Wednesday, July 3, 2013

የግብፅ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞርሲ ከሥልጣናቸው እንደማይነቃነቁ በቁርጠኝነት አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ፍንክች እንደማይሉ አቋማቸውን ዛሬ – ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ምሽት ላይ ባደረጉትና በሃገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮና በቴሌቪዥን በቀጥታ በተላለፈ ንግግር ያስታወቁት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቃዋሚዎቻቸው አደባባይ ወጥተው እንዲወርዱ እየጠየቋቸው ባሉበት ወቅት ነው፡፡
የዛሬ ዓመት አካባቢ በሃገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደ ነፃ ምርጫ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሆናቸውን ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሞርሲ ሕገመንግሥታዊ ኃላፊነቶቻቸውን በመወጣት እንደሚቀጥሉ አስረግጠው ተናግረዋል፡፡
የሃገሪቱ ጦር እጁን ከፖለቲካው ቀውስ ውስጥ እንዲያወጣም አሣስበዋል ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ንግግራቸው፡፡
በሚስተር ሞርሲ እና በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ያለው ልዩነት እስከነገ፤ ረቡዕ ባለው ጊዜ ካልተፈታ ለግብፅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይበጃል የሚሉትን የራሣቸውን የጎዳና ትልም እንደሚደነግጉ የጦር ኃይሎቹ መሪዎች ማስጠንቀቃቸውና ቀነ-ገደብ መቁረጣቸው ይታወሣል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ንግግራቸውን እያሰሙ በነበሩበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ ተቃዋሚና ደጋፊዎቻቸው የሆኑ ሰልፈኞች የካይሮን አደባባዮችና ጎዳናዎች አጨናንቀዋል፡፡
ከመሪያቸው ጎን ቆመው እነርሱ “ማንኛውም ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት” ያሉትን የጦሩን እርምጃ በቁርጠኝነት እንደሚፋለሙ እየዛቱ ያሉት የሞርሲ ደጋፊዎች በዋና ከተማይቱ ናስር ቀበሌ የተሰባሰቡ ሲሆን ሞርሲ ሥልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን ጥያቄአቸውን የሚያሰሙት ተቃዋሚዎች ደግሞ ማዕከላዊውን የካይሮ ጣሕሪር አደባባይ ሞልተውታል፡፡
በሁለቱ ወገኖች መካከል በተነሣ ግጭት ካይሮ ውስጥ ዛሬ (ማክሰኞ) የሰባት ሰው ሕይወት መጥፋቱን የሕክምና ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ም
ወታደሮች ካይሮ ቤተመንግሥት አጥር ግቢ ላይ፤ ማክሰኞ፣ ሰኔ 25/2005 ዓ.ምወታደሮቹ “ሕገመንግሥቱን ለማቋረጥ፣ ሕግ አውጭውን አካል ለመበተንና  የሽግግር አስተዳደር ለማቋቋም እየተዘጋጁ ነው” የሚል ሾልኮ የወጣና ለመንግሥቱ የዜና አገልግሎት ሽው ያለ ጭምጭምታ ጠቁሟል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት “የተመረጠን ፕሬዚዳንት ለመገልበጥ የሚደረግን ሙከራ ለማቆም” ከታንኮች ፊት ቆመው መስዋዕት እንደሚከፍሉ እየዛቱ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ሞርሲ ተቃዋሚዎቹን ሰልፈኞች እያዳመጡ መሆናቸውን እንዲያሣዩ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ማክሰኞ ጠዋት ስልክ ደውለው ጠይቀው ተቃዋሚዎችም የግብፅን ዴሞክራሲያዊ ሂደት መንገድ እንዲከተሉ አሳስበዋል፡፡
አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሔ እንዲሹ ለግብፃዊያኑ ጥሪ አሰምተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ሣምንታት ውስጥ በተካሄዱ ሰልፎችና በተነሱ ግጭቶች ሳቢያ ከሃያ በላይ ሕይወት መጥፋቱ ተዘግቧል፡፡ audio

ለጅምላ ጭፍጨፋ ህጋዊ ሽፋን?

በእስከ ነጻነት
  • ሰሞኑን በጣም እጅግ በጣም አስደናቂ፣ አስገራሚና ዘግናኝ ዜናዎች እየተሰማ ነው።
  • በርግጥ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር አዲስ ነገር አደለም ሊሆንም አይችልም።
የህወሃትን ባህርይ ለምናውቅና የነጻውን አለም ህይወትና ሰብአዊ መብት አክብሮት ለቀመስነው ግን በጣም እጅግ በጣም የሚያስገርም፤ የሚያስደነግጥ: ከዚያም አልፎ  ይህን መቀበልና መዚህ መቀጠል አንችልም  ወያኔ ካልጠፋ ስራም: ኑሮም፤ ትምህርትም እምነትም የለም ክተት የሚያሰኝ ነው:
ዜናው እ አ አቆጣጠር ሰኔ 26 2013 በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዠን  (እኔ  የኢትዮጵያ ሳተላይት መገናኛ፣ Ethiopian Satellite media) ብዬ ብጠራው ደስ ይለኛል) ባስተላለፈው ዜና፡ የወያኔው የደህንነት አባላት ለሚፈጽሙት ማንኛውም ጥፋት በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር አይጠየቁም የሚል የህግ ረቂቅ ለምክር ቤት መቅረቡን አርድቶን ነበር። ይሁን እንጂ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እንዴት ጅምላ ጭፍጨፋ የህግ ሽፋን ሊሰጠው ይችላል በሚል ጥርጣሬ ተወጥረን እያለ፡  ነገሩ እኛ ያሰብነው ሳይሆን ወያኔ ያቀደው ሆነና በዛሬው እለት የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ታጣቂዎች ለሚፈጽሙት ጅምላ ጭፍጨፋ ወይም ንብረት ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር አይጠየቁም የሚል ህግ ባሻንጉሊት ስብስቦች አስጸድቋል፡ ነፃ  እርምጃ ባገሪቱ ታውጇል፡ ለትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ጸጥ ለጥ ብለህ ካልተገዛህ ባደባባይ ትረሸናለህ፤ ለሞትህም ሆነ ለመቁሰልህ ማንም አይጠየቅም፡የሚል ቀጭን ትዛዝ እና አዋጅ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተጭኗል።
ይህ ማለት ምን ማለት ነው? አብረው እየተከናወኑ ያሉት አባሪ ተግባራትስ ምንድናቸው?
በዝርዝር ሳይሆን ጠቅለልና አጠር ያለ የወያኔ ተግባራትን  ወደሗላ መለስ ብሎ መቃኘት አስፈላጊ ይሆናል፡
ህውሃት ገና የዕኩይ ጥንስሱ ሳይፈላ በስብሃት ነጋ አጋፋሪነት የመጀመሪያ አገራዊ አንድነትን ለመናድ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያመቻች የበረሃ ሲኖዶስ ማቋቋምና፤ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን በእምነቱ በጎለበቱና በጸኑ አባቶች ሳይሆን በህውሃት ካድሬዎች እንዲያዝ በረሃ ስልጠና መሰጠቱንና ካድሬዎች የመነኩሴ ልብስ ለብሰው በየገዳማቱ ያሉትን መናኝ ባሃታዊያን፤ መነኩሳትን፤ አረጋውያን ካህናትን አፍነው፤ ገድለው መጨረሳቸውንና አዲስ አበባም ሲደርሱ ዋናውን ፓትርያርክ ከነባር ካደሬዎች አንዱን አባ ገ/ማርያምን ማስቀመጣቸውን ቤተ ማህቶት እ. አ. አቆጣጠር ጥር 23 2013 ምስጢራዊው የበረሃው ሲኖዶስና የማህ በረ ቅዱሳን ፓትርያርክ፣ ከአብየ አዲ እስከ አዲስ አበባ በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሁፍ በሚገባ ዘርዝረው፤ ዋቤ አጣቅሰው አሰቀምጠውታል:   
በዛ ወቅት እነስበሃት ነጋ  ለእስልምና እምነት ተከታዮች የተሳሳተ ግንዛቤ ነበራቸው ብዬ እገምታለሁ፡  በነስ ቁንጽልና በጥላቻ የተቃኘ ህሊና ኢትዮጵያ የአማራና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ፤ ስለኢትዮጵያ የሚጨነቁ አማሮችና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ናቸው ብለው ራሳቸው የፈጠሩትን ውሽት አምነው፤ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችንን በቀላሉ መቀየር፤ እንችላለን ከሚል ግምት በመነሳት በረሃ እያሉ ያላሰቡበትን አሁን ግን በቀላሉ ልንተገብረው እንችላለን ከሚል ንቀት ተነሳስተው የሃባሽን እምነት ተከተሉ የሚል በየትም አለም ታይቶና ተሰምቶ የማይታውቅ እኔ የሰጠሗችሁን እመኑ የሚል ትእዛዝ ሊጭንባቸው ሞክረዋል። የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን ናቸውና፤ እንደነ ስብሃት፤ መለስና  መሰሎች የባንዳ ቅርንጫፍ አደሉምና፤ ሃገር የመናድ ፍላጎትም ሆነ ተንዳ የማየት ፍላጎት የላቸውምና ዞር በል አሏቸው፡ ተቃውሟቸውንም በሰላማዊ ድምጻችን ይሰማ ሲሉ አቤት ሲሉ ሁለት አመት ሊሞላቸው ጥቂት ወራት ብቻ ቀራቸው።Ethiopian government abusing and torches Ethiopian Muslims.
በእበሪት የተወጠረው ወያኔ ይህን ሁለተኛ አመቱን የያዘውን  እምነቴን አንተ አትመርጥልኝም የሚለውን ሰላማዊ ተቃውሞ በሰላማዊ መንገድ እልባት እንደመሰጠት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን በሃሰት ወንጅሎ እንደለመደው በሃይል ለመጨፍለቅ  የእስልምና እምነት ተከታዮች ያልሆኑ ግን ልክ በረሃ ካድሬ መነኩሳትን እንዳስተማረና የኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያንን እንደተቆጣጠረ ሁሉ አሁንም በስለላ የሰለጠኑ አረብኛ ቋንቋን የተማሩና ቁርአንን የቀሩ 987 በእስራኤል የሰለጠኑ የደህንነት አባላት በየመስጊዶቹ ማሰማራቱን እየሰማን ነው። እነዚህ የደህንነት ሰላዮች በየመስጊዱ  የሚሰማሩት መስጊድ ሊያረክሱ፤ ብጥብጥ ሊያስነሱ፤ ከዛም የሚፈልጉትን ለማጥፋት፤ ለመግደል የተዘጋጁ መሆናቸውን የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፡
ሼሆችን፤ ይማሞችን ቢገሉ፤ መስጊድ ቢያቃጥሉ በወንጀልም ሆነ በፍታብሄር እንደማይጠየቁ በህግ ተረጋግጦላቸዋል፡
የሚገርው ደግሞ  እስራኤል ከሰለጠኑት 987 ሰላዮች መካከል የእሰልምና ተከታዮች 11 ብቻ መሆናቸው ነው፡ (11 ግን ምትሃታዊ ቁጥር ነች እንዴ? የኢኮኖሚ እድገት 11% ሌላም፡ ይቺ  እንኳ ለፈገግታ ነች እልፏት) ከነዚህ ስልጣኞች ውስጥ 613ቱ ደግሞ የትገራይ ተወላጆች ናቸው፡ ራሳቸው ባስቀመጡት ስሌት፤ ብሄር ብሄረ ስቦች ቀመር ቢተነተን  ለአንድ ሚሊየን 11 ሰላይ ሂሳብ ማለት ነው፡ በዚህ ሂሳብ ሲሰላ ትግራይ የሚደርሳት የሰልጣኝ ሰላይ ብዛት 55 ገደማ መሆን ነበረበት፤ አሁን ግን ትግራይ 1115% አንድ ሽህ አንድ መቶ አስራ አምስት በመቶ ድርሻ ወስዳለች ማለት ነው። ከ22 አመት አገዛዝ በሗላ 1115% የደህንነት አባላት ከትግራይ ተመልምለውና ስልጥነው፡ መስጊድ ለመበጥበጥና ስልክ ለመጥለፍ ሲዘጋጁ በምንም መስፈርት አገሪቱን እየገዛ ያለው ኢትዮጵያዊ አገዛዝ ነው የሚል ብዥታ ሊኖር እንዳይችል አድርጎታል፡ የገሃዱ አለም ቁልጭ አርጎ እንዲሚያስረዳው ኢትዮጵያ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር የቅኝ አገዛዝ ለመውደቋ ከዚህ በላይ  ማረጋገጫ የሚያስፈልግ አይመስለኝም።
ዋናው ቁጥሩ አደለም፡ የህውሃት ደህንነቶች በጅምላ ለሚፈጁት (በርግጥ ከዚህ ቀደምም ተጠያቂ ሆኖ የሚያውቅ የለም) ለወንጀላቸው ተጠያቂ እንደማይሆኑ መስጊድ፤ ቤተክርስቲያን ቢያቃጥሉ እንደማይጠየቁ፤ የህግ ሽፋን መሰጠቱ የህውሃትን አገር የማፍረስ፤ ዘር የማጥፋት፤ እና ለምንም ተጠያቂነት ሊወስድ አለመፈለጉንና አለመዘጋጀቱን ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ነው፡
በዚህ አጋጣሚ ግን እስራኤል ለአረብ ሃገራት ያላትን ጥላቻ በኢትዮጵያ የአስልምና እምነት  ተከታዮች ላይ ለመወጣት ስላዮችን ማሰልጠኗ ታሪካዊ ስህተት መፈጸሟን ሳልጠቅስ ማለፍ አልፈልግም። ወያኔን ስልጣን ላይ ለማውጣትና ስልጣኑ ላይም ለማቆየት እንግሊዝና አሜሪካ የተጫወቱትን ሚና፤ ሰላዮችንና ያፈና ሰራተኞችን በማስልጠንና ማፈኛ መሳሪያ በመሸጥ ህንድ፤ ቻይና እና እስራኤል ተጠያቂ መሆናቸውን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሊገነዘቡት ይገባል።፡አሁን አቅሙ ላይኖረን ይችላል ግን የቴክኖሎጂ እድገት ሌላውን ለማጥፋት ያመረቱት መሳሪያ በራሳቸው ላይ ሊውል የሚችልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፤ እነዚህ ሃገራት አቶ ገ/መድህን አርአያ እንደጠቀሱት ለ8 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እልቂት ተባባሪ መሆናቸውን መረዳትና መዝግቦ ለትውልድ ማስተላለፍ የያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው።
ስለዚህ በትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ታጣቂዎች ለግንባሩ የማያጎበድዱትን፡ እንቢ አልገዛም ያሉትን ኢትዮጵያውያን፤ በጅምላ እንዲፈጁ፤ ንብረታቸውን እንዲያቃጥሉ፤ እንዲዘርፉ እና ዘር እንዲያጠፉ ትዕዛዝና የህግ ሽፋን ተሰጥቷቸዋል። ዘር በማጥፋታቸው፤ ህዝብን በመጨረሳቸው፤ ንብረት በማውደማቸው ይሸለሙ እንደሆነ እንጂ በወንጀልም በፍታብሄርም እንደማይጠየቁ ግልጽ ሆኗል፡
የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር ተግባራዊ ተሞክሮ የሚያስረዳን ደግሞ በጣም ግልጽ ነው፡ በደኖ፤ ወተር፤ አርባ ጉጉ፤ ጋምቤላ፤ አዲስ አበባ፤ አረካ፤ አዋሳ፤ ሸካ ማጂ፤ አሶሳ፤ ጉሙዝ፡ ወልቃይት ጠገዴ ስንቱ ተዘርዝሮ ይዘለቃል፡በነዚህ ቦታዎች ሁሉ ሁሉ ወያኔ የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው የፈጸመው። አሁን ይህ በአዋጅ ደረጃ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መሆኑ ግልጽ ነው፡
የትግሬ ነጻ አውጭ ግንባር በየንዳንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ላይ የሞት ፈርድ አውጆበታል የሚቀረው ተግባራዊ የሚሆንበት ቀን ብቻ ነው።
ስለዚህ የትግሬ ነጻ አውጭ ታጣቂዎች በጅምላ ሲፈጁን ቆመን ሞታችንን እንጠብቅ? እንደ ጅግራ አንገታችንን ሰጥተን እንታረድ ወይስ ይህ ሁሉ ከመድረሱ በፊት እንደ ግብጾች ወያኔ አሁኑኑ ስልጣን እንዲለቅ ህዝባዊ አመጽ እንጀምር፡ አሁን፤ ዛሬ፡ ወያኔ ስልጣን አሁኑኑ ካልለቀቅህ ስራም፤ ትምህርትም፤ ኑሮም፤ እምነትም፤ ሃገርም የለም ብለን እየመከትንና፤ እየተከላከልን እንሙት? ወያኔ ግድያውን ነገ ይጀምራል፡ ጊዜ የለም፡ ያለችው ጊዜ አሁን ይች ቅጽበት ነች።
መልሱን ለያንዳንዳችሁ እተዋለሁ።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይጠብቅ
እስከ ነጻነት

Tuesday, July 2, 2013

የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አዋጅ ጸደቀ



ኢሳት ዜና :-በሚኒስትር ማእረግ ደረጃ እንዲቋቋም የታሰበው የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት መ/ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ከአንድ ሳምንት ዕይታ በኋላ ዛሬ ለፓርላማው ቀርቦ እምብዛም ውይይት ሳይደረግበት መጽደቁ ታውቋል፡፡

የኣመቱ ሥራውን ሰኔ 30 የሚያጠናቅቀውና ለዕረፍት የሚዘጋው ኢህአዴግ መራሹ ፓርላማ በተጣደፈ አሰራር ያጸደቀው በዚሁ አዋጅ መሰረት የሚቋቋመው መ/ቤት መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተንና የማቅረብ እና የደህንነት አገልግሎት የመስጠት እንዲሁም በአገር ውስጥ የጸረ ሸብርተኝነት እና የበረራ ደህንነትን የማስጠበቅ ሥራዎችን በኃላፊነት
ይሰራል።

መ/ቤቱም ካለበት ህገመንግስታዊና አገራዊ ሃላፊነት እንዲሁም ካለው ስልጣንና ተግባር በመነሳት በሚኒስቴር መ/ቤት ፕሮቶኮል ደረጃ እንደሚሰራ በአገሪቱም የተለያዩ ቅርንጫፍ መ/ቤቶችን ከፍቶ እንደሚንቀሳቀስ አዋጁ ያስረዳል፡፡

ማንኛውም ሰው በመ/ቤቱ መረጃ ሲጠየቅ የመተባበር፣ የሠጠውንም መረጃ በሚስጢር የመያዝ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ይህንን የተላለፈም በወንጀል እንደሚጠየቅ ደንግጓል፡፡

አገሪቱ በተለይም በኤደን ባህረሰላጤ አካባቢ የሚስተዋለውን ተለዋዋጭ የስጋት ምንጭ ለመከላከልና ለመቋቋም የሚቻለው ብቃት ያለው የመረጃና ደህንነት ተቋም ሲገነባ ነው በማለት አዋጁ የወጣበትን ምክንያት አስቀምጧል።

የአዋጁን መጽደቅ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ ተቃውመውታል። አዋጁ አዎንታዊ ጎኖች እንዳሉት የገለጹት አቶ ግርማ ለትርጉም አሻሚ የሆኑ አሻሚ ድንጋጌዎች መካተታቸው ለተቃውሞአቸው ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ እንዲሁም ኢህአዴግ የተለያዩ ደህንነት መስመሮች  እንዳሉዋቸው አስታወሱት አቶ ግርማ ምናልባትም አዲሱ ጠ/ሚ የደህንነት መስመሩ አንድ ወጥ በሆነ እና እርሳቸው በሚያዉቁት መንግድ ብቻ እንዲህ   በመፈለጋቸው የተደነገገ ሊሆን እንደሚችል አስተያየታቸውን ተናግረዋል

በአዲሱ አዋጅ አንድ የደህንነት ሰራተኛ አስቸጋሪ ሁኔታ ካልገጠመው በስተቀር በዜጎች ላይ አንድ ጥፋት ቢፈጽም ሊጠየቅ እንደሚችል በአዋጁ መደንገጉን የገለጹት አቶ ግርማ ፣ ይሁን እንጅ “አስቸጋሪ ሁኔታ” የሚለው ሀረግ ለትረጉም አሻሚ ነው በማለት ገልጸዋል ። መረጃን በመቀበልና ይፋ በማድረግ በኩልም አዋጁ ችግሮች እንዳሉበት አቶ ግርማ ተናግረዋል
“ብሄራዊ የደህንነት መስሪያ ቤት ተቃዋሚዎችን እንዳይሰልል፣ ወይም በተቃዋሚዎች ላይ እንግልት እንዳይፈጽም የሚያስገድድ ድንጋጌ አለ ወይ?”  በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አዋጁ” ምንም ” እንደማይል  ገልጸዋል።

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነቶች ሀይሎችን በተለያዩ የሀይማኖት እና የመንግስት ተቋማት ማሰማራቱን፣ ሌሎች አዳዲስ የደህንነት ሰራተኞችም በስልጠና ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

መንግስት በእስራኤል አገር የሰለጠኑ የደህንነት ሀይሎችን አሰማራ


ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የብሄራዊ ጸጥታና ደህንነት መስሪያ ቤት በእስራኤል አገር በታል አራድ ኔጊቭ ማሰልጠኛ ጣቢያ ያሰለጠናቸው 987 የደህንነት ሰራተኞች በመላ አገሪቱ በሚገኙ 572 ታላላቅ መስጊዶች እና በቴሌኮሚኒኬሽን መስሪያ ቤት ማሰማራቱን ከደህንነት መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል ፡፡
ከሰልጣኞች መካከል 11 ዱ ብቻ የእስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ ቀሪዎቹ አረብኛ አቀላጥፈውየሚናገሩ ፣ ቁራንን በስርዓት የተማሩ እና እስልምናን ስርዓቶች ሙሉ በሙሉ የሚፈጽሙ ናቸው፡፡
ቀሪዎቹ ሰልጣኞች በቴሌ ኮሚኒኬሸን መስሪያ ቤት የተመደቡ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ በስልክ ጠለፋ ስራ ላይ ይሰማራሉ፡፡ ከሰልጣኞች መካከል 631 ዱ የትግራይ ብሄር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በትምህርት ደረጃም የ2002 ምሩቃን በብዛት ይገኙበታል።
በቴሌ የተቀጠሩት አዲሶቹ የደህንነት ሰራተኞች መንግስት ከፈቀደላቸው ውጭ ሌላ የስልክ ግንኙነት የተጠቀሙትን ሚኒስትሮች በድምጽ እንዲለዩ በተሰጣቸው ፈተና መሰረት የተወሰኑ ሚኒስትሮችን ስም ዘርዝረው አቅርበዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶክተር ከሰተ ብርሃን አድማሱ፣ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር አቶ ሙክታር ከድር፣ የንግድ ሚኒስትርነት አቶ ከበደ ጫኔ፣ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ዘርፍ (ክላስተር) አስተባባሪ አቶ ሙክታር ከድር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታው አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣እንዲሁም የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት ከፈቀደላቸው የስልክ ግንኙነት ውጭ በራሳቸው መንገድ ስልክ ሲያወሩ ተገኝተዋል ።
ባለስልጣኖቹ በእነዚህ ስልኮች ተጠቅመው የተናገሩት በ ዶ/ር ደብረ ጽዩን አማካኝነት ወደ መረጃ እና ደህንነት ቢሮ መተላለፉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ኢሳት መንግስት በእስራኤል አገር ልኮ ያሰለጠናቸውን የደህንነት ሰራተኞች እውነተኛ ስም እና ዝርዝር ታሪክ አስፈላጊ ነው ብሎ በሚያምንበት ጊዜ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ለማስታወቅ ይወዳል፡፡

ኢትዮጵያዊነት እንዴት ያኮራል ኢትዮጵያዊ በመሆኔ በጣም እኮራለው ፍቅራችን ከድሮም እንዲህ ነው ልትከፉፍሉ አትሞክሩ አንድ ህዝብ አንድ አገር


Monday, July 1, 2013

ESAT Daliy News - Amsterdam July 01, 2013 Ethiopia



የግብፅ ጦር ፕሬዚዳንት ሙርሲ ለተቃዋሚዎች ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጡ 48 ሰዓታት ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2005 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብፅ  ጦር በአገሪቱ  ለተከሰተው ቀውስና  ለተቃዋሚዎች ጥያቄ ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ምላሽ እንዲሰጡ 48 ሰዓት  ሰጠ ።
ጦሩ የፕሬዚዳንቱ  መንግስት አሁን ለተፈጠረው  ቀውስ  ፈጥኖ ምላሽ  መስጠት ካልቻለ ለሰላም ሲል የራሱን  ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ  እንደሚተገብር አስታውቋል ።
ይህ  የጦሩ መግለጫ  የወጣው  ተቃዋሚዎቹ  ከሰዓት በኋላ  በካይሮ  የሚገኘውን የፕሬዚዳንት ሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማቾች ዋና መስሪያ ቤት  ከወረሩ በኋላ ነው ።
የፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት በእሳት የተቀጣጠለ ሲሆን ፥  በውስጡ  የሚገኙ  ንብረቶችም ተዘርፈዋል ።
በዋና ፅህፈት ቤቱ  አከባቢ  በነበረው  ግጭትም  ስምንት  ያህል  ሰዎች ተገድለዋል ።

ሚኒስትሮች ስልጣናቸውን  እየለቀቁ ነው
በፕሬዚዳንቱ ላይ  የተቀሰቀሰው  ተቃውሞ  በመላው  የግብፅ  ከተሞች የተቀጣጠለ ሲሆን ፥ እስካሁንም  አምስት ሚኒስትሮች ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው ለቀዋል ።
የቱሪዝም ፣የውሃ ፣ የአከባቢ ፣  የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ እንዲሁም  የህግና  ፓርላማ  ጉዳዮች ሚኒስትሮች የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለጠቅላይ  ሚኒስትር ሂሻም ቃንዲል  አቅርበዋል ።
የግብፅ  የአገር  ውስጥ  ሚኒስቴር  እንዳስታወቀው በትናንቱ  የተቃውሞ ሰልፍ ላይ  ብቻ  ከ14 እስከ 17 ሚሊዮን  የሚጠጉ  ሰዎች  ለተቃውሞ  አደባባይ ወጥተዋል ።
በአንፃሩም  ትናንት  ሙርሲን ደግፈው አደባባይ  የወጡ  ሰዎች ነበሩ ።
በሁለቱ  ጎራ  በተቀሰቀሰም  ግጭት እስካሁን 14  ሰው   መገደሉንና  በ100  የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው  ተነግሯል ።
ተቃዋሚዎቹ  ፕሬዚዳንት  ሙርሲ እስከ  ነገ ስልጣን  እንዲለቁ ማስጠንቀቂያ  ሰጥተዋል ።
ይህንን  ማድረግ ከተሳናቸው  ግን  በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን  እንደሚቀጥሉ  ነው የገለፁት ።

ምንጭ: ቢቢሲ