Saturday, February 23, 2013

አቶ አዲሱ ለገሰ የመለስ ዜናዊ ፎቶ እንዲወርድ መመመሪያ ሰጡ


(ኢ.ኤም.ኤፍ) በአዲስ አበባ የተሰቀሉት የመለስ ዜናዊ ፎቶዎች ስድስት ወራትን አስቆጠሩ። ፎቶዎቹ አንዳንድ ቦታ ላይ… ቆሽሸውና ነትበው መቀዳደድ ጀምረዋል። የከተማውንም ውበት እየቀነሱት ነው። አሁን የሚያስፈጽመው መገኘቱን እርግጠኛ መሆን ባይቻልም፤ “ፎቶዎቹ ይውረዱልን!” የሚሉት ወገኖች እየበዙ ናቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ “ፎቶዎቹ ይነሱ! በመለስ ስም መነገድ ይብቃ!” የሚሉትን ሃሳቦች የሰነዘረው ያቀረበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነበር። አሁን ጥያቄውን የሚያስተጋቡ ሰዎች ጨምረዋል። አቶ አዲሱ ለገሰ፤ የቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር በትላንትናው እለት ተመሳሳይ ጥያቄ አቅርበዋል። “በየጎዳናው የተሰቀሉት የመለስ ፎቶዎች እንዲነሱ” ብለዋል – በተለሳለሰ አነጋገር። አቶ አዲሱ ለገሰ ይህን ያሉት የመለስ ዜናዊ መታሰቢያ ድርጅትን ወክለው ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው። አሁን ችግሩ ያለው “ይህንን ለማድረግ የሚመለከተው ማነው?” የአዲስ አበባው ከንቲባ ወ/ሮ አዜብን ይፈራል፤ አዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ህወሃትን ይፈራሉ። ፓርላማው ከኢህአዴግ ጽ/ቤት መመሪያ ካልመጣ ምንም መመመሪያ አያወጣም። “ማን ያስፈጽመው?” ለሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚሰጥ ጠፍቶ ሁሉም ተፋጠዋል። የማይደፈረውን ሞት የደፈረው መለስ ዜናዊ እና ፎቶዎቹም ቀስ በቀስ እያረጁና እየተቀዳደዱ ናቸው። አንዳንዶች “ይህ ሁኔታ የስርአቱን መቆሸሽ እርጅና ያሳያል” የሚሉ ወገኖች አሉ። እኛ የማይደፈረውን የደፈረው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ሲያልፍ R.I.P. (Rust in Pieces) ብለን ነበር። አሁን መንገድ ላይ አርጅተው ለተቀዳዱት ፎቶዎች በተመሳሳይ መልኩ R.I.P. (Rust in Pieces) ብንል አሁን የሚታየውን ሁኔታ አንጸባራቂ እውነታ ነው ብለን እናምናለን። በአጠቃላይ የአቶ መለስ ዜናዊ ያረጁ ፎቶዎች እንዲነሱ የመጠየቁ ሂደት ከኢህአዴግ ውጭ እና በኢህአዴግ ውስጥ እንደቀጠለ ነው። ሆኖም ‘ፎቶዎቹን በድፍረት ማን ያንሳቸው?’ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አጥቶ፤ የመንገድ ላይ ፎቶዎቹ የክረምት ውሃ እና የበጋ ጸሃይ እየተፈራረቀባቸው ይገኛሉ።

14 አመት ወጣት ኢትዮዽያዊ በቤተሰብና ሀገር ናፍቆት ምክንያት እራሱን አጠፋ

The young man with the adoptive family ሀብታሙ የ 14 አመት ወጣት ነበር። ሁለት ሌላ ወንድሞች አሉት ከኢትዮጵያ ወላጆቹ ስለሞቱበት ሚላኖ በ(Paderno Dugnano) የሚኖሩ አሳዳጊዎች ከአንደኛው ወንድሙ ጋር ሊያሳድጉት ይዘዉት ይመጣሉ። የዛሬ 10 ወር የአገሩን ናፍቆትና ከውንድሙ መለየቱን ባለመቀበል በእግሩ ጉዞ ይጀምራል ከ አንድ ሳምንት ቀን ከ ለሊት ጉዞ በኋላ ናፖሊ በምትባል ባቡር ጣቢያ ፖሊሶች ይይዙታል አሳዳጊዎቹ መጥፋቱን አመልክተው ስለነበር። አሳዳጊዎቹ እነደሚሉት ሶስቱንም ለምን አንድ ላይ እንዳላመ ጧቸዉ እና ወደአገሩ መሄድ እንደሚፈልግ ይጠይቃቸው እንደነበር ነው ጉዞ ወደአገሩ ጀምሮ ሲመለስ የተናገሩት። ምንም ዕንኳን ከጣሊያን ወደ ኢትዮጵያ በግር መጓዝ የከበደ ቢሁንም ሀብታሙ ግን ሞከረ፤ ብዙ አስተያየት ነው የተሰጠበት ያገር የወገን ናፍቆት የማይታሰበዉን ጉዞ አስጀመረ በማለት ሌላም ሌላም … የሀብታሙ አሳዳጊዎች ተገኝቶ ወደቤት ሲመጣ የገቡለት ቃል ወዳገሩ እንደሚልኩትና ቤተሰቡን አይቶ እንደሚመለስ ነበር ግን ከ10 ወር የአገር ናፍቆት ጋር እራሱን ሰቅሎ ተገኘ። እንደናፈቀ ወደማይመለሱበት ተጓዘ። አሳዛኝ ፍፃሜ!!!

ESAT Kignit OSLO Norway Artist Tamagn Beyene Part II 22 February 2013 Ethiopia


Friday, February 22, 2013

ጠቅላይ ሚኒስት ሃይለማርያም ደሳለኝና ጸጋዬ በርሄ ለሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያ ሰጡ


ለስድስተኛው ፓትርያሪክ ምርጫ እየተደረገ በሚገኘው ቅድመ ዝግጅት፣ የየራሳቸውን ‹ምርጥ› ይዘው የቡድን እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉ አካላትን ያስተባብራሉ ለተባሉ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት መንግሥት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተሰማ፡፡ ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት÷ የአስመራጭ ኮሚቴው ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ እና የምሥራቅ እና ምዕራብ ሐረርጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ናቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ኀይለ ማርያም ደሳለኝ
ለሐራዊ ምንጮች የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ለሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማስጠንቀቂያው የተሰጣቸው ሰኞ፣ የካቲት 11 ቀን 2005 ዓ.ም በብሔራዊ ቤተ መንግሥት ተጠርተው ሲኾን፣ ያነጋገሯቸውም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኀይለ ማርያም ደሳለኝና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አማካሪ አቶ ጸጋዬ በርሄ ናቸው፡፡ ባለሥልጣናቱ÷ የፓትርያሪክ ምርጫው ቤተ ክርስቲያኒቱ ባጸደቀችው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ መሠረት ብቻ መፈጸም እንደሚገባው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ ‹‹የራሳችኹን ሕገ ደንብ አክብራችኹ መሥራት ሲያቅታኹ በመንግሥት ላይ የሚቀርበውን ሰበብ ማስቆም አለባችኹ፤ በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ፣ በየሆቴሉና በየልኳንዳ ቤቱ እየተሰበሰቡ የሚመክሩትንና የምታስተባብሯቸውን ቡድኖችም መግታትና መቆጣጠር አለባችኹ፤›› የሚል ማሳሰቢያ መስጠታቸው ተነግሯል፡፡
ሦስቱ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በምርጫው ዙሪያ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ቡድኖች ስለመኖራቸው በማመን አስተያየት መስጠታቸው ተመልክቷል፡፡ የተለያዩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን በቢሯቸውና በማረፊያቸው ሲያነጋግሩ የተለያየ ስምና መታወቂያ ይጠቀማሉ ስለሚባሉት የቡድኖቹ መሪዎችም ሊቃነ ጳጳሳቱ ሲያብራሩ፣ ‹‹የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መታወቂያ የሚያሳዩና ከመንግሥት እንደተላኩ የሚናገሩ፣ መንግሥት እንዲመረጥ የሚፈልገው አቡነ እገሌን ነው፤ አቡነ እገሌን መምረጥ አለባችኹ፤ አቡነ እገሌን ካልመረጣችኹ የእገሌ ተቃዋሚ አባል ናችኹ ማለት ነው፣ እናሰራችኋለን፤ ከሥራ እናባርራችኋለን፤›› የሚሉ በመኾናቸውና ይህም በየዕለቱ የሚታዘቡት ጉዳይ በመኾኑ በመንግሥት ወደማማረር መድረሳቸውን አስረድተዋል ተብሏል፡፡
በዚህ ሳምንት ሰኞ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጋራ የተደረገውን ውይይት ተከትሎ የመንግሥት ስቭል፣ ፖሊስና ወታደራዊ ደኅንነት ጥምር ግብረ ኀይል በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽር ውስጥ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ክትትልና አሠሣ፣ በስመ ደኅንነት ሲንቀሳቀሱ ነበር የተባሉ 40 ግለሰቦችን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተዘግቧል፡፡ አሠሣው እኒህ ስመ ደኅንነቶች በየፊናቸው ከሚመሯቸው ቡድኖች (የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳትን ለፕትርክና በማጨት የተስማሙ የመነኰሳትና ካህናት ስብስቦች ናቸው) ጋራ ያዘወትሯቸዋል በሚባሉ ካፌዎች፣ ሬስቶራንቶች፣ ሆቴሎችና ልኳንዳ ቤቶች ተጠናክሮ ቡድኖቹን የመበተንና የማስጠንቀቅ ሥራ ሲሠራ መዋሉ ተነግሯል፡፡
በመንበረ ፓትርያሪኩ ቅጽርና ዙሪያ ሲንቀሳቀሱ በጥምር የደኅንነት ኀይሉ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት 40 ግለሰቦች መካከል 35ቱ ተይዘው ማንነታቸውን ሲጠይቁ ያሳዩት መታወቂያ ሐሰተኛ ኾኖ ተገኝቷል፤ የአምስቱ መታወቂያ ደግሞ ትክክለኛ ቢኾንም ከሚመለከተው አካል ትእዛዝ ሳይሰጣቸው ራሳቸውን ለቡድናዊ ጥቅም አሰማርተው መገኘታቸው ተረጋግጧል ተብሏል፤ አብዛኞቹ ከክልሎች የመጡ፣ በአንድ ወገን የተሰጣቸውን ቡድናዊ ተልእኮ ለማስፈጸም የሚላላኩ እንጂ የመንበረ ፓትርያሪኩን መግቢያና መውጫ በሮች እንኳ በቅጡ የማያውቁ መኾናቸው በቁጥጥር ሥር ሲውሉ በታየባቸው መርበትበትና ድንጋጤ ይበልጥ ራሳቸውን ያጋለጡ መኾኑ ተገልጧል፡፡
በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ወገኖች መንግሥት ‹‹ተጽዕኖ አላደረግኹም፤ ጣልቃ አልገባኹም›› ለማለት ያህል የወሰደው ርምጃ ሊኾን ይችላል በሚል መረጃውን በጥርጣሬ ይመለከቱታል፤ በአንጻሩ የምርጫው እንቅስቃሴ ከመንግሥት ቀጥተኛ እይታና ቁጥጥር ውጭ ሊኾን እንደማይችል ይከራከራሉ፡፡ ሌሎች ወገኖች ደግሞ መንግሥት በጥምር የደኅንነት ኀይሉ እያካሄደው ስለ መኾኑ የተዘገበው የቁጥጥር እንቀስቃሴ የየራሳቸውን ፓትርያሪክ አጭተው በመንበረ ፓትርያሪኩ የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች÷ በአንድ በኩል የመንግሥትን የጸጥታ፣ የደኅንነትና የመከላከያ መዋቅሮች ለሚሹት ዓላማ ለመጠቀም የሄዱበትን ርቀት (በመንግሥት ቋንቋ የኪራይ ሰብሳቢዎችን ትስስር) የሚያሳይ ሲኾን በሌላ በኩል ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ክብሯን ለማስጠበቅ ካለመቻሏ የተነሣ የምትገኝበትን አስከፊ ተቋማዊ ውርደት/ዝቅጠት እንደሚያሳይ ተመልክቷል፡፡
በዚህ ዜና ርእሰ ጉዳይ እንደሰማነው ከቀድሞውም እንደሚታወቀው ሁሉ፣ የዚህ ተቋማዊ ውርደት መነሻዎች የእኛው ሊቃነ ጳጳሳት እንደኾኑ መጠቀሱ በእጅጉ የሚያሳፍር ነው፡፡ ቡድኖቹን በማንቀሳቀስ ረገድ÷ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለብፁዕ አቡነ ማቲያስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ‹‹ቀጣዩ ፓትርያሪክ ከወሎ መመረጥ አለበት፤ ጊዜው የወሎ ነው›› የሚለውን ቡድን (w – group) በመደገፍ ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን ወይም ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘካናዳን፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን በመደገፍ ስማቸው ይነሣል፡፡ የድጋፉ ስለምንነት በተለይ ለመጀመሪያዎቹ ሁለቱ በዋናነት ከጎጠኝነት ጋራ የተያያዘ ቢኾንም ሁሉም በቀጣይ ስለሚያገኘው ሹመት፣ ሥራ ወይም የኾነ ዐይነት ግላዊና ቡድናዊ ጥቅም ወይም አንዱ ሌላው ላይ ስላለው ቂምና ጥላቻ መኾኑ ደግሞ በእጅጉ ከማሳፈርም አልፎ በእጅጉ ያሳዝናል፡፡
ሹመትና ሥራ ወይም የኾነ ዐይነት ሌላ ጥቅም ፈልጎ አሉታዊ የምርጫ ድጋፍ ማድረጉ፣ በቂምና ጥላቻ መነዳቱ በውጤቱ የሚገኘውን ሹመት መንፈሳዊ ወይም ከመንፈስ ቅዱስ ነው እንደማያሰኘው ግልጽ ነው፡፡ እስኪ ይህም ይኹን ብንል እንኳ፣ የየራሳቸውን ፓትርያሪክ አጭተው በየካፌው፣ በየሬስቶራንቱ፣ በየሆቴሉና በየልኳንዳው ተሰብስበው የሚዶልቱት የ‹መነኰሳት›፣ ‹ካህናት›ና ወይዛዝርት ስብስቦች ለሹመቱም ለሥራውም የሚታመኑ፣ የሚበቁም እንዳልኾኑ ባለፉት ዓመታት በሚገባ የምናውቃቸው ናቸው፡፡
‹‹አቡነ ማቲያስን ለማስመረጥ ቤቴንም ቢኾን እሸጣለኹ›› የሚሉት ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ
ለአብነት ያህል÷ ‹‹መንግሥት የሚፈልገው አቡነ ማቲያስን ነው፤ አቡነ ማቲያስን መምረጥ አለባችኹ፤ አቡነ ማቲያስን ካልመረጣችኹ እናስራችኋለን፤ እናባርራችኋለን›› በሚል እየተንቀሳቀሱ ያሉት እነ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ መጋቤ ካህናቱ ኀይለ ሥላሴ ዘማርያም እና ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ ምን እያደረጉ ነው? ቡድናዊና ግላዊ ጥቅም፣ ቂምና ጥላቻ የሚገፋቸው እኒህ ግለሰቦች፣ ለፕትርክና ሊመረጡ ይችላሉ ያሏቸውን ሌሎች ብፁዓን አባቶች ስም በየሚዲያው የማጥፋት ዘመቻ ይዘዋል፤ ሚዲያውም ያለአንዳች ሚዛናዊነት የእነርሱን ክሥ ያስተጋባል (የዛሬው ሰንደቅ ጋዜጣ አንዱ ነው፤ በዛሬው ዕለትም እኚህ ሴትዮ በአድልዎና በሕገ ወጥ መንገድ ከያዟቸው የቤተ ክህነት ቤቶች መካከል አንዱ የኾነውንና በአራት ኪሎ የሚገኘውን ቀራንዮ የጉዞ ወኪል የከፈቱበትን ቢሮ የሰንደቅ ጋዜጣ ማከፋፈያ አስመስለውት ውለዋል)፡፡ በስመ ደኅንነት የሚንቀሳቀሱ ነገር ግን የጸጥታና ደኅንነት ባልደረቦች የሚመስሉ በርካታ በገንዘብ የተገዙ ግለሰቦች መንበረ ፓትርያሪኩን እንዲያጥለቀልቁ ያደረጉት በቀዳሚነት እነእጅጋየሁ ናቸው፡፡
እነንቡረ እድ ኤልያስ በአዲስ አበባ አራቱ አህጉረ ስብከት፣ በባሕር ዳር፣ በደሴ፣ በሐዋሳ፣ በድሬዳዋ፣ በአሰበ
ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ
ተፈሪና በጅጅጋ አህጉረ ስብከት ስልክ እየደወሉ ከጠቅላላው መራጭ ከ600 በላይ የሚኾኑ መራጮችን ስም ዝርዝር አሳውቁን እያሉ ጸሐፊዎችንና ሥራ አስኪያጆችን እያስገደዱና እያስፈራሩ ነው፡፡ በተወሰኑ አህጉረ ስብከትም ሥራ አስኪያጆቹ የካህናት፣ ገዳማትና አድባራት አበ ምኔቶችና እመ ምኔቶች እንዲሁም የምእመናን ተወካዮችን ሰብስበው ድምፅ መስጠት ያለባቸው ለአቡነ ማቲያስ መኾን እንደሚገባው በማሳሰቡ ረገድ ተሳክቶላቸዋል፡፡ ጉዳዩን በተመለከተ የአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ሁለት ጸሐፊዎችና ሥራ አስኪያጆች ለየሊቃነ ጳጳሳቱ ሪፖርት ያደረጉ ሲኾን ሊቃነ ጳጳሳቱ ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ለእነ ንቡረ እድ ኤልያስና ለተላላኪዎቻቸው ስመ ደኅንነቶች ጠንከር ካለ ማሳሰቢያ ጋራ ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል፡፡
የእነእጅጋየሁ ድፍረት በዚህ ብቻ የሚያበቃ ሳይኾን አስመራጮችን በግልጽ እስከማጨናነቅም የደረሰ መኾኑም ታውቋል፡፡ ለአስመራጭ ኮሚቴው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚያስረዱት የሴትዮዋ ድፍረት፣ ‹‹አቡነ እገሌ በዕጩነት መካተት ወይም መመረጥ እንደማይገባቸው የሚያስረዱ መጣጥፎችን በኮሚቴው ስብሰባዎች ላይ ለማስነበብ እስከ መሞከር የደረሰ ነው፤›› ይላሉ፡፡ የመረጃ ምንጮቹ የአንባቢውን ማንነት ባይገልጡ ም ሙከራው የአስመራጭ ኮሚቴውን ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን አስደንግጧል፤ በተለይም የታዋቂ ምእመናን ተወካዮቹን እነ ቀኝ አዝማች ኀይሉ ቃለ ወልድንና አቶ ዓለማየሁ ተስፋዬን ክፉኛ አስቆጥቷል፡፡ ‹‹በስመ ደኅንነቶቹ ላይ የተወሰደው ርምጃ አስመራጭ ኮሚቴውን ሳያነቃቃው አልቀረም፤›› ይላሉ የዜናው ምንጮች፡፡
የኾነው ኾኖ ነገ፣ የካቲት 14 ቀን 2005 ዓ.ም የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ አጣርቶ የመረጣቸውን አባቶች ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ የሚያቀርብበት ዕለት ነው፡፡ እስከ ትላንት ምሽት በነበረን መረጃ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ከካህናትና ምእመናን በተሰበሰቡ ጥቆማዎች ብዛት ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸው ታውቋል፡፡
ቀደም ባስነበብነው ዘገባ እንዳስረገጥነው፣ በብዙ ዕጩዎች መጠቆም ለፓትርያሪክነት መታጨትን ወይም ለፓትርያሪክነት መመረጥን አያረጋግጥም፡፡ የአስመራጭ ኮሚቴው መግለጫ ደጋግሞ እንደሚያሳስበው የጥቆማው መረጃዎች ለዕጩዎች መለያ እንደ ግብአት ብቻ የሚያገለግል ነው፤ ዕጩዎቹ እነማን እንደሚኾኑ የሚታወቁት ቅ/ሲኖዶስ በነገው ዕለት ከኮሚቴው ተለይተው በሚቀርቡለት አባቶች ላይ ተወያይቶ ስማቸውን በብዙኀን መገናኛ ይፋ ሲያደርግ ብቻ ነው፤ ፓትርያሪኩም የሚታወቀው የካቲት 21 ቀን በሚሰጠው የመራጮች ድምፅ ብቻ ነው፡፡

አባት እና አባቶች፤ ከንብ እና ከንብ abetokichaw


እኛ ምርጫን የተለማመድነው በልጅነታችን ነበር።ለሁለት ተቧድነን እግር ኳስ ልንጫወት ስንሻ ሁለት መራጮች የቡድን አባት ተብለው ይሰየሙና የምንረጠው እኛ ተደብቀን ሄደን የምርጫ ምልክታችንን ይዘን እንመጣለን። ከዛም “አባት እና አባቶች” እንላቸዋለን… አቤት፤ ከአንበሳ እና ከነብር…? አንበሳን ያለ አንበሳውን ነብርን የፈለገ ነብሩን ይወስዳል። ሌላው ደግሞ አባትና አባቶች ከቡኒ እና ከረመዲ…? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል። (ቡኒ እና ረመዲ የእርግብ ቀለሞችም ስሞችም ሆነው ያገለግላሉ። እንደዛሬ ራሳችን በራሪ ከመሆናችን በፊት ርግቦችን እናረባ ነበር።)
እናልዎ አሁን የሟሟያ ምርጫ ተቃርቧል። እንዳልኩዎት ወዳጄ ሃና መታሰቢያ በቂርቆስ ከክፍለ ከተማ ለምርጫ የሚወዳደሩ እጩዎችን ዝርዝር ፎቶግራፍ አንስታ አሳይታናለች። በዚህ የምርጫ ጣቢያ ወይዘሮ አዜብ መስፍንም ይወዳደራሉ። የእርሳቸው የምርጫ ምልክት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሰዎች የምርጫ ምልክት ንብ ነው።
ስለዚህም ከእኛ ልጅነት እንኳ ያልተሻለ የምርጫ ውድድር ሊደረግ ነው ማለት ነው። አዎ ወደድንም ጠላንም፤ “አባት እና አባቶች… ከንብ እና ከንብ…?” ልንባል ነው። ሁሉም ንቦች ሁሉም ተነዳፊዎች…! ስለዚህ ምርጫው በጣም ከማይናደፍ እና በጣም ከሚናደፍ ነው ማለት ነው…? እንዲህ አይነቱ ምርጫ ምርጫ ለመባል ይበቃልን!? እግዜር ይወቀው ልል ነበር…!? ይህንን መላ ቅጡ የጠፋ ነገርን እግዜር ይወቅ ብሎ ማለት አምላክን መፈታተን ነው!? እናም እዛው የጉዳዩ ባለቤት ይወቅ እንላለን!
እኔ የምለው…
ወዳጆቼ የኢህአዴግ ዋና ስራ ሂደት ባለቤቶች፤ ይቺ ንብ የምርጫ ምልክት በቃ ለዘላለም ሆነች ማለት ነው? አረ ብትቀየር ይሻላል። ሰዉኮ እነዚህ ሰዎች እስከመቼ እየተቀያየሩ ይነድፉናል እያለ ነው!? ታድያ መንግስት እንኳ ባይቀየር የምርጫ ምልክቱ ቢቀያየር አንድ ለውጥ ነውኮ…! እናንተስ መናደፉ እየደክማችሁም እንዴ!? (እየተባልን ነው…!)

ህወሃት ሊወድቅ ነው (ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!) – በያሬድ አይቼህ



ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነጻነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።
ፓለቲካ አይነት ፡ አይነት አለው። የምርጫ ፓለቲካ እና የነጻነት ፓለቲካ አንድ አይደሉም። የምርጫ ፓለቲካ ንጹህ ነው ፡ ጭምት ነው። የነጻነት ፓለቲካ ግን ይጨክናል ፡ ይቆሽሻል።
የአገራችን ዘመናዊ የፓለቲካ ታሪክ ሲቃኝ በተደጋጋሚ የሚታየው ፡ ባለፉት 40 ዓመታት አብይ ለውጥ አራማጆች ከየዋህነታቸው እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልታቸው የተነሳ ለአገራቸው የነበራቸው ራዕይ ተጨናግፏል ፡ መክኗል ፤ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ብዙ ታላላቅ ሊሂቃኖቻችንም በከንቱ ጠፍተዋል።
ካለፉት ያልተሳኩ የነጻነት ሙከራዎች ተምረን ፡ አሁን ያለውን ትልቅ የነጻነት ዕድል በተሳካ መልኩ ለመጠቀም ከፈለግን ፡ ለነጻነታችን መጨከን እና መቆሸሽ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኗል።
ሙከራ 1፦ መንግስቱ እና ገርማሜ ነዋይ
አፄ ኃይለስላሴ ላይ ተደርጎ የነበረው የ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አራማጆች ፡ ወንድማማቾቹ መንግስቱ ነዋይ እና ገርማሜ ነዋይ ፡ ውጥናቸው ለምን እንደ መከነ ሲመረመር ዋናው ምክንያቱ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልት ነው።
የንጉሳዊው ስርዓት በኢትዮጵያ ጭሰኛ ላይ ያደርግ የነበረውን ጭቆና ችላ ማለት ያልቻሉት ወንድማማቾች ፡ ንጉሱን ከስልጣን አስወግደው ፍትሃዊ የመንግስት እና የምጣኔ ሃብት ስርዓት ለመቅረጽ መመኘታቸው ድንቅ ነበር።
ሆኖም ግን እቅዳቸው ያልበሰለ ፡ ያልጨከነና ለመቆሸሽ ያልደፈረ ነበር። ከዚያም የተነሳ መፈንቅለ መንግስቱ ከሸፈ። መግደል የነበረባቸውን በጊዜው አለመግደላቸው ፡ ማሳተፍ የነበረባቸውን ባለማሳተፋቸው ፡ መቅደም የነበረባቸውን ባለመቅደማቸው የተነሳ የነበራቸው ራዕይ ተኮላሽቷል። የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች የዋህነታቸውና ፡ ንጹህነታቸው አስበልቷቸዋል።
ሙከራ 2፦ ጄኔራል መርድ ፡ ጄኔራል አምሃ እና ጄኔራል ፋንታ
በ1980 ዓ.ም የደርግን ስርዓት የተቃወሙ ጄኔራሎች ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያምን ከስልጣን አንስተው ፡ በጊዜው ከነበሩ አማጽያን ጋር ተወያይተው አገራዊ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር መፈንቅለ መንግስት ሞክረው ነበር። ሙከራው አልተሳካም ነበር። ያልተሳካበትም ምክንያት ያው ንጹህና ጭምት ስልት ነበር።
የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የተከሰተው ኮ/ል መንግስቱ ወደ ምስራቅ ጀርመን ለጉብኝት ሲሄዱ ነበር። በዚህ ወቅት የጠንሳሾቹ ትልቁ ስህተት ተፈጸመ። ስህተቱም “ኮ/ሉ ይበሩበት የነበረውን አውሮፕላን አየር ላይ እንዳለ ይመታ” የሚለውን ሃሳብ አለመቀበላቸው ነው።
“አውሮፕላኑ የህዝብ ንብረት ነው” ፡ “በአውሮፕላኑ ውስጥ ፡ ከኮ/ል መንግስቱ ሌላ ፡ የሌሎችን ሰዎች ህይወት ማጥፋት የለብንም” ከሚሉ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልቶች የተነሳ ኮ/ሉ ምስራቅ ጀርመን በሰላም ደረሱ። መፈንቅለ መንግስቱም መከነ።
የግንቦት 1980ው ሙከራ ከየዋህነት እና ከገርነት የተነሳ ከሸፈ። ያኔ ጄነራሎቹ ጨክነው እና ቆሽሸው ቢሆን ኖሮ ፡ አሁን አገራችን የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች ግዛት ከመሆን ይልቅ ፡ የህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የመመስረት አጋጣሚያችን ሰፊ ይሆን ነበር።
ሙከራ 3፦ አዲስ አጋጣሚ
አገራችን ላለፉት 21 ዓመታት ስታምጥ ኖራ አሁን ከምጧ የምትገላገልበት ወቅት ላይ ደርሳለች። ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊወጣበት የማይችለው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ህወሃት እንደ ቀድሞው ተመልሶ ሊያንሰራራ አይችልም።
ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት የነጻነት ሙከራዎች ተምረን አሁን ያገኘነውን አጋጣሚ በመጠቀም የስልጣንን ልጓም ለህዝብ ካላስጨበጥን ፡ ከጭምት እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልት የተነሳ ፡ አዱሱ አጋጣሚ ሊያመልጠን ይችላል።
ስለሆነም ፓለቲካችን የምርጫ ፓለቲካ ሳይሆን የነጻነት ፓለቲካ ስልትን መጠቀሙ ቁልጭ ያለ ጉዳይ ነው። ሳንጨክንና ሳንቆሽሽ ነጻነት አይኖርም። በፍጹም አይኖርም። በጭራሽ አይኖርም። ልብ በሉ! ካለፈው ተምረን የተለየ ስልት ካልተጠቀምን ወደ ባርነት እና ወደ ጭቆና ተመልሰን እንዳረጋለን።
ምን እናድርግ? እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!
ግልጽና ቁልጭ ያለ የነጻነት ትግል አማራጭ የሌለው ስልት ነው። በዚህ ወቅት “የትግራይ ህዝብ ወያኔ ነው ወይስ አይደለም?” የሚለውን የሞኝ ዘፈን ትተን ነገሩን ቀለል ማድረግ ነው። የትኛው ትግሬ ‘ነቅዟል’ ፡ የትኛው ትግሬ ‘አልነቀዘም’ የሚለው የሚታወቀው ከነጻነት በኋላ ብቻ ነው።
በነጻነት ትግል ወቅት ንጹሃን ሰዎች ሰለባ መሆናቸው የማይቀር ነው። ለዚያ ህሊናችንን እናስፋ። ህወሃት በስብሶ እንደ ተነቃነቀ ጥርስ ሆኗል ፡ የሚመነግለውና የሚነቅለው የህዝብ መስዋዕትነት ብቻ ነው።
በዚህ ወቅት ፡ ጽዋው እስኪሞላ እና የሃይል ሚዛኑ እስኪያዘነብል ድረስ ፡ ቢያንስ እንደ ግብጽ አብዮት 1 ሺ ሰማዕታት ፡ ቢበዛ ደግሞ እነደ ሶርያ የነጻነት ትግል ከ30 እስከ 60 ሺ ሰዎች ሊሰዉ እንደሚችል በመገንዘብ ህሊናችንን እናዘጋጅ። የሚሰዉ ይሰዋሉ።
ጥቂቶች ተሰውተው 80 ሚሊዮኖች ነጻ ይሆናሉ።
አዎ! የሚሰዉ ይሰዋሉ። “ለምን የድሃ ልጅ ይሙት?” “ለምን ዲያስፓራ አይዋጋም?” ለሚሉት የሰነፎችና የቱልቱላዎች ንትርክ አሁን ቦታና ጊዜው አይደለም። ህወሃት የትግራይን ህዝብ በዘፈን እና በከንቱ ሽንገላ አታሎ የእሳት ራት አድርጐ ስልጣን ላይ ተንፈራጥጧል። ዛሬ ለአገራችን ነጻነት የሚሰዉ ወገኖቻችን ይሰዋሉ።
ደም ሳይፈስ ነጻነት አይኖርም! ይህንን መራራ እውነታ እንቀበል። እንቆሽሽ። ከነጻነት በኋላ እንጸዳለን ፡ እንቀደሳለን።
ሌላው ጉዳይ ፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ ፡ በተለይም በትግራያን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃት መገንዘብ ነው። በህብረተሰባችን ውስጥ ትግራያን አበይት የስርዓቱ ተጠቃሚና ‘ባለጊዜ’ ናቸው ፡ የሚለው እምነት በሰፊው ስላለ በልዩ ልዩ ክልሎች የሚኖሩ ትግራያን ላይ ጥቃት ሊደርስ ይችላል። ያ አይነቱ ክስተት ሊያስደነግጠንም ፡ ከነጻነት ትግላችን ሊያደናቅፈንም አይገባም።
የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች እና ‘ባለጊዜዎች’ ቢኮረኮሙ ፡ ኩርኩሙን ታሪክ ሚመዘግበው ለነጻነት ትግል ከሚከፈለው ዋጋ ጋር ደምሮ ነው። እግረ መንገዳችንን እነርሱንም ነጻ እናወጣቸዋለን።
ያም ሆነ ይህ፦ “ጅብ ከሚበላህ ፡ ጅብ በልተህ ተቀደስ።”

ESAT Daily News Amsterdam 22 February 2013 Ethiopia