Friday, May 3, 2013

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ በነ አንዷለም አራጌ፣እስክንድር ነጋ በፍርድ ቤት ውሳኔ ስቅስቅ ብለው አነቡ !

ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ አነቡ !
በኢትዮጵያ እንባ እንግዳ ነገር ባለመሆኑ የዶክተሩን ማልቀስ ምን የተለየ ያደርገዋል የሚለኝ አይጠፋም፡፡ነጋሶ በጀርመን አገር የሞቀ ኑሮና የሚያስመካ መተዳደሪያ ነበራቸው፡፡ኢህአዴግ ይዟቸው ከመጣ በኋላም ወደ ቤተመንግስት አስገብቶ በፕሬዘዳንትነት ሰይሟቸዋል፡፡ህገ መንግስቱ ሲረቅም ነጋሶ ከአርቃቂዎቹ አንዱ ነበሩ፡፡እነዚህ ነገሮች ዶክተሩን በአጀብ ለማኖር ከበቂ በላይ ነበሩ፡፡ነገር ግን አንድ ማለዳ ነጋሶ መለስን‹‹መንግስቱ ኃይለማርያምን መሰልከኝ ››በማለት መናገራቸው እንደ ሃጢአት ተቆጥሮባቸው የቤተመንግስት ቆይታቸው ተቀጨ፡፡ከስንብቱ በኋላ የተቆረጠላቸውን ጡረታ እየተቀበሉ አንደበታቸውን በመሸበብ መኖር እንደሚችሉ የሚገባቸው ቢሆንም ነጋሶ በግላቸው ተወዳድረው የህዝብ ድምጽ ማግኘት በመቻላቸው ፓርላማ ገቡ፡፡በዚህ ያልተደሰተው ኢህአዴግ ጡረታቸውን በመንጠቅ የሰጣቸውን የመኖሪያ ቤት ነሳቸው፡፡ምንም ያጡት ነጋሶ ኦነግን ወይም አንዱን የብሄር ድርጅት ይቀላቀላሉ ተብለው ሲጠበቁ ህብረ ብሄራዊ የሆነውን አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲን ተቀላቀሉ፡፡
ነጋሶ እንባ አውጥተው በአደባባይ ያነቡት ዛሬ ስድስት ኪሎ በሚገኘው ሰበር ሰሚ ችሎት ነው፡፡የፖለቲካ፣የህሊና እና የነጻ ሚዲያው አባላት የተለያየ ኬዝ እየተጋገረባቸው ለእስራት ሲዳረጉ ነጋሶ በቻሉት መጠን ሁሉ በየፍርድ ቤቱ በመመላለስ ጉዳያቸውን ይከታተላሉ፡፡ድርጅታቸው አንድነት እስረኞችን ለማሰብ በየወሩ በሚያደርገው የመታሰቢያ ስነ ስርዓትም በመገኘት ነጋሶን የሚስተካከል አመራር የለም፡፡ዶክተሩ አንዷለም አራጌ፣እስክንድር ነጋ፣ናትናኤልና አበበ ቀስቶ የስር ፍርድ ቤት ያሳለፈባቸው ውሳኔ የህግ ጥሰት አለበት በማለት ለሰበር ሰሚ ይግባኝ ማለታቸው ተቀባይነት በማግኘቱ የተንዛዛውን የፍርድ ሂደት በትእግስት ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡የነጋሶ ተስፋ የተጋባባቸው የህሊና እስረኞቹ ቤተሰቦች፣ወዳጆችና ሌሎች በነጻ ተሰናብተዋል የሚል ቃል ለመስማት በመጓጓት የፍትህ አዳራሹን አጨናንቀዋል፡፡
ፍርደኞቹ ያቀረቡትን መከላከያ በንባብ በማስደመጥ የጀመሩት ዳኛ የአቃቤ ህግን ምላሽ በማስከትል ተገቢ ያሉትን ውሳኔ አስደምጠዋል፡፡የስር ፍርድ ቤት የወሰነውን አጽንተናል በማለት፡፡ይህንን መቋቋም የተሳናቸው ነጋሶ በተቀመጡበት ወንበር ሆነው ስቅስቅ ብለው አንብተዋል፡፡የእስክንድር ባለቤት ሰርካለም ድምጻን ከፍ አድርጋ ‹‹አንተ ንጽህ ነህ እንዲህ ስለተባለ ምንም ሊሰማህ አይገባም››በማለት ጋዜጠኛውን ለማጽናናት ራሷን ስታበረታ በብዙ መከራ ውስጥ ያለፉት ነጋሶ ግን እንባ ቀድሟቸዋል፡፡ወዳጆቼ ፕሬዘዳንት ሲያለቅስ ማየት ምን ስሜት ይፈጥርባችሁ ይሆን?

አለማቀፍ መንግስታት እና ድርጅቶች በእነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና አንዱአለም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዙ


ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በአል በሰላም አደረሳችሁ
ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በወጣቱ ፖለቲከኛ አንዱአለም አራጌ፣ በእውቁ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ በናትኤል መኮንን፣ ክንፈሚካኤል ደበበ ፣ ምትኩ ዳምጤ ፣ ዮሃንስ ተረፈ ፣ ሻምበል የሺዋስ ይሁን አለም እንዲሁም አንዱአለም አያሌው ላይ የስር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሳኔ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ   ሚያዚያ 24፣ 2005 ዓም   ማጽደቁ አለማቀፍ ውግዘት እያስከተለ ነው።
የአለማቀፉን የጸረሽብር ትግል የምትመራው እና የኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ተደርጋ የምትታው አሜሪካ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩዋ በኩል ውሳኔውን ከማውገዝና እስረኞቹ እንዲፈቱ ከመጠየቅ አልፋ የጸረ ሽብር ህጉ እንደገና እንዲታይ ጠይቃለች። ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቸው የጠቀሱት ቃል አቀባዩ መንግስታቸው የህሊና እስረኞቹ እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጫና እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
” በዛሬው ውሳኔ አሜሪካ በጣም አዝናለች። ውሳኔው በኢትዮጵያ ውስጥ መንግስትን በሚተቹት ላይ ሁሉ  በፍርድ ስም የሚሰጠው የፖለቲካ ውሳኔ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የሚያጠናክር ነው። አሜሪካም ጋዜጠኞቹ እንዲፈቱ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ ታደርጋለች ብለዋል ቃል አቀባዩ ።
የተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችም በህሊና እስረኞች ላይ የተላለፈውን ውሳኔ በማውገዝ መንግስት የአለማፍ ህግ ማክበሩን ለማሳየት የነበረውን አንድ እድል በድጋሜ አበላሸ ብለዋል። ፍሪድም ናው፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሲቪከስ፣ ወርልድ አልያንስ ፎር ሲትዝንስ ፓርቲሲፔሽን፣ ኮሚቴ ቱ ፍሪ እስክንድር ነጋ፣ ኢስት ኤንድ ሆርን ኦፍ አፍሪካ   ዘ ኤልክትሮኒክ ፍሮንቲየር ፋውንዴሽን ፣ ኢንግሊሽ ፔን ፣ ዘ ኢንተርናሽናል ፕሬስ ኢንስቲቲዩት፣ ዘ ኢንተርናሽናል ውሜንስ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፌንስ ኢንሸቲቭ፣ ዘ ናሽናል ፕሬስ ክለብ፣ ፔን አሜሪካን ሴንተር፣ ፔን ካናዳ፣ እንዲሁም ዘ ወርልድ አሶሴሽን ኦፍ ኒውስ ፔፐርስ ኤንድ ኒውስ ፐብሊሸርስ በጋራ ባወጡት መግለጫ በጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን የ18 አመት እስራት ከማውገዝ ባለፈ፣ መንግስት ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታየንና ሌሎችንም የህሊና እስረኞች ማሰሩ መንግስት የጸረ ሽብር ህጉን በመጠቀም ጠንካራ ትችቶችን የሚያቀርቡት ለመምቻነት ማዋሉ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያለውን ፍላጎት ጥያቄ ውስጥ የሚከት መሆኑን ገልጸዋል።

ውሳኔው ከተላለፈ በሁዋላም የተባበሩትን መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እስክንድር ነጋ እያንዳንዱዋን ቀን በእስር ቤት ባሳለፈ ቁጥር ፣ መንግስት የፖለቲካና ሲቪክ መብቶችን ለማክበር የገባውን ቃል ኪዳን እየጣሰ መሆኑን ሊያውቀው ይገባል ብሎአል።  

በሌላ በኩል ደግሞ 16 አመት የተፈረደበት ክንፈሚካኤል ደበበ ወላጅ እናት የ70 አመት አዛውንቷ ወ/ሮ ብጽዓት ሀይለጊዮርጊስ ልጃቸው ንጹህ እና ምንም ወንጀል የሰራ አለመሆኑን ገልጸው ፍርድ ቤቱ የ5 አመት የእስር ጊዜ ቅናሽ ማድረጉ እንዳላስደሰተቻው ገልጸዋል
ልጃቸው እውነቱን ይዞ በመታገሉ በጣም እንደሚኮሩ የገለጹት ወ/ሮ ብጽአት ፣ ልጃቸው አሸባሪ በመባሉ ማዘናቸውንም አልሸሸጉም

ESAT Daily News Amsterdam May 03, 2013 Ethiopia


Wednesday, May 1, 2013

የህማማት ማሰታወሻ (ከተመስገን ደሳለኝ )


እስክንድር ነጋን ልቀቅ!…
ይህ ሳምንት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ‹‹ሰሞነ ህማማት›› ተብሎ በፀሎትና በስግደት ይከበራል፡፡ ይህ የሆነው
ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ በሀሰት ተወንጅሎ ለስቅላት ተላልፎ የተሰጠበት፣ በሰው ልጅ ከሚደርስ
ስቃይ፣ መከራና ግርፋት ሁሉ የከፋውን የተቀበለበት ሳምንት በመሆኑ ነው፡፡
…የፖለቲካ ተንታኝና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኦርቶዶክስ ክርስትና ሀይማኖት ጥብቅ አማኝ ነው፤ የሀይማኖቱን
ትእዛዛቶች በጥብቅ ያከብራል፤ ሁሉንም አፅዋማትም ይፆማል፡፡ ዛሬ በግፍ ታስሮ በሚገኝበት የቃሊቲ ወህኒም ሆኖ እንኳ
የኩዳዴን ፆም ከመፆም አልሰነፈም… (በነገራችን ላይ እስክንድር የሚገኝበት ‹‹ዞን ሶስት›› ፈርሶ እንደገና ሊሰራ ስለሆነ
እስረኞቹ ወደሌላ ቦታ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተነግሯቸዋል)
እስክንድር የተወለደው ጥቅምት 27 ነው፡፡ ይህ ዕለት ደግሞ ለእምነቱ ተከታዮች የ‹‹መድሐኒያለም ዕለት›› እየተባለ
የሚከበረበት ቀን ነው፡፡ እርሱም ቢሆን ምንጊዜም ጠዋት ወይም ማታ ከስድስት ኪሎ ዩንቨርስቲ ከፍ ብሎ በሚገኘው
‹‹ምስኪያዙና መድሐኒያለም ቤተ-ክርስቲያ››ን የፈለገ አያጣውም፡፡
…የፊታችን ሀሙስ (ሚያዚያ 24 ቀን 2005 ዓ.ም) የእስክንድር ነጋ ይግባኝ ‹‹ለመጨረሻ ጊዜ›› ተብሎ ተቀጥሯል፡፡
ዕለቱ ለክርስትና እምነት ተከታዮች ‹‹ፀሎተ ሀሙስ›› ታስቦ የሚውልበት ቀን ነው (አይሁዳውያን ኢየሱስ ክርስቶስን
አሳልፈው ሰጥተው ሲያበቁ ስለሁከት፣ ስለመግደል በወሀኒ ታስሮ የነበረውን በርባንን ‹‹ፍታልን!›› ያሉበትን እና
የሐዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በትህትና ያጠበበትን ለማስታወስ ነው ቀኑ ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ተብሎ የተሰየመው)
…በድህረ ምርጫ 97 ለእስር ከተዳረጉ ጋዜጠኞች መካከል እስክንድር ነጋ አንዱ ነበር፡፡ የተፈታውም በ‹‹ይቅርታ››
ሳይሆን ፍርድ ቤቱ ‹‹ነፃ ነህ!›› ብሎ አሰናብቶት ነው፡፡ ቀኑም የ‹‹ፀሎተ-ሀሙስ›› ዕለት ነበር፡፡ …የከነገ በስቲያ
ሚያዚያ 24 ግጥምጥሞሽስ ምን ያሰማን ይሆን?
የሆነ ሆኖ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት እግዚአብሄር ሙሴን እንዲህ እንዳለው ይነግረናል፡-
‹‹እኔ እግዚአብሄር ነኝ፤ ከባርነት አወጣችኋላሁ፤ ከተገዥነታቸውም አድናችኋለሁ፤ በተዘረጋ ክንድ በታላቅ ፍርድም
እታደጋቸኋለሁ፤ አምላክም እሆናቸኋለሁ፡፡›› (ኦሪት ዘጸአት ም.6 ቁ.6-7)
በወቅቱ ብዙ ሺህ ንፁሃን፣ ፈርኦን በተባለ ጨካኝ ንጉስ ስር ይሰቃዩ ነበር፡፡ እናም ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሄር
ሙሴን ወደ ፈርኦን ላከው፡፡ ሙሴም ቤተ-መንግስቱ ውስጥ ድረስ ዘልቆ በዙፋኑ ለተቀመጠው ፈርኦን እንዲህ ሲል
የአምላኩን መልዕክት ነገረው፡-
‹‹እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፡- በፊቴ ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለህ? ያገለግለኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ!››
…በምንወዳት ሀገራችን ኢትዮጵያም እስከዛሬ ድረስ ያየነው ስርዓቱና ምንደኞቹ ንፁሃንን በሀሰት ከሰው፣ በሀሰት
ምስክርና በሀሰት ማስረጃ ወደ ጨለማ (ወህኒ) ሲወረውሩ ነው፡፡
በመላ ሀገሪቷ የነገሰውም የህግ የበላይነት አይደለም፤ የፈርኦን የበላይነት እንጂ፡፡ ፈርኦኖች ደግሞ ምን ጊዜም ከመከራ እንጂ
ከታሪክ ተምረው አያውቁም፡፡ መልካሚቷን ምክርም ሊሰሙ አይወዱም፡፡ ስለዚህም ብቸኛው አማራጭ በአደባባይ
ተሰባስበን፡-
‹‹በፊታችን ለመዋረድ እስከመቼ እምቢ ትላለችሁ? ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ ወንድምና እህቶቻችንን ልቀቅ!››
4/30/13 የህማማት ማሰታወሻ (ከተመስገን ደሳለኝ ) | Zehabesha Amharic
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/2602 3/3
ከጠቅላይ ፍ/ቤት እስከ
ሚንስትሮች ም/ቤት -
ከተመስገን ደሳለኝ
የነእስክንድር ነጋ ይግባኝ ውሳኔ
ለኤፕሪል 8 ተሸጋገረ
ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ
አለበት!! – ከጋዜጠኛ ተመስገን
ደሳለኝ
‹‹እስክንድር ነጋን ልቀቅ!
በቀለ ገርባን ልቀቅ!
አንዱአለም አራጌን ልቀቅ!
ርዕዮት አለሙን ልቀቅ!
ውብሸት ታዬን ልቀቅ!
የሱፍ ጌታቸውን ልቀቅ!
አቡበክር አህመድን ልቀቅ!
ብዙ… ብዙ ሺህ ንፁሃንን ልቀቅ!››
እያሉ መጮኹ ኢያሪኮን ለማፍረስ ያልተመለሰው የጭቁኖች ጩኸት መነቃነቅ የጀመረውን ስርዓት ለመፈረካከስ
ብቸኛው ምርጫችን እንደሆነ ዛሬም ደግሜ እናገራለሁ፡፡
‹‹ልቀቅ! ልቀቅ! ልቀቅ!››
Ze-Habesha Website is not responsible for accuracy of information or endorses the
contents provided by external sources. All blog posts and comments are the opinion of
the authors.

ESAT Daily News Amsterdam May 01, 2013 Ethiopia



የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኅብረት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የትግል ጥሪ አስተላለፈ


ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ያለተፎካካሪ ሥልጣኑን በኃይል የተቆጣጠረውን ኢህአዴግ በማስወገድ የሕዝብ ሥልጣን ባለቤትነትን ለማምጣት ብቸኛው መፍትሔ በፅናትና በቆራጥነት መታገል ብቻ መሆኑ ተገለፀ።
የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጊዜያዊ ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ሀገራችን ከገባችበት ፈተናና ሕዝቡ ከሚቀበለው ሥቃይ ልናላቅቀው የምንችለው ከያዘን የፍርሃት ቆፈን ተላቀን ባንድነት በመቆም ቀኑ የደረሰውን አምባገነን ሥርዓት ወደተመኘው መቃብር ለመሸኘት በጽናት መታገል ብቻ ነው ብሏል።
የ33ቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ከሕዝቡ ጋር ሆነው ለሚያደርጉት ትግል በሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን፣ አቅማቸውንና ጊዜያቸውን አስተባብረው ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ፓርቲዎቹ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊም ድምፁ ለታፈነውና የሰቆቃ ሕይወት ለሚገፋው ወገናቸው ድምፅ በመሆን የትግሉ አጋርነታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የኑሮ ውድነቱ ሕዝቡን በመኖርና ባለመኖር መካከል በጣለበት በአሁኑ ወቅት መንግሥት “ይህ የሆነው የኢኮኖሚው ዕድገታችን ፍጥነት ነው፣ ጤፍ የሚበላው ሰው በመጨመሩ ነው” እያለ በሕዝቡ ላይ ያላግጣል ያለው መግለጫ፤ ከዚህ ንቀት የተሞላበት አምባገነናዊ ሥርዓት ለመገላገል ብቸኛው መፍትሔ የተደራጀ ትግል ማድረግ ነው ብሏል።
በ33ቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኅብረት የወጣው ይህ መግለጫ ለዓለም ዐቀፍ ማኅበረሰብና ሃገራት፤ በሀገራችን ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን በደልና ሥቃይ በመረዳት ከሕዝብና ከሕዝቡ ትግል ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል።

መንግስት በድምጻችን ይሰማ አስተባባሪዎች ላይ በድጋሜ ዘመቻ ሊከፍት ነው


ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባገኘው አስተማማኝ መረጃ  ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድምጻችን ይሰማ በማለት በየሳምንቱ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የስርአቱን ህልውና እየተፈታተነው በመምጣቱ መንግስት ችግሩን በድርድር ከመፍታት ይልቅ በከፍተኛ እና መካከለኛ እንዲሁም በቀበሌዎች አካባቢ ያሉ የተቃውሞ አስተባባሪዎችን በመለየት ሰብስቦ ለማሰር እና ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ለመመስረት ማቀዱ ታውቋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ታማኝ የኢህአዴግ ካድሬዎች በቅርቡ በጦላይ እና በብርሸለቆ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግል ስልጠና ለመውሰድ እንደሚገቡ ታውቋል። ከህብረተሰቡ፣ ከቀበሌ አመራሮች እና ከአባላት የሚውጣጡት ሰልጣኞች ስልጠናቸውን እንደጨረሱ የሙስሊሙን እንቅስቃሴ ይመራሉ የሚሉዋቸውን ሰዎች በመለየት ለዚህ ስራ ተብሎ ለተቋቋመው አካል ሪፖርት ያደርጋሉ።
መንግስት ልዩ ትኩረት ይደረግባቸዋል ብሎ የዘረዘራቸው አካላት የዩኒቨርስቲ እና የሁለተኛ ደረጃ መምህራን ፣ነጋዴዎች እና በየአካባቢው የእስልምና ትምህርት በሚሰጥባቸው መደርሳዎች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች ናቸው። በአሁኑ ጊዜ ልዩ ትኩረት የተጣለባቸው የድምጻችን ይሰማ አመራሮች በድብቅ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑንም ከምንጫችን ለመረዳት ተችሎአል።
ለወደፊቱ በሚያዙት አመራሮች ላይ የግንቦት7 ቅጥረኞች፣ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙትን ደግሞ የኦነግ ቅጥረኞች እና የተለያዩ አክራሪዎች መናጆ በመሆን ለህገምንግስታዊ ስርአቱ አደጋ በመደቀን ክስ ለመመስረት መታቀዱንም ለማወቅ ተችሎአል።
መንግስት በአቶ አቡበክር አህመድ የሚመራው የድምጻችን ይሰማ ኮሚቴ አባላትን ካሰረ በሁዋላ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ሊበርድ ይችላል የሚል እምነት የነበረው ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ እምነቱ ወደ ተግባር ሲለወጥ አልታየም። በዚህም የተነሳ በአሁኑ ጊዜ ተቃውሞውን በየአካባቢው ያስተባብራሉ በማለት የጠረጠራቸውን ሙስሊሞች በማጥናት በድጋሜ ለማሰር በዝግጅት ላይ ነው።
የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በሙስሊሙ ጉዳይ ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መግባታቸውን ከከፍተኛ ባለስልጣናቱ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክት ሲሆን፣ የሀይማኖት እንቅስቃሴው ቀስ በቀስ ወደ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ሊለወጥ እና መላውን ህዝብ ያሳተፈ እንቅስቃሴ ሊጀመር ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ እየደረሱ መምጣታቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ችግሩን ውስብስብ ያደረገው ደግሞ አብዛኞቹ የኢህአዴግ ሙስሊም አባላትና ደጋፊዎች የድምጻችን ይሰማ እንቅስቃሴን መደገፋቸው ነው።