Saturday, June 1, 2013

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጉዳይ ለሃምሌ ሁለት ተቀጠረ ፕ/ር መስፍን ምስክርነት ይሰጣሉ


በ “ፍትህ” ጋዜጣ “የሁለተኛ ዜግነት ህይወት እስከመቼ”፣ “የፈራ ይመለስ” እና “መጅሊሱና ሲኖዲሱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ማጥመቂያ” በሚሉ ርዕሶች በተለያዩ እትሞች ባሰፈረው ዘገባ ተከስሶ ጉዳዩ ሲታይ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ምስክሮችን ለመስማት ለሃምሌ ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ ከትላንትና በስቲያ በከፍተኛው ፍ/ቤት 16ኛ ወንጀል ችሎት የጋዜጠኛው ምስክሮች ሊደመጡ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም ፍ/ቤቱ የተከሳሽን የመከላከያ ቃል ሲያዳምጥና ስለምስክሮቹ ከጠበቆች መግለጫ ሲሰማ ሰዓት ያለቀ በመሆኑ የምስክሮችን ቃል ለመስማት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ “የህዝብን ሃሳብ በማናወጥ” ፣ “ህዝብን በህገ መንግስቱ ላይ ማነሳሳትና” “የመንግስትን ስም ማጥፋት” በሚሉ ሶስት ጉዳዮች ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ ሲታይ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስገን፤ የመከላከያ ምስክሮቹ ምስክርነታቸውን ለመስጠት ሀሙስ ዕለት በፍርድ ቤቱ ተገኝተው ነበር፡፡ ሆኖም በጊዜ እጥረት ሳይመሰክሩ ቀርተዋል፡፡
ከጋዜጠኛ ተመስገን ምስክሮች ውስጥ 1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድ የህግ ባለሙያ ሲሆኑ ሁለተኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም እና 3ኛ ምስክር ጋዜጠኛ እንዳልካቸው ሀ/ሚካኤል ከህግ፣ ከጋዜጠኝነትና ከመናገር ነፃነት እና መሰል ጉዳዮች አንፃር ምስክርነታቸውን በቀጣዩ ቀጠሮ እንደሚያቀርቡ ተገልጿል፡፡ የፌደራል አቃቤ ህጎች በ1ኛ ምስክር ዶ/ር ያሬድና በሁለተኛ ምስክር ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም ላይ እንዳይመሰክሩ ተቃውሞ ያቀረቡ ሲሆን የተቃውሞው ምክንያት ዶ/ር ያሬድ የህግ ባለሙያ ቢሆኑም ህገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን እንደሌላቸው በመግለፅ ሲሆን 2ኛ ምስክር የሆኑት ፕ/ር መስፍን ደግሞ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ሊቀመንበር የነበሩ ቢሆንም ከ1997 ዓ.ም ወዲህ በነበራቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ገለልተኛ ሆነው ይመሰክራሉ የሚል እምነት እንደሌለ በመግለፅ ነበር፡፡
ፍርድ ቤቱም በኋላ 1ኛ ምስክር ህገ-መንግስቱን የመተርጎም መብት ባይኖራቸውም ተከሳሽ የተከሰሱባቸው ፅሁፎች ከህግ አንፃር እና ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ አኳያ አግባብ ናቸው አይደሉም ያስከስሳሉ አያስከስሱም፣ በሚለው ላይ ብቻ እስከተናገሩ ድረስ ችግር እንደሌለው ጠቁሞ፤ ፕ/ር መስፍንም የኢሰመጉ ሊቀመንበር በነበሩበት ጊዜ ድርጅቱ ስላወጣቸው ሪፖርቶችና ተያያዥ ነገሮች ብቻ ከተናገሩ የፖለቲካ እንቅስቃሴያቸው ከምስክርነት ያግዳቸዋል የሚል ህግ እንደሌለ በመግለፅ የተከሳሹን ምስክሮች ቃል ለመስማት ፍ/ቤቱ ለሃምሌ ሁለት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
addis admas

አባይና የሲና በረሃ መተላለቅን የሚያስከትሉ አደገኛ የቀውስ ምንጭ


Image
”
ኢትዮጵያ ከትናንት ግንቦት 20/2005የአባይ ወንዝን የተፈጥሮ አቅጣጫ መቀየሯ የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንና ጉዳዩ የሚመለከታቸዉ ሀገራት መነጋገሪያ አጀንዳ ሆኗል፡፡ ዋናው ጉዳይ ምሽት ላይ አልጀዚራ በኢንሳይድ ስቶሪ /inside story/ ፕሮግራሙ ከኢትዮጵያ አቶ በረከት ስምዖንን፤ ከግብፅ ላማ ኤል ሃሎንና ከእንግሊዝ ሊዮ ፓስካልን በማስገባት ዉይይት ያደረገበት ነው፡፡ በዚህ ላይ በኋላ እመለስበታለሁ፡፡ አሁን ግን መገናኛ ብዙሃን፤ ግብፅና ሱዳን ምን አሉ የሚለዉን እንመልከት፡፡
በጉዳዩ ላይ ሰፊ ዘገባ የሰጠው አህራም የተባለዉ የግብፅ ድረ-ገፅ ነው፡፡ ቢቢሲ፤ አልጀዚራና ዋሽንግተን ፖስትም እንዲሁ፡፡ ሁሉም ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን በተለያየ መጠን ለጉዳዩ ሽፋን ሰጥተውታልማለት ይቻላል፡፡ ከብዛታቸውና ከምንጫቸው ተመሳሳይነት አንፃር የያንዳንዱን ዘገባ አቅጣጫ ከማየት ይልቅ በዚህ ጉዳይ ላይ በስፋት አስተያየታቸውን ወደሰጡት ግለሰቦች አትኩሬአለሁ፡፡
ከላይ ከቁንጮው እንነሳ፡፡ ማለቴ ከግብፅ መንግስት አቋም፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ አሁን በአባይ ወንዝ ላይ እየተካሄደ ያለው ግንባታ በውሃ መጠኑ ላይ መቀነስን ሊያስከትል የሚችል እንዳልሆነ የሚገልፅ ነው፡፡ በአባይ ላይ የሚገነባ ማንኛውም ፕሮጀክት ከመጀመሩ በፊት የወንዙን አቅጣጫ በማስቀየር ቦታውን ለግንባታ ምቹ ማድረግን ይጠይቃል ብሏል መግለጫው፡፡ ስለሆነም ከተለመደው ውጭ የሆነ አዲስ ነገር የለም የሚል ይመስላል፡፡
የግብፅ ካቢኔም በጉዳዩ ላይ ትናንት በዝግ ከመከረ በኋላ ባወጣት ቁራጭ መግለጫ የግድቡ ግንባታ ተጀመረ ማለት ግብፅ እውቅና ሰጥታዋለች ማለት አይደለም ብሏል፡፡ ያም ሆኖ የግብፅና ሱዳን የውሃ ድርሻን የማይቀንስ እስከሆነ ድረስ ማንኛዉንም የልማት ፕሮጀክት እደግፋለሁ ብሏል ካቢኔው፡፡ ካቢኔው ጨምሮ እንደገለፀው ለማንኛውም የሶስትዮሽ ኮሚቴውን የጥናት ሪፖርት ይፋ መሆን እንደሚጠብቅ ገልጧል፡፡ ሪፖርቱን ተከትሎ የሚይዛቸዉን አቋሞች /የሚወስዳቸዉን እርምጃዎች/ ከወዲሁ እንዳዘጋጀም ካቢኔው ጠቁሟል፡፡ ምን እንደሆኑ ፍንጭ ከመስጠት ቢቆጠብም፡፡ በዝች መግለጫ መጨረሻ የገባችዉ አረፍተ ነገር ደግሞ “ግብፅና ሱዳን በአንድ ልብ ሆነን በጉዳዩ ላይ ተባብረንእየሰራን ነዉ” ትላለች፡፡ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እያደላች ነው የሚለዉን ዘገባ ለማጣጣል የገባች አረፍተ ነገር ሳትሆን አትቀርም፡፡
ዘግይቶ እንደተረዳሁት ደግሞ ዛሬ ግንቦት 22/2005 ፕሬዝዳንት ሙርሲ ከተመረጡ ሚንስትሮች ጋር በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
የሃገሪቱ የሹራ ምክር ቤት ደግሞ በመጭው እሁድ በዚሁ ጉዳይ ላይ ለመምከር የአስቸኳይ ስብሰባ ቀን ቆርጧል፡፡ በስብሰባው የውጭ ጉዳይና የደህንነት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎችን ጨምሮ 6 ኮሚቴዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፡፡
እኔ እንዳገኘሁት መረጃ ከሆነ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርበሃገሪቱያሉትንየኢትዮጵያአምባሳደርሞሃሙድድሪርንአስጠርቶበጉዳዩላይቃላቸዉን
ተቀብሏቸዋል፡፡ምስኪን!ምንብለዉይሆን?የሚኒስቴሩየስራሃላፊዎችከበውበጥያቄ ሲያዋክቧቸው፡፡እንደመረጃውሰዎቹበኢትዮጵያዉሳኔመከፋታቸዉንለአምባሳደሩገልፀውላቸዋል፡፡
በሌላ በኩል የግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ቴዎድሮስ /ዳግማዊ/ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ጣልቃ ገብተው ነገር እንዲያበርዱ በግብፅ ፕሬዝዳንት ተጠይቀዋል፡፡ አንድ የቤተክርስቲያኗ የህግ ባለሙያ እንዳሉት ፕሬዝዳንቱ ለጳጳሱ ደውለው የጋራ መፍትሄ በሚገኝበት መንገድ ላይ ከኢትዮጵያው አቻቸው ጋር እንዲመክሩ ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሆኖም ይሄ ሃሰት ነው፤ ማንም ምንም አላለንም የሚል ማስተባበያ ከቤተክርስትያኗ ወጥቷል፡፡
ከአባይ ወንዝ የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየር ጋር በተያያዘ ስማቸው በተደጋጋሚ የተነሳዉ የግብፅ ውሃና መስኖ ልማት ሚንስትሩ ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ናቸው፡፡ እሳቸዉ የንግግራቸው መጀመሪያ ያደረጉት ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፅ ነው፡፡ ይህ አቋማቸው እንዳለ ሆኖ የወንዙ የፍሰት አቅጣጫ መቀየሩ ግን ለግብፅ ምንም ጉዳት እንደሌለው ለጋዜጠኞችአረጋግጠዋል፡፡ “የተለመደ የግንባታ ሂደት መገለጫ ብቻነዉ” ብለውታል፡፡የአንድ ሃገር ሚኒስትር ከዚህ በላይ ሊሉት የሚችሉት በጎ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ የሃራቸውን ጥቅም የሚጎዳ ነገር ካለ እሱን መቃወም አለባቸው፤ ከሚጠቅማቸው ጋር ደግሞ መተባበር፡፡ እሳቸው ያሉትም ይህንኑ ነው፡፡ አሁን በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም፤ የጋራ ኮሚቴው ሪፖርት እስከሚወጣ እንጠብቃለን ነው ያሉት፡፡
እኝህ ሰው በቅርቡ በሃገሪቱ በተደረገው የስልጣን ሽግሽግ ባሉበት እንዲቆዩ ሲደረጉ እንኳን ደስ አለዎት በማለቴ የተረቡኝ እንደነበሩ አስታውሳለሁ፡፡ ሰውየው ምንም ያህል ትችት ቢሰነዘርባቸውም ስለኢትዮጵያ ያላቸውን በጎ እይታ በአደባባይ ከመግለፅ ያልተቆጠቡ ናቸው፡፡
ሌላዉ በዚህ ጉዳይ በንቃት የተሳተፉት በኢትዮጵያ የግብፅ አምባሳደር ሞሃመድ እድሪስ ናቸው፡፡ የህዳሴው ግድብ ግብፅ የግዷንም ቢሆን ልትቀበለው የሚገባ የማይቀር ክስተት /reality/ ነው ብለዋል፡፡ የግብፅ የድርድር ግብ መሆን ያለበትም ግድቡን ማስቆም ሳይሆን ሁለቱም ወገኖች ተጠቃሚ በሚሆኑበት መንገድ ላይ ሊሆን እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡“የአስዋን ግድብ ለኛ አንደሚያስፈልገን ሁሉ የህዳሴዉ ግድብም ለኢትዮጵያውያን ብሄራዊ ሃብታቸው ነዉ”ሲሉ ነው እዉነታውን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ የቆረጡት፡፡ አምባሳደሩ አሁን ኢትዮጵያ ያደረገችው ነገር ዱብ እዳ ሳይሆን ካለፈው ህዳር ጀምሮ የምናውቀው ነው ብለዋል፡፡
“በሁሉም መድረኮቻችን ኢትዮጵያ በኛ ላይ ጉዳት እንደማታስከትል ደጋግማ አረጋግጣልናለች፤ እኛም ይህንኑ አምነን ተቀብለናል” ያሉት አምባሳደሩ ግብፅ ሶስቱም ወገኖች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር እየፈለገች መሆኗን ተናግረዋል፡፡እኔ የነዚህን ባለስልጣናት ንግግር በአወንታዊ መልኩ ነው ያየሁት፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ኢትዮጵያ እነሱን የመጉዳት ሃሳብ እንደሌላት መረዳታቸዉን ገልፀውልናል፡፡ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ቀስ በቀስ ቅቡል እየሆነ መምጣቱን አመላካች አስተያየት ነው፡፡
ሆኖም የሀገሪቱና የአለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘገባ አሉታዊ ነው፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ ከግድቡ ጋር ያሉ አወንታዊ ጎኖችን ዘወር ብለዉ እንኳን ሳያዩ ሊያስከትል ይችላል ብለዉ ባሰቡት ተፅዕኖ ላይ ብቻ ነዉ ያተኮሩት፡፡
ባለስልጣኖቹ ከተናገሩት ውስጥ ሲመርጡ እንኳን ይህንኑ ፍላጎታቸውን የሚያሟላላቸዉን ንግግር ብቻ እንጅ በመቻቻልና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩትን አገላለፆች በተደጋጋሚ ዘለዋቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያክል ሞሃመድ ባሃ ኢልዲን ግብፅ በጥቅሟ ላይ የሚመጣን ማንኛውንም አይነት ፕሮጀክት እንደማትደግፍ መግለፃቸውን ሲያራግቡ በግብፅ ላይ የተደቀነ አደጋ የለም ማለታቸውን ግን ብዙዎቹ አድበስብሰውት አልፈዋል፡፡ምሁራኖቻቸውም እንዲሁ ናቸው፡፡ አንድ ምሁር “ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ሙርሲ ጉብኝት ማግስት የናይል ወንዝን የፍሰት አቅጣጫ ማስቀየሯ የግብፅና ህዝብና መንግስት ለማታለል የምትከተለውን ስልት የሚያሳይ ነው” ብሏል፡፡ የግብፅ ባለስልጣናት የህዝባቸውን ጥቅም አሳልፈው ሰጥተዋል ሲልም ወቅሷል፡፡ ለዚህም የግብፅ ህዝብ የጃቸውን ሊሰጣቸው ይገባል ነው ያለው፡፡
ሌላው የሚጠበቅ ግን ቢሆንም መታወቅ ያለበት የግብፅ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቋም ነዉ፡፡ ፓርቲዎቹ ይህንን ጉዳይ ለፖለቲካ ጥቅም ማግኛ ሲጠቀሙበት ተስተውለዋል፡፡ እነሱ እንደ ጠንካራና ለግብፅ ህዝብ የቆሙ፤ ሙስሊም ብራዘርሁድ የሚመራው መንግስት ደግሞ እንደ ልፍስፍስና የህዝቡን ጥቅም አሳልፎ የሰጠ አድርገው አሳይተዋል፡፡ የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንቱ ኤል ባራዲ በቅርብ ሰዓት በግል ቲዊታቸው የሲና በረሃና ኢትዮጵያ መተላለቅን የሚያስከትሉ አደገኛ የቀውስ ምንጭ እንደሆኑ ተንብየዋል፡፡ይችን ነገር ከኛ ሃገር ተቃዋሚዎች የኮረጇት ሳትሆን አትቀርም፡፡ በነገራችን ላይ የኛዎቹ እስካሁን ድምፃቸዉ አልተሰማም፡፡ የአባይ መንገዱን መቀየር አልሞቃቸውም፤ አልበረዳቸውም፡፡
በአንፃሩ የቀድሞው የአረብ ሊግ ዋና ፀሃፊና የዚሁ የናሽናል ሳልቬሽን ፍሮንት ሌላው አመራር የሆኑት አሚር ሙሳ የታችኛው ተፋሰስ ሃገራት በተለይም ግብፅ በአባይ ወንዝ ላይ በሚካሄድ ፕሮጀክት የተነሳ መጎዳት እንደሌለባቸውና በዚህ ጉዳይ የአፍሪካ ቀንድ ውጥረት ውስጥ መግባት እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡ ለዚህም በመፍትሄነት ያቀረቡት ኢትዮጵያ የግብፅን ፍላጎት፤ ግብፅም የኢትዮጵያን ፍላጎት ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት እንዳለባቸው ነው፡፡ ግብፅ በአስቸኳይ ወደ ድርድር መግባት እንዳለባት ጠይቀዋል፡፡
በሰሞኑ የመገናኛ ብዙሃን ዘገባዎች ውስጥ ግብፅ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባት የሚጠቁሙ አስተያየቶችም ተስተናግደዋል፡፡ ወታደራዊ እርምጃና የሲዊዝ ቦይን መዝጋት በዚህ ስር የታዩ ናቸው፡፡ሼክ ሃሚድ የተባሉ የአንድ ሃይማኖታዊ ቡድን መሪ እንዳሉት ሁኔታው ሲገመገም አሁን ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ጦርነት አውጃለች እንደማለት ነዉ፡፡ ስለሆነም እኛም ያለንን አቅም ሁሉ ተጠቅመን መብታችንን እናስከብራለን ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቱ ቅድሚያ ሊሰጠዉ ይገባል ብለዋል፡፡ ይህ እንግዲህ በግልፅ ሲቀመጥ ጦርነት ተከፍቶብናልና ለጦርነት እንነሳ ማለት ነው፡፡ሆኖም ይህ ሀሳብ በአንድ የቀድሞ ጦር አዛዥ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ ጀነራል ሞሃመድ አሊ ቢላል የህዳሴዉን ግድብ በአውሮፕላን ለመምታት መሞከር ከብዙ የአለም ሃገሮች ጋር ያጣላል ነው ያሉት፡፡ ከነዚህም ውስጥ እስራዔልንና ቻይናን አንስተዋል፡፡ ሁሉ ካልተሳካ ግብፅ ያላት አማራጭ ለአለም አቀፍ ፍርድ ቤት፤ ለፀጥታው ምክር ቤት ወይም ለአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ክስ ማቅረብ ነው ብለዋል፡፡ ሌላ ወታደራዊ ባለስልጣንም ይህ ሃሳብ የግድቡ ግንባታ በተበሰረበት የሆስኒ ሙባረክ ዘመን ተነስቶ እንደነበር ለጋዜጦች ተናግረዋል፡፡ ያኔ የጦርነት አማራጭ በጥብቅ እንደተወገዘ አስረድተዋል፡፡በሌላ በኩል ግብፅ ኢትዮጵያን በግንባታው ዙሪያ የሚያግዙ ሀገራት መርከቦች በስዊዝ ቦይ እንዳይጠቀሙ ብትከለክል ውጤት ልታገኝ ትችላለች ሲል አንድ የግብፅ ተቃዋሚ ፓርቲ ሃሳቡን አካፍሏል፡፡
ይህ በንዲህ እንዳለ የሱዳኑ የውሃ ሃብትና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ሞሃመድ ሃሰን በጉዳይ ላይ ለመምከር ወደ ካይሮ ሄደዋል፡፡ እዛ እንደደረሱም ከግብፁ አቻቸው ጋር ተመካክረዋል፡፡ ምን እንደዶለቱ ግን እስካሁን ወሬ አላገኘሁም፡፡ ወደ ሱዳን ከገባሁ አይቀር በዚሁ የሱዳን ሁኔታ እንመልከት፡፡
በግብፅ የሱዳኑ አምባሳደር ከማል ሃሰን የአባይ ወንዝ አቅጣጫ የመቀየር ዜና አስደንጋጭ እንደሆነና ሱዳንና ግብፅየአረብ ሊግን ጣልቃ ገብነትሊጠይቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል በሚል ትናንት በርካታ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውት ነበር፡፡ ሆኖም ከምሽት ጀምሮ በአንዳንድ የግብፅ ጋዜጦችና በሱዳኑ ሱዳን ትሪቡን ድረ ገፅ የወጣ ዘገባ አምባሳደሩ ይህንን ማለታቸውን የሚያስተባብል ነው፡፡የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እኛ እንዲህ አይነት ንግግር ካፋችን አልወጣም ብሏል፡፡ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችው ነገር በሱዳን ላይ ምንም ጉዳት እንደሌለው አረጋግጠናል፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ሁላችንም ተጠቃሚ በምንሆንበት ነገር ላይ ከኢትዮጵያም ሆነ ግብፅ ጋር ለመተባበር ዝግጁ ነን ሲል አቋሙን አሳውቋል፡፡
እስኪ አሁን ደግሞ ትናንት ምሽት በአልጀዚራ ስለተላለፈዉፕሮግራምላንሳ፡፡በኢንሳይድስቶሪፕሮግራምላይከአዲስአበባየመንግስትኮሚዪንኬሽን
ሚኒስትሩአቶበረከትስምዖን፤ከካይሮየአካባቢጥበቃባለሙያዋላማኤልሃሎናከለንደንደግሞ
ደራሲዋሊዮፓስካልቀርበዋል፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጅ ገና ሲጀምር የህዳሴውን ግድብ በግብፅ ህልውና ላይ የተደቀነ አደጋ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡ የግብፅ ህዝብ በ2050 /በነሱ አቆጣጠር/ 150ሚሊዮንስለሚደርስግብፅተጨማሪ21 ቢሊዮንኪዉቢክሜትርውሃያስፈልጋታል፤ግድቡግንእንኳንይህንእድልሊሰጣት18 ቢሊዮንኪዩቢክሜትርውሃያሳጣታልሲልበመደምደምይነሳል፡፡የሃይልማመንጨትአቅሟንና
የግብርናምርትመጠኗንምይቀንሰዋል፤በዚህምሚሊዮኖችለረሃብይጋለጣሉይላልጋዜጠኛዉ፡፡አቶ በረከት በሰጡት ምላሽ ታዲያ እንደማስበው የኢትዮጵያ ፍላጎት በግብፅም ሆነ ሱዳን ላይ ይህን ያህል ጭንቅ መፍጠር ሳይሆን የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ነው አሉ፡፡
ጋዜጠኛዉ “ፍላጎታችሁ ጉዳትማድረስላይሆንይችላልግንሂደቱይህንጣጣሊያመጣይችላል”ሲል አቋረጣቸው፡፡በረከትምሂደቱየሚያስከትለዉእንደውምየተሻለየዉሃመጠንነዉ፡፡ምክንያቱምእኛ
በአካባቢያችንየምናከናውነውየተፈጥሮሃብትእንክብካቤስራየከርሰምድርዉሃመጠንንየሚያሳድግነው
ሲሉተከራክረዋል፡፡
በዚህ ግዜ ጋዜጠኛው ሊዎ ፓስካልን ግብፅ የሱዳንን መሬት ተጠቅማ በኢትዮጵያ ላይ የሃይል እርምጃ ልትወስድ የምትችልበት እድል እንዳለ ጠየቃት፡፡ እርሷም ስትመልስ ግብፅ ይህን ስልት ቀድማም ትጠቀምበት እንደነበር አስታውሳለች፡፡ በተለይም ሶማሊያንናኤርትራንበመጠቀምኢትዮጵያንየማዳከምስልትትከትልእንደነበርአውስታለች፡፡
አሁንግንየኢትዮጵያጡንቻበአካባቢውእየፈረጠመመሆኑንታነሳናየጦርነትአማራጭለግብፅአዋጭ
እንዳልሆነ በተዘዋዋሪ አስረድታለች፡፡
ጋዜጠኛው ውሃን እንደጦር መሳሪያ አድርጎ ማየቱ ያላስደሰታቸዉ አቶ በረከት“እኛዉሃያጣላናልብለንአናስብም፡፡ይህአንተየምትለዉምግዜያለፈበትተረትነዉ”
ብለውታል፡፡እንደሚኒስትሩኢትዮጵያወጭውንብቻዋንትሸፍነውእንጅጥቅሙ የሁሉም ሀገሮች ነው፡፡ ግብፅም ሆነች ሱዳን በበጋ ወራት ሳይቀር ወጥነትና ብዛት ያለው ዉሃ ሊያገኙ እንደሚችሉ የተከዜው ግድብ ለሰሜን ምስራቅ የሱዳን አካባቢዎች ያስገኘዉን ጥቅም በአብነት በማንሳት አብራርተዋል፡፡
በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈረሙ ስምምነቶች ኢትዮጵያን ያገለሉ እንደሆኑና ይህንን በመቀየር ኢትዮጵያም ሆነች ሌሎቹ ሃገራት በጋራ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር መዘርጋት እንደሚገባ ተከራካሪዎቹ አንስተዋል፡፡ ፓስካ“ኢትዮጵያየድርሻዋንካልተጠቀመችማለውሃው/ለወንዙ/ ደህንነት ለምንትጨነቃለች?”ስትልመልሳጠይቃለች፡፡ኤልሃሎበበኩሏየቀድሞውጠ/ሚ መለስ ዜናዊ ንግግርንበማስታወስግድቡየኢትዮጵያብቻሣይሆንየአካባቢውሃብትእንደሆነአሳይታለች፡፡
በአጠቃላይ ሲታይ ውይይቱ መግባባት የሰፈነበት ነበር፡፡ ሆኖም ከኢትዮጵያው ሚኒስትር በስተቀር ሌሎቹ ጉዳዩ በቀጥታ የማይመለከታቸውና የመወሰን ስልጣንየሌላቸዉመሆኑየውይይቱንፋይዳያሳንሰዋል፡፡ውይይቱበሶስቱሃገራትከፍተኛ ባለስልጣኖች መካከልቢሆንይሻልነበር፡፡ነገርግንሱዳንናግብፅበአሁኑሰዓት/ቢያንስየገምጋሚውቡድንሪፖርት
ይፋእስኪሆን/ለመነጋገርዝግጁየሆኑአይመስልም፡፡
ስለብዙ መገናኛ ብዙሃን ብዙ አውርቼ ስለ ኢሳት ትንሽ እንኳን ካላልኩ ወዳጆቼ ይቀየሙኛል፡፡ በመጨረሻ ኢሳት ምን እንዳለልንገራችሁ፡፡“የወንዙንአቅጣጫየማስቀየሱስራለግንቦት20 በዓልየድረስድረስስለሆነስራውበአግባቡአልተፈፀመም” ብሏል፡፡ እዛው በቦታው ያነጋገርኳቸው ሰዎች እንደነገሩኝ የግንባታዉ ሂደት እጅግ ተጓትቷል ሲል ዘግቧል፡፡ ሶስተኛ አማራጭ ይሏችኋል ይህ ነዉ፡፡ ግብፅና ሱዳን አባይ ተቀየሰ ብለው ሲደነግጡ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ትንሽ ዘወር አለ እንጅ ከናንተው አይቀርም እያለ ነው፡፡
እንግዲህ ዛሬ እንዲህ ተዉሎ ተመሽቷል፡፡ ነገም ሌላ ቀን ነዉ፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ደግሞ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው የአለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን ሪፖርት ይፋ ይሆና፡፡ ያኔ ደግሞ የሚወራዉን እንሰማለን፡፡
ስለ አባይ ምን ተባለ? /የተሻሻለ/
kebede kassa

Thursday, May 30, 2013

መንግስት በጉምሩክ ባለስልጣናት ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደ ሌሎች ባለስልጣናት ማዞር ፈርቷል ተባለ



ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-መንግስት በቅርቡ በገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሥራ ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ላይ የወሰደውን እርምጃ ወደሌሎች በሙስና የሚጠረጠሩ ባለስልጣናት ለማስፋት ፍርሃት እየታየበት መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር ከኢትዮምህዳር ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለምልለስ ገልጸዋል፡፡
ዶክተሩ ግንቦት 20 ለወጣው ኢትዮምህዳር ጋዜጣ እንደተናገሩት “በሙስና ተከስሰው ወደወህኒ የወረዱት የአንድ መ/ቤት ሠራተኞችና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሐብታሞች ናቸው፡፡ የሙስናው ደረጃ በጣም የተስፋፋና የአገሪቱን አብዛኛውን ተቋማት ያዳረሰ ለመሆኑ ከኦዲት ሪፖርቱ ፍንጭ አግኝተናል፡፡ ይሁንና የክሱን ውስንነት በምናይበት ጊዜ ከጉምሩክ ውጪ ያሉ ስማቸው በሙስና የሚነሳ ተቋማትን ለመንካት ፈራ ተባ የተባለ ይመስለኛል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ዳኛቸው አያይዘውም በአንድ ስርዓት ውስጥ የፖለቲካዊና የሕግ አይነኬዎች ከኖሩ ስርዓቱ ትልቅ ችግር ውስጥ የወደቀ መሆኑን እንደሚያሳይ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት በራሱ ውስጥ ሙስና መኖሩን ማመኑ በራሱ ትልቅ ነገር መሆኑን ዶ/ር ዳኛቸው ጠቁመው ነገር ግን መንግስት በሙስና ዙሪያ የሚሰጠውን መግለጫ ዜጎች አሜን ብለው መቀበል እንደሌለባቸው መክረዋል፡፡
“በአሁኑ ወቅት እንደሚታየው ጥቂት ሰዎችን ከተወሰኑ ተቋማት በመውሰድ በማስር ብቻ ችግሩ የግለሰቦች የሞራል ዝቅጠት አድርጎ የማቅረብ ነገር እያየን ነው፡፡ ነገር ግን በኔ አስተያየት ሙስናው ከስርዓቱ ጋር በእጅጉ የተያያዘ ነው” ብለዋል፡፡
“ሁሉም ሹመኞች ሙሰኞች ስለሆኑ በምን የሞራል መመዘኛ አንዱ ከሳሽ ሌላው ተከሳሽ ይሆናል” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም “ሁላችንም የሰው ልጆች እስከሆንን ድረስ እርስበርሳችን ተካሰን ለመተራረም እንሞክራለን እንጂ ከሰማየሰማያት የመላዕክት ዐቃቤ ሕግ አምጥተን ችሎት ልናቆም አንችልም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በተያያዘም ያለፉት 22 ዓመታት የኢህአዴግ የአገዛዝ ዘመን ሕዝቡን ፍርሃት ውስጥ እንደጣለው ዶ/ሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ “…ልክ የገንዘብ የመግዛት አቅም እንዳሽቆለቆለው ሁሉ የሕዝቡም በነጻነት የመናገር ድፍረት እየወረደ መጥቷል” በማለት አስረድተዋል፡፡
ይህንን አባባላቸውን በምሳሌ ሲያስረዱ “ ለሶስት አመታት ያህል በሕዝብ ትራንስፖርት ስገለገል ቢያንስ ቢያንስ ከምኖርበት አሮጌው አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ስድስት ኪሎ ድረስ
ስሄድና ስመለስ ስድስት ታክሲዎችን ስለምጠቀም ከበርካታ ሰዎች ጋር የመገናኘት ዕድል ነበረኝ፡፡ ይህንኑ ዕድል ተጠቅሜ አንዳንድ የፖለቲካ ጨዋታዎችን ስጀምር አብረውኝ የሚጓዙ ሰዎች ለማናገር ወይንም ከእኔ ጋር ለመወያየት እንደሚፈሩ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ይህ የፍርሃት ድባብ በታክሲ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሬስቶራንት፣ በቡና መጠጫ ስፍራዎች፣ በአጠቃላይ በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች የሚስተዋል መሆኑን ተረድቻለሁ፡፡ ምናልባት እዚህ ላይ
የሶስዮሎጂ መምህራን አቀራረብህ ሳይንሳዊ አይደለም፣በቂ መረጃ የለህም ሊሉ ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን በተለይ ከምርጫ 97 በኃላ የአፈናና የፍርሃት ድባቡ እንደተጠናከረ ከመንግስት ውጪ ያሉ ዜጎች እንደሚመሰክሩ ጥርጥር የለኝም” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
እንደዶ/ር ዳኛቸው ገለጻ ሕዝብን የማስፈራራትና የማቀብ ስርዓት በትክክል እየሰራ ነው የሚባለው ሕዝቡ ይህንን አድርግ፣አታድርግ ተብሎ ሳይታዘዝ ከፍርሃት በመነጨ ራስን ማገድ ሁኔታ ላይ ሲወድቅ ነው በማለት አገሪቱ የምትገኝበትን ተጨባጭ ሁኔታ ዳስሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት ድህረ ገጾችን ለማፈን 26 ቢሊዮን ብር ክፍያ ለቻይና መንግስት ፈጸመ

ግንቦት ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአስተማማኝ የኢትዮጵያ የመረጃ መረብ የደህንነት ሰራተኛ ባገኘው መረጃ መንግስት ለስርአቱ አደጋ ይሆናሉ ብሎ የገመታቸውን የመገናኝ ብዙሀን ወደ አገር ቤት ሰርገው እንዳይገቡ ለመከላከል ከ1.2 ቢሊዮን ዶላር ወይም ወደ 26 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ መክፈሉን ለማወቅ ተችሎአል።
በቁጥር አንድ እንዲታፈን ትእዛዝ የተላለፈበት ኢሳት ሲሆን ድህረገጹ ራዲዮው እና ቴሌቪዥኑን ሙሉ በሙሉ  እንዲታፈን ስምምነት ላይ ተደርሷል።  ፣ የአሜሪካ ድምጽ  እና የጀርመን ድምጽ የራዲዮ ጣቢያዎች ደግሞ በሚያቀርቡት ዝግጅት ይዘት አይነት አፈና እንዲካሄድባቸው ሲወሰን አሁንም ድረስ ስርአቱን የሚጻረሩ ድረጎች ሙሉ በሙሉ እንደታፈኑ ይገኛሉ።
ኢሳት ድረገጹ ቢታፈንበትም ራዲዮ እና ቴሌቪዥኑ ካለፉት 5 ወራት ጀምሮ ያለ ምንም ችግር እየተላለፈ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ የዲሽ አቅጣቻውን በየጊዜው በመቀያየር ኢሳትን በመከታተል ላይ ይገኛል። አንድንድ ባለስልጣናትም ኢሳትን እየተከታተሉ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ መጀመራቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በተመሳሳይ ዜናም መንግስት በፊስ ቡክ እየደረሰበት ያለውን ውግዘት እና የለውጥ ማእበል ለመግታት ‹‹ ሬሳው ›› ሲል ስም የሰጠውን የአፈና ቴክኖለጅ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ ሙከራው ተግባራዊ ከሆነ ሙሉ ለሙሉ የፊስ ቡክ ግንኙነቶችን ለመገደብ እድል እንደሚያገኝ የደረሰን መረጃ ያሳያል። ካለፈው ወር ጀምሮ ስራውን ለማስጀመር የተደረገው ተደጋጋሚ ጥረት አለመሳካቱ ታውቋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ESAT Daily News Amsterdam May 30, 2013 Ethiopia


የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ | Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy

የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓም ተጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከተካሄደ በኋላ ህዝባዊ ትግሉን ወደፊት የሚያራምዱ ዉሳኔዎችን ካሳለፈ በኋለ ባለፈዉ ሰኞ ምሽት እጅግ በጣም በደመቀ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ይህ የንቅናቄዉ አራተኛ መደበኛ ጉባኤ ንቅናቄዉ ባለፉት ሁለት አመታት የተጓዘባቸዉን መንገዶች፤ ያቀዳቸዉን ስራዎችና የዕቅዱን አፈጻጸም በጥልቀትና በስፋት በመዳሰስ መጪዉ የትግል ወቅት የሚጠይቀዉን የመስዋዕትነት ደረጃ ከወዲሁ ተመልክቶ ዘረኛዉን የወያኔ አገዘዝ በማስወገድ የኢትዮጵያን ህዝብ የፍትህና የዲሞክራሲ ጥማት ሊያረኩ ይችላሉ ብሎ ያመነባቸዉን አበይት ዉሳኔዎች አሳልፏል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የንቅናቄዉን የአለፉት አምስት አመታት ጉዞና በዚህ በአራተኛዉ ጉበኤ ላይ የስልጣን ዘመናቸዉን የጨረሱት የንቅናቄዉ ምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ዕቅድና የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ በጉባኤዉ ላይ አዲስ ለተመረጡ የአመራር አባላት ንቅናቄዉ የታሰበበትን ግብ እንዳይመታ አንቀዉ የያዙትን እንቅፋቶች እንዲያስወግድና እንዲሁም የንቅነቁዉ ጥንካሬ በታየባቸዉ መስኮች አቅሙን አጣናክሮ በይበልጥ በመስራት የኢትዮጵያ ህዝብ ከንቅናቄዉ የሚጠብቀዉን የታሪክ አደራ እንዲወጣ አሳስቧል። በጉባኤዉ ወቅት አባላት ያደረጉት አመራሩን የመንቀፍ፤አቅጣጫ የማሳየት፤ ሀሳብ የማመንጨትና በአጠቃላይ በእያንዳንዱ የጉባአዉ ስብሰባ ላይ ባሳዩት ንቁ ተሳትፎ ንቅናቄዉ በህዝባዊ አመጽና እምቢተኝነት ዘርፎች ብቻ ሳይሆን በዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍም እያደገ መምጣቱን አሳይተዋል።
የግንቦት ሰባት አራተኛ መደበኛ ጉባኤ የምክር ቤትና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፤ ኦዲትና ቁጥጥር ኮሚቴ እንዲሁም የስነ ስርአትና የግልግል ኮሚቴ ሪፖርቶችን አዳምጦ ሰፊና ጥልቅ ዉይይት ካካሄደ በኋላ ሪፖርቶቹን አጽድቋል። ከዚህ በተጨማሪ የንቅናቄዉን እስትራቴጂና ይህንኑ እስትራቴጂ ተሸክሞ በተግባር የሚተረጉመዉን መዋቅር በአጽንኦት ከፈተሸ በኋላ በስትራቴጂዉ ላይ መጠነኛ ለዉጥ በማድረግ የእስትራቴጂዉንና የመዋቅር ለዉጡን ተቀብሎ አጽድቋል። ይህ የንቅናቁዉ አራተኛ ጉባዜ ንቅናቄዉን ላለፉት ሁለት አመታት የመሩትንና ያገለገሉትን የምክር ቤት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ የስነ ስርአትና ግልግልና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግኖ በማሰናበት በምትካቸዉ ንቅናቄዉን ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት የሚያገለግሉ የምክር ቤት አባላት፤ የኦዲትና ቁጥጥር፤ እንዲሁም የስነ ስርአትና ግልግል ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ ኢትዮጵያ ዛሬ የምትገኝበትን ሁኔታ በዝርዝር ከቃኘ በኋላ ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ዉጊያ የተያያዘዉ አገር ዉስጥና በዉጭ አገሮችም ስለሆነ ወያኔን በእነዚህ ሁለት የትግል መስኮች እንደአመጣጡ ከገጠምነዉ የሚሸነፍ ድርጅት መሆኑን ሙሉ በሙሉ በመቀበል አባላቱ ባሉበት ቦታ ሁሉ የሚሰሩት ስራ ወያኔን በማስወገድ ላይ እንዲያተኩር አሳስቧል። ከአለም ዙሪያ ከተለያዩ አገሮች የመጡ የግንቦት ሰባት አባላትን ያሰባሰበዉ አራተኛዉ የግንቦት ሰባት መደበኛ ጉባኤ የትግል ቃል ኪዳን የታደሰበት፤የመስዋዕትነት ዝግጅት የታየበትና አባላት የትግልና የስራ ልምድ የተላዋወጡበት ከምን ግዜዉም ባላይ የተሳካና የተዋጣለት ጉባኤ ነበር። በመጨረሻ ጉባኤዉ የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አራተኛ ጉባኤ ለአባላቱና በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ የትግል ጥሪ በማስተላለፍ ደማቅ በሆነ ስነሰርአት ተፍጽሟል።
የግንቦት ሰባት የፍትህ ፤ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ
የግንቦት ሰባት አራተኛ ጉባኤ አቋም መግለጫ | Official Site for Ginbot 7 Movement for Justice, Freedom and Democracy
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
H.I.M. Haile Selassie and bronze statue of Ghanaian President Kwame Nkrumah
ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ: ፕሬዚደንት ንኩሩማ ሃዉልት
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (ኦ ኤ ዩ) የአፍሪካ ሕብረት (ኤ ዩ በየአፍሪካ አንድነትን የተካው) ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ከተማ  የወርቅ ኢዩቤልዩውን በማክበር ላይ ነው፡፡ በሜይ 1963 አፍሪካ አንድነት ሲመሰረት፤የጋናው ፕሬዜዳንት ክዋሚ ንኩርማ የመዝጊያ ንግግሩን የደመደመበት በተለይ በእድገት ላይ ያለችውንና ተቀኚ የነበሩትን የአፍሪካ ሃገራት ወደ ነጻነት ለመራችው ኢትዮጵያ ለክብሯ በመረጠውና ባዘጋጀው ግጥሙ ነበር፡፡ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴን አስመልክቶ ንኩሩማ  ሲናገር: ‹‹ግርማዊ ሆይ! በጓደኞቼና በራሴ ስም የሚቀረኝ ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ በተለይም ለግረማዊነትዎ ያለኝን አክብሮት በመግለጽ በዚህች ታሪካዊ ሃገር ባደረግነው ቆይታ የተቸረንን አቀባበልና መስተንግዶ ሳላመሰግን ማለፍ አይቻለኝም፡፡ ንኩሩማህ ዘወትር ባነበብኩት ጊዜ ትውስታ የሚያጭርብኝን ይህን የግጥሙን ስንኝ አሰማ፡፡  የራሱ የንኩሩማህ ቃላት እነዚህ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ብሩህ አንቁ
ከለምለሞቹ ተራሮች መሃል
የጨለመባቸውን በነጻነት ጎዳና ስታጓጉዝ
የአባይ ወንዝ አናት
ኢትዮጵያ ትነሳለች!
ኢትዮጵያ የብልሆች ምድር
ኢትዮጵያ፤ የቀደምት አፍሪካ ሕግጋት ማሕደር
ለምለም የእውቀት ገበታ
የእኛ አፍሪካ የባህሏችን  አለኝታ
ብልኋ ኢትዮጵያ ትነሳለች፤ ገና
ደምቃ በሙሉ ክብር
አቤት የአፍሪካ ተስፋ
መዳረሻዋ  እድል
በ2011 በአፍሪካ ሕብረት ግቢውስጥ የግ ቀ.ኃ.ሥ. ሃውልት እንዲቆም ሃሳቡ ሲቀርብ፤የኢትዮጵያ ‹‹ታላቁና ባለራዕዩ መሪ›› በመቃወምና ኢትዮጵያዊነቱን በመርሳትና በመካድ  ሲናገር ምንጊዜም ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ስናነሳ የሚታወሰን ክዋሚ ንኩሩማ ነው፡፡ ይህን ለመቀበል መቸገር አሳፋሪ ነው የሚሆነው›› በማለት የራሱን አሳፋሪ ክህደት ፈጸመ፡፡የከሰለ ልብ ባለቤት መሆን እንዴት ያሳፍራል! ሃፍረተ ቢስነት እንዴት ያሳፍራል! ቀደምት የአፍሪካ እንድነትን ምስረታና ተግባራዊነት ያረጋገጠን መሃንዲስ እውነታ መካድስ እንዴት ያለ አሳፋሪ ተግባር ነው፡፡የማይቻለውንና የማይሞከረውን የሁለት ጎራ ፍጥጫ፤ የ “ሞኖሮቪያ”ንና የ “ካዛ ብላንካን” ቡድናዊ መራራቅን አቀራርቦና አስማምቶ፤ አስታርቆና አዋህዶ የአፍሪካ አንድነትን ምስረታ እውን ስለመደረጉ ታሪክ የግርማዊ ቀ ኃ ሥን ውታ ጨርሶ የማይዘነጋው ነው፡፡ የአፍሪካ እንድነትን እውን ለማድረግ ያለመሰልቸት በትጋት ጥረዋል፡፡የአፍሪካ አንድነትን ለመመስረትም ስለ ፓን አፍሪካኖዝምም ለአፍሪካ ምሉእ ነጻነትም ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉና አሁን ለደረሰበትም ደረጃ ተጠቃሽና ባለውለታነታቸው የማይዘነጋ ነው፡፡
….የወደፊቷን የአፍሪካን ራዕይ ከነጻነት አኳያ ብቻ ሳይሆን በአንድነታችንም አኳያ ነው የምናየው፡፡ይህን አዲስ ትግል በማወቅ ካለፈው ባገኘነው ውጤት መበረታታትና ጥንካሬ ተስፋ እናደርጋለን፡፡በመሃላችን ልዩነት እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ አፍሪካውያን የተለያየ ባህል ባለሃብቶች ነን፤ልዩ ተሰጥኦና ልምዶች ያሉን ነን፡፡ ያም ሆኖ ሰዎች በበርካታ የሚያለያያቸው ሁኔታ ቢኖረንም በመግባባትና በመተሳሰብ አንድነት ማምጣትም እንደምንችል እንገነዘባለን፡፡… ታሪክ እንደሚያስተምረንና እንደሚያስታውሰን አንድነት ሃይል መሆኑን፤በመገንዘብ ግባችንን በማስቀደም፤ለጣምራ ግባችን የተባበረ ሃይላችንን ለዚሁ በማዋል ለዕውነተኛው የአፍሪካ ወንድማማችነት አንድነት ልንቆም ግድ ነው፡፡ …እንደ ነጻ ሰብአዊ ፍጡራን ጥረታችን አዲስ ግንኙነት ለመፍጠር መቆም ይገባናል፡፡በራሳችን መተማመንን፤ግባችን በማድረግ እኩልነትን ከሌሎች በእኩልነት ላይ መሰረት ካደረጉ ጋር ሁሉ አንድ ልንሆን ተገቢ ነው………
በግንባር ቀደም የአፍሪካ አንድነት አመሰራረት ላይ የምስረታውን አባቶች በምቃኝበት ወቅት፤ ለግላቸው የመዳብ ሃውልት ይቁምላቸው በሚል ሙግት ለመግጠም አይደለም፡፡እኔን አጅግ ያሳዘነኝ፤እራሳቸውን በከለላ ውስጥ እሰገብተው፤ እራሳቸውን መሆን ስለሚቸግራቸው፤ አጋጣሚውን በመጠቀም፤ታሪክን በማወላገድና መሰረቱን በማሳት፤ጭፍን ‹‹ራዕይ›› አለን የሚሉት በአፍሪካ መስራች አባቶች ስምና ተግባር ተከልለው፤(ይልቁንስ በራሳቸው ስምና ማንነት መቆም ባለመቻላቸው) የኢትዮጵያን የኖረና የዘመናት መታወቂያ ለማፈራረስ የቆመውንና የቆሙለትን ትልማቸውን ለማሳካት መጣራቸው ነው፡፡ ታሪክ ስለሥልጣንና ማንነት ቢሆን ኖሮ ቀ ኃ ሥን ማንም ቀድሞ አይገኝም፡፡ ቀ ኃ ሥ ከማንም የአፍሪካ መሪ የላቀ አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በዘመኑ የአፍሪካ አንድነትን ከመሰረቱት አቻ መሪዎች ‹‹የአፍሪካ አንድነት አባት›› ተብለው በ1972 ዓም በተካሄደው 9ኛው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ላይ በይፋ ተመርጠዋል፡፡ ቀደም ሲል በምስረታው ወቅት በ1963 ዓም የመጀመርያው የአፍሪካ አንድነት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዳግመኛም በ1966 ድጋሚ ሊቀመንበር ሆነው እንዲመሩ ዳግም ተመርጠው በሁለት ዘመናት በሊቀመንበርነት ተመርጠዋል ፡፡ የአፍሪካን ኮሎኒያሊዝም ቅስም ለመስበርና ከአፍሪካ ምድር ጨርሶ እንዲጠፋ ለማድረግ ግንባር ቀደሙ ናቸው፡፡ከኋላ የመጣ አይን አወጣ እንዲሉ የማንም ጭራ ነስናሽ ጥብቅና የሚሹ አይደሉም ይሄው ጭራ ነስናሽ የራሱን ሃውልት ለማቆም የነግ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገችው ይቺ በንኩሩማህ ስም የተቸረች ሙስናዊ አካሄድ የትም አታደርስም፡፡
ታሪክ በርካታ እንቆቅልሾች አሉት፡፡ምናልባት በሃውልቱ መቆም ወቅት ንከሩማህ ወይ ሞት በማለት አጥበቀው ሲሞግቱ የነበሩ ስለፓን አፍሪካኒዝም በተነሳ ቁጥር መታወሱን ብቻ ያቀነቀኑት ንክሩማህ ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ስር የሰደደ ፍቅርና አክብሮት ቢያውቁ ኖሮ በመቃብራቸው ውስጥ መንደፋደፋቸው አይቀርም፡፡ንክሩማህ በልቡ ውስጥ ለኢትዮጵያ የተለያ ጓዳ ነበረው፡፡ምንም እንኳን ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ቀደምት ቢሆንም ኢትዮጵያን ደግሞ እንደ አፍሪካ አንጸባራቂ የጸረ ኮሎኒያሊዝም ብርሃን በመመሰል ከቅኝ ገዢዎች ጋር ሲያደርጉ በነበረው ትግል ወቅት የዚህች የነጻ ኢትዮጵያ ኮከብነት መሪያቸው እንደነበረ ያስታውሳሉ፡፡ከዚሁ አኳያ የኢትዮጵያን የጸረ ኮሎኒያሊዝምን ጥቃት በመታገል ነጻነቷን ጠብቃ መቆየቷ የሚያኮራ መሆኑን በማስገንዘብ፤የአፍሪካ አንድነት አሽከርካሪ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡
እርግጥ ንክሩማህ ስለ ፓን አፍሪካኒዝም ንቁ ተሟጋች መሆናቸው ባይካድም፤ ለፓን አፍሪካኒዝም ግን አንድም ግጥም አላበረከተም፡፡ አፍሪካ ስለአፍሪካ ብሩህ እሳቤ ያለው ቢሆንም ለአፍሪካ ግጥም አላሰፈረም፡፡ ንክሩማህ ፓን አፍሪካኒዝምንና አፍሪካ ይወድ ነበር፤ለኢትዮጵያ ግን የበረታ ፍቅር ነበረው፡፡ለዚህም ነው በምስረታው ወቅት በመዝጊያው ላይ ባደረገው ንግግሩ ላይ ስለኢትዮጵያ ግጥም ጀባ አለ፡፡ ከዓለም መሪዎች መሃል ለኢትዮጵያ ታሪካዊነትና ግንባር ቀደምትነት፤ ስለ ሕዝቦቿ መስተንግዶ የጻፈ ብቸኛ መሪ ንክሩማ ነው፡፡
ቀ ኃ ሥ ወቅቱ ሲመጣ ሃውልታቸው እንደሚገነባ አያጠራርም ምክንያቱም ‹‹እውነት በርብራብ ስር ወድቃ አትቀርም፤ ቅጥፈትም በዙፋን ላይ ተኮፍሶ አይኖርምና››::
ወደኋላ መለስ ብለን ስናስታውስ፤ ንክሩማህ የበረታ ፓን አፍሪካኒስት ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ‹‹ትንቢተኛም›› ነበር፡፡ ንክሩማህ ማየት የተሳናቸው ባለራዕዮች ኢትዮጵያን ወደ ዘር ፖለቲካ አረንቋ ውስጥ ከመድፈቃቸው አስቀድሞ ኢትዮጵያ ገና እንደምትልቅ ያወቀ ነበር፡፡ንክሩማሕ የኢትዮጵያን ገኖ መዝለቅ ሃፍረት ለባሾች ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ …. ከማለታቸው በፊትና ከመቀላመዳቸው አስቀድሞ ያውቅ ነበር፡፡ንክሩማህ ባለጊዜ አስመሳዮች ለራሳቸው ስም ለመገንባት ጉብ ቂጥ ከማለታቸውና ‹‹ኒዮሊቤራሊዝም›› ከመዝፈናቸውና ደሟን ጨርሰው እንባዋን ከመምጠታቸው አስቀድሞ ስለማንኛውም በዝባዢና አስመሳይ ለቀስተኛ ጠንቅቆ ያውቅ ነበር፡፡
በእርግጥም የንክሩማህ ግጥም ‹‹ትንቢት›› ነበር፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ትነሳለች እንደ ንጋት ጸሃይ በርታ እንደ ውድቅት ጨረቃ ደምቃ ኢትዮጵያ ትነሳለች! ከምር ገና በላይዋ ላይ ያጠላውን ጥቀርሻ ዲክታተርሺፕ አስወግዳ ት ትነሳለች፡፡ኢዮጵያ ካጠመዳት ክፉ ደዌ ተላቃ እንደገና እንደ ብርቅዬ አልማዝ ታበራለች! ከዘረኝነትና ሃይማኖት ክፍያ ትላቀቃለች፡፡ ኢትዮጵያ ከወረራት የመከራ ከበባ ተላቃ፤ ልጆችዋን ካስመረራቸው ክፉ አሳቢና እኩይ ምርጊት አላቃ እጆችዋን ከተበተባት የዘርና የጎሳ ፖለቲካ፤ ከችግርና ከመከራ፤ ከእልቂትና ከደዌ ነጻ አድርጋ ልጆችዋን በአንድነት ታቅፋለች፡፡  ኣምላክም መልሶ ያቅፋታል::
ንክሩማህ እውነተኛው የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡መጤዎቹ ኢትዮጵያ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ያላት ቢሉም ንክሩማ ግና አስቀድሞ ሃሰት በማለት ኢትዮጵያማ የሰው ዘር መገኛ ማዕከል ነች ብሏቸዋል፡፡ ኢትዮጵያን በፈላጭ ቆራጭነት ሊገዙና ሕዝቦቿንም ለመራና ሰቆቃ ሲዳርጉ ንክሩማ ግን አስቀድሞ ‹‹እምቢኝ! ኢትዮጵያማ የአፍሪካ አንጸባራቂ ሉል ናት፡፡ ማንጸባረቅ ማብራት አለባት! ልቀቋት ትግነንና ታብራ ብሏል፡ ንክሩማ ‹‹ ኢተዮጵያ የብልሆች ሃገር ናት፤አባይን የጦር መንስኤ ሊያደርጉ ሲዶልቱ ንክሩማ እምቢኝ! ‹‹ኢትዮጵያ የአባይ መመንጫ ናት›› አባይ ደሞ የህይወትን ስጦታ ለአፍሪካ ያድላል ብሏቸዋል፡፡ መንፈሳችንን ለማጉደፍና ለማጣጣል ሲሸርቡና ለመከራና ለስቃይ ሲያዘጋጁን፤ ንክሩማ እምቢኝ!‹‹ኢትዮጵያማ የአፍሪካ ራዕይ ተስፋ ነች›› አላቸው፡፡ ንክሩማ የጋና ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያም ልጅ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በተስፋ አስቆራጭ ትቢያዎች ልንቆሽሽ መስሎ ሲሰማን በንክሩማ ትንቢታዊ አባባል ብርታት እናግኝ፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ገና ትትነሳለች›› ስለዚህም በግርማዊ ቀ ኃ ሥላሴና በንክሩማ  መሃል ውድድር የለም፡፡ ሁለቱም የኢትዮጵያ የተከበሩ ልጆች ናቸውና:: ንክሩማን ማክበር ማለት ቀ ኃ ሥላሴን ማክበር ነው፡፡ የሜይ 1963ቱን የንክሩማን ግጥም ሳነብ፤ ቀ ኃ ሥላሴ በኦክቶበር 1963 በተባበሩት መንግሥታት ስብሰባ ላይ ያደረጉት ንግግር ትዝ ይለኛል፡፡ በዚያ ንግግራቸው ቀ ኃ ሥላሴ ለአፍሪካን ፓን አፍሪካኒዝም ጥብቅና ከመቆማቸውም ባሻገር የአፍሪካን  ነጻነት ጠብቆና አክብሮ ለማቆየት የሚያስፈልገውን አይዲዮሎጂ በሚገባ አስገንዝበው ነበር፡፡
…አንዱን ዘር ከፍተኛ ሌላውን ዝቅተኛ አድርጎ የሚያሳየው ፍልስፍና ጨርሶ እስካልተወገደ ድረስ፤ አንደኛ ዜጋና ሁለተኛ ዜጋ የሚለው ደረጃ እስካልፈረሰ ድረስ፤ የአንድ ፍጡር ቀለም ከዓይኖቻችን ቀለም የተለየ ትርጉም እንደሌለው እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ሁሉም ሰብአዊ መብቶች ከዘርና ከጎሳ ከቀለም ልዩነት ባሻገር ለሁሉም እኩል እስካልሆኑ ድረስ፤ በተስፋነት ብቻ የሚታሰቡ እንጂ አንዳችም እርባና አይኖራቸውም… እኛ አፍሪካዊያን አህጉራችን ከዳር እስከዳር ሰላም እስክትሆን ድረስ አስፈላጊ ከሆነ ትግላችንን አናቆምም፡፡ ደግሞም ድልን በእጃችን እንደምናደርግ ጥርጥር የለንም፡፡ መልካምነት እኩይነትን እንደሚረታው ስለምንገነዘብ ድል እንደማይርቀን እርግጠኞች ነን፡፡
ቦብ ማረሊም እነዚህን ቃላቶች ለዜማው ‹‹ዋር›› (ጦርነት) ለሚለው የአፍሪካ የትግል ዜማ የሆነውን  ሙዚቃውን አጅቦበታል፡፡(ምናለ አንድ ባለሙያስ የንክሩማን ግጥም ወደ ዜማ ቢለውጠው… ኢትዮጵያ ትትነሳለች፤ ትገናለች…  ታበራለች…. ወደ ላይ ትወጣለች::)
በምትገነዋ ኢትዮጵያ አንድን ጎሳ፤ ሃይማኖት፤ቋንቋ፤ጾታ ከሌላው አብልጦ የሚያጎላ፤ ፍልስፍና አይኖርም፡፡ በኢትዮጵያ አንደኛ ደረጃ ዜጋና ሁለ፤ተኛ ደረጃ ዜጋ አይኖርም፡፡በነገዋ ገናና ኢትዮጵያ ዘር ጎሳ፤ ሃይሞኖት፤ወረዳ፤ጾታ፤ሁሉ ከዐይኖቻችን ቀለሞች መለያየት ያለፈ ትረጉም አይኖራቸውም፡፡ በምትገነዋ ኢትዮጵያ ሁሉም እኩል የሰብአዊ መበት ባለቤት ይሆናል፡፡
ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ  ሕብረት
ወይ ጉድ! የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ስለ አፍሪካ አንድነት/አፍሪካ ሕብረት አስተያየት ማስፈር ልብ ሰባሪ ጉዳይ ነው፡፡ በ2013 በዓለም ካሉት 47ሃገራት እድገት ከማያሳዩት ሃገራት መሃል 36ቱ በአፍሪካ ይገኛሉ፡፡ በአንድ ወቅት የታንዛኒያ መሪ የነበሩት ጁሊየስ ኔሬሬ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ‹‹የመሪዎች የወሬ ማሕበር›› በማለት ጠቅሰውት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ‹‹የፈላጭ ቆራጭ ጋጠወጥ ራስ ወዳድ መሪዎች ክበብ›› ይሉታል፡፡ጋናዊው ታዋቂ ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴ ‹‹እባካችሁ ስለ አፍሪካ አንድነት ድርጅት ማውራት ይብቃን፡፡ በአህጉራችን ካሉት ድርጅቶች ሁሉ አዘቅዝቆ የሚሄድና እርባና ቢስ የሆነ ድርጅት ነው፡፡‹‹ዴሞክራሲን›› እንኳን በሚገባ ሊተረጉም ያልቻለ ድርጅት ነው፡፡ የራሱ የሆነ ወጥነት ያለው ተግባር ጨርሶ የሌለው ነው›› ይለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕበረት ዋና መስሪያ ቤት በቻይና መንግሥት ምጽዋት በ200 ሚሊዮን ዶላር ተሰራ በተባለና የቻይና ስጦታ “ለታዳጊዋ” አፍሪካ በተበረከተ ጊዜ ቅሬታዬን አስቀምጬ ነበር፡፡ የቻይና የግንባታ ኩባንያ ስራውን በአጠቃላይ ከቻይና በተገኘ ቁሳቁስና ቻይናዊያን ዜጎች ሰራተኞች ገነባው ሲባልና አስፈላጊውን ቁሳቁስ ሁሉ ያሟላውም ያው ቻይና ኩባንያ ነው ሲባልና ወንበርና ጠረጴዛም ሳይቀር ከቻይና ተጓጓዘ መባሉም ክፉኛ አሳዝኖኝእንደነበር ገልጫለሁ፡፡ በስጦታው ርክክብ ወቅትም የአፍሪካ ‹‹ሃፍረተ ቢስ መሪዎች›› ተርታ ገብተው እንደ ውሃ ወረፍተኛ ለቻይና የምስጋና ውርጅብኝ ሲያጎርፉ  ‹‹የአፍሪካ ትንሳኤ… የአፍሪካ ሬኔሳንስ ተጀመረ ለማስቀጠልም መንገዱን አግኝተናል በማለት አሸሸ ገዳሜ ሲሉ ነበር፡፡››
አፍሪካ አልተነሳችም አልኩ፡፡ አፍሪካ ለልመና ተዳርጋለች፡፡‹‹የቻይና ትንሳኤ በአፍሪካ ተጀምሯል›› በአዲስ አበባ የተገተረው አዲሱ የአፍሪካ ሕብረት ግንብ የአፍሪካ የሃፈረት ግንብ  እንጂ የአፍሪካ ኩራት ግንብ አይደለም፡፡ የአፍሪካ መሪዎች በአንድነት ለአፍሪካ ሚሆን ቋሚ ቢሮ ለመገንባት አቅሙን ካጡ፤ ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚሆነውን መስራት ከተሳናቸው ያሁኑን ግንብ ‹‹የአፍሪካ ምጽዋተኞች አንድነት አዳራሽ›› ከማለት አላልፍም:: የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት እና ሰብአዊ መብት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/የአፍሪካ ሕብረት በአፍሪካ የፖለቲካ፤ የኤኮኖሚ እና የሶሻል ግንኚነቶችንና ነጻነትን ከማጠናከርና ተግባራዊ በማድረግ ወደ ልማት አቅጣጫውን ከማራመዱ አስቀድሞ ማከናወን ያለበት ሰብአዊ መብትን ነው፡፡ የአፍሪካን  ልማት  ለማከናወንም ሆነ አቅዶ ወደ ግብ ለማድረስ የሰብአዊ መብት መከበር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ሕዝቦች በነጋ በጠባ ለመከራና ስቃይ እየተዳረጉና የግፍ ኑሮ፤ የባርነት ቀንበር ተሸክመውጀርባቸው በተደራራቢ ችግር ጎብጦ ልማትን አመጣለሁ ብሎ ሩጫ ለመውደቅና ለከፋ መከራ ለመዳረግ መጣር ብቻ ነው፡፡
የአፍሪካ አንድነት ጸረ ኮሎኒያሊዝም፤ኒዮ ኮሎኒያሊዝም ጸረ ጸረ ጸረ ብሎ የሚደረድራቸው ማለቂያ የሌላቸው ጸረዎች በችግርና በመከራ ላሉ ሕዝቦች አንዳችም ጠቀሜታ የሌላቸው ልፈፋዎች ብቻ ናቸው፡፡ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ጤት አልባ ከዚያም አልፎ ዋጋ ቢስ መሆኑን ለሰብአዊ መብት ካለው አመለካከትና ከከወነው ተግባር ነው፡፡ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ክፍሎች ጦርነት የየቀናት ክስተት ነው፡፡ሰዎች በየቦታው ሲተላለቁ የአፍሪካ አንድነት እጁን አጣጥፎ ከመመልከት ውጪ አንዳችም እርምጃ አልወሰደም፡፡ የአፍሪካ ጉልበተኛና ፈላጭ ቆራጭ ገዢዎች ከውጪ ወራሪ በከፋ መልኩ ሕዝቦችን ሲጨፈጭፉ ለስደት ሲዳርጉ በግፍ ከመኖሪያቸው ሲያፈናቅሉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አይኑን ጨፍኖ፤ ጆሮውን ደፍኖ፤አፉን ለጉሞ የድርጊቱ ተባባሪ መሆንን የመረጠ ነው፡፡ ለሕዝቦች እልቂት ደንታ የሌ፤ልው ድርጅት/ ሕብረት፡፡ የሩዋንዳ እልቂት በሚሊን የሚቆጠሩትን ንጹሃን ዜጎች በሞት ሲቀጥፍ የአፍሪካ አንድነት ቢሮውን ዘግቶ አርቲ ቡርቲ ከማራገብ ውጪ ምንም ያደረገው አልነበረም፡፡ ሌላው ቀርቶ የአፍሪካ አንድነት ግድያውን ‹‹ጄኖሳይድ›› ለማለት እንኳን ድፍረቱና ወኔው አልነበረውም፡፡!
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት/ የአፍሪካ ሕብረት ሶማልያ ለሁለት አሰርት ዓመታት በመበታተን ላይ ሳለች፤ የጎሳ መሪዎች ተቀራምተዋት ለጥፋት ሲዳርጓት እንኳን መድረስ ቀርቶ ከሩቅ ሆኖም ማስጠንቀቂያም ሆነ ማስፈራሪያ አልሰነዘረም፡፡ ለተፈጠረው ችግር ሌሎች ሃገራት ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ በሚያመቻቸው መንገድ ጣልቃ ገብተው ሲያማትሩ የአፍሪካ አንድነት በቂ ጦር እንኳን ለመላክና ሕዝቡን ከመከራ ለመታደግ አልሞከረም፡፡ በኮት ዲቭዋር የተፈጠረውን ችግር የፈረንሳይ ወታደሮች ገብተው ሲፈነጩበት የአፍሪካ እንደነት በስፋራው ቀርቶ በአካባቢውም አልደረሰም፡፡ በማሊም የተፈጠረውን ሽብር ለማስታገስና ስርአት ላመስያዝ የፈረንሳይ 5000 ወታደሮች ሲዘልቁ የአፍሪካ አንድነት ከጠቅላይ ቢሮው ንቅንቅም አላለም፡፡ በኢትዮጵያም የምርጫ  በጠራራ ጸሃይ ሲሰረቅና ተሸናፊው አሸናፊ ሆኖ ሲወጣ በዝምባብዌ፤በኬንያ፤ በዩጋንዳ ተመሳሳይ የምርጫ ውጤት ዘረፋ ሲካሄድ የአፍሪካ አንድነት በገለልተኛነት ከዳር ቆሞ ከተመልካችነት አላለፈም፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሰብአዊ መብትን ጥሰት በተመለከተ፤ ወንጀለኞችን መደገፍን  ሙያ ብሎ ይዞታል፡፡ የሱዳኑ ኦማር አል በሺር በሰብአዊ መብት ጥሰትና በጦር ወንጀለኛነት በግፍ ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከሰው መያዣ ሰነድ ሲተላለፍባቸው ‹‹የአፍሪካ ሕብረት አባል ሃገራት በሮም የተፈረመውን የፍርድ ቤቱን ስምምነት አናከብርም በማለት የሱዳኑን አልበሺርን አሳልፈን አንሰጥም አቋም ያዙ›› ይህ ደግሞ ነግ በኔ በሚል ስጋትና አስቀድሞ መንገድ ለመዝጋት ሲሉ ተመሳሳይ ወንጀለኛ መሪዎች የወሰዱት አቋም ነበር፡፡ በዚህም የአፍሪካ ሕብረት ተግባሩን መወጣት ባለመቻሉና ፍላጎትም በማጣቱ አይ ሲ ሲ ዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ጣልቃ መግባቱ አስፈላጊ ሆነ፡፡ ከ2011 አንስቶ በሰባት የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ይሄው ፍርድ ቤት የማጣርያ ምርመራውን በማካሄድ ላይ ነው፡፡
የአፍሪካ ሕብረት የሌለው ቢሮ ያላቋቋመው የመብት ማስከበርያ ጽ/ቤት የለም ግን አንዳቸውም ለተግባር አልበቁም፡፡ የአፍረካ ሕብረት የሰብአዊ መብት ቢሮ፤ የአፍሪካ ሕብረት የልጆች መብት፤ የሴቶች መብት፤ በማለት በርካታ ኣዋጅ አውጥቷል ቢሮም አቋቁሟል፡፡ የአፍሪካ ሕብረት የፖለቲካ ቢሮም አለው፡፡ የዚህም ቢሮ ተግባሩ ሰብአዊ መብትን ማስከበር፤ የዴሞክራሲ ስርአትን ትግበራ ማረጋገጥ፤ምርጫዎችን በአግባቡ ተካሂደው የህዝብ ፍላጎት ማሟላት ቢሆኑም አንዱንም አላከናወነም፡፡ በአባል ሃገራት ምርጫ ወቅት ዳጎስ ያለ ወጪ በመመደብ ታዛቢዎች ቢሊክም ታዛቢዎቹ ሆቴላቸውን ሳይለቁና ምርጫ ጣቢያዎችም ቢሆን እንደነገሩ ደረስ መለስ ከማለት አልፎ አንዳችም ውጤት ያለው ትዝብት አላከናወኑም፡፡ በየሄዱበት ሃገር ያለው ገዢ ፓርቲ የሚሰጠውን መግለጫ ደግፈው ተጋብዘውና ተሸልመው ከመመለስ ውጪ ምንም አላደረጉም:: በ2010 ነፍሳቸውን በተገቢው ቦታ ያኑረውና መለስ ዜናዊ 99.6 በመቶ ምርጫ አሸነፍኩ ሲል፤በቀድሞው የቦትስዋና ፐሬዜዳንት ማሲሬ ለታዛቢነት የተሰማራው ቡድን ምርጫው ፍትሃዊና ሰላማዊ ነበር፤ የምንግስት መዋቅርን መጠቀምና ሕገ ወጥ የሆነ ሂደትም መራጩንም ማስፈራራትና መስገደድም ያልነበረበት ምርጫ ነበር በማለት ማሲሬ ቀልማዳ ትዝብቱን ተፈራረመ፡፡ ሲደመድምም ምርጫው የአፍሪካን አንድነት የምርጫ ደንብና ስርአት ያሟላ፤ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት ያካተተ፤… የአፍሪካ ሕብረት ተቃዋሚዎች ከምርጫው አስቀድሞ ያሰሙትን ቅሬታ የሚያረጋገጥ አንዳችም ሁኔታ አልታየም፡፡ ክሱን ወይም ውንጀላውን የሚረጋግጥ አንዳችም ሁኔታ አላየንም በማለት ነበር፡፡
አፍሪካ ከመቼውም በከፋ መልኩ አሁን ተበታትናለች፡፡ፓን አፍሪካኒዝም አፈር ዲቤ በልቷል፤ እድሜ ለአፍሪካሕብረት፡፡አሁን በአፍሪካ ላይ በማንዣበብ ላይ ያለው አዲስ አየዲዮሎጂ ነው፡፡ የአፍሪካ ጨቋኝ ገዢዎች በድፍረትናበማን አለብኝነት የዘር ብሔርተኝነትን በስልጣን ለመቆየት አመቺ ስለሆናቸው በመንዛት ላይ ናቸው፡፡ የዘርማንነት፤ የዘር ጥራት፤የዘር መኖርያ፤ በሚል ሰበብ ሕዝብን መጨፍጨፍና ከራሳቸው ከገዢዎች ውጪ ያለውን ዘር በሚልያስቀመጡትን ሁሉ ለማጥፋትና ብቸኛ ዘር ሆነው ለመኖር እየገሰገሱ ነው፡፡
በኢትዮጵያም ‹‹የብሔር ፌዴራሊዝም›› በሚል ቆንጆ መጠቅለያ የተጀቦነ ፖለቲካዊ ሂደት እየተንደረደረነው፡፡ኢትዮጵያዊያን በማንነታቸው በትውልዳቸው በቀያቸው መገለልና መገፋት መፈናቀል እየደረሰባቸው ነው፡፡በክልልተደልድለው ያለፍላጎታቸው ስም ወጥቶላቸው ለጥቃት ተዘጋጅተዋል፡፡ ጥቂት የገዢው መደብ አባላት በድሎት እንዲኖሩናያለሃሳብ እንዲንደላቀቁ 80 ሚሊዮን ሕዝብ ለግፍ ተዳርጓል፡፡እንዳይናገር በሆዳም ካድሬዎችና ለጊዜው ገዢዎችእራሳቸውን በሸጡ አጎብዳጆች ተወጥሮ መከራ እየወረደበት ነው፡፡ ሆዳሙ ያዜማል ሆዳሙ ይገጥማል፤ ሆዳሙ ይጨፍራል፤ሆዳሙ ቅኔ ያፈሳል ሆዳሙ ያጨበጭባል ሆዳሙ ይደሰኩራል፤ ሆዳሙ ሆዱን ይሞላል ሕዝቡ ግን ለመከራና ስቃይተዳርጓል፡፡
ታላቁ የአፍሪካ ደራሲ ቺኒዋ አቼቤ  (Things Fall Apart) ለምንድን ነው በአፍሪካ ሁሉም ነገርየሚፈራርሰው በሚል መነሾ ጻፈ፡፡የኔ መለስ አጭር ነው፡፡ባለፈው የግናሽ ምእተ አመት ነጻነት የአፍሪካን ግፈኛገዢዎች ተጠያቂ የሚያደርግ ድርጅት ለመፍጠር ባለመቻሉ ነው እላለሁ፡፡ላለፉት 50 ዓመታት የአፍሪካ መሪዎችተጠያቂነትን አሻፈረን ብለዋል፡፡ የዚህ ተጠያቂ ሕዘቡ እንደሆነ ለማሳመን ጠረታቸው መጠን የለውም፡፡አፍሪካ ከቅኝገዢዎች በተተወለት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለው፡፡ሰበብ እየተደረገ ዘወትር በማያልቅ ጥሪ የሚጠቆመው፤ ነጮች፤ የቅኝገዢዎች ቅሪት፤ ካፒታሊዝም፤ ኢምፕሪያሊዝም፤ ኒዮ ሊቤራሊዝም፤ ግሎባላይዜሽን ነው መሸሻው፡፡ ….. የዓለምየገንዘብ ተቋም ነው፤የዓለም ባንክ ነው፤……የአህጉሩ ያለማደግና ያለመልማት ሰበቡ  የመኑስናው፤ የመልካምአስተዳደር እጦት ሁሉም በመጥፎና እርኩስ መንፈስ የመጡ እንጂ የአህጉሩ አይደሉም ማለት ይዳዳቸዋል፡፡ነገሮች ሁሉ በአፍሪካ ፍርስርሳቸው የሚወጣበት ሰበብ የአፍሪካ ‹‹መሪዎች›› የሕዝቦቻቸውን ሰብአዊ መብትባለማክበራቸው ነው፡፡የአቼቤን አባባል ለማጠናከር፤ አፍሪካ አሁን ያለችበት ሁኔታ ውስጥ ያለችበት መንስኤየአፍሪካ መሪዎች እንደመሪ ሊሆኑና ሊያደርጉ የሚገባቸውን የመሪነት ሚና መጫወት ባለመቻላቸው ነው፡፡ ‹‹ጥቂትየአፍሪካ መሪዎች የሕዝቦቻቸውን ክብርና ሰብአዊ መብት በአግባቡ ያከብራሉ፡፡ አፍሪካ መሪዎች ናቸው በሚባሉትገዢዎቿ እያደናቀፉ እየጣሏት እንዴትስ መነሳትና መግነን ትችላለች? ለመነሳት በሞከረች ቁጥር ያንን የመርገምትቦት ጫማቸውን ማጅራቷ ላይ አሳርፈው እንዳትነሳ፤ እንዳታድግ፤ እንዳትለማ ረግጠው ይዘዋት እንዴት ብላ ነውየምታድጋው? ያም ሆኖ ጊዜው ሲደርስ አፍሪካ ፍርስርሳቸው የወጡባት አፍሪካ ተሰባስበው አንድ የገነነች አፍሪካሆና ትነሳለች!ስለዚህም ለአፍሪካ አንድነት/ አፍሪካ ሕብረት 50ኛው ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ ለግ ቀ ኃ ሥላሴና ለክዋሚህንክሩማህ የማበረክተው ስንኝ
ኢትዮጵያ ከፍ በይ! የኢትዮጵያ ትንሳኤ! የአፍሪካ ትንሳኤ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንጸባራቂ ማዕድ ትነሳለች ትገናለች
ከፈላጭ ቆራጭ ስርአት ተላቃ
የግድበ አፍሪካ ምድር እንደሚበራው የበጋ የንጋት ፍንጣቂ
በአፍሪካ ምሽት ሰማይ እንደምትበራው የጨረቃ
ብርሃን አንቂ ኢትዮጵያ ትንሳኤዋ ያበራል ትገናለች::
ኢትዮጵያ ከራስ ደጀን ጉብታ ጫፍ ትንሳኤዋ ይታያል
እስከ ኪሊማንጃሮ ዘልቆ ይጠራል
ከፖለቲካው አረንቋ መታወቂያነት
እስከ ሀገራዊ ኩራት በልዩነት
ኢትዮጵያ አስከብራ የሁሉንም ማንነት ትነሳለች::
በአፍሪካ ምድር የነጻነት ብርሃኗን ትረጫለች
የሊቃውንት ሃገር ኢትዮጵያ ከመንደርተኛ አዋቂዎች በላይ ተንብያ
ህዝቦቿ ተሰባስበው ተዋህደው ተፋቅረውና ተግባብተው
ሰብአዊነትን ወግነው አንድነትን መቻቻልን አንግበው
ኢትዮጵያ ትነሳለች ትገናለች::
ኢትዮጵያ የነግህ የአፍሪካ ተስፋ
በትንሳኤዋ የረገጧትን የጨፈለቋትን  አልፋ
ቅጥፈታቸውን ጭካኔያቸውን ሙስናቸውን
ያን ያለፈ ዘመናቸውን ከነምኞታቸው ገንዛ በብረት ሳጥን
የሕግ የበላይነትን አስከብራ፤ኢትዮጵያ እንደ ጸሃይ ታበራለች::
በምድሯም ሰላም እስከ ዘልዓለሙ እንዲሰፍን ታደርጋለች
የኢትዮጵያ ትንሳኤ በማይደፈሩት ሃቀኛ ወጣቶቿ
ከፍ ትላለች ተደግፋና ተሞሽራ በልጆቿ
ኢትዮጵያ እስከማዕዜኑ ትገናለች
ለወጣቱ ትውልድም  የዘልአለም ቤቱ ትሆናለች::
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):