Thursday, June 6, 2013

ከ”ሻብያና ኦነግ ወደ “ግብፅ ጦርነት እየተፋጠነ ነው ?


እኔ እንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ የአባይን መገደብ እደግፋለው እንዲያውም ከሀይድሮኤሌክትሪክ ግድብ በተጨማሪ አባይን ለመስኖ ብንጠቀመው በምግብ እራሳችንን ለመቻል ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ያስገኛል ብለው ከሚያምኑት ወገን ነኝ።የጀብሀን፥ሻብያንና የወያኔን የኋላ ታሪክ ስናጠና ከምስረታቸው ጀምሮ አረብ ሀገሮችን በማስተባበር የጦርመሳሪያና ስንቅ ስትረዳቸው የነበረችው ግብፅ ነበረች።በናይል ወንዝ አለኝ ከምትለው ህገወጥ የይገባኛል ጥያቄ የተነሳ ኢትዮጵያን በተመለከተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲይዋን የቃኘችው “ከማዳከም አንፃር መሆኑ” ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነውና አዲስ ክስተት አይደለም ።ሀገርን በማስገንጠል እና በበርካታ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጥቅም በተፃፃሪ በመቆም ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን ሲያሳየን የኖረው ሟቹ አምባገነን መለስ ዜናዊ “አባይን ለመገደብ” ሲያስብ በአንድ በኩል እየተስፋፋ የነበረው የአረቡ አለም አብዮት ኢትዮጵያ ገብቶ ስልጣኔን አጣለሁ ከሚል ስጋት ፤ግድቡ ባይሰራ እንኳን ከሁለት አስረት አመታት በላይ ተወዝፎ የኖረ መሪ ስለነበር የታሪክሽሚያ በማድረግ የበታችነት ስሜቱን ይሞላለት ዘንድ “አባይን የደፈረ መሪ ” እየተባለ በሚጠላው ሕዝብ ላይ ለመኮፈስ ፤ ከእያንዳንዱ “ልማት” ጀርባ ኢፈርትና ህወሀታዊ ነጋዴዎችን መጥቀም ስትራቴጅው ስለሆነ ከፕሮጀክቱ ጀሌዎቹን ተጠቃሚ ማድረግ ፤ መርዘኛው አላማ ግን በሀገር ውስጥ ፖለቲካ ሻቢያ መጣባችሁ፥ኦነግ ሊበላችው ነው፥ አሸባሪዎች በፈንጅ ሊጨርሷችሁ ነው፥ግንቦት ሰባትና ሌሎች ድርጅቶች በሻብያ እየተረዱ ነው አይነት ፕሮፓጋንዳዎች በህዝቡ ውስጥ የተፈለገውን ውጤት አላመጣ ብለው “አሸባሪነት” ማላገጫ መሆኑን ሲገነዘቡ እውነተኛዋ ግን አደገኛዋ ጠላታችን ግብፅ ጋር “የአባይ ግድብ” ከስራው ይልቅ ፕሮፓጋንዳውን በማጦዝና ግብፃውያንን በማስቆጣት የጦርነትነጋሪት እንዲጎስሙ በመገፋፋት አንድም ለውጭ ወራሪ ሁሌም አንድ የሚሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብን ድጋፍ ለማግኘት መሞከር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የስርዓቱን ተቃዋሚዎች “በአሸባሪነትና በሻብያ እረዳትነት መፈረጅ”ለውጥ አለማምጣቱን ስለተረዱ “ጠንከር ጠንከር ያሉትን ተቃዋሚዎችን” በግብፅ ይረዳሉ ብሎ በማናፈስ በሕዝብ እንዲተፉ ማድረግ አብይ ምክንያቶች ይመስሉኛል።ለዚህም ነው ገና ተግባር ላይ ሳይውል “Project X” ሲባል ነበር የተባለውን የአባይ ግድብ እያንዳንዷን ጥቃቅን ነገር በማጉላት ከግብፅ ጋር እሰጣገባ መግባት እንደስትራቴጅ የታየው አንድ ግድብ ሲገደብ የወንዙን አቅጣጫ ማስቀየር ተራና የተለመደ ክስተት ሆኖ ሳለ “አባይ ተቀየሰ” የሚለው ዜና ሆን ተብሎ የሚዲያ ትኩረት እንዲያገኝ በማድረግ ግብፆችን አስቆጥተው “መጡባችው” የሚለው ፕሮፓጋንዳ አየሩን የሞላው። እንደ እውነቱ ከሆነ የግብፅ መንግስትና ወያኔ በጋራ እየሰሩ የሁለቱ ሀገር ሕዝቦች በየመንግስቶቻቸው ያላቸውን ቅሬታ በጋራ እያስቀየሱ ያሉ ይመስለኛል ስለዚህ ጦርነትም አይኖርም ግድቡም “እየተፋጠነ ነው” የሚለውን ዜና ለሚቀጥሉት “ብዙ” አመታቶች እንሰማለን።
ሀና መታሰቢያ 28/09/05

No comments:

Post a Comment