Friday, June 7, 2013

የተለያዩ የግል ተቋማት የህክምና ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ


ኢሳት ዜና:-ከ14 የግል ኮሌጆች የተሰባሰቡ 5 ሺ የሚጠጉ ተማሪዎች ትናንት ሰኔ 27፣ 2005 ዓም የትምህርት ማቆም አድማ በማድረግ ወደ ትምህርት ሚኒስቴር አምርተዋል።
የትምህርት ሚ/ር ባለስልጣናትም ተማሪዎቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቀው ፣ ተማሪዎቹ የትምህርት ሚኒስቴርን ግቢ ለቀው ካልወጡ በፖሊስ ተገደው እንደሚወጡ ሲነገራቸው ተወካዮችን ወክለው መሄዳቸው ታውቋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናትም ተማሪዎች ላቀረቡት ጥያቄ ለዛሬ መልስ እንደሚሰጡ በመግለጻቸው ተማሪዎች ግቢውን ለቀው ወጥተዋል።
ይሁን እንጅ ተማሪዎችን በመወከል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር ያቀናው ተማሪ ፣ ዛሬ መልሱን ይዞ ይመጣል ተብሎ ሲጠበቅ ቢውልም ፣ ሳይመለስ ቀርቷል።
ተማሪዎች  በተደጋጋሚሚ ስልክ ቢደውሉለትም ሊያገኙት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።
ተማሪዎቹ ያቀረቡት ጥያቄ መንግስት የክሊናክል ነርስ ተማሪዎችን በተመለከተ በድንገት ያወጣው  አዲስ መመሪያ ተማሪዎችን ለከፍተኛ ወጪ የሚዳርግ በመሆኑ ይቀየርልን የሚል መሆኑን አንድ የነርሲንግ ተማሪ ለኢሳት ገልጻለች
በጉዳዩ ዙሪያ የትምህርት ሚኒስቴር ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

No comments:

Post a Comment