Saturday, July 20, 2013

ከቀዶ ጥገና በውሃላ 7 ዓመት ያልነቃው ኢትዮጵያዊው ህጻን መሃመድ አብድላዚዝ


65245_600119153351923_1342592408_n
ኢትዮጵያዊው ህጸኑ መሃመድ አብድላዚዝ የመጨረሻ ቀዶ ጥገና ለማድረግ ወላጆቹ ይዘውት ሳውድአረቢያ ታዋቂው ሆስፒታል
ሱለይማን ፈቂ በቀጠሮ ቀን ቀዶ ጥገና ለማድረግ ገብቱዋል
የህጻኑ ህመም በአፍንጫው ውስጥ ሲወለድም ትርፍ ስጋ በቅሎበት ስለነበር መተንፈስ አስቸግሮታል
ታደያ ይህንን ስጋ ነው ለማከም የመጣው ከሰዓታት ቆይታ ቡሃላ ከቀዶ ጥገና
ክፍል ወጣ ወላጆች የልጃቸው አለመንቃት ቢጠባበቁም የውሃ ሽታ ሆነ ዶክተሮች በተስፋ ይነቃል ቢሉም
1ቀን አለፈ አስደንጋጭ ክስተት ሆነ መሃመድ ግን አልነቃም ዶክተሮች ለወላጆች ልጃቹ ማደንዘዣ በዝቶበት
በዶክተሩ ስህተት አለመንቃቱንና በዚህ ምክንያት ዶክተሩ ከስራው ተቀንሶ ወደ ሃገሩ መባረሩን እና
በዚህም ምክንያት ልጁ እስኪነቃ ድረስ ክፍል ተሰጥቶት እንዲታከም ተነገራቸው
ቢሆንም ዛሬ ነገ ሲባል ቀናቶች አለፉ መሃመድ ግን አልነቃም እንዲህ እያለ የ3ዓመቱ ህጻን መሃመድ ባስገራሚ ሁኔታ
7 ዓመት አስቆጠረ አሁን 10 አመት ልጅ እዛው ክፍል ከአልጋው ሳየነሳ አደገ የሚተነፍሰው ኦክስጂን ተገጥሞለት በተለያዩ
መሳሪያዎች በመታገዝ ነው ታድያ መሃመድ እስካሁን አልነቃም እንደተኛ ነው ሱብሃን ይደንቃል ያላህ ስራ
ነገሩን በትግስት የሚጠባበቁት ወላጆች ጉዳዩን ለሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚንስትር በማሳወቅ እና በመክሰስ ሚንስትሩ
ሆስፒታል ድረስ በመምጣት ጎብኝተውታል በዚህ በወላጆች ድርጊት የተደናገጡት የሆስፒታሉ ባለ ንብረቶች
ለጊዜውም ቢሆን የልጁን እንክብካቤ ቢቀንሱም በዚህ ሁኔታ ከሞተ ግን ከተጠያቂነት መዳን ብቻ ሳይሆን ይህ ታዋቂ ሆስፒታል
ሊዘጋ ስለሚችል እንክብካቤያቸውን ቀጥለዋል እናት አባት በሰው ሀገር ለ7 ዓመት ሆስፒታል ከልጃቸው አጠገብ በመገኘት የልጃቸውን መንቃት ይጠባበቃሉ
ወላጆች ነገሩን ጅዳ ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤንባሲ በተደጋጋሚ ቢያመለክትም የዜግነታቸውን እንኵአን መልስ የሚሰጣቸውን
አላገኙም ባንድ ወቅት ኤንባሲ ሄደው እያለቀሱ መጮህ ጀመሩ በወቅቱ አምባሳደር መርዋንን አግኝተው
ሆስፒታል አምጥተውት አምባሳደሩ ልጁን ከጎበኘው ክዛም ከሆስፒታሉ ማናጀሮች ጋር አውርተው ከጨረሱ ቡሃላ ይባስ ብለው
ተሳድበው እንዴት ለኛ ሳትነግሩ ትከሳላቹ በማለት አሹፈውባቸው ጥለው ወጡ ታዲያ እነዚህ ወላጆች የት ይሂዱ ሱብሃነላህ
እኔም እንደ ዜጋ ልጁ ያለበት ድረስ በመሄድ አይቼዋለው ከእንግዲህ የሚጠበቀው የክሱ ውጤት ነው ኢንሻአላህ አላህ ወደ ሌላ
ሐገር ሄዶ የተሻለ ህክምና እንዲያገኝ አላህም ጨርሶ አፍያ እንዲያረገው በዱአ አንርሳው በዚህ ረመዳን ኢንሻአላህ
አደራ አማና ነው ለ7 አመት የተኛው መሃመድ አሁንም አልነቃም
Share Mareg Amana newu

No comments:

Post a Comment