Friday, March 8, 2013

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሶስተኛ ጊዜ በ ‹‹ልዕልና›› ጋዜጣ


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለሶስተኛ ጊዜ  በ ‹‹ልዕልና›› ጋዜጣ
እንደምን ሰነበታችሁ? ይህ ለአፋና እጅ የማይሰጥ የህዝብ ድምፅ ነው፡፡
ዳግም ተመልሰናል!!
ለዜጎች ክብር የማይሰጠው ኢህአዴግ፣ ህዝብ በሚከፍለው ግብር መልሶ የሚያፍነው ኢህአዴግ፣ የሀይማኖት ተቋማትን ወደ ‹‹አጋር ፓርቲ››ነት እየቀየረ ያለው ኢህአዴግ ፍትህ ጋዜጣን እና አዲስ ታይምስ መፅሄትን በጉልበት ከነጠቀን በኋላ፣ ለሶስተኛ ጊዜ በሌላ ጋዜጣ ተመልሰናል፡፡ ጋዜጣዋ ‹‹ልዕልና›› ትባላለች፡፡ ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ለአንዴ ብቻ ታትማ ተቋርጣ ነበር፡፡ አሁን ግን የነበረባት የመንግስት ዕዳ ተከፍሎ፣ አሳታሚ ድርጅቱ በሀገሪቱ የአክሲዮን ሽያጭ ህግ መሰረት ወደ እኛ መዞሩን አበስራለሁ፡፡ እናም ዛሬ በዕለተ ቅዳሜ ለአንባቢያን ትደርሳለች፡፡ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ግን ‹‹አርብ አርብ ይሸበራል፤ …›› እንዲል ንጉስ ቴውድሮስ፣ ልዕልና ጋዜጣም የዕለት አርብ ድምፅ ሆና ትቀጥላለች፡፡
እንደመውጫም ይሆነኝ ዘንድ በአዲሷ ጋዜጣችን ላይ ‹‹ከተዘጋው በር ጀርባ›› በሚል ርዕስ ላቀረብኩት ፅሁፍ መግቢያ ያደረኩትን እዚህም ልድገመው፡-
እነሆ በሶስተኛው በር ተገናኝተናልና አብዝቼ አላማርርም፡፡ ባማርርስ የት እደርሳለሁ? ማነው አገዛዙንስ ከስሶ የረታ? ደግሞስ ከመቼ ወዲህ ነው በሀገሬ መሬት ላይ ህግ የበላይ ሆኖ የሚያውቀው? ለማንኛውም የጠፋው ብርሃን በዚህ መልኩ ዳግም ይፈነጥቅ ዘንድ ስለተከፈለው ዋጋ ወይም ውጣ ውረድ ገድል የመፃፍ ፍላጎት የለኝም፡፡ ፍላጎቴ ከባልደረቦቼ ጋ በፀና መንፈስ በጀመርነው ጎዳና እንተም ዘንድ የመንግስትን አፈና አውግዛችሁ የሞራል ድጋፍ ለሰጣችሁን ኢትዮጵያውያን፤ እንዲሁም የአለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ተቋማት ላሳያችሁት አጋርነትና ተቆርቋሪነት፣ በሀገሬ ላይ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ይሰፍን ዘንድ ዋጋ በከፈሉና እየከፈሉ ባሉ ወንድምና እህቶቼ ስም ልባዊ ምስጋናዬን ማቅረብ ነውና-ቺርስ ለነፃነታችን!
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ
Image

ESAT Daily News Amsterdam 08 March 2013 Ethiopia


“በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”

benishangul asosa
ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ያነሳል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው። በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ተረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች ድምጻቸውን አላሰሙም ነበር። አሁንም በተቆራረጠ አንደበት አስተያየቱን ቀጠለ።
በወቅቱ ፓዌ እንደነበር ያስታወሰው አስተያየት ሰጪ “አሰፋ ኢናቦ” ሲል ስም ጠራ። አሰፋ ኢናቦ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ ነበር። ድንገት በደረሰው ጭፍጨፋ የተበሳጩ ከመንደር አራት ስምንት ኪሎሜትር ርቆ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ አሰፋ ኢናቦን አስገድደው ወሰዱት። በመጨረሻም ሰፋሪውን እያሳዩ የበቀል ኃይላቸውን አሳረፉበት፤ ቦጫጨቁትና እዛው ተቀበረ። በስፍራው ስለተደረገው ሁሉ በቂ መረጃ ያለው መሆኑን የሚናገረው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው በቀትር በአደባባይ ህዝብ የጨፈጨፉትና ያስጨፈጨፉት አልታሰሩም። ህግ ፊት አልቀረቡም። ለይስሙላ ታስረዋል ተብለው ተለቀዋል።
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ የሚኖሩት የሺናሻ ብሔረሰብ አባላት ሲሆኑ ቀደም ሲል ጀምሮ “አገሩ የናንተ ነው። ባለመብቶች እናንተ ናችሁ። ውሳኔው ሁሉ የራሳችሁ ነው” ስለተባሉ በክልሉ በአንድ ትምህርት ቤት የሚማሩ የአማራ ብሔር አባላት እኩል የትምህርት እድል እንደማያገኙ፣ እሱም የችግሩ ሰለባ እንደሆነ ያስረዳል። ነጻ ሚዲያ ቢኖር ግፉ በተዘረዘረ ነበር ሲል ቁጭቱን ይገልጻል።
አገሬውን “ሆን ብለው ክፋት እየጋቷቸው በየጊዜው አማራ ውጣ፣ አማራ ሂድ …” በማለት እንደሚፎክሩ ያስረዳው ቅሬታ አቅራቢ አስገራሚውና አስደንጋጩ ጉዳይ የአማራ ክልል “እመራዋለሁ” የሚለው አካል ለህዝቡ መከራከር አለመቻሉ ነው።
በጉራፈርዳ በክልሉ መንግስት ትዕዛዝ የከፋ ወንጀል ሲሰራ፣ አንደኛ ክፍል ለሚማር ህጻን “ክልሉን ልቀቅና ውጣ” የሚል ደብዳቤ ሲሰጥ ተቆጣጣሪና ተቆርቋሪ አለመኖሩ መጨረሻ የሌለው ግፍ አማራው ላይ እንዲካሄድ ስምምነት ያለ እንደሚያስመስል የሚገልጹ ጥቂት አይደሉም።
ሰሞኑን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል አማራውን የማፈናቀል ዘመቻ መጀመሩ ይፋ ሆነ እንጂ ችግሩ የቆየና ማዕከላዊ አገዛዙም ሆነ የክልሉ መስተዳድር ጠንቅቀው የሚያውቁት ጉዳይ እንደሆነም አስተያየት ሰጪዎቹ ይናገራሉ። የካቲት 28፤2005 (ማርች 7፤2013) የተላለፈው የአሜሪካን ሬዲዮ አማርኛ ክፍል ያነጋገራቸው የችግሩ ሰለባ አሁን ያለውን ችግር የሚገልጹት በተማጽኖ ነው።
በቤንሻንጉል መተከል ዞን ቡሎን ወረዳ የሰፈሩና ከ15 እስከ 20 ዓመት በረሃውን አልምተው፣ ወልደው ከብደውና ንብረት አፍርተው ይኖሩ የነበሩ አምስት ሺህ በላይ ነዋሪዎች ከየካቲት19 እስከ 30 ቀን 2013 ዓም መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ ታዝዘዋል። ለቪኦኤ የተማጽኖ ቃላቸውን ያስተላለፉት አቶ የሺህ ዋስ ትንሳኤ ድምጻቸው ያሰሙት ባህር ዳር “መንግስታቸው” ደጅ ቆመው ነው።
ባህር ዳር ሆነው “ሰሚ አጣን” በማለት ድምጻቸውን ያሰሙት አቶ የሺህ ዋስ “ለክልሉ መንግስት ለምን አመለከታችሁ በሚል ስለምንታሰር እባካችሁ ለፌደራሉ መንግስት አሳውቁልን” ሲሉ ተደምጠዋል። አገር ቤት የመንግስትም ሆነ “የግል” የሚባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ጆሮ የነሷቸው በሚመስል ኑዛዜ ያቀረቡት አቶ የሺህ ዋስ “ፈልሶ የመጣ፣ ውጣ አማራ” እየተባሉ የውጭ አገር ዜጋ እንኳን በማይጠራበት ሁኔታ ክብረ ነክ ስድብ እንደሚሰደቡ አመልክተዋል።
ከመንግስታችሁ ሸኚ አምጡ መባላቸውን፣ በርካቶች ሸኚ ለማምጣት ከብቶቻቸውን በርካሽ መሸጣቸውን፣ ሸኚም ካመጡ በኋላ ተቀባይነት አለማግኘቱን አቶ የሺህ ዋስ ያስረዳሉ። አያይዘውም ባፋጣኝ ክልሉን ለቀው ካልወጡ የክልሉ መንግስት ባለስልጣናት ምን ሊከሰት እንደሚችል የዛቱባቸውን ተናግረዋል።

የብአዴን ሊ/መንበር ደመቀ መኮንን (ፎቶ: ምንጩ ያልታወቀ)
ባስቸኳይ ክልሉን ለቀው ካልወጡ “የፌደራል ፖሊስ ደብድቦ ያስወጣሃል” የሚል ማስፈራሪያ የደረሳቸው መሆኑንን ያመለከቱት አቶ የሺህ ዋስ፣ የአማራ ክልል ባለስልጣናትን ማግኘትና ማነጋገር አለመቻላቸውን ከክልሉ መንግስት መቀመጫ ባህር ዳር ሆነው መናገራቸው ጉዳዩን አወሳስቦታል። ለሰሚውም ግራ ሆኗል። ቪኦኤ እንዳለው የክልሉን ባለስልጣናትም አግኝቶ ማነጋገር አልተቻለም።
ለጊዜው የክልሉ መንግስት ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው ወይም የሚሰፍሩበት ቦታ እስኪመቻችላቸው ከክልሉ ጋር በመነጋገር አደጋ ላይ ለሚገኙት ከአምስት ሺህ  በላይ ሰዎች መፍትሔ እንዲያፈላልግ የተጠየቀው የክልሉ መስተዳድርም ሆነ “የጭቁኑ አማራ ተወካይ ነኝ” የሚለው ብአዴን/ኢህአዴግ ጉዳዩን አስመልክቶ እስካሁን ያሉት ነገርም የለም።
የአማራ ክልል ለምና ሰፊ መሬቱን ለሱዳን አሳልፎ በመስጠት፣ ሁመራንና ወልቃይት ገባውን ለትግራይ ክልል አሳልፎ በማስረከብ የሚታወቀውን ብአዴንን የሚመሩት አቶ ደመቀ መኮንን በአማራው ስም “ቅምጥ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር” ሆነው በውለታ መሾማቸው የሚታወስ ነው።

http://www.goolgule.com/benishangul-evicted-by-federal-police/

Thursday, March 7, 2013

በኬንያ ምርጫው እየተጭበረበረ ነው ሲሉ ራይላ ኦዲንጋ ቅሬታ አቀረቡ


የካቲት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-በምርጫው ከተሸነፉ ዳግም ምርጫ እንዲደረግ አለያም የጥምር መንግስት እንዲቋቋም እንደሚጠይቁ የኬንያውጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ አስጠነቀቁ።

እስካሁን የተደረጉት የድምጽ ቆጠራዎች በምርጫው የጆሞ ኬንያታ ልጅ ኡሁሩ ኬንያታ እየመራ እና የ ኦሬንጅ ዲሞክራቲክሙቭመንቱ ራይላ ኦዲንጋ በሁለተኝነት እየተከተሉ እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

ይህንኑ ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ምርጫው ለመጭበርበሩ እና በድምጽ ቆጠራው ሂደት ስርቆት ለመፈጸሙበቂ ማስረጃዎች አሉን ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በአሁኑ ጊዜ  እየተካሄደ ያለውና በዲሞክራሲያዊነቱ በጎ አስተያየቶች እየጎረፉለት ያለው የዘንድሮ የኬንያ ምርጫ ወደመጨረሻው ላይ ችግር እንዳይፈጠር ስጋቶች ብቅ እያሉ ቢሆንም፤ እንደባለፈው ምርጫ ጊዜ ደም አፋሳሽ ችግርየሚከሰትበት መንገድ ግን እጅጉን የጠበበ እንደሆነ ነው ዘገባዎች የሚያመለክቱት።

ኦዲንጋ አቤቱታ ቢያቀርቡም ለደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ጥሪ እንደማያደርጉ አረጋግጠዋል። የአገሪቱ ዋነኛ የምርጫአስፈፃሚ አካል ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ኦዲንጋን ቅሬታ ውድቅ አድርጎታል። የምርጫ ኮሚሽኑ ሊቀመንበር አህመድይስሀቅ ሀሰን፤ የምርጫ ውጤቱ እንዲጭበረበር የሚያደርግ ምንም ዓይነት ክፍተት የለም ነው ያሉት።

ቀደም ሲልም የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱን በተመለከተ ከተወዳዳሪ ፓርቲዎች በጽሁፍ የቀረበ ምንም አይነት አቤቱታእንዳልነበር የምርጫ ኮሚሽኑ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊ ሊሊያኔ ማሂሪ ዛጃ  መናገራቸው ይታወሳል።

ይሁንና የኤክትሮኒክ ድምጽ መቁጠሪያው ከተበላሸ በሁዋላ የድምጽ ቆጠራ ሂደቱ እጅጉን መዘግዬቱን ቢቢሲ ጠቁሟል። በአሁኑ ጊዜ የምርጫ ኮሞሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ ከዲፕሎማቶች ጋር ስብሰባ ተቀምጧል።

እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ 2007-2008 በተካሄደው የኬንያ ምርጫ ሚስተር ራይላ ኦዲንጋ የድምጽ ቆጠራ ሂደቱበፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ ደጋፊዎች እንደተጭበረበረ መናገራቸውን ተከትሎ በተነሳው አመጽ ከ 1000 በላይ ኬንያውያንመሞታቸው ይታወሳል።

ታክሲ ውስጥ በ 1 ብር ከ 35 ሳንቲም ሳቢያ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ረዳቱ በጥይት ተመታ


የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-ከትናንት በስቲያ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ  ኪዱ ገብረሥላሴበተባለ  የታክሲ ተሳፋሪና በረዳቱ መካከል በተፈጠረ የ1.35ብር አለመግባባት ምክንያት ረዳቱ በጥይት ተመታ።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ ድርጊቱ የተፈጸመው ቦሌ መድኃኔዓለም ከሚገኘው ካልዲስ ካፌ ፊት ለፊት ሲሆን፣ ተጠርጣሪው አቶኪዱ ገብረ ሥላሴ ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡

ነጋ ንጉሡ የተባለው የታክሲው ረዳትም፤ ሃያት ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዷል፡፡

የታክሲው አሽከርካሪ አቶ ጌትዬ ቆንጥር እንደገለጹት፣ ተሳፋሪው ሽጉጡን ሊተኩስ የቻለው የአገልግሎት ማብቂያ ቦታቸውላይ ሲደርሱ “ውረድ አልወርድም” በሚል ክርክር ነው፡፡

ሾፌሩ አክለውም፦“ታክሲያችን አገልግሎት የሚሰጠው ከመርካቶ እስከ ቴሌ መድኃኔዓለም ድረስ ነው፡፡ በዚያ ቀንምተሳፋሪዎችን ከካዛንቺስ ጭነን ወደ ቴሌ መድኃኔዓለም ለማድረስ እየተጓዝን ነበር፡፡ በስተመጨረሻም ቴሌ መድኃኔዓለምስንደርስ ለሁሉም ተሳፋሪዎች እንዲወርዱ ስንናገር፣ ሁለቱ ግን ለመውረድ ፈቃደኛ አልሆኑም፤” ብለዋል፡፡

እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤ከካዛንቺስ- ቴሌ መድኃኔዓለም ድረስና ከካዛንቺስ- ቦሌ ድልድይ ድረስ ታክሲዎች የሚያስከፍሉትታሪፍ በተመሳሳይ 2.70 ብር ነው፡፡ በመሆኑም ተጠርጣሪው አቶ ኪዱ መሄድ የምፈልገው ቦሌ ድልድይ ነው በማለትከሾፌሩና ከረዳቱ ጋር አምባጓሮ ቢፈጥርም፣ ሾፌሩም ሆኑ ረዳቱ ከዚህ በላይ መሄድ እንደማይችሉና ቢሄዱም በሕግእንደሚጠየቁ ለተጠርጣሪው ይናገራሉ፡፡

በሁለቱም ንግግር የተበሳጨው ተጠርጣሪ ግን ምላሹ ከታክሲ መውረድ ሳይሆን በጎኑ የሰደረውን ሽጉጥ በማውጣት በሾፌሩላይ ማነጣጠር ነበር፡፡

ጋዜጣው እንዳለው ይህን የተመለከተው ረዳትም ሽጉጡን ከተጠርጣሪው ለማስጣል ትግል ይገጥማል ።በዚህም መካከልተቀባብሎ ከነበረው ሽጉጥ የተተኮሰች ጥይት የረዳቱ የግራ ጎን ውስጥ ተቀርቅራለች፡፡

ረዳቱም ከተጠርጣሪው አቶ ኪዱ ሽጉጡን ታግሎ በመቀበል በቦታው ለነበረው የካልዲስ ጥበቃ እንደሰጠው ጉዳዩንየሚመረምሩት ኮንስታብል አዱኛ ገልጸዋል፡፡

ከዚያም ፖሊስ ወዲያው በአካባቢው ደርሶ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር አውሎታል፡፡

ተጠርጣሪው  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ የቀን ሠራተኛ ሲሆን፣ በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ክስ ተመስርቶበታል። ተጠርጣሪው ኪዱ ገብረሥላሴ የያዘው መሣሪያም ፈቃድ ያለው እንደሆነ በፖሊስ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ዜናውን ባነበቡትሁሉ ዘንድ አቶ ኪዱ ገብረሥላሴ ከባለዘመነኞቹና ከአድራጊ ፈጣሪዎቹ ሹመኞች አንዱ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምትአሳድሯል።

ታክሲ ውስጥ በተፈጠረ ተራ ንትርክ  የእለት ጉርሱን ለማግኘት የሚለፋን ደሀ ረዳት በሽጉጥ መምታት ጥጋብና እብሪትካልሆነ በስተቀር ምን ሊባል ይችላል? ብለዋል በጉዳዩ ላይ በፌስቡክ አስተያየታቸውን የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን።

የታክሲ ረዳቱ ነጋ በሃያት ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ ሲሆን፣ በሰውነቱ ውስጥ ያለውን ጥይት ለማውጣትኦፕራሲዮን ሊሆን እንደሚችል ምንጮች  ተናግረዋል፡፡

ESAT Daily News Amsterdam 07 March 2013 Ethiopia



Tuesday, March 5, 2013

በጀርመን የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ


የካቲት ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:- እ.ኤ.አ. በማርች 01 ቀን 2013 ዓ.ም. በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ዘብ በጠራው የተቃውሞ ሠልፍ ላይ ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡ ቁጥራቸው ከ400 በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተገኙ ሲሆን ፣  በተለያዩ መፈክሮችና የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ በማሸብረቅ ጉዞውን ወደ ኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አድርጓል።
”የህሊና እስረኞች ይፈቱ!” ፣”የፕሬስ ነጻነት ይከበር!” ”ሃሳብን በነጻነት የመግለፅ መብት ይከበር!” ”ጅሃዳዊ ሐረካት የወያኔ ፈጠራ ነው!” ”የሃይማኖት ነፃነት ይከበር!” ”በአለም ዙሪያ ያሉ የወያኔ ቆንስላ ፅ/ቤቶች የኢትዮጵያን ህዝብ አይወክሉም!” ”የአውሮፓ ህብረት ለአፋኙ የወያኔ አገዛዝ የሚያደርገውን የገንዘብ ድጋፍ ያቁም!”  ”ከአባይ በፊት ሙስናና ዘረኝነት ይገደብ!” የሚሉ መፈክሮች በሰፊው የተደመጡ ሲሆን ከአንድ ሰዓት ተኩል የእግር ጉዞ በኋላ ተሰላፊው  ቆንስላው ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሲደርስ በከፍተኛ ጩኸት እና ፉጨት ተቃውሞውን ማሰማት ችሏል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ተወካይ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወካዮች በአካል ተገኝተው አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎም ከኔዘርላንድ የላከው ደብዳቤ መነበቡን ኢንጂነር ዳዊት ፋንታ የላከው ዘገባ ያመለክታል።