Sunday, June 9, 2013

የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች**

ኢትዮዽያውያን በየመን
በአመት 500ሺ የሚጠጉ ኢትዮጲያውያን አገራቸውን ጥለው ወደ አረብ አገራት እየተሰደዱ እንደሆነ አምባገነኑ መንግስት አመነ። ኢህአዴግ አገራችን አድጋለች ልማት ላይ ነች እያለ 24 ሰአት ቢለፈልፍም እውነታው እንደሚያስረዳው ወጣቱ በሃገሩ ውስጥ ለመኖርም ሆነ ለመስራት በርካታ ችግሮች ያለበት በመሆኑ ስደትን እንደ ዋንኛ መፍትሄ ይዞታል። በህጋዊ መንገድ ብቻ በቀን 1500 ኢትዮጲያዋያን እየተሰደዱ እንደሆነ በስደት ላይ የሚያተኩር ስብሰባ ላይ የተጠቆመ ሲሆን በደቡብ ኢትዮጲያ የሚገኙ ወላጆች ልጆቻቸውን ሲመርቁ “ደቡብ አፍሪካ ያስገባህ!” እንደሚሉም ተነስቶአል። በዚሁ ጉዳይ ላይ በገጠሩ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችም ሳይቀር ትምህርታቸውን እያቋረጡ ስደትን የመረጡ ሲሆን በገጠሩ ክፍል የወጣቶች ቁጥር እጅግ በሚያሰጋ መልኩ እየቀነሰ እንደሆነ ታውቋል። ወደ ውጪ ከሚካሄደው ስደት በተጨማሪ ወደ ከተሞች የሚተመው ወጣት ጉዳይ መላ ካልተባለ ወደፊት የእርሻ ስራዎችን የሚሰራ ሰው እጥረት አጋጥሞ የግብርና ምርት ውድቀት እንደሚከሰት እየተነገረ ነው።
———
በአባይ ጉዳይ ከግብጽ ጋር ግጭት ውስጥ የገባው አምባገነኑ ኢህአዴግ አጋጣሚውን በመጠቀም ሃገር ወዳድ ለመምሰል እየተሯሯጠ ይገኛል። ኤርትራን እያጨበጨበ ያስገነጠለው እና በኋላም ከሻቢያ ጋር በተደረገ ውጊያ በርካቶች የሞቱለትን ባድመን አሳልፎ የሰጠው አምባገነኑ ቡድን አሁን የሌ የጦርነት ከበሮ እየደለቀ ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ ይገኛል። የሰው መብት እየተጣሰ፣ ህዝቦች በዘራቸው ምክንያት ለአመታት ከኖሩበት እየተፈናቀሉ ልማት ብላችሁ አትድረሱብን በሚል ከዲያስፖራው ሰሚ ያላገነው አምባገነኑ ኢህአዴግ ይችን ግጭት ተጠቅሞ ገንዘብ ለመሰብሰብ እየተዘጋጀ ነው። እንደሚታወቀው የግድቡን ሲሚንቶ የወያኔው መሰቦ ካለ ተወዳዳሪ እንዲያቀርብ እንደተደረገ ይታወቃል።

በመረጃ የዳበረ ህዝብ አምባገነኖችን ቀባሪ ነው!!
#ፀረአምባገነን

No comments:

Post a Comment