Wednesday, September 11, 2013

ፋክት› መፅሄት ቅዳሜ አትወጣም! (ጋዜጠኛ ተመሰገን ሰሳለኝ )


Temasgan
በዛሬዋ የ2005 ዓ.ም የመጨረሻ ቀን የመፅሄቷ ባልደረቦች ‹ራስ አምባ ሆቴል› ተሰባስበን ነበር፡፡ የምሳ ግበዣውን ጨምሮ ለአራት ሰዓት ያህል በፈጀው ቆይታችን ‹በአዲሱ ዓመት መፅሄቷን በምን መልኩ የተሻለች ልናደርጋት እንችላለን?› የሚለው ዋና የመወያያ አጀንዳችን ሆኖ ውሏል፡፡ በመጨረሻም ሚዲያው ከተመሰረተበት መርህ ጋ የሚስማማ ዕቅድ አውጥተን፣ በሁለት ወር ውስጥ ሙሉ በሙሉ ስኬታማ ለማድረግ ወስነን ተለያይተናል፡፡ የፊታችን ቅዳሜ ይወጣ የነበረው ህትመትም የተሰረዘው፣ በእሁዱ ኤዲቶሪያል ስብሰባ ላይ ሲሆን፣ እንደ ምክንያት ያስቀመጥነውም፣ የአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ዕትም፣ የአዲሱ ዕቅድ ትግበራ እንዲጀመርበት ማስቻል አለብን የሚል ነው፡፡ ዕቅዱ የሁለት ወር በመሆኑ በመጀመሪያው ዕትም ሙሉ በሙሉ አይፈፀምም (በፎቶግራፍ ላይ የምትመለከቷቸው በሙሉ የመፅሄቱ አምደኞች ናቸው)Journalist Temasegan Dasaleg
‹ሞተ ዘኢይመውት (የማይሞት እሱ ሞተ)› ቢልም ግእዙ፣ ኢህአዴግ ‹የሞት አይፈሬውን› (በራሱ አባባል ‹ሞት አይደፍረኝም›) የመለስ ዜናዊን ሞት ያላመነ በሚመስል መልኩ ማደናገሩን ቢያንስ በአዲሱ ዓመት ይተዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ግምገማው ይቀጥላል፡፡
ዛሬ የተጠናቀቀው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ የደረሰበት ድምዳሜ በሁሉም መንገድ የተወጠኑ ተግባሮች ሙሉ በሙሉ በተሳካ ሁኔታ መፈፀማቸውን በማረጋገጥ ሲሆን፣ ሊሳካ ያልቻለው ደግሞ ‹የልማት ሰራዊት› መፍጠሩ ብቻ እንደሆነ ነግሮናል፤ መቼም ኢህአዴግ ‹የልማት ሰራዊት› ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልፅ ነው፤ አባል ማብዛት፣ ማብዛት፣ አሁንም ማብዛት ምድሪቱንም መሙላት ነውና፡፡ በአናቱም ህገ-መንግስቱን ከሚያከብሩ ፓርቲዎች ጋር ተስማምቶ ለመስራት ውሳኔ ላይ መድረሱን አያይዞ ገልጿል፤ የዚህ ትርጓሜ ደግሞ እንዲህ ማለት ነው፡- የእነልደቱና ሞሼን-ኢዴፓ፣ የእነ አየለ ጫሚሶ-ቅንጅትን፣ የእነተስፋዬ ቶሎሳ-ኦብኮን… ወዘተርፈዎች ብቻ ካልሆነ በቀር ሌላ ፓርቲ አልሰማም፤ አላይምም፡፡ የሆነ ሆኖ ይህች ኢትዮጵያ፣ መንግስቷም ኢህአዴግ ነውና መጪው ዘመንም እንዳለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ሁሉ፡- በልተን ማደራችንን፣ የመሰለንን ሃሳብ ማንፀባረቃችንን፣ በህግ-ፊት እኩል መሆናችንን፣ በመረጥነው መተዳደራችንን… እነርሱ ‹ገምግመው› ሲያረጋግጡልን፣ አኛ ደግሞ ‹በባንዲራው…›› እያልን ስንማጠን አሮጊውን እየሸኘን፣ አዲሱን ዓመት እንቀበላለን፡፡ ግና! ማን ይሆን? እንዲህ ‹ኑ እንውረድ ቋንቋቸውንም እንደበላልቀው› ብሎ ሲያበቃ ባቢሎን ያስመሰለን? ሀ/ አሜሪካ ለ/ሻዕቢያ ሐ/መለስና ጓደኞቹ መ/…..
በዛሬው ዕለት ፍትህ ሚኒስቴር ከ400 በላይ ለሚሆኑ እስረኞች ምህረት ማድረጉን ከተናገረ በኋላ፣ እነርሱ-‹ሽብርተኛ›፤ እኛ-የህሊና እስረኞች የምንላቸውን ወንድምና እህቶቻችንን ግን ይህ ምህረት እንደማይመለከት አሳውቋል፡፡ ኢህአዴግ ምን ግዜም እንዲህ ነው፣ እስክንድርን ልቀቅ ሲባል-በስርቆት የታሰሩ ዘራፊዎችን ይለቃል፤ አንዱአለምን ፍታ ሲባል-የትዳር አጋራቸውን በጭካኔ ጨፍጭፈው የገደሉትን ይፈታል፤ አቡበከርን ልቀቅ ሲባል-በአስገድዶ መድፈር የታሰሩትን ይለቃል፤ ‹ዘመነ በርባን›ም ይሏችኋል ይህ ነው፣ ሌላ አይደለም (የመለስ ራዕይ፣ ሙት ዓመት፣ ፋውንዴሽን… ጂኒ ቁልቋል የሚሉትም ‹በርባናዊነት› ካልሆነ ምን ሊሆን ይችላል? መቼም በህግ ከመጠየቅ በተፈጥሮ ሞት ያመለጠን ሰው ሰማየ-ሰማያት ሰቅሎ ‹መሲህ› ማድረግ ከዚህ ውጪ ምን ሊሆን ይችላል?)
በመጨረሻም ምስጋና ሁለት፡-
በትላንታናው ዕለት የታተመው ‹ካፒታል› ጋዜጣ መፅሀፌን (የመለስ አምልኮን) የዓመቱ ምርጥ መፅሀፍ ብሎ መርጧልና ‹እግዜር ያክብርልኝ› እላለሁ፡፡
ገጣሚ ደበበ ሰይፉ፡-
‹አበባዬ ሆይ-ለምለም
አበባዬ ሆይ-ለምለም
አብዮት-ለምለም
መስከረም-ለምለም› እንዲል
የነፃነት ዘመን ይሁንልን!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
Source/WWW. ECADFORUM.COM

No comments:

Post a Comment