታወቂያ ያለበት የህክምና ተቋም ውስጥ ይዞኝ ገባ – ፈቃዴን ከጠየቀኝ በኋላ፡፡ ክሊኒኩ መጀመሪያ ከገባንበት ቦታ በንፅህና አስር እጅ የተሻለ ነው፡፡ ታካሚዎች ተራ ይጠብቃሉ፡፡ ወንዱ ልክ እንደጓደኛው እጄን ይዞኝ ለካርድ ክፍል ሠራተኞች ምልክት ሠጥቷቸው ወደ ሃኪሙ ክፍል ወሰደኝ፡፡ ታዳጊው ደላላ ለክሊኒኩ ቤተኛ መሆኑ ያስታውቃል፡፡ ይሄኛው እንኳን የክሊኒክም ወግ አለው፡፡ የተራቀቁና ዘመን አመጣሽ ባይሆኑም የተለመዱት የህክምና መሳሪያዎች ይታያሉ፡፡ ዶክተሩ ወንዱን ስላየ ነው መሠለኝ በቀጥታ “ስንት ወርሽ ነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ “አራት ወሯ ነው፤ ጓደኛዋ አደራ ብሎኝ ነው” ሲል ወንዱ ፈጠን ብሎ መለሰ “እሺ አሁን ትሠሪያለሽ?” የዶክተሩ ጥያቄ ነበር ዋጋውን እንዲነግረኝ እና ከጓደኛዬ ጋር ተማክሬ እንደምወስን ገለፅኩለት፡፡ “እዚህ ክሊኒክ ግሉኮስ የሚባል ነገር የለም፤ ዋጋው ደግሞ አንድ ሺህ ሠባት መቶ ብር ነው” አለኝ ፍርጥም ብሎ፡፡ ከሃኪሙ ክፍል እንደወጣን ለወንዱ የፍርሃት ስሜት ውስጥ እንደገባሁና እዚህ ክሊኒክ ውስጥ ያሰራች አንዲት ሴት ባገኝ ሁኔታውን ጠይቄያት እንደምደፋፈር ነገርኩት፡፡ እኔ ግን የፈለግሁት ሊያሰሩ የመጡ ሴቶችን ለማነጋገር ነበር፡፡ ወንዱም ያልኩትን ለመፈፀም ለአፍታ እንኳ ሳያመነታ “ተከተይኝ” ብሎ ይዞኝ ሄደ፡፡ ጥግ ጥጋቸውን ይዘው የሚያቃስቱ ሴቶች ነበሩ፡፡ በአንድ ጠባብ ክፍል ውስጥ ባሉ አልጋዎች ላይ በሆዳቸው የተኙም ሴቶች ተመልክቼአለሁ፡፡ ወደ አንዷ ሴት ጠጋ አልኩና ጠየቅኋት “ህመሙ ለትንሽ ደቂቃ ነው አትፍሪ” የሚል ማበረታቺያ ሰጠችኝ፡፡ “የስንት ወር ነው ያሰራሽው?” አልኳት፡፡
“እኔ መውለድ ነበር የምፈልገው፤ሆኖም የአረብ አገር ቪዛ መጣልኝና ላስወርድ ፈለግሁኝ፤ ሜሪስቶፕስ ሄጄ ወርሽ ገፍቷል አንሰራም ሲሉኝ ደላላው ወደዚህ አመጣኝ” አለችኝ፡፡ ልጅቱ በነበረችበት ክፍል ውስጥ 18 ሴቶች ነበሩ፡፡ ዘጠኙ ወደ አረብ አገር የሚሔዱ ናቸው፡፡ የዕለቱ ዕለትና በንጋታው የሚበሩ ሴቶችም ነበሩ፡፡ ከክፍሉ ስንወጣ ለደላላው ሀያ ብር ሠጠሁትና ስልኩን ተቀብዬ እንደምደውልለት ነግሬው ተለያየን፡፡ በዚያው ሰሞን በአንድ የዘመድ ለቅሶ ላይ በሜሪስቶፕስ ክሊኒክ ውስጥ የምትሰራ አንዲት ሲስተር አገኘሁና በፅንስ ማቋረጥ ዙሪያ አንዳንድ ነገር ተጨዋወትን፡፡ ሲስተሯ እንደነገረችኝ ወደ ክሊኒኩ ፅንስ ለማቋረጥ ከሚመጡ ሴቶች አብላጫውን ቁጥር የሚይዙት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ናቸው፡፡ እሷን የሚያስጨንቃት ታዲያ ሦስት ወር ከሆናቸው በኋላ ወደክሊኒኩ መጥተው የሚመልሷቸው ነፍሰጡር ሴቶች ጉዳይ ነው፡፡ ክሊኒኩ ከፀነሱ ሦስት ወር ለሞላቸው እንስቶች አገልግሎት እንደማይሰጥ ሲነግራቸው፤ ወደ ህገወጥ ቦታ መሄዳቸው ክፉኛ እንደሚያሳስባት ትናገራለች፡፡ “አንዲት ሴት እስከ ሁለት ወር የሚደርስ ፅንስ በመድሀኒት ማቋረጥ ትችላለች፡፡ አንድ ፍሬ ክኒን በመጀመርያው ቀን ትውጥና በሶስተኛው ቀን ደግሞ አራት ፍሬ እንድትውጥ ይደረጋል፡፡
አብዛኛዎቹ ሴቶች ግን መድሃኒቱን አይመርጡም፡፡” ያለችው ሲስተሯ፤ ምክንያቱን ስንጠይቃቸው አረብ አገር ስለሚሄዱ እንደሆነ ይነግሩናል ትላለች፡፡ አንዳንዶቹ ግን ፅንሱ በመጀመሪያ በዋጡት መድሃኒት ብቻ የሚወርድ ስለሚመስላቸው በዛው ይቀራሉ፤ ይሔ ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል ብላለች፡፡ “አንዳንዶቹ እንደውም የሔዱበት አገር ተመርምረው ነፍሠ ጡር መሆናቸው ሲታወቅ ተመልሠው ይመጣሉ፤ይሔም ሌላ ኪሳራ ነው” የምትለው ባለሙያዋ፤ አረብ አገር እሄዳለሁ ብላ ፅንስ ለማቋረጥ የመጣች አንዲት ሴት የገጠማትን አሳዛኝ አደጋ ታስታውሳለች፡፡ “ልጅቷ ወደ አረብ አገር ልትሄድ ስትል ነው ለማስጠረግ የመጣችው፤ ቀኗ በመግፋቱ አንሠራም አልናትና ሌላም ቦታ መሄድ እንደሌለባት መክረን ሸኘናት፤ እሷ ግን ባህላዊ ፅንስ የማቋረጥ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ በመሄድ በሠጧት የግሉኮስ ላስቲክ ምክንያት ማህፀኗ በመበሳቱ፤ደሟ ወደ ሆዷ ፈስሶ ህይወቷ አለፈ” ብላለች – ሲስተሯ፡፡ ተዘዋውሬ ባየኋቸው የሜሪስቶፕስ ክሊኒኮች አብዛኛዎቹ አገልግሎት ፈላጊዎች ወደአረብ አገር የሚጓዙ ሴቶች መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ፡፡
በዚህም ምክንያት በቀን ጥቂት ሴቶችን ብቻ ያስተናግዱ የነበሩ የክሊኒኩ ቅርንጫፎች፤ አሁን ከአቅማቸው በላይ እየሆነባቸው ቀጠሮ እስከ መስጠት ደርሠዋል፡፡ ክሊኒኩን ያጨናነቁት በዋናነት የአረብ አገር ተጓዥ ሴቶች ቢሆኑም ክሊኒኩ በፊት ከሚሠጠው በማሽን የመጥረግ አገልግሎት በተጨማሪ በመድሀኒት የመጥረግ አገልግሎት መጀመሩም የተጠቃሚዎቹን ቁጥር እንደጨመረው ሲስተሯ ትናገራለች፡፡ “በመድሃኒት ፅንስ ማቋረጥን ብዙዎች እንደጨዋታ ነው የሚያዩት፤ ምክንያቱም እምብዛም የህመም ስሜት የለውም” የምትለው ባለሙያዋ፤ ዋናው ነገር ሴቶች ፅንስ ለማቋረጥ ብለው በየመንደሩ በመሄድ ህይወታቸውን ለአደጋ ከማጋለጥ መቆጠባቸው ነው፤ ማናቸውንም ጉዳዮች የህክምና ባለሙያዎች በማማከር ቢፈፅሙት ራሳቸውን ከሞት አደጋና ከጤና እክሎች ሊጠብቁ ይችላሉ ስትል ትመክራለች፡፡ በአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል፣ የፅንስና የማህፀን ስፔሻሊስት ዶክተር ገላኔ ሌሊሳ ሲናገሩ፤ ማንኛውም ህክምና በትክክለኛ ባለሙያ መከናወን እንዳለበት ገልፀው፣ የእርግዝናው እድሜ እየገፋ በመ ቁጥር አደጋዎቹም እየከበዱ እንደሚሄዱ ያስረዳሉ፡፡ አንዲት ሴት በመጀመሪያዎቹ አስራ ሁለት ሳምንት የምታደርገው ውርጃዎች ትንሽም ቦሆን ችግር አላቸው ምንኛውም ሴት እስከ ስምንት ሳምንት ያልሞላው ጽንስ አንዳንዴ በተፈጥሮም የሚቋረጥበት አጋጣሚ ይኖራል፤ በህክምናም ሊቋረጥ ይችላል የሚሉት ዶ/ር ገላኔ፤ ይሄ የተለየ ችግር ያመጣል ተብሎ አይታሰብም ብለዋል፡፡
አንዲት ሴት ፅንሷ ከተቋረጠ በኋላ እረፍት ሳታደርግ ለጉዞ ብትነሳ ወይም ወደ ስራ ብትገባ ችግር ያጋጥማታል ማለት አይደለም ያሉት ዶ/ር ገላኔ፣ ነገር ግን ማንኛውም ህክምና ሁሌም ክትትል ያስፈልገዋል፤ ህክምናው ትክክለኛ ውጤት ማስገኘቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ለምሳሌ ከህክምና በኋላ፣ እንደተጠበቀው ፅንሱ ሳይቋረጥ ቢቀር በጣም አስጊ ስለሚሆን ክትትል ማድረግ ይኖርባታል ብለዋል ዶ/ር ገላኔ፡፡ የፅንስ ማቋረጥ ህክምና በሁለት መንገድ እንደሚካሄድ ዶ/ር ገላኔ ጠቅሰው፣ አስር ሳምንት ያልሞላው ጽንስ በመድሀኒት ሊቋረጥ ይችላል፤ የፅንሱ እድሜ ከዚህ በላይ ከሆነ ግን የግድ መጠረግ ይኖርበታል ብለዋል፡፡ ከሁለቱ ዘዴዎች መካከል በመድሃኒት ጽንስ የማቋረጥ ዘዴ ተመራጭ ነው፣ ምክንያቱም ከማህፀን ጋር ምንም ንክኪ ስለሌለው የማህፀን መኮማተርን አያስከትልም፡፡ ስለዚህ ያልተፈለገ እርግዝና ሲከሰት ጊዜው ሳያልፍ ወደ ትክክለኛው የህክምና ባለሙያ መሄድ ያስፈልጋል ሲሉ ዶ/ር ገላኔ ይመክራሉ፡፡
addisadmas

Friday, March 29, 2013

አለማቀፍ መንግስታዊ ድርጅቶች ባደረጉት ጫና ካራቱሬ ገንዘብ ለመበደር አለመቻሉን አስታወቀ


መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ እንደዘገበው ኦክላንድ የምርምር ድርጅቶችን የመሳሰሉ አለማቀፍ ተቋማት ባሰረፉት ጫና ኩባንያው ከአለማቀፍ ድርጅቶች ገንዘብ ለመበደር ባለማቻሉ ከህንድ መንግስት ለመውሰድ ሳይገደድ አይቀርም።
የኩባንያው ስራ አስኪያጅ ሳይ ራካማራሺና እንደተናገሩት በ100 ሚሊዮኖች ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ከሌላ ወገን ለማግኘት ፈቃድ አግኝተዋል።
ካራቱሬ በኢትዮጵያ ሰፊ የእርሻ መሬት በመውሰድ ሩዝ በማምረት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው። ድርጅቱ 6  ሚሊዮን 500 ሺ የሚያወጣ ሩዝ ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረቡን ገልጿል።
የህንዱ ኩባንያ ከ100 ሺ ሄክታር በላይ መሬት 108 ሺ ዶላር በመክፈል ብቻ በሊዝ መግዛቱን ብሉምበርግ ዘግቧል።
ሟቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊ የአገሪቱን መሬት በነጻ በሚባል ሁኔታ ለውጭ ባላሀብቶች መስጠታቸው ከፍተኛ ወቀሳ እንዲሰርባቸው ማድረጉ ይታወሳል።

ኢትዮጵያውያን ደቡብ አፍሪካ የኢሕአዴግን ስብሰባ በተኑ፤ ቴዎድሮስ አድሃኖም ተደብቀው አመለጡ


ዘ-ሐበሻ) በደቡብ አፍሪካ ሮዝባንክ ከተማ የተጠራው የኢሕ አዴግ ሥብሰባ በኢትዮጵያውያን ብርቱ ትግል መቋረጡንና መበተኑን የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ሪፖርተር ከሥፍራው ዘገበ። በልማት ስም የተጠራውና በውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የተጠራው ይኸው ስብሰባ የስር ዓቱ ደጋፊ የሆኑ ከ20 የማይበልጡ ሰዎች ቢገኙም ስብሰባው ይደረግበት የነበረውን ሃያት ሆቴል የስር ዓቱ ተቃዋሚዎች በመሙላት ስብሰባው እንዳይደረግ አድርገዋል።
የድምጻችን ይሰማ፣ የኦነግ፣ የግንቦት ሰባት እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላትና ደጋፊዎች በአንድነት የኢሕ አዴግን ስብሰባ እንዳይደረግ በማድረግ
- ከልማት በፊት የሕዝብ ነፃነት ይቅደም
- በቅድሚያ መገደብ ያለበት ወንዝ ሳይሆን የ ኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ነው በሚል ሕዝቡ ጩኸቱን በማሰማቱ ስብሰባው ተቋርጦ ደጋፊው ሕዝቡ ጥቃት ያደርስባቸዋል በሚል ፍራቻ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ደብቆ ከአዳራሹ አስመልጧል።
የኢሕአዴግ ስብሰባ እንዳይደረግ ያስተጓጎሉት ኢትዮጵያውያን ኢሕ አዴግ በከፈለበት የሃያት ሆቴል አድራሽ ስብሰባ በማድረግ በቀጣይ በአንድነት ስለሚያደርጉት የጋራ ትግል ዙሪያ መነጋገራቸውን፤ የተዘጋጀውን ውሃ እና መጠጥም የኛ ገንዘብ ነው በሚል እንደጠጡት የዘገበው የዘሐበሻ ሪፖርተር የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሃያት ሆቴል ስብሰባው ከተስተጓጎለበት በኋላ ደጋፊዎቹን በኢምባሲው ውስጥ መሰብሰቡ ታውቋል። ከኢትዮጵያ ኢምባሲ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ከሮዝባንክ ከተማም ኢትዮጵያውያን ወደ ኢምባሲው በመሄድ ተቃውሟቸውን እንዳሰሙም ሪፖርተራችን ጨምሮ ዘገቧል።
zehabesha.com

የመንግስት ባለስልጣናት እያስፈራሩዋቸው መሆኑን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት ተፈናቃዮች ተናገሩ


መጋቢት ፳  (ሃያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተፈናቅለው በምእራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ ሜዳ ላይ ወድቀው የሚገኙት አማራ ተወላጅ አርሶደአሮች ከክልሉ ዋና ከተማ እና ከዞኑ የተውጣጡ ባለስልጣናት ዛሬ ሰብስበው ያነጋገሩን ቢሆንም ፣ ተስፋ የሚያስቆርጥ መልስ ሰጥተውናል በማለት ለኢሳት ተናግረዋል።
አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ባለስልጣናቱ ከተማውን ለቀው ወደ ወረዳቸው እንዲሄዱ፣ የተቀሙትን ሀብትና ንብረት በተመለከተ ጥያቄ ሲያቀርቡም ” ቀድሞ ማን ሂዱ አላችሁ አናውቅም” ብለው እንደመለሱላቸው ተናግረዋል።
ያለምንም መጠለያ 2 ሺ አባወራ ሜዳ ላይ ተጥሎ እንደሚገኝ የተናገሩት ተፈናቃዮች፣ ከንጽህና ጉድለት ጋር በተያያዘ በሽታ ተነስቶ ህጻናትና ሴቶች ሊያልቁ ይችላሉ በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል። ተፈናቃዮች ምግብ እየቀረበላቸው መሆኑን ተናግረዋል፣ ምግቡን የሚያቀርብላቸው ግን ቀይ መስቀል ይሁን መንግስት አላወቁም።
አንዲት እናት በወለደችበት እለት አካባቢውን ለቃ እንድትወጣ መደረጉን ተፈናቃዮች ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ  አሁንም የቤንሻንጉል ጉሙዝን ክልል ለቀው ባልወጡ አርሶአደሮች ላይ የሚፈጸመው ግድያና እንግልት መጨመሩን በከማሼ ዞን የሚኖሩ ለመፈናቀል ተራቸውን በመጠባበቅ ላይ ያሉ አርሶአደሮች ገልጸዋል።
የተፈናቃዮችን ሀብት ለመዝረፍ በሚደረግ ሙከራ ዛሬ አንድ ግለሰብ በጥይት ተመትቶ መሞቱን ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁን አርሶደሮች ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ “  ለዜጎች መሞት፣ መፈናቀልና መሰደድ ተጠያቂው መንግስት ነው!!! ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃለን ” በሚል ርእስ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።
ፓርቲው በመግለጫው ” አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት የሚከተለው ቋንቋን መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝምና የስርዓቱ አራማጆች ካላቸው የስልጣን እድሜን የማራዘም ጉጉት ተደማምረው ለሃገራችን እንዲሁም ተቻችሎ፣ ተዋልዶ፣ ተዛምዶና ተዋድዶ ለዘመናት ይኖር ለነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ ግልፅና አስፈሪ አደጋ ወደ መሆን እንደደረሱ በግላጭ እየታየ ነው፡፡” ብሎአል።
በማያያዝም ” ያ ለዘመናት አብሮን የቆየው በጋራ የመኖር ዕሴት እየተደመሰሰ በምትኩ የሚያጋጩ ስልቶች እየተፈጠሩና እየተተገበሩ ወደ ሰቆቃ ተለውጠው ይገኛሉ፡፡ የዜጎች ሰላዋዊና ህጋዊ መብት እየተጣሰም ነው፡፡ በኢትዮጵያችን ውስጥ አብሮ የመኖር፣ ከቦታ ቦታ የመዘዋወርና በፈለጉት ቦታ ሃብት የማፍራት ህልውና እያከተመ መጥቷል፡፡ ለዚህ ክፉ ድርጊት ተጠያቂ የሚሆነው ደግሞ የዜጎችን መዘዋወር መብትና ሃብት የማፍራት መብት ማረጋገጥ የተሳነው መንግስትና መንግስት ብቻ ነው፡፡” ብሎአል።
” ከቤኒሻንጉል ክልል የአማራ ተወላጅ የሆኑትን ዜጎች የዘመናችን ሹመኞች ከኢ-ሰብዓዊነት ባፈነገጠ መልኩ ከእቃ ለሚሰጥ ክብር ባነሰ ሁኔታ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ በጅምላ እየተጫኑ መጣላቸውን ቀጥለዋል፣  የሚለው አንድነት ” በርካታ ህፃናትም የዚህ ግፍ ሰለባ ሆነዋል፤ እየታፈኑ የሚሞቱትም ቁጥራቸው በርካታ” ብሎአል።
ፓርቲው በመቀጠልም “በጣም የሚያሳቅቀው ደግሞ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት 59 ሰዎች ሞት ጉዳይ ነው፡፡ ካላግባብ በጭካኔ  ለብዙ ዓመታት ከኖሩበት፣ ከወለዱበትና ከከበዱበት ስፍራ ሃላፊነት በጎደለው ሁኔታ በአንድ መኪና እየታጨቁ እንዲወጡ በማድረግ ገደል ውስጥ ገብተው እንዲሞቱ የተፈረደባቸው ዜጎችን ህይወት እንዲቀጠፍ ያደረገውም በቸልታ እየገዛ ያለው የኢህአዴግ መንግስት ነው፡፡ መንግስት በነዚህ ዜጎች ላይ ለደረሰው ኢ- ሰብዓዊ ድርጊትና ህይወት ማጣት ተጠያቂ ነው” በማለት ፓርቲያችን ያምናል ብሎአል።
“ለውጭ ዜጎች እንዲበለፅጉበት በትንሽ ሳንቲም፤ ግልፅነት በጎደለውና በሙስና በተተበተበ አሰራር ለቻይና ኩባንያዎች፣ ለህንድ ኩባንያዎች፣ ለሳዑዲ አረቢያ ኩባንያዎች ወዘተ ለዜጎቻቸው ቀለብ እንዲያመርቱበት በገመድ እየተለካ የሚሰጠው የአዲስ አበባን ስፋት አምስት ጊዜ የሚበልጥ መሬት እንዴት ለዜጎቹ ይነፈጋል? ለምንስ ኢትዮጵያውያን ተዘዋውረው በኩርማን መሬት ላይ ሃብት የማፍራት መብታቸውን ተነፈጉ? ይህንን ኢሰብኣዊነት ዓለማቀፉ ማህበረሰብ፣ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንዲያውቁት እንፈልጋለን፡፡” ብሎአል አንድነት በመግለጫው።
ኢህአዴግንንና በእሱ የሚመራውን መንግስት ታሪክና ሕዝብ ይፋረደዋል፡፡ ይህንንም በደል እያዩና እየሰሙ ዝም ማለት የወንጀሉ ተባባሪ መሆን ማለት ነው፡፡ ዛሬውኑ ተቃውሞአችንን፣ ጩኸታችንን እናሰማ፤ በደል ሰቆቃ በቃ እንላለን፡” በማለት ጥያቄ የሚያቀርበው አንድነት፣ ለዚህ ሁሉ አገራዊ ቀውስ ተጠያቂው መንግስት መሆኑን” ገልጾ፣  ዜጎች እንዲሞቱ፣ እንዲጎሳቆሉና እንዲሰደዱ ያደረጉ ወንጀለኞች በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ የሴቶችና ህፃናት መብት እንዲከበር፣ ማፈናቀሉ አሁኑኑ እንዲቆም፣ ተጎጅዎችም ካሳ እንዲከፈላቸው እንጠይቃለን፡ በማለት አቋሙን አንጸባርቋል።
የአማራ ክልል ባለስልጣናት እስካሁን በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫ ወይም ማብራሪያ አልሰጡም።

ESAT Daily News-Amsterdam March 29 2013 Ethiopia


Wednesday, March 27, 2013

ፈለገ ፕ/ር አስራት ወልደየስ የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!


“ዛሬ ውድ ሀገራችን ደብዘዋ ጠፍቶ፣ ሕዝቧ ምስቅልቅሉ ወጥቶ ፣ሥነልቡናው እየተሰለበ፣ዓይኑ እያየና ጆሮው እየሰማ፣ ባህሉ እየተንቋሸሸ፣ታሪኩ እየተደለዘና ቅርሱ እየተመዘበረበት የውሻ ሞት እየሞተ ነው። በእንደዚህ ያለ የመከራ ጊዜና ወቅት አንገቱን ደፍቶ፣ያልከፋው መስሎ ሆደሰፊ በመሆንና ሳይቸኩል ፈጣሪውን ለምህረት እየተማፀነ ራሱን ሳያጋልጥ ለትግል የሚሰናዳ ታላቅ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ነው። ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የደገሱለት ድግስ እንደሱማሌና እንደላይቤሪያ እንዲሆን ስለነበረና ይህም አልሳካ በማለቱ፤ ይሄን ውጤት ያስገኘው የኢህአዴግ መልካም አስተዳደር ነው በማለት ዓለምን አደንዝዘው ያዙት። ይህም ድንዘዛ እንዲቀጥል ከኢህአዴግ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ ፍጹም ሰላም መኖሩን፣ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኮሚንስቱ ስለተነሱለት በደስታና በመፈንደቅ መኖሩን ፤ የአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን ዲሞክራሲ እየፋፋ መሆኑንና ከአንዳድ ጥቃቅን ችግሮች በሰተቀረ የሰብኣዊ መብት በኢትዮጵያ መከበሩን ዲሞክራት ሀገሮች ነን የሚሉ ሁሉ ህዝባቸው በማታለል ላይ ናችው።”
ፕ/ር አስራት ወልደየስ በመዐህድ የወጣቶች ስብሰባ ላይ ከተናገሩት የተወሰድ።
ሙሉ ንግግራቸውን ከታች ካለው ቪዲዮ ላይ ይከታተሉ።
http://www.ethiotube.net/video/19536/Professor-Asrat-Woldeyes

እንደዛቱት አቶ አማረ አሞኘ የጠ/ፍርድ ቤት የመሃል ዳኛ በችሎት አልተገኙም::


ዛሬ ማርች 27/2005 ዓ.ም ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ የተቀጠረው የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለኤፕሪል 8 ቀን 2013 መዘዋወሩ ተሰማ። በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ፍርድ ቤቱ እንደተለመደው ጉዳዩን ለመርመርና ለመወሰን ተጨማሪ ጊዜ ያስፈልገኛል ባለው መሠረት ተጨማሪ ጊዜ ጠይቋል።
ከሰሞኑ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአዲስ አበባ “ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡”ብለው እስከ ሚ/ሮች ምክር ቤት ድረስ ሄደዋል የተባሉት ዳኛ አማረ አሞኘ በችሎቱ አለመገኘታቸው ተናግረዋል።

Tuesday, March 26, 2013

“ኢህአዴግ በህዝብ (ያልተመረጠ) ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም”

N G


“ … አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም” ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ።
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን በመወከል ሬዲዮ ፋና በሚያዘጋጀው የ”ሞጋች” ቃለ ምልልስ ክፍለ ጊዜ ላይ ተገኝተው ነበር። ቃለ ምልልሱ ከመጀመሩ በፊት “ጋዜጠኛው” ፕሮግራሙ ፈረንጆቹ እንደሚሉት “ሃርድ ቶክ አይነት ነው” አለ። ይህን ጊዜ ቀልቤን ሳበኝ። የቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜና የጠያቂው ጠልቆ የመግባት ችሎታ ታየኝና ዶ/ር ነጋሶ ሲዝረከረኩ ለመስማት ተዘጋጀሁ።
ጥያቄ ተጀመረ። ዶ/ር ነጋሶ መመለስ ቀጠሉ። የመጀመሪያዎቹ ጥያቄዎች የተለመዱ፣ የተረገጡ፣ የተሰለቹና በየመድረኩ ብዙ የተባለላቸው ሆኑብኝ። ዶ/ር ነጋሶም ሳይቸገሩ ከፈገግታ ጋር መለሱ። በመነሻው የቀረቡትን የተለመዱ ጉዳዮች በመዝለል በሶስት ጉዳዮች ላይ በማተኮር ሪፖርት ለማዘጋጀት ወሰንኩ።
ስለ ጠያቂው
አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው
ጠያቂው ጋዜጠኛ ነጋሶን ሲጠይቅ ላዳመጠ ጋዜጠኛ ሳይሆን ትክክለኛ ስሙ “ካድሬ” ነውና በዚህ ይስተካከል። መጀመሪያ ላይ “ይባላል፣ ይነገራል፣ ይደመጣል፣ አስተያየት ይሰጣል …” በማለት አግባብ ያለው አካሄድ ተከተለና በኋላ ላይ ግምገማ ፍርሃቻ ነው መሰል ነጋሶን አላናገር ብሎ ጭልጥ ያለ ክርክር ውስጥ ሲገባ ከኋላው አቶ ሴኩ ቱሬ ጌታቸው ምናምን የሚያሳዩት ይመስል ነበር። ያም ቢሆን “ገራም”፣ ቀስ ብሎ የሚናገርና በድርጅት ፍቅር የደረቀ አይመስልም።
የግራ ዘመም ስለመሆናቸው
ነጋሶ አሁን የሚመሩት አንድነት ፓርቲ የሊብራል ፖለቲካ እሳቤ አቀንቃኝ ነው። እሳቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ “የግራ ዘመም” ፖለቲካ አፍቃሪ ነበሩ። ኢህአዴግ ውስጥም ዋናው የልዩነታቸው መሰረት የግራውን መንገድ በትክክል መከተል ያለመቻልና የመበረዝ ችግር ነው። ዛሬ ምን ተገኘና ነው አዲስ አቋም የተያዘው በሚል ጠያቂው ያነሳው ሃሳብ የስሙን ያህል ባይሆንም ሙግት አስነስቶ ነበር። ጥያቄው ግን ምላሽ ያገኘው ውይይቱ ሲያልቅ ነው።
“ግራ ዘመም ምንድነው” አይነት ጥያቄ አንስተው ከዓለም ወቅታዊ ሁኔታ ጋር መመሳሰል አግባብ እንደሆነ በማስገንዘብ አስተያየታቸውን የሰጡት ነጋሶ፣ “ትክክለኛ” የሚሉትን ሶሻሊዝም እንደሚናፍቁ አልሸሸጉም። ይህ አስተሳሰባቸውና እምነታቸው አንድነት ከሚከተለው መንገድ ጋር እንዴት ሊጣጣም እንደሚችል የገለጹት ግን ዓለምን መምሰል በሚለው እሳቤ ነው። ጠያቂው በውይይቱ ማሳረጊያ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በድጋሚ ይህንኑ ጉዳይ አንስቶ ነበር። ነጋሶ ግን “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። አቋሙን መቀየር ወንጀል አይደለም” በሚል ዘጉት። አዎ፣ አቋም ለያውም በፖለቲካው ጎዳና የሚቀያየር፣ ዓለምን እያዩ የሚበውዙት የካርታ አይነት ጨዋታ ነው። እናም “እሰይ አበጀሁ” አይነት መልስ መልሰው ተሰነባበቱ።
የጣመኝ ፈርሙ” ክርክር
የምርጫ የስነ ምግባር ኮድ ጉዳይ ለዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምርጥ የተባለና የነጋሶ የህግ ግንዛቤ በቀላሉ ነገሮችን በማስረዳት ጎልቶ የወጣበት ነበር። እንዲህ ተባባሉ። ጠያቂው “የምርጫ ስነ ምግባር ኮዱን ብትፈርሙ ምን ትሆናላችሁ?” አለ። “አዋጅ በሆነ ጉዳይ ላይ ለምን እንፈርማለን። እንደዚህ ከሆነ ባገሪቱ በየጊዜው በሚወጡ ህጎች ላይ እንፈርማ?” የነጋሶ ውድ መልስ ነበር።
ጥያቄ፦ ብትፈርሙ ምን ይጎዳችሁዋል …?
ነጋሶ፦ ለምን እንፈርማለን? ለህዝብ ጥቅም ሁላችንም ስንሰራ ኢህአዴግ በሚለው ተንበርክከህ ኢህአዴግን በምርጫ በማጀብ አይደለም …
ጥያቄ፦ ጉዳት አለው ህዝቡ ይጎዳል? ህግ ሆኗል አይደለም?
ነጋሶ፦ የስነ ምግባር ኮዱ ብቻውን በቂ አይደለም፤…. የኢህአዴግ አዲሱ ሊቀመንበር በመጀመሪያው ንግግራቸው ያሉትን አልሰማህም?
(ፎቶ: Martin Edström)
ጥያቄ፦ … ምን ጉዳት ይደርስባችኋዋል?
ነጋሶ፦ እነሱ ቢወያዩና ችግራቸውን ቢያስወግዱ ምን ችግር አለው?
ጥያቄ፦ ፖለቲካ አብሮ የመኖር ጥበብ ነው። አብሮ መስራት ጥቅም አለው፤
ነጋሶ፦ ያ! ያ! አብሮ መስራት በእኩልነት ነው እኮ!! ኢህአዴግ አንድ የፖለቲካ ሃይል ነው ወይስ አይደለም? ለምን እንበረከካለን? ንግረኝ?
ጥያቄ፦ ለህጉ ትገዙ አይደል?
ነጋሶ፦ ያ!! እኮ፤ አዋጅ ሆኖ በወጣ በስንት ህግ ላይ እንፈርማለን? ይህ ከሆነ ፓርላማ ቢስማማም ባይስማማም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሁሉም ጉዳዮች ላይ መፈረም አለበት ማለት ነው፤
በቀጣይ ወደ ሌላ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ አልፉ። ማጠቃያው ላይ አነሳዋለሁ፡፡
ለስደተኞችና ለስደተኛ አስተሳሰብ ትገዛላችሁ?
ጠያቂው ሊሞግት ያሰበበት ዋናው ጉዳይ መድረክም ሆነ አንድነት ከዲያስፖራው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በሚያውጣጣና በትጥቅ ትግል ከሚያምኑ ወገኖች ጋር ለመደመር ነበር። ከውጪ ሃይሎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ እንደሚታሙና ለዚህም መረጃ እንዳለው አንስቶ ላቀረበው ጥያቄ ማሰሪያ ያደረገው “አገር ቤት ያለውን ህዝብ አክብሮት አትሰጡትም። ለስደተኛና ለስደተኛ አስተሳሰብ ልዩ አክብሮት አላችሁ” የሚል ነበር።
ነጋሶ ከወትሮው ለየት ብለው ፖለቲካኛ የሆኑበትን መልስ የሰጡት ዲያስፖራውም ሆነ ማንም፣ ጋዜጠኛውን ጨምሮ ቢደግፉዋቸው ደስተኛ መሆናቸውን በማመለካት መልስ ጀመሩ። አስከትለውም “በየኤምባሲው ደጅ አይታጡም” እንባላለን አሉ። ነጮቹ የሚሰጡት ድጋፍ ለተሰጠበት ዓላማ እንዳልሆነ ለምን አትናገሩ ይባላል? በማለት ጠየቁ።
ስለ ዲያስፖራውና “ስደተኛ አስተሳሰብ” ስለተባሉት ሲናገሩ የሰላማዊ ትግል መንገዱ አያዋጣም የሚሉዋቸው እንዳሉ አመለከቱ። ሲያጠቃልሉት ማንም ይሁን ማን “ሰላማዊ ትግል አያዋጣችሁም ለሚሉን ከፈለጋችሁ ገንዘባችሁን አትርዱን እንላቸዋለን” በማለት የራሳቸውን መንገድ እንደሚከተሉ ገልጸው ጥያቄውን ቆለፉት።
አገር ውስጥ ያለውን ህዝብ አታከብሩትም ለሚለው ግን “በርግጥ በሚፈለገው ደረጃ ህዝብ ውስጥ ላንቀሳቀስ እንችላለን” በማለት ራሳቸውን ጥፋተኛ አስመስለው ቢሮ ይታሸግብናል፣ እኛን የሚደግፉ ከስራ ይባረራሉ፣ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አይፈቀድልንም፣ ሰላማዊ ሰልፍ እንድናደርግ አይፈቀድም፣ መምህራን እኛን ስለደገፉ ይባረራሉ፣ … ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ኢህአዴግ እንደሆነ ተናገሩ።
ኢህአዴግን ተቀብለውና ደግፈው ከሚሰሩ ፓርቲዎች ጋር አብረው መስራት እንደማይችሉ ሲገልጹ “ኢህአዴግን ከሚደግፉት ጋር ተቀምጠን ምን አብረን ልንሰራ እንችላለን” ካሉ በኋላ “ኢህአዴግን እንደመንግስት እውቅና ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱት መካከል ኢዴፓ በርካታ ልዩነቶች አሉት ግን ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና በመስጠት ይቀበላል። እናንተስ?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ኢህአዴግ በህዝብ፣ በምርጫ ገዢ ያልሆነ ፓርቲ ስለሆነ እውቅና አንሰጠውም” የሚል ግልጽ መልስ ሰንዝረዋል።
“ስለ አንቀጽ 39 ለምን አሁን ትጠይቀኛለህ?”
ነጋሶ ፓርቲያቸው አንቀጽ 39 እና የመሬት ጉዳይ ላይ ስላለው አቋም ግልጽ ያለ መልስ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ ተጠይቀው ነበር። በግራም ሆነ በቀኝ፣ እሳቸው በጻፉት መጽሃፍ ላይ ካቀረቡት ሃሳብ ጋርና ቀደም ሲል ኢህአዴግ በነበሩበት ወቅት ሲያራምዱት ከነበረው ሃሳብ አንጻር የሃሳብ መንሸራተት እንዳጋጠማቸው በማስመሰል ጠያቂው ሊሞግታቸው ሞክሮ ነበር። በተደጋጋሚ ለማስረዳት ቢሞክሩም ሊቀበላቸው ባለመቻሉ “አንድ ሰው ድንጋይ አይደለም። የአቋም መቀያየር ወንጀል አይሆንም” በማለት አሳርገውታል።
በጥቅሉ ግን ካላይ የተነሱት ሁለት መሰረታዊ ሃሳቦች ህዝብ ውሳኔ ሊያሳልፋቸው እንደሚገባ አመልክተዋል። መገንጠል መብት ቢሆንም እርሳቸው እንደማይደግፉት በግልጽ አስቀምጠው ያለፉት ነጋሶ፣ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት በመመስረት የሚመለሱ ጉዳዮች እንደሆኑ ግን አስምረውበታል። ምንም እንኳ ፓርቲያቸው የኒዎ ሊብራል ሃሳብ አራማጅ ቢሆንም በግላቸው በነጻ ኢኮኖሚ ስም መንግስት ከዋናና ህዝብን ከሚያገለግሉ ዋና ዋና የኢኮኖሚ አውታሮች መውጣት አለበት ብለው እንዳማያምኑ አስምረውበታል። በመድረክ ውስጥ ያሉት ፓርቲዎች ተመሳሳይ አቋም ባልያዙበት ሁኔታ ግንባር መመስረቱ ችግር እንዳለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና ዋና የሚባሉት የልዩነት ቁልፍ ጉዳዮች ህዝብ ውሳኔ እንዲሰጥባቸው በመዘርዘር አልፈዋቸዋል።
ጠያቂው መሃል በመግባት አንቀጽ 39ን ትቀበላላችሁ? በሚል ላቀረበላቸው “አሁን ለምን ትጠይቀኛለህ” በማለት አስረግጠው መልስ ሰጥተዋል። በዚሁ የራዲዮ ፋናን ስቱዲዮ በስንብት ለቀው ወጥተዋል።
ነጋሶ እንደ ፖለቲከኛ ድርጅቱ ላይ ደረሱ የተባሉትን ችግሮች በየመካከሉ በማስገባት ጥያቄን በጥያቄ መመለስ ቢችሉ ኖሮ ይበልጥ አሸናፊ ሆነው መውጣት ይችሉ ነበር። ለምሳሌ ስለህጋዊነት ሲነሳ የራዲዮ ፋና አፈጣጠር ህጋዊ አለመሆኑንና ኤፈርት ስለተቆታጠረው የኢኮኖሚ የበላይነት፣ ስለ እስርና የሚዲአ አፈና … በየመልሶቻቸው መካከል በማስገባት ቢመልሱና ጥያቄ ቢሰነዝሩ ቢያንስ ሃሳባቸውን በአድማጭ ላይ አራግፈው መውጣት በቻሉ ነበር። እንዲህ ያለ ሰፊ የሚዲያ ሽፋን ሲገኝ መሰረታዊ ብቻ ሳይሆን ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት የሚያጉረመርሙትን ጉዳዮች በማንሳት የራሳቸውን ልምድና ተሞክሮ ማካፈል ይችሉ ነበር። ጠያቂው ከኢህአዴግ ስለተለዩበት ምክንያት በሰሚ ሰሚ ላነሳላቸው ጥያቄ “ቆቅ” ፖለቲከኛ ሆነው መረጃ ማስተላለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው የዕለቱ ድክመታቸው ቢሆንም ሊሞገቱ ተጋብዘው ሞግተው ስለመውጣታቸው የዚህ ሪፖርት አቅራቢ ምስክራቸው ነው፡፡
http://www.goolgule.com/interview-negasso/

አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ ግፊት እየተደረገ ነው/ወያኔዎች ተደናግጠዋል!!

Imageአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተከፈተው በር ሰተት ብለው መግባት አለባቸው:: በወያኔ ውስጥ የተደረገውን የስልጣን ሽግሽግ ተከትሎ አዳዲስ ለውጦች እየታዩ ሲሆን የአቶ ሃይለማርያም የበላይነት ጎልቶ ለመውጣት እያቆበቆበ መሆኑን ከ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አከባቢ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ ከአከባቢው የህወሃት አክራሪዎች መወገድ እና የአቶ ደብረጺሆን የግለኝነት አትኩሮት ለአቶ ሃይለማርያም እድሉን ገርበብ አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የአቶ ደብረጺሆን ግለኝነት በሙስና ስም ሊደፈቅ እንደሚችል ያከባቢው ገማቾች ሲናገሩ ወታደራዊው አካል ራሱን ለማዳን ሲል በተጠንቀቅ ከሃይለማሪያም አዲስ ካበበው ቡድን ጋር እንደሚሰለፍ አንዳንድ ፍንጮች ታይተዋል:: አቶ ሃይለማርያም በሙሉ መንፈስ ባይሆኑም ድፍረት እንዳገኙ ከደቡብ ጉባዬ በሁዋላ እየታየ ሲሆን የደቡብ ባለስልጣናት አንድነት ወያኔን አስደንግጦታል::
የሕወሓት የቀድሞ ታጋዮች የአሁን ባለስልጣናት በአቶ ሃይለማርያም ዙሪያ ጥያቄ በማንሳት ላይ ቢሆኑን በባህር ዳር በተደረገው ጉባዬ ላይ ያላቸውን የበላይነት እንዲያሳዩ ከፓርቲያቸው ግፊት እንደተደረገባቸው ምንጮች ጠቁመዋል::የደቡብ ባለስልጣናት አብዛኛዎቹ በግል አቶ ሃይለማርያምን በደቡቡ ጉባዬ ወቅን አግኝተው ያናገሯቸው ሲሆን በአንድነት ራሳቸውን ችለው እንዲወጡ እና ከሕወሓት የበላይነት እንዲላቀቁ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው መክረዋል::ለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚረዳቸው ከወቅታዊ ጉዳዮች ጋር አስታከው ተወያይተውል::
በህወሓት ውስጥ ያለው ፍትጊያ በአባይ ወልዱ የበላይነት ያበቃ ነው ብለን መደምደም እንደማንችል እና መሃል ሰፋሪ ሆነው ወዳሸናፊው ለማዘንበል የግለኝነት ሚና እየተጫወቱ ያሉት ደብረጺሆን ደቡቦችን አመቻችቶ መያዝ አስፈላጊ እንደሆን ስለተረዱት በሃይለማርያም ድፍረት ጀርባ ሆነው ጨዋታውን ማጋጋል ተይይዘውታል::
ምንጮቹ በአከባቢያቸው ያለውን ሁኔታ በማየት እንዳሉት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በሃይለቃል ጭምር የሚደፋፈራቸው የደህንነት አማካሪው አለቃ ጸጋይ ከፓርቲው መነሳቱን ተከትሎ በደብረጺሆን ተዘዋዋሪ ቁጥጥር ስር መሆኑን ከጠ/ሚ ቢሮ የተገኙ መረጃዎች ሲጠቁሙ እንደት ከስልጣን እንደሚባረር ታቅዶለታል::
በስበሃት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋይ የነበሩት እና በአሁን ሰአት በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በማሰባሰብ በአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያነሱ እና ከሕወሓት ሰው ጠፍቶ ነው ወይ ከደቡብ ለትግሉ አስታውጾ ያላበረከቱ ሰዎች የሚመሩን ነገ ስጋት ሆኖብናል የሚሉ ታጋዮች ይህን ፕሮፓጋንዳ ይዘው በአቶ ስበሃት በኩል መሰለፋቸው በዚህ ሰሞን እንደገና ተረጋግቷል የተባለውን የወያኔ ክፍፍል እንደ አዲስ አግሎታል::
የሃይለማርያም ስልጣን መያዝ ያልጣማቸው አክራሪ ሕወሓቶች ከባህር ዳር መልስ አዲስ አበባ ውስጥ በስበሃት ነጋ ሰብሳቢነት  አርከበ እቁባይ ;ብርሃነ ገብረክርስቶስ ;አዲሳለም ባሌማ;አባዲ ዘሙ ;አለቃ ጸጋይ በርሄ; ቅዱሳን ነጋ; ሃይለኪሮስ እና ሌሎችም ተሰባሰበው በህወሃት ውስጥ ስለለው ሁኔታ እና ራሳችን በፈጠርናቸው ደቡቦች ልንዋጥ ነው የሚል እደምታ ያለው ውይይት አካሂደው ነበር:;
በአንድ ወገን ሆነው በአባይ ወልዱ መሪነት ብኣዴንን አስከትለው የስብሃትን ቡድን እየተዋጉ የሚገኙት አዜብ መስፍን እና ሌሎች..ሳሞራ የኑስን እንደመከታ አድርገው ቢተሙም ሳሞራ ሁኔታዎችን ከመከታተል ዉች ተሳትፎው የተልፈሰፈሰ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ወይም በስበሃት አጠራር የከተማ ጮሌዎች ወደ ከፍተኛ የስልጣን እርከን መምጣታቸው እያንገበገባቸው ሲሆን መለስ ዜናዊ ላልሰለጠኑ አናሳ ብሄሮች ሸጠን በማለት በሟቹ ላይ ከንፈር ነክሰው እየሞገቱ ሲሆን ይህም አልበቃ ብሎ ከድርጅታችንን መመሪያ እና ደንብ ዉጭ በተለያየ ቦታ የመለስን ምስል ማየት ሰለቸን በሚል ምስሉ እንዲነሳ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ምናልባት ሁኔታዎችን ያረግብ ይሆናል በሚል አቶ አዲሱ ምስሉ እንዲነሳ ቢናገሩም አቶ በረከት ጠላት እና ወዳጅን አጥርቶ ለመለየት በሚል እንዲቆይ አድርገዋል..
የስበሃት ቡድን ዉስጥ ውስጡን በትግራይ ለሚገኙ የሕወሓት የበታች አመራሮች እንዲሁም በሰራዊቱ ውስጥ ለሚገኙ የህወሓት መኮንኖች በሚያሰራጩት ፕሮፓጋንዳ በበረሃ ወንድም እና እህት ታጋዮችን ሰውተን ደማችንን አፍሠን የልጅነት ወዛችንን ጨርሰን ለዚህ የደረስነው ለደቡብ  ሰዎች እና ለከተማ ጮሌዎች ስልጣን ለመስጠት አይደለም አብረውን የታገሉ ኦሆዴዶች እንኳን ያላገኙትን ስልጣን ነው ያገኙት በማለት እና ለነገ የፖለቲካ ኪሳራ ያመጡብናል የሚያዘነብሉት ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ነው ለኛ አደጋ ስለሆኑ ከአሁኑ ልናሶግዳቸው ይገባል   በማለታቸው የወያኔ የውስጥ ቀውስ ግሎ ይገኛል::
በአሁን ሰኣት የደህንነት መዋቅሩን እና የጦር ሰራዊቱ ባለስልጣናት አጣብቂኝ ውስጥ ለማስገባት እየሰሩ የሚገኙት ደብረጺሆን አቶ ሃይለማርያም ያላቸውን ሃይል ተጠቅመው የወሳኝነት ሚና እንዲጫወቱ እያደፋፈሯቸው ሲሆን ከጎናቸው እንደሚሆኑ እና ምንም እንደማይመጣ እየመከሯቸው ሲሆን ለሁለት አመት ነው ያስቀመጥንህ የሚለውን የአለቃ ጸጋይ ዛቻ ከአሁን በኋላ ሰሚ የሌለው ጩሀት እንደሆነ መናገራቸውን ምንጮቹ አስቀምጠዋል::
የደቡብ ባለስልጣናት ማሰብ/ድፍረት መጀመር; የህወሃት ክፍፍል መጋል; የኦህዲድ አህያዊ ሞኝነት; የብኣዴን በዝምታ ነገሮችን መከታተል; የኢሕኣዴግ ባልተጠበቀ መልኩ ቀውስ ውስጥ መግባት እና ሌሎች ተደማምረው የወያኔን ውድቀት የሚያመላክቱ ሲሆን በሃገሪቷ ላይ የፖለቲካ ለውጥ እንዲኖር ለማየት የሚጓጓውን ህዝብ ስል ነቀል ለውጥ እንዲያደርግ መስራት ደሞ የእያንዳንዳችን ሃላፊነት ነው::

ሳዑዲና ዓባይ ምን አገናኛቸው?


ሳዑዲ ዓረቢያንና አፍሪካን (ዓባይን) የከፈለውን ቀይ ባህርን ስናስብ እንዴት ሳዑዲ ዓረቢያ ከዓባይ ጋር ልትያያዝ የምትችለው ብለን ላናስብ እንችላለን፡፡ ምንም ዓይነት መቀራረብም ሆነ ጉርብትና የላቸውም፡፡ የሰውየውን መልዕክት አዘል ንግግር ስናስብ ደግሞ ሳዑዲ ዓረቢያ ለግብፅና ለሱዳን ጠበቃ ለመቆም የተናገረችው ሊመስለን ይችላል፡፡ ይህንንም ከተለያዩ መላምቶችና ምክንያቶች ብለን ከምናስባቸው ጉዳዮች እየተነሳን ልናትት እንችላለን፡፡ ሆኖም ግን የዓባይ ውኃ ፖለቲካን ጠለቅ ብለን ስንመረምር የምናገኘው እውነት ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ በዓባይ ውኃ ፖለቲካ ውስጥ እጇን ለማስገባት መፈለጓን እንረዳለን፡፡ ይህንም ከኢትዮጵያው ባሮ (ጋምቤላ) በተከዜ አትባራ (ፖርት ሱዳን) እስከ ቶሽካ ፕሮጀክቶች እንደሚከተለው እንቃኛለን፡፡
ሳዑዲ ስታር የማንና ለማን ነው?
ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ጥግ ብቻውን አገር ሆኖ የሚታየው ትልቁ የሚሊኒየም አዳራሽ በአንድ ወቅት በውጭ በኩል ባለው ግድግዳው እጅግ ትልቅ የሆነ ማስታወቂያ ሰቅሎ ነበር፡፡ ስለ “ሳዑዲ ስታር አግሪካልቸራል ዴቭሎፕመንት” ኩባንያ የሚለፍፈው ያ ማስታወቂያ እጅግ አረንጓዴ የሆነ የሩዝ ማሳ ያሳያል፡፡ ባለቤቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሳዑዲው ዜጋ ሼክ መሐመድ አል አሙዲ ናቸው፡፡ በምዕራብ ጋምቤላ ወደ 10,000 ሔክታር መሬት እጅግ ርካሽ በሆነ የሊዝ ኪራይ (158 ብር በዓመት ለአንድ ሔክታር) የተረከበው ይህ ድርጅት እስከ 2020 ድረስ ወደ 2.5 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ ያፈስበታል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ዋና ምርቱ ሩዝ ሲሆን፣ በዋናነትም ለውጭ ገበያ የሚቀርብ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በምግብ ራሷን ያልቻለችው ኢትዮጵያ ለም መሬቶችን ለግዙፍ ኩባንያዎች እየሰጠች ሲሆን፣ በዋናነትም የውጭ ምንዛሪን ለማግኘት፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማምጣት እንደሆነ ይታመናል፡፡ ከዚህ አንፃር እሳቤው ባይከፋም ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ እንደሆነ ግን ሳንገልጽ አናልፍም፡፡
እንግዲህ ሳዑዲ ስታር የተባለው የሼክ አል አሙዲ ድርጅትም ምርቱን በዋናነት ለሳዑዲ ዓረቢያ ሊያቀርብ የታሰበ እንደሆነ የታመነና የተነገረ ነገር ነው፡፡ ባለሀብቱም ከሳዑዲ ንጉሣዊ ቤተሰቦች ጋር ባላቸው መቀራረብ ጋር ተነጋግረው የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነ በአንድ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲናገሩ መስማቴን አስታውሳለሁ፡፡ ይህ የሚያሳየን ሳዑዲ ዓረቢያ በአንድም በሌላም መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው የዓባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የራሷ የሆነ የጥቅም ፍላጎት አላት ማለት ነው፡፡ ጋምቤላ ውስጥ ያሉ ወንዞች የዓባይ ገባር መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡
ዋናው ጥያቄ የሚሆነው ይህ ጥቅም እያለ እንዴት የሳዑዲው ምክትል መከላከያ ሚኒስትር በእንደዚያ ዓይነት አካሄድ “ኢትዮጵያ የዓረቡን ዓላም ከመጉዳት ቦዝና አታውቅም” ሊሉ ቻሉ? እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ አገሮች የተሻለ ነው የሚሉትን ጥቅማቸውን እንደሚያሳድዱ ግልጽ ሊሆንልን ይገባል፡፡ ይህ ጥቅማቸውም ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባሕላዊ፣ ሃይማኖታዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ከዚህም በመነሳት ሚዛን ወደሚደፋው ጥቅማቸው ያጋድላሉ ማለት ነው፡፡ ሳዑዲ ዓረቢያም ያን እንዳደረገች የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ያምናል፡፡ ይህንም ለመረዳት በሳዑዲ ዓረቢያና በታችኞቹ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች (ግብፅና ሱዳን) መካከል ያለውን ከዓባይ ውኃ ጋር የተያያዘ ግንኙነት ማጤን ይገባል፡፡
የግብፁ ቶሽካ ፕሮጀክትና ሳዑዲ ዓረቢያ
አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞው የግብፅ መሪ ሆስኒ ሙባረክ እ.ኤ.አ በ1997 “New Nile Valley Project” “የአዲሱ የናይል ሸለቆ ፕሮጀክት” በሚል ግዙፍ የሆነውን የሰሐራ በረሃን የማልማት ዕቅድ ነድፈው ያም ዕቅድ ተግባራዊ እየሆነ ይገኛል፡፡ በተያዘለት ዕቅድ ከተከናወነ ይህ ፕሮጀክት እ.ኤ.አ በ2017 ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል የማጠናቀቂያ ጊዜው እስከ 2020 ድረስ መሆኑን በቅርብ ጊዜ ከወደ ግብፅ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዋናነት ሁለት ምዕራፎች ሲኖሩት አንደኛው በሰሜን ምሥራቅ ግብፅ የሚገኘው የአል-ሰላም ቦይ (canal) ፕሮጀክት ነው፡፡ እሱም ውኃ ከዓባይ ግርጌ በመጥለፍ ወደ ሲና በረሃ ማሻገር ነው፡፡
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ይህን በማድረግ ብዙ መቶ ሺሕ ሔክታር መሬት በማልማት 750 ሺሕ ግብፃውያንን ለማስፈር ያለመ ነው፡፡ ዋናውና ትልቁ ፕሮጀክት ግን የቶሽካ ፕሮጀክት ሲሆን፣ ይህም የደቡብ ምዕራብ ግብፅ በረሃን ለማልማት ያቀደ ፕሮጀከት ነው፡፡ በግብፃውያኑ ዘንድ ይህ ፕሮጀክት አሁን ባለው ሁኔታ እ.ኤ.አ 2020 ያልቃል ተብሎ ይታሰባል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት አዲስ ግብፅን በበረሃው ለመፍጠር ያቀደ ሲሆን፣ የተለያዩ በርካታ የውኃ ቦዮችንና የውኃ መምጠጫ ፓምፖዎችን በመገንባት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ይህን በማደረግ በረሃውን በማልማት ወደ ሦስት ሚሊዮን ግብፃውያንን የማስፈር ዕቅድ አላቸው፡፡ እንደ ግብፃውያኑ ከሆነ ይህ ፕሮጀክት ውኃውን የሚያገኘው በናይል ላይ ከተሠራው የአስዋን ግድብ ጀርባ ከሚገኘው የናስር ሐይቅ ነው፡፡ ግብፃውያኑ ይህን ሥራ የትኞቹንም የላይኛውን የተፋሰስ አገሮች ሳያናግሩ ሲሠሩት ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት ያሰቡ አልመሰሉም፡፡ እነሱ እ.ኤ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር የተፈራረሙት በሌሎቹ አገሮች ውድቅ የተደረገው “ስምምነት” ለራሳቸው በሰጡትና በመደቡት 55.5 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ራሽን/ኮታ መሠረት “ያላቸውን” ውኃ ለመጠቀም በማሰብ ነው፡፡
ሆኖም ግን ይህ ኮታ በሌሎቹ የላይኛው ተፋሰስ አገሮች ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው ግብፃውያኑ ውኃውን ከየት እንደሚያመጡት አሁንም ግልጽ አይደለም፡፡
እንግዲህ የሳዑዲ ዓረቢያ ሚና በዚህ ፕሮጀክት ላይ ምንድን ነው? ስንል ታላቅ ኢንቨስትመንትን እናገኛለን፡፡ የሳዑዲው ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ቢን አብዱላዚዝ አልሳዑድ “ዘ ኪንግደም አግሪካልቸራል ዴቨሎፕመንት” የተሰኘ ኩባንያ ባለቤት ሲሆኑ፣ ግብፅ ውስጥ በጥቅሉ ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ካፒታል ያንቀሳቅሳሉ፡፡ በቶሽካ ፕሮጀክት ደግሞ ከ10 ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ተረክበው የተለያዩ የግብርና ምርቶችን ለማምረት ከግብፅ የውኃና የመስኖ ልማት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመዋል፡፡ በየዓመቱም በሚሊዮኖች ለዚሁ የቶሽካ ፕሮጀክት አካል ለሆነው መሬት እንደሚያፈሱ ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ እዚህ ላይ ሊሰመርበት የሚገባው ጉዳይ ግብፅ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ያሉት የሳዑዲ ቤተሰብ የሆኑት የንጉሡ ዘመድና ልዑሉ እንጂ ከኢትዮጵያዊ እናት የተገኙት ሼክ አል አሙዲ አይደሉም፡፡ ይህም ማለት ለሳዑዲ ዓረቢያ ቤተ መንግሥትም ሆነ ለምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ የሚቀርቡት ሼክ አል አሙዲ ሳይሆኑ ልዑል አል ዋሊድ ቢን ጣላል ናቸው፡፡ ስለዚህ የምክትል መከላከያ ሚኒስትሩ ንግግር ከዚህ አንፃርም ሊታይ ይችላል፡፡
ዓባይ ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ከሚለው ፅሁፍ የተወሰደ
በዘሪሁን አበበ ይግዛው
ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው zerihun.yigzaw@graduateinstitute.ch ማግኘት ይቻላል፡፡a

Monday, March 25, 2013

የአማራ ክልል ተወላጆች የተባረሩት በህገወጥ መንገድ ስለገቡ ነው በማለት ባለስልጣናት ተናገሩ


መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ለዓመታት በቤንሻንጉል ክልል ይኖሩ የነበሩ  የአማራ ክልል ተወላጆች ፦“በሕገወጥ መንገድ ስለገቡ ወደመጡበት መመለስ አለባቸው” ተብለው ከይዞታቸው መፈናቀላቸውን አዲስ አድማስ ዘገበ።
በሚኖሩበት አካባቢ የእርሻ ቦታ በማጣታቸው የተሻለ ሥራ ለመፈለግ  ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ከአማራ ክልል ወደ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያሶ ወረዳ በመሄድ ኑራቸውን ሲመሩ የቆዩ  በርካታ ሰዎች በወረዳው ባለሥልጣናትና ፖሊሶች፤ ሰብአዊ መብታቸው ተጥሶ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ነው ለጋዜጣው የገለፁት።
ስለ ጉዳዬ የተጠየቁት የያሶ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ሻምበል ዳኛ በበኩላቸው ‹‹ከየትኛውም ክልል የሚመጡ ሰዎች ለወረዳው ካላሳወቁና ካላስፈቀዱ ሕገወጥ በመሆናቸው ወደ የመጡበት እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ደርሰናል›› ብለዋል።
ቅሬታ አቅራቢዎቹ እንደሚሉት ግን ፤ ካለፉት ስምንት ዓመታት ጀምሮ ይኖሩበት ከነበረው ክልል የመሸኛ ደብዳቤ አምጥተው በያሶ ወረዳና በየቀበሌዎቹ የነዋሪነት መታወቂያ ተሰጥቷቸው ነው ጎጆ ቀልሰው ሲኖሩ የቆዩት።
ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ በቅርቡ “ከሌላ ቦታ መጥታችሁ እየሠራችሁ የአካባቢውን ተወላጅ ሰነፍ አደረጋችሁት” በሚል ምክኒያት ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ሳይሰበስቡ ከክልሉ እንዲወጡ መደረጋቸውን ነዋሪዎቹ ይገልጻሉ፡፡
በያሶ ወረዳ ውስጥ የከተማ ነዋሪነትና የንግድ ፈቃድ በማውጣት ላለፉት ሰባት ዓመታት በሥራ ላይ መቆየታቸውን የጠቀሱ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ አንድ ግለሰብ፤ መታወቂያቸውና ቀደም ሲል ይኖሩበት ከነበረው ክልል ያመጡት መሸኛ ደብዳቤ ተወስዶ እንደተቀደደባቸው፤ እንዲሁም በከተማው የሠሩትን ቤት መላ እስኪያስይዙና ንብረታቸውን እስኪሰበስቡ ድረስ ጊዜ እንዲሰጣቸው ቢጠይቁም፤ ‹‹ቤትና ንብረቱ የሚገባው ለወረዳው ነው›› በሚል ወረዳውን ለቀው እንዲወጡ በመገደዳቸው በከተማው አቅራቢያ በሚገኝ ስፍራ ተደብቀው እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማይ ዞን በያሶ ወረዳ ውስጥ በሀሎ ትክሻ፣ በሆኒ፣በሊጐ፣ በባብርኮ፣ በሻብቲ፣ በድልድል፣ በቲኒጆ መጢ እና በመሰል ቀበሌዎች በግምት ከስድስት እስከ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ከአማራ ክልል የመጡ ሰዎች እንደሚገኙ  ግለሰቡ ገልጸዋል።
እንደማንኛውም ዜጋ ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ ሠርቶ የመኖር መብታቸውን መሠረት አድርገው ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የተሻለ ሥራ ፍለጋ መሄዳቸውንና ሕገወጥ ሰፈራ አለማድረጋቸውን የጠቀሱት ግለሰቡ፤ በደሉን እያደረሱባቸው ያሉት የወረዳው ባለሥልጣናት በመሆናቸው አቤት የሚሉበት ቦታ ማጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ቤተሰባቸውን እና ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ ከየቀበሌው እየተያዙ በያሶ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የታሠሩ በርካታ ሰዎች መኖራቸውንም አጋልጠዋል፡፡
“የክልሉ ነዋሪ ወዶንና ተቀብሎን በሰላም ነበር የምንኖረው” የሚሉት የሀሎ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሌላው አርሶ አደር በበኩላቸው፤የመኖሪያ ቤት ለመሥራት ሳይቀር የክልሉ ተወላጆች መሬት ቆርሰው እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል፡፡
ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ግን ጐጐታ በተባለ ቀበሌ ከአማራ ክልል የመጡ 43 ሰዎች እንዲሁም በሀሎ ሙከአርባ ቀበሌ የ25 ሰዎች መታወቂያ ተቀዳዶ ሲጣል መመልከታቸውን፣ ከተቀደዱት መታወቂያዎች አንዱ የእርሳቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደሩ እንደሚሉት የጉሙዝ ተወላጅ ከሆኑት ባለመሬቶች አንድ ገበሬ በጉልበቱ አርሶ 20 ኩንታል እህል ቢያመርት፤ 10ሩን ለባለመሬቱ እኩል አካፍሎ በስምምነት ሲኖሩ ነበር፡፡
“እስከአሁን በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከታሠሩት በርካታ ሰዎች በተጨማሪ በመኪና ተጭነው ነቀምትና ጊንቢ የተወሰዱት ሰዎች ጉዳይ አስጨንቆናል” ያሉት ሌላው ግለሰብ ለታሠሩ ወገኖቻቸው ስንቅ ሊያቀብሉ የሚሄዱትም በዚያው እየተያዙ እንደሚታሠሩ ተናግረዋል፡፡
ስንቅ ሊያቀብሉ በመሄዳቸው ሦስት ቀን ታስረው እንደተለቀቁ የተናገሩት እኚህ ግለሰብ “ከክልላችን መሸኛ ደብዳቤ አምጥተን ሕገ-ወጥ ናችሁ የምንባለው ፓስፖርት ማውጣት ነበረብን ወይ?” በማለት ይጠይቃሉ፡፡
‹‹በኖርንባቸው ሰባትና ስምንት ዓመታት ሠርተን ለመለወጥ ከማሰብ በስተቀር በነዋሪውም ሆነ በአካባቢው ላይ ያደረስነው አንዳችም ችግር የለም” የሚሉት እኚህ ግለሰብ ‹‹ውጡ ከተባልንም ንብረታችንን እስክንሰበስብ ጊዜ ይሰጠን፡፡ የአማራ ክልላዊ መንግሥትም ቦታ ይሰጠን›› ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የዜጐች ከቦታ ቦታ የመዘዋወር መብትን በተለከተ አስተያየታቸውን የሰቱት የሕግ ባለሞያ አቶ ግዛው ለገሠ የሕገ-መንግሥቱ አንቀፅ 32 “የመዘዋወር ነፃነት” በሚል ርእስ ስር ‹‹ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ አገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ፤ በመረጠው የአገሪቱ አካባቢ የመኖርና የመኖሪያ ቦታ የመመስረት እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከአገር የመውጣት መብት እንዳለው መደንገጉን ገልፀዋል፡፡
ኢሳት ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ስለተፈናቀሉ ሰዎች በባህርዳር የሚገኙ ተፈናቃዮችን አነጋግሮ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።

ሜድሮክ ወርቅ እና ሌሎችም የሼክ አላሙዲ ድርጅቶች የታክስ ጥያቄ ተነሳባቸው


መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ለመንግስት ቅርበት ያለው ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በኢትዮጵያ ውስጥ ከህወሀት ኩባንያ ከሆነው ኢፈርት በመቀጠል ሁለተኛ የሆነው የሼክ ሙሀመድ አላሙዲ ንብረት ሚድሮክ ኢትዮጵያ ለመንግስት መክፈል የነበረበትን ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ክፍያ አላስገባም።
ኩባንያው ከሚያስታድራቸው ሆቴሎች ጋር በተያያዘ 632 ሚሊዮን ብር እዳ እንዳለበት ጋዜጣው ዘግቧል።
ሚድሮክ ገንዘቡን በአንድ ወር ውስጥ እንዲያስገባ ትእዛዝ እንደደረሰው የኩባንያውን ምንጮች ዋቢ በማድረግ ጋዜጣው ዘግቧል።
በሚድሮክ ኢትዮጵያ ስር ያሉ ሚድሮክ ወርቅ፣ ናሽናል ማይኒንግ፣ ፋርማኪዩር ኩባንያ፣ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን እና ሚድሮክ የትምህርት እና ስልጠና ኢንስቲቲዩት ባለፉት 2 አመታት የትርፍ ግብር ሪፖርት ዜሮ ሆኖ መገኘቱም ተዘግቧል። 
 ጋዜጣው ያነጋገራቸው አንድ የድርጅቱ ሰራተኛ የተጠቀሱት ኩባንያዎች የትርፍ ግብር ዜሮ ነው መባሉ አስደንግጧቸዋል። ‹‹በአገሪቱ ውስጥ በመሥራት ላይ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ ድርጅቶች በትርፍ ግብር መልክ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ለመንግሥት ፈሰስ ሲያደርጉ እነዚህ ትላልቅ ኩባንያዎች አላተረፉም ሲባል ለመስማት ይከብዳል” በማለት ግለሰቡ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ጉዳዩን በማስመልከት ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ ወደ ሚድሮክ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ብናደርግም ሳይሳካልን ቀርቷል።
ሚድሮክ ኢትዮጵያ ለገደንቢ የወርቅ ማእድንን ከኢትዮጵያ መንግስት እጅግ በርካሽ ዋጋ ከ16 አመታት በፊት መግዛቱ ይታወቃል። ኩባንያው ለረጅም ጊዜ ከወርቅ ሽያጭ ትርፍ አላገኘሁም በማለት 2 በመቶ ብቻ የሮያሊቲ  ክፍያ እየከፈለ  ቆይቷል።
ከምርጫ 97 በሁዋላ ህዝቡ ስለ ወርቅ ማእድኑ ጥያቄ ማቅረቡን ተከትሎ ኩባንያው ከ98 እስከ 2004 ባሉት አመታት 772 ሚሊዮን ብር የትርፍ ግብር፣ 241 ሚሊዮን ብር የሮያሊቲ እና 4 ሚሊዮን ብር የሰራተኛ ግብር መክፈሉን አስታውቋል።
ክፍያው የተፈጸመው በአምስት አመታት ውስጥ ለተከናወነው የወርቅ ሽያጭ ብቻ ሲሆን ፣ ላለፉት 11 አመታት ለተካሄደው የወርቅ ሽያጭ ኩባንያው ግብር ያልከፈለበት ምክንያት እንቆቅልሽ እንደሆነ ቀጥሎአል። መንግስትም በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሲሰጥ አይሰማም።
ባለፉት 3 አመታት በአለም ላይ የታየው የወርቅ ዋጋ መናር ሚድሮክ ኢትዮጵያ ከወርቅ ሽያጭ ከፍተኛ ሀብት እንዲያጋብስ አድርጎታል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ወር በፊት የተሻለ የውጭ ምንዛሬ ያስገኙ ድርጅቶች በሚል 175 ኩባንያዎችን አወዳድሮ ፣ ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ 100 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ በማስገባት አንደኛ ሆኖ መሸለሙ ይታወሳል። በዚያው አመት ግን ድርጅቱ ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ ማከናወኑን አስታውቆ ነበር።
በአለፉት አስራ ስድስት አመታት ኩባንያው 4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ ወርቅ ለገባያ አቅርቧል። ይሁን እንጅ ኩባንያው እስካሁን ለመንግስት ያስገባው የትርፍ ግብር ገ ከ40 ሚሊዮን ዶላር አይበልጥም።
ሚድሮክ የሚያወጣው ወርቅ የሚጣራው ስዊዘርላንድ ውስጥ ነው።
ሼክ ሙሀመድ አላሙዲ የገዢው ፓርቲ ደጋፊ መሆናቸውን በይፋ እንደሚናገሩ ይታወቃል። ለድርጅቱም ከፍተና የሆነ ገንዘብ ይለግሳሉ። ሰሞኑን በተካሄደው የኢህአዴግ ጉባኤም የክብር እንግዳ ሆነው ተጋብዘዋል። አቶ በረከት ስምኦን የጻፉትን መጽሀፍ ያሳተሙላቸው ሼክ አላሙዲን ሲሆኑ ፣ አቶ በረከት ከምርጫ 97 በሁዋላ ታመው በነበረበት ወቅት ያሳከሙዋቸው ሼክ አላሙዲን መሆናቸውን በወቅቱ ተናግረው ነበር። በርካታ የቀድሞ የኢህአዴግ ባለስልጣናት  ስራቸውን እየለቀቁ ሚድሮክ ኢትዮጵያ መቀጠራቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት እስክንድር ነጋ የታሰረው በአሸባሪነቱ እንጅ በጋዜጠኝነቱ አይደለም ሲል ለአውሮፓ ህብረት መልስ ሰጠ


መጋቢት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-የኢህአዴግ አገዛዝ በእስር ላይ የሚገኘውን እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በተመለከተ  ከአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት ለቀረበት ጥያቄ በጽሁፍ በሰጠው መልስ ” እስክንድር ነጋ የጋዜጠኛነት ስራውን በመስራቱ ሳይሆን አሸባሪ ድርጅቶችን ሲረዳ በመገኘቱ ነው” የተፈረደበት ብሎአል።
እስክንድር ነጋ በህቡእ ከሚንቀሳቀሰው ግንቦት7 ከተባለው ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው፣  ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እየሰረጉ ለሚገቡ አሸባሪዎች ስልጠና ይሰጥ እንደነበርና ከኤርትራና ከግንቦት7 መሪዎችንም በስውር ያገኛቸው እንደነበር” ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባላት የሰጠው መልስ እጅግ አሳፋሪ ነው ሲል አንድ ታዋቂ ጋዜጠኛ አስተያየቱን አስፍሯል።
በቅርቡ 30 የሚሆኑ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ2012 የፔን አሜሪካን ሴንተር ፍሪደም ቱ ራይት ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል። የጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ባለቤት ሰርካለም ፋሲል ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ከአንድ አመት ለ8 ወራት ያክል ጊዜ መታሰሩዋ እና በእስር ቤትም የመጀመሪያውን ወንድ ልጃቸውን ናፍቆት እስክንድርን መውለዷ ይታወቃል።

ESAT Daily News Amsterdam 25 March 2013 Ethiopia


የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ ነው


ከመጋቢት 2 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርት ማቆም አድማ ላይ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሃብ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል እየተወሰዱ እንደሆነ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለፁ፡፡


የትምህርት ጥራት መጓደል፣ የአስተዳደራዊ ችግሮችና በምግብ ጥራት መጓደል ምክንያት ጥያቄያቸውን ለኮሌጁ አስተዳደር ቢያቀርቡም ምላሽ በማጣታቸው የትምህርት መቆም አድማ ለማድረግ የተገደዱት ቅድስት ስላሴ መንፈሰሳዊ ኮሌጅ ደቀመዛሙርት በርሀብ ተጎድተው ራሳቸውን በመሳት በመጀመራቸው በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል መወሰድ መጀመራቸውን ስምቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ተማሪዎች ተናግረዋል፡፡   

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጠኛም በቅድስት ስላሴና በየሆስፒታሎቹ ተዘዋውሮ እንደተመለከተው አባ እያሱ ሰብስቤ የተባሉ ተማሪ በየካቲት 12 ሆስፒታል እንዲሁም ደቀመዝሙር በኃይሉ ሰፊ ምኒሊክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን አረጋጧል፡፡ አመሻሹ ላይም ገ/እግዚያብሄር የተባሉ ተማሪ በአምቡላንስ ከኮሌጁ ተወስደዋል፡፡ ተማሪዎቹ በደል አድርሰውብናል ከሚሉዋቸው የኮሌጁ ሀላፊዎች ውስጥ መምህር ፍስሀፂዮን ደሞዝ አካዳሚክ ዲን እና መምህር ዘላለም ረድዔት የቀን ተማሪዎች አስተባባሪ በዋነኝነት ተጠቅሰዋል፡፡

ደረሰ ስለተባለው ችግር ለማጣራት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኢትዮጵያ ኦርቶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊ ብፁዕ አቡነ ህዝቅኤል በኮሌጁ ጉዳይ ስብሰባ ላይ እንደሆኑ ተናግረው የነበረ ቢሆንም ተሰብሳቢ ባለመሟላቱ ስባሰባው እንዳልተደረገ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Saturday, March 23, 2013

ESAT Meade Esat Ethiopia March 23 2013


የተመስገን ደሳለኝ ብዕር እየዶለዶመ ይሆን


ከሳምንት በፊት ተመስገን ደሳለኝን ሲያዳልጠው የምትል ጽሁፍ አስነብቤ ነበር፡፡የጽሁፉ አጠቃላይ ምልከታ ተመስገን በልዕልና ጋዜጣ ‹‹የተቃዋሚዎች ድክመትና ለስልጣኑ ያላቸው ርቀት››በማለት ላቀረበው ሰፋ ያለ ጽሁፍ በተለይም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን በተመለከተ ለሰነዘራቸው አንድ ጫፍ ለረገጡ አስተያየቶች በበኩሌ የማውቃቸው እውነታዎች በተመስገን እንደተባለው አለመሆኑን ለማሳየት ነበር፡፡ከሳምንት በኋላ ደግሞ ለንባብ የበቃችው ልዕልና ጋዜጣ እኔ በፌስ ቡክ የለቀቅኩትን ጽሁፍ የፓርቲው ማስተባበያ በማደረግ ‹‹አንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ቡድኑን አስመልክቶ የወጣውን መግለጫ አስተባበለ፡፡››በማለት ለንባብ አብቅቶታል፡፡
እኔ በራሴ ስምና የግሌ አስተያየት መሆኑን ደጋግሜ የገለጽኩበት ጽሁፍ እንዴት ተደርጎ የአንድነት ማስተባበያ ተደርጎ ሊገለጽ እንደሚችል የሚያውቁት ከመነሻው ፓርቲውን ለመተቸት ብዕራቸውን ከወረቀት ያገናኙ ብቻ ናቸው፡፡የተቃዋሚዎች ውስጣዊና ውጫዊ ችግር ተፈትቶ ለስልጣን የሚበቁበት ዘመን እንዲመጣ እመኛለሁ በማለት እንደ አንድ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ ስትራቴጂስት ስልት ሲቀይስና ሲመክር የነበረ ግለሰብ እንዴት ፓርቲው ያልሰጠውን ማስተባበያ ፓርቲው እንደሰጠ በማድረግ አንባቢን ውሸት ይመግባል፡፡በዚህስ በውሸት ከምንከሳቸው የገዢው ፓርቲ የፕሮፓጋንዳ ማሰራጫዎች በምን እንለያለን ?
በኒውስ ሌተርና በኦን ላይን ሚዲያ አማካኝነት እንዲሰራጭ በመደረጉ ሊሆን ይችላል፡፡ለማንኛውም ይህም ቢሆን ፓርቲው ማስተባበያ እንደሰጠ ተደርጎ ለመውሰድ የሚያስደፍር አይደለም፡፡ምክንያቶቼን ልዘርዝር
1)ጽሁፌ የሚጀምረው ለተመስገን ያለኝን አድናቆት በመግለጽ ነው፡፡ለእርሱ ያለኝን ወዳጃዊ ስሜት ለማንጸባረቅም በቁልምጫ ‹‹ተሜ››በማለት ስሙን አንስቼያለሁ፡፡እንዴት ነው ወዳጆቼ ፓርቲ ማስተባበያ በቁልምጫ እየጠራ ሲያወጣ አልታያችሁም ?
2)ፓርቲው ለጽሁፉ ምላሽ እንዲሰጥ በመሻት ከአመራሮቹ ለአንዱ በመደወል ጆሮዬን ጭው ያደረገ ምላሽ እንደሰጠኝ ገልጬ ነበር፡፡እንዴት ነው የፓርቲው ጆሮ ጭው የሚለው?
3)በጽሁፌ ደጋግሜ ፓርቲው እያልኩኝ ጠቅሻለሁ ፡፡ማስተባበያው በፓርቲው እውቅና የወጣ ቢሆን ኖሮ ‹‹ፓርቲያችን››በሚሉ ቃላቶች የሚደገፍ ይሆን ነበር፡፡አይመስላችሁም ?
4)የጽሁፌ ማሳረጊያ‹‹በግሌ ተሜ የመግለጫውን ሙሉ ቃል ሳያነብ ለትችት መቻኮሉ አግራሞት ጭሮብኛል፡፡››የሚል አረፍተ ነገርን ሰርቷል፡፡በግሌ ማለት ምን ማለት ይሆን ;እረ ኤቲክሱን ምን በላው ?
5)በአንድነት ልሳን ፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ላይ ስሰራ እንደ መቆየቴ በፍኖተ ነጻነትና በፓርቲው መካከል ያለውን ቁርኝት እንዳውቅ አድርጎኛል፡፡ፓርቲው ጋዜጣው በፓርቲው አመለካከት ብቻ እንዳይታጠርና የሌሎች ሀሳብ እንዳይታፈን በማሰብ ፍኖተ ነጻነት የሁሉም ልሳን እንድትሆን በወሰደው ውሳኔ መሰረት ኢህአዴጋውያን ሳይቀሩ ሀሳብን በሀሳብ ለመሞገት ቢነሱ በሩን ክፍት በማድረግ የማገልገል የሞራል ዝግጁነት ነበረው፡፡ፍጹም የስራ ነጻነት የነበራቸው የጋዜጣው አዘጋጆች(ዋና አዘጋጁ ነብዩ ሀይሉ የፓርቲው አባል አልነበረም) ሞያው ለሚጠይቀው ዲሲፕሊን በመገዛት መንፈስ ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ገዢው ፓርቲን የተቹ የባልደረቦቼ ብዕሮች በተቃዋሚው ጎራ (አንድነትን)ጨምሮ ለተመለከቷቸው ስህተቶች አልራሩም፡፡ይህም ጋዜጣይቱን ከፓርቲ ልሳንነት ባሻገር የሁሉም አድርጓት በሳምንት ሁለት ጊዜ እስከ መታተም በመድረስ የአንባቢዎቿን ቁጥር 20.000 አድርሳ ነበር፡፡በዚህ አጋጣሚ የእኛ ጋዜጣ በመሆኗ እኛ ብቻ ልንናገርባት ይገባል ያላሉትን የፓርቲውን አመራሮችና አባለት ላመስግን፡፡እናንተ ለስልጣን ብትበቁ ኢቴቪ ምን አይነት መልክ ሊኖረው እንደሚችል በፍኖተ ነጻነት አሳይታችሁኛልና ምስጋና ይሁንላችሁ፡፡
6)ከጽሁፉ ስር ዳዊት ሰለሞን የሚለው ስሜ መስፈሩ ምን ያመለክታል ይህ ጥያቄ ነጩን ነጭ የማለት ድፍረት ለሌለው ብዕር መጠየቅ አንድነት እንዴት ዳዊት ይሆናል፡ልዕልና የእኔን ጽሁፍ የፓርቲው በማድረግ ካወጣች በኋላ አንድ ወዳጄ ደውሎ እንደምን ዋሉ ክቡር ሊቀምነበር ብሎኛል፡፡እንዴት ነው ዶ/ር ነጋሶ ላይ መፈንቅለ ስልጣን አደረግኩ እንዴ ?
አስቂኙ የማስተባበያ ማስተባበያ
አንድነት ማስተባበያ አወጣ በማለት ዜና የሰራችው ልዕልና ጋዜጣ ሳትነግረን ለማስተባበያው የራሷን ማስተባበያ አውጥታለች፡፡አንድነት የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን አከበረ ያለው የተመስገን ጽሁፍ የመረጃ ምክነት እንዳለበት መጥቀሴ አይዘነጋም፡፡አሁን ልዕልና ያኔ ተሜ ያልጠቀሰውን መረጃ በማውጣት ፓርቲው በ2003 ቀኑን ማክበሩን ፍትህ ጋዜጣ ዘግባ ነበር ብላናለች፡፡አስቂኙ ነገር ፍትህ ዘግባ ነበር መባሉ ነው፡፡በቃ ፍትህ የዘገበችው ሁሉ እውነት ነው ማለት ነው፡ወይ ልዕልና;አሁንም መረጃው ስስ ነው፡፡አንድነት የባህል ቀንን እንጂ የብሄር ብሄረሰቦችን ቀን በኢህአዴግ ቀረርቶ አክብሮ አያውቅም፡፡ለአንድነት የብሄር ብሄረሰቦች ጉዳይ በዕለቱ ከመጨፈር ብዙ ይርቃል፡፡ገዢው ፓርቲ የብሄር ጉዳይን የያዘበት መንገድ ለኢትዮጵያ የማይበጅ መሆኑን በማመኑን አጥብቆ ይታገለዋል፡፡ልዕልና ሆይ ይህን ማወቅ ከፈለግሽ የፓርቲውን ፕሮግራም ለማንበብ ሞክሪ፡፡
ስለ ብሄራዊ ቡድኑ የጠቀስኩት ነገርም ቅንነት በጎደለው መልኩ ተንሸዋርሮ ቀርቧል፡፡አንድነት መግለጫውን ማውጣቱን አስተባበለ በማለት ልዕልና አቧራ ለማስነሳት የሞከረች ቢሆንም በወቅቱ እኔ ያልኩት ተመስገን የመግለጫውን መንፈስ አልተገነዘበውም ፡፡የመልእክቱን አንኳር ነጥብ ስቶታል እንጂ መግለጫው አልወጣም አላልኩም ፡፡በአንድ ቋንቋ እየጻፍን ይህን ያህል የባቢሎን ግንብ ሰራተኞች የመሰልንበት መንገድ ምስጢር ሆኖብኛል፡፡እናም ነገሬን ልስፈር የሳምንቱም ጽሁፍ ሆነ የአሁኑ የእኔ (የዳዊት)እንጂ የፓርቲው አይደለም፡፡ሳላውቀው የሳምንቱን ጽሁፍ በአንድነት ማህተም አውጥቼው ከነበረም ይነገረኝና ሂሴን ላዋጥ፡፡

Friday, March 22, 2013

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም



ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል
hidassie dam


“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።
ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።
49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።
መንግስት በተለያየ መድረክ በተደጋጋሚ ፕሮጀክቱ “በአገር ውስጥ ባለሙያ፣ በአገር ውስጥ ሃብት፣ የሚከናወን የህዳሴ መገለጫ ነው” በሚል ብሄራዊ መነቃቃት የተፈጠረበት የአቶ መለስ ማስታወሻ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ስለ አክሲዮን ድርሻና አክሲዮን ስለገዙ አገራት እስካሁን የተናገረው የለም።
ግድቡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ መገለጹ ይታወሳል። የአባይ ግድብ ከሱዳን ድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቤኒሻንጉል ክልል እንደሚገኝ መንግስት የግድቡን ሥራ ይፋ ሲያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ ፋና በዛሬው እለት ባሰራጨው ዜና “የወንዙን ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ እየተሰራ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፥ “ወንዙ ይሄድበት የነበረውን ቦታ 1780 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ የመካከለኛው ክፍል የሚያርፍበት እንደሚሆንም” የፕሮጀክቱ ሥራአስኪያጅ  ኢንጅነር ስመኘው መናገራቸውን ጠቅሷል። “አቅጣጫውን የማስቀየሩ ስራ ከመጭው ክረምት በፊት” ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መሃንዲሱ ጠቅሰው፥ በቅርቡም ዕውን ይሆናል ብለዋል። ግድቡ ግንባታው የተጀመረበት 1ኛ ዓመት በዓልም ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ፥ እንዲሁም መጋቢት 24 ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ስፍራ በተለያዩ ስነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና  ‘መለስ ቃልህ ይከበራል፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እውን ይሆናል’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል” በማለት የዜናው ዘገባ ገልጾዋል።
http://www.goolgule.com/abay-dam-not-ethiopias/

ባሁኑ ሰዓት በአማራው ወገናችን ላይ እየደረሰ ያለው አማራን የማጥፋት ሴራ፤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚካሄደው ተግባር ዋናው አካል ነው።


በአሁኑ ሰዓት አማርኛ ተናጋሪው ወገናችን ላይ መለኪያ የሌለው ግፍ እየተፈፀመበት ነው። ይህ ግፍ፤ የአማራውን ወገናችን ለማጥፋት ከሚደረግ ወንጀል ሌላ፤ መገንዘቢያ ቀመር የለውም። የዛሬው እስከመቼ ይኼን ጉዳይ ይመለከታል። 

በሥልጣን ላይ ያለው ዘውገኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ አስተዳደሩ በዘውግ ላይ የተመሠረት ስለሆነ፤ አንደኛውን አስበልጦ ሌላውን አሳንሶ መመልከቱና በዚያ ፈለጥ ማስተዳደሩ ምንነቱ ነው። አልፎ ተርፎ ግን፤ አንድን ወገን ለይቶ፤ በዚህ ወገን ላይ የተለዬና ጭካኔ የተሞላበት በደል መፈፀም፤ መሠረታዊ ተልዕኮውን እንድንመረምር ያስገድደናል። 

ዘውገኛው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ለምን አማራውን ለይቶ ማጥቃት ፈለገ? ለምን? የአማራው ወገን የፖለቲካ ምኅዳሩ ለኔ በተለዬ ተዘጋብኝ ብሎ አልጮኸም። በአስተዳደር የሚደርስበትን በደል ለማሰማት እጁን አላወጣም። የሚወክለውና ጥብቅና የቆመለት፤ ከአምባገነኑም ክፍል ይሁን ከዚያ ውጪ የራሱ የሆነ የፖለቲካ ፓርቲ የለውም። ታዲያ ለምን ጥቃት ተፈረደበት? 

ከኛ በኩል የሚታየን እንዲህ ነው። አማራው፤ ኢትዮጵያ ሀገሬ ናት ብሎ፤ በሀገሪቱ ውስጥ በየትም ቦታ ሠፍሯል። በደርግ ጊዜና በዘውገኛው አምባገነን ጊዜ ደግሞ፤ አማራ የሆኑ ወገኖቻችን፤ የሚኖሩበት ቦታ መሽንሸኑና መራቆቱ ስለበዛበት፤ ከተወለዱበት ክልል ውጪ፤ በጠፍ መሬቶች፤ መሬቱን አልምተውና ከብት አርብተው ይኖራሉ። ባሁኑ ሰዓት፤ ከያሉበት እየተለቀሙ፣ ሀብታቸው እየተዘረፈ፤ አንዳንዶቹ እየታሰሩ፤ ሌሎች ደግሞ እየተገደሉ፤ ድራሻቸው እንዲጠፋ፤ በሁሉም የዘውገኛው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት መዋቅሮች አየተዋከቡ ነው። ይህ በአማራው ወገናችን በተለይ የሚፈፀም ተግባር ነው። ይኼም የሚደረገው ኢትዮጵያዊ ነን ብለው በማመናቸውና ኢትዮጵያ የኔም ነች ብለው በመቆማቸው ነው። ታዲያ እኛ ምን እንላለን? 

ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ የዘውገኛውን አምባገነን የትግሬዎች ግንባር መንግሥት እቃወማለሁ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የራሱን መንግሥት እንዲያቋቁም እታገላለሁና በኢትዮጵያዊነቴ ቆሜያለሁ ያልን በሙሉ፤ ሰዓቱ አሁን ነው። ይህ በደል የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን በደል ነው። ይኼን በደል ተቃውሞ መነሳት፤ ለኢትዮጵያዊነት መነሳት ነው። ለዚህ ጉዳይ ጀሮ ዳባ ልበስ ብሎ ፊትን ማዞር፤ ኢትዮጵያዊነትን መካድ ነው። ለዚህ ያልቆምን ለምን? ከዚህስ የበለጠ ኢትዮጵያዊነት ከየት ሊመጣ? አማራው አልቆ በሌሎቻችን እስኪመጡብን ድረስ ልንጠብቅ ነው ወይ? 

የአምባገነኖች ሂደት ግልፅ ነው። ፋሽስቱ ሞሶሎኒ፤ በአይሁዳዊያን ተደግፎ ቆሞ፤ መጀመሪያ አጠቃቸው፤ ቀጥሎ ደግሞ የራሱን የልጁን ባል ረሸነው። ይኼ ዘውገኛ አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ መንግሥት ደግሞ ዛሬ አማራዎች ላይ ቢዘምት፤ ነገ ተከታይ ተጠቂ ፈላጊ መሆኑን አንዘንጋ። ሌሎቻችን ቀርቶ የትግራይም ወገናችን ተራውን ጠባቂ ነው። ልብ በሉ፤ በዚህ የአማራውን ወገናችንን የማጥፋት ዘመቻው ጎን ለጎን፤ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገናችንን ማጥቅት ይዟል። ለምን? የፖለቲካ ምኅዳሩ ጠበበብን ብለው አልተነሱም። በቀላሉ ሊመለሱ የሚገባቸውና የሚችሉ ጥያቄዎቻቸውን በአግባቡ አቀረቡ። የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች፤ በዘውግ አልተነሱም። ጥያቄያቸው ተገቢና ቀላል ነበር። ነገር ግን ሁሉን ኢትዮጵያዊያን የሚመለከት ጥያቄ ነበር። መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይግባ ነው። ይኼ ግን ኢትዮጵያዊያን በሙሉ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሒዶ ቤተክርስትያን ተከታዮችም ያነሱት ጥያቄ ነው። በዚህም ኢትዮጵያዊያንን በያሉበት በኢትዮጵያዊነት አሰባሰቡ። ይኼን ኢትዮጵያዊነት የሚጠላው ዘውገኛ አምባገነን ዘመተባቸው። 

እንግዲህ የምንመለከተው፤ የኢትዮጵያን ዳር ደንበር ቆርሶ ለባዕድ መስጠት፣ ለሙን መሬት ባለቤቶቹን ነዋሪዋች አባሮ ለውጭ ከበርቴ አልምቶ ወደ ሀገሩ ምርቱን እንዲወስድ መስጠት፣ የተማረውን ኢትዮጵያዊ በሙሉ ማባረርና ኢትዮጵያዊ የሆነን በሙሉ ማጥቃት ትርጉሙ፤ ኢትዮጵያን ከመጥላትና ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ከማጥፋት ዕቅድ የመነጨ ነው። እናም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የፈለገ ሁሉ ይኼን ለመቋቋም መነሳት አለበት። 

ባሁን ሰዓት በአማራው ወገናችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የወገን ማጥፋት በደል ተቃውሞ መነሳት ለኢትዮጵያዊነት መቆም ነው። ይኼን አለማድረግ ደግሞ በተቃራኒው መሆን ነው። ስለዚህ፤ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ፤ በያለንበት የፖለቲካ ፓርቲ፣ የኅብረተሰብ ድርጅቶችና በግለሰብ፤ የአማራውን መጨፍጨፍ በመቃወም መነሳት አለብን። ይህ ጉዳይ የተጨፍጫፊው ወገናችን ጉዳይ ብቻ አይደለም። ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ፤ ጉዳዩ ነው።
 

 ድል ለ ኢትዮጵያ ህዝብ !!!

ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ ሚንስትሮች ም/ቤት


መጋቢት 18/2005 ዓ.ም የእነ እስክንድር ነጋ ይግባኝ ለመጨረሻ ጊዜ ተብሎ ተቀጥሯል፡፡ በዚህ መዝገብ የተከሰሱት የህሊና እስረኞች ይግባኝ ከጠየቁ አምስት ወር አልፏቸዋል፡፡
ለምን? …በአዲስ መስመር እንነጋገርበት፡፡
የይግባኙን ውሳኔ ያዘገየው የፖለቲካ ተንታኝ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ የተከሰሰው በሀሰት ስለሆነ ነው፡፡ በእርግጥ ይህንን ያልኩት እኔ አይደለሁም፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመሀል ዳኛ የሆነው አቶ አማረ አሞኘ ነው፡፡ ባለፈው ወር ዳኛው አቃቢ ህጎቹን ሰበሰበና እንዲህ አላቸው፡-
‹‹ይህን ሰው አሻባሪ ነው ብላችሁ ስትከሱት ያቀረባችሁት ማሰረጃ በተለያየ ጊዜ የፃፈውን ፅሆፎች፣ ቃለ-መጠይቆች እና በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ መድርክ ላይ ተናገረው ያላችሁትን ብቻ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ ፅሁፉና ንግግሩ ያስከተለው አደጋ አልተገለፀም፤ ወይም ምንም አይነት አደጋ አላስከተለም ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ተከሳሹ ላይ ቅጣት ለመጣል አያስችልም፡፡ ስለዚህም ሌላ ጥፋተኝነቱን የሚያረጋግጥ ማሰራጃ ካላችሁ አቅርቡ? አሊያም በሚቀጥለው ቀጠሮ ሲቀርብ በነፃ እለቀዋለሁ፡፡››
አቃቢ ህጎቹ ምንም ማስረጃ አልነበራቸውምና በደፈናው ‹‹ሰውየው አሸባሪ ስለሆነ ዝም ብለህ፤ ይግባኙን ውድቅ አድርግና የከፍተኛው ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አፅናበት›› የሚል ይዘት ያለው ተመሳሳይ አቋም አንፀባረቁ፡፡ ዳኛው ምን አይነት መንፈሳዊ ኃይል ተጭኖበት እንደ ሆነ እንጃ! ‹‹በፍፁም ከህግ ውጪ አልሰራም፤ ህሊና አለኝ›› ብሎ ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ ይላል፡፡
ይህን ጊዜም ነገሩ ቦግ ያደረገው አንድ አቃቢ ህግ
‹‹አንተ እስክንድርን እለቃለሁ የምትለው ያገርህ ልጅ ጎንደሬ ስለሆነ ነው!››
ይለዋል ቁጣ በተቀላቀለበት ድምፅ፡፡ ዳኛ አማረም ይበልጥ ተናዶ
‹‹እኔ እሰከ ዛሬ ድረስ ያገለገልኩት ሀገሬን ኢትዮጵያ እንጂ የትውልድ መንደሬን አይደለለም፡፡ ደግሞም ዘረኝነት የለብኝም›› ሲል መለሰለት፡፡
በእንዲህ አይነት ሁኔቴ መዋዘገቡ በመካረሩ መግባባት አልቻሉምና ጉዳዩ ሚንስትሮች ምክር ቤት ደረሰ፡፡ በሚንስትሮች ም/ቤትም ስብሰባውን የመራው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ደመቀ መኮንን ሲሆን፣ ዳኛውም አብሮ ቀርቧል፡፡ አቶ ደመቀ መጀመሪያ ዳኛው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠየቀ፡፡ ዳኛውም ስለክሱ አጠር አድርጎ ካብራራ በኋላ እንዲህ ሲል ደመደመ፡-
‹‹እስክንድር ነጋን ‹አሸባሪ› ብሎ ለመፍረድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ ስላልቀረበ በሚቀጥለው ቀጠሮ በነፃ አሰናብተዋለሁ፤ እንዲህ ማድረግ አትችልም የምትሉኝ ከሆነ ግን ክቡራን ሚንስትሮች በዕለቱ በችሎት ለመሰየም ፍቃደኛ አለመሆኔን በትህትና ትረዱኛላችሁ ብዬ አስባለሁ!››
ከዚህ በኋላ ሚኒስትሮቹ መወያየት ጀመሩ፡፡ ተከራከሩ፤ በመጨረሻም አቶ ደመቀ እንዲህ አለ፡-
‹‹እኔም ከአቶ አማረ ጋር እስማማለሁ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰውዬ /እስክንድር/ የተነሳ ከፍተኛ አለም አቀፍ ጫና እየደረሰብን ነው፡፡ ስለዚህም ብንፈታው ተጠቃሚዎቹ እኛው ነን ብዬ አስባለሁ፡፡››
አንድ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹በመሰረተ ሃሳቡ ላይ እስማማለሁ፡፡ ነገር ግን እስከዛሬ አስረነው ‹ነፃ ነህ› ብለን ብንለቀው የፖለቲካ ኪሳራ ስልሚያስከትልብን፣ ከፍርዱ ላይ ቅንስናሽ አድርገን ይቅርታ ጠይቆ እንዲወጣ ብናደርግ የተሻለ ነው፡፡››
ሌላ ሚኒስትር ቀጠለ፡-
‹‹እስክንድርን እኔ አውቀዋለሁ፤ የአሜሪካን ሀገር መኖሪያ ፍቃድ እና ብዙ ሀብት እያለው እዚህ ነገር ውስጥ የገባ ሰው ነው፡፡ እናም በፍፁም ይቅርታ ለመጠየቅ ፍቃደኛ አይሆንም››
ሌላኛው ሚንስትር ቀጠለ፡-
‹‹ኧረ ለመሆኑ መለስ አለም አቀፍ ጫና እንደሚያስከትል እያወቀ ለፓርቲያችን ጥቅም ብሎ የገባበትን ጉዳይ፣ ዛሬ እርሱ አልፏል ብለን ጫና ይምንፈራበት ምክንያት ከየት የመጣ ነው? በቃ! መለስ አደገኛ ሰው ነው ብሎ አስሮቷል፡፡ አለቃ! እዛው ይበስብስ!››
የሚንስትሮች ምክር ቤትም ቢዚህ ጉዳይ ላይ መስማማት ሳይችል በመቅረቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዘዳንት አቶ ተገኔ ቀርቦ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ቀጠሮ ይዘው ተለያዩ፡፡
…በእርግጥ ከአቶ ተገኔ ማብራሪያ በኋላ የሚኒስትሮች ም/ቤት ምን አይነት አቋም ላይ እንደደረሰ ለማወቅ ያደረኩት ጥረት ሊሳካ አልቻለም፡፡ መረጃውንም እስከ ዛሬ ያቆየሁት ለዚህ ነበር፡፡ አሁን ግን የቀጠሮ ቀን ሰለደረሰ ልነግራችሁ ተገደድኩ፡፡
እናም የፊታችን ረዕቡ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚከተሉት አራት ነገሮች አንዱን እናያለን ብዬ አስባለሁ፡፡
1. የሚንስትሮች ም/ቤት ጫናው ስለከበደው በነፃ ይለቀዋል፣
2. መለስ እያወቀ የገባበትን ጫና አንፈራም! (ራዕዩ እናስቀጥላለን እንደማለት ነው) በማለት የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሳኔ ያፀናሉ፣
3. ከተፈረደበት 18 ዓመት ላይ ቅንስናሽ አድርገው፣ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወደ ማግባባቱ ይሄዳሉ፣
4. ዳኛው አሞኘ እንደፎከረው ከችሎቱ ይቀርና አሁንም ‹‹የመጨረሻ›› ቀጠሮ ይሰጣል፡፡
የሆነ ሆኖ እንዲህ የሚል አንድ እውነት ‹‹በመሪዎቻችን›› ግንባር ላይ ተቸክችኳል፡፡ ‹‹ሲቪሉ ጀግና እስክንድር ነጋ እያርበደበደው ነው!››
አዎ! እኔም እላለሁ፣ የእስክንድር እና መሰሎቹ የግፍ እስር አርብድብዶ ብቻ አይተዋችሁም!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ! ውድቀት ለአምባገነኖች!!