አንደነት ፓርቲ ከአዲሳባ ህዝብ ጋር በመሆን ”እሪታችንን” እያሰማልን ነው! (ገለቶማ!)
ፓረቲው ከሶስት ሳምንት በፊት ሊያካሂድ አስቦት የነበረው የእሪታ ቀን ሰላማዊ ሰለፍ መንግስት ”ቀፈፈኝ” ብሎ ሲያዛውረው ሲያዛውረው ዛሬ ላይ ለመካሄድ በቅቷል።
አንድነት በቀደመው የሰላማዊ ሰልፍ እቅዱ በአዲሳባ የሚገኙ መሰረታዊ አገልግሎቶች፤ እነርሱም ውሃ፣ መብራት፣ ትራንስፖርት እና ስልክ ላይ ያለው መስተጓጎል ኢህአዴግ ሀገር ለመምራት ብቃት እነደሌለው ማሳያ ናቸው በሚል፤ እሪታ ሊያሰማ አቅዶ የተነሳ ቢሆንም፤ ሰለፉ በተራዘመባቸው ሶስት ሳምንታት ውስጥ ተጨማሪ ታላላቅ በደሎች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በመፈጸማቸው የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ እነርሱንም ያካተተ ሆኗል።

ከነዚህ ታላላቅ በደሎች ውስጥ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረስ ያለው፤ ግድያ፣ ድብደባ እና እስር፤ በዞን ዘጠኝ ብሎግ ጸሀፊያን እና በጋዜጠኞች ላይ የተደረገውን እስር በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተቃውሞ ከተሰማባቸው ጉዳዮች መካከል ይገኛሉ፤
ውሃ የለም!
መብራት የለም!
ኔትወርክ የለም!
ፍትህ የለም!
የሚሉት መፈክሮች ጎልተው ከወጡት መከክል ይገኛሉ።
መብራት የለም!
ኔትወርክ የለም!
ፍትህ የለም!
የሚሉት መፈክሮች ጎልተው ከወጡት መከክል ይገኛሉ።
በመጨረሻም፤
በሰልፉ ላይ የተገኙት የማህበረሰብ አካላት ምንም አይነት ውሎ አበል እንዳልተከፈላቸው ለማውቅ ተችሏል! (ይቺን ነገር መንግስት ከሰማ ያለ አበል የተካሄድ ሰልፍ ህገ ወጥ ነው እንዳይል መፍራት ነው!)
የሰልፉን ገጽታ የሚያሳዩ ተጨማሪ ስዕሎች ከፌስ ቡክ ወዳጆቼ አሰባስቤ በድረ ገጻችን ውስጥ አድርጌዋለሁ!
No comments:
Post a Comment