Saturday, November 24, 2012

በሀረር ከተማ ከ500 በላይ ሱቆች ይፈርሳሉ መባሉን ተከትሎ አለመረጋጋት መፈጠሩ ተሰማ


ህዳር ፲፭ (አስራ አምት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሀረር ከተማ ሸዋ በር እየተባለ በሚጠራው  የገበያ ማእከል የሚገኙ ከ500 ያላነሱ ሱቆች ይፈርሳሉ በመባሉ በዛሬው እለት አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር ዘጋቢዎቻችን ከስፍራው ገልጸዋል።
አብዛኞቹ ሱቆች ካለፉት 30 አመታት ጀምሮ በጉራጌ ተወላጆች የተያዙ ሲሆን፣ ክልሉ ነጋዴዎችን በማስወጣት ለአካባቢው ተወላጆች ለመስጠት  እንዳቀደ መነገሩን ተከትሎ ነው አለመረጋጋቱ የተፈጠረው።
ተገቢው ካሳ እና ምትክ ቦታ ሳይሰጥ ሱቆችን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ መተላለፉ፟ ነጋዴዎችን ግራ አጋብቷል።
ሸዋ በር የገበያ ማእከል ከ2 አመት በፊት ሆን ተብሎ እንዲቃጠል ተደርጓል በሚል ከፍተኛ ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment