Thursday, November 15, 2012

ኢሣት ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ እንዳይሠራጭ ታፈነ


ከአንድ ዓመት ተኩል ስኬታማ አፈና በኋላ የተጣለበትን ተደጋጋሚ የአየር ሞገድ እመቃ ተቋቁሞ ላለፉት ጥቂት ሣምንታት በኢትዮጵያ ሥርጭቱን ጀምሮ የነበረው የኢሣት ቴሌቪዥንና

Ethiopian Satellite Television, ESAT TVሬዲዮ ከትናንት በስቲያ ኅዳር 4 ቀን 2005ዓ.ም ምሽት ጀምሮ ዝነኛ ሥርጭቱ መቋረጡ ታወቀ፡፡ ባለፉት የሥርጭት ጊዜያት ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የብሶት መተንፈሻና የታፈኑ የሀገር ቤት ዜናዎች ማወጃ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰሞኑን ግን ኢቢኤስ የሚባለው ወያኔ-ዘመም የቴሌቪዥን ጣቢያ ከአረብሣት ወጥቶ ወደናይልሣት መግባቱን ተከትሎ የሁለቱም ሞገድ የሚተላለፍባቸው 10815 የማሰራጫ ፍሪኩየንሲ መዘጋቱ ተረጋግጧል፡፡
ይህን የማፈን ድርጊት የፈጸሙትም የወያኔው መንግሥትና የቻይና የቴክሎጂ ጠበብት እንደሆኑ ኢንሣ (INSA) ከሚባለው ከሥራ አመራር እስከጽዳትና ዘበኛ ድረስ የተመረጡ የትግሬ የጉልበትና የኢንተሊጀንስ ባለሙያዎች ብቻ ከሚሠሩበት የወያኔው መንግሥት የፀረ ድረገፅ ሚዲያ ተቋም በፌስታል ተጠቅልሎ እንዳልባሌ ከወጣ ዕቃ መረዳት ተችሏል፡፡ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት የኢቢኤስ ወደናይልሣት መግባት ከኢሣት መታፈን ጋር የቀረበ ግንኙነት አለው ተብሏል፡፡

አሁን ዘግይቶ የደረሰ አስደሳች ዜና፡- ኢሣት ሠራ!

የዚህ ዜና አቀናባሪ ዜናዎቹን ወደማጠናቀቁ ላይ ሳለ ምሣ ቢጤ ሊቀምስ ሣሎን ተቀምጦ ቲቪ ሲከፍት ኢሣት ከ24 ሰዓት መታፈን በኋላ ወደ ኢትዮጵያ አየር መመለሱን ባይኑ በብረቱ አረጋግጧል፡፡ ያላረጋገጠው እስከምን ጊዜ ሳይታፈን እንደሚቆይ መሆኑንም ለመረዳት ችላችኋል ተብሎ ተገምቷል፡፡ ያ ነገረኛ ኢቢኤስ የተባለው በመለስ ሞት ደረቱን ጥሎ በአደባባይ ያለቀሰው ቲቪ ግን አሁንም አይሠራም፡፡ ለኢሣት መታፈን ጦሱ እሱ ሳይሆን እንደማይቀር ይህ ዘጋቢ ክፉኛ ሲጠራጠር መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ የኢቢኤስን የወያኔ ቤተኛነት መጠራጠር ስለማይቻል እሱን መጠንቀቅ እንደሚገባም ብዙዎች ከወዲሁ እያስጠነቀቁ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል – ኢቢኤስን በሩቅ በማለት፡፡ ኢሣቶችም ይህን ነገር አያጡትም ተብሎ ይገመታል፡፡

No comments:

Post a Comment