Thursday, October 10, 2013

በኦስሎ በተካሄደው የግንቦት7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የተሳካ እንደነበር ትህዴን ዘገበ


tpdm
በተለያዩ አገራት የሚገኙ የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ፣ ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንቦት-7 ጋር
ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አባላት የግንቦት-7 አመራር ከአባላቱ ጋር
በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አጠናክረን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንቦት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣፥
በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በአፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የኢህአዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ
በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ ዕግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች የኢህአዴግ ስርዓት መለያ
ከሆነው በዘር የመከፋፈል አባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣፥
የግንቦት-7 አመራርና አባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ጠንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው አስተማማኝ
ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበታለን ሲሉ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣፥

No comments:

Post a Comment