Monday, July 29, 2013

የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ወያኔ ግቢ ውስጥ ሲልከሰከስ ታዬ! ጦቢያን ገረመው


ይሌ በዜግነት ምክንያት ፕሬዝደንት ይሆናል አይሆንም የሚባለው ቀልድ ጉንጭ አልፋ ነው፡፡ ወቅታዊ ቀልድም ይመስለኛል፡፡ መለስ ዜናዊና በረከት ስምዖን በፍላጎታቸውና በወፍዘራሽ የዜግነት ፍልስፍናቸው ‹ኤርትራዉያን› ሆነው ሲያበቁ ‹የጎረቤት ሀገር ኢትዮጵያን› አንቅጥቅጠው እየመሩ ባሉበት ሁኔታ ኃይሌን ከኢትዮጵያዊነት አንጻር ማማት ለራሱም ሳያስቀው አይቀርም፡፡ ኃያ ዓይነቱ ጨዋታ የፖለቲካ ጨዋታ ነው፡፡ ‹በእውኑስ አሁን ኢትዮጵያ እየተመራች ያለችው በኢትዮጵያውን ነውን?› ብለንም መልሱ በአንድዬ እጅና በታሪክ ማሕጽን ውስጥ የሚገኝ ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን - ለራሳችን፡፡ ኃይሌን በዜግነት ችግር ማንቀራበጥ ለወያኔ ድራማ ማጠናከሪያ ውሻል ማቀበል ይመስለኛል፡፡

 አንደኛ ነገር ወያኔ ሕግ ማውጣት እንጂ ማክበር አያውቅበትም፤ እንዲያውም ያቆመው ሕግ የማይጠቅምና በረዳቶቹ ዘንድ ትዝብት ውስጥ የሚጥለው መስሎ ካየው በአንድ አዳር ያን ሕግ ተብዬ ሰርዞ በምትኩ ሌላ ሊያወጣ የሚችል የዘመኑ መንግሥታዊ ጨቡዴ መሆኑ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ እናም ችግሩ የዜግነት እንደማይሆን ይገባል ይልቁንስ፡፡ የኃይሌ ሀገርን መምራት ያለመቻል ችግር ያለው ከዜግነት አንጻር ሊመስለኝ አልፈልግም፡፡ ስንትና ስንት የፈጠጠ ጉድለት እያየንበት በዚህ ውሃ የማያነሳ ጉዳይ ጊዜ ማባከኑ በማይሠራ ሕግና ከ‹ተጻፈበት ቀለም› የዘለለ ዋጋ በሌለው ወረቀት ላይ በከንቱ ከመጯጯህ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡

ከሰሞነኛ የሀገራችንና የዓለማችን አንዳንድ ሥራ ፈት የዜና ማዕከላት ወሬዎች መካከል አንዱ የኃይሌ ገ/ሥላሤ የሥልጣን አራራ መሆኑን በግሌ መረዳን ሳላሳውቅ ወደሁለተኛው አንቀጽ በመግባቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ እናም በግሌ - ጉዳዩ በቀጥታ እንደሚያገባው አንድ ኢትዮጵያዊ - ስለዚህ መካሪ ያጣ የገንዘብና የሥልጣን በሽተኛ ሰውዬ የሚሰማኝን ጥቂት ነገር ልበል፡፡ ያገባኛል ያልኩት ያለኝ ዜግነት አንድ ብቻ - ያም ኢትዮጵያዊነት ብቻ በመሆኑም ብቻ አይደለም፤ ያገባኛል ያልኩት ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ መመኪያና መኩሪያ ስለሌለኝ ብቻም አይደለም፤ ያገባኛል የምለው ይህን ሰው በሚገባ ስለማውቀው እንኳንስ ሀገርን የመሰለ ትልቅ ነገር ለመምራትና ቤቱንም በአግባቡ ለማስተዳደር የሚያቅተውና በዘመናዊ የቴክሎጂ መሣሪያ ቢመረመር የጤናማነቱ ጉዳይ ቤተሰብ ለመመሥረት ጭምር የማያስቸለው እንደሚሆን በከፍተኛ ደረጃ ስለምጠራጠር ነው - የኔ ‹ሥራ› መጠራጠር ነው - የ‹አልጠረጠርም› ባይ ሥራ ደግሞ ጥርጣሬን ማስወገድ የሚያስችል ማስረጃ ማቅረብና ጠርጣሪን ማሣፈር ነው፡፡ አዎ፣ ደደብን ደደብ ካላሉት ቤተ መንግሥት ውስጥ በማያውቀው ነገር ገብቶ ይፈተፍታል ይባላል፡፡  ኃይሌ እውነቱን ይረዳው - ሕዝቡ አብጠርጥሮ ያውቀዋል - ከዋናው በር እስከመኝታ ቤቱ እናውቃለንና ዝምተኝነታችንን አይበዝብዝብን፤ በሀብቱ ወይም በወያኔያዊ ጥገኝነቱ ፈርተን የማንናገር ከመሰለው ተሳስቷልና ከአሁኑ ይታረም - ቢያንስ እሱና እሱን መሰል ቅሌታሞች እንዲፈነጥዙብን አንፈቅድም - እውነቱን በመናገር የእሱነቱን ማንነት እናጋልጣለን፡፡ እናም ዘመድ ካለው በጊዜ ይምከረውና የሥነ ልቦና ዐዋቂ/ሐኪም እንዲያክመው ያድርግ፤ አለበለዚያ ብዙ ጣጣ ውስጥ ይገባል፤ በእልህ የጀመረውን የዕብድ ውሻ መንገድ እገፋበታለሁ ካለ በግል ሕይወቱ ጭምር እየገባሁ በምዘባርቃቸው አንዳንድ ጉዳዮች በጣም ላስከፋው ከወዲሁ ቃል እገባለሁ፤ ከዛሬ ጀመርኩ፡፡ ይሉኝታ የሚሠራው ይሉኝታ ላለው ነው፤ ከፈጣሪ መንገድ እንዳፈነገጥሁ ይገባኛል - ጊዜ ካለኝ ንስሃ እገባለሁ እንጂ እንዲህ ያለውን መናኛ ስብዕና ከማጋለጥ አልመለስም፡፡ በሚሆነው አዝናለሁ - ምርጫ ግን የለኝም፡፡
እርሱ በኛ ላይ ከሚያደርገው ብልግና ይልቅ የአንድን ሰው ገመና ገሃድ ማውጣትና ሀፍረትን የሚያውቅ ከሆነ በሀፍረት እንዲሸማቀቅ ማድረግ ከተቆርቋሪ ዜጎች ይጠበቃልና የእርሱን ብልግና የምታውቁ ሁሉ ከእንግዲህ አትሳሱለት፤ ለይሁዳ የሚሳሳ አንጀት ሊኖረን አይገባም፡፡ ገና ለገና ባንዲራችንን - ሊያውም ኋላ ኋላ ላይ ኢትዮጵያን በትክክል የማይወክል የወያኔን ደባደቦ ባንዲራ እየመረጠ - አውለብልቧል ብለን እላያችን ላይ ሲያቀረሽ ዝም ማለት የለብንም፡፡ ይሄ ቆሻሻ የውሻ ልጅ በኢትዮጵያማ እንዲህ አይጨማለቅም! የሌሎቹ አነሰንና ደግሞ ይህ ማይም የወያኔ እግር አጣቢ በስማችን ይነግድብን? አላሙዲንና ኃይሌን ለመሰሉ ውሾች - በአእምሮ ሣይሆን በሆድ የሚያስቡ ደንቆሮ ዓሣሞች የሚያዝን ኅሊና የለኝም፡፡
ይቅርታና ምሕረት ሌላ ነው - ሆን ብሎ ሀገርን ለገንዘብና ለዝና እንዲሁም ለሥልጣን የሚሸጥ የዲያብሎስ አጋንንት ግን በምንም መንገድ ሊታለፍ አይገባም፡፡ ወያኔ ጋር እየተሸራሞጡና ሣምባን ከካሊፕሶ እየጨፈሩ ሕይወቴን የቀን ጨለማ እንዲውጠው ያደረጉትን ሁሉ - ማንም ይሁኑ ማን - ምንም ይሁኑ ምን - በተቻለኝ ሁሉ ሌላው ቢቀር በብዕር እዋጋቸዋለሁ፡፡ የነዚህን ሰዎች ግፍና በደል ለመሸፈን የሚሞክር ሁሉ የነሱ ተባባሪና ረዳት ነውና በበኩሌ ጥቁር ውሻ እንዲወልድ እራገማለሁ፤ እናም ተራገምኩ - ‹ይህን መልእክት ሆን ብሎ ያፈነ  ወይ ያሳፈነ በዚህ መልእክት ውስጥ የተጠቀሰ የመርገምት ቃል ሁሉ በራሱና በትውልዱ ይድረስ!›፡፡ ከአሁን በኋላ ለኃይሌ የሚራራ አንጀት ያለውና ከእርሱ ጎን የሚቆም ሁሉ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ተባብሮ ታሪክንና ሀገርን ለማጥፋት ከጥልቁ የእሳት ባህር የመጣ እንጂ ሕዝባዊ ወገናዊነት ያለው ጤናማ ዜጋ ሊሆን አይችልምና ኃይሌንና መሰል የወያኔ ቡችሎችን የማይቃወም ከወያኔ አንድ ነው - ስለሆነም እየመጣ ያለው የእሳት ዝናም በእርሱም ላይ ይዝነብ፡፡
ዕድሜውም ልክ እንደወያኔ ሁሉ አጭር ይሁን፤ የወያኔ ጣዕረሞት የርሱም ዕጣፋንታ እንዲሆን ፈቃደ መለኮት ይሁንልኝ - ‹እንዴት? በምን ምክንያት?› እያላችሁ አትጠይቁ (መጠየቅ ያስቀስፋል! Kidding … )- የወያኔ ዕድሜ በሰማያዊ የጊዜ አቆጣጠር በክፍልፋይ ሴከንዶች የምትቆጠር ናት - ወያኔ ጣር ላይ ነው፡፡ ጣር ላይ ያደረሰው የምሥኪኖች ዕንባና የሚዋኝበት የደም ባህር እንጂ የሌላ እንዳይመስላችሁ በተለይ አንዳንዶች በሰው ሥራ ላይ እንዳትመኩ - ማለቴ እንዳትኮፈሱ፡፡ የታዘዘው ኃይል ገና ተገቢ ሥራውን በቅጡ አልጀመረምና! (የነቢይነት ተሰጥዖ የለኝም - እምናገረው የውስጤ የሚነግረኝን እንጂ እንደሁሴን ጅብሪል ፊት ለፊቴ የተሰቀለ ጀንዲ ወይም አንሶላ ላይ የተነጠፉ ቃላተ ትንቢትን እያነበብኩ አይደለም - ስለዚህ ይህን ‹ስሜት ወለድ› ፈለገ-ሃሤት  ጠቅሶ ሰውን ማስደሰት እንዳይቻል በማይም ቃሌ ገዝቻለሁ - ቆዳ ታጣቂውና አንበጣ በሊታው ዮሐንስ በባዶ እግሩ በበረሃ እየዞረ ምን ነበር ያለው? … (አሃ፣ ወዴት ጠጋ ጠጋ - የስሙኒ ቲማቲም በኪሎ 25 ብር ገዝተው ‹እየቆረጡ›ና የአንድ ብሩን ነጭ ፊያሽኮ ቪኖ  በ45 ብር ገዝተው ‹እየኮመኮሙ› የምን ‹ጊዜው ቀርቧል፤ ንስሃ ግቡ› እያሉ በከተማ በረሃ ባስካርባ እየሄዱ መጮህ ነው?)ዓለም
ኃይሌ ፍጹማዊ ገብጋባ ነው - ከሚቋምጥለት ሥልጣን ጋር ምን አገናኘው እንዳትል - ትስስሩን  እናገራለሁ፡፡ ገብጋባነቱ ደግሞ አንድና ሁለት ብቻ ሣይሆን ዓለም የምትጠቀማቸው ቁጥሮች አይገልጹትም፡፡ እንዴ! ለመሆኑ ኃይሌ ከነአካቴው ሰው ነው ማለትስ ይቻላልን? ቀጣዩን የአንዲት ቀን ገጠመኝ (anecdotal episode) እዩና ራሳችሁ ፍረዱ፡፡ ይህ ሰው ልምራችሁ ሲልም ይታያችሁ፡፡
ኃይሌ ይህን እውነተኛ ታሪክ እንዲያስታውስ ወዳጆቹ ንገሩት - የዚህን ደብዳቤም ግልባጭ ላኩለት፡፡ አንድ ወቅት ወደርሱ ቤት የሚገባ የውሃ ጉድጓድ ይቆፈር ነበር፡፡ የቁፋሮው ሥራ እየተካሄደ ሳለ ከሚቆፍሩት ወዛደሮች አንድኛው በናዳ ሕይወቱ ያልፋል፡፡ ያን ሬሣ ወዳገሩ (ወደጎጃም) ለመላክ ሥራውን ይቆጣጠር በነበረ አንድ ጓደኛየ አማካይነት የአካባቢው ማኅበረሰብ ገንዘብ እንዲያዋጣ ይጠየቃል፡፡ ቦታው ቦሌ ነው፡፡ ሁሉም የቻለውን ረዳ፡፡ ያ ከዚያን ጊዜ በፊት ኃይሌን ከቆንቋናነት አንጻር የማያውቀው ጓደኛየ ኃይሌን ከቤቱ አስጠርቶ ችግሩን ይገልጥለትና የረድኤት እጁን እንዲዘረጋ ይጠይቀዋል፡፡ ሀገርና ወገን ወዳዱ ኃይሌ፣  በኦሎምፒክ ሜዳዎች ባንዲራ ሲሰቀል የዐዞ ዕንባውን የሚረጨው አስመሳዩ ኃይሌ ወዲያውኑ ሃያ ብር ያወጣና ይሰጣል፡፡ ጓደኛየ ክው ብሎ ይደነግጣል - እዚያ አካባቢ የነበሩ ወዛደሮችና አላፊ አግዳሚ ተራና በጣም ድሃ ዜጎች ከዚያ ገንዘብ እጅግ የሚበልጥ ሰጥተዋልና የጓደኛየ ድንጋጤ የሞት ያህል ሆኖ አጽናኝ አስፈልጎት እንደነበር ከብዙ ዓመታት በኋላም አሁን ድረስ እያንዘረዘረው ያስታውሰዋል፡፡ ጓደኛየ ሲረጋጋ “ምነው ኃይሌ? ይህን ያህልማ እኔም አያቅተኝም፤ ከአንተ እኮ የምንጠብቀው … ይህ ልጅ እኮ ሲሰራ የነበረው ወዳንተ ቤት ይገባ በነበረ መስመር ነው፡፡ ካንተማ …” በማለት ሲወተውተው “እንዴ - ደም ተፍቼ እኮ ነው የማገኘው፤ መሬት ወድቆ እኮ አላገኘሁትም …”ብሎ እያጉመተመተ ቤቱ ይገባና ያቺን ሃያ ብር አስቀርቶ 200 ብር ይሰጠዋል፡፡ ኃይሌ እኮ ለጫማ ጠራጊ አንድ ብር ሰጥቶ ሃያ አምስት ሣንቲም መልስ ለመቀበል ዝርዝር እስኪገኝ ድረስ ግማሽ ሰዓት የሚጠብቅ እጅግ ሰፍሳፋና ‹ሀገርና ወገን ወዳድ› ብርቅዬ ዜጋ ነው፡፡ …
መስጠት አለመስጠት የግል ጉዳይ ነው - በመሠረቱ፡፡ እኔ የምለው ግን የዚህ ዓይነት የተለዬ ጋብሮቭ ኢትዮጵያን ልምራ ብሎ መናገር ሳይሆን ማሰብም አይገባውም፡፡ ይቅርና በወያኔ የውሸት ሥልጣን፣ በነገይቱ ኢትዮጵያም ቢሆን ማሰብም የለበትም፡፡ አመራር ከቸርነት ይጀምራል፤ ያለውን አለምክንያት ይበትን ወይ ይዝራ ማለት አይደለም - ግን እስከዚህን አስተዛዛቢና አንጀትን እስከወዲያኛው የሚቆርጥ ደረጃ የሚንገበገብ ሰው የቤቱንም ቆሎና ስኳር እየቆጠረ - የሞሰብ እንጀራ ላይ በሣር ምልክት እያደረገ በሻይሎካዊ ባሕርይ ሌሎችን ሰላም መንሳቱ አይቀርምና ወደ ቁጩም ሆነ ወደእውነተኛ የሥልጣን ወንበር ሊጠጋ አይገባውም፡፡ ከነብሂሉ ‹ሆዳም ሰው ፍቅር አያውቅም›፡፡ ገብጋባ ሰው ሆዳም ነው፤ ሆዳም ሰው ገብጋባ ነው፤ ገብጋባ ሰው ራሱን አይወድም፤ ገብጋባ ሰው ሰውን አይወድም፤ ገብጋባ ሰው ሀገር አያውቅም፤ ገብጋባ ሰው ፍቅር አያውቅም፤ ሆዳም ሰው ለሆዱ ሲል ሀገሩንም ወገኑንም ቤተሰቡንም ይሸጣል፡፡ ኃይሌ ለገንዘብና ለዝና ሲል ዓለምን ሸጦኣል ፤ ዓለምም ዘወርዋራ ናትና ፊቷን አዞረችበት - በመጨረሻም የሀብትና የዝና ጥሙ አንጎሉ ላይ ሲያናፍልበት ተመልክታ ብታስጠነቅቀውም ሊሰማት ባለመቻሉ እሷም ናቀችው - ከሕዝብ ጋር ሲላተም እያየችም አላዘነችለትም፤ በቂ የጥሞና ጊዜ ስጥታው ነበርና - ዓለም እንዲህ ነች፤ ሕይወትም፡፡ ተፈጥሮው ለአመራር ሳይሆን ገንዘብና ዝና ለማሳደድ ነው - ኃይሌ ገንዘብና ዝና አይጠግብም - እሱን መሰሎችም እንዲሁ፡፡ ኃይሌ ያቋቋመው በጎ አድራጎት አለ? ኃይሌ እንዲህ ያለ መልካም ነገር ለእገሌ ሠራ ተብሎ ያውቃል? በመጀመሪያ ለዕርዳታና ለመሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎች ወደኃይሌ ቤት የሚሄድ ሰው ያለም አይመስለኝም - ሁሉም ስለሚያውቀው - ማን አፉን ያበላሻል? ለወትሮ ጅብ ነበር ወደማያውቁት ሀገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ የሚል፤ ዛሬ ደግሞ ዘመን ተዛወረና ደደቡና ማይሙ ኃይሌ በሚታወቅለት ለፍዳዳ አንደበቱ የሕዝብን የነጻነት ትግል ለማኮላሸት ከሀገር መሠሪ ጠላቶች ጋር ይለፋደድ ያዘ፡፡ ‹ልጅ አይውጣለት› ብዬ አልረግመው ነገር ሆኖብኝ ተቸገርኩ እንጂ ሰውዬው ብዙ ያናግራል፡፡ ብቻ እግዜር ይይለት - ዕድሜውንም እንደሚያመልክበት እንደመለስ ያድርገው! በቃ፡፡ ከጠሉ ወዲያ ልምምጥ የለም፤ የኛ ነበር - የኛነት አስጠላው - የዝና ሰይጣናዊ መንፈስ እኛን እንዲጠየፍ አስገደደው - በኛም ላይ ሽንቱንና ለከት ያጣ ቅርሻቱን ይለቅብን ጀመረ፡፡ ስለዚህ ሞቱን እንጂ ብልግናውን ላለማየት ቆርጫለሁ - ይሆናል፡፡ እንኳን ኃይሌ ጎብላላዎቹ ሐምሌና ነሐሴም ያልፋሉ፡፡
የኃይሌ ተፈጥሮ ሀገርን መምራት ሳይሆን ሮጦ የራሱን ስምና የሀገርን ስም ማስጠራት ነው፡፡ ሁሉም ሰው የየራሱ ተፈጥሮ አለው፡፡ ለመሪነት የራሱ የሆነ ግርማ ሞገስና የዕውቀት ደረጃ አለው - እንዳሁኑም የወያኔ ዘመንም ሆነ እንዳለፉት መሪር አገዛዞች ሳይሆን እንደጥንቱ አፍላጦናዊ ፍልስፍና፡፡ ማይሙ ኃይሌ ተፈጥሮ የለገሰችው ችሎታ መሮጥን ነው - በቃ፤ እግርና ጭንቅላት ደግሞ ለዬቅል ናቸው - በአቀማመጣቸው እንኳን ተቃራኒዎች መሆናቸውን ያጤኗል፡፡ ከተፈጥሮ ችሎታው ከሩጫ አልፎ መሪ አድርጉኝ ቢል ግን ወጥ መርገጥና አሳዳጊ የበደለው መሆኑን በይፋ ማሳወቅ ነው - ለወያኔ ሥልጣን አይመጥንም ማለት እንዳልፈለግሁ ግን አስረግጬ መናገር እፈልጋለሁ - ለወያኔ ሹመት በትንሹ ግዑዝ ድንጋይ መሆን ከበቂ በላይ ነው - አምባሳደር ለመቀበልና ለመሸኘት ደግሞ እንደራስ ሆቴል አንበሣ በምሥል መልክ ወንበር ላይ የሚዘፈዘፍ ግርማ ወልደጊዮርጊሳዊ ጥውርም ሲበዛ ነው፡፡ ኃይሌን በሚመለከት አጥንቴ ድረስ ዘልቆ ክፉኛ የተሰማኝ የኢትዮጵያን ሕዝብ መናቁና ሀገር ሻጭ ወያኔን መጠጋቱ ነው - ምንም ነገር ሳይቸግረውና ማይማዊ ደደብነቱ አስገድዶት (በነገራችን ላይ እንደወያኔዎች ሁሉ በሰይጣናዊነት እንደሚታማም አውቃለሁ - በማስጠንቆል የደረሰበትን የሀብትና የዝና ጣሪያ የማናውቅ መስሎትም ከሆነ ተዘናግቷልና እንደምናውቅ ይወቅ፤ ከተመቸኝና ከፈለግሁ ወደፊት በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እመለስበታለሁ)፡፡ እንኳንስ እርሱ እኔ ራሴ - ኃይሌ ንፍጡን እያዝረከረከ ደብተሮቹን በጉያው ወትፎ ወዳልጨረሰው ትምህርቱ ይሄድ በነበረበት ሰዓት ከፖለቲካው ባልራቀ ሁኔታ ሀገሬን አገለግል የነበርኩትና በመቶዎች የሚቆጠሩ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው መጣጥፎችን ለሀገሬ ያበረከትኩት ሰውዬ ለቀበሌ አመራር እንኳን እበቃለሁ ብዬ አላስብም፤ ምክንያቱም ተፈጥሮየ ለአመራር ሳይሆን ለመጻፍና ምናልባትም ለማላውቀው ለሌላ ነገር ነው፡፡ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረልኝ ብዬ እንደኃይሌ ‹ለዚህ ቦታ ምረጡኝ› ብል መናገሩንና መወዳደሩን እንደምችል ባውቅም ካለተፈጥሮ ዝንባሌና ችሎታ ገብቼ መፈትፈቱ ግን የኋላ ኋላ ችግር እንደሚያመጣብኝ እረዳለሁና አልሞክረውም፡፡ ይህን የምለው ለጊዜው ሌላ እውነተኛ ማነጻጸሪያ ስላጣሁና እውነቴንም ስለሆነ ነው፤ ጊዜ ሰጠኝ ተብሎ ወደአንድ ነገር ቢሞጀሩበት ችግር ነው - የግብጹ ሞሐመድ ሞርሲን ልብ ይሏል - የተፈጥሮ ጥሪን መረዳት ተገቢ ነው ወንድሞቼ እንዲሁም እህቶቼ፡፡ እናም ኃይሌ መቶ ሀገር ቀርቶ አንድ ሺህ ሀገር ቢዞርም በኢሣት እንደሰማሁት  አዟዟሩ የሩጫ እንጂ ፖለቲካዊ የሥራ ጉብኝት ባለመሆኑ ዙረቱ እንደተባለው ዕቃ ለመሸመትና ያማረ ሆቴል ተከራይቶ ለመንፈላሰስ ካልሆነ በስተቀር ለምንም ዓይነት የፖለቲካ ተሹዋሚነት አያበቃውም፡፡ ይህ ሰው ጭንቅላት የሚባል ነገር በጭራሽ ስለሌለው እንጂ - እንደእንስሳ ሽምጥ ለመጋለብ ከሚጠቅም ደመነፍሳዊ አንጎል በስተቀር ማለት ነው - ትንጥዬ አንጎል ብትኖረው ኖሮ ወደዚህ ቅሌትና ውርደት አይገባም ነበር፡፡ በደደብነቱ ሳቢያ ልቦናው ታውሮበት እንጂ እኔና እርሱ እንደዮሐንስ መጥምቁ አባባል የጫማቸውን ማሠሪያ ለማሰር ወይ ለመፍታት የማንበቃ ስንትና ስንት ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ኢትዮጵያውን ቀኒቱን እየተጠባበቁ ናቸው - በበሣል አመራራቸው እንደእስራኤል በጥቂት ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ሌሎች ሀገሮች ወደደረሱበት የሥልጣኔና የዕድገት ማማ ለማድረስ(አባብሌ ዲግሪው ላይ አለመሆኑን ‹ፕሊዝ› ተገንዘቡልኝ - ለዲግሪ ለዲግሪውማ ‹ፕሮፌሰሮች› ክንፈ አብርሃምና አንድርያስ እሼቴስ ነበሩን አይደል? በአካልም በመንፈስም በኅሊናም ሙታን ሆነው ሀገር ሻጮች ጋር ተባበሩብን እንጂ)፡፡ ከዚህ ሰው ሳይሆን ምቹ ሁኔታን የማጣታችን ሁኔታ አኳያ የዚህን ንፍጣም ሰውዬ ምኞትና የሕጻን ፍላጎት የሚመስል ጤንነት የጎደለው ቅዠት ስታዘብ አንዳች የመደፈር ጸጸት ይወረኛል፤ በምትንቀው መናኛ ሰው እንደመደፈር ያለ ደግሞ የጸጸት መንስኤ የለም - ደግሜ ልራገም መሰለኝ - የሥራውን ይስጠው፤ እሱ ሕዝብን እንደናቀ በዓለምም እንዳስገመተን ሞት ግን ውለታ ይዋልልንና ንቆ አይተወው፡፡  ራስን ያለማወቅ ችግር - እርግጥ ነው - የዓለማችን ራስ ምታት መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይሁንና ራስን አለማወቅ የፈለገውን ያህል  ችግር ያስከትል እንጂ እንደኃይሌ ያለ ሰው በምናውቅለት የሥራና የትምህርት ወይም የችሎታና የልምድ ታሪክ ከመሬት ተነስቶ የጠላት መሣሪያ ልሁን ብሎ መነሳቱ ዕብደት ካልሆነ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡
 
‹ምላሴ ጥቁር ነው፤› እርግማኔ አይደርስም አልልም፡፡ በሥርዓት ደረጃ እየዘገየብኝ ተቸገርኩ እንጂ በግለሰብ ደረጃ እርግማኖቼ ዒላማዎቻቸውን መትተው ወደሰገባቸው የሚመለሱባቸውን ጊዜያት ማስታወስ አይከብደኝም፡፡ አበበ ገላው በመብረቃዊ የቁጣ ድምጹ የተሸሸገና በያዝ ለቀቅ የፖሊስና ሌባ ጨዋታ ከሟች ጋር ድብብቆሽ ይጫወት የነበረን ነቀርሣ አፋፍሞ የመለስን ሞት ማፋጠኑ አይዘነጋም፡፡ በዚያም ምክንያት የጎጃም ባላገር እንዲህ ብሎ ስንኝ መቋጠሩ በ‹ኢቲቪና በኢትዮጵያ ኤፍ ኤሞች› በስፋት ተዘግቧል፡፡
ሽጉጥ አልታጠቀ መትረየስ የለው፤
ባንደበቱ ገዳይ አበበ ገላው፡፡
እኔም በእርግማን ሰው መግደሌ ይፋ ሆኖ ወደሕዝብ ጆሮ የሚደርስልኝ ከሆነ ያገሬ ባላገር እንዲህ ብሎ ሳይቀኝልኝ እንደማይቀር ተስፋ አደርጋለሁ፤ ምኞት መቼም አይከለከልም፡፡
ሞይዘር አልታጠቀ ፊሻሌ የለው፤
በጠሎቱ ገዳይ ጦቢያን ገረመው፡፡
ስለዚህ ኃይሌን እረግሜያለሁና ‹ከኔ እርግማን› ነጻ መውጣት ከፈለገ አሁኑኑ ይቅርታ ጠይቆ ከ‹ውድድሩ› ይውጣና አርፎ ሌላ የሚችለውንና የሚገባውን ሥራ መሥራቱን ይቀጥል፡፡ በበኩሌ ጦሬን ሰክቻለሁ - በፈጣሪ ፊት ተንበርክኬ የእርሱን መጨረሻ እንዲያሳየኝ በዕንባ ጭምር ጠምጄ ይዠዋለሁ - ሌሎችም ዕርዱኝ - እንረዳዳና ይህን ተናግሮ አናጋሪ የወያኔ ዕብድ ውሻ እናስወግድ - የተከፋች ‹አብዮት ልጇን› እንደምትበላም እናሳየው፡፡ መዳኛው አንድና አንድ ብቻ ነው - ያም ተጸጽቶ ሕዝብንም ይቅርታ ጠይቆ መመለስ ብቻ ነው(በወያኔ ትዕዛዝ ወደ አሥመራ ተልኮ ሻዕቢያ ሥር በመደፋት የአማራውን ሕዝብ ለውርደት የዳረገው ንጉሤ አስገልጥ(?) የተባለ ቀልማዳ ከሃዲ እንዴት እንደሞተና ሕዝብ አድሞበት ሬሣው በኩሊ እንደተቀበረ ልብ ይሏል፤ ሕዝብ ከጠላ መድረሻ የለም - በተለይ የኢትዮጵያ! ያቆየንና ገና ብዙ እናያለን ውድ ወርቃማ ኢትዮጵያውያን!) ፡፡ ይህን ደግሞ ይወቅ - ከተገፋና በበደል ብዛት ከሚንተከተክ አእምሮ ኃይል ይመነጫል፤ ያ ኃይል ደግሞ አጥፊም አልሚም ሊሆን ይችላል - ጦርም ዳቦም ከአእምሮ ይፈልቃል፡፡ እየተረጋገምን ዘር ከምናጠፋ እየተሳሰብን ዘር ብናለማ ይሻላልና ይህን መልእክቴን - ሳታናንቁብኝ - ለርሱው ለደንቆሮው ኃይሌ አድርሱልኝ - ሁኔታዎች ቢመቻቹ በአካል ባገኘውና እስከዶቃ ማሰሪያው ብነግረው በወደድኩ - ግን … ፡፡ (እንዳስፈላጊነቱ እቀጥላለሁ!)
 THE MALEDA TIMES

ሰበር ዜና ፤ መቀሌ – የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም!!


47f31-1044632_186255854871283_437829438_n5b15d
July 29th, 2013
በር ዜና፤ አቶ ጌታቸው ገ/ስላሴ የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣አቶ ወልዳይ የተባሉና የመቀሌ ዞን የፀጥታ ኃላፊ እንዲሁም ከመቀሌ ወጣቶች ማህበር ተወከልኩ ያለ ግለሰብ የአንድነት አመራሮቸን በመጥራት “መንግስት አጠቃላይ ግምገማ ላይ ስለሆነ የፀጥታ ኃይል እጥረት አለብን” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አትችሉም ብለዋቸዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችም መልሳቸሁ ህግ የተከተለ አይደለም፤ እኛ ህገመንግስታዊ መብታችንን ጠይቀናል በየትኛውም ሁኔታ ሰልፉን አንሰርዝም፡፡” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በመቀሌ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አባላት በደህንነት ኃይሎች ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑ የደርሰን ዜና ያመለክታል።
የሰላማዊ ሰልፍ “የአሸባሪዎች ተላላኪ ናችሁ የመቀሌ ህዝብ እንደዚህ አይነት እንቅስቃሴ አይፈልግም” በማለት አንድነት ፓርቲን የሚመለከት በራሪ ወረቀት የመበተንም ሆነ የቅስቀሳ ስራ የሚያከናውን ሰው ላይ ጥብቅ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉም ዝተውባቸዋል፡፡ ሆኖም በመቀሌ የሚገኙት የአንድነት አመራሮች ለሰላማዊ ሰልፉ ቅስቀሳ ለመጀመር ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለአከባቢው ባለስልጣናት አሳውቀዋል፡፡

ESAT Daliy News Amsterdam July 29 2013 Ethiopia


Sunday, July 28, 2013

ኢትዮጵያ 250 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል በነጻ በማባባያነት ለኤርትራ !!* ባድመን መልሶ ለማስረከብ ድርድር….


0
vcc
* ባድመን መልሶ ለማስረከብ ድርድር….No nation, big or small, rich or poor, can get away by militarily occupy a sovereign territory of another nation
ተስፋዬ ኒውስ በሚል የሚታወቅ ድረገጽ ኢትዮጵያ ኤርትራን ለማግባባትና ወደ ድርድር ለማምጣት 250 ሜጋ ዋት የኤሌልክትሪክ ሃይል በነጻ እንደምትሰጥ የኤርትራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኡስማን ሳለህን ጠቅሶ ዘግቧል።
ለንዶን በተካሔደ የኤርትራ ተወላጆች ዓመታዊ ፌስቲቫል ላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ የተባለው እውነት ከሆነ ኢህአዴግ ባድመን ጨምሮ ኤርትራ የኔ የምትላቸውን ቦታዎች ለማስረከብ መስማማት አለበት። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላትንም ከስፍራው ላመንሳት ይስማማል።
ኤርትራን ወደ ሰላም ንግግር ላማምጣት ተደረገ በሚባለው በዚህ የማግባቢያ ስምምነት ላይ ድረ ገጹ ከኢትዮጵያ ወገን ማረጋገጫ አልጠቆመም። ወይም አሸናጋይና ሃሳቡን ያቀረቡ ናቸው ከተባሉት ሩሲያ፣ ቱርክና ኳታር ወገኖች የተሰጠ ነጻ አስተያየት አላካተተም። ኢህአዴግም ዜናውን አስመልክቶ በይፋ ያስተባበለው ነገር ስለመኖሩ የተሰማ ነገር የለም።ይሁን እንጂ የኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር በሎንደን ከወገኖቻቸው ጋር መሰብሰባቸውና በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መናገራቸው እውነት ነው።
በኤርትራ የኑሮ ውድነትና ችግር በቃላት ሊገለጽ ከሚችለው በላይ አስቸጋሪ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሻዕቢያ ካትዮጵያ ጋር ያለውን ችግር ለመቋጨት ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍላጎት እንዳለው የሚገልጹ ክፍሎችም አሉ።
Ethiopia Offers Electricity in Exchange for Dialogue: Minister Osman
Posted on 27 July 2013. Tags: 250MW to Eritrea, Badme, border dispute, Dialogue, Eritrea, Ethiopia, Ethiopia Electric Offer to Eritrea, Normalization
No nation, big or small, rich or poor, can get away by militarily occupy a sovereign territory of another nation
No nation, big or small, rich or poor, can get away by militarily occupy a sovereign territory of another nation. NEVER!
By TesfaNews,
Eritrea’s Foreign Minister, H.E. Osman Saleh disclosed that his country politely declined Ethiopia’s latest ploy to seduce Eritrea into negotiation with a 250MW free electric power offer.
In a seminar he conducted last week at the annual festival of Eritrean community members in London, Minister Saleh explained that Ethiopia tried very hard to sell the proposal through Russia, Qatar and Turkey.
Minister Osman, however, clarified that Eritrea’s one and only one condition to enter into dialogue or normalize relation is for Ethiopia willingly vacate its troops out of sovereign Eritrean territory including the town of Badme.
As President Afwerki made it clear through its envoy at the African Union on the January 28th AU summit, normalization of relation can start in the afternoon as long as Ethiopia withdrew from Eritrean territories including Badme in the morning hours.
Minister Saleh further underlined that the problem with Ethiopia has nothing to do with the issue of “political will” or “dialogue” and cannot be characterized as a deadlock as the border dispute between the two countries has been resolved through Final and Binding arbitration ten years ago. What is left now is to see the end of Ethiopia’s occupation of sovereign Eritrean territories as it cannot be justified legally or politically.
The minister finally concludes that the various ploys played by Ethiopia and its handlers to frustrate Eritrea into submission with sanctions and threats of sanctions has been futile in the past and won’t do so in the future.http://www.tesfanews.net/

Saturday, July 27, 2013

ዘንድሮ ከቀረቡት የሙስና ጥቆማዎች መካከል ከግማሽ በላይ ኮምሽኑን የሚመለከቱ አይደሉም


በጋዜጣው ሪፖርተር
ለፌዴራል የሥነምግባርና የጸረ ሙስና ኮምሽን በ2005 በጀት ዓመት ከቀረቡት የሙስና ጥቆማዎች መካከል በኮምሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁት ከግማሽ በታች መሆናቸው ተጠቆመ።
ከኮምሽኑ የተገኘ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንዳመለከተው በበጀት ዓመቱ ለኮሚሽኑ የቀረቡት 3ሺ710 ጥቆማዎች ሲሆኑ ጥቆማዎቹን የመመዝገብና የመለየት ስራ ተከናውኗል። ከቀረቡት ጥቆማዎች 1ሺ670 (45 በመቶ)በኮሚሽኑ ሥልጣን ሥር የሚወድቁ ሲሆኑ 2ሺ40 (55 በመቶ) ከኮሚሽኑ ስልጣን ክልል ውጪ ሆነዋል። በተጨማሪም ከቀረቡት ጥቆማዎች 42ቱ የከለላ አቤቱታዎች የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 21ቹ የመጀመሪያ ከለላ ሲሰጣቸው 16ቱ ከለላ የማያሰጣቸው ሆነው ተገኝተዋል፤ ቀሪዎቹ 5ቱ በመጣራት ላይ ይገኛሉ። ከቀረቡት ጥቆማዎች መካከል ከግማሽ በላይ ኮምሽኑን የሚመለከቱ ሊሆኑ ስላልቻሉበት ምክንያት በሪፖርቱ የተጠቀሰ ነገር የለም።
በበጀት ዓመቱ 508 የምርመራ መዝገቦችን በራስ ኃይል መርምሮ ለማጠናቀቅ ታቅዶ 449 ተመርምረው ተጠናቀዋል። ክንውኑ ዝቅ ሊል የቻለው የበጀት ዓመቱ የአዲስ ሰራተኞች ቅጥር በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ነው ብሏል።
በራስ ኃይል ከተመረመሩ የሙስና ወንጀል መዝገቦች መካከል 60 በመቶ በሚሆኑት ላይ በማስረጃ የተደገፈ የ“ያስከስሳል” ውሳኔ ለማሳረፍ ታቅዶ በራስ ኃይል ከተመረመሩ 336 መዝገቦች መካከል ለ163 መዝገቦች የያስከስሳል ውሳኔ ተሰጥቷል። (81 በመቶ) ተዘጋጅተው ከቀረቡ 380 የክስ ቻርጆች መካከል 362 የክስ ቻርጆች በበቂ ማስረጃ ተደግፈው ተዘጋጅተዋል።
በኮሚሽኑ ስልጣን ክልል ስር ከሚወድቁት ቀላል የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች መካከል ስልጣን ባላቸው መርማሪ አካላት እንዲመረመሩ ከተላኩ ጥቆማዎች መካከል ክትትል በማድረግ በበጀት ዓመቱ የሚመለሱትን ሽፋን ከ71 በመቶ ወደ 80በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ ሥልጣን ባላቸው መርማሪ አካላት እንዲመረመሩ ከተላኩ 246 ጥቆማዎች መካከል ክትትል በማድረግ 231(94 በመቶ) ተመልሰዋል።
በኮሚሽኑ ስልጣን ክልል ስር ከሚወድቁት ቀላል የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች መካከል የሚመለከታቸው መ/ቤቶች አጣርተውና እርምጃ ወስደው ከተላኩ ጥቆማዎች መካከል ክትትል በማድረግ በበጀት ዓመቱ የሚመለሱትን ሽፋን ከ71 በመቶ ወደ 80 በመቶ ለማሳደግ ታቅዶ  የሚመለከታቸው መ/ቤቶች አጣርተውና እርምጃ ወስደው እንዲያሳውቁን ከተላኩ 230 ጥቆማዎች መካከል ክትትል በማድረግ ቀደም ሲል የተላኩትን ጨምሮ 278 ተመልሰዋል።
ምርመራ ከሚካሄድባቸው የሙስና ወንጀል ጉዳዮች መካከል 60 በመቶ የሚሆነውን የያስከስሳል ውሳኔ ለመስጠት ታቅዶ ውሳኔ ካገኙ ምርመራቸው የተጠናቀቀ መዝገቦች 336 ሲሆኑ 163ቱ የያስከስሳል ውሳኔ ተሰጥቷቸዋል።
በበጀት ዓመቱ 1ሺ 488 የምርመራ መዝገቦች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ታቅዶ በ880 መዝገቦች ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል። ክንውኑ ዝቅ ሊል የቻለው የበጀት ዓመቱ የአዲስ ሰራተኞች ቅጥር በወቅቱ ባለመፈጸሙ ምክንያት ነው።
በ900 የችሎት መዝገቦች ላይ ክርክር ለማድረግ ታቅዶ በ638 መዝገቦች ላይ ክርክር ተደርጓል። ክንውኑ ዝቅ ያለው ወደ ችሎት የቀረቡ ጉዳዮች በማነሳቸው ነው።
ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 411 ሀምሌ 17/2005

ሰበር ዜና – የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ቤት በፖሊሶች እየተበረበረ ነው


ብርበራው ቀኑን ሙሉ እንደሚደረግ ታውቋል
===============================
በደቡብ ወሎ ዞን በሀይቅ ከተማ የሚገኙ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቤት ላይ ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ብርበራ እንደተጀመረ የዞኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የወረባቡ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ እድሪስ ሰኢድ ለፍኖተ ነፃነት እንዳስታወቁት ዛሬ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ “የጦር መሳሪያ ሰውራችኋል” በሚል ፖሊሶችና ሚኒሻዎች በሀይቅ ከተማ ባሉ ከ16 በላይ በሚሆኑ የአንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት መኖሪያ ቤት ውስጥ ብርበራ አካሂደዋል፡፡ ብርበራው ከተካሄደባቸው አመራሮች መሀከል አንዱ የሆኑት የወረዳው የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ኃላፊ አቶ አራጌ ሑሴን ለሪፖርተራችን እንደገለፁት 5 ፖሊሶችና 1 ሚሊሻ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምረው መኖሪያ ቤታቸውን ፈትሸዋል፡፡ አቶ አራጌ ሁሴን አክለውም “እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ ምንም አታገኙም አልኳቸው፤እንዳልኩትም 2 ሰዓት የፈጀ ብርበራ አድርገውም አንዳች ሳያገኙ ወጥተዋል” በማለት ገልፀዋል፡፡
“ብርበራው መንግስት በአንድነት አባላት ቤት ውስጥ የጦር መሳሪያ አገኘሁ በሚል የተለመደ ድራማ ለመስራት እንደተዘጋጀ የሚያስረዳ ነው” ያሉት የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ወሎ ዞን ሰብሳቢ አቶ ብስራት አቢ ኢህአዴግ የደቡብ ወሎ ህዝብ በግዳጅ አንድነት ፓርቲን እንዲያወግዝ በተለያዩ ከተሞች ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፎችን እንደጠራ አስረድተዋል፡፡ በአንድነት አባላት ቤት የሚደረገው ብርበራ እስከ ምሽት ሊቀጥል እንደሚችልም ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

Thursday, July 25, 2013

“ለዚህ (መንግሥት) ታላቅ ክብር አለኝ”

ሃይሌ! ወደ ፓርላማ?
haile gebreselasse


የዛሬ 10 ወር የሻለቃ ሃይሌ ገ/ሥላሴ ወደ ፖለቲካ የመምጣት ሁኔታን አስመልክቶ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ሃተታ አቅርቦ ነበር፡፡ (እዚህ ላይ ይመልከቱት) ሰሞኑን አትሌቱ ወደ ፖለቲካው የመግባት ፍላጎቱንና “በምርጫ” ለመወዳደር መፈለጉ ብዙ እየተባለበት ይገኛል፡፡ ከዚህ አንጻር አሁን ላለው ሁኔታ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ከዚህ በፊት ያቀረብነውን ሃተታ በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“ለኢትዮጵያ የጥምር መንግስት ያስፈልጋታል” በማለት በ1997 ምርጫ አጥብቆ ሲከራከር የነበረውና በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ ኢንቨስትመንት ውስጥ የገባው ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከነበሩት መንግስታትና ትውልዶች ይልቅ አሁን ላለው ትውልድ ከበሬታ እንዳለው በመግለጽ አስተያየቱን ሰነዘረ። የክብር ሪኮርዶቹን በሙሉ ለቀነኒሳ ያስረከበው ሃይሌ በእጁ የሚገኘውን ብቸኛ ሃብቱን (የህዝብ ክብር) እያሟጠጠ መሆኑ እየተገለጸ ነው።
ሃይሌ ይህንን የተናገረው መስከረም 12 ቀን 2004 ዓ ም ከተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች ጋር በመንግስት ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) አስተያየት በሰጠበት ወቅት ነበር። የቀድሞውን ስርዓትና ትውልድ “ድንጋይ ዳቦ በነበረበት፣ ፍራፍሬ ከጫካ ያለምንም ድካም ከሚሰበሰብበት” ዘመን ጋር ያወዳደረው ሃይሌ፣ “የአሁኑ ትውልድ” በማለት ያሞካሸውን ስርዓት ከተፈጥሮ ጋር ጦርነት በማካሄድ ለውጥ ማስመዝገበ መቻላቸውን አስምሮበታል።
“የባለ ራዕዩ መሪ” አቶ መለስ ገድል ለመዘከር በተዘጋጀ ቅንብር ላይ  በተደጋጋሚ አስተያየት ሲሰጥ የታየው ሃይሌ “አሁን የት ነው ያለነው?” በማለት ጠይቆ “አሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ለማግኘት ነው የምንጋፋው? አውሮፓ ሄደን እዛው ለመቅረት ነው…” በማለት ስደትን መርጠው ከአገራቸው የሚወጡትን ሸርድዶ አልፏል። አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ለስደት የሚዳርግ ጉዳይ የለም ወደ ማለት አዝምሞ ተናግሯል። ሃይሌ ይህን ይበል እንጂ በተቃራኒው እስረኞች እንዲፈቱና የፖለቲካ እርቅ እንዲሰፍን እሰራለሁ ከሚሉት ፕሮፌሰር ይስሃቅ ጋር በሽምግልና እያገለገለ መሆኑ በአገሪቱ ውስጥ የሚታው እስርና እንግልት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚጠቅሱ አስተያየት ሰጪዎች የሃይሌን አስተያየት “ለንብረት ዋስትና የሚከፈል የንግግር ቫት” በማለት አጣጥለውታል።
ከኤርትራ ጋር ከተደረገው በቀር በኢትዮጵያ ይህ ነው የሚባል ጦርነት እንዳልተካሔደ ኢህአዴግን የሰላም አባት አስመስሎ ሃይሌ አመልክቷል። በዚሁም ምክንያት ቀደም ሲል ለጦርነት ይውል የነበረው የአገሪቱ በጀት ሙሉ በሙሉ ወደ ልማት ዞሯል ብሏል። የኢህአዴግ ተወካይ መስሎ አስተያየት የሰጠው ሃይሌ “ይህ አሁን የታየው ለውጥ በአስርና አስራ አንድ ዓመት ውስጥ የታየ ነው። አሁን ባለው አካሄድ ከአስር ዓመት በኋላ እንደርሳለን?” ሲል የራሱን ትንቢት አስቀምጧል።
ተቆራርጦ በሚቀርበው አስተያየት እነ ፕሮፌሰር እንድሪያስን በማጀብ ሃይሌ  በመዝገበ ቃላት ላይ ኢትዮጵያን “ረሃብ” በማለት የሚተረጉማት ቃል እንደሚቀየር በልበ ሙሉነት ተናግሯል። “ከሃያ ዓመት በኋላ” አለ ሃይሌ “በመዝገበ ቃላት ላይ የኢትዮጵያ ውርስ ትርጉም ሃብታም በሚል ይቀየራል” ብሏል።
“ድሮ ትረዱን ነበር፤ እናመሰግናለን። አሁን ደግሞ እንረዳችሀዋለን እንላቸዋለን” ሲል አውሮፓና አሜሪካን የመሳሰሉ ታላላቅ አገሮች የኢትዮጵያን እጅ እንደሚናፍቁ ሃይሌ ከምኞት ባለፈ ስሜት ውስጥ ሆኖ ተናግሯል። አገሪቱን ለሃያ አንድ ዓመታት ሲመሩ የነበሩት አቶ መለስ ባልገለጹበት ሁኔታ ሃይሌ ከአስር እስከ ሃያ ዓመት ኢትዮጵያ ሃብታም አገር እንደምትሆን መናገሩ ከምን የመነጨ እንደሆነ ሊገባቸው እንዳልቻለ ብዙዎች እየገለጹ ነው።
“ሙስና ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል” ሲል ኢህአዴግን የመከረው ሃይሌ የበታች ባለስልጣናት መንግስትን እንዳያሰድቡ መክሯል። “መንግስት ይህንን አድርጉ ላይል ይችላል” የሚለው ሃይሌ የበታች ባለስልጣኖች የሚፈጽሙት ሙስና “መንግስትን ያስወቅሰዋል” በሚል ተቆርቋሪነቱን በይፋ አስታውቋል። ዋናዎቹን የሙስና ተዋናዮች ነጻ በማውጣት የታች ባለስልጣኖችን “እያንገዋለለ” አሳጥቷቸዋል።
“… ለህሊናቸው ሲሉ እንደ መንግስት በማሰብ መስራት አለባቸው” ሲል ትዕዛዝ አዘል ምክርና ማሳሰቢያ ለበታች ባለስልጣናት ያስተላለፈው ሃይሌ የአስተያየቱ መነሻ ከኢህአዴግ ጋር የፈጠረው ዝምድና ውጤት እንደሆነ እየተነገረ ነው። አንድ አስተያየት ሰጪ “ሃይሌ ሃብቱ እየበዛ ሲሄድና የተበደረው ገንዘብ ሲጨምር ኢህአዴግን ወክሎ መናገር ጀመረ” ብለዋል።
አትሌቶችን ሰብስቦ የአቶ መለሰን ሃዘን ሳግ በያዘው ድምጽ እያለቀሰ የገለጸው ሃይሌ ነፍሳቸውን ይማረውና በአቶ መለስ አይወደድም ነበር። በህይወት እያሉም በተደጋጋሚ ያናንቁት ነበር። ሃይሌን እንደሚያደንቁት ተጠይቀው አርቲስት ቻቺን በማሞገስ ጭራሹኑ እንደማያወቁት ዘለውት አልፈውት ነበር። ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት ለሃይሌ ቁብ እንደሌላቸው የሚያውቀው ሃይሌ ከአንድ ማስታወቂያ ሰራተኛ ልቆ በፕሮፓጋንዳ ተግባር ላይ መሰማራቱ በቅርብ ጓደኞቹና በአድናቂዎቹ ዘንድ መነጋገሪያ አድርጎታል።
በአዳማው የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ በመገኘት ውድ ሽልማቱን ለሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በማበርከት የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ የታየው ሃይሌ፤ በዚያው ጉባኤ ላይ አቶ መለስንና ኢህአዴግን ማሞገሱ በወቅቱ በርካታ አስተያየት እንዲሰነዘርበት ምክንያት መሆኑ አይዘነጋም። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ ያነጋገራቸው እንዳሉት ሃይሌ ወደ ፖለቲካው መንደር በፍጥነት እየተንደረደረ መሆኑን በማስረዳት የሚያውቁትንም ተናግረዋል።
ጣና ሃይቅ ዳርቻ ከልማት ባንክ በአርባ ሚሊዮን ብር የገዛውን ሆቴል ከሁለት ወር በኋላ ሼኽ መሃመድ አላሙዲ በትዕዛዝ እንደነጠቁት በታላቅ ቅሬታ ለህዝብ አስታውቆ የነበረው ሃይሌ የባህር ዳርን ቤተ መንግስት የመጠቅለል ታላቅ ፍላጎት እንዳለው ነው የቅርብ ወዳጁ ለመረጃ አቀባያችንየተናገሩት።
በኦሜድላ ስፖርት ክለብ ውስጥ ሰራተኛ የነበሩትና ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሃይሌ ቅርብ ሰው “ሃይሌ ቤተመንግስትን ይወዳል። ኢትዮጵያንም የመምራት ህልም አለው” በማለት ጭራሽ ተሰምቶ በማያውቀው ጉዳይ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
የአማራ ክልል መንግስት ለሲድኒ ኦሊምፒክ ጀግኖች ግብዣ ባደረገበት ወቅት የባህር ዳር ቤተ መንግስት ጎብኝተው እንደነበር አስተያየት ሰጪው ያስታውሳሉ። ሃይሌ የጃንሆይን መኝታ ክፍል ከተመለከተ በኋላ አሰበ። ከአፍታ በኋላ አልጋቸው ላይ ተቀመጠ። አልጋውን ወደ ላይ ወደታች ካወዛወዘው በኋላ “… ይህንን ቤተ መንግስት…” በማለት እንደሚኖርበት መዛቱን አስታውሰው ተናግረዋል።
ሃይሌ ዝም ብሎ እንደማይናገር ያወሱት እኚሁ በቅርብ የሚያውቁት ሰው ሃይሌ ይህንኑ ህልሙን ተግባራዊ ለማድረግ ዘመቻ የጀመረ እንደሚመስላቸው አስታውቀዋል። በቀጣዩ 2005 ምርጫ ሃይሌ እንደሚሳተፍ በርግጠኛነት ተናግረዋል። ሃይሌ ሁለት ጊዜ በግል ፓርላማ ለመግባት እንደሚወዳደር ካስታወቀ በኋላ ባልታወቀ ምክንያት ራሱን ከምርጫ ዘመቻ ማግለሉን መግለጹ ይታዋሳል።
ሃይሌ ፖለቲከኛ የመሆን የኖረ ህልም እንዳለው ያወሱት ባልደረባው ከተናገሩት በተቃራኒ ሃይሌ የፈለገውን መሆንና ማድረግ የግል ውሳኔው እንደሆነ የሚከራከሩለት አልጠፉም። ሃይሌ ሃብት አለው፣ ከፍተኛ ዝና ገንብቷል። ኢትዮጵያዊያን የማይረዱት እውቅናና ክብር በውጪው ዓለም እንዳለው የሚገልጹት ተከራካሪዎች “አንድ ሰው በተናገረ ቁጥር ለንግግሩ ቀንድና ጭራ መቀጠል ነውር ነው። ሰዎች የመሰላቸውን እንዳይናገሩም የሚገድብ ክፉ ልምድ ነው” ባይ ናቸው። “አያይዘውም ሃይሌ የኢህአዴግ አባል ቢሆን እንኳ አስገራሚ አይሆንም” በማለት ጠርዝ ደርሰው ይሟገታሉ።
በርካታ አትሌቶች የኦህዴድ አባላት እንደሆኑ የሚጠቁሙት እነዚህ የሃይሌ ተከራካሪዎች “ሃይሌ ኢህአዴግን ቢቀላቀል መነጋገሪያ የሚሆነው ጉዳይ ብአዴን ወይስ ኦህዴድ ይሆናል የሚለው ነው” ብለዋል። አርሲ የተወለደው ሃይሌ በሩጫ ከተሳካለት በኋላ በተለያዩ ጉዳዮችና መጠነኛ ግንባታ ወደ ባህር ዳር መጠጋጋቱ በትውልድ አካባቢው ተወላጆች ቅሬታ እንዳስነሳበት በተለያዩ ጊዚያቶች መዘገቡ የሚታወስ ነው።

የመንግሥትን ስም ማጥፋት ማለት የክቡርነታቸውን…? (ፕ/ር መሰፍን ወልደማርያም)



ስም ምንድን ነው? መታወቂያ ነው፤ መጠሪያ ነው፤ ስም ማጥፋት ሲባል ስም አለ ማለት ነው፤ ከስምም አልፎ የገነነ ስም አለ ማለት ነው፤ ስለዚህም ሊጠፋ የሚችለው የገነነ ስም ሲኖር ብቻ ነው ማለት ነው፤ ደራርቱ ቱሉ፣ ፋጡማ ሮባ፣ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ የገነኑ ስሞች ናቸው፤ አንድ ሰው እነዚህን የገነኑ ስሞች አጠፋህ ቢባል ሊገባን ይችላል፤ ዘለቀ ወርዶፋ፣ አየለ ተከስተ ስማቸው ጠፋ ቢባል፣ መጀመሪያ የሚቀርበው ጥያቄ እነማን ናቸው? ዱሮስ የገነነ ስም ነበራቸው ወይ? የሚል ይሆናል፤ ስለዚህ መሰላሉን ያልወጣውን ሰው ውረድ ቢሉት ትርጉም የለውም።Prof. Mesfin Woldemariam
ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ስም ነው፤ ዘርፈሽዋል ማናለብህ ስም ነው፤ ክቡር ፕሬዚደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ስም ነው፤ ታደሰ ክፍሎም ስም ነው፤ ደራርቱ ቱሉ ስም ነው፤ ውቢቱ ማስረሻ ስም ነው፤ አዜብ መስፍን ስም ነው፤ ቴዎድሮስ ካሣሁን ስም ነው፤ አበበ ቶላ ስም ነው፤ ሚካኤል በላይነህ ስም ነው፤ ሐጎስ በየነ ስም ነው፤ … እነዚህ ሁሉ ስሞች በመሆናቸው አንድ ቢሆኑም ከእያንዳንዳችን ጋር ባላቸው ግንኙነት ይለያያሉ፤ አንዳንዶቹን እናውቃቸዋለን፤ በተለያዩ መንገዶችም ቢሆን ከኑሮአችን ጋር የተያያዙ ስለሆኑ፣ ያስደስቱናል ወይም ያስከፉናል፤ ስለዚህም ሲያስደስቱን እናወድሳቸዋለን፤ ሲያስስከፉን እንወቅሳቸዋለን፤ ዋናው ጥያቄ የሚመጣው እዚህ ላይ ነው፤ ውቢቱ ማስረሻ፣ ዘርፈሽዋል ማናለብህ፣ ታደሰ ክፍሎም፣ አበበ ዋቅቶላ ማን እንደሆኑና ምን እንደሆኑ አላውቅም፤ ስለዚህ የነሱን ስም አንሥቼ የምደሰትበትም ሆነ የምከፋበት ምክንያት የለኝም፤ የኔ አይደሉም፤ የሚያስደስቱኝና የሚያስከፉኝ የኔ የምላቸው ናቸው፤ የኔ የምላቸው እነማን ናቸው? ወድጄም ሆነ ተገድጄ ጭንቅላቴ ላይ በእግራቸው የቆሙ ሰዎች አሉ፤ እኔ የኔ ባልላቸውም እነሱ የራሳቸው፣ ዕቃቸው አድርገውኛል፤ የምነቅፋቸውም ራሳቸውን የኔ ሳያደርጉ እኔን የነሱ ስላደረጉኝ ነው፤ ስለዚህም የኔ የሆኑት ሁሉ ሳወድሳቸው አይከፍሉኝም፤ ስወቅሳቸውም አይከሱኝም፤ ሳወድሳቸው ደስ የሚላቸውና የሚኩራሩት ስወቅሳቸው ለምን ይቆጣሉ? የማወድሳቸውም ሆነ የምወቅሳቸው የራሴን ጥቅም እያሰብሁ መሆኑን ሳይገነዘቡት ቀርተው ነው? ወደአራት ዓመት ግድም ሲሆነኝ ገና ጣልያን ሳይገባ አንዲት እግራቸው የማይንቀሳቀስላቸው አሮጊት ጎረቤት ነበሩ፤ ጠዋት ተሸክመው በር ላይ ያስቀምጧቸዋል፤ እንደልባቸው ሲለፈልፉ ይውሉ ነበር፤ በደንብ የማስታውሰው ‹‹ሠይፉ ዘለቀ … ተለቀለቀ! መስፍን ስለሺ ይበቃል ለሺ!›› እያሉ በየዕለቱ ይጮሁ ነበር፤ መስፍን ስለሺ የአራዳ ዘበኛ ሀነው በፈረስ ይታዩ ነበር፤ ሠይፉ ዘለቀ በድቅድቂት የሚሄዱ ነበሩ፤በኋላ አንደሰማሁትና ትንሽ ትንሽ እንደማስታውሰው ለጣልያን ገብረው ውርደት ደርሶባቸው ነበርና የአሮጊትዋ ትንቢት የያዘ ይመስላል፤ ለማናቸውም ሴትዮዋ ተከሰሱ ሲባል አልሰማሁም።
ከስድሳ ዓመታት ያህል በፊት በኒው ዮርክ አንድ ሰው በስም ማጥፋት ክስ መሠረተ፤ ፍርድ ቤቱ ከሱን ሲመረምር ከሳሽ ፖሊስ መሆኑን ተረዳ፤ ፖሊስ የሕዝብ አገልጋይ ነው፤ ስለሆነም በፖሊስ ላይ ከተገልጋዮቹ ሰዎች ትችት ቢቀርብበት የስም ማጥፋት አይሆንም፤ በተጨማሪም ዜጎች ሁሉ የማይገረሰስ ሀሳብን የመግለጽ መብት ስላላቸው፣ የሕዝብ አገልጋይ የሆነው ፖሊስ ስም እንዳይጠፋ ተብሎ ሕገ መንግሥታዊውን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት መገደብ አይቻልም በማለት የኒው ዮርኩ ፍርድ ቤት በየነ፤ ፍርድ ቤቱ በብይኑ ላይ አንድ መሠረታዊ ሀሳብን አስገነዘበ፤ ስም ማጥፋት የሚባለው በተራ ሰው ላይ ወይስ በሕዝብ አገልጋይ ላይ የተፈጸመ መሆኑን መለየት እንደሚያስፈልግ አመለከተ፤ በአገራችንም አጼ ቴዎድሮስ ወንድምዋን የገደሉባት ሴት በሄዱበት ሁሉ እየተከተለች ንጉሠ ነገሥቱን ስትሰድብ፣ በሆነ ባልሆነው ሁሉ ገደል የሚጨምሩትና በእሳት የሚያቃጥሉት ንጉሠ ነገሥት ይቺን በንዴት የተቃጠለች ሴት ምንም አላደረጓትም! አጼ ምኒልክንም አሞካሽቶ ገጣጣ ያላቸው ምንም የደረሰበት አይመስለኝም፤–
በሰማይ የሚጠድቅ በምድር ያስታውቃል፤
ከከንፈሩ ተርፎ ጥርሱ ጣይ ይሞቃል፤
በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በያመቱ በዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ውስጥ ንጉሠ ነገሥቱ በግጥምም በመፈክርም በጣም ይሰደቡ ነበር፤ አንድም ተማሪ በስም ማጥፋት ሲከሰስ አላየሁም፤ በሌላ መንገድ ቀጥተዋቸው እንደሆነም አላውቅም፤ ግን ብዙዎቹ ተመርቀዋል።
ከላይ የተገለጹት ሁሉ ስለግለሰቦች ነው፤ ሕጉ በግለሰቦች ላይም ቢሆን በኒው ዮርኩ ፍርድ ቤት ውሳኔ እንዳየነው፣ በኢትዮጵያም የወንጀል ሕግ አንቀጽ 612 የማያስቀጡ ትችቶችና ንግግሮች በሚል ርእስ ስር ተደንግጓል፤ በኒው ዮርኩ ፍርድ ቤት የምንገነዘበው የከሳሹን የመክሰስ መብት የሚገድብ ሲሆን፣ በወንጀለኛ መቅጫው ሕግ ደግሞ የምንገነዘበው ሊከሰስ የታሰበውን ተከሳሽ ያለመከሰስ መብት የሚገልጽ ነው፤ ሁሉም በግለሰብ ደረጃ መሆኑን ልብ እንበል።
የመንግሥትን ስም ማጥፋት የሚባል የሌለ ነገር ነው፤ ካለማወቅ የመጣ የሥልጣን ድፍረት ነው፤ ከላይ እንደተገለጸው በስም ማጥፋት ክስ ለመመሥረት ከስምም የገነነ ስም ያስፈልጋል፤ መንግሥት ምን ስም አለውና ስሙ ይጠፋል? የአጼ ኃይለ ሥላሴ ስም ይጠፋል፤ የመንግሥቱ ኃይለ ማርያም ስም ይጠፋል፤ የመለስ ዜናዊ ስም ይጠፋል፤ የመንግሥት ስም የሚጠፋው እንዴት ነው? ሦስቱም የተጠቀሱት ስሞች በአለፉት ሰባና ሰማንያ ዓመታት ውስጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተከታታይ የሚያያይዛቸው ሁኔታ ነበረ፤ ወይም ባህላዊ የፈረስ ስም እየሰጠናቸው ብንሄድ አባ ጠቅል፣ አባ ገልብጥና አባ ሰንጥቅ ልንላቸው አንችል ይሆናል፤ ፈረሱ አንድ ነው፤ ጋላቢዎቹ የተለያዩ በመሆናቸው እያንዳንዳቸው እንደየፍላጎታቸው ወይም እንደየተግባራቸው ለጋላቢዎቹ የወጣላቸው ስም ይለያያል፤ አባ ገልብጥ ከርፋፋ ነው ብንል በስም ማጥፋት ለመክሰስ የሚችለው ጋላቢው ነው ወይስ ፈረሱ? አባ ሰንጥቅ ተንጋሎ የተፋ ለራሱ ከፋ አንደሚባለው ያለ ጅልነት ያለበት ነው ብንል ከሳሹ ማን ሊሆን ነው?
ሕግን የጭቆና መሣሪያ ማድረግ የተጀመረው በወያኔ ዘመን ነው፤ ዓይን ባወጣ ውሸት ‹‹ሕገ መንግሥቱን ሕገ አራዊት ብሏል›› በማለት ፍርድ ቤትን አሳምኖ (ለፍርድ ቤት አስረድቶ አይደለም) በሐሰት ማስፈረድ የተቻለው በወያኔ ዘመን ነው፤ ሕጋዊ የፖሊቲካ ፓርቲ ስብሰባዎችን ‹‹መንግሥትን በኃይል ለመገልበጥ መዶለት›› ተብሎ እንደማስረጃ በግልጽ የተሠራውን ቪዲዮ ለፍርድ ቤት አቅርቦ ማሳመንና ማስፈረድ የተቻለው በወያኔ ዘመን ነው፤ በሰላማዊና ሕጋዊ የፖሊቲካ ትግል መንግሥትን ለመለወጥ መሞከር መንግሥትን በኃይል እንደመገልበጥ ተደርጎ የታየውና ክስ የተመሠረተበት በወያኔ ዘመን ነው።
አንድ ነገር በጋዜጣ ተጽፎ አደባባይ ሲወጣ ከሦስት ነገሮች አንዱ ወይም ሁሉም ይከሰታሉ፤ አንዱ የተጻፈው ሐሰት ነገር ሊሆን ይችላል፤ ሁለተኛ አስተያየቱ የማይወደድ፣ ብዙ ሰዎች የማይቀበሉት ይሆናል፤ ሊሆን ይችላል፤ ሦስተኛ አንድ ግለሰብን በሰብእናው ወይም በሥራው የሚጎዳ ሊሆን ይችላል፤ እንግዲህ የተባለው ነገር ሐሰት ከሆነና ሐሰት ነው የሚለው ሰው እውነትን ይዞ ከሆነ ሐሰትን ለማጋለጥ ከባድ አይሆንም፤ ሐሰቱን ከእውነቱ ጋር አጋፍጦ ቀልጦ እንዲጠፋና እውነቱ ጎልቶ እንዲታይ ማድረግ ነው፤ ትክክለኛ ዳኛ ካገኙ እውነትና ሐሰት በማስረጃ ይሸናነፋሉ፤ እውነቱ ከታወቀ በኋላ አደባባይ በወጣው ሐሰት ጉዳት ደርሶብኛል የሚለው ተራ ዜጋ ከሆነ ካሣ የመጠየቅ መብት ይኖረዋል፤ የሕዝብ አገልጋይ ከሆነ ግን ሆን ተብሎ ለመጉዳት በክፋት እንደተጻፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤ አንደኛው በዚህ ያልቃል።
ሁለተኛው የተነገረውን ወይም የተጻፈውን የአንድ ሰው አስተያየት በሕግ ወይም በግድ ማስለወጥ አይቻልም፤ በሕገ መንግሥቱ የተደነገገው ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የግል አስተያቱን ወይም እምነቱን ለገለጸው ሰው ይመክትለታል፤ የእኔ አስተያየት ከአንተ አስተያየት ወይም የእኔ እምነት ከአንተ እምነት ይሻላል ብሎ በሕግ ክርክር ለማሸነፍ አይቻልም፤ ከመቶ ሃምሳ ዓመታት በፊት ሚል የሚባል የእንግሊዝ ፈላስፋ እንዳለው የዓለም ሕዝብ በሙሉ ተሰብስቦ አንዱን ሰው አስተያየትህ ወይም እምነትህ ትክክል አይደለም ብሎ ሊረታው አይችልም።
ሦስተኛ የተባለው ነገር ግለሰብን በሰብእናው ወይም በሥራው ግልጽ በሆነ መንገድ ከጎዳውና ጉዳቱ ከተረጋገጠ፣ የተባለው ጎጂ ነገር በአደባባይ የተነገረው ሆን ተብሎ ለመጉዳት መሆኑ፣ ወይም ባለማወቅ፣ ወይም በስሕተት መሆኑ ተለይቶ መረጋገጥ አለበት፤ ካሣውም ሆነ የወንጀል ጥፋቱ ከዚያ በኋላ የሚወሰን ይሆናል።
ይህንን ሁሉ ከአልን በኋላ የመንግሥትን ስም ማጥፋት ወደሚለው ስንመለስ ከባድ የአስተሳሰብ ችግር ይገጥመናል፤ መንግሥት ከሕዝብ የተለየ ህልውና እንደሌለው አያከራክርም፤ በአንድ መንግሥት ስር የሚተዳደረው እያንዳንዱ ሰው ወደደም አልወደደም፣ ተቀበለውም አልተቀበለውም በዚያ መንግሥት ስር በመሆኑ የመንግሥቱ አካል ነው፤ ባዕድ አይደለም፤ ስለዚህም ግለሰቡ በመንግሥት ላይ የሚያቀርበው ነቀፌታም ሆነ ሐተታ ጉዳት ያስከትላል የሚባለው ለማን ነው፤ አገር የሚባለው ውስጥ ግለሰቡ አለ፤ ሕዝብ የሚባለው ውስጥ ግለሰቡ አለ፤ መንግሥት የሚባለው ውስጥ ግለሰቡ አለ፤ ስለዚህም የመንግሥትን አመራር የሚነቅፈው ግለሰብ የመንግሥትን ስም አጠፋ ማለት ድርብርብ ስሕተቶችን ያሳያል፤ በመጀመሪያ ነገር መንግሥት ከግለሰቡ የተለየ ህልውናም ሆነ ስም እንደሌለው አለመገንዘብ ነው፤ ሁለተኛም ግለሰቡ መንግሥትን፣ ሕዝብን፣ አገርን ከዚህም ሁሉ ጋር ራሱን ለማሻሻል በበጎ ፈቃድ ለበጎ ዓላማ የሚፈጽመውን ተግባር ወደክፋት መለወጥ አግባብ የለውም፤ ሦስተኛ የመንግሥት ስም ማጥፋት ብሎ ክስ መመሥረት አንድ መንግሥትን ዘለዓለማዊ አድርጎ በመገመት ክፉ ስሕተት መፈጸም ነው፤ በደርግ ዘመን የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ይሰደብ ነበር፣ ዛሬ ደግሞ በወያኔ ዘመን የአጼ ኃይለ ሥላሴና የደርግ አገዛዞች ይሰደባሉ፤ መንግሥት ዘለዓለማዊ አይደለም፤ ባለመሆኑም ይወቀሳል፤ ይነቀፋል፤ ይለወጣል፤ ይህንን ማድረግ የመንግሥት ባለቤት የሆኑት ዜጎች መብትና ሥልጣን ነው።
የመንግሥትን ስም ማጥፋት የሚለው የስጋት መግለጫ ዘዴ የአምባ-ገነን አገዛዞችና ሎሌዎቻቸው የሚያቀነቅኑት ማታለያና ማደናገሪያ ነው እንጂ ሕጋዊ መሠረት የለውም፤በማኅበራዊ ጉዳይ የእውነት ምንጩ ሕዝብ እንጂ መንግሥት አይደለም።
ግለሰቡ ራሱን ለመጉዳት አስቦ ጉዳት የሚያደርሰው በራሱ ላይ ነው ማለት ዋናውን ዓላማ መሳት ነው።

Breaking News] Serkalem Fasil Joins Ethiopia’s Exiled Journalists


Serkalem1-300x232
Awramba Times (Phoenix, Arizona) – Serkalem Fasil, award-winning Ethiopian journalist and former co-publisher of the weekly newspapers Asqual, Menilik, and Satenaw has left Ethiopia with her son yesterday.
According to our confidential sources, Serkalem has already departed to the United states and detail has not been given on the matter.
In November 2005, Serkalem was arrested along with thirteen newspaper editors including her husband, Award winning blogger, Eskinder Nega. Eskinder has been jailed seven times by the Ethiopian government and is still in prison under the nation’s sweeping anti-terror legislation. He has been convicted and sentenced to 18 years in June 2012 on trumped up terrorism and treason charges. Amnesty International, Human Rights Watch and CPJ have condemned the ruling as baseless and politically motivated.
Serkalem Fasil won a “Courage in Journalism Award” from the International Women’s Media Foundation in 2007.
Source:www.ethiopianrivew.com

አውራምባ ታይምስ የእስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል “ከእኛ እንደ አንዱ ሆነች” አለ!


July 25, 2013
Serkalem
አውራምባ ታይምስ የእስክንድር ነጋ ባለቤት ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል “ከእኛ እንደ አንዱ ሆነች” አለ!
አውራምባ ታይምስ ድረ ገጽ ታማኝ ምንጮቼ ነገሩኝ ሲል እንደነገረን ከሆነ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል አንድ ልጇን ናፍቆት እስክንድር ነጋን ይዛ አሜሪካ ገብታለች፡፡
ሰርካለም የዛሬ አመት ለባለቤቷ እስክንድር ነጋ የተሰጠውን አለም አቀፍ ሽልማት ለመቀበል አሜሪካ አቅንታ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ወደ አሜሪካ የሄደችው ላትመለስ መሆኑን አውራምባ ምንጮቼ ነግረውኛል ብሎናል፡፡ (በቅንፍም የእኛ ምንጮች ግን እስካሁን ምንም አልነገሩንም፡፡) ከቅንፍ ውጪ አውራምባን ለመረጃው እናመሰግናለን!  በአዲስ መስመር፤
መንግስታችን ሆይ…
ተከፍተን
ተገፍተን
ተሰደን
ተሳደን
ሄደን
ካገር ወጥተን
ሰፋልህ ሰፈሩ…
ሞላልህ አኬሩ…
ወይስ ይቀጥላል
እስክናልቅ ካገሩ…!?

በኦሮሚያ 10 ተጠርጣሪ ሙሰኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ተመዝብሯል
owwce


  • ተጠርጣሪዎቹ ሽፈራው ጃርሶ የሚመሩት ቦርድ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ናቸው
ከሙስና ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አሥር የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ባለፈው ሰኞ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡
ኮሚሽኑ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው ከእነዚህ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተጨማሪ፣  ሌሎች 15 የሥራ ኃላፊዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የፍርድ ቤት ማዘዣ አውጥቶ ፍለጋ መጀመሩን ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉት የኮንስትራክሽን ዕቃዎች ግዥና የመንግሥትን የፋይናንስ ሕግ ባልተከተለ መንገድ ኪራይ ፈጽመዋል በሚል ጥርጣሬ መሆኑን፣ የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለአንድ ዓመት ባካሄደው ጥናታዊ ምርመራ በዚህ የሙስና ወንጀል መንግሥትን በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ እንዳሳጣው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የኮሚሽኑ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር የዋሉት የክልሉ ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቢፋ በዳዳ፣ ምክትላቸው አቶ ጎዳና ዳባ፣ የፋይናንስ ቡድን መሪ አቶ ተሾመ አዱኛ፣ አቶ ተክሉ ተፈራ፣ የማኔጅመንት ኮሚቴ አባላት ወ/ሮ መስከረም ኤጀርሳ እና አቶ ግርማ ቂጣታ፣ የመጋዘን ኃላፊዋ ወ/ሮ ራሔል አሰፋና የክፍያ ሰነድ አዘጋጅዋ ወ/ሪት ሳምራዊት ግርማ፣ የጨረታ ኮሚቴ አባላት አቶ ዘለቀ ጎንፋና አቶ ዱላ ማሞ ናቸው፡፡
የኦሮሚያ ክልል ውኃ ሥራዎችና ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከተመሠረተ ሁለት አሥርት ዓመታትን ያስቆጠረ የክልሉ ግዙፍ የልማት ድርጅት ነው፡፡
ኢንተርፕራይዙ በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች ክልሎች የሚካሄዱ የመስኖ ግድቦችና የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶችን ግንባታ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንገዶችንና ስታዲየሞችን ከመገንባቱም በላይ፣ በፌዴራል መንግሥት የሚመራውን ለደዴሳ ስኳር ፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ግድብ በደዴሳ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡
ኢንተርፕራይዙ ሁለት ቢሊዮን ብር የተመዘገበና 500 ሚሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል ባለቤት ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ የሚተዳደረው በሥራ አመራር ቦርድ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት የሥራ አመራር ቦርዱን በመምራት ላይ የሚገኙት ቀደም ሲል የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትር በኋላም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የተፋሰስ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው ጃርሶ ናቸው፡፡
በጉዳዩ ላይ የክልሉን የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ታከለ እንኮሳ አስተያየት እንዲሰጡ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡ (ሪፖርተር)

Wednesday, July 24, 2013

ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሁለተኛ ዙር መዋጮ የመንግስት ሰራተኞች ፈቃደኛ አልሆኑም ተባለ

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው አመት የወር ደሞዛችን በአመት ከፍለናል አሁን ግን ዳግመኛ ለመከፈል አቅሙ ስሌለለን እና እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም  ስለማንችል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ገንዘብ ልንከፈል   የምንችለው ባገኘንበት  ጊዜ ብቻ ነው ” በማለት በአማራ ክልል የሚገኙ የመምህራን ማህበራት አስታውቀዋል፡፡
መንግስት ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከሰራተኛው ለመቁረጥ አቅዶት የነበረ ቢሆንም ፣  በክልል ቢሮዎች  ብቻ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት የመንግስት ሰራተኛች ”  የተሰጠን ቦንድ ይወሰድ እና ነጸ እንሁን ፤ 10 ፐርሰንት ብቻ ይቆረጥብን ፤ በልቼ ማደር ስላልቻልኩ ለሚቀጥለው ዓመት ይተላለፍልኝ” የሚሉ እጅግ በርካታ ደብዳቤዎች ለፍትህ ቢሮ ፤ ለሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ በግልባጭ እንዲያቀውቁዋቸው ተደርገው በሰራተኞች ቀርበዋል፡፡
የተወሰኑት ሰራተኞች ደግሞ  ” የልጆቻችንን መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ስላቃተን እና የትምህርት ክፍያ ስለበረታብን  ለብአዴን መዋጮ የሚቆረጥብን እንዲቆም እንጠይቃለን” የሚሉ ጥያቄዎችን አቅርበዋል።
የመንግስት አመራሮችም ” ያልተቸገረ የለም፣  ችግሩን ችላችሁ ገንዘብ እንዲቆረጥ ተስማሙ” በማለት ሰራተኛውን ለማሳመን ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ህዝቡ ግድቡን ለማስፈጸም የሚያበረከትው ድርሻ ትንሽ መሆኑንና አብዛኛው በመንግስት ወጪ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጃ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒሰትር የግድቡን እቅድ ይፋ ሲያደርጉ፣ ግዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ድጋፍ ይሰራል ማለታቸው ይታወቃል።

ESAT Daliy News Amsterdam July 24 2013 Ethiopia

http://www.youtube.com/watch?list=SPKH8s2pMt15IZDZcwCAx6FDPqOb31cnFn&v=a2ha3C9ZZdw

የፓርላማው ውይይት መታፈኑን በይፋ ያጋለጠው የኢቲቪ ጋዜጠኛ ከሥራ ተባረረ

(በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ እንደዘገበው)
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚ ተቋማት ኃላፊነት” በሚል ጥቅምት 23 ቀን
2005 ዓ.ም ያደረገውን ውይይት በኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በኩል ተቆራርጦና ተዛብቶ እንዲተላለፍ
ተደርጓል በሚል አንድ ዜና መዘገቡ ይታወሳል።
ይህን ዜና በሰንደቅ ጋዜጣ የህዳር 5 ቀን 2005 ዓ.ም ዕትም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን
ተወቀሰ” በሚል ርዕስ ከቀረበ በኋላ፤ በዚህ ዘገባ ላይ ተመድቦ የሠራው የቀድሞ የኢቲቪ ባልደረባ ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ ረቡዕ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም በጉዳዩ ላይ ለዝግጅት ክፍላችን ምላሹን ሰጥቷል።

ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ
(ፎቶ ከሰንደቅ ጋዜጣ)
እነዚህ ዘገባዎች ከተስተናገዱ በኋላ፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ለሰንደቅ ጋዜጣ መረጃ እንደሰጠና ሚስጢር እንዳወጣ
ተቆጥሮ የዲስፒሊን ክስ ቀርቦበታል። ኢ.ሬ.ቲ.ድ በዲስፒሊን ክሱ ላይ አራት ከፍተኛ የሥራ አመራሮች በምስክርነት
ዘርዝሮ አቅርቧል። የድርጅቱ የዲስፒሊን ኮሚቴ በከሳሽ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና በጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻ መካከል የክስ ዝርዝር እና የመልስ መልስ ደብዳቤዎች ሲያዳምጥ ከሰነበተ በኋላ ግንቦት 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በቁጥር ቴ02.1/131-304/02/8/ በተፃፈ ደብዳቤ ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ ከግንቦት 10 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ
ከሥራ የሚያሰናብተውን ቅጣት አሳልፏል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ባለቤትነት በጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ
ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደው ስብሰባ በመልካም
አስተዳደር፣ በተጠያቂነት፣ በሙስና ችግሮችና በመሳሰሉት ላይ ልዩ
ትኩረት በመስጠት የተካሄደ ሲሆን በዚህ ውይይት ላይ የኢፌዲሪ
ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የትምህርት ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን
ጨምሮ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ፣
በሚኒስትር ማዕረግ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ አባይ
ፀሐዬ፣ የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር
ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፣ የእምባ ጠባቂ ተቋም ዋና እምባ ጠባቂ ወ/ሮ
ፎዚያ አሚን፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን
ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን፣ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል
ከንቲባ አቶ አበባው ስጦታው እና ሌሎችም የሥራ ኃላፊዎች
ተገኝተው ነበር።
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የጠራውና የአስፈፃሚ አካላትና
የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናን በተመለከተ የተደረገው ውይይት፣
በዕለቱ በሥፍራው ባልነበረ ጋዜጠኛ ተገቢ ባልሆነ መልኩ
ተቆራርጦና ተዛብቶ ለሕዝብ መቅረቡ ትክክል እንዳልነበረ በይፋ
በመግለፁ ምክንያት ከሥራ የተሰናበተው የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ድርጅት ባልደረባ የነበረው ጋዜጠኛ አዲሱ
መሸሻን ስለሁኔታው ፋኑኤል ክንፉ አነጋግሮታል።
ሰንደቅ፡- የዚህ ዜና መነሻ አንተን አድርገው ለመውሰድ ያስቻላቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህን ምላሽ መስጠት የሚችሉት እነሱ ናቸው። በሰጡኝ የክስ ዝርዝር ላይ ግን ሌላ ምክንያት ነው
ያስቀመጡት። ወይም ደግሞ ላነሳኸው ጥያቄ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችለው የዚህ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ብቻ ነው።
ሰንደቅ፡- እንዴት?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም “ኢቲቪ የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ” ለሚለው ዜና መነሻ
ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በእኔ በኩል ያልኩትም አንዳች ነገር የለም። እንደማንም አንባቢ ይህ ዜና በሰንደቅ
ጋዜጣ ከወጣ በኋላ ነው የተመለከትኩት። ስለዚህም መረጃ ከእኔ አግኝታችሁ ከሆነ አግኝተናል፤ ካላገኛችሁ አላገኘንም
ለሚለው ምላሽ መስጠት የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ይመስለኛል።
ሰንደቅ፡- በርግጥ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ለዚህ ዜና መነሻ መረጃውን ያገኘው ከሌላ ሶስተኛ ወገን መሆኑን
ማረጋገጥ እንችላለን። ሆኖም ግን ይህ ዜና በወጣ በሳምንቱ ህዳር 12 ቀን 2005 ዓ.ም. እርሶ ለሰንደቅ ጋዜጣ
ማስተባበያ መስጠትዎ የሚታወስ ነው። በወቅቱ ከዜናው ጋር በተያያዘ ለምን ማስተባበል ፈለጉ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል የሕዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት ያዘጋጀውን ፕሮግራም የቀረጽኩት እኔ በመሆኔ ነበር። በሰንደቅ ጋዜጣም የተሰራው ዜና “የባለስልጣናት ድምጽ
ታፈነ” የሚል በመሆኑም ጭምር ነው። ከዚህ አንፃር እንደአንድ ጋዜጠኛ ውይይቱን አፈነ ተብሎ መወንጀል በጣም
አደገኛ ነው። እንዲሁም ማንስ አፈነው? እንዴት ታፈነ? ለሚሉት ጥያቄዎችም ምላሽ የሚፈልጉ መሆናቸው ግልፅ
የሆነ ነገር ነው። በተለይ በውይይቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩትን ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ኃላፊነት ታሳቢ
ስታደርግ በእኔ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን ድንጋጤ መገመት ከባድ አይደለም። የእነዚህን ከፍተኛ ባለስልጣናት
አንደበትን ለማፈን በእኔ በተራ ረዳት አዘጋጅ ቀርቶ በሌላው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የሚሞከር ተግባር ተደርጎ
የሚወስድ አካል ያለ አይመስለኝም።
ይህ ችግር ከተፈጠረ በኋላም ከስራ ባልደረቦቼ ጋር ተወያይቻለሁ። እንዲሁም አንድ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር
ለማግኘት ጥረት ባደርግም አልተሳካልኝም። የሆኖ ሆኖ ከባልደረቦቼ ጋር ከመከርኩ በኋላ ፕሮግራሙ ታፍኗል ብሎ
ለዘገበው ጋዜጣ ማስተባበያ በመስጠት እራሴን ከጉዳዩ ነፃ ማድረግ እንዳለብኝ ተማምነናል። የመንግስት ከፍተኛ
ባለስልጣናቱም እኔ አለማድረጌን ሊገነዘቡ የሚችሉት ፕሮግራሙ ታፍኗል የሚለውን ዜና ባሰራጫው ሚዲያ መሆኑ
አሻሚ አይደለም። ስለዚህም በዚህ ጉዳይ ላይ ንፁህ መሆኔን ለማረጋገጥ ለሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በጉዳዩ ላይ
ያለኝን መረጃ ለመስጠት ተገድጃለሁ።
ሰንደቅ፡-እርሶ እንደዚህ ቢሉም፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ታህሳስ 01 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ
ደብዳቤ የዲስፕሊን ኮሚቴው “አቶ አዲሱ መሸሻ በየነ በፕሮግራሙ ኢ.ሬ.ቴ.ድ የባለስልጣኖች ድምጽ አፍኗል።
ፕሮግራሙ ቆራርጧል የሚል የተሳሳተና ከኃላፊነት የራቀ እና በሀሰት የተሞላ መግለጫ ለሰንደቅ ጋዜጣ” ሰጥቷል ሲል
ይከሳል። በዚህ ላይ የእርሷ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት የኢ.ሬ.ቴ.ድ “የከፍተኛ ባለሥልጣናትን ውይይት በማፈን ተወቀሰ”
ያለው ሰንደቅ ጋዜጣ እንጂ እኔ አዲሱ አይደለሁም። በወቅቱም በሰጠሁት ማስተባበያ ተቋሙን በተመለከተ ያልኩት
አንዳች ነገር የለም። የማፈን ነገር ተፈጽሟል ከተባለም ግለሰቡ እንጂ ተቋሙ ሊሆን አይገባም በማለት ነበር ተቋሙን
የተከላከልኩት። በሌሎችም ተቋማት ግለሰቦች ከተቋሙ ዓላማ በመውጣት የሚፈጽሙት ስህተት በእኛም ተቋም
በተመሳሳይ ሁኔታ ተፈጽሟል። ይህ ማለት ግን ግለሰቦች ከተቋም በላይ ናቸው ማለት አይደለም። ስለዚህም ግለሰቦች
በሰሩት ጥፋት በግል መጠየቅ አለባቸው እንጂ በተቋም ደረጃ ስህተቱ ሊታይ አይገባም። ስለዚህም አንድ ሰው በራሱ
መነሻ በፈጸመው ተግባር የተቋም አድርጎ መውሰድ ከሕግም ከሞራልም አንፃር የሚያስኬድ አይመስለኝም።
ሰንደቅ፡- የተከሰስክበት የደብዳቤ ይዘት ሚስጥር በማውጣት የሚል ነው። የሰጠኸው ማስተባበያ ከሚስጥር መጠበቅ
ጋር እንዴት ትገልፀዋለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ ደረጃ ሚስጥር ማባከን ከመጥፎ ፍላጎት (intention) የሚመነጭ ነው። ሚስጥር
የሚባክነው ተቋምን ወይም ግለሰብን ለማጥቃት ከመፈለግ የሚመጣ ክፉ መንፈስ ነው። ከዚህ አንፃር ስትወስደው፣
እኔ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ የሰራሁትን ፕሮግራም የሚመለከት ዜና በመሰራቱ ብቻ ማስተባበያ ሰጠው እንጂ ምን
አጠፈሁ። ከእኔ ጋር ተያያዥነት ያለው ዜና ባይወጣ እኔም ባልተናገርኩ፤ እነሱም ክስ ያሉት ክስ ባልመሰረቱብኝ ነበር።
ስለዚህም የጋዜጠኝነት ሙያዬን (integrity) በሚያጠፉ “አፋኝ” ተብሎ በተሰየመ ሁኔታ ስሜ ጠፍቶ፣ ስሜን
ለመመለስ መከላከሌ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ከሚስጥር ማባከን ከመጠበቅ ጋር ምን ያገናኘዋል?
ሁለተኛው፣ “የዴሞክራሲ ተቋማት ሚናና የአስፈፃሚው ተቋማት ኃላፊነት” በሚል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የተካሄደው ውይይት ዋናው ዓላማው፣ ውይይቱ ለሕዝብ እንዲቀርብ ነበር። ተደራሽነቱም ለሕዝቡ ነው። ለሕዝቡም
ግልፅ መረጃ ለማቅረብ የተዘጋጀ ውይይት ነበር። ከሁሉ በላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው የስብሰባ ይዘት፣
የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋ በዚህች ሀገር ውስጥ የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ ለሕዝብ ማሳየት ነበር። ሕዝቡም አደጋውን
በመረዳት ከመንግስት ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ግንዛቤ ለማስጨበት ያለመ ስብሰባ ነበር። ይህ ታዲያ
ምን ሚስጥር አለው? ሚስጥር ከሆነ መጀመሪያውኑ ሚዲያውን አይጋብዙም ነበር። በወቅቱም ፕሮግራሙ ሲቀረጽም
ሚስጥር ነው ያለ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን አልነበረም።
ሌላው በዚህ ተቋም ውስጥ በቆየሁበት የስራ ዘርፎች ሚስጥር ተብለው የሚቀረፁ ስራዎችን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
በሚስጥር ደረጃ የተቀረፁ ስራዎችንም ሰርቼ አውቃለሁ። በዚህ ደረጃ የሰራኋቸውን ስራዎች እንኳን ለሶስተኛ ወገን፣
በተቋሙ ውስጥ ማወቅ ከሚገባቸው ሰዎች ውጪ ዉይይት አድርጌም አላውቅም። አለቆቼም ይህን ጠንቅቀው
ያውቁታል።
ሰንደቅ፡- የዲሲፕሊን ኮሚቴው እንደሚለው ከሆነ “በስሜት ያደረኩት ነው” ሲሉ አቶ አዲሱ በኢዲቶሪያል ስብሰባ
ላይ ገልጸዋል ይላል። በዚህ ላይ የእርስዎ አስተያየት ምንድን ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በነገራችን ላይ የነበረው ኢዲቶሪያል ስብሰባ በአዋጅ ከተሰጠው ስልጣን ብዙ ርቆ የሄደ ነው። ግልፅ
የፖሊስ ምርመራ ነበር የተደረገብኝ። አስራ አራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ባሉበት የተደረገ ስብሰባ ሲሆን አውጣ፣
አታውጣ የሚሉ ጥያቄዎች ነበሩ። እኔ ለማስፈራራት፣ ለማሸማቀቅ የተደረገ ኢዲቶሪያል ስብሰባ ነበር። የቀረበብኝ
ውንጀላ እስከሀገር ክህደት የሚደርስ መሆኑ ነበር የተነገረኝ። የፖለቲካ ይዘት ፈጥረውለት እኔ አንገት ለማስደፋት
በአደባባይ ውጣና ማስተባበያ ስጥ ብለውኛል። የሚገርመው እኔ ነኝ ፕሮግራሙን የቆረጥኩት ያለው አመራር በዚህ
ስብሰባ ውስጥ አንዱ ወቃሽ ሆኖ የተገኘበት ነበር።
ሰንደቅ፡-በዚህ ስብሳባ ደረሰብኝ የሚሉት ጉዳት አለ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- አለ እንጂ። ከዚህ በፊት የኢዲቶሪያል ስብሳባ የምናደርገው አየር ላይ የዋሉ ፕሮግራሞችን ጠንካራና
ደካማ ጎናቸውን ለመገምገም ነው። ከዚህ ዜና ጋር በተያያዘ የተደረገው ኢዲቶሪያል ግን መንፈሱን የተለየ ነው። የአንድ
ተቋም ኃላፊዎች ተሰብስበው የፖሊስን ስራ በመተካት ያን ሁሉ ወከባ ማስፈራራት ሲፈጥሩ መመልከት በጣም አሳዛኝ
ተግባር ነው። በእኔ ውስጥ የፈጠረው ስሜት ለረጅም ጊዜ ውስጤን ጎድቶታል። በተለይ የኢ.ሬ.ቴ.ድ ተጠሪነቱ ለህዝብ
ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑ ይታወቃል። የምክር ቤቱን ውይይት መቁረጡን በግልፅ መናገሩን ሳይፈራ፣ ለምን እኔን
ውይይቱ ተቆርጧል ብልሃል ብሎ ከስራ ሊያሰናብተኝ እንደፈለገ አልገባኝም።
ሰንደቅ፡-በታህሳስ 01 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው ወጪ በሆነው ደብዳቤ ላይ “ፕሮግራሙን ያዘጋጁት
ባልደረባችን አቶ አዲሱ መሸሻ” የሚል ሲሆን፣ በጥር 20 ቀን 2005 ከዲሲፕሊን ኮሚቴው የወጣው ደብዳቤ
በበኩሉ “ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ” ናቸው ይላል። ከዲሲፕሊን ኮሚቴው በዚህ
መልኩ ደብዳቤዎቹ ሊዘጋጁ ቻሉ? ፕሮግራሙን የሰራው ማነው ሊባል ይችላል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ዲሲፕሊን ኮሚቴው ያወጣው ደብዳቤ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ነው። ለክሱ እንዲረዳቸው አንድ
ደብዳቤ በእኔ አዘጋጁ። ለመከላከል እንዲረዳቸው ደግሞ ፕሮግራሙን ከ90 በመቶ በላይ የሰራው አቶ ሳሙኤል ከበደ
ናቸው የሚል ደብዳቤ አዘጋጅ። ይህ በራሱ የሚነግርህ ነገር አለ። በማኛውም ዋጋ እኔ መክሰስ እና ከስራ ማፈናቀል
ለዲሲፕሊን ኮሚቴው የተሰጠው ተልዕኮ ነው። አቶ ሳሙኤል በወቅቱ ትምህርት ላይ ነበሩ። እንዴትም እንደመጡ
አላውቅም።
እውነቱ ግን ጥቅምት 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ቅዳሜ ፕሮግራሙን ሰርቼ ሙሉ ዝግጅቱ እሁድ ጥቅምት 25 ቀን
2005 ዓ.ም. ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ዜና በኋላ የሚቀርብ መሆኑ ነው። በዚህ ዕለት የሚተላለፍ መሆኑን የሚገልፅ
ከውይይቱ የተወሰዱ አጫጭር ንግግሮች የሚያሳይ ማስታወቂውን /ስፖት/ የሰራሁትም እኔው እራሴ ነኝ።
ሰንደቅ፡- አሁን በዚህ መልስ በእርሶ ላይ የተወሰደው እርምጃ በሌላው ሰራተኛ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን
ነው?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ይህ ጥያቄ ከነሳህልኝ በውይይቱ ላይ አንድ የተሰነዘረ ነጥብ ልንገርህ። በዚህ ውይይት ከተሳተፉት
ተሳታፊዎች መካከል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ዓሊ ሱሌማን አንዱ ናቸው። እሳቸው
ከገጠማቸው አስቸጋሪ የፀረ-ሙስና ትግል ሲገልፁ፤ “የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚታገሉ እና የሙስና
ተግባራትን የጠቆሙና ያጋለጡ ሰዎች በአለቆቻቸው የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እየተወሰዱባቸው ቤሰቦቻቸው
ተበትነዋል። በዚህም የተነሳ እነዚህ ግለሰቦች ምነው ይህን ባልተናገርኩ እያሉ አንገታቸውን ደፍተው ተሸማቀው
እየሄዱ ነው። እነዚህ ሃይሎች ገነው ወጥተው ለፀረ-ሙስና ትግል የተሰለፉ ኃይሎች ግን አንገታቸውን ደፍተው
ይገኛሉ” ነበር ያሉት።
ሰንደቅ፡- አሁን እርሶ ላይ የደረሰውን ነገር ከዚህ ከአቶ አሊ ሱሌይማን አባባል ጋር እንዴት ያስታርቁታል?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የኮሚሽነሩን አስተያየት በእኔ ላይ መፈጸሙን ስመለከት በጣም አስገርሞኛል። ምክንያቱም
በውይይቱ ላይ ተገኝቼ የቀረጽኩት ውይይቱን ለሕዝብ ለማቅረብ እንጂ፣ በዚህ የውይይት ፕሮግራም መቆራርጥ መነሻ
እና በመልካም አስተዳደር ዕጦት ሰለባ ለመሆን አልነበረም። የሆነው ግን በእውነት አስገራሚ ነው። ከስራ
ተፈናቅያለሁ። ልጆቼን ለጊዜው ለወላጆቼ ሰጥቻለሁ። ባለቤቴን ከፍዬ ነው፤ የማስተምረው። የፓርላማውን ውይይት
በፈለጉት መንገድ የቆረጡት ግን ደረታቸውን ነፍተው ለእኔ የስንብት ደብዳቤ ፅፈው ሰጥተውኛል። ኮሚሽነሩም ያሉት
ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሂደቶች ነበር። ለእሳቸው አስተያየት ከእኔ በላይ ማረጋገጫ ማን ሊያቀርብ ይችላል?
እዚህ ላይ ማወቅ ያለብህ በጋዜጣችሁ ዝግጅት ክፍል ይህን እድል አግኝቼ ለመናገር ቻልኩ እንጂ ስንቶቹ የሆዳቸውን
ይዘው የቢሮክራቶች ሰለባ ሆነው ቁጭ ማለታቸውን መዘንጋት የለብንም።
ሰንደቅ፡- ተጠሪነታችሁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። አሁን ደርሶብኛል የምትለውን የመልካም አስተዳደር
ችግር በአካል ሄደህ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባህል፣ የቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
ያመለከትከው ነገር የለም?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- በመጀመሪያ የወሰድኩት እርምጃ እራሴን ማረጋጋት ነበር። በዚህ ጉዳይ አንተ ሶስተኛ ወገን ስለሆንክ
እንጂ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ ድፍረት የተሞላበት ነው። መዋሸት የማልፈልገው ከስራ ተሰናብተሃል የሚለውን
ውሳኔ ስሰማ ደንግጫለሁ።
ሰንደቅ፡- ለምን?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- ምክንያቱም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠራው ስብሳባ ታማኝ ባለመሆኑ ይቅርታ መጠየቅ
የነበረበት ኢ.ቴ.ሬ.ድ ነው። ይህን የምለው የእኛ ተቋም አስፈፃሚ መስሪያቤት በመሆኑ ተጠሪ ለሆነበት ተቋም በሰራው
ስህተት ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል የሚል እምነት ስለነበረኝ ነው። የሆነው ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት
በአግባቡ አልተስተናገደም የሚል መከራከሪያ ባነሳሁት ግለሰብ ላይ፣ የስራ ስንብት ደብዳቤ ሲሰጥ ምን ሊሰማህ
ይችላል። እንደዚህ ዓይነት ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንዴት ይወስዳሉ ብለህ ትገምታለህ። ስለዚህም ግራና ቀኙን
ለመመልከትና የተፈጠረብኝን ጫና ለመርሳት ወደ ሆነ ቦታ ዞር ማለትን ነበር የመረጥኩት።
ሰንደቅ፡- ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ምን ትጠብቃለህ?
ጋዜጠኛ አዲሱ፡- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ከእኔ ስራ መፈናቀል በላይ አጀንዳ ያለው
ይመስለኛል። ምክንያቱም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ተቋም፣ በምን ምክንያት ውይይቱን ሊቆርጠው
ይችላል? ውይይቱ መቆረጡንም ምክር ቤቱ ያውቃል። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ምክር ቤቱ ውይይቱ እየተቆራረጠ
መቅረቡን እንደሚያውቅ እየታወቀ፣ ለምን የሃሰት መረጃ እንዳቀረብኩ ተቆጥሮ ከስራ ገበታዬ እስናበታለሁ?
የፓርላማው ውይይት በትክክል አለመዘገቡን በመቃወም ምላሽ መስጠቴ ዋጋው ከስራ መሰናበት ከሆነ፣ ከእኔ የስራ
ዋስትና በላይ ፓርላማው ሊመለከተው የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህን መሰል ብልሹ የመልካም አስተዳደር ከተለመደ
ተቋሙም ወዴት እየሄደ እንደሆነ ቆም ብሎ ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።¾
(ምንጭ፡- ሰንደቅ ጋዜጣ 8ኛ ዓመት ቁጥር 411 ሀምሌ 17/2005)