ሰማያዊ ፓርቲ ለጽ/ቤት መጠቀሚያ ተከራይቶ ነበረውን ቢሮ በግድ ካልወጣችሁ ሲሉ ከነበሩት የጉለሌ ክ/ከተማና ወረዳ 03 ካድሬዎች መካከል በተነሳው ውዝግብ መፍትሄ ለማፈላለግ መሀከል የገባው የመነን አካባቢ ፖሊስ በውይይት ለመፍታት ሁለቱም አካላት ከቤቱ እንዲወጡና ፖሊስ ቤቱን እንዲጠብቅ፤ በቀጣዩ ቀን ለመነጋገር ስምምነት ተይዞ የፓርቲው አባላት ወደቤታቸው ለመሄድ ከጽ/ቤቱ ለቀው ቢሄዱም ከመንገድ ላይ
1.ወ/ት ሀና ዋለልኝ (የሴቶች ጉዳይ ኃላፊ)
2.አቶ ዮናስ ከድር (የምክር ቤት አባል)
3.ወ/ት እየሩስ ተስፋው
4.አቶ ዮናታን ተስፋዬ
5.አቶ አቤል ኤፍሬም
6.አቶ አህመድ መሀመድ
7አቶ እያስፔድ ተስፋዬ
የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስና የደህንነት አካላት ወደ ጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው አሁን በደረሰን መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በፊት እንደሚታወሰው የጃልሜዳ አካባቢ ፖሊስ የፓርቲውን አባላት እያሰረ ይደበድብ እንደነበረ ፤ አሁንም ከአንድ ሰአት በላይ አባሎቹን ምን እያደረጋቸው እንደሆነ ማወቅ አለመቻሉ እየተደበደቡ ይሁን? የሚለውን ስጋት በከፍተኛ ሁኔታ አጭሯል፡፡
No comments:
Post a Comment