Thursday, January 30, 2014

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ

ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

coup map


በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡
forecast-dot-2014በቀዳሚነት የመፈንቅለ መንግሥት የሚያሰጋቸው አገራት ጊኒ፣ ማዳጋስካር፣ ማሊ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኒጀር፣ ጊኒ ቢሳው እና ሱዳን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፑብሊክና ደቡብ ሱዳን ናቸው፡፡ ከአውሮጳ ምንም አገር በዝርዝሩ ውስጥ ያልገባ ሲሆን ዩክሬይን አደጋው ጥላ ካጠላባቸው በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሆናለች፡፡ ከወደ አሜሪካ ዩኳዶርና ሃይቲ ቀዩ የአደጋ ምልክት የታየባቸው ሲሆን ከእስያ ታላንድ፣ አፍጋኒስታን እና ፓኪስታንን ጨምሮ ስድስት አገራት የመፈንቅለ መንግሥት የቀይ ምልክት አደጋ ካለባቸው 40 አገራት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
ከ40ዎቹ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ 25ኛ ላይ ትገኛለች፡፡ በየጊዜው የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ህወሃት/ኢህአዴግ ሥልጣኑን ለራሱ ታማኞች ብቻ በመከፋፈል እንዲያም ሲል በቤተሰብ ደረጃ በማውረድ እየሸነሸነው በመሆኑ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የበይ ተመልካች ሆኗል፡፡ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ሰሞኑን ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ አዲስ አድማስ ሲዘግብ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን እና የነጻው ሚዲያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቁን ገልጾ ነበር፡፡
አፋኝ ሕጎችን በማውጣትና ማንኛውንም ዓይነት የግለሰብ መብት በመንፈግ በአንጻሩ ሊኖር የማይችል የቡድን መብት አስከብራለሁ የሚለው ህወሃት/ኢህአዴግ በተመሳሳይ የሚወጡ መረጃዎችን በማጣጣል ዋጋ ቢስ ሲያደርግ መቆየቱን የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡ በተቀረው ደግሞ “ልማት፣ ህዳሴ፣ ውዳሴ፣ … ” በማለት የለውጥ ሃሳብ ከመጣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ይስተጓጎላሉ በሚል በሕዝቡ ዘንድ ማደናገሪያ በመፍጠር በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን የፖለቲካ ፓርቲዎች “ጸረ ልማት” በማለት እንደሚወነጅላቸው ያማርራሉ፡፡ በምርጫ ማጭበርበርና ማንኛውንም ፖለቲካዊ ሆነ ማኅበራዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ በሙሉ ቁጥጥር ሥር ማዋል ኢህአዴግ በሥልጣን ለመቆየት የሚጠቀምባቸው ዓይነተኛ መንገዶቹ እንደሆኑ በስፋት ይጠቀሳል፡፡
ይህንን የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ የቀመሩት ምሁር ስሌታቸውን ለማቀናበር የተለያዩ መረጃዎችን መጠቀማቸውን ገልጸዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል የአገራቱ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ በቅኝ ግዛት የመያዝ ሁኔታ፣ የአገራቱ ዕድሜ፣ ከነጻነት በኋላ የኖሩበት ዓመታት፣ የፖለቲካ መረጋጋት፣ የእርስበርስ ግጭት፣ የነጻ ምርጫ ሁኔታ፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ በየቀጣናው ያለ የመፈንቅለ መንግሥት እንቅስቃሴ፣ ወዘተ የተወሰኑት ናቸው፡፡ ይህንን አያይዘውም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ ማድረግ የግድ መፈንቅለ መንግሥት ይሆናል ማለት እንዳይደለ ነገር ግን አደጋውን ተመልክቶ አስፈላጊ እርምጃዎች በመውሰድ እንዳይሆን መከላከል ዓይነተኛ አማራጭ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ (ካርታዎቹ የተወሰዱት ከጄይ ዑልፌልደር ብሎግ ነው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የዛሬ ዓመት የአሜሪካንን የደኅንነት ምክርቤት ጠቅሶ ባወጣው ዜና በ2030 እኤአ ከሚከሽፉ መንግሥታት (failed states) መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዘግቦ ነበር፡፡ ዜናውን ከዚህ በታች በድጋሚ አትመነዋል፡፡

“በ2030 ከሚከሽፉ መንግሥታት አንዷ ኢትዮጵያ ነች”

ዘገባው የ15 አገራትን ዝርዝር አውጥቷል
የአሜሪካ የብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር በ2030 የሚከሽፉ 15 መንግሥታትን (failed states) ዝርዝር አውጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” ይከሽፋሉ ተብለው ከተተነበዩት የአፍሪካ፣ የእስያና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ነች፡፡
እጅግ የነጠረ፣ ያልተዛባና የተጠና ዘገባ ለአሜሪካ የስለላ ተቋማት፣ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አውጪዎችና ለዓለምዓቀፍ ግንኙነት ተመራማሪዎች በማውጣት የታወቀው የአሜሪካ ብሔራዊ የደኅንነት ምክርቤት ከተቋቋመ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ምክርቤቱ በሚያወጣቸው ዘገባዎች የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የተለያዩ መ/ቤቶች ተጽዕኖ እንደማያደርጉበት የሚናገር ሲሆን፤ ዘገባዎቹንም ከአድልዎ እና ከአሜሪካ መንግሥት አቋም ነጻ በመሆን እንደሚያዘጋጃቸው ይናገራል፡፡
NICየም/ቤቱ ዘገባ በተለይ ምርጫ ከተካሄደ በኋላ ለመጪው ፕሬዚዳንት የወደፊቱን የዓለማችን መልክ ምን እንደሚመስል የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ አስተሳሰቦች እና ዓለምአቀፋዊ ዝንባሌዎች ላይ አቅጣጫ የሚጠቁም ትንበያ ያደርጋል፡፡ ለፕሬዚዳንቱ ዓለምአቀፋዊ የደኅንነት ዘገባ ያቀርባል፤ ለብሔራዊ የጸጥታ ምክርቤት እና ለአገር ውስጥ ደኅንነት መ/ቤት ምክር ያቀብላል፤ በአጠቃላይ የአሜሪካን የስለላና የደኅንነት ማኅበረሰብ ሊከተል በሚገባው ጉዳይ ላይ አቅጣጫ የሚያስይዝ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
በዚሁም መሠረት ባለፈው የታህሳስ ወር “በ2030 የዓለም አቅጣጫ፡ አማራጭ አገራት” በሚል ርዕስ አንድ ዳጎስ ያለ ጥናት አቅርቧል፡፡ ይኸው 160ገጽ ያለው ዘገባ የዛሬ 17ዓመት የዓለማችን ገጽታ ምን እንደሚመስል ከየአገራቱ በተወሰደ ጥናትና እዚያው በሚገኙ ተመራማሪዎች የሰበሰበውን ያካተተ ነው፡፡ ዓለማችን የምታዘነብልባቸው ቀዳሚ ሁኔታዎች አንዱ ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ድህነትን ለመቀነስ፣ በትምህርት ለማደግ፣ በቴክኖሎጂና በህክምና ለመራቀቅ እንዲሁም በገቢም የመካከለኛው መደብ ላይ ለመድረስ የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ከተጠቀሱት አንዱ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው፡፡
ሌሎቹ ዓለምን አንድ አድርጎ በመዳፉ ሥር የሚገዛ ኃይል የማይነሳ መሆኑ ከሚታዩት ከፍተኛ ዝንባሌዎች ተጠቃሽ ሲሆን አሜሪካ ምንም እንኳ “የዓለም ፖሊስ” የመሆኗ ሁኔታ የሚቀንስ ቢሆንም የዓለምን አቅጣጫ መቆጣጠሯ ይቀራል ማለት እንዳልሆነ ይጠቁማል፡፡ የዓለም የሕዝብ ቁጥር ከመጨመሩ አኳያ “እያረጁ” የሚሄዱ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገታቸው እንደሚያሽቆለቁልና ከገጠር ወደከተማ ፍልሰት እንደሚጨምር፤ 60በመቶ የሚሆነው የዓለማችን ሕዝብ በከተሞች አካባቢ ኑሮውን እንደሚያደርግ ይተነብያል፡፡ በዚህም ምክንያት የውሃ፣ የምግብና የኃይል (ኤነርጂ) ፍላጎት ከሕዝብ ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያድግ ይናገራል፡፡ የቴክኖሎጂ ምጥቀትና የማኅበራዊ ሚዲያ አገልግሎትም የዓለማችንን አቅጣጫ እንደሚቀይር ያስረዳል፡፡
የቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት በስፋት እንደሚቀጥልና በበርካታ ፈርጆች ትብብርና ስምምነት እየፈጸሙ ሰፋ ያለ ዓለምአቀፋዊ ኅብረት እንደሚያደርጉ የሚናገረው ይህ ሪፖርት በየአገራቱ እየሰፋ የመጣው በድሃና በሃብታም መካከል ያለው ክፍተት የማኅበራዊ ቀውስ እንደሚያስከትል ይጠቁማል፡፡ ይህም ቀውስ በአንዳንድ አገራት ውስጥ እየሰፋ በመምጣት ለተባባሰ ግጭትና ክስረት እንደሚያጋልጥ የኑሮ ልዩነቱም የማኅበራዊ ቀውሱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያደርሰው ይተነትናል፡፡ የሃይማኖት ሚና እንደሚጨምር የጠቆመው ዘገባ ይህንኑ ተከትሎ መካረርና ግጭት እንዲሁም አሸባሪነት ለመስፋፋት ሃይማኖት ምክንያት እየሆነ እንደሚሄድ ይናገራል፡፡
በዘገባው ከተነገረው በተጻጻሪ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከተጠናቀቀ ወዲህ እስካሁን በ44 አገራት ጉዳይ በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ጣልቃ በመግባት ጦርነት ያካሄደችው አሜሪካ የዓለም ኃያል ሆና እንደምትቀጥል በመናገር ሪፖርቱን የሚያጣጥሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ እንደማስረጃም አድርገው አሜሪካ በተለያዩ አገራት ያላትን 737 የወታደራዊ ተቋማት ይጠቅሳሉ፡፡ ስለሆነም ዘገባው የአሜሪካ የበላይነት የመቀነሱን ጉዳይ አንስቶ የተናገረውን አይቀበሉም፡፡
እኤአ በ2030 የሚክሽፉት 15ቱ መንግሥታት (ፎቶ: ጂአይ)
ዘገባው የዓለማችንን የወደፊት ሁኔታ ሲተነብይ በዋንኛነት ከጠቀሳቸው ጉዳዮች አንዱ በ2030 የሚከሽፉ መንግሥታትን ዝርዝር ሰጥቷል፡፡ “በግጭት መብዛትና በአካባቢ ጥበቃ ቀውስ ምክንያት” የሚከሽፉ መንግሥታት ተብለው ከተጠቀሱት 15 አገራት መካከል ኢትዮጵያ እንዷ ስትሆን አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን፣ ባንግላዴሽ፣ ቻድ፣ ኒጀር፣ ማሊ፣ ኬኒያ፣ ቡሩንዲ፣ ሩዋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ፣ ማላዊ፣ ሃይቲና የመን የተቀሩት ናቸው፡፡
ይሁንና ይኸው ም/ቤት እኤአ በ2015 ፓኪስታን የምትከሽፍ አገር ትሆናለች በማለት ትንቢት ሰጥቶ ይኸው እስካሁን አለች በማለት ዘገባውን የሚያጣጥሉ ክፍሎች ኢትዮጵያም ሆነ ሌሎቹ አገራት ለመክሸፋቸው በቂ ማስረጃ የለም በማለት የዘገባውን ጥቆማ ይቃረናሉ፡፡ በሌላ በኩል እንዲህ ያለው የመክሸፍ ሁኔታ ሊዋጥለት የማይችለው ኢህአዴግ “ህዳሴ፣ ውዳሴ” ከማለት ይልቅ ይህንን ጉዳይ አጥብቆ ሊያስብበት እንደሚገባና የሥርዓት መበስበስ አመላካች የሆነውን “የመንግሥት ሌቦች” መበራከት መፍትሔ ሊያበጅለት እንደሚገባ ደጋፊዎቹና አመራሩ በየጊዜው የሚያነሱት ነጥብ ነው፡፡
በዚሁ የኢትዮጵያ እንደ አገር የመክሸፍ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው አሁን ካላቸው ተግባር አኳያ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ በአውሮጳ የሚገኙ የፖለቲካና ዓለምአቀፋዊ ግንኙነት ተመራማሪ “ችግሩ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የተቃዋሚውም ነው” ይላሉ፡፡ “በአገር ውስጥ ያለው ተቃዋሚ ከውስጥ የሥልጣን ሽኩቻና ከስብሰባ/ውይይት ጋጋታ ባለፈ መልኩ ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ሊያደርግ የሚችል የተቀናጀና ውጤታማ ተግባር ሊፈጽሙ ይገባቸዋል” የሚሉት ምሁር በውጭ ያለውም “ከጊዜያዊና ጥቃቅን የራስ ክብር የመፈለግ አካሄድ በመላቀቅ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ጡንቻውን በወያኔ ላይ ማሳረፍ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡ “የደኅንነት ተቋሙ ባወጣው ዘገባ ላይ በግልጽ እንደተነበየው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ የመጨመሩ ያህል በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህንኑ ለውጥ ማምጣት የሚችል የዘመኑ ቴክኖሎጂ ለአሉባልታና ተራ የፖለቲካ ወሬ ከመጠቀም ይልቅ አገር ለማዳን ተግባር ሊጠቀምበት ይገባል” በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፡፡
የደኅንነት ምክርቤቱ ያወጣው ሙሉ ዘገባ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
http://www.goolgule.com/coup-forecasts-for-2014/

“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ

"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ

displaced anuaks


  • “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
  • መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም፤” ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ፣ ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡
በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ ለሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ፣ የውጭ ኩባንያዎች ሰፋፊ መሬቶች አንዳንዶቹ እንደሚሉት ቤልጂየምን የሚያህል መሬት ተሰጥቶ እየተካሄደ ስላለው ኢንቨስትመንት በቂ ማብራሪያ በሪፖርቱ ስላልተካተተ እውነቱ ሊብራራ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚካሄድ የግብር ኢንቨስትመንት ችግር የለውም ያሉት አቶ ግርማ፣ በመንግሥት ላይ እየቀረበ ያለው ክስ አርሶ አደሮች እንዲፈናቀሉ ማድረጉ አንዱ ነው ብለዋል፡፡
forced displacementየውጭ ኩባንያዎቹ ብድር የሚያገኙት ከኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን የመገናኛ ብዙኃን እየዘገቡ መሆኑን በማስታወስ፣ “በኢትዮጵያ ገንዘብና በኢትዮጵያ መሬት ለምንድን ነው የውጭ ኩባንያዎች መጥተው የሚያለሙት?” በማለት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” በማለት አቶ ግርማ የሚኒስትሩን ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ጥያቄ ያቀረቡት ብቸኛው የግል ተመራጭና የምክር ቤት አባል ዶ/ር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ሲሆኑ፣ በሰፋፊ የግብርና መሬት ላይ በሚካሄደው ኢንቨስትመንት የምዕራባዊያን ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ለምን የማስተዋወቅ ሥራ አይሠራም በማለት፣ የህንድና የቻይና (የምሥራቁ የዓለም አገሮች) ኩባንያዎች የጐላ ተሳትፎ ሚዛኑን መጠበቅ ይገባዋል የሚል መልዕክት ያለው ጥያቄያዊ አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊዎች በጋራ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ወንድይራድ ማንደፍሮ በሰፋፊ መሬቶች ላይ ለሚካሄድ የግብርና ኢንቨስትመንት ሲባል አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም ብለዋል፡፡
ሁለቱም ምስሎች በጋምቤላ አካባቢ ከሳተላይት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ቀያዮቹ ነጥቦች በሙሉ በመሬት ነጠቃ ከቀያቸው የተፈናቀሉና ቤታቸው የፈረሰ አባወራዎችን ሲሆን ቢጫዎቹ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በግዳጅ የሰፈሩበትን ነው፡፡
ሁለቱም ምስሎች በጋምቤላ አካባቢ ከሳተላይት የተወሰዱ ናቸው፡፡ ቀያዮቹ ነጥቦች በሙሉ በመሬት ነጠቃ ከቀያቸው የተፈናቀሉና ቤታቸው የፈረሰ አባወራዎችን ሲሆን ቢጫዎቹ ደግሞ ተፈናቃዮቹ በግዳጅ የሰፈሩበትን ነው፡፡
“የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሆኑ ነፃ መሬቶችን ብቻ ነው ለሰፋፊ የግብርና ኢንቨስትመንት የምንሰጠው፡፡ ማንም ከቀዬው አልተፈናቀለም፤” በማለት አስረድተዋል፡፡
በሰፋፊ መሬቶች ላይ የሚደረግ የግብር ኢንቨስትመንት ከፍተኛ የገንዘብ አቅም እንደሚጠይቅ የተናገሩት ማኒስትር ዴኤታው፣ ከዚህ ጋር የተያያዙ ችግሮች መኖራቸውን ግን አልሸሸጉም፡፡
በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ሆነ በባለሀብቶቹ ቀደም ብሎ ተይዞ የነበረው እምነት ኢንቨስትመንቱ ቀላል እንደነበር፣ ነገር ግን በተግባር ሲታይ ጊዜ የሚወስድና አቅም የሚጠይቅ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ለባለሀብቶቹ የሚሰጠውን የመሬት መጠን እየቀነሰ እንደሚገኝ፣ በአጠቃላይ ግን ትልቅ አቅም የሚፈጥር ዘርፍ እንደሚሆን አብራርተዋል፡፡
በዚህ ዘርፍ በፌዴራል መንግሥት ፈቃድ የተሰጣቸው ባለሀብቶች 43 መሆናቸውን አስረድተው፣ ከእነዚህ ውስጥ 15 የሚሆኑት ብቻ የውጭ ኩባንያዎች ናቸው ብለዋል፡፡ በመሆኑም በዘርፉ በአብዛኛው እየተሳተፉ የሚገኙት የአገር ውስጥ ባለሀብቶች መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው በበኩላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ መሬት መቀራመት የለም ብለዋል፡፡
አሁን ባለው የዓለም የዕድገት ሁኔታ የገንዘብ አቅም ያለው በምሥራቃውያን አካባቢ መሆኑን፣ ምዕራባውያኑ በዘርፉ ያልተሳተፉት የአቅም ችግር ስላለባቸው እንደሆነ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
“የመሬት መቀራመት ጉዳይ እየተነሳ ያለው ከዚሁ የዓለም ጂኦ ፖለቲካ አካባቢ ነው፡፡ ከምሥራቅ የዓለም አገሮች ወደ አፍሪካ እየመጣ ያለ ኢንቨስትመንት ስለማይወደድ ነው፤” ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩም ሆነ የሥራ ባልደረቦቻቸው የውጭ ኩባንያዎቹ እያገኙ ስላለው ከፍተኛ ብድር ግን ማብራሪያ ሳይሰጡበት ታልፏል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም እንደሚያስረዳው፣ በ2006 ዓ.ም. የመኸር ወቅት 253 ሚሊዮን 805 ሺሕ 340 ኩንታል ምርት ሊገኝ እንደሚችል፣ ይህም ካለፈው ዓመት ዘጠኝ በመቶ መጨመሩን ነው፡፡ (ሪፖርተር)
http://www.goolgule.com/why-ethiopia-needs-foreign-farmers/

Wednesday, January 29, 2014

የኢትዮጵያውያን ምሬት፡ የሕይወት ማሽቆልቆልና በፍርሃት መሽማቀቅ አፋጣኝ መፍትሄ ይሻል

ኢትዮጵያ በሕወሃት ዘመነ አመራር የታወቀችባቸው ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ብዙ “እንዴ!”የሚያሰኙ ጥሩ ሀሳቦችም ፈልቀዋል – አፈጻጸማቸው እትየለሌ ቢሆንም። ከነዚህም መካከል መሠረተ ልማት፡ በጤናና በትምህርት መስኮች መሻሻሎች መታየታቸው ወዘተ መልካም ይነገርላቸዋል – የቢል ጌትስን የራስ ተጠቃሚነትና ኢምፓየር ግንባታ ወደጎን ትተን! በዕጦት ደረጃም በሀገራችን የሰብዓዊ መብቶች አለመከበር፣ የፍትህ አለመኖርና ለአብዛኛው ሕዝባችን የምግብ ዕጦት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው።
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
Prime Ministers Katainen and Hailemariam (Credit: ERTA)
ለምሳሌም ያህል፡ ሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 30 ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግንና መንግስትን መቃወምን ግልጽ ቢያደርግም፡ እሁድ ዕለት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ለመሰጠት ለመቃወም: ለሚመለተው አሳውቀው ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ተፍ ተፍ ሲሉ የአዘጋጁ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ጎንደር ውስጥ ተይዘው ታስረዋል። በተመሳሳይ መንገድ ትግራይ ውስጥም የአረና አመራሮች ሕዝቡን ቀሰቀሳችሁ በሚል ውንጀላ አዲግራት ውስጥ አመራሩና አባሎቹ ክፉኛ ተደብድበዋል – ጉዳት የደረሰባቸውም ሕክምና ለመሻት ተገደዋል። ይህንኑ አስመልክቶ፡ አንዱ ተደብዳቢ መምህር አብርሃ ደስታ የሚከተለውን ጽፏል፡
    “ህወሓቶች በተግባራቸው ሊያዝኑ ይገባል። ህዝብን ፖለቲካ እንዲያውቅና ራሱ ከጭቆና እንዲከላከል ለማገዝ በምንሞክርበት ግዜ መንግስት ወደ ተራ የሽፍትነት ተግባር መሰማራቱ የሚያስደምም ነው … እኛ ለህዝብ ነፃነት ነው የምንታገለው። ትግላችን ሰለማዊ ነው። ወታደርና ፖሊስም የለንም። እኛ ያለን ህይወት ነው። ያለችንን ህይወት ለህዝብ ደህንነት ስንል መስዋእት አድርገናል። በህዝብ ፊት ተደብድበናል። በፖሊስና አስተዳዳሪዎች ፊት ተደብድበናል። እኛ መክፈል ያለብን ህይወትን ነው።”
ይህ በግልጽ የሚታየው የዛሬይቱ ኢትዮጵያ የስብዓዊ መብቶች አንጸባራቂ ሥዕል ነው። ይህ ሁኔታ በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሀግሪቱ ውስጥ እየተካሄደ ያለ የመንግሥት ሕገ ወጥነት ነው!
በኤኮኖሚው መስክ ያለው ችግር ግዙፍ ነው። ድህነት ከመቀረፍ ይልቅ፡ ሥር እየስደደ መሆኑን ብዙዎች ያማርራሉ። ለጥቂቶች ግን ሀገሪቱ ምድራዊ ገነት ሆናለች። ሕዝቡ እየተደበደበም፡ በየቀኑ አልዋጥ ባይ ፕሮፓጋንዳ በግድ እየተጋተ ነው!
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው ለብዙዎቹ የአዲስ አበባ መሽቀርቀር እንደአጠቃላይ የሃገሪቱ የልማትና ዕድገት መለኪያ ተደርጎ እንዲወሰድ የተቀነባበረ ጥረት የሚድረገው። የምርጫ ዘመን በመቃረቡ፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቅርቡ ስንዴ ለውጭ ገብያ ሻጭ ልትሆን ነው በማለት ጥር 18፣ 2014 አርሲ ሆነው ማስማታቸው ልብ ሊባል ይገባል። ነገር ግን ኢትዮጵያ በልማት ገና ሀ ሁ … ላይ ናት – በምግብ 40 በመቶ የሚሆነውን ሕዝቧን በቀን ሶስቴ ሳይሆን፡ አንዴም መመገብ ያልቻለች አገር ናት! ይህ በመሆኑ አይደል እንዴ የምዕራቡ ዓለም፡ በቋሚነት ከ10 በመቶ በላይ የሆነውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ክዓመት ዓመት በዓለም አቀፍ እህል ዕርዳታ ሕይወት በመስጠት ላይ ያለው?
ከሁሉም ጎልቶ የሚነገርለትና የሕወሃት ሰዎችም ቶሎ የሚስፈነጠሩበት የአገሪቱ ከትላልቅ ጦርነቶች መላቀቋ ነው። ስለዚህም የሕወሃት ሰዎችና ደጋፊዎቻቸው በመመጻደቅ ሲናገሩ መስማቱ የተለመደ ሆኖአል። በዚህም መነሻነት፡ እንዲህ ይላሉ: ባለፉት 20 ዓመታት፡ ሕወሃት ለረዥም ዘመናት አገሪቱን ያደሙትን ጦርነቶች አቁሞ ልማት ላይ እንድታተኩር አደረገ የሚባለው በብዛት ይሰማል። የሕወሃት ስዎችም ይህ በተደጋጋሚ እንዲነገርላቸው ብዙ ጥረቶች አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። እራሳቸውም በተደጋጋሚ እራሳቸውን በዚህ ሲያሞካሹ ይሰማል፤ ለውጭ የፕሮፓጋንዳ ድርጅቶችም ይህንን እንዲያስተጋቡላቸው፡ ከፍተኛ ክፍያዎችን በየጊዜው ፈጽመዋል።
እስከዛሬ አጥጋቢ ግንዛቤ ያላገኘው ግን፡ ድሮም ሆነ ዛሬ የጦርነቶች አጋጋይ ሕወሃት መሆኑ ነው። የኤርትራንና የትግራይን መገንጠል ጉዞ በተግባር ሲተረጉም ኖረ። ቀኑ ደርሶ ጅብሃ ሲገነጠል፡ ሕወሃት ባዶ የሥልጣን ወንበር ስለታየው፡ ኢትዮጵያዊነትን መረጠ። በትግል አጋሩ ጅብሃ ዘንድ ይህ እንደክህደት እንዳይታበት – በሰላም ሂዱ፡ ኢትዮጵያ ከእናነተ ሰላም እንጂ ሌላው ቀርቶ የባህር በር እንኳ አያስፈልጋትም አለ። ይህንን አስመልክቶ፡ በየካቲት ወር 1994 ስብሃት ነጋ ለዓለምሰገድ አባይ በሰጡት ቃለ መጠይቅ የሕወሃት ቀደምት ፓሊሲ መገንጠል ሆኖ እስከ 1985 መቆየቱን ያረጋግጣሉ። ከቃለ መጠይቁ ውስጥ በጣም አስገራሚው ነገር ግን፡ ብዙ የሕወሃት ተዋጊዎች ኢትዮጵያዊነትን ገና ድሮ አሽቀንጥረው የጣሉ በመሆናቸው፡ ዛሬም ቢሆን በተለይ ከአማራ ጋር ኢትዮጵያዊ ሆኖ መገኝትን በሙል ልብ አለመቀበላቸውን ነው ያመላከቱት [See Identity Jilted: Re-imagined Identity (1998)]።
ያለፈው አልበቃ ብሎ፡ ዛሬም ሕወሃት ሀገሪቱ ውስጥ ሽብርና ፍርሃት በማንገስ የውስጥ ግጭቶችን በመተንኮስ: የተለያዩ ብሄረስቦችን አባሎች በማፈናቀልና ችግሮችን በማባባስ ተጠቃሚ ለመሆን ሲምክር ይታያል – ድ/ር ቴድሮስ ፍጹም “እኔ ያለሁበት ፓርቲ ውስጥ ይህ አይደረግም!” ብለው ዝናቸውን አጋልጠው ቢገዘቱም። ነገሩ ግን፡ ዛሬም በምሥራቅ በተለያያዩ የኦሮም ክፍሎችና ኢትዮጵያውያን ሶማሌዎች መካከል፡ በደቡብም እንዲሁ በተለያዩ ጎሣዎች መካከል፡ አማራንና ኦርሞችን በማጋጭት፡ ጥላቻና መቃቃርን በዜጎች መካከል ለመፍጠር ብዙ ሲሞክር ቆይቷል። አንዳንድ ቦታዎችም፡ ለምሳሌ ቦረና፡ ተሳክቶለት ስሞኑን የብዙ ዜጎች ደም ፈሷል፤ ሕይወትም ተቀጥፏል። ቤት ንብረቶችም ተደምስሰዋል። ሌላው ቀርቶ፡ የሕክምና ባለሙያ የነበሩት የአገር አስተዳደር ሚኒስትሩ – የዛሬው የሃይማኖትች ጉዳይና የጸረሽብር ኤክስፐርቱ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም – ኬንያ በሥጋቷ ምክንያት (2012ን በማስታወስ) ልተቀስቅሳቸው ብትሞክርም፡ ነገሩ አውቆ የተኛ ቢነቀንቁት አይሰማ ሆኖ እሳችውም እንደክረምት ድብ ክፉኛ አሸልበዋል።
ለማንኛውም፡ በዓለም ላይ እንደሕወሃት የተሳካለት የለም – ዕድሉን ሃገራችንን ለማሻሻል በሚገባ አልተጠቀመበትም እንጂ! ስለሆነም ክሥራ ይልቅ ፕሮፓጋንዳ፡ ዕውነትን ተናግሮ ችግሮችን በጋራ ከመፍታት ይልቅ፡ ሁሉንም ስው ማሞኘት እንችላለን በሚል ትዕቢት ብዙ የሚያሳፍሩ ተግባሮች ሲያከናወን ይታያል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፡ በበጎነታችው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደጉን የሚመኙ የውጭዎቹ የፖለቲካ፡ የዲፕሎማሲና ኅብረተስባዊ መሻሻሎችን አራማጆች ይህንን የሕውሃትን የሰላም ማስፈን የዋህ መስል ቅጽል በአመኔታ የሚጋሩት በሁለት ተክፈለው ይታያሉ፡ –
(ሀ) በእውነትም ጦርነትና የንጹሃን ዕልቂት መቆሙን፡ ኢትዮጵያ ክድህነት ተላቅቃ ማየት የሚሹ ወገኖች፤
(ለ) ጊዘው የበለጸጉት ሃገሮች ወደታዳጊ ሀገሮች ውስጥ ዘልቀው በመስፋፋትና በኢኮኖሚ ትብብር ስም የራሳቸውን ኤኮኖሚያዊ፡ የበላይነት ማቆየት የሚሹበት፡ ፖለቲካዊና ስትራተጂካዊ ጥቅሞቻቸውን የሚያበራክቱበት በመሆኑ፡ ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተዳብረው፡ የሕወሃትን ገድል መተረኩ፡ ለሚሹት ዓላማ አንድ ጥቅም ትስስሮሽ መፍጠር የሚያስችል መሣሪያ አድርገው የሚጠቀሙበት ወገኖችም እዚሀ ውስጥ ተስልፈዋል።
ከላይ የተመለከቱት ከተለያየ አግጣጫ ተነስተው ሁለቱም አንድ የሚገናኙበት መጋጠሚያ፡ ስለኢትዮጵያ በጎ ነገር እንዲስተጋባ ማድረጋቸው ነው። በተለይም በሁለተኝው ክፍል የሚገኙት፡ በተቻለ መጠን ስለኢትዮጵያ በጎውን በማጋነን፡ የሕወሃትን የስብዓዊ መብቶች ጽልመት፡ ጎስኝነት፡ ሙሰኝነት የሚሸፋፍን አመለካከት በምዕራባውያንም ሆነ ምሥራቃዊ ሚዲያዎች ላይ በጊዜው ያስደስኮሩላቸዋል።
በተጨማሪም፡ እነዚህ ሀገሮች ለኢትዮጵያ ግዙፍ ዕርዳታ መፍሰሱን ይደግፋሉ። ነገር ግን ይህ ዕርዳታ በብዙ መስኮች – በተለይም በግብርናው – መስክ የሀገሪቱን ችግሮች፡ በምግብ ምርት እራስን ከማስቻል ይዘት ስሌለው፡ ትኩረታችውም ሆነ ጥረታቸው – በዘለቄታ ሀገሪቱን ከምግብ ዕርዳታ ተመጽዋች ነጻ ለማድረግ አላስቻለም። በመሆኑም፡ እየተደረገ ያለው፡ ትላንት እንደነበረ ሁሉ ዛሬም ኢትዮጵያ አንድ ሶስተኛ መንግሥታዊ በጀቷን በዓለም አቀፍ ዕርዳታ ተመጽዋችነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ የውስጥና የውጭ ፖሊሲዋን በማክራየት እንድትቀጥል አስገዳጅ ሁኔታ ተፈጥሮባታል።
በአሁኑ ወቅት፡ በተለያዩ ምክንያቶች (የስብዓዊ መብቶች አለመከበር ችግር፡ የየራሳቸው የሀገሮቹ የኢኮኖሚ ችግሮች) መንስኤነት፡ ከለጋሽ ሀገሮች በቀጥታ የሚገኝው ዕርዳታ በክፍተኛ ድረጃ ቀንሷል (ክአሜሪካና እንግሊዝ በስተቀር)። በዚህም ምክንያት የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የሚስጠውን ብዙውን የዕርዳታና ብድር ጫና ድርሻ ተሸካሚ ሆኖአል።
ለምሳሌ፡ ሌላው ቀርቶ ስብዓዊ ዕርዳታን እንኳ በተመለከተ፡ 12 የአውሮፓ ኅብረት ሀገሮች (እንግሊዝን አይጭምርም) በ2012 ለኢትዮጵያ በባይላተራል መንገድ ለዕርዳታ ያዋጡት €24 ሚልዮን ሲሆን፡ በ2013 ይህ መዋጮ ወደ €12.4 ሚልዮን ወርዷል። ከነዚህም መካከል ትልቁን ቅናሽ ያደረገችው ጀርመን ናት – ከ€8.2 ሚልዮን ወ €4.2 ሚልዮን ዝቅ በማድረግ። በመሆኑም፡ከዚህም ከዚያም አስባስቦ የበጀት ምንጮች በማስባስብና ተጨማሪ ምክንያቶች በመፍጠር (ነፍስ ወክፈ መልሶ ማቋቋም) በ2013 እንዳደረገው፡ የአወሮፓ ኮሚሽን በ 2011-2013 12 ሚልዮን ኢትዮጵያውያን ለመርዳት እንዲቻል €130 ሚልዮን ለግሷል።
አሁን ለሁሉም ለጋሾች ከባድ የሆነው “የልማት” ዕርዳታውም እንዲሁ በበዙ ጥያቄዎች ላይ መውደቁ መሆኑ ይሰማል።
በዓለም ዙሪይ ያለፉው ሩብ ምዕተ ዓመት የልማት ጊዜ በመሆኑ፡ ብዙ ታዳጊ አገሮች ከፍተኛ ተጠቃሚ ሆነዋል። ኢትዮጵያ ይህ ዕድል ቢገጥማትም፡ መሣሪያ ያነገቡት የሕወሃት ሰዎችና አጫፍሪዎቻቸው ግንባር ቀድም ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሥርዓት በመዘርጋቱ፡ የትላንቱ ጦረኞችና የዛሬዎቹ የስላም ደጋፊ-መስል የአንድ ብኄረስብ ሰዎች፡ ሆን ብለው ዕኩልነትን የሚጻረር የፖለቲካ፡ የኤኮኖሚ፡ የደህንነትና ማኅበራዊ ፓሊስዎችን በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።
ይህ ግን ዘላቂ መሠረት ስሌለው፡ ዛሬ የኤኮኖሚው የጥንድ ዕድገት ውደሳው ጋብ ብሎ፡ ሀገራችን የመንግሥት ብልግናና የሃስት ፕሮፓጋንዳ ከሚመገቡት መካክል ወድቃለች። በዚሁም ምክንያት (ሽፋኑ የውሃ ዕጥርረት፡ ድርቀት፡ የሃይማኖትና የብኄረቦች አለመቻቻልና ግጭቶች ላይ ቢመካኝም)፡ ተደጋጋሚ ዓለም አቅፍ ጥናቶችኢትዮጵያ ከሚወድቁት የአፍሪቃአገሮች (Failed States) መካከል ተደምራ፡ የወደፊት ጽዋዋ አስፈሪ እንደሚሆን ቀንደኛ ደጋፊዎቿ ድምዳሜ ላይ መሆናቸውን በግልጽ የምንሰማበት ዘመን ላይ ደርስናል።
ድሮስ ቢሆን፡ የሕዝብ ዓመኔታ ያጣ መንግሥት፡ መሣሪያውን ደግኖ በኅይል ለመግዛት ከመሞከር ውጭ ምን አማራጭ አለው? ጊዜው የጥላቻ፡ የክፋትና የቂም በቀል በመሆኑ፡ በአንድ በኩል፡ የሕወሃት ስዎች ዘረፋ ላይ የተሰማሩ ሲሆን፡ በሌላ በኩል ደግሞ፡ የኢትዮጵያውያንን ስብዓዊ መብቶች በመግፈፍና መርገጣቸውን በማባባስ፡ ሃገሪቱን ወደ ቀውስ ጎዳን እየገፉ ናቸው። በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንዴት ዕድገት ይኖራል?
እንዲያውም፡ የራሱን የአገዛዝ ዘመን ለማራዘም ሲል፡ የኢትዪጵያ ሕዝብ ፍላጎትና አመለካከት ሳይጠየቅ ኤርትራን በፊርማው እንድትገነጥል ያደረገ፡ አገሪቱን የባሀር በር ለማሳጣት የደፈረ የመንግሥታዊ ባህልና ኃላፊነትና ግንዛቤ የሌለው ሕወሃት፡ ለሱዳን የኢትዮጵያን መሬት ቆርጦ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑ ሕዝቡን በቃ! የሚል ድምዳሜ ላይ ማድረሱ አያጠራጥርም!
በዓለም ታሪክ ውስጥም ሕወሃት “ታዋቂ” የሚሆነው፡ ራሱን ሥልጣን ላይ ለማቆየት፡ የሀገርን ልኡላዊነትና መሬት ቆርሶ ለጎረቤት ሀገርና ለከፍተኛ ብድር ስጭና ገንዘብ ለዋጭ አሳልፎ የሚሰጥ በመሆኑ ነው።
ዛሬም ሆነ ነገ፡ ለሀገራችን ዘላቂው መፍትሄ ግን መንግሥት የሕዝብን ፍላጎት ለማክበር መቻሉና ለዚህም ተጠያቂነት ያለበት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው። ይህንን ለማድረግ፡ አሁንም ትንሽ የተስፋ መስኮት አለ – የሕውውሃት ስዎች ኃላፊነት የሚስማቸው ቢሁን። ይህ ለሕወሃትና ግብረአበሮቹ ተቀባይ ሳይሆን ቢቀር፡ ቀሪው ምርጫ ሕዝቡ እየተረገጠ መቀጠል፡ ወይንም እነርሱ ከመድረኩ መወገድ ነው።
እስካሁን በዚህ ድህረ ገጽ ይህንን አሳብ አላራመድንም ነበር። የሁኔታው አስከፊነት ግን አሁን የወቅቱ አስፈላጊ እርምጃ አድርጎታል!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/10852

Tuesday, January 28, 2014

አቤ በእስር ቤት በነበረው መልካም ባህርይ.......

“ ሰው ጥሩ” ( አርአያ ተስፋማሪያም)

January 27, 2014

አሜሪካ መኖር ከጀመረ 16 አመት አለፈው። ለፍቅር ሲል ከፍተኛ መስዋእትነት የከፈለ ታዋቂ አርቲስት ነው። እጅግ ለሚያፈቅራት ልጅ አቀንቅኖላታል። ይህ ድምፃዊ፥ አበበ ተካ ነው። “ሰው ጥሩ..” የሚለው የግጥም ድርሰት በህልሙ ነበር የታየው። ፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ትባላለች።
አቤ በህልሙ “ፍቅረኛውን ጥቅጥቅ ባለ ጫካ ውስጥ እየሮጠ ሲከተላት..ሲሮጥ…ሳይደርስበት ይቀራል። ከዛም ደክሞት ለምለም ሳር በሆነ ሜዳ ቁጭ ብሎ…”ሰው ጥሩ..” እያለ ያዜማል፤”. ህልሙን ለገጣሚ ሙልጌታ ተስፋዬ (ነፍሰ ሄር) ይነግረዋል። ዘፈኑም ተሰራ። “ምንድነው ቀለበት፣.. እንዳንቺ አላየሁም በዝች ምድር ላይ፣.. አገሯ ወዲያ ማዶ፣..በይ ካልረሳሽኝ-ንገሪኝ..” ዜማዎች ለፍቅረኛው እታገኝ የተደረሱ ናቸው። አበበ ተካ በ1989ዓ.ም “ምርጥ የአመቱ ድምፃዊ” ተብሎ የገንዘብና ወርቅ ሽልማት አግኝቷል።
ብዙ ጊዜ መድረክ ላይ ሲዘፍን እንባው ይፈስ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በመለየት ስቃይ ውስጥ አሻግሮ የእርሱ አይነት እጣ (የመለያየት) የደረሰባቸውን እያሰበ ጭምር ነበር።…አበበ በ1990ዓ.ም ለንደን ይጓዛል። በዛው የጣሊያን ፓስፖርት አሰርቶ ፍቅረኛውን ለማግኘት ወደ አሜሪካ ይበራል። እንዳቀደው ግን አልሆነም። ፓስፖርቱ ተመሳስሎ የተዘጋጀ ስለነበረ በአሜሪካ ፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ተላከ። 5 አመት ተፈረደበት። ጎንደር ይኖሩ የነበሩት አባቱ አቶ ተካ የልጃቸውን መታሰር እንደሰሙ (በደም ግፊት) ደንግጠው ሕይወታቸው አለፈ። እስር ቤት እንዳለ መርዶ መጣበት።..
አቤ በእስር ቤት በነበረው መልካም ባህርይ 1አመት ከ8 ወር ከታሰረ በኋላ እንዲለቀቅ ተደረገ። በብዙ ፈተና ያለፈበትን ፍቅረኛውን የማግኘት ህልም እውን ሆነ። አበበ አሁን ድረስ ፈጣሪን ያመሰግናል። ከፍቅረኛው እታገኝ ሙላው ጋር ጎጆ ቀልሰው ሶስት ልጆች አፍርተዋል። ልጆቹ ትእግስት አበበ፣ ብርሃን አበበ፣ አዲስኪዳን አበበ ይባላሉ። አበበ እጅግ ሲበዛ ትሁትና ሰው አክባሪ ሲሆን በዲሲ የሚኖሩ ሃበሾች ትልቅ ከበሬታ ይሰጡታል። ስለእርሱ ሲናገሩ፥ « አበበ የትዳርና ፍቅር ተምሳሌት ነው። ጨዋና ቤተሰቡን አክባሪ ሰው ነው። ብዙ ቦታ ልታይ- ልታይ አይልም። ከስራው መልስ ከቤተሰቡ ጋር ነው የሚያሳልፈው። ስለ ሃገሩ ኢትዮጲያ በየመድረኩ ያዜማል።» በማለት ምስክርነት ይሰጣሉ። በየሳምንቱ ቅዳሜ በ”ዱከም” መዝናኛ የሚዘፍነው አበበ ሲናገር፥ « የሰው ልጅ በተለይ በስደት አገር ያለው ሃበሻ ወገኔ..ከሚወደው አገሩ፣ከቤተሰቡ፣ ከፍቅረኛው…እንዲገናኝ ሁሌም ፈጣሪን እለምናለሁ።
የተለያየ ሰው ናፍቆቱን ሳይወጣ ክፉ አይንካው!! ተነጣጥሎ መኖር ከባድ ስቃይ ነው። የናፍቆትና ብቸኝነት ስቃይን የደረሰበት ያውቀዋል። » ይላል። ከኳስ የቡና ክለብ አድናቂና ደጋፊ የሆነው ድምፃዊ አበበ ሁለተኛ አልበም ሊያወጣ ነው። በአንድ ሰው አገናኝነት ገጣሚና ደራሲ Fasil Tekalign የላካቸውን ጨምሮ የግጥምና ዜማ ስራዎች ቅድመ ዝግጅት እየተደረገባቸው ነው። በእውነተኛ ታሪክ ዙሪያ የተመሰረቱ እንዲሁም አገርና ህዝብን የተመለከቱ ዜማዎች ይገኙበታል።..የሰው ልጅ ህልሙ ሲሰምር እንዴት ያስደስታል!!
( አበበና ፍቅረኛው እታገኝ (ከፎቶ ማህደር) ..እንዲሁም በቅርብ ተገናኝተን..)

በቂ ጥበቃ ያልተደረገለት ሰርግ በሰው ደም ተጨማልቆ ተጠናቀቀ

በዳዊት ሰለሞን
በአዲስ አበባ ሐምሌ 19 መናፈሻ ትናንት 18/05/2006 እሁድ 10፡00 ገደማ በሰርግ ታዳሚዎችና በአካባቢው በሚገኙ ወጣቶች መካከል በተነሳ ግጥት ብዙዎች ክፉኛ ተጎድተው ወደ የካቲትና ምኒልክ ሆስፒታሎች መወሰዳቸውን በሰርጉ የታደሙ ሰዎች ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡
ፈረንሳዊ ዜግነት ያለው ሙሽራ ኢትዩጵያዊቷን በሚያገባበት ሰርግ ላይ ለመታደም ከ300 የሚልቁ ሰዎች በአዳራሹ በመገኘት የሙሽሮቹን ደስታ ሲካፈሉ ቆይተዋል፡፡የጥሪ ካርድ በመመልከት ወደ አዳራሹ እድምተኛውን ሲያስገቡ የነበሩ አስተናባሪዎች ያለ ጥሪ ወረቀት ወደ አዳራሹ ለመግባት ከፈለጉ ወጣቶች ጋር ሲጨቃጨቁ መቆየታቸውን የሚናገሩት የሐምሳ አለቃ ሹምዬ ያለው ሾልኮ ወደ አዳራሹ መግባት የቻለ ወጣት ከአንዲት እድምተኛ የእጅ ስልክ ሰርቆ ሊወጣ ሲል በመያዙ ጭቅጭቁ ወደ ለየለት ድብድብ ማምራቱን ይናገራሉ፡፡
‹‹ድንጋይ፣ ብረትና ዱላ ማንነት ሳይለዩ በሰው አካል ላይ ማረፍ በመጀመራቸው እጃቸው የተሰበረ፣ የተፈነከቱና የተረጋገጡ ሰዎች ብዛት ቁጥር አልነበረውም፡፡ከውጪ የነበሩ ወጣቶች ጓደኛቸው ሰርቆ ተይዟል መባሉን እንደውሸት በመቁጠር ድንጋይ መወራወር በመጀመራቸው መልስ ለመስጠት የሰርጉ ታዳሚዎች ያገኙትን ይዘው ድንጋይ ወርዋሪዎቹን መፋለም ይጀምራሉ፡፡በዚህ መሐል ከሁለቱም ወገን ለጉዳት በመዳረጋቸው ሆስፒታል መመላለስ የሰርጉ አዘጋጆች አጣ ፈንታ በመሆን ሰርጉ ተጠናቅቋል ››ብለዋል፡፡
ሰርጉን ለማጀብ የተገኙ ሁለት መኪኖችም በድንጋይ የፊትና የኋላ መስታወቶቻቸው ረግፎባቸዋል፡፡ሰርጉ እንዲከናወንበት አዳራሹን ያከራየው የሐምሌ 19 መናፈሻ አስተዳደር በቂ ጥበቃ ባለማዘጋጀቱና በአካባቢው የነበሩ ፖሊሶችም ለራሳቸው ደህንነት በመስጋት መሰወራቸው ለሰው አካልና ለንብረት መጎዳት ከፍተኛ አስተዋእጾ ማበርከቱን ሐምሳ አለቃ ተናግረዋል፡፡

ከቀይ ወደ ሰማያዊ ጉዞ

ቹቸቤ

ከቀለማት ሁሉ ‘ቀይ’ አገራችንን አቅልሞ መዶሻው ቁልቁል ሲወቅረን ማጭዱ ከታች ሲያጭደን ኖረን ያለቀው አልቆ የተረፍነው ፈዘንና ደክመን ባለንበት ሰዐት ማጭዱንና መዶሻውን በብጫ ቀለም  ሸፍነው በትግራይ ስም አጨዳውን የቀጠሉበትና ቀን የሰጣቸው ጎጠኞች አገርም ሕዝብም ሊያጠፉ እንደገና በወገን ደም እያጨቀዩን ይገኛሉ። ቢሆንም ተስፋችን አላሟጠጠም። ብርቱዎች ቆርጠውና ቀልጥፈው ለነጻነት የሚደረገውን ትግል በሁሉም መስክ አፋፍመዋል። አዲስ የሆነው ነገር ከቀይና ነጭ ሽብር በሁዋላ ሰማያዊ ሰላማዊ ትግል የሚል መፈጠሩ ነው። ታሪክ ያልዘገባቸው ግን ከቀይ ሽብር ወደ ብጫ ስካር በሚል ጠጅ ቤት የቀሩ የአብዮት ትራፊ ወጣቶችን ህይወት ነው።Ethiopia’s Blue party (Semayawi party) leaders in police control
ርዕሱን በቀለም ጀምረነዋልና ሰማያዊ ፓርቲ በአውሮፓና በአሜሪካ ሃዋርያውን ልኮ ዓላማውን ሲያሳውቅ የሰነበተው በልደትና  በጥምቀት ሰሞን ነበርና ፓርቲው በመወለዱ ደስ ያላቸውና በመጠመቁና በማጥመቁም የጨፈሩ በርካቶች ናቸው። ወጣቱ ትውልድ ያገባኛል ይገባኛልም  ሲል ደስ ይላል። ደስታ ብቻም ሳይሆን ተስፋም ይሰጣል። ይልቃል ሰማያዊን ፓርቲዬ ብሎ ያላወቀውን ሲያሳውቅ ያወቀውንም  ሲያጠምቅ ሰንብቶ ወደ አገር ቤት የመልስ ጉዞ ከማድረጉ በፊት ለምታደርጉልን ድጋፍ አድናቆት አለኝ በማለት የኢትዮጵያ የወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክን እድምተኞች አመስግኖ እንደጋገፍ እንበርታ በማለት ተሰናብቷል። ሌላኛው አጋሩ ብርሃኑም ደከመኝ ሳይል የተጠየቀውን ሁሉ ሲመልስ አርፍዷል። የልብ የልቡን ጥያቄ ያቀረበው እንደልቡም ጥሩ ውይይት መርቷል። ይቺን ማስታወሻ ስጽፍ ውይይቱ በሰፊው ቢሰራጭስ የሚል ማመልከቻ ላስገባ ነበር ግን የልቤን ልባሙ ሰው አውቆ ኖሮ ያሰብኩትን ሆኖ አገኘሁት።
ሰማያዊ ፓርቲ በወጣቶች የተገነባ ድርጅት ነው። እድሜ ጠገብ አዛውንቶችና እውቀት ጠገብ ምሁራኖችም ከጀርባው ይኖራሉ ብለን እናምናለን። እንዳለፈው ትውልድ የሀገር ፍቅር ስሜታቸውን ለሀገር ጥፋት የቆሙ መሰሪዎች እንዳይጫወቱበት ካለፈው በሚገባ ይማራሉ የሚል ተስፋም ይኖራል። ከምንም ነገር በላይ ግን አበቃለት የተባለው ወጣት የበቃለት ቁርጠኛ የነጻነት ታጋይ ሆኖ ሲነሳ ማየትን ያህል የሚያስደስት ነገር የለም። ወጣቱ ታሪክንና ትናንትን መማርያው አድርጎ እውቀትን ግን መመርያው ካደረገ ነገን ያሰበበት መድረሱ እርግጥ ነው። የዛሬዎች ጎልማሶች ትናንት በስሜትና በሀገር ፍቅር ተነስተው ዛሬ አገራቸውን ለሚያምሱ ጎጠኞች መሳርያ መሆናቸውን ሲያስቡ ልባቸው መድማቱ አይቀርም። የዚያኑ ያህል ዛሬን ድረስ የተሰራባቸውን ግፍ መለየት የማይቸሉ ወይም ያንን ቢለዩና ቢናገሩ ታሪካቸውና ህይወታቸው ወና ስለሚሆንባቸው በ’ተከድኖ ይብሰል’ የሚኖሩ ብዙ አሉ ይህንን ለቀጣዩ ትውልድ አልመኝም።
የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ካለፈው ሊማሩ የሚገባው ይህ ነው። ከምንም ነገር በላይ ዛሬ የማሰብና ያሰቡትን የመናገር መብት ያለበት ድርጅትን አጠናክሮ መንቀሳቅስና በተግባር ደግሞ መፈተንን ማስመስከር ይገባቸዋል። የስልጣንና የስራ ክፍፍልን ለሁሉም ማዳረስና ድርጅት አንጂ ግለሰብ ብቻ የሚገንበት እንዳይሆን ተግቶ መስራትም ይጠበቅባቸዋል። የዘመናችንን ጎጠኛና ሁዋላ ቀር ገዢ ማንነት በሚገባ እንዲታይ ዱላውንና ጥቃቱን ተቀብለው በቁርጠኛነት መነሳታቸው ደግሞ  ያኮራል። ከዘረኞቹ ገዢዎች ጋር ከሚደረገው ትግል ባሻገር ደግሞ የተኙትን የሚያነቃ የሰነፉትን የሚያበረታ ስራ መስራታቸውም ግሩም ነው። ተባብሮ ከመተኛት ከፊት ቀድሞ ሌሎቹንም ማነሳሳትም  ቸል የሚባል አይደለም። አንዳንዴ ከትብብርና ከውህደት በፊት መሆን ያለባቸው ነገሮችን በመዘንጋት የትብበር ጥሪ ማብዛቱም ደግ አይደለም። ስኳር ቡናው ውስጥ ስለገባ አያጣፍጠውም  ከስር ሄዶ ይተኛል እንጂ፣ እንዲጣፍጥ መማሰል አለበት። ቡናው እስኪፈላ መቆላት መፈጨት መንተክተክ አለበት ስኳሩም  እንዲሁ ብዙ ጉዞ አለው። እንዲያም ሆኖ መጥፎ ቡናን በስኳር ብዛት ማጣፈጥ አይቻልም። ድርጅቶችንም  ተባበሩ ስላልናቸው  ጠንካራ ና ውጤታማ ሊሆኑ አይችሉም።
በመጨረሻም ምሰጋናና ማበረታቻችን ሁሉ እያደረግን ከቀይ ወደ ሰማያዊ የምናደርገው ጉዞ የተሳካ እንዲሆን  ድጋፋችን አይለያቸው። “ግባችን እሩቅ መንገዱ ጠመዝማዛ ነው” ከሚለወ ተስፋ አስቆራጭ መፈክር “መንገዱ በስኬት የተሞላ ከግብ  መዳረሻችንም ቅርብ ነው” በሚል አዲሰ መፈክር  ልሰናበት።
http://ecadforum.com/Amharic/archives/10824/

Monday, January 27, 2014

“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”


teddy


ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣልፍቅር ያሸንፋል– የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው
እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው
የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡
መነሻው ምንድነው? “አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤
የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣
ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣
አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…”
እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት – ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን ለመጓዝ፣ ትልቁ መድሃኒት ፍቅር ነው፡፡ ይቅር ተባብሎ የቀድሞ ስህተቶችን ለማስተካከልና በህብረት ተጠራርቶ የቀድሞ ትክክለኛ ነገሮችን ለማሳደግ፣ ፍቅር ያስፈልጋል፡፡ አቡጊዳ ብለን ነው ፍቅርን የምንጀምረው፡፡ “ዳህላክ” ላይም፣ ለልጆቻችን ቂምን አናውርስ ብለናል፡፡ “ካስተማርሽው ፍቅርን በጊዜ፣ አይሻለሁ ወይ ባሱ ጊዜ…” ኢትዮጵያና ኤርትራ ተራርቀው የተፈጠረው ግጭት የሩቅ ጊዜ ታሪክ አይደለም።
የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው ግጭት፣ ብዙ የተበተነ ቤተሰብ፣ የደማ ስሜት አለ፡፡ ይሄ ቁስል ዘላለም እንደመረቀዘ መቀጠል አለበት? መዳን መፈወስ የለብንም? ይቅር መባባልን ነው በ“ያስተሰርያል” የዘፈንነው፡፡ ለምንወልዳቸው ልጆች፤ ለምንፈጥራቸው አዲስ ትውልዶች የምናወርሰው ቂምን ከሆነ፣ ያለፈው መቁሰል ሳይበቃ ለወደፊትም ሌላ አደጋ እንዲፈጠር እየተባበርን ነው ማለት ነው፡፡ የሚሻለው መፍትሔ፣ እኛ የወረስነው አለመግባባት ካለ፣ በቂም ሰበብ የተቋሰልነው ነገር ካለ፣ የአዲሱን ትውልድ ህይወት እንዳያውክ፣ እኛ ጋ መቆም አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡
የዘመናችን ፈተናዎች ሳያንሱ፣ የቅርብ ጊዜ የቂም ታሪክንም እየተሸከመን፣ ከዚያም አልፎ የሩቅ ጊዜ የቅሬታ ታሪኩንም እየቆሰቆስን ቂምን የምናወርስ ከሆነ፣ ለማናችንም ሕይወት የማይጠቅም፣ የልጆቻችንንም ተስፋ የሚያጨልም አደጋ እየፈጠርን እናልፋለን፡፡ ቂምን መሻር፣ ቁስልን መፈወስ፤ ከዚያም አልፎ ለሁላችንም የሚበጅና የተስፋ ብርሃንን የሚያደምቅ ነገር መስራት የምንችለው በፍቅር ነው፡፡ ከ “አቡጊዳ” እስከ “ያስተሰርያል”፣ “ዳህላክ”፣ ቀላል ይሆናል”…እና ሌሎች ዘፈኖች ይህንን መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡ ግን ልዩ አዋቂ ስለሆንኩ ወይም ልዩ ሃይል ስላለኝ አይደለም፡፡ በፈጣሪ ሃይል ነው። ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣል። የትውልዱን ድምጽ በኔ አድርጐ ማውጣቱን አምናለሁ፡፡ አሁን፣ ቅን እና ጥሩ ትውልድ አለ፡፡ የዚህ ቅን ትውልድ ድምጽ የፍቅር ድምጽ ነው። ግራ የሚያጋቡ፣ የሚያስጨንቁና የተተበተቡ ችግሮች ሁሉ በፍቅር ይፈታሉ፡፡ ከቂም፣ ከቁስል በፍቅር እንዳን፣ ፍቅር ያሸንፋል የሚለው መልዕክት የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነው፡፡ ይህ ቅን ትውልድ ተቀራርቦ፣ ተሰባስቦ አንድ ላይ የፍቅር ድምፁን የሚያስተጋባበት እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ነው የፍቅር ጉዞ፡፡
በፖለቲካም ሆነ በሌላ ምክንያት፣ በተለያየ ችግርና አለመግባባት በአገራችን ለተከሰተው ቂምና ቁርሾም፣ እዚህ አገር ቤትም ሆነ በየአገሩ ተበታትነው የሚገኙ ወገኖቻችን፣ ቢያንስ ለልጆቻቸው ሲሉ ይቅር መባባልን እንዲቀበሉ ለመጋበዝ፤ የአዲሱ ትውልድ ስሜትም ይሄ እንደሆነ የሚገልፁ ዝግጅቶችን ለማቅረብ ነበር ያቀድነው፡፡ ዝግጅቱን በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች በስፋት ለማዳረስ ነው፤ በሄኒከን ከሚተዳደረው በደሌ ቢራ ጋር ተነጋግረን ውል የተፈራረምነው፡፡ በተፈራረምንበት እለት እንደተገለፀውም፤ የቋንቋና የብሔር ስብጥር ውስጥ ህብረትና አንድነታችንን የሚያጠናክር፣ ቂም እንዳንወርስና መልካም መንፈስን ለመጋራት አንድ ላይ የሚጮህ የፍቅር አላማ ያለው ዝግጅት ነው፡፡ ግን፣ የኢትዮጵያ ታሪክም ሆነ የኢትዮጵያውያን ሕይወት አንተ እንደምትለው፣ በፍቅርና ሰላም ብቻ የተሞላ ሳይሆን፣ በቂምና በግጭትም የተበረዘ ነው፡፡
አይደለም? ምን ጥርጥር አለው! ያሉና የነበሩ ነገሮች ናቸው፡፡ የህይወት እና የደስታ ውድነት ትርጉም የሚኖረው ከሞትና ከሀዘን ጋር ነው፡፡ የፍቅር ውበት የሚጐላው፣ ከጥላቻ ጋር ሲነፃፀር ነው። ነገር ግን ያሳዘኑን ነገሮች ላይ ብቻ ስናተኩር፣ አዲሱንና የወደፊቱን ትውልድ ያውካል፡፡ እዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ፍቅር መድሃኒት ነው፡፡ የነገር ሁሉ መጀመሪያና መጨረሻ ነው፡፡ ሁላችንም ህፃናትን ማቀፍና መሳም የምንወደው ለምንድነው? ገና ሲወለዱ፣ ገና ከመነሻው ሲፈጠሩ ፍፁም ፍቅር ስለሆኑ ነው፡፡ ያ የፍቅር ሃይል ነው የሚስበን፡፡ ህፃኑም እናቱ ጉያ ውስጥ የሚገባው በፍቅር ሃይል ነው፡፡
እንኳን ሰውን የመሰለ ክቡር ፍጥረት ይቅርና አውሬ የምንላቸው እንስሳት ውስጥም የምናየው የተፈጥሮ ሃይል ነው፤ ፍቅር፡፡ ነገር ግን በኑሮ ውስጥ በብዙ ውጣ ውረድ፣ ብዙ ቅሬታዎችና እንከኖች ስለሚያጋጥሙን ፍቅራችንን ሊበርዙብን ወይም ውስጣችንን መርዘው የውስጥ ህመም ሊሆኑብን ይችላሉ፡፡ ባዘንበትና በተቀየምንበት ነገር ላይ ቆመን ተውጠን ስንቀር በሽታ ይሆኑብናል፡፡ ለቅያሜ እልባት እየሰጠንና እየሰረዝን ካልሄድን፣ ይባስ ብለን ለልጅ ልጅ እያወረስን ከቀጠልን፣ በማህበረሰብ ደረጃ እንደዝገት ውስጣችንን እየበላ ይጨርሰናል ወይም እንደተዳፈነ እሳት በሆነ አቅጣጫ ተግለብልቦ ያቃጥለናል፡፡
እና ምን ይሻለናል ብለን ስናስብ፣ በቀድሞ ዘመን ወይም ባለፍንበት ጊዜ የተፈፀሙ መልካም ነገሮችን ወይም ስህተቶችን እንዳልነበሩ ማድረግ አንችልም። ወደኋላ ተመልሰን በህይወት የሌሉ ሰዎችን መሸለም ወይም እዳ ማስከፈል አንችልም፡፡ እነሱ በዘመናቸው አልፈዋል፡፡ ነገሩ ያለው የዛሬ ነዋሪዎች ላይ ነው፡፡ በቀድሞ ሰዎች ታሪክ የምንደሰትበትና የምናዝንበት፣ ትክክል የሆኑና የተሳሳቱ ስራዎች፣ የወደድነውና የተቀየምንበት ነገር ይኖራል፡፡ ቀጥለው የመጡ ትውልዶች የትኛውን ስሜት መያዝ፣ የትኛውን ስሜት ማውረስ አለባቸው? እኛስ የትኛውን ወርሰን የትኛውን ማሳደግ አለብን? ቅሬታና ቂምን ይዘው ያወርሱናል ወይስ ፍቅርንና መዋደድን? ቅያሜና ቂም ብንወርስ ምን ይበጀናል? ወደ ኋላ ተመልሰን እዳ ማስከፈል አንችል? ህይወት የሚቀጥለው፣ ካለው ነገር ላይ በመነሳት ነው፡፡ ስህተቶችን ትተን፣ ትክክል የሆኑትን ይዘን፣ ያን እያሳደግን ነው መቀጠል ያለብን፡፡
ታላላቆቻችን በተለያዩ አለመግባባቶች ውስጥ ያልፋሉ፡፡ አለመግባባትና ቅሬታ ባይፈጠር መልካም ነበር፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ቢያንስ፣ የታላላቆችን አለመግባባት ወደ አዲሱ ትውልድ እንዳይሻገርና መጪውን ጉዞ እንዳያውክብን፣ ታላላቆቻችን ስለ አዲሱ ትውልድና ስለመጪው ትውልድ መጨነቅ ያስፈልጋቸዋል ብዬ አስባለሁ። ፍቅር ያሸንፋል የሚለው የታናናሾች የአዲሱ ትውልድ ድምጽም ጐልቶ መሰማት እንዳለበት አምናለሁ፡፡ የፍቅር ጉዞ የዚህ የአዲሱ ትውልድ መንፈስ ነው፡፡ የፍቅር ጉዞ ዝግጅት ከበደሌ ቢራ ጋር ተፈራርመህ በሳምንቱ ነው ውዝግብ የተፈጠረው። እንዴት ነበር የሰማኸው? ከጊዜ በኋላ ነው የሰማሁት፡፡
አንደኛ በድሬዳዋ አንድ ተብሎ የሚጀመረው ጉዞ፣ ትልቅ የፍቅር መልዕክት የያዘ ስለሆነ፣ ያልተበታተነ ትኩረት ይፈለጋል፡፡ ከዚህ ውጭ ባለው ጊዜ ደግሞ፣ በሚቀጥለው መስከረም ወይም ብዙ ሳይቆይ አዲስ አልበም ለማድረስ የጀመርኩት ስራ አለ፡፡ ሁለቱም ቀናተኛ ስራዎች ናቸው፡፡ አእምሮህ ሌላ ነገር እንዲያስተናግድ አይፈቅዱልህም፡፡ በዚህ ምክንያት፣ ባልደረቦቼ በኢንተርኔት በተፈጠረው ውዝግብ ዙሪያ ሊያናግሩኝ ሲሞክሩ ስራ ላይ ሆኜ ብዙም ፈቃደኛ አልነበርኩም፡፡ ሲደጋገም ግን ሰማሁ፡፡ ማኔጀሬ (ዘካሪያስ) ተጨንቆ ነው የነገረኝ። ከሥራ አስኪያጅ አንፃር ሆነህ ስታየው መጨነቁ አይገርምም፡፡ ግን ተረጋግተን ነው የተነጋገርነው፡፡ አልተረበሻችሁም? ነገሩን አቅልለን አላየነውም፡፡ የፍቅር ጉዞ ትልቅ ዝግጅት ነው፡፡
ነገር ግን፣ በብዙ ወጣ ገባ መንገድ ከማለፍ እና ብዙ ውጣ ውረድ ከማየት የተነሳ፣ ችግሮችን ማስተናገድ ትለማመዳለህ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ የፍቅር መልእክት፣ በቴዎድሮስ ካሳሁን የተፈጠረ ሃሳብ አይደለም፡፡ የነበረ ያለና የሚኖር የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡ ያንተ ድርሻ ያ ሃሳብ ሲሰጥህ መቀበል ነው እንጂ፤ አንተ ከምትጨነቀው በላይ ከምንም አስበልጦ፣ ፈጣሪ ስለ አላማውና ስለሃሳቡ፣ ስለ እኛ እና ስለትውልዱ ስለሚጨነቅ፣ ብዙ አልተሸበርንም፡፡ ሁሉንም ነገር ለበጐ ያደርገዋል ብዬ አምናለሁ፡፡
“ጥቁር ሰው” በሚለው ዘፈንህ በአድዋ ጦርነት ዙሪያ ምኒልክንና ሌሎች የታሪክ ሰዎችን በማንሳት ዘፍነሃል፡፡ የምኒልክ ታሪክ ላይ ያለህን አስተሳሰብ በቅርቡ ቃለ ምልልስ አድርገህ በመጽሔት ታትሟል፡፡ ከዚህ ቃለ ምልልስ ጋር ተያይዞ ነው የምኒልክ ጦርነት ቅዱስ ነው የሚል አወዛጋቢው አባባል የተሰራጨው፡፡ በመጽሔት ታትሞ በወጣው ቃለምልልስ ላይ፣ እንደዚያ አይነት አባባል የለም፡፡ “አካሄዱን ያየ አመጣጡን ያውቃል” በሚል ርዕስ በእንቁ መጽሔት ታትሞ የወጣውን ቃለምልልስ ማየት ይቻላል፡፡ በምኒልክ መቶኛ የሙት ዓመት መነሻነት የተደረገ ቃለምልልስ ነው፡፡
በዚህ ቃለምልልስ ውስጥ ማንንም የሚያስቀይም አባባል የለበትም፡፡ ነገር ግን በኢንተርኔት ሲሰራጭ የኔ ያልሆነ አባባል ታክሎበት የተከፉ ሰዎች እንዳሉ ስሰማ፣ የተሳሳተውን መረጃ ለማስተካከል ምላሽ ሰጥተናል፡፡ እኔ ብቻ ሳልሆን፣ የመጽሔቱ አዘጋጅም አወዛጋቢው አባባል እኔ የተናገርኩት እንዳልሆነ፣ በመጽሔቱ ህትመት ውስጥም እንዳልነበረ አስረድቷል፡፡ ነገር ግን ውዝግቡ በዚህ አልተቋጨም፡፡ ለምን የፍቅር ጉዞን የሚያስተጓጉል ነገር ተፈጠረ አልልም፡፡ እዚህ ምድር ከተገለጡትም ሆነ ካልተገለጡት ሃይሎች ሁሉ የሚልቀው ፍቅር ነው፡፡ ክብደቱም የዚያኑ ያህል ነው፡፡
ስለዚህ የፍቅር ጉዞ ብለህ ስትነሳ፣ ያለ እክል እና ያለ ችግር ትደርሳለህ ማለት አይደለም፡፡ እንኳን ትልቁና ከባዱ ጉዞ ላይ ይቅርና፣ እንደ ቀላል የምናያቸው ጉዞዎች ላይም፣ ወደ ናዝሬት ወይም ወደ አዋሳ ለመሄድ ስትነሳ እንኳ፣ በመኪኖች መጨናነቅ ጉዞህ ሊጓተት ይችላል። ጐማ ቢተነፍስ ወይም ሞተር ቢግል፣ ጐማ ለመቀየርና የራዲያተር ውሃ ለመለወጥ መቆምህ አይቀርም፡፡ ከሁሉም የከበደው የፍቅር ጉዞ ላይማ፣ ለምን ፈተና ይፈጠራል ማለት አይቻልም። ከምንም በላይ ይቅር መባባልን የሚያበዛ የእርቅ መንፈስን ይዘህ ስትጓዝ፣ እንዲያውም ከተቻለ ታላላቆችህም እንዲግባቡልህና መግባባትን እንዲያወርሱ ስትጮህ፣ በዚህ ምክንያት ካንተ ጋር የማይግባባ ነገር ሲፈጠር፣ ነገሩን ንቀህ የምታልፈው አይሆንም፡፡ ምንም እንኳ፣ በተሳሳተ መረጃ ምክንያት የተፈጠረ ቅሬታ ቢሆንም፣ አንተም በተራህ የቅሬታ ባለቤት መሆን የለብህም፡፡ ፍቅር ሁሉንም ያቅፋል፡፡ በተሳሳተ መረጃ የተነሳ ያልወደደህንም ሰው ማቀፍ አለበት። የቃለምልልሱ ሁለተኛ ክፍል በሚቀጥለው ሳምንት ይጠብቁን፡፡ (አዲስ አድማስ)
http://www.goolgule.com/teddy-afro-love-is-more-powerful-than-hate-and-revengee/

በ‹‹ልማታዊ ጋዜጠኝነት›› እና በ“ኢትዮ ሱዳን ድንበር” ላይ ውይይቶች ተዘጋጁ

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ “በልማት ጋዜጠኝነት” ዙሪያ የፓርቲና የመንግስት ተወካዮች አቋማቸውን የሚገልፁበት ውይይት ለዛሬ ያዘጋጀ ሲሆን፤ ሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮ ሱዳን ድንበር በተመለከተ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም ሃሳብ የሚያቀርቡበት ውይይት ያካሂዳል፡፡ 
‹‹ልማታዊ ጋዜጠኝነት›› በሚለው ርዕሰ ጉዳይ የተለያዩ ሃገሮችን ልምድ የሚያሳይና በኢትዮጵያ የሚኖረውን ቦታ የሚፈትሽ ውይይት በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል እንደሚካሄድ የገለፀው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒዩኬሽን ትምህርት ክፍል፤ የፓርቲ እና የመንግስት ተወካዮች አቋማቸውን እንደሚያቀርቡ ጠቁሟል፡፡ 
“ልማታዊ ጋዜጠኝነት” ለድሃ አገራት የሚጠቅምና የሚስማማ ነው በማለት የሚደግፉ እንዳሉ ሁሉ፤ በተቃራኒው ጋዜጠኝነት የመንግስት ጥገኛና አፈቀላጤ እንዲሆን ያደርጋል በማለት የሚተቹ መኖራቸው ይታወቃል፡፡ 
በሌላ በኩል የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ ዛሬ በዘጠኝ ሰዓት በጽ/ቤቱ ውይይት የሚያዘጋጀው ሰማያዊ ፓርቲ፤ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ልምድ እንዳላቸውና ሃሳባቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጿል፡፡ መንግስት፣ ከሁመራ እስከ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ድረስ ባለፉት ሁለት ወራት ድንበር እያካለለ መሆኑን በሱዳን የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች እንደተሰራጨ የገለፀው የፓርቲው የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ ዮናታን ተስፋዬ፤ መንግስት ጉዳዩን ደብቆ ይዟል ብሏል፡፡ 
መንግስት በድንበር ጉዳይ የሚሰነዘሩ ትችቶች መሰረት የለሽ ናቸው ብሎ ማስተባበሉ ይታወሳል። 


http://addisadmassnews.com/

Saturday, January 25, 2014

የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው አቶ በቀለ ገርባ አልተፈታም፤

የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው አቶ በቀለ ገርባ አልተፈታም፤ በውሸት በተቀነባበረ ሴራ በህገወጥ ፍርድ በግፍ ያለ አግባብ የታሰረውና እና አሁን የእስር ጊዜውን ጨርሶው ያልተፈታው መምህር በቀለ ገርባ። «አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው» የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች በእስር ቤት የሚገኘው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በባለፈው እሁድ የእስራት ቅጣቱን አጠናቆ የነበረ እና መፈታት የነበረበት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ነው የሚገኘው። በቅርቡ ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ቃሌቲ ሄደን አግኝተነው ነበር። አመክሮ ለማግኘት እንደ መስፈርት የሚወሰደው፤ በቆይታው ወቅት የነበረው ስነ ምግባር በበቂ ሁኔታ እንዳሟላ እንደተገለፀለት ነግሮናል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቱ በፊት ማእከላዊ ያሳለፋቸው 41 ቀናት ሲደመሩ ነው ባለፈው እሁድ መውጣት የነበረበት። ማእከላዊ በእስር የቆየባቸው ቀናት መያዝና እና አለመያዝ የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር የይሁንታ ፈቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ ተነግሮታል። በህጉ መሰረት ከሆነ ግን ማንም መፍቀድ ሳይጠበቅበት ሊደመርለት ይገባ ነበር። ትላንት ይህን ጉዳይ ይዘው የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ለጠየቁ ቤተሰቦቹ «አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው» የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በቀለን ለመጠየቅ የሚፈልግ በስራ ቀናት ጠዋትና ከሰዓት፤ በእረፍት ቀናት ደግሞ ጠዋት ብቻ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን 2 ሄዶ ማግኘት ይችላል። ፍትህ ለበቀለ ገርባ!

Thursday, January 23, 2014

ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት (ዳዊት ከበደ ወየሳ፣ አትላንታ)


Reeyot Alemu, the 31 year-2012 Courage in Journalism Award winner.
(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)
ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ:: የማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በሚከበርበት ወቅት በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያደረገው አስተዋፅኦ ይታወሳል:: በህይወት በነበረበት ወቅት ለሰው ልጅ እኩልነት ተሟግቷል; የነጻነት ቀንዲልን ለኩሷል:: ሆኖም እኩልነት እና ነጻነትን ሳያጣጥም በበርሚንግሃም እስር ቤት ተጥሎ ፍዳውን እንዲቆጥር ተፈርዶበት ነበር:: በመጨረሻም የሰውን ልጅ ክብር እና ነጻነት በማይደግፉ ሰዎች ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል – መልካም ስራዎቹ ግን አላለፉም::
ዛሬም በአገራችን ስለፍትህ, ስለነጻነት የሰበኩና የደሰኮሩ; የጻፉና የመሰከሩ… ለሃቅ ቆመው፣ ግፍ የተሰራባቸው፣ ከአገር የተሰደዱና የወጡ፤ በግፍ ሰንሰለት ለጨለማ እስር የተዳረጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮት፣ አንዷለም እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በሰብአዊነት መሰረት ላይ ስላነጹ እና ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ መጨረሻቸው እስር እና እንግልት ሆኗል::
እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ… ብሎም የህዝብ ልሳን ሆኖ ለህዝብ የቤዛነት ዋጋ መክፈል የሚያስከብር እንጂ የሚያሳስር አልነበረም:: በመሆኑም ለነጻ ፕሬስ መክፈል የሚገባቸውን ዋጋ ከመጠን አሳልፈው የከፈሉት፤ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታዬ… ሶስቱም ከአገራቸው አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል:: በአለም አቀፍ ደረጃም በልዩ ልዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትና ተቅውውማት ለሽልማት ታጭተው አሸናፊ ሆነዋል::
የ’ነዚህ የስራ ባልደረቦቼ ብዕር… ህዝብን ሳይሆን የተወሰኑ ወገኖችን አሸብሮ ሊሆን ይችላል:: እነርዕዮት አለሙ በዚህ አይነት ሰበብ አስባብ በቃሊቲ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ታግተው፤ ነጻነታቸውን አጥተውና ህክምና ተነፍገው ይታሰሩ እንጂ፤  ለእውነት የቆሙ ወገኖች ግን ለመልካም ስራቸው ሽልማትን አልነፈጓቸውም::
ማርቲን ሉተር ኪንግ በበርሚንግሃም እስር ቤት ታስሮ ቢማቅቅም የአሜሪካም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አልዘነጋውም:: ቆይቶም ቢሆን የአለም አቀፉ ኖቤል ተሸላሚ እስከመሆን ደርሷል:: ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የኖቤል ተሸላሚ ባይሆኑም አለም ግን አልረሳቸውም:: ከታሰሩበት የጨለማ ወህኒ ቤት ጀርባ፤ ከብረት ፍርግርግ እና ከግድግዳዎቹ ባሻገር በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህን ጋዜጠኞች በመልካም ስራቸው ያስታውሷቸዋል; ይዘክሯቸዋል:: ስለሆነም የጻድቃን ሞት፤ የሰማዕትነት ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠረው ሁሉ… የነ እስክንድር፣ ውብሸትና ርዕዮት እስር፤ ከቶውኑ ዋጋ ቢስ እና ፍሬ አልባ ሊሆን አይችልም::
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት በፕሬስ ጉዳይ ተደጋጋሚ የሆነ እስር ደርሶብኛል:: በ’ነዚህ የእስር እና እንግልት ጊዜያት ግን… ከጨለማው እስር ቤት ማዶ ለምን እንደታሰርኩ የሚረዱ ሺዎች በመኖራቸው ሁልጊዜ እጽናና ነበር:: በተደጋጋሚ እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀኝ እና የዋስ መብቴን አስጠብቆ ከእስር እንድወጣ ያደርገኝ የነበረው ወላጅ አባቴ፤ “የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው:: ስለዚህ አንገትህን ቀና ልታደርግ እንጂ ልትሸማቀቅ አይገባህም::” የሚል አጽናኝ ቃል ሁሌ ይነግረኝ ነበር:: ዛሬ አባቴ በህይወት የለም:: ቃሉ እና ምክሩ ግን አብሮኝ አለ:: በእስር ላይ ለሚገኙ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ “አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” የሚለውን መልዕክት አጋራቸዋለሁ::
ዛሬ በጋዜጠኞቻችን ላይ የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው መታሰራቸው ሳያንስ; ከታሰሩም በኋላ በሃሰት ሊወነጅሏቸው የሚሹ ብዙ ግራ ዘመም ሰዎች መኖራቸውን ታዝበናል:: በአሜሪካ ከፍተኛ የአየር ሽፋን አግኝቶ ዲሞክራቶችን በመሳደብ የሚታወቀው ራሽ ሊምቦ የተባለ ጋዜጠኛ በቅርቡ ኔልሰን ማንዴላ በሞት ሲለዩ… “ብታምኑም ባታምኑም ኔልሰን ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ::” ብሎ ሰፊ ሙግት ፈጥሮ ነበር:: ይህ አባባሉ ለኛ እና ለሌሎች አፍሪቃውያን ሊገርመን ይችል ይሆናል:: ነገር ግን የራሳቸው አመዛዛኝ ህሊና ያልፈጠረባቸውና ይህን ሰው በጭፍን የሚከተሉት ሰዎች “አዎ ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ” ብለው ቢሉ ሊገርመን አይገባም::
ዛሬም ባገራችን በተመሳሳይ መልኩ የነርዕዮት አለሙን መልካም ስም ጥላሸት ለመቀባት እላይ ታች የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ… እኛ ግን እንላለን:: “ወንጀል አልሰራችሁምና አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” ስማችሁ ከቃሊቲና ከቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ፤ በጠራው ሰማይ ላይ ያንጸባርቃል፤ ቃለ ሃቃቹህ በአየር ናኝቶ… ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ሁሉ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቷል::
የማርቲን ሉተር ኪንግ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቹ እንደሚወደሱ ሁሉ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት የነርእዮት አለሙ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቻቸው በተደጋጋሚ ይነሳሉ ይዘከራሉ:: ዛሬ ማንዴላን አሸባሪ ብለው የሚከሱ ሰዎች እንደመኖራቸው መጠን; በተመሳሳይ መልኩ ለነርእዮት አለሙ ተመሳሳይ ስም የሰጡና ያሰጡ… ለመስጠት እና ለማሰጠት የሚጥሩ ሰዎች አሉ:: እኛ ግን የተለኮሱ ሻማዎች ይዘን ልደት ስናከብር; የብርሃናችን  ጮራ፤ ሌሎች የፈጠሩትን የጨለማ ድባብ ሰንጥቆ… አንዳች ብርሃን እንደሚፈነጥቅላቸው በማመን ነው:: ዛሬ የርዕዮት አለሙን የልደት ቀን ስናከብር፤ ያለፍትህ የታሰሩትን ፍትህ የሚፈልጉትን፤ ነጻነት የተጠሙትን ነፍሶች በማሰብ ጭምር ነው::
መልካም ልደት – ርዕዮት!

Wednesday, January 22, 2014

ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ

ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው።
በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል።
ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ የሚጠራውን ቦታ አልፈዋል” በሚል  ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሰርቶ ኮሚቴ መቋቋሙን ያወሱት ባለስልጣኑ፣ “ይሁን እንጅ ኮሚቴው ምንም አይነት የድንበር ማካለል ሳያደርግ እስከዛሬ ቆይቷል ።”
“አሁን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን ውይይት የምትገዛው ደብዳቤ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡት ደብዳቤ መሆኑን  ባለስልጣኑ ጠቅሰው ፣ ኮሚቴው በጊዜው ችግሩን በሰላም ለመፍታት የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበርም አክለዋል።
“ሱዳኖች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት ለመውሰድ አቅም አልነበራቸውም ” የሚሉት ባለስልጣኑ ፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995/96 የግብጹን መሪ አዲስ አበባ ላይ ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ የ ትግራይና የአማራ ክልሎች ለኢንቨስተሮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የሱዳን  መሬት  መስጠታቸውን ገልጸዋል። ሱዳኖች ቀደም ሲል ጀምሮ ግዛታችንን መልሱ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥያቄያቸው እየገፋ ምጣቱን አብራርተዋል። 1965 ዓም ጀምሮ መሬት የሚባል ለሱዳን አለመሰጠቱትነ አጠንክረው የተናገሩት ባለስልጣኑ፣ በቅርቡ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ሱዳኖች ያቋቋሙት ኮሚቴ አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡን ገልጸዋል።  አዲሱም ሀሳብ ” መሬቱን እንደያዛችሁት ቆዩ፣ የዜጎቻችሁን መብቶች እናስጠብቃለን፣ ነገር ግን ቢያንስ በንደፈ ሃሳብ ደረጃ መሬቱ የእኛ መሆኑን የሚያሳየውን ካርታ ተቀብላችሁ አረጋግጡልን ” የሚል መሆኑን ባለስልጣኑ አስረድተዋል
“በረኻት የሚባል የትግራይ ከተማ ላይ ሆናችሁ ሞባይላችሁን ብታወጡ የሚያሳያችሁ ሱዳንን ነው፣ እንዲሁም አርማጭሆ ላይ ሆናችሁ ሞባይሎቻችሁን ብታዩ ያላችሁበት ኢትዮጵያ የሚባለው ቦታ ሱዳን ነው ” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ “የፈለገውን ፖለቲከኛ መሸወድ ይቻላል፣ ሳይንሱን ግን መሸወድ አይቻልም” በማለት ገልጸዋል
የአርማጭሆ መሬት ለሱዳን ተሰጠ እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው ያሉት ባለስልጣኑ ፣  “አንዳንድ ጊዜ የሱዳን ፖሊስ ድፍረቱ ሲኖረው እየገባ ግጭት ይፈጥራል፣ የኛ ሚሊሺያዎችም የሚሰንፉ አይደሉም ፣ እንዲያውም የእኛ ሚሊሺያዎች የሱዳንን ወታደሮች እንደ ወታደር አይቆጥሩዋቸውም” በማለት በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር ፖሊሶች መካከል ያለውን ልዩነት ተናግረዋል።
“አይናችን የሚያየውን ሁሉ እንይዛለን ማለት አይደለም” ያሉት ባለስጣኑ፣ በእርግጥ እንያዝ ካልን ካርቱምንም መያዝ እንችላለን ሲሉ የሱዳንን የመከላከያ ብቃት አጣጥለዋል።
አቶ መለስ በነበሩበት ጊዜ በሱዳኖች በኩል ለቀረበው ሃሳብ መልስ እንዲሰጥ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኮሚቴ በሀሳቦች ልዩነት የተነሳ እስካሁን መልስ መስጠት አለመቻሉንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል።  አንዳንዱ የኮሚቴ አባል “ከአሁን በሁዋላ ሰዎቻችን ተነሱ ቢባሉስ እንዴት እሽ ብለው ይነሳሉ” የሚል ሀሳብ ያቀርባል ብለዋል።
“ጥያቄችን የሞራል እና የሶሻል እንጅ  የህግ ድጋፍ የለውም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው አንዱ የኮሚቴው አባል ቢሆኑም መልስ ለመስጠት እንኳን እንደተቸገሩ ተናግረዋል።
“በ1965 በሞፈር ዘመት መሬት የያዙ አርሶአደሮች ከአርባ አመት በሁዋላ የያዛችሁት መሬት አገራችሁ አይደለም ሲባሉ ቢቃወሙ የሚገርም አይሆንም” የሚሉት ከፍተኛው ባለስልጣኑ፣ “የህግ ክርክሮች ቢነሱ የማንኮራባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ቅሉ እስካሁን ግን የድንበር ማካለል ስራ አልተጀመረም  ።
ሱዳን ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2007 ሰፊ መሬት ከኢትዮጵያ  ለሱዳን መሰጠቱን የአካባቢውን አስተዳዳሪ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።

አዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ


ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ።


የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የድርጅቱ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ከወራት በፊት ከተሾሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር አንዳንድ ወገኞች እያገናኙት መሆኑ ስህሀት ነው ይላሉ ጋዜጠኞቹ።  በተለይ በቀጣዩ አንድ ዓመት በአስተዳደራዊ መልኩ ከሕትመት እንዲወጡ ለማድረግ የታሰቡ ጋዜጦችና መጽሄቶችን ጉዳይ ለማሳካት ቁርጠኝነት እንዳላቸው በመገመት አቶ ዘርአይ መሾማቸውን ይናገራሉ፡፡

አቶ ዘርዓይ በባህርያቸው ግትርና አምባገነን መሆናቸውን ያስታወሱት ጋዜጠኞች፣ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዴሞክራሲ ተቋማት ጉዳይ ላይ ያደረጉት ውይይት ከዕውቅናየ ውጪ እንዲቆራረጥ ተደርጓል በሚል በአንድ የግል ጋዜጣ ተቃውሞ ያቀረበውን አንድ ጋዜጠኛ ያለምንም ማንገራገር ከድርጅቱ እንዲሰናበት ማድረጋቸው የአምባገነንነታቸው አንድ መገለጫ ነው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ያወሳሉ።

የኢቴቪ ባልደረባ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገረው አቶ ዘርዓይን እንደዋና ስራ አስኪያጅ በቀላሉአግኝቶ ማነጋገር፣ችግርን ማስረዳት ለሰራተኞች እንኩዋን የሚቻል አለመሆኑን በመጥቀስ ወደእሳቸው ቢሮ ከመግባትጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ መግባት ይቀል ነበር ብሎአል፡፡

በእሳቸው አመራር ዘመን በድርጅቱ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ሳይቀር የኪራይሰብሳቢነት ዝንባሌ ገዝፎ መታየቱን፣ በተለይ የእሳቸው ተከታይ የሆኑ  ጋዜጠኞች ቢያጠፉ እንኩዋን አይቶ ዝም ከማለት ያለፈ እርምጃ አይወስዱም ነበር ብለዋል፡፡
አቶ በረከት ስምኦን የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ዓመታት ከአቶ ዘርዓይ ጋር መግባባት እንዳልነበራቸውና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አቶ ዘርዓይ ታዛዥነታቸው ከማንም ይልቅ ለህወሃት ሰዎች ብቻ በመሆኑ ነው ሲሉ ጋዜጠኞች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አቶ በረከት አዛዡን ማንሳትም፣ መቃወምም ተቸግረው መቆየታቸውን ጋዜጠኛው ተናግሯል።

የአቶ ደስታው ከብሮድካስት ባለስልጣን ዳሬክተርነት ሲነሱ ምናልባት በራሱ የሚተማመን ፣ሕግና ስርዓትን ብቻ አክብሮ የሚሰራ ተሹዋሚ ሊመጣ ይችላል የሚለውን ጭላንጭል ተስፋ የአቶ ዘርዓይ ሹመት እንደሻረው ጋዜጠኛው አክሎ ተናግሯል።

በቦረና ኦሮሞና በቡርጂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች እየተሰደዱ ነው

ቦረና አከባቢ የሚኖሩ ቡርጂዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የግጭቱ መንስኤ በቡርጂ መንደር ተገድሎ ተገኘ ተባለ የቦረና ብሄረሰብ አባል አስከሬን ነው፡፡ ባለፉት 70 እና 80 ዓመታት በዚያ አከባቢ ከመኖራቸውም በላይ የኦሮሚኛ ተናጋሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቡርጂዎች ዛሬ ለመፈናቀል ያበቃቸው ምክንያት ሴራ እንሆነ ይናገራሉ፡፡ እንደአስተያየት ሰጪዎች መረጃ ታህሳስ 25 በድሬ ወረዳ ሜጋ ከተማ የቡርጂ ተወላጅ ተማሪዎች ክፍል እንዳይገቡ ተከለከሉ፡፡ በ27/ 04 /2006 ዓ.ም በቦዳ ጫጩ ሩምሴ ቀበሌ አቶ ጃርሶ ተባለ የቦረና አባል ሁን ተብሎ በካድሬዎች የግጭት መንስኤ እንዲሆን የተቀነባበረ ሴራ ተገድሎ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ በዚሁ እለት በቦዳ ዜሮ ቀበሌ አቶ ገልገሎ ሁቃ የተባለ የበረና አባል ተገድሎ ተገኘ ፡፡ በዚሁ ግጭት ጫልሰሞ ጮልጎ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባል በኢታኔ ገልዶ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ሱማሌ ህርቦ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ ደግሞ በቦዳ ዜሮ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ቦዴ ፊርጤ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባልም ተገደሉ፡፡
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የቡርጂ ሰዎች
1. አቶ ጉዮ ሞሉ
2. አቶ እብቻ ሎሌ
3. አቶ ብሩ አሸቱ
ቡርጂዎች ይህንን ተከትሎ
1. ቦዳ ዜሮ ቀበሌ
2. ቡላዳ ቀበሌ
3. ዲደ ሜጋ ቀበሌ
4. ኦላ ሰፋ መንደር ተፈናቀሉ ሲሆን በሜጋ ከተማ የህዝብ አዳራሽ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

በግጭቱ የተነሳ ከአንድ ሺህ በላይ ቡርጂዎች መሰደዳቸው ታውቋል፡፡

Monday, January 20, 2014

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!

ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
 
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።Ethiopian government to hand over land to Sudan
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን  እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን።
ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ  ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ  የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።
“የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-” ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን  የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!  በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!

Saturday, January 18, 2014

ለሕዝብ ግልፅ ያልሆነው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ


በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን aበርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።
በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳዩን በተመለከተ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መረጃ እንደሌለው ገልፀዋል። ነገር ግን በግል በሁመራ ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃውን ለማጣራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በሁመራ የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰብ ነዋሪዎች “መሬቱ ለሱዳን ይሰጣል” ተብሎ እየተወራ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል። በተጨማሪም የአካባቢው ባለስልጣናትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውንም የሚገልፁት አቶ አብርሃ ባለስልጣናቱም “የምናውቀው ነገር የለም” እንዷላቸውም ነው የገለፁት።
ፓርቲው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እያጣራ መሆኑን የገለፁት አቶ አብርሃ፤ ከስርዓቱ ባህሪ በመነሳት በድንበር ማካለሉ ላይ እምነት መያዙ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። “ሥርዓቱ ለስልጣን ብሎ እንጂ የሀገር ድንበር ለመጠበቅ አይደለም። ከዚህ ጉዳይ ተነስቶ የኤርትራን ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የሱዳንም ጉዳይ ሊያጠራጥር ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ያለው ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አለን። ሥርዓቱ ዳርድንበር ከመጠበቅ ባለፈ፤ የውጪ ኃይሎችም ጋር ቢሆን በስልጣን የሚቆይበትን መንገድ ሊያፈላልግ ይችላል” በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል።
የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ በመደገፉ በምትኩ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ተሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬም በተመለከተ አቶ አብርሃ ሲመልሱ፤ “የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩ ነው። ነገር ግን የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ ቢደግፈውም፣ ባይደግፈውም የእኛ ግድብ ነው። የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩና የምንፈልገው ቢሆንም፤ ስለደገፈ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ሊኖር አይገባም። ከአባት፣ አያቶቻችን የተረከብነው መሬት ለሌላ አካል ሊሰጥ አይገባም። ድርጊቱ ተፈፅሞ ከሆነ እንታገለዋለን” ሲሉ መልሰዋል።
“መንግስት በጉዳዩ ላይ ግልፅ መሆን አለበት” የሚሉት አቶ አብርሃ፤ በጉዳዩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግልፅ መደረግ አለበት ብለዋል። ድንበሩ ሲካለልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።
“የድንበር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ኢህአዴግ በመንግስትነቱ ሳይሆን በፓርቲነቱ ስለሚሰራ ጥርጣሬ አለን” የሚሉት አቶ አብርሃ ስለሆነም ለጉዳዩ ማረጋገጫ የሚሆን ግልፅ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ቀጠናው የተረጋጋ ባለመሆኑ የድንበር መካለል እንደሌለበት የጠቀሱት አቶ አብርሃ የድንበር ማካለሉ ሂደት ተጀምሮም ከሆነ መቆም አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች መረጋጋት በሌለበት በድብብቆሽ ወደ ድንበር መካከል መገባት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ታደሰም እንደ አቶ አብርሃ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ነገር ግን መንግስት በውጪ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ጠንከር ያለና ኢትዮጵያውያንን ለሚጠቅም ተግባር ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የድንበር ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንደመሆኑ ግልፅ አሰራርን መከተል አለበት ብለዋል። ከመንግስት ባለፈ ሚዲያውም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
አቶ ጫኔ በመንግስት በኩል የሀገር ድንበርን በተመለከተ የመድበስበስ አካሄድ መኖር የራሱ አደጋ እንዳለው ይገልፃሉ። ፓርቲያቸውም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያሳስበው እንደሆነና በጉዳዩም ላይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት እየጣረ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ፓርቲም በአካባቢው ከሚገኙ አባሎቹም መረጃ የማሰባሰብ ስራም እያከናወነ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ልዩነት እንዳለውም ጠቅሰዋል። ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘም ያሉ ችግሮች የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ችግሮች የሚመነጭ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም በመንግስት በኩል የኢትዮ ሱዳንን ድንበር ማካለል ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጎዳ መልኩ የሚፈፀም ከሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመን የማጋለጥና የመቃወም ስራ እንሰራለን ብለዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ አቋም መወሰዱን ይናገራሉ። ፓርቲው የወሰደው አቋም፤ ጉዳዩን የማጋለጥና ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
“የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡ ጀርባ ሆኖ ድንበር የማካለል ስራ እየተሰራ በመሆኑ እንቃወመዋለን። ጉዳዩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውቀው አይመስለንም። ምን ያህል መሬት ለሱዳን ይሰጣል? ለምንስ ይሰጣል? ታሪካዊ ባለቤትነቱ የማነው? የሚለው መታየት አለበት የሚሉት አቶ ስለሺ፤ ድንበሩን በድብብቆሽ የማካለሉ ተግባር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ፓርቲው ከልዩ ልዩ ምሁራንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሰዎች እንደተረዳው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ባለፉት ሰርዓቶች ቢነሳም ጉዳዩ ሳያስተናግዱት መቆየታቸውን አስታውሰው ኢህአዴግ ግን መነሻው ግልፅ ባልሆነ መንገድ የድንበር ማካለል ጥያቄውን አሁን ማንሳቱን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ኢህአዴግ በሱዳን ድንበር አሸባሪ የሚላቸው ወገኖች ተደራጅተው እንዳይመጡበት ገዢ መሬት ለማሳጣት ድንበሩን ለድርድር አቅርቦ እንደሚሆንም እንገምታለን ብለዋል።
ፓርቲውም ይሄንኑ ጉዳይ እንደ አጀንዳ በመያዝ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ከፓናል ውይይቱ በሚነሳው ኀሳብ ደግሞ ሕዝቡ አቋም እንዲይዝና እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ወደ አካባቢው በማቅናት በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።
“በአሁኑ ወቅት መሬቱ በእርግጥም ለሱዳን አልተሰጠም” ያሉት አቶ ስለሺ፤ ሆኖም ግን በድንበር ማካለሉ ላይ ድርድር ተካሂዶ በወረቀት ደረጃ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም በኀሳብ ደረጃ ተስማምቶ በመጪው መጋቢት የመሬት ርክክብ እንደሚፈፀም የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሆነም ተናግረዋል።
“ጉዳዩን እየደበቀው ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው” የሚሉት አቶ ስለሺ፤ “ነገሩ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነው” ብለውታል። የድንበር ማካለል ጉዳይ የሉአላዊነት በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሊፈፀም አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል። ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ሉአላዊነት ደንታቢስ በመሆኑም የድንበር ማካለሉን ለስልጣኑ ብሎ ከመፈፀም ወደኋላ አይልም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ፓርቲያቸው ሕዝቡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ከማድረግ ባለፈ ኢህአዴግ በድርድር የተስማማባቸው ስምምነቶች በመጪው ትውልድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ነው ጨምረው የገለፁት።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪም እንደሌሎቹ የፓርቲ አመራሮች ጉዳይ የሚያሳስበው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል። አጣሪ ቡድኑ በሚያመጣው መረጃ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ መኢአድ እንደ ፓርቲ ድንበሩ በቅድመ አያቶቻችን አባቶቻችን የተካለለ በመሆኑ እንደገና መከለል የለበትም የሚል አቋም እንዳለው ገልፀዋል። የፓርቲው አቋም የአከላለል ሂደቱ ግልፅ ይሁን አይሁን ከማለት ባለፈ ድንበሩ እንደገና መከለል አይገባውም የሚል እንደሆነ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ድንበር ማካለል ቀደም ሲል በነበሩ ስርዓቶች ሳይነሳ አሁን የተነሳበት ምክንያት የአማራውን ብሔር በመልከአምድር እና በቁጥር ለማሳነስ የሚደረግ ሴራ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ሁሉ ሊቃወመው ይገባል ብለዋል።
በመንግስት በኩል የድንበር ማካለሉን ሂደት ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ በተለይ ጎንደር አካባቢ ሱዳኖች ይገባናል ስለሚሉት መሬት ግልፅ አቋም መያዝ አለበት የሚሉት አቶ አበባው፤ “ሕዝቡ ድምፁ ሊሰማና የታሪክ አዋቂዎችና አባቶች በጉዳዩ ሊጠየቁ ይገባል። ሽፍንፍን ባለ ሁኔታ ድንበር ማካለል ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ ለሱዳንም ሆነ ለኢህአዴግ አይጠቅምም” ሲሉ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን አድርጎ እና እያደረገ ከሆነም እንደገና ነገሩን እንዲያጤነው” ሲሉ አሳስበዋል።
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው የፓርቲው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እየተወያየባቸው ካሉ ሦስት አስቸኳይ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማከለል ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የላላ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጐዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱ አሁንም በዚህ ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ከዚህ በፊትም የሀገሪቱን ታሪካዊ ባለቤትነት በጣሰ መንገድ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መደረጓን አቶ ሀብታሙ አስታውሰዋል። አሁንም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም ስለሚችል ከፍተኛ ሰጋት አድሮብናል ብለዋል።
“በሱዳን በኩል እየተጠየቀ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ነው” የሚሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይሄንን ሉአላዊ ግዛት ለሱዳን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ እንደገና ከተደራደረበት ከሕዝብ ጋር በመሆን የምንታገለው ነው ብለዋል።
እስካሁን በመንግስት በኩል ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲያቸው ደጋግሞ እያሳሰበ መሆኑን የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ የድርድሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ለህዝቡ ግልፅ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
“ከዚህ በፊት ከ60ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የረገፉበት የባድመ ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። የአሰብ ወደብን በተመለከተም ኢህአዴግ ቸልተኛ አቋም በመከተሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ጎድቷል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ አሁንም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል በተመለከተ ኢህአዴግን እንድንጠራጠረው አድርጎናል ብለዋል።
ኢህአዴግ በተፈጥሮአዊ ባህሪውን እና ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚመነጭ አስተሳሰብ መረዳት እንደሚቻለው ግንባሩ በሉአላዊነት ላይ የተዛባ አቋም ያለው በመሆኑ አሁንም የሀገሪቱን ሉአላዊነት በመጠበቅ ላይ ስጋት አለን ሲሉ አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።
“ሀገር ማለት ሕዝብ ነው ነው ብለው ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 60 ሺህ ሰው አስጨርሰዋል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግና የአባይን ግድብ መደገፉን ተከትሎ መሬት ቆርጦ ለመስጠት ከታሰበ ተገቢም፣ ትክክል አይደለም ብለዋል። ድንበር እየሰጡ ግድብ መገደብ ሰጥቶ መቀበል አይደለም በማለት ተቃውመውታል። ግድብ መገደብ የሀገሪቱ መብት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።
በዚሁ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ለማነጋገር ጥረት አድርገናል። ነገር ግን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦፊሴላዊ ጉብኝት ጋር በተያያዘ ስራ ስለበዛባቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በተመሳሳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች በኩልም መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። በመስሪያ ቤቱ አሰራር በቃል አቀባዩ በኩል መረጃ ስለሚሰጥ ሊሳካልን አልቻለም።
በተጨማሪም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ቴሌፎናቸው ስለማይሰራ ልናገኛቸው አልቻልንም። በጠቅላይ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋውን አነጋግረን አቶ ሽመልስን ወይም አምባሳደር ዲናን ብቻ ማነጋገር እንደምንችል ገልፀውልናል። በቀጣይ ሳምንት የመንግሥትን ምላሽ ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።
9