Friday, July 5, 2013

በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲ እጣ ፈንታ አልታወቀም

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የግብጽ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፕሬዚዳንቱ በተቃዋሚዎች የቀረበውን ጥያቄ  በ48 ሰአታት ውስጥ እንዲመልሱ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የግብጽ ቀጣይ እጣ ፋንታ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም።
ፕሬዚዳንት ሙርሲ ህገ መንግስቱን ለማስከበር የህይወት መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ሲገልጹ፣ የመከላከያ ባላስልጣናት ደግሞ የራሳቸውን መፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል። የመከላከያ አዛዦች ፍላጎት በውል ባልታወቀበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ ጥምር መንግስት ለማቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል።
በፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል።
ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣን ከያዙ በሁዋላ የራሳቸውን ፓርቲ ሰዎች የሚጠቅሙ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባለፈ ለአገሪቱ ህዝብ የሰሩለት የለም በሚል ወቀሳ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ደግሞ ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት ውስጥ ለውጥ እንዲያመጡ አይጠበቅባቸውም በማለት ይከራከራሉ።

No comments:

Post a Comment