Thursday, January 9, 2014

ከመር የሱፍ የተባለው የኦሮመኛ ዘፋኝ ሚኒሊክን የአፍሪካ ሂትለር በማለት አዲስ ዜማ አወጣ

ከመር የሱፍ በሚኒሊክ ዙሪያ ዜማ እንደሚያወጣ በቅርቡ ዜናችን ማስነብባችን ይታወሳል::በዚህ ሳምንት ብቻ ከአዲስ አበባ ጸረ ሚኒሊክና ቴዲ አፍሮ መልእክት ያላቸው ዜማዎች ተለቀዋል  :: የከመር የሱፍን  ethiotube.net  የሙዚቃ ክሉቡን በድህረገጹ Kemer yesuf is back   በማለት አውጥቶታል:: ethiotube ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቴዲና ሚኒሊክ  ላይ በሚካሄደው ዘመቻ ላይ ከኦሮሞ ፈርስት ከሚባለው ዘረኛ ድርጅት ጋር መቆሙን በተደጋጋሚ አስመስክርዋል::ጃዋር መሀመድ ኢትዮቱዩብ አምስተኛ አመቱን ሲያከብር የክብር እንግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው::
ethiotube-anti-teddy-afro 
ባለፈው በአብዲ ፈቲ የተባለ የኦሮሞ ፈርስት አባል የተሰራውን  የቴዲን ስም እንዲሁም  በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች   አይን ያወጣ ስድብና ዘለፋን ያካተተን video   “ቴዲን አጋለጠው “በሚል አጋነው ምስሉን ድህረገጻቸው ላይ ፖስት ማድረጋቸው ሚታወስ ነው::

No comments:

Post a Comment