Tuesday, July 9, 2013

አቶ ድሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ሆኑ

July 09, 2013
diriba kumaአዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) እየተካሄደ ያለው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጉባኤ አቶ ድሪባ ኩማን የከተማዋ ከንቲባ አደርጎ ሾመ፡፡ ጉባኤው የቀድሞው ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን እና ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ወልደገብርኤል አብርሃን በአዲሱ ምክር ቤትም በነበራቸው ስልጣን እንዲቀጥሉ መርጧቸዋል፡፡ አዲሱ ከንቲባ ድሪባ ኩማ የከተማዋን ቁልፍ ከተሰናባቹ ከንቲባ ኩማ ደመቅሳ በመረከብ ከአፈ ጉባኤዎቹ ጋር ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
አዲሱ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ለምክር ቤቱ የካቢኒ አባላቶቻቸውን በማቅረብ አስፀድቀዋል ።በዚህም መሰረት
አቶ አባተ ስጦታው ምክትል ከንቲባ
አቶ ሀይሌ ፍሰሃ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ
አቶ ይስሃቅ ግርማይ የአቅም ግንባታ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ጌታቸው ሀይለማርያም የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ጥላሁን ወርቁ የጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ገብረ ፃዲቅ ሀጎስ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ
ወይዘሮ ብዙነሽ መሰረት የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ኤፍሬም ግዛው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ
አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ፎርኢኖ ፎላ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ሰለሞን ሀይሌ የመሬት ማኔጅመንትና ልማት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ዲላሞ ኦቶሬ የትምህርት ቢሮ ሀላፊ
አቶ ፀጋዬ ሀይለማርያም የፍትህ ቢሮ ሀላፊ
ወይዘሮ ፍሬህይወት አያሌው የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል ።

ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ (ወያኔ) ኢምባሲ



ሰኞ፣ ጁላይ 8፣ በዋሽንግተን ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በሗላ 4 ሰዓት ላይ ነው ዳዊት ከበደ ወደ ግርማ ብሩ ቢሮ ከሌሎች ካድሬዎች ጋር ሲገባ የታየው።
(ECADF) – ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና በተለይም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ላይ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በማካሄድ የሚታወቀው የአውራምባ ታይምስ ኢዲተር ዳዊት ከበደ በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ (የወያኔ ኢምባሲ) ሲገባ መታየቱን ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
የዋሽንግተን ምንጮቻችን ጉዳዩን እንዳብራሩት ከሆነ የኢምባሲው ሰራተኞች አመሻሹ ላይ ወደየቤታቸው ሲሄዱ ያስተዋሉ ሲሆን ዳዊት ከበደ ግን ከገባበት ቢሮ ለሰዓታት ሲወጣ አልታየም።
ዳዊት ከበደ በባለቤትነት ያስተዳድረው የነበረው “የአውራምባ ተይምስ ጋዜጣ” ባልደረቦች በወያኔ ቁንጮዎች የሀሰት ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ቤት በመሰቃየት ላይ እያሉ ነው ወደ አሜሪካን ሀገር ቪዛ ተመቶለት የወጣው። ሁኔታው በአንዳዶች ላይ ጥርጣሬን አጭሮ የነበረ ሲሆን፣ ይባስ ብሎ ዳዊት ከበደ አወጣጡን በተመለከተ የሚናገረው የተጣረሰ ታሪክ ይበልጥ እንዲጠራጠሩት አድርጓቸዋል።ዳዊት ከበደ እየበራ ነው እየጠፋ!?
በቅርቡ እየወጡ ባሉት መረጃዎች መሰረት ዳዊት ከበደ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) የመቀጠር ፍላጎት አሳይቶ የነበረ ሲሆን.. በተለያዩ ምክንያቶች ጥያቄው ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
ይህ በዚህ እንዳለ “አለማቀፉ የበቃ ንቅናቄ በኢትዮጵያ” (BEKA – Global Civic Movement for Change in Ethiopia) ዳዊት ከበደ በውይይት መድረኩ እንዳይሳተፍ መታገዱን ለአባላቱ ባሰራጨው ደብዳቤ አሳውቋል።
የበቃ ንቅናቄ ባሰራጨው ደብዳቤ ጨምሮ እንደገለጸው ከሆነ፣ ከወራት በፊት ዳዊት ከበደ በአንድ የተቃዋሚ ፖለቲከኛ መኖሪያ ተጋብዞ በተገኘበት ወቅት በግብዣው ላይ የተገኙትን እንግዶች ተደብቆ ቪዲዮ ሲቀርጽ ተይዟል።

Friday, July 5, 2013

ወርቅነህ ገበየሁ ለምን ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት?

በረከት ስምዖን አደጉ ወይስ ተገፉ?

workneh and bereket


ሰሞኑንን ይፋ የሆነውን የአዲስ የሚኒስትሮችና የ”ከፍተኛ” ባለሥልጣናት ሹመት ተከትሎ ከውስጥም ከውጭም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው። ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ሹመቱን ይፋ ከማድረጋቸው በፊት ሪፖርተር “ምንጮቼ ነገሩኝ” በማለት አቶ በረከት ስምዖንን የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር የሚያደርጋቸው አዲስ ሹመት እንደሚሰጣቸው ዘግቦ ነበር። ይህንኑ ዜና ተከትሎ “ኢትዮጵያ በኦፊሴል በኤርትራ መመራት ጀመረች” በማለት ቅድመ አስተያየት የሰነዘሩ ጥቂት አልነበሩም።

ሚዲያውን መዳፋቸው ስር አኑረው የቆዩት አቶ በረከት ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትርነታቸው ተነስተው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም የፖሊሲና ጥናት አማካሪ ሚኒስትር ተደርገው መሾማቸው “በረከት አደጉ ወይስ ተገፉ?” የሚል ጥያቄ አስነስቷል።
ከመለስ ህልፈት በኋላ ኢህአዴግ ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳላቸው ያሳዩት አቶ በረከት ከድርጅታቸው ይሁንታ ውጪ “አቶ ሃይለማርያም ጠ/ሚኒስትር ይሆናሉ። የሚቀረው የስርዓት ማሟላት ጉዳይ ነው” ማለታቸው  የህወሃትና የኦህዴድ ሰዎችን ክፉኛ አበሳጭቶ እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች “አቶ በረከት አማካሪ ሆነው ወደ ጠ/ሚኒስትር ቢሮ መዛወራቸው ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር የመገፋት ወይም ስራ አልባ የማድረግና ከቀጥተኛ ተሳታፊነት የመታቀብ ያህል ነው” ባይ ናቸው።
“በዜግነታቸው ብቻ በኢትዮጵያ ፖለቲካ የመሳተፍ መብት የሌላቸው አቶ በረከት ሲፈነጩበት ከነበረው የኢህአዴግ ሚዲያ bereketመሰናበታቸው በራሱ በርካታ ጉዳዮችን የሚያመላክት ነው” የሚሉት ምንጮች “የፖሊሲና የጥናት ጉዳዮች ከፍተኛ የቀለም እውቀትና ልምድ የሚጠይቅ ሃላፊነት ነው። አቶ በረከትም ሆነ አቶ ኩማ ለዚህ አይመጥኑም። ውሳኔው ማቀዝቀዣ ውስጥ የማስገባት ያህል ነው” ሲሉ አቶ በረከት ያላቸው የአደባባይ ሚና ማክተሙን ያወሳሉ።
በሌላ በኩል የተለየ አስተያየት የሚሰነዝሩ ክፍሎች እንደሚሉት “አቶ በረከት የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ እለት እለት ሥርስራቸው ሆነው እንዲሰሩ የተሰጣቸው ስልጣን ነው። ይህ የሚያሳየው እሳቸው አሁንም ፈላጭ ቆራጭ ሆነው መቀጠላቸውን ነው” በማለት የሃሳብ ልዩነታቸውን ያስቀምጣሉ።
አቶ በረከትና አቶ ሃይለማርያም የቀረበ ግንኙነት እንደነበራቸው፣ አቶ መለስ በህይወት እያሉም ቢሆን ሶስቱ እንደማይለያዩ ያመለከቱት ክፍሎች፣ የህወሃት የበላይ አመራርና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር መሪ የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስትር ውስጥ የሚሰይሙት ሚኒስትር፤ ሪፖርትር እንዳለው አቶ በረከት ካልሆኑና የህወሃት ሰው ከተሾመ “በትክክልም አቶ በረከት ወደ ማቀዝቀዣ ክፍል ገብተዋል ማለት ነው” ሲሉ ሁለት ጫፍ ያለው አስተያየት ሰንዝረዋል።
አቶ ኩማ አሁን ባለው ኦህዴድ ውስጥ አንጋፋና ታማኝ፣ በቅጣት ከሶስት ዓመት ማዕቀብ በኋላ ወደ መንግስት ሃላፊነት የተመለሱ፣ kumaኦህዴድን ማጥራት ሲፈለግ በትር የሚጨብጡ፣ በመሆናቸው ከንቲባነቱን ሲለቁ እንዳያፈገፍጉ አዲሱ ሃላፊነት እንደተሰጣቸው አብዛኞች ይስማማሉ። አቶ ኩማ ካላቸው ልምድና ዕውቀት አንጻር አቶ ሃይለማርያምን በፖሊሲ ጉዳዮችና በጥናት ረገድ ለማማከር የሚችሉ ሰው እንዳልሆኑ ስምምነት መኖሩን የሚጠቁሙ ጥቂት አይደሉም። ከዚህ አንጻር በዓለምቀፋዊ ዋና ከተማነት ከምትታወቀው አዲስአበባ ከንቲባነት ወደ አማካሪነት ኩማ ደመቅሳ “ሲሾሙ” እንደ ሥልጣን ሽረት ከተቆጠረ፤ የበረከት ስምዖን በተመሳሳይ መልኩ መታየት የማይችልበት ምክንያት ሊኖር እንደማይችል የሚከራከሩ አሉ፡፡ የአዲስ አበባ ከንቲባ ሥልጣን በምክትል ጠ/ሚ/ርነት ሲያድግና ኢህአዴግ በምርጫ የመሸነፍ ቅንጣት ችግር ሳይኖረው ኩማን ከከንቲባነት ሥልጣን ማንሳቱ የብቃት ማነስና አለመፈለግ እንደሆነ ተጨማሪ አስተያየቶች አሉ፡፡
ለሶስትና አራት ዓመት ህጻን “ከክልላችን ስለተባረርክ የትምህርት ገበታህ ላይ መቀመጥ አትችልም” የሚል ደብዳቤ የሚጽፉና በሙስና በከፍተኛ ደረጃ የሚታሙት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ትምህርት ሚኒስትርነት የተሻገሩት አቶ ሃይለማርያም ደቡብ ክልል ላይ ያለውን ሰንሰለት ለመበጣጠስ እንዲያመቻቸው እንደሆነ ይገመታል። ሃዋሳ ነዋሪ የሆኑ ለጎልጉል እንደገለጹት አቶ ሽፈራው የዘረጉት ድር መበጣጠስ እንዳለበት የታመነው አሁን አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠር የክልል በጀት እንደፈለጉ ከሚያስኬዱበትና ያለገደብ ሥልጣናቸውን ከሚያከናውኑበት የክልል ፕሬዚዳንትነት ወደ ሚኒስትርነት “መሾም”፤ የሥልጣን ሽረት ተብሎ ከመጠራት ውጪ ምንም ሊባል እንደማይችል በሽፈራው ሽጉጤ አመራር የተማረሩ ብቻ ሳይሆኑ ደጋፊዎቻቸውም ያመኑበት ጉዳይ ነው፡፡
የትምህርት ሚኒስቴርን መምራት ያቃታቸው አቶ ደመቀ በስራ ብዛት ሰበብ የምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸውን ወንበር ብቻ እንዲይዙshiferaw መደረጉን ያመለከቱት ክፍሎች “አቶ ሽፈራው በሹመቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ከሚቀርቧቸው ሰምተናል። ሃዋሳ በክልሉ መስተዳድር ውስጥ እሳቸው የሰገሰጓቸውም ስጋት ላይ ናቸው” ብለዋል፡፡ በቀጣይ ሃይለማርያም “ታማኛቸውን” በመሾም (“በማስመረጥ”) እውነተኛ የደኢህዴን ሊቀመንበርነታቸውን እንደሚያረጋግጡም ይጠበቃል፡፡
ደመቀ መኮንን በምክትል ጠ/ሚኒስትርነታቸው ብቻ እንዲቀጥሉ የተደረጉት ምን አልባትም አዲስ በሚቋቋመው የደህንነት ሚኒስቴር ውስጥ በአማራ ክልል ከነበራቸው “ልምድ” አኳያ ለኮታ ማሟያ ታስበው ነው በሚል ካድሬው በስፋት እንደሚያወራ እየተሰማ ነው። አቶ ደመቀ በአማራ ክልል የደህንነቱ መሪ እንደነበሩና በዚሁ በተግባራቸው “የተመሰገኑ ታማኝ” ለመሆን መብቃታቸውን የሚቀርቧቸው ይናገራሉ።
ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት እየሰደቧቸው በመቸገራቸው እንደነበር የሚያስታውሱት እኒህ ክፍሎች “አቶ ደመቀ የአማራው ክልል መሬት ተላልፎ ሲሰጥ አቶ አያሌው ጎበዜ አልፈርምም ሲሉ፣ እሳቸው መፈረማቸው ይፋ ከሆነ በኋላ DemekeM‘ከሃዲ’ የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። ህጻናት ልጆቻቸውም ትምህርት ቤት መማር ያልቻሉት ለአባታቸው በተሰጠ ስም ትምህርት ቤት ውስጥ ጓደኞቻቸው ስለሚያበሽቋቸው ነው” በማለት አቶ ደመቀ ቀደም ሲል ጀምሮ ከደህንነቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ታማኝ እንዳሰኛቸው አስታውቀዋል። ከዚሁ ውለታቸውና ልምዳቸው አንጻር በደህንነት መ/ቤት ውስጥ ይካተታሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 27 ቀን ለተሰየመው ፓርላማ በቀረበው ሹመት መነጋገሪያ ከሆኑት መካካል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው፣ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በተለያዩ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ መድረኮች ችግር እንደተጣባው የተመሰከረለትን የትምህርት ሚኒስቴርን እንዲመሩ መመደባቸው፣ አንዲሁም የአቶ ደመቀ በ”ስልጣን በዛባቸው” ሰበብ የሚኒስትርነት ቦታቸውን መነጠቃቸው በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው።

የወርቅነህ ገበየሁ “ነገዎ” ሹመት

የፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ የትራንስፖርት ሚኒስትር ስለመደረጋቸው ከሚቀርቡት ምክንያቶች መካከል ቀደም ሲል ለረዥም ዓመታት ከደህንነቱና ከሽብር መከላለከል ግብረ ሃይል ጋር የነበራቸው ቁርኝት ከፍተኛ መሆኑ በግንባር ቀደም ይገለጻል። ለጎልጉልአስተያየት የሰጡ እንደሚሉት ኢህአዴግ የትራንስፖርቱን ዘርፍ በቅርብ መቆጣጠር ይፈልጋል።
በምርጫ 97 ወቅት ለታየው ህዝባዊ መነቃቃት የትራንስፖርቱ ዘርፍ፣ በተለይም የታክሲና የግል ማመላለሻዎች የነበራቸው ሚና ከፍተኛ እንደነበር አስተያየት ሰጪዎቹ ያስታውሳሉ። ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እስከወዲያኛው እንዳይታሰቡ ለማድረግ ዘርፉን ከደህንነቱ ጋር በቅርብ ማጠላለፍ፣ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ እየገነባሁ ነው የሚላቸውን መንገዶች፣ የስልክና የብሮድ ባንድ መስመሮች፣ የባቡር ትራንስፖርት በቅርብ ለመቆጣጠርና የቁጥጥሩ ሰንሰለት ውስጥ ለማስገባት አቶ ወርቅነህ ሁነኛ ሰው ሆነው መገኘታቸውን እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ።
አዲሱ ቴሌን ጨምሮ የትራንስፖርት ዘርፉን ከደህንነቱ መዋቅር ጋር በቀላሉ ለማያያዝ ልምዳቸውና የመረቡ አባል ሆነው Workineh-Gebeyehu-መቆየታቸው የትራንስፖርት ሚኒስትር ያደረጋቸው አቶ ወርቅነህ፣ የጄኔራልነት ማዕረጋቸው ከሳቸው ጋር ይቆይ ወይም ይነሳ የተገለጸ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት ክፍሎች፣ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ የህወሃት አመራሮች አቶ ወርቅነህን በታማኝነት መድበው የተቀበሏቸው ሰው ስለመሆናቸው ጥርጥር የላቸውም።
አቶ ወርቅነህ ታማኝ ስለመሆናቸው፣ በዚሁ ታማኝነታቸው ስልጣናቸውን ሳይጠቀሙ በፌዴራል ፖሊስ ዋና ዳይሬክተርነት ለረዥም ጊዜ መቆታቸውን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች በበኩላቸው አቶ ወርቅነህ በአገር አቀፍ ደረጃ ከሰባት ሚኒስትር መስሪያቤቶች ተውጣጥቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የ”ደህንነት ኮር” ውስጥ አባል እንደነበሩ ይናገራሉ። ይህንን ኮር በአዲስ እየተዋቀረ ስለሆነ አቶ ወርቅነህ ወደ ትራንስፖርት ሚኒስትርነት የተዛወሩት ከደህንነቱ የኮር መዋቅር ውስጥ እንዲወጡ ስለተፈለገ መሆኑን ይገልጻሉ።
ዝርዝር ጉዳዩን ለማብራራት እንደሚቸገሩ የሚናገሩት እነዚህ ክፍሎች በሚኒስቴር መስሪያ ቤት ደረጃ እንዲዋቀር አዋጅ የታወጀለት የደህንነት መ/ቤት ሚኒስትርና የበላይ ሃላፊዎች ይፋ ሲሆኑ ነገሮች ይበልጥ እንደሚጠሩ ተናግረዋል። በኢህአዴግ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረውና አሁን ድረስ ሙሉ በሙሉ እንዳልጠራ የሚነገርለትን ልዩነት ተከትሎ የተሸናፊውን ወገኖች የማጥራት ስራ በተለያዩ ስልቶች እንደሚሰሩ የጠቆሙት እነዚህ ክፍሎች፣ የደህንነት ሚኒስትር ሲቋቋም የሚሾሙት ባለስልጣን ከቀድሞዎቹ መካከል እንደማይሆን ምልክት ማየታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
የኢህአዴግ ንብረትና የንግድ ተቋም የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ከዚህ የሚከተለውን የአዲስ ሹመትና ተሿሚዎች ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሃሙስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰላኝ የቀረቡ እጩዎችን ሹመት በአንድ ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።በዚህም መሰረት
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወላሳ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ – የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው አስፋው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ነገዎ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ መሸሻ – በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሃንቢሳ ቦንሳ – የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ በለው – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ በከር ሻሌ ዱሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
አቶ በለጠ ታፈረ ደስታ – የአካባቢ ጥበቃና የደን ሚኒስትር
አቶ መኮንን ማንያዘዋል እንደሻው – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
ሆነው የተሾሙ ሲሆን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ተገኔ ጌታነህ አማካኝነት ቃለ መሃላቸውን ፈጽመዋል።

በግብጽ የፕሬዚዳንት ሙርሲ እጣ ፈንታ አልታወቀም

ሰኔ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የግብጽ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ ፕሬዚዳንቱ በተቃዋሚዎች የቀረበውን ጥያቄ  በ48 ሰአታት ውስጥ እንዲመልሱ ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ የግብጽ ቀጣይ እጣ ፋንታ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልታወቀም።
ፕሬዚዳንት ሙርሲ ህገ መንግስቱን ለማስከበር የህይወት መስዋትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ሲገልጹ፣ የመከላከያ ባላስልጣናት ደግሞ የራሳቸውን መፍትሄ ሀሳብ አቅርበዋል። የመከላከያ አዛዦች ፍላጎት በውል ባልታወቀበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንቱ ጥምር መንግስት ለማቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው ይፋ አድርገዋል።
በፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል በተነሳ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልተወቀ ሰዎች መገደላቸውም ታውቋል።
ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣን ከያዙ በሁዋላ የራሳቸውን ፓርቲ ሰዎች የሚጠቅሙ እርምጃዎችን ከመውሰድ ባለፈ ለአገሪቱ ህዝብ የሰሩለት የለም በሚል ወቀሳ ሲቀርብባቸው ቆይቷል። የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ደግሞ ፕሬዚዳንቱ በአንድ አመት ውስጥ ለውጥ እንዲያመጡ አይጠበቅባቸውም በማለት ይከራከራሉ።

ESAT Daliy News Amsterdam July 05 2013 Ethiopia


Wednesday, July 3, 2013

አንድነት አባሎቼን በማሰር የማደርገውን የሕዝብ ንቅናቄ ማደናቀፍ አይቻልም አለ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ(አንድነት) የተሰጠ መግለጫ
አንድነት ፓርቲ የሶስት ወራት የህዝባዊ ንቅናቄ የትግል ስልቱ  የመጀመሪያውን የአደባባይ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ሰኔ 30/10/2005 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እንደሚያደርግ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሁልጊዜም ህግ ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ፓርቲያችን የአገሪቱ ህገ መንግስት በሚደነግገው መሰረት የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለሰሜን ጎንደር ዞን ማወቅ ለሚገባቸው የመንግስት አካልና ለከተማ መስተዳድሩ አሳውቆ ወደ ቅስቀሳ ከገባ ጥቂት ቀናት አልፈዋል፡፡
Imageምንም እንኳን ህግ አክብረን ሰላማዊ ትግላችንን ብንቀጥልም በሰሜን ጎንደር ዞን በምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብርሃ ጅራ ከተማ የፓርቲያችን አባላት የሆኑት አቶ አለልኝ አባይ፣ አቶ እንግዳው ዋኘው፣ አቶ አብርሃም ልጃለምና አቶ አንጋው ተገኝ አንድነት ፓርቲ የሰጣቸውን ተልኮ ተቀብላችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለምን በተናችሁ ተብለው ከቅዳሜ ጀምሮ በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ አቶ ማህሙድ ሸሪፍ፣ አቶ ጀማል ሰይድና አቶ አለሙ አባይነህ ፓርቲው የጀመረውን የሚሊዮኖች ድምፅ የሚያሰባስብ ፔቲሽን ለምን ታስፈርማላችሁ ተብለው ታስረዋል፡፡
ይህ ተግባር ህጉን ጠብቆ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ፓርቲያችን ላይ አሁንም በገዥው ፓርቲ ህግ ጥሶ ሰላማዊ ሰልፉን የማደናቀፍ ተግባር እየተፈፀመ ስለመሆኑ ግልጽ ማሳያ ነው፡፡ ይህና ሌሎች የገዢው ፓርቲ እኩይ ድርጊቶች አንድነትን በፍፁም ወደኋላ ሊመልሱት እንደማይችሉ ማሳወቅ እንወዳለን ፡፡ ይህን በድፍረት እንድንናገር ያስቻለን ከዓላማ ቁርጠኝነታችን በተጨማሪ ህግ አክባሪነታችን ነው፡፡ ስለዚህ በቅስቀሳ ቡድኑ ላይ ከሚካሄደው ዛቻና ማስፈራሪያ ውጭ በተለያዩ ወረዳዎች የፓርቲያቸውን ተልዕኮ ለማሳካት በፍፁም ሰላማዊነት እየሰሩ ያሉ አባላት ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትግላችንን ሊቀለብሰው እንደማይችል ተገንዝቦ መንግስት ከህገ ወጥ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡
እነዚህ አባሎቻችንም በአስቸኳይ እንዲፈቱ እየጠየቅን ምንም አይነት ህገ ወጥ እርምጃ መብታችንን ከመጠየቅ እንደማይገድበን በድጋሚ ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡
በዚሁ አጋጣሚ ገዢው ፓርቲ ካድሬዎችና የፀጥታ ሀይሎች በአንድነት አባላት ላይ እየወሰዱ የሚገኙትን እስርና ማስፈራሪያ ፊትለ ፊት በመቃወም ቁርጠኝነቱንና አጋርነቱን በማሳየቱ አንድነት ፓርቲ ለጎንደር ህዝብ የአክብሮት ምስጋናውን ያስተላልፋል፡፡
የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት!!!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ሰኔ 24 ቀን 2005 ዓ.ም
አዲስ አበባ

በአዲስ አበባ የወተት እጥረት እጅግ አሳሳቢ ሆኖዋል


DSCN3499በአዲስ አበባ የወተት እጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። አስተያየታቸውን የነገሩን ነዋሪዎች እንዳሉት ፥ በምርቱ ላይ እጥረት ብቻ ሳይሆን የዋጋ መወደድም ይስተዋላል። በካፌዎች የአንድ ስኒ ማኪያቶ ዋጋ እስከ 8 ብር መድረሱን የካፌ ተጠቃሚዎችም ያነሳሉ።የካፌ ባለቤቶች የወተት መጥፋት ለእነሱም ስራ ማነቆ መሆኑን በመግለፅ ፥ ቀደም ሲል ከሚገዙበት ዋጋ በላይ ለመግዛትም አንዳንዴ ጨረታ እንደሚገቡም ጭምር ይናገራሉ። በስድስት ኪሎና በሌሎች አካባቢዎች በተለይ ጠዋት ጠዋት ወተት በማከፋፈያዎች ሱቅ በር ላይ ረጃጅም ሰልፎች ይስተዋላሉ። በእነዚህ ማከፋፈያዎች ውስጥም አንድ ሊትር ወተት እስክ ከ16 እስከ 18 ብር ድረስ ዋጋ ይሸጣል። ወተት የተትረፈረፈባቸው አከባቢዎች ከዚህ በተቃራኒ ከአዲስ አበባ በቅርብ እርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ አርሶ አደሮች ወተታችንን የሚገዛን አጣን ፤ ልፋታችንም ውጤት እያስገኘልን አይደለም ይላሉ። የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በበኩላቸው አልፎ አልፎ ገበያ የማናገኝ በመሆኑ ከአከባቢው የምንሰበስበው ወተት መጠኑ ይቀንሳል ብለዋል። የኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲቲዩት በበኩሉ በዚህ አካባቢና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚስተዋሉትን ችግሮች ለመፍታት እየሰራሁ ነው ብሏል። ከሰሜን ሸዋ ዞን አንዱና ዋነኛው የወተት አምራች በሆነው የደገም ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወይዘሮ መብራት ጋረደው ስለ ስራቸውና በአከባቢው ስላለው የገበያ ችግር ሲናገሩ ፤ ካሏቸው ሁለት ላሞች በየቀኑ አጥጋቢ የሆነ የወተት ምርት ያገኛሉ። ይሁን እንጂ የወተቱ ዋጋ በገዢ ድርጅቶች የሚወሰንና መዋዠቅ የሚታይበት ነው ይላሉ። ሌሎች አርሶ አደሮች የነገሩን ከወይዘሮ መብራት ሀሳብ ጋር የሚስማማ ሲሆን ፥ ወተቱን ለማግኘት የሚያወጡት ወጪና ለወተቱ የሚከፈላቸው ክፍያ የማይመጣጠን ሆኗል። በዚህ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአርሶ አደሩ ወተት የሚሰበሰቡት ድርጅቶች ማማ ፣ ሾላ ፣ ፋሚሊ፣ ናሂማ ወይም ቢፍቱና የሰላሌ የወተት ህብረት ስራ ዩኒየን ናቸው።
ዩኒየኑ በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚታዩትን የገበያ እጥረቶችና የዋጋ ችግሮች ለመቅረፍ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሆነ ስራ አስኪያጁ አቶ ሃይሉ ታደሰ ይናገራሉ።
በደብረ ፅጌ ከተማ ላይ ማቀዝቀዣ ያለውና በርካታ ወተት ማከማቸት የሚችል ተቋም ለመገንባት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቁመዋል።
አቶ ሃይሉ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካን በጫንጮ ከተማ ላይ ዩኒየናቸው እየገነባ እንደሆነና በቅርቡም እንደሚጠናቀቅ ነው የተናገሩት።
ይህንን ፋብሪካን ወደ ስራ ለማስገባትም ቢሆን የመብራት ችግር እንዳለባቸው ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ስጋና ወተት ቴክኖሎጂ ልማት ኢንስቲቲዩት የአቅም ግንባታ ዳይሬክተር አቶ ደሳለኝ ገብረ መድህን ዩኒየኑን የመብራት ችግር ለመፍታት እይተንቀሳቀስን ነው ብለዋል።