Saturday, October 19, 2013

ወድቆ ይነሳል ጀግና..ቴዲ አፍሮ ስለዋልያዉ


ከኦሎምፒክ እና አለም ሻምፕዮኖች መልስ የድል ዜማዎች የተለመዱ ናቸዉ፤እግር ኳሱ ግን በብሶት ዜማዎች ሲታሽ ቆይቶ አሁን ቀን ወጥቶለታል፤መስፍን የተባለ ዘፋኝ “መቼ ይሆን…”በሚለዉ ዘፈኑ የብሶቱን ጣሪያ ነክቶታል፤”ይድነቃቸዉ ቀና ቢሉስ-ጠፍቶ ቢያዩት አሻራቸዉ”,,,እያለ ሆድ የሚያብሰዉን የዉጤት ድርቅ አቀንቅኖታል
፤እንዳለ አድምቄ የኳስ ሜዳን ግርግር ከዉጤቱ ባሻገር ህይወቱን ብቻ ዳስሶታል..ብ ምን አለፋችሁ ከአሁኑ ዋልያ በፊት የነበሩት ለአበበ–ማሞ–ምሩጽ–ሀይሌ–ደራርቱ..እያለ የሚሄድ ትርክት እንጂ ለኳስ ተጫዋች የወጣ ዘፈን ኢምንት ነበር፤ገፋ ካለ “የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ..እኛም ሀገር አለ ገብረመድህን ሀይሌ” አይነት ግጥሞች ይዘወተሩ ነበር፤(የምታቁት ካለ ክተቡትና እንዝናናበት)አሁን ግን ዋልያ ና ሉሲ በየዘፋኞቹ አፍ ገብተዋል፤ የኳስ ሜዳ ልጅ የሆነዉ ቴዲ አፍሮ ነገ ለብሂራዊ ቡድኑ አዲስ ዘፈን እንደሚለቅ ይፋ ሁንዋል፤ሲንግሉ “መሬት ሲመታ” የሚል ርእስ ተሰጥቶታል፤የግጥሞቹ መልእክት በናይጄሪያዉ ጨዋታ ተመልካቹ ሞራሉ እንዳይነካ የሚል ይዘት ያለዉ ነዉ፤ምክንያቱ ደግሞ ጀግና የሚኮነዉ ወድቆ ከተነሱ በኋላ ነዉና የሚል መልእክት አለዉ!! የመልሱ ጨዋታ ላይ ዋልያዉ ከወደቀበት እንደሚነሳ እምነት ማሳደሩን ግጥሞቹ ይገልጻሉ፤ዘፋኙ የተወለደበት አከባቢ የብዙ ኳስ ተጫዋቾች መነሻ ሰፈር(መሳለሚያ ሞቢል)እንደመሆኑ ብዙዎች ይህንን ይጠብቁ ነበር፤ነገ በሚለቀቀዉ ሲንገል ላይ አንድ ዝነኛ የአትሌቲክስ ባለታሪክ ለዋልያዎቹ ድል እንደምሳሌ እንደሚነሳ የዉስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል፤ምናልባትም የይቻላሉ ሀይሌም ሊሆን ይችላል!!ለማንኛዉም የእንዳለ አድምቄን የኳስ ሜዳ ግርግር እየኮመኮማችሁ የቴዲ አፍሮን አዲሱን የዋልያዎች ዘፈን ጠብቁ!!
http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=-OndwidS-8I

No comments:

Post a Comment