Saturday, August 31, 2013

ከስልጣን የተነሳው የደህንነት ሹም፣ እስር ቤት ተወረወረ!!


(ኢ.ኤም.ኤፍ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በህይወት በነበረበት ወቅት፤ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ምክትል የደህንነት ሹም ሆኖ ይሰራ ነበር። ወልደስላሴ የህወሃት ታጋይ የነበረ ሲሆን፤ በትግላቸው ወቅት… ወንድ እና ሴት ታጋዮችን “ፍቅር ስትሰሩ ተገኝታችኋል” በማለት ብዙዎችን በመረሸን  ይታወቃል። ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ የመለስ ዜናዊ ክርስትና እናት ልጅ የሆነው፤ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ የቤተ መንግስቱ ዋና ኃላፊ፣  ወልደስላሴ ደግሞ የቀድሞው ደህንነት ሃላፊ ክንፈ ገብረመድህን ረዳት ሆኖ እንዲሰራ ተደርጎ ነበር።
….
አሁን ጌታቸው አሰፋ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ያለውን ስልጣን እያደራጀ የመጣ ይመስላል። ከስር ሆኖ የሚያዘው ወልደስላሴ እስር ቤት ገብቷል። ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ከቤተ መንግስት እየደወለ ት እዛዝ እና መመሪያ አይሰጠውም። ጌታቸው አሰፋ አሁን ነጻ ሰው ነው። ይህ ነጻነቱ የሚቆየው ግን ቀጣዩ የህወሃት/ኢህአዴግ ስብሰባ እስከሚደርስ ይሆናል። እስከዚያው ድረስ ግን እነ ኢሳያስን በአይነ ቁራኛ መጠበቅ አለበት። አዜብ መስፍን ከኢፈርት ስልጣንዋ ወርዳ፤ ስለመለስ ፋውንዴሽን ብቻ እያወራች እንድትኖር እድል ሰጥቷታል። ቢሆንም ግን ህወሃት ውስጥ ሌሎች የጌታቸው አሰፋ ጠላቶች አሉ። እስከሚቀጥለው የህወሃት ስብሰባ እና ሌላ ውጥንቅጥ ድረስ፤ ድራማውን ከዳር ሆነን እናያለን።

አዜብ መስፍንን በቁጥጥር ስር ለማዋል ግምገማ እና ጥናት በይፋ ተጀምሯል::

ምንሊክ ሳልሳዊ

በወያኔ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣን የሆነውን እና ለመለስ ዜናዊ እና ለባለቤታቸው አዜብ መስፍን ቅርብ የነበረውን እንዲሁም የቤተመንግስት የደህንነት ሃላፊ አቶ ዘርኡ አንገታቸው በስለት አሳርዶ፣ የመገናኛ ሚ/ሩ አቶ አየነው በገመንድ አንቆ..የገደለ እና ብዙ ወንጀሎች የሰራው በሙስና የተዘፈቀው ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ መንገዶች ሁሉ ወደ ወይዘሮ አዜብ እያመሩ መሆናቸውን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ጠቁመዋል::
ይህ በሙስና እና በጭካኔው ወደር ያልተገኘለት የሕወሓት የደህንነት አናት በበቀለኛው በአቶ ስብሃት ቡድን በኩል በተደረገ ከፍተኛ ርብርብ ከስልጣን ወርዶ ከቆየ በኋላ ስልታንን ያለአግባብ በመጠቀም ምንጩ ያልታወቀ ሃብት በማፍራት በሚል ተወንጅሎ ወደ ወህኒ ተወርውሯል::ይህ ግለሰብ በአሁን ወቅት በወህኒ ቤት ከሚገኘው ከቀድሞው የገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ድይሬክተሩ እብሪተኛው ገብረዋሃድ ወልደጊዮርጊስ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ወዳጅነት እና ቅርርብ ያለው ሲሆን ገብረዋህድ በበኩሉ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የተለየ ግንኙነት የነበረው እና አስተማሪዋ የነበረ ሲሆን ለዚህም ስልጣን ያበቃችው እሷ እንደሆነች ሲታወቅ የጸጥታ ሹሙ በቁጥጥር ስር መዋል ወይዘሮ አዜብን ለመያዝ እሳቤ ያደረገ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል::ወይዘሮ አዜብ መስፍን በቅርቡ የተላያዩ የህወሓት ድርጅቶችን በጋራ ከሚመራው ኤፈርት ተብሎ ከሚጠራው ድርጅት ስራ አስኪያጅነት መውረዳቸው የታወቀ ሲሆን በስልታን ዘመናቸው ድርጅቱ ኦዲት የሂሳብ ምርመራ ተደጎለት የማያውቅ እና ለመንግስት አስፈላጊውን ግብር እና ሪፖርትም ጭምር ያልሰጠ በመሆኑ በቀድሞው ስራ አስኪያጅ ላይ የቀረበው ክስ ወይዘሮ አዜብንም የሚጠብቃቸው እና በቤተሰቦቻቸው ስም የተመዘገቡ ቀረጥ መከፈል ሲገባቸው ያልከፈሉ ጨረታ በዝምድና ሳያሸንፉ የሚወስዱ አላግባብ የሚበለጽጉበት ሁኔታዎች በምርመራ መገኘታቸው በባለቤታቸው ስም እና ዝና ለመነገድ መሞከራቸው ከፓርቲው ውጪ የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ሴትየዋ በአቶ ስብሃት ቡድን ጥርስ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓቸዋል::
ወይዘሮዋ ባለበታቸው በነበረበት ሰአት ከከፍተኛ ደረጃ የሚፈሩ እና ፓርቲውን ለመዘወር በየስብሰባው አደገኛ ቃላቶችን የሚናገሩ የነበሩ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የአሁኑ የደህንነት ሹም ወንጅለውት ከስልጣን በማውረድ አሁን ወደ ወህኒ የወረዱትን ወልደስላሴን ማሾማቸው ይታወቃል::የስበሃት ቡድን ደጋፊ የሆኑት አቶ ጌታቸው አሰፋ በዚህ ጉዳይ ቂም ቋጥረው መለስ ከሞቱ በኋላ እስከዛሬ ድረስ ከወይዘሮ አዜብ ጋር የጎሪጥ እንደተያዩ ነው::
በአንድ ወቅት እብሪተኛ እና የሃያልነት ስልጣን በእጇ የነበረው አዜብ ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ቀስ በቀስ በፖለቲካ ባላንጣዎቿ እየተገፋች ዋጋቢስ እየሆነች መታለች::በአሁኑ ወቅት አዜብ ምንም አይነት ስራ የሌላት እና ቤት ውስጥ ተቀምታ የምታሳልፍ የፖለቲካ ቁማር የተበላሽባት ወይዘሮ ሆናለች::ውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉት በችሎታ ማነስ እና በሙስና ከኤፈርት የተባረረችው አዜብ በእፈርት ስር የሚተዳደሩ ሰራተኞች ከፍተኛ የሆነ ስሞታ ሲያሰሙባት እና ሲከሷት እንደነበር ይታወቃል::
ምንጮቹ እንዳመለከቱት ወይዘሮ አዘብ በአባይ ወልዱ በሚመራው የሕወሓት አንጃ ውስጥ በረከት ስምኦንን አስከትላ እየተንቀሳቀሰች ሲሆን መሰረቱን መሃል አዲስ አበባ ላይ የተከለው እና ማእከላዊ መንግስቱን እንዳሰኘው የሚያሽከረክረው በደብረጺሆን እና በደህንነቱ ሹም ጌታቸው የሚመራው ሌላው የሕወሓት አንጃ ስብሃት ነጋን አስከትሎ “ብረታሙ” በሚል መጠሪያ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ::ይሀ ብረታሙ እያለ ራሱን የሚጠራው የሕወሓት አንጃ የጸረ ሙስናን ዘመቻውን በበላይነት የሚመራ ሲሆን ወይዘሮዋ ቤተመንግስት በነበሩ ጊዜ የፈጸሟቸውን አሰቃቂ ሙስናዎች እና ተግባራት ለፍትህ ለማቅረብ አስፈላጊውን ጥናት እና ግምገማ እያደረገ ነው ሲሉ ምንጮች መረጃውን ሰተዋል::

Thursday, August 29, 2013

ፓሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ነገ ሊያነጋግር ነው


ሰማያዊ ፓርቲ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ፓሊስ የፓርቲውን አመራሮች በመጥራት ለነገ ሊያነጋግራቸው ቀጠሮ መያዙን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ፡፡
ፓርቲው በበኩሉ ሊካሄድ የታቀደውን የተቃውሞ ሰልፍ በምንም አስገዳጅ ሁኔታ ሊሰርዝ እንደማይችል በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የፓርቲው አመራሮች ተናግረዋል፡፡
ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ፀሐፊን፣ ሊቀመንበሩንና የሰልፍ አስተባባሪዎችን ለማነጋገር ጥሪ እንዳቀረበላቸው ታውቋል፡፡
በፀጥታ ዙሪያ ልናነጋግራችሁ እንፈልጋለን የሚለው የፖሊስ መጥሪያ ፓርቲው የእሁዱን ስብሰባ እንዲሰርዝ ለማግባባት ያለመ እንደሆነ ታውቋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፓርቲያቸው የእሁዱን ስብሰባ ለማካሄድ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ተናግረው፤ ምንም አስገዳጅ ሁኔታ ከያዙት አቋም እንደማያስቆማቸው ለኢሳት ተናግረዋል፡፡
በታሪክ፣ በሞራልም ሆነ በህግ ተጠያቂ የሚያስደርገን ነገር ስለሌለ ሰላማዊ ሰልፉ የማይቀር መሆኑን የፓርቲው አመራር ተናግረዋል፡፡
በትላንትናው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማህበራት ፍቃድ ጽ/ቤት የፓርቲውን ሰልፍ ህገወጥ ነው ማለቱን አስመልክቶ የተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ‹ሕጋዊ ወይም ህገ ወጥ› የሚባል ሰልፍ አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡
የፓርቲው የሰልፍ አስተባባሪ ዝግጅት ክፍል ለእሁድ ሰልፍ የሚያደርገው ዝግጅት ከገዥው ፓርቲ የተለያየ ወከባ እየደረሰበት እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
መብራት በተደጋጋሚ የመጥፋት ተግባርና በመኪና ቅስቀሳ ለማድረግ የተደረገ እንቅስቃሴ በፀጥታ ሀይሎች ጫና እየተደረገበት እንደሆነ ፓርቲው አስታውቋል፡፡
የኢህአዴግ አባላት ቤት ለቤት በመሄድ ህዝቡ ለእሁድ የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ እንዲወጣ ቅስቀሳ ማድረግ ላይ እንደሚገኙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
መንግስት እያስተባበረ የሚገኘው የሀይማኖቶች ጉባኤ ሰልፍ ህዝቡ አክራሪነትን እና ጽንፈኝነትን ለማውገዝ በሚል የተጠራ ቢሆንም እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ሌላ አቅጣጫ ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
ሁለት ቀን ብቻ የቀረው የእሁዱ የመንግስትና የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ በሀገሪቱ የፖለቲካ አካሄድ ከብዙ ዓመታት በኋላ ያጋጠመ ክስተት ተደርጎ ታይቷል፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።


ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው።
ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “የቀደምኩት እኔ ነኝ” በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፤ ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ፤ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን ተናግረዋል።
በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።
ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን ደረስ ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል።
ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፤ በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ ፤ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ለሰልፉ ሲዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር አልፈለጉም።
ከዚህም በላይ ሰንደቅ እንዳለው፤ የርዕሰ ደብር በሪሁን መግለጫ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ከነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን የሚያመለክት ነው። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ የማሳወቂያ ደብዳቤ፡ያስገባው ግን ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ/ም ነው።
ሀቁ ይህ ቢሆንም፤የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፦” የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም” ብለዋል።
አክለውም፦”ፓርቲው ሰልፍ የሚያካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው” ብለዋል።
ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ስላሳወቁበትን ቀን እና ስለ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተቃውሞ አቀረበ

ፓርቲው ከ33ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ጋር ተለያየ




በግንቦት ወር 2005 ዓ.ም. የመጀመሪያውን የተቃውሞ ሠልፍ ያካሄደው ሰማያዊ ፓርቲ፣ በመጪው እሑድ በሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተዘጋጀው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ተቃውሞ አቀረበ፡፡
ሁለተኛውንና በርካታ ሰዎች እንዳሚሳተፉበት ሲገልጽ የከረመውን ሰላማዊ ሠልፍ የሚያካሄደው ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. እንደነበር ፓርቲው አስታውቆ፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በተደራቢነት በዕለቱ ሠልፍ እንደሚያደርግ ያስተላለፈው ጥሪ ትክክል አይደለም ብሏል፡፡
yiliqalየሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ያስተላለፈውን፣ ‹‹አክራሪነትና ጽንፈኝነትን እናውግዝ›› የሚል የሠልፍ ጥሪ የተቃወመው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ከአንድ ወር በላይ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ሲያስተዋውቅና ጥሪ ሲያደርግ መክረሙን ገልጿል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ቀድሞ ማሳወቅ ለሚገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በደብዳቤ ማስገባቱን፣ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌታሁን ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡
‹‹እኛ በጠራነው ሰላማዊ ሠልፍ ላይ ሌላ ሠልፍ እንዲጠራ መፍቀድ መንግሥት በትንሹ የከፈተውን ቀዳዳ ለመዝጋት ፈልጐ ነው፤›› የሚሉት ሊቀመንበሩ፣ በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ሰላማዊ ሠልፍ መጥራት ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ እንዳልሆነላቸውና መንግሥት የጉባዔውን ሠልፍ እንዲሰርዝ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ቀንና ሰዓት የተጠሩ ሁለት የተለያዩ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰላማዊ ሠልፈኞች ሲገናኝ ወደ ግጭት ሊያመሩ ስለሚችል፣ መንግሥት ፓርቲው ቀድሞ መጥራቱንና ለሚመለከተው አካል ማሳወቁን በመገንዘብ ዕርምጃ እንዲወስድ፣ ፓርቲው ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም. አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ መግለጫ ማውጣቱን ኢንጂነር ይልቃል ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ሰማያዊ ፓርቲ ለበርካታ ወራት አንድነት ፓርቲን ጨምሮ ከ33 ፓርቲዎች ስብስብ ጋር ኅብረት ፈጥሮ ሲሠራ የቆየ ቢሆንም፣ ሰሞኑን ከስብስቡ እንዲወጣ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ ከ33ቱ ፓርቲዎች ስብስብ መገለሉን በሚመለከት አስተያየታቸውን ለሪፖርተር የሰጡት ኢንጂነር ይልቃል፣ ‹‹የሚያግባባን ነገር ሲገኝ በጋራ ሆነን ለመሥራት ተስማማን እንጂ፣ ማንም ተባራሪና አባራሪ የለም፡፡ መሰብሰባችን በስምምነት እንጂ የሕግ ድጋፍ ኖሮት የተደረገ ስምምነት አይደለም፤›› ብለዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሲሰጡ፣ ‹‹ለኢትዮጵያ ሕዝብና ፖለቲካ የሚመጥን የፖለቲካ ፓርቲ አለ ብለን አናምንም፤›› ማለታቸውና ሰማያዊ ፓርቲ እየጣረ ያለው ክፍተቱን ለመሙላት መሆኑን መናገራቸው ሌሎቹን ማስከፋቱ ይነገራል፡፡
የ33 ፓርቲዎች ስብስብ፣ ‹‹እንዴት እንደሌለን እንቆጠራለን?›› የሚል ጥያቄ አንስቶ እንደነበር መስማታቸውን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ ለምን እንደተናገሩ ጠርተው ሳያናግራቸው ስንቶቹ ተሰብስበውና በስንት ድምፅ ወስነው አብረው መቀጠል እንደማይችሉ ሳይገለጽላቸው ስለመለያየት ማውራት፣ ለእሳቸው የልጆች ጨዋታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹እኛ ከወጣን ከ33 ፓርቲዎች ስብስብ ውስጥ ሰው የሚያውቀውና ስሙ የሚታወቅ ፓርቲ ይኖራል እንዴ?›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነትን በአደባባይ መናገር ስላልተለመደ እንጂ ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹ለምን ተናገረ?›› በሚል አብሮ አለመሥራትን ማወጅ፣ ሕዝቡን ተስፋ ከማስቆረጥ ያለፈ ጥቅም እንደሌለው ኢንጂነር ይልቃል ጠቁመዋል፡፡ (ምንጭ: ሪፖርተር)

በመስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ እያወዛገበ ነው

‘‘ቀድመን ሰልፍ የጠራነው እኛ ነን’’ ሰማያዊ ፓርቲ
‘‘የቀደምነው እኛ ነን’’ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ
‘‘ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ የሚያካሂደው ሰልፍ ህገ-ወጥ ነው’’ የአ.አ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ የስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት
በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካከል የቀደምኩት እኔ ነኝ በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጉዳዩን በማስመልከት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።semayawiparty
እንደ ፓርቲው ሊቀመንበር ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተናግረዋል። በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን (ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም) ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል። ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ባለፈው ሰኞ (ነሐሴ 20 ቀን 2005) በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ሰልፉን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ምንም እንኳ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር ባይፈልጉም በዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በሰጡበት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች እና በ116 ወረዳዎች በተካሄደ ሕዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማ ደረጃ ነሐሴ 15 እና 16 ቀን 2005 ዓ.ም በተዘጋጀው ማጠቃለያ የሰላም ኮንፈረንስ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን እየታየ ያለው የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴ የሀገራችንን ልማት የሚያውክ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን የሚያናጋ እና የሃይማኖት መልክ የሌለው የጥፋት እንቅስቃሴ ከመሆኑም በላይ በሕገ-መንግስታችን የተደነገገውን የኃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የሚፃረር ስለሆነ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞአችንን እንግለፅ በማለት የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መንግስት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች፣ የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤም እንዲያስተባብር መወሰኑን ተናግረዋል።
ከዚህ መግለጫ መረዳት የሚቻለው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን መረዳት ይቻላል። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን አመልክቷል።
የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ ጉዳዩን በተመለከተ የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም ብለዋል። ሰልፉ የሚካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው ከማለት ውጪ ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ያሳወቁበትን ቀን እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል። (ምንጭ: ሰንደቅ)

የእኛ “መንግስት” (ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ)



August 29, 2013
“በእያንዳንዱም መንግስት የሚያድሩ ብዙ ልዩ ልዩ ነገዶች ይኖሩ ይሆናል፡፡ ስለ ሆነ መንግስት አንዱን ነገድ አጥቅቶ ሌላውን ነገድ ለመጥቀም ሥራው አይደለም፡፡ አስተካክለን ካሰብን ዘንድ መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡ ለአንዱ ነገድ ወይም ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት ለመንግስት የሚገባ ሥራው አይደለም” ይህንን መግቢያ የወሰድኩት በልዑል የኢትዮጵያ መንግስት አልጋ ወራሽ ተፈሪመኮንን ማተሚያ ቤት የካቲት 1 ቀን 1917 ዓ.ም ከታተመው የነጋ ድራስ ገብረ ሕይወት ባይከዳኝ‹‹መንግስትና የሕዝብ አስተዳደር›› መፅሀፍ ነው፤ ዛሬም ያለንበትን ዘመን ይዋጃልና፤ በተለይ ስለ‹‹ነገድ›› የተጠቀሰውን አርቀን ሰቅለን፣ ‹‹ለጥቂት ሰዎች ብቻ ማድላት›› የምትለዋን ሀረግ በወጉ ካጤንናት ለጊዜያችን በልክ የተሰፋች መሆኗን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፡፡J
እናም የስርዓቱን የአስተዳደር ዘይቤ ያለፍርሃት አደባባይ ካዋልነው የቀድሞ ገዥዎቻችን የተጓዙበትን ጎዳና እየተከተለ መሆኑን ለመተንተን የምሁራንን ጥናት መጠበቅ ግድ አይለም፤ ምክንያቱም ለዓመታት የተመለከትነው እውነታ የሚነግረን የአመራሩን እና በዙሪያው የሠፈሩ የጥቅም ተጋሪ ግለሰቦችን ብልፅግና ታሳቢ ያደረገ፣ ከታግሎ መጣል ህግ የተቀዳ፣ የራስ ሀገርንና የራስ ሕዝብን በምርኮ ያስገበረ ፖለቲካ መንበሩን ነው፤ ገብር፣ ገብር፣ ገብር…!!
ዛሬ መንገድ ዳር ረሀብ አዙሮ የጣለው ወንድምህ ስቃይ እንደ ጥላ የሚከተልህ፤ ህፃናት በትምህርት ገበታቸው ላይ በጠኔ ተሸንፈው መመልከቱ የሰርክ አሳዛኝ ክስተት የሆነብህ ከሰው ሰራሽ ችጋር፣ ከሰው ሰራሽ የቀዬ ፍንቀላ፣ ከሰው ሰራሽ እርዛት… የመነጨ መርገምት እንጂ የሰማይ ቁጣ አይምሰልህ፤ እመነኝ መለስም ሆነ ተተኪዎቹ ስኬት አድርገው የሚሰብኩትም ይህንን ነው፤ ‹ሀገር አቀናን!› የሚሉትም ይህንን ነው፤ ሰሞኑን የሚያሰለቹህ ተረኛ ምሁራንም ‹‹ትምህርትና ጤናን በተመለከተ መለስ ‹እልል› የሚያስብል ሥራ ሰርቷል›› የሚሉህ ጣራና ግድግዳ እየቆጠሩ ነው፤ ይህ አይነቱ መደዴ ሙገሳም ለፕሮፓጋንዳ የሚሆን ሪፖርት ለማዘጋጀት ከሚረዳ ቁጥር የዘለለ አበርክቶ አንደማይኖረው አትዘንጋ፡፡
እውነት እውነት እልሀለሁ፡- ይህ የሆነበት ብቸኛው ምክንያት መንግስት በስልጣን ላይ ስለሚቆይበትመንገድ ብቻ መጨነቅን ግዴታው በማድረጉ ነው፤ ይህንን ለመረዳትም እያገባደድን ባለው ክረምት የመንግስት ትኩረት በምን ላይ አንደሆነ የሚያሳይ ማስረጃን ጨርፌ ላሳይህ፡፡
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የእስልምና እምነት ተከታዮች መንግስት በሃይማኖታቸው ጣልቃ መግባቱን በመቃወም እና የታሰሩ ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ በመጠየቅ እያደረጉ ያለውን ትግል በሰላማዊ መንገድ አጠንክረው ሲቀጥሉ፤በተቃራኒው ‹‹ፀጥታ አስከባሪዎች›› አንዳንዴ በጥይት፣ አንዳንዴ በአስለቃሽ ጢስ፣ አንዳንዴ በማጋዝ…ምላሽ ሲሰጡ…
በርግጥ መንግስት ከኃይል እርምጃው በተጨማሪ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎችን (በምን አግባብቶ ወይም በምን አስፈራርቶ እንደሆነ ባይታወቅም) ወደ አደባባይ በማስወጣት መብት ጠያቂዎቹን ከ‹‹አክራሪ››ነት እና ‹‹ወሃቢዝም››ነት ጋር አያይዘው የውግዘት በረዶ እንዲያዘንቡባቸው እያደረገ ነው፡፡ ኢቲቪም ይህንን ኩነት እየተከታተለ ማራገቡን ቀጥሎበታል፤ ‹‹የቲፒ ከተማ ነዋሪዎች ‹አክራሪዎችን አወገዙ››፤ ‹‹በደቡብ ወሎ ኩታ በር ዞን አንድነት ፓርቲ ህገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰልፍ ተካሄደ››፤ ‹‹የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ‹የሼሁ ግድያ ድራማ አይደለም› አሉ፣ ‹የሼህ ኑሩ ኢልም ነው፣ የአሸባሪዎች ብር ነውም›ብለዋል››፤‹‹የመርሀቤቴ ነዋሪዎች ፅንፈኞችን በመቃወም የአቋም መግለጫ አወጡ››፤…
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- አንድነት ፓርቲ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የ‹‹ፀረ-ሽብር ሕጉ›› እንዲሰረዝና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የተቃውሞ ሰልፍ እና የአዳራሽ ስብሰባዎችን እያካሄደ ነው፤ መንግስትም አንዳንዴ የአፀፋ የድጋፍ ሰልፍ ሲያካሄድ፤አንዳንዴ የአዳራሽ ስብሰባዎች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ ‹መጋኛ› ሲሆንባቸው፤ አንዳንዴም የአስተባባሪዎቹን መኪና ጎማ ሲያፈነዳ፤ አንዳንዴም አዳራሽ ከልክሎ ሲያደናቅፋቸው… መዋሉ ፋታ የነሳው ይመስላል፤ በወላይታ የተጠራውን የአዳራሽ ስብሰባም ‹በጠቅላይ ሚኒስትሩ የትውልድ ቦታ እንዴት ተደርጎ!›› ያሉ ካድሬዎች የአንድነት ሰዎችን አዋክበው ስብሰባውን አክሽፈዋል፤
ክረምቱእንዲህእየተገባደደነው፡-ገዥው ፓርቲ ‹የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ አንደኛ ሙት ዓመት አከብራለሁ› በሚል መላ ኢትዮጵያን ችግኝ መትከያ፣ መላ ዜጎቿን ደግሞ ወደ አርሶ አደርነት በአስማት የቀየራቸው አስመስሏቸዋል፤ቴሊቪዥንና ራዲዮንም አስፈላጊነታቸው በየመንደሩ ችግኝ መተከሉን እየተከታተሉ መዘገብ ብቻ እስኪመስል ድረስ እንዲህ ሲሉ ጀምበር ወጥታ ትጠልቃለች፡- ‹‹የላይ አርማጮህ ነዋሪዎች ችግኝ ተከሉ››፣ ‹‹በመቀሌ ከተማ ‹ዘመቻ መለስ› በሚል የችግኝ ተከላ ተካሄደ››፣ ‹‹አቃቂ ኮረብታ ላይ በሚሊዮን የሚቆጠር ችግኝ በኦሮሚያ ፌደራል ፖሊስ አባላት ተተከለ፤ ቦታውም ‹መለስዜናዊ ኮረብታ› ተብሎ ተሰይሟል››፣ ‹‹በምዕራብ ሀረርጌ አስራ ሰባት ሚሊዮን፣ በወልበራ አስራ አራት ሚሊዮን ችግኝተ ተክሏል››፣ ‹‹በመንዝ ላሎ ወረዳ ተቆጥሮ የማያልቅ ችግኝ ተከላ ተደርጓል››፣ ‹‹የብአዴን አመራርና ካድሬ በባህር ዳር ከተማ በቢሊዮን የሚቆጠር ችግኝ ተከሉ፤ በፕሮግራሙ ላይ ጓድ አዲሱ ለገሰ ‹ችግኝ የምንተክለው አገሪቱ በአረንጓዴው ልማት በአለማችን ማግኘት የሚገባትን ቦታ እንድታገኝ ለማድረግ ነው› ሲል፣ ጓድ በረከት ስምዖን ደግሞ ‹ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአለማችን በአንድ ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ችግኝ እየተከሉ ያሉባት ብቸኛ ሀገር ናት› ብሏል››፤‹‹ዝክረ መለስ 1ኛ ዓመት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ከሐምሌ አስራ አምስት ቀን ጀምሮ ሁሉም ቀበሌዎች በስሙ ‹ፓርክ› ሰይመው ችግኝ ተከላ እያካሄዱ›› መሆኑን ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ከንቲባ መግለፁን የአማራ ክልል ብዙሃን መገናኛ ዘግቧል፤ ‹‹በወልቂጤ ከተማ በተደረገው ችግኝ ተከላ ላይም አንዲት ወጣት ‹መለስ ለሴቶች የተለየ አመለካከት ነበረው›› ማለቷም በዘገባው ተጠቅሷል፤ …ማን ነበር የመለስ ራዕይ ‹ችግኝ መትከል ነው› ያለው? …ኢህአዴግ ይሆን?
ከዚሁ ጎን ለጎን (አሁንም ሙት ዓመቱን ለማሰብ) በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች የእግር ጉዞ ተደርጓል፣ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓትም ተካሄዷል፤መነሻውን መቀሌ፣ መድረሻውን አዲስ አበባ ያደረገ ‹‹የመለስ ቱር አረንጓዴ ልማት›› የብስክሌት ውድድርም ሊጠናቀቅ ገና አንድ ሳምንት ይቀረዋል፤ በብሄራዊና ሀይማኖታዊ በዓላት ቀንለሃያ አንድ ጊዜ ይሰማ የነበረው የመድፍ ድምፅም፣ የመለስን አንደኛ ሙት ዓመት ለማብሰር ተተኩሷል፤ …በግድ አልቅሱ፣ በግድ ተዝካር አውጡ፣ በግድ ችግኝ ትከሉ፣ በግድ ተወያዩ፣ በግድ አደባባይ ውጡ፣ በግድ የፎቶ ግራፍ ኤግዚቢሽን ጎብኙ፣ በግድ.. ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ እና የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ ከአንድ ሺህ ሰባት መቶ በላይ ለሚሆኑ የዩኒቨርስቲ ከፍተኛ መምህራን ‹የአቅም ግንባታ ስልጠና› እየሰጡ ነው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምሁራኖቹን ማሰልጠን ያስፈለገበት ምክንያት ‹‹ብቃት ያለው ምርጥ የተማረ ኃይል ለማፍራት››መሆኑን ቢነግርህ አይግረምህ፤ ይህ ኢትዮጵያ ነውና የዐዋቂነት ማረጋገጫው መማር፣ ማንበብ፣ መመራመር… አይደለም፣ የፖለቲካውን ኃይል መያዝ እንጂ፤ ‹ስልጣን ላለው ሁሉምሚስጥረ-ጥበብይገለፅለታል› እንዲል አብዮታዊ ዲሞክራሲ መለስ ዜናዊም በሁሉም መስክ ‹አስተማሪ› ነበር፤ የህግ ባለሙያዎችን ሰብስቦ የሀገሪቱን ወንጀለኛ መቅጫ ህግ ትርጓሜ ሲተነትን ደጋግመህ ሰምተኸዋል፤ በቀጣዩ ቀን ደግሞ ለግብርና ባለሙያዎች ከውሃ ማቆር እስከ በላብራቶሪ የሚዳቀል ምርጥ ዘር ድረስ ባሉጉዳዮችዙሪያ የሁለት ቀን ማብራሪያ መስጠቱን ታስታውሳለህ፤ እመነኝ ተተኪው ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ነው እያደረገ ያለው፤ የሆነ ሆኖ ኃ/ማርያም ለምሁራኖች ከሙያቸው ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ጭምር በሰጣቸው ስልጠና ላይ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት ነበር ‹‹የኢንዱስትሪዎች በበቂ ሁኔታ አለመኖሩ፣ በክፍል ውስጥ የምናስተምረውን ንድፈ ሃሳብ በተግባር ለማሳየት እንቅፋት ሆኖብናል››፤ በርግጥጠቅላይ ሚንስትሩ‹‹መፍትሄ››ያለውን የተናገረው ብዙም ሳይጨነቅ ‹‹እኔ ኢንዱስትሪን ‹ዲፋይን› የማደርገው ግብርናም ኢንዱስትሪ ነው ብዬ ነው››በማለት ነበር፤…ግና!ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል በተጨባጭ አላብራራም፡፡ለምሳሌ ህክምና የሚያጠና ተማሪ በምን መልኩ በሞፈርና ቀንበር የተግባር ልምምድ ማድረግ እንደሚችል፤ወይም ፖለቲካ ሳይንስ የሚያጠና ተማሪ የተግባር ልምምዱን በግብርና ኢንዱስትሪ እንዴት ሊወጣው እንደሚችል? ማለቴ ነው፡፡
ለዓመታት በርካታ ምሁራን ብቃት አልባ ተማሪዎች እንደ ሰማይ ከዋክብት የመብዛታቸው መንስኤን ከትምህርት ፖለሲው ጋር የሚያነፃፅሩበትን ሀቲት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ባገኘው የሀገር መሪነት ስልጣን ገልብጦ በዩንቨርስቲ ቆይታው መምህራኖቹ የነበሩትንም ጭምር ‹‹አቅም አንሷችኋልና-እገነባችኋለሁ›› ሲል ከመስማት የከፋ እንደ ሀገር ክሽፈት የለም (በነገራችን ላይ ከወራት በፊት ለኃይለማርያም ደሳለኝ፣ በረከት ስምዖን፣ ቴውድሮስ አዳህኖም፣ ሶፍያን አህመድ በአጠቃላይ ሁሉም የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አንድ ህንዳዊ ፕሮፌሰር በኢህአዴግ ጽ/ቤት ‹‹ልማታዊ መንግስት›› እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል ሲተነትንላቸው፣ እነርሱም ደብተርና እስክርቢቶ ይዘው በንቃት ሲከታተሉ የቴሌቪዥ ዋና ዜና ሆኖ የቀረበበትን ምክንያት ዛሬም ድረስ ሊገለፅልኝ አልቻለም፤ በተለይም ፕሮፈሰር እንድርያስ እሸቴ ‹‹በቃሉ የፀና…›› በሚል ርዕስ መለስን አስመልክቶ በተዘጋጀ ዶክመንተሪ ፊልም ላይ ‹‹በዓለማችን ለመጀመሪያ ጊዜ ልማታዊ ስርዓተ መንግስት ‹ዴሞክራሲያዊ ሊሆን ይችላል፤ መሆንም አለበት› ብሎ በአደባባይ የተከራከረው እኔ እስከማውቀው ድረስ መለስ ነበር›› ማለቱን፣ ተተኪዎቹ ፍልስፍናውን ገና እየተማሩት ከመሆኑ አንፃር ስናየውሀገራችን ያለችበት ሁኔታ ጉዞው ወዴት ነው? ያስብላል፡፡ …ከቶስ በተማሪ ፖለቲከኛ የሚተዳደር ሕዝብ ከኢትዮጵያ በቀር ወዴት ይኖራል?)
ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- የህዳሴውን ግድብ ከዳር ለማድረስ በቂ ገንዘብ ስላልተገኘ ተደጋጋሚ የቦንድ ሽያጭ እየተካሄደ ነው፤ አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞችም በካድሬ ባልደረቦቻቸው ጫና በድጋሚ ቦንድ ለመግዛት መወሰናቸው ተሰምቷል፤ በርግጥ ከፍተኛ የኢህአዴግ የአመራር አባላት በአውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በመካከለኛው ምስራቅ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ቦንድ እንዲገዙ ለመቀስቀስ የአዘጋጇቸው ስብሰባዎች ‹‹ቅድሚያ የዜጎች መብት ይከበር›› ባሉ የሀገራችን ልጆች መክሸፉም የክረምቱ የመንግስት ዋና ሥራ ነው፤ ክረምቱ እንዲህ እየተገባደደ ነው፡- በነቢብ የኢትዮጵያ፣ በገቢር የገዥው ፓርቲ የግል ንብረት የሆነው ቴሌቪዥን ጣቢያ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ ከሃያ በላይ ‹‹ዶክመንተሪ ፊልም›› አሳይቷል (ገና ይቀጥላልም) በርዕሳቸው እንደሚከተለው እንዘርዝራቸው፡- ‹‹ኢፍቲን›› በሶማሊያ ላይ የሚያጠነጥን፣ ‹‹የጥቁር ህዝቦች ልሳን (መለስ በአፍሪካ)››፣ ‹‹ከፓን አፍሪካ እስከ አፍሪካ ህዳሴ›› የጠቅላይ ሚንስትር መለስን ህይወት የሚዳስስ፣ ‹‹ዘመነ አፍሪካ››፣ ‹‹የአፍሪካ ልሳን-መለስ››፣ ‹‹መለስ ማን ነው?››፣ ‹‹ሀገሬ-ቤቴ››፣ ‹‹ባለራዕዮቹ›› ስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ደውል›› እና ‹‹ደውል 2›› ህገወጥ-የሰዎች ዝውውርን በተመለከተ (በተለያያ ጊዜ የተላለፉ)፣ ‹‹የዲያስፖራ የልማት እንቅስቃሴ››፣ የካርታ ስራ ድርጅትን በተመለከተ፣ ‹‹የጥልቅ አስተሳሰብ ባለቤት›› በፕ/ር እንድርያስ እሸቴ ህይወት ዙሪያ የሚያጠነጥን፣ ምድር ባቡር ኮርፕሬሽንን በተመለከተ፣ ‹‹ያልተለመደ ጉብኝት›› የአዲስ አበባ አስተዳደር የአምስት ዓመት የመንግስት ግንባታዎችን በተመለከተ፣ ‹‹ሼህ ኑር ለምን ሞቱ?›› የደሴውን ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በተመለከተ፣ ‹‹የተስፋ ስንቅ››፣‹‹በቃሉ የፀና›› በድህረ መለስ ላይ የሚያተኩር፣ ‹‹ያልተጠኑ ገፆች›› በመለስ ዜናዊ ህይወት ዙሪያ (በርግጥ በዚህ ፊልም እህቱ ጠላ፣ ወንድሙ አንባሻ በመሸጥ መተዳደራቸውን በምስልም በድምፅም ማቅረቡ ምን የሚል መልዕክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደሆነ ለማወቅ ግራ ያጋባል፤ …ምናልባት እንዲያ እየዘረፈ ለቤተሰቦቹ ‹ሶልዲን› የማይሰጥ ‹ቆነቋና› ነበር ለማለት ይሆን? ወይስ ለአዜብ መስፍን ‹የወር ቀለባችንን እንቸገራለን› የአንድ ሰሞን ማስተዛዘኛ ምስክር ፍለጋ ነው?
በጥቅሉ ለኢህአዴግ ሕዝብን የማስተዳደር፣ ሀገርን የመምራት መገለጫ ይህ ነው፤ ሌላ አይደለም፤ ግና! ለዘመናት ያልተመለሱ ጥያቄዎቻችን ዛሬም መጮኻቸውን አላቋረጡምና እነሆ እንዲህ ቀጥለዋል፡- ሀገር ማስተዳደር ‹መለስ ጀግና ነበር› እያሉ ማሰልቸት ነውን? የመንግስትስ ስራ (ግዴታ) ምንድር ነው? ሀገሪቱን ‹‹መለስ-ፓርክ›› ወደሚል ስያሜ ከመቀየራችሁ በፊት፣ ለጤፍ ዋጋ አለቅጥ መናር ምክንያቱን ስለምን መመርመር ተሳናቸው? ሀገሪቱን በ‹አራጣ› እንደያዘ ስግብግብ ነጋዴ በሚሊዮኖች ህይወት ላይ የማይሞላ ‹ሳፋ› ደቅኖ አዋጣ፣ ግዛ፣ ክፈል፣ ገብር… እያለ የሚያስጨንቀው ማን ነው? ስለመለስ ‹የሃሳብ ምጡቅነት› መስካሪ ምሁራኖቻችን ለጎዳና ኑሮ የተዳረጉ ኢትዮጵያውያን ስንት ሚሊዮን እንደደረሱ እና እልፍ አላፍት ታዳጊዎቻችን በሴተኛ አዳሪነት እንደተሰማሩ የምትነግሩን መቼ ነው?እንዲህ የመሆኑ ምክንያትስ በማን ይሆን? ‹የሁለት ዲጂቱ›ዕድገት ሸክምን የማለዘብ አቅም ከሌለውፋይዳው ምንድር ነው? ‹ሳቅ ትዝታ› ስለሆነባቸው ጎጆዎች ለምን አትነግሩንም? መለስ ‹ያለመለማት› ኢትዮጵያ ወዴት ትሆን? ‹ፖለቲካ› ማለትስ ይህ ነውን? …ነጋ ድራስ ገ/ህይወት እንዳሉት ‹‹…መንግስት መቆሙ ለሕዝቡ ሁሉ ጥቅም ነው፡፡ ጥረቱም ህዝቡን ሁሉ በትክክል ለመጥቀም ያልሆነ መንግስት ሊቆም አይችልም፡፡›› የመተራረሚያው ጊዜም በጣም ያለፈ ይመስለኛል፡፡ አገዛዙን ‹እንደ መንግስት› መቀበሉም እንዲሁ፡፡

የአዲስ አበባ መስተዳድር ሰማያዊ ፓርቲ በመጪው እሁድ ሰልፍ የሚያደርግ ከሆነ፤ሰልፉ ህገወጥ ነው አለ።

ኢሳት ዜና :- ሰንደቅ እንደዘገበው በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው።
ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “የቀደምኩት እኔ ነኝ” በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
ስለጉዳዩ ተጠየቁት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ፤ ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ፤ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ሊቀመንበሩ ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን ተናግረዋል።
በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል።
ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን ደረስ ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል።
ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን የተናገሩት ሊቀመንበሩ፤ በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ ፤ በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ለሰልፉ ሲዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር አልፈለጉም።
ከዚህም በላይ ሰንደቅ እንዳለው፤ የርዕሰ ደብር በሪሁን መግለጫ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ከነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን የሚያመለክት ነው። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ የማሳወቂያ ደብዳቤ፡ያስገባው ግን ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ/ም ነው።
ሀቁ ይህ ቢሆንም፤የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ፦” የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም” ብለዋል።
አክለውም፦”ፓርቲው ሰልፍ የሚያካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው” ብለዋል።
ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ስላሳወቁበትን ቀን እና ስለ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

Tuesday, August 27, 2013

የአንድነቶች ሰላማዊነት ጽናት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮሚያ!

ግርማ ሞገስ (girmamoges1@gmail.com)
ሰኞ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም.
“አንድነት ፓርቲ ሳይገድል እየሞተ ህገ-መንግስቱን የማስከበር ሰላማዊ ትግሉን አጠንክሮ ዛሬም ወደፊትም ይቀጥላል፡፡” የሚለውን መርሃቸውን አንድነቶች ካስተዋወቁን ከርመዋል። ባለፈው ሳምንት በባሌ ሮቤ እና በፍቼ ኦሮምያ የተተከሉት መረን የለቀቁ አምባገነን አስተዳደሮች እና ደህንነቶች የፈጸሙባቸውን ወደር የለሽ የአንደበት፣ የሳይኮሎጂ እና የአካል ጥቃት በፈገግታ በመቀበል እየሞቱ ሳይገድሉ በሰላማዊ ትግል ህገ-መንግስቱን ለማስከበር ያላቸውን ጽናት ደግመው አሳይተውናል አንድነቶች። አንድነቶች የሚሰብኩትን የሚፈጽሙ መሆናቸውን ኢትዮጵያ እንደገና ባለፈው ሳምንት ተመልክታለች። የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች አረመኔነት አሳፋሪ ነበር። በፍጹም የስልጣኔ አየር የነፈሰባቸው አይመስሉም። ዘመናዊ አስተሳሰብ ለአንድ ቀንም የጎበኛቸው አይመስሉም። ይባስ ብሎ የባሌ ሮቢ እና የፍቼ አስተዳዳሪዎች እና ደህንነቶች ከህጋዊ የመንግስት መዋቅር ውጪ ጸረ-ነፃነት ወረበሎች (ቦዘኔዎች) ያደራጁ ይመስላሉ። ይኽ ጉዳይ ጥናት ሊደረገበት ይገባል።udj bale robe
በባሌ ሮቢ ኦሮሚያ ያየነው አፈና እስከአሁን በሰሜን ኢትዮጵያ እና በደቡብ ኢትዮጵያ ካስተዋልናቸው አፈናዎች ሁሉ ዘግናኝ ነበር። የመቀሌው አፈና የተፈጸመው የድምጽ ማጉያ በመከልከል፣ የመቀስቀሻ በራሪ ወረቀቶችን በመንጠቅ፣ እና አንድነቶችን በማሰር እንደነበር እናስታውሳለን። የባሌ ሮቤ አምባገነኖች ግን ህውሃት በመቀሌ የፈጸመውን በሙሉ ቢፈጽሙም የአንድነቶችን በታጋሽነት እና በጽናት የታነጸ ሰላማዊ ትግል ሊያቆሙት አለመቻላቸውን ሲገነዘቡ ተራ ማስፈራራት ጀመሩ። ሐሙስ ነሃሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ተወካዮች ከባሌ ሮቤ ከተማ ከንቲባ፣ ምክትል ከንቲባ፣ የፀጥታ ዘርፍ ሃላፊ እና ከከተማው ካቢኔዎች ጋር 3 ሰዓት የፈጀ ውይይት አደረጉ። በዚኽ ውይይት ላይ ነበር የባሌ ሮቢ ባለስልጣኖች “አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን ማድረግ አይችልም፤ እኛ ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ ስጋት አለብን፡፡ የቀድሞው ጠ/ሚር አቶ መለስ በፓርላማ እንደተናገሩት በአካባቢያችን የአልቃይዳ ክንፍ አለ” የሚል ማስፈራሪያ አዘል በማሰማት ለሰላማዊ ሰልፉ ትብብር መንፈጋቸውን የገለጹት። እሁድ በተቃረበ ቁጥር የባሌ ሮቤ አምባገነኖች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ግለቱ እየጨመረ ቢሄድም አንድነቶችን ሊያስቆም አልቻለም። በዚኽን ጊዜ “እሁድ የገበያ ቀን ስለሆነ ሰልፍ ማድረግ አይቻልም። ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገ ደም ይፈሳል።” ማለት ጀመሩ የባሌ ሮቢ ባለስልጣኖች።
የአንድነቶችን ጽናት፣ ትዕግስት፣ ሰላማዊነት እና ቁርጠኛነት መስበር እና ሰልፉን ማሰናከል አለመቻላቸውን ሲገነዘቡ የባሌ ሮቤ ባለስልጣናት ቅዳሜ ምሽት ለእሁድ አጥቢያ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች እና አባላትን ካረፉበት ሆቴል በግዳጅ አስወጥተው አገቱ። በዚኽን ጊዜ ነበር የቀሩት አንድነቶች ሰላማዊ ሰልፉ እንዳይደረግ የወሰኑት። የመጣው ይምጣ ብሎ ሰልፍ በመውጣት በመሃይም አምባገነኖች የሰለጠነ የሰላም ትግል ሰራዊት ማስመታት ስህተት ነው። ሰላማዊ ሰልፉ እንዲቀር መደረጉ ትክክለኛ ውሳኔ ነው። በድስፕሊን የታነጹ ሰላማዊ ትግል መሪዎች ገና ዘመቻውን ሲጀምሩ መቼ ማቆም እንዳለባቸውም ጭምረው ያውቃሉ። ይኽ ብስለት ያላቸው ጀግኖች የሚያደርጉት ማፈግፈግ ነው። በዚኽ አይነት ነበር እሁድ ቀን ነሐሴ 19 ቀን 2005 ዓ.ም. በባሌ ሮቤ የታቀደውን የሚሊዮኖችን ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ የታፈነው። በዚኽ አይነት ነበር በባሌ ሮቤ አካባቢ አለ ሲሉን የነበረው ሽብርተኛ የአልቃይዳ ቅርንጫፍ እራሳቸው የባሌ ሮቤ ባለስልጣኖች መሆናቸውን ያረጋገጡልን። ይኽ ሁሉ ሲፈጸም የባሌ ሮቤ ወጣቶች ከአንድነት ፓርቲ ጎን መቆማቸውን ኢትዮጵያችን ልታውቅ ይገባል።
ፍቼ ሌላዋ ከተማ ናት። የመጀመሪያው ሁለት አባላትን ይዞ ፍቼ የገባው የሰላማዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ቡድን በፍቼ አስተዳደር እና ደህንነት ካድሬዎች ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመበት። የእጅም የእግርም ጉዳቶች ደርሰባቸው ሁለቱ የዴሞክራሲ ሰራዊቶች። አንድነቶች በደረሰው ጥቃት አልተፈቱም። እንዲያውም ጊዜ ሳያባክኑ አዲስ ቡድን ወደ ፍቼ በመላክ ለነሐሴ 19 ቀን ያቀዱትን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ ለማሳካት ጎንበስ ቀና ማለት ጀመሩ። በዚኽ እርምጃቸው አንድነቶች በማይነቃነቅ ድስፕሊን የታነጹት የሰላማዊ ትግል ሐዋርያት መሆናቸውን ለፍቼ ህዝብ አሳዩ። እየሞቱ ሳይገሉ ህገ መንግስታዊ መብት ለማስከበር ያላቸውን ቁርጠኛነት አንድነቶች አስመሰከሩ። አንድነቶች የሚሉትን የሚፈጽሙ የሰብዓዊ መብቶች አስከባሪ ወታደሮች መሆናቸውን ፍቼዎች በአድናቆት አስተዋሉ። ይኽን ያስተዋሉት የፍቼ ወጣቶች ለአንድነቶች ትብብር መለገስ ጀመሩ። የፍቼ አስተዳደር እና ደህንነቶች ያሰማሩዋቸው ቦዘኔዎች በፍቼ ከተማ የሚገኘውን የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ለመስበር ሲሞክሩ የፍቼ ወጣቶች ድርጊቱን በመቃወም ከአንድነቶች ጎን ተሰለፉ። በፍቼ የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍም ቢሆን በአንድነቶች እና በፍቼ ወጣቶች ሰላማዊነት እና ጽናት የተገኘ እንደነበር ኢትዮጵያ በአድናቆት አስተውላለች።
ሶስተኛው የእሁድ ነሃሴ 19 ቀን 2005 የሚሊዮኖች ድምጽ ለነጻነት ዘመቻ እቅድ በአዳማ/ናዝሬት ከተማ ማድረግ እንደነበር ይታወቃል። ይሁን እንጂ የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከአንድነት ፓርቲ ለተጻፈለት ደብዳቤ ነሃሴ 19 በከተማው ስብሰባ መኖሩ እና የኃይል እጥረትም እንዳለበት ጠቅሶ ሰላማዊ ሰልፉን አንድነት ፓርቲ ወደ ጷጉሜ 3 ቀን 2005 ዓ.ም እንዲያዛውር ጠይቋል። አንድነት ፓርቲም የቀረበለትን ጥያቄ መቀበሉን ገልጿል። የአዳማ/ናዝሬት ከተማ አስተዳደር ህገ መንግስታዊ እውቅና ካለው አንድነት ፓርቲ ጋር በዚኽ አይነት ስልጡን እና ተራማጅ መንገድ ከስስምምነት መድረሱ ከባሌ ሮቤ እና ከፍቼ ከተማዎች አምባገነን አስተዳዳሪዎች ፍጹም የተለየ አድርጎታል። ከሁለቱ ከተሞች አስተዳደሮች የአዳማ ከተማ አስተዳደር የተሻለ መሆኑን ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሁን አልመ አስተውሏል። በዚኽ እርምጃው የአዳማ/ናዝሬት አስተዳደር ሊመሰገን ይገባዋል። ሊኮራም ይገባዋል። ኋላቀሮቹ የባሌ ሮቤ እና የፍቼ አምባገነን አስተዳደሮች ሊያፍሩ ይገባል። የሚያስተዳድሩትን ህዝባቸውን በንቀት አፍነውታል። እነዚህን ሁለት ከተሞች ለጉብኝትም ሆነ ለንግድ የሚጓጉ ከተሞች እንዳይሆኑ አድርገዋል እነዚህ አስተዳዳሪዎች። የሚያስተዳድሩትን ህዝብ እና የቀረውን አለም ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል። በእነዚህ እና በመሳሰሉት ከተሞች ላይ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የሚፈሰው ገንዘብ ከምንጩ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል። ከምንጩ ስል ለጋሽ አገሮችን ይጨምራል። ተዳባዳቢነት ዴሞክራሲያዊነት አይደለም! መሃይምነት ነው።
ለአንባቢያን፥
“እየሞትን ሳንገድል ህገ-መንግስት የማስከበር ሰላማዊ ትግላችንን እንቀጥላለን” የሚለው የአንድነቶች መርህ ከምራቸው እንደሆነ ባልፈው ሳምንትም አስተውለናል። ፍጹም ሰላማዊነታቸው እና የመርህ ጽናታቸው በሚፈጸምባቸው የአካል ድብደባ እንደማይነቃነቅ ፍቼ ላይ አይተናል። በዚኽ ባለፈው የፈተና ሳምንት አንድነቶች መኪና በመከራየት፣ ወረቀቶች በማሳተም፣ ለህክምና ወጪ ባማድረግ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ብዙ ወጪዎች እንዳደረጉ መገንዘብ አያዳግትም። ትግሉ የጋራ በመሆኑ ቋሚ ተመልካች መሆን ያዳግታል። የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል ለምንል በሙሉ የዳር ተመልካች መሆን ያዳግተናል። በባሌ ሮቤ እና በፍቼ በአንድነቶች ላይ የደረሰውን አይተን እና ሰምተን እጃችንን አጥፈን መቀመጥ ህሊናችንን ያዳግተዋል። የዜግነት ሚና መጫውት ያልጀመርን መጀመር፣ የጀመርን ደግሞ መቀጠል አለበን። ተሳትፎዋችንን ማሳደግ አለብን። አንድነቶች አንድም ክፉ ቃል ሳይሰነዝሩ እና ፈገግታ ከፊታቸው ሳይለያቸው ይኽን ሁሉ ስቃይ የሚቀበሉት ለግላቸው ብር ለማካበት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። እየሞቱ ሳይገድሉ በአምባገነነኑ መለስ የረቀቀውን ፀረ-ሽብር ህግን ለማሰረዝ እና የኢትዮጵያችንን የፖለቲካ ትግል ባህል ለመቀየር እንደሆነ ልቦናችን ያውቀዋል። ስለዚህም አንድነቶች የጀመሩትን የሚሊዮኖች ድምጽ ለነፃነት ዘመቻ በመቀላቀል ታሪክ እንስራ።
የሚከተሉትን በማድረግም አንድነቶች መሰራት የጀመሩትን ታሪክ መቀላቀል እንችላለን።
እርዳታ፥ በገንዘብ!
እርዳታ፥ በአሳብ!
እርዳታ፥ መረጃዎች በፍጥነት በማሰራጨት!
እርዳታ፥ ፊርማዎች በማሰባሰብ!
እርዳታ፥ እንደገና በገንዘብ!
ፊርማ ለማስቀመጥም ሆነ ገንዘብ ለመላክ ይኽን የአንድነቶች ድረ ገጽ ይጎብኙ፥ www.andinet.org

Saturday, August 24, 2013

ከአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ ዓመት 100 ዳኞች ለቀቁ


መረጃው የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው” የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት
ዘንድሮ ብቻ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በዳኝነት ሙያ ያገለግሉ የነበሩ መቶ ዳኞች ስራ መልቀቃቸውን ምንጮች ገለፁ፡፡ ከ86 በላይ ዳኞችም የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተው መልስ እየተጠባበቁ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ የኔነህ ስመኝ በበኩላቸው፤ መረጃው የተሳሳተና ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡፡ “እንደማንኛውም መስሪያ ቤት አንዳንድ መልቀቂያዎች ይገባሉ፤ ይስተናገዳሉ” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በተጠቀሰው መጠን ዳኞች ስለመልቀቃቸውም ሆነ መልቀቂያ ስለማስገባታቸው የማውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡
ዳኞቹ በደሞዝ ማነስ ፣በጥቅማጥቅም ማጣት፣በእርከን እድገት አለመኖርና በስራቸው ላይ በሚደርስባቸው ጣልቃ ገብነት ከስራ ለመልቀቅ መገደዳቸውን ምንጮቹ ገልፀው፣ በቅርቡ የገቡ መልቀቂያዎች ከሶስት ወር በፊት እንደማይስተናገዱ እየተነገራቸው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ “በክልላችን የዳኛ ደሞዝ ከፖሊስ ደሞዝ ያንሳል” ያሉት አንድ ስራ የለቀቁ ዳኛ፤ የፖሊስ የስራ ሂደት 2800 ብር ደሞዝ ሲያገኝ ዳኛ ግን 2639 ብር ብቻ እንደሚያገኝ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
የዳኝነት ስራ የህሊና ስራ እንደመሆኑ አንድ ዳኛ ለአድልኦና ለጉበኝነት እንዳይጋለጥና ፍትህ እንዳያዛባ ምቹ ሁኔታዎች ሊፈጠሩለት ይገባል ያሉት ምንጮቹ፤ በክልሉ ይህ ስለማይመቻች ፍትህ ከማዛባት ስራውን መልቀቅና መቸገር ይሻላል በሚል ዳኞች ስራ እንደለቀቁና ሌሎችም ለመልቀቅ ማመልከቻ እያስገቡ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ም/ቤቱ የዳኞች በብዛት መልቀቅ ስላሳሰበው ስብሰባ ካደረገ በኋላ ዳኞች በስራቸው ላይ እንዲቆዩ ጭማሪ ይደረግላቸው ብሎ መወሰኑን የጠቆሙ ሌላ ሥራ የለቀቁ ዳኛ፤ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላሉት 500 ብርና ከዚያ በላይ ሲጨመርላቸው ታች ሆነው ብዙ ለሚሰሩትና ለሚደክሙት ግን በ150 ብር ጭማሪ ብቻ መሸንገላቸው ዳኞችን አበሳጭቷቸዋል ብለዋል፡፡ ይህም ለመልቀቃቸው ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፍ/ቤቱ በየአመቱ ከስልጠና ማዕከል የሚወጡ ዳኞችን እንደሚቀበል የገለፁት ምንጮቹ፤ እነዚህ ዳኞች ሲቀጠሩ በፍ/ቤት ሁለት አመት የማገልገል ግዴታ እንዳለባቸውና ሁለት አመቱን ሳይጨርሱ ከለቀቁ 50 ሺህ ብር እንደሚቀጡ ጠቁመው፤ ሙያተኛው ላይ የሚደረግ ጫና መቆም አለበት ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “ከሙያው ስነ-ምግባር የተነሳ ዳኛ ትርፍ ስራ መስራት አይችልም” ያሉት እነዚሁ ዳኞች፤ በዚህ የተነሳ የዳኛው ህይወት ከኑሮ ውድነቱ ጋር መጣጣም አልቻለም ብለዋል፡፡ በሌላው የመንግስት መስሪያ ቤት የተለያዩ ማበረታቻዎችና የደሞዝ እርከን ጭማሪ እንደሚደረግ ጠቁመው፣ በፍ/ቤት አካባቢ ይህ አይነት አሠራር የለም፣ አስር አመት የሰራም ሆነ ዛሬ የተሾመ ዳኛ እኩል ደሞዝ ነው ያላቸው ብለዋል፡፡

ኖርዌይ ኤምባሲ እና ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው


ኖርዌይ ኤምባሲ እና  ኢ/ር ኃይሉ እየተወዛገቡ ነው
 
“ያከራየኋቸውን ቤት ለመልቀቅ እምቢተኛ ስለሆኑ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቄያለሁ”
- ኢ/ር ኃይሉ
ኖርዌይ ኤምባሲ ከኢ/ር ኃይሉ ሻውል የተከራየውን ባለ ሁለት ፎቅ የመኖሪያ ህንፃ ለ15 አመታት ሲጠቀምበት እንደቆየ የገለፁት የአዲስ አድማስ ምንጮች፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል ውዝግብ የተፈጠረው ቤቱን ልቀቅ፣ አልለቅም በሚል ነው ብለዋል፡፡ በ97 ምርጫ የምርጫ ዘመቻ ቅንጅትን በፕሬዚዳንትነት የመሩት ኢ/ር ኃይሉ ሻውል፣ ከኤምባሲው ጋር በነበራቸው የኪራይ ውል መሰረት ከ7 ወራት በፊት ቤቱን እንዲያስረክባቸው እንደጠየቁ ተናግረዋል፡፡ በ3200 ካሬ ሜትር ግቢ ውስጥ የተሰራው ባለ ሁለት ፎቅ መኖሪያ ህንፃ በ1200 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው፡፡
ቤቱን ስለምንፈልገው ልቀቁልን በማለት ከሰባት ወራት በፊት በደብዳቤ ብንጠይቅም፤ ኤምባሲው ለመልቀቅ ፈቃደኛ አልሆነም የሚሉት ኢ/ር ሃይሉ፣ ከአንድ አመት በፊትም ኤምባሲው ቤቱን እለቃለሁ ቢልም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ብለዋል፡፡ “ቤቱን በትክክል ከፈለጋችሁት ግዙን” በማለት ለኤምባሲው አማራጭ አቅርበው ተቀባይነት እንዳላገኘም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ጉዳዩን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቃቸውን ኢ/ር ኃይሉ ጠቅሰው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ኤምባሲው ቤቱን እንዲለቅ ጥያቄ አስተላልፏል ብለዋል፡፡
“ህግና ስርዓትን ተከትዬ ቤቱን እንዲለቁ በትዕግስት ጠብቄያለሁ፡፡ እምቢ ካሉ በግል ንብረቴ ከእነርሱ ጋር እንካ ሰላንቲያ አልገጥምም” ያሉት ኢ/ሩ፤ ጥቁርን በመናቅና በማን አለብኝነት የሚካሄደውን ህገወጥነት ፈፅሞ አልቀበልም ብለዋል፡፡ ኤምባሲው የያዘብኝ ቤት ከመኖሪያ ቤቴ ጋር በአጥር ስለሚገናኝ በቤቴ በኩል አፍርሼ በመግባት ግቢውን ለማስተካከል ወስኛለሁ ብለዋል ኢ/ር ኃይሉ፡፡ ወደ ኤምባሲው በተደጋጋሚ ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ምክትል አምባሳደሯን ለማነጋገር ብንሞክርም “አሁን ቴሌ ኮንፈረንስ ላይ ነኝ፤ ማናገር አልችልም” የሚል ምላሽ በፀሀፊያቸው በኩል ተናግረው፤ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
ስለዚሁ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፕሮቶኮል ክፍል ደውለን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሀላፊ ለማግኘት ሙከራ ብናደርግም ለስብሰባ ከግቢ ውጭ ናቸው በሚል ምላሽ ልናናግራቸው አልቻልንም፡፡
addis admas

Friday, August 23, 2013

የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን ቤት ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ እንደሚፈጅ አንድ ሰነድ አመለከተ


ኢሳት ዜና :- በከንቲባ ድሪባ ኩማ የሚመራው አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰሞኑን ይፋ ባደረገው ረቂቅ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የኮንዶሚየም ቤት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ጠቆሟል።
አስተዳደሩ ለኮንዶሚየም ቤቶች ብቻ ከ800ሺ በላይ ዜጎችን ቢመዘግብም በቀጣይ አምስት ዓመት ለመስራት ያቀደው 178 ሺ ቤቶችን ብቻ ነው፡፡
አስተዳደሩ ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም ሥራ ላይ አውለዋለሁ ባለው የስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ የቤቶች ልማትን በተመለከተ የያዘው ዕቅድ እጅግ አነስተኛ ሆኖ መገኘት በየደረጃው ያሉ አባላትና ካድሬዎችን ጭምር አስደንግጦአል፡፡
በአሁኑ ወቅት 20 በ80 በሚባለው የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤት ለመሆን ከ800ሺ በላይ ነዋሪዎች ተመዝግበው እየተጠባበቁ ባሉበት ሁኔታ በአምስት ዓመት 178ሺ ቤቶችን ብቻ እገነባለሁ በሚለው ስሌት ሲታሰብ 800ሺ ተመዝጋቢውን ለማዳረስ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ የሚፈጅ መሆኑ ሕዝቡን በከፍተኛ ደረጃ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነው ተብሎ ተሰግቶአል፡፡
የቤቶች ልማት ቢሮው ይህን ዕቅድ የያዘው የአስተዳደሩን አቅምና የእስካሁኑን የግንባታ ልምድ ግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑን መረጃው ያመለክታል፡፡ የኩማ አስተዳደር በአምስት ዓመት ቆይታው 36ሺ700 ከባለአደራ አስተዳደር የተረከበውን ቤቶች ጨምሮ በጠቅላላው በሰልጣን ጊዜው መገንባት የቻለው 175ሺ246 ያህል ቤቶችን ብቻ ነው፡፡
ፕሮግራሙ ከተጀመረ ባለፉት ስምንት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለተጠቃሚዎች የተላለፉ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ብዛት 100 ሺ 559 ያህል ነው፡፡ አዲሱ ዕቅድም ሲሰራም ይህን የመገንባት አቅም ታሳቢ አድርጎ መሆኑን ታውቋል፡፡
ይህ ረቂቅ ዕቅድ የአስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ሰሞኑን በየደረጃው ላሉ የአስተዳደር አካላት ለውይይት በቀረበበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ አንዳንድ ተሰብሳቢዎች በዚሁ መድረክ ላይ ይህን ዕቅድ ሕዝቡ አይቀበለንም፣ ማሳመንም አንችልም በሚል ተሻሽሎ እንዲቀርብ ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በአዲሱና አወዛጋቢ በነበረው የሊዝ አዋጅ መሠረት በቀጣይ አምስት ዓመታት በአዲስአበባ ብቻ ካሉ ነባር ባለይዞታዎች ግማሽ ያህሉን ወደሊዝ ሥርዓት ለማስገባት የተያዘው ዕቅድም በተመሳሳይ ሁኔታ በራሱ አመራር አባላት ተቃውሞ ገጥሞታል።
የሊዝ አዋጁ ነባር ይዞታን በተመለከተ ይዞታዎች ሲሸጡ ወደአዲሱ የሊዝ ሥርዓት እየገቡ እንደሚሄዱ ቢደነግግም  አስተዳደሩ በምን መልኩ 50 በመቶ ያህል ነባር ይዞታዎችን ወደሊዝ ሥርዓት ለማስገባት እንዳቀደ ግልጽ አይደለም ፡፡
የስብሰባው ተካፋዮችም ይህ የሊዝ ጉዳይ አገር አቀፍ ሕግ ሆኖ ሳለ በአዲስአበባ ይጀመር የመባሉ ጉዳይ እና የአፈጻጸሙ ሁኔታ የህዝብን ድጋፍ ያሳጣል በሚል ሳይቀበሉት ቀርተዋል፡፡ ይህ የአምስት ዓመት የስትራቴጂክ ዕቅድ በቀጣይ ህብረተሰቡ ተወያይቶበት ስራ ላይ ይውላል ተብሎአል፡፡

Thursday, August 22, 2013

ህወሓት ወያነ አይደለም! Abraha Desta


ህወሓትን ለመጥቀስ ‘ወያኔ’ የሚለው ቃል ተጠቅሜ አላውቅም። ከወራት በፊት ታድያ ለምን ‘ወያነ’ የሚል ቃል እንደማልጠቀም አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ በውስጥ መልእክት ልኮልኝ ነበር። በሆነ ምክንያት መልስ አልሰጠሁም ነበር።
አሁን ግን ትንሽ ልበል። ምክንያቱም ከሁለት ቀናት በፊት ከዞን ዘጠኝ አባላት (ጓደኞቼ) በአካል ተገናኝተን ‘ወያነ’ ስለሚለው ቃል ተጫውተን ነበር። ርእሰ ጉዳዩ ‘የህወሓት /ኢህአዴግ መንግስት ወያነ እንዲባል አይፈልግም፤ ወያነ ብለው ለሚፅፉ ወይ ለሚናገሩ ሰዎች በተለየ ሁኔታ ይጠምዳል’ የሚል ነበር።
እኔ ግን በዚህ ሓሳብ በከፊል አልስማማም። ምክንያቱም ህወሓቶች ‘ወያነ’ የሚል ስም አይጠሉትም። የሚኮሩበት ስማቸው ነው። ‘በህወሓት ምትክ ‘ወያነ’ የሚል ቃል የሚጠቀሙ ዜጎች በጥቁር መዝገብ ውስጥ ይገባሉ’ በሚል ግን እስማማለሁ። ምክንያቱም አንድ ሰው ህወሓትን በመጥፎ ለማንሳት ፈልጎ ‘ወያኔ’ የሚል ቃል ሲጠቀም የህወሓት መሪዎች ሁለት ነገሮች ይገነዘባሉ።
(አንድ) ያ ‘ወያኔ’ የሚል ቃል የሚጠቀም ሰው ከትግራይ አለመሆኑ ይገነዘባሉ። ምክንያቱም ከትግራይ ከሆነ ትግርኛ ቋንቋ ይችላል። ትግርኛ ከቻለ ‘ወያነ’ የሚለው ቃል ትርጉሙ ያውቃል። የወያነ ትርጉም ካወቀ ህወሓትን ለመስደብ ‘ወያነ’ የሚል ቃል መጠቀም አይችልም። ምክንያቱም ‘ወያነ’ የትግርኛ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‘አብዮተኛ፣ ለጭቆና የማይምበረከክ፣ መንግስትን ለመቃወም ድፍረት ያለው፣ የማይፈራ፣ ጨቋኝ ስርዓት ለመጣል የሚታገል’ ማለት ነው።
ስለዚህ ‘ወያነ’ የሚለው ቃል ስድብ ወይ አፀያፊ ቃል አይደለም። ለዚህ ነው ትግርኛ ተናጋሪዎች ለህወሓት ወያነ ብለው መሳደብ የማይችሉት። ምክንያቱም ‘ወያነ’ ካሉ እያሞካሹ እንጂ እየተሳደቡ አይደሉም።
(ሁለት) ህወሓትን ለመንቀፍ ወይ ለመቃወም ‘ወያነ’ የሚል ቃል የሚጠቀሙ ዜጎች በህወሓትኛ አተረጓጎም ‘ፅንፈኛ ተቃዋሚዎች’ ተደርገው ይወሰዳሉ። ህወሓትም ለስልጣኑ ሲል እነኚህ ሰዎች በልዩ ሁኔታ ይጠምዳቸዋል። ምክንያቱም ‘ወያነ’ ካሉ ለህወሓት ልዩ ጥላቻ እንዳላቸው ይረዳል። ህወሓት ወያነ እንዲባል ስለማይፈልግ ግን አይደለም።
‘ወያነ’ የሚል ቃል የትግርኛ ቋንቋ አንድ አካል እንጂ ለህወሓት ብቻ የተሰጠ ስም አይደለም። በቋንቋው መሰረት ጭቆናን ለማስወገድ የሚታገል ሁሉ ወያነ ተብሎ ይጠራል። ህወሓቶች በትግሉ ወቅት የትግራይን ህዝብ ለማነሳሳት የተጠቀሙት ዋነኛ ቃል ‘ወያነ’ ነው። ወያነ ስትባል የተለየ የጀግንነት ስሜት ይሰማሃል። በዚህ መሰረት ‘ወይን’ እያሉ ብዙ ሰው ከጎናቸው ማሰለፍ ችለው ነበር።
ለዚህ ነው ህወሓትን ለመሳደብ ወያነ የማልለው። (1) መሳደብ አያስፈልግም (2) ‘ወያነ’ የሚል ቃል ለማወደስ እንጂ ለመውቀስ እንደማይሆን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ለህወሓት ‘ወያነ’ ብዬ ከጠራሁት እያወደስኩት ነው። ይህ ደግሞ ፍፁም አላደርገውም። ምክንያቱም (አንድ) ህወሓት የሚወደስ ተግባር አላየሁበትም፤ (ሁለት) ህወሓት ወያነ እንዳልሆነ ስለተገነዘብኩ ነው።
ህወሓት ወያነ አይደለም። እንዴት? በትጥቅ ትግሉ ወቅት የትግራይ አርሶ አደሮች ፀረ ጨቋኝ ስርዓት ተነስተው ያለ ምንም ፍርሓት አብዮታዊ እርምጃ ሲወስዱ ‘ወያነ’ የሚል ማዓርግ አግኝተው ነበር። ይገባቸዋል። አዎ! እነሱ ትክክለኛ ወያነ ነበሩ። ለነሱ ወያነ ብዬ ማወደስ እችላለሁ። ምክንያቱም መስፈርቱ ያሟላሉ። ለውጥ ፈልገው ፀረ ገዢዎች የሚታገሉ አርበኞች ነበሩና።
የአሁኑ ህወሓት ግን ወያነ አይደለም። ምክንያቱም ገዢውን መደብ ለመጣል በትግል ላይ ያለ የአርበኞች ስብስብ አይደለም። የደርግን ስርዓት ከተገረሰሰ ወዲህ ህወሓት ነፃ አውጪ ግንባር ሳይሆን ራሱ ገዢ መደብ (ገዛኢ ደርቢ) ነው። ወያነ የሚባል ግን ገዢውን መደብ ለመጣል የሚታገል ነው። ስለዚህ ህወሓት ወያነ አይደለም፤ ገዢ መደብ ነው። ለገዢ መደብ ወያነ አይባልም።
ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) የአንድ ነፃ አውጪ ቡድን ስም ነው። የድሮ ስም ነው። ስሙ ስልጣን ለመያዝ የትጥቅ ትግል የሚያካሂድ ቡድን ይወክላል። የአሁኑ ህወሓት ግን ስልጣን ለመያዝ የሚታገል ቡድን ሳይሆን ገዢ መደብ ሆነዋል። ስለዚህ ስሙ ተግባሩና ደረጃው አይወክልም። ስልጣን ከያዘ ወዲህ ስሙ መቀየር ነበረብት። ግን ለምን የድሮ ስሙ ይዞ መቆየት መረጠ? ይቺ ‘ወያነ’ የምትለዋን ህዝብ ለመቀስቀስ የምታስችል ወኔ የምታላብስ ስም ላለማጣት ፈልጎ ነው። ስለዚህ ህወሓቶች ወያነ የሚል ስም አይጠሉትም፤ እንደውም ይወዱታል።
ግን ህወሓት ምንድነው? አማርኛ የለውም እንዴ? አማርኛ ተናጋሪዎችም ህወሓት ይላሉ። በእንግሊዝኛስ ምንድነው? ህወሓት አወቃቀሩም ቃሉም ትግርኛ ነው። ‘ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ’ ይወክላል። ወደ አማርኛ ሲመለስ ‘ የትግራይ ህዝብ አብዮታዊ ነፃ አውጪ’ እንድ ማለት ነው። ይሄው እስካሁን ነፃ አውጪ! እስካሁን ተፋላሚ፣ ተዋጊ ቡድን። በተግባር ግን ገዢ መደብ።
ሌላው የሚገርም ነገር የፓርቲው የትግርኛና የእንግሊዝኛ ስም የተለያየ መሆኑ ነው። በትግርኛ ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ) ወይ በአማርኛ (የትግራይ ህዝብ አብዮታዊ ነፃ አውጪ) ሲሆን በእንግሊዝኛ ግን TPLF (Tigray People’s Liberation Front)። TPLF (Tigray People’s Liberation Front) ወደ ትግርኛ ሲመለስ ‘ግንባር ሓርነት ህዝቢ ትግራይ’ (ግሓህት) ወይ በአማርኛ ‘የትግራይ ህዝብ ነፃነት ግንባር’ (ትህነግ) ይሆናል። ህወሓት ወደ እንግሊዝኛ ሲመለስ ደግሞ ‘Tigray People’s Revolution for Liberation’ ይሆናል። ስለዚህ ምስቅልቅሉ የወጣ ስም ነው።
ባጠቃላይ የገዢው ድርጅት ስም ‘ህወሓት’ መሆን የለበትም። ምክንያቱም ግንባር አይደለም። ግንባር ስልጣን ለመያዝ የሚታገል ድርጅት ያመለክታል። ህወሓት ደግሞ ስልጣን ይዟል። ህወሓት ወያኔ መባል የለበትም። ምክንያቱም ወያነ አይደለም፤ ገዢ መደብ ነው።
‘ወያነ’ ብዬ የምለው ነፃነታቸውን ለመጎናፀፍ የፖለቲካ ለውጥ በመሻት ሰለማዊ የስልጣን ሽግ ግር እውን እንዲሆን ሙሉ ወኔ ተላብሰው በጀግንነት ለሚታገሉ ጓደች ነው።
ህወሓት ወያነ አይደለም።
(ግን ስም’ኮ የፈለገው ቢሆን መጥርያ እንጂ ምንም አይደለም።)

አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል (ክፍል ፭)

timthumb
August 22, 2013
ናደዉ፦ከዋሽንግተን ዲሲ
የወያኔ ጉጅሌዎችን ስዉር አጀንዳ ፅሁፍ ከዚህ ሆድ አደር ተላላኪ ታሪክ በኋላ ወደ ሌሎቹ እዘምታለሁ፤በማህበር ተጠርንፈዉ እስከሚመጡልኝ ወይም እስከሚመጡብኝ ድረስ ማጋለጤ በሰፊዉ ይቀጥላል፧ለጠላቴ አልተኛም እንደ በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ የታች አርማጭሆ ልጅ መሆኔ ቀረ?!
ምርጫዉ ስንሻዉ ወይም ብዙዎች የዲሲና አካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚጠሩት በትናቸዉ/ፍርሻው ስንሻዉ ባለፈዉ እሁድ ደግሞ አዲስ የጥላቻና የጋጠወጥ ስድብ ከረጢቱን ዘረገፈዉ፣ አዎ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ በሚገኙት በሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሪ በፈርስቲ ኢጂራ ፕሬዘዳንት በሼክ ነጂብ ላይ፧ በወያኔ ጉጅሌ በጀት በሚተዳደረዉ ወናፍ መንደርተኛ ራዲዮኑ እሳቸዉን ብቻ ሳይሆን ባለቤታቸዉንና የሙስሊሙን ሕብረተሰብ የድምፃችን ይሰማ እንቅስቃሴም ጭምር፥እንደወያኔ አስተዳዳሪዎቹ ሁሉ እሱም ሲሳደብ ዉሎ አደረ ፧ተወካያቸዉ መሆኑም አይደል?!መሽቶ ነጋ በቅዳሜ ማታና በእሁድ ቀን ፕሮግራሞቹ፤እኔም በዚህ ባንዳ ዙርያ በተከታታይ ለማወጣቸዉ ፅሁፎቼ ስል አለፍ አለፍ አድርጌ መቅረፀ ድምፄን ይዤ መከታተሌ አልቀረም፧ሚስቴና ልጆቼን ተደብቄ በሌሉበት መሆኑ ይታወቅልኝ !ምክንያት፥የዚህን ተሳዳቢ ሰዉዬ ቱማታ ላለመስማት ቤቱን ጥለንልህ እንዉጣ የሚለዉ ብስጭታቸዉ ስላሳሰበኝ ብቻ !!
ለእለቱ ለስድብ ኢላማነት የተመረጡትን እኝህን የሀይማኖት መሪ እንዲህ አለ፦ በአክብሮት ዘለፋዬን እርስዎም ባለቤትዎም የሀይማኖትዎም ተከታዮች በጥሞና ያዳምጡኝ ብሎ የራዲዮን ፕሮግራሙን ጀመረ፣የተለመደዉን የጥላቻ ስድብ ዉርጅብኝ በይሉኝታ ቢስና ፀያፍ ቃላቶቹ ለቀቀዉ አዎ እሱ ማንን ፈርቶ?!
ዛሬ ገና ለዚህ ተከታታይ ፅሁፌ ተገቢና ትክክለኛ ርእስ መስጠቴን አረጋገጥኩ። አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል። ያልኩትን፧ በትምህርተ ጥቅስ አስቀመጥኩት፤ ለምን እንዲህ አልክ ብትሉኝ መልሴ እንደሚከተለዉ ይሆናል፧! እኚህ ሰዉ ስለዚህ መሰሪ የደርግ ካድሬ ብዙ ምስጢር እንደሚያዉቁ ስለማዉቅ ብቻ ሳይሆን ዛሬ የሚያዉቁት ነገር ምናልባትም ላለፉት አስርተ አመታት ለዋሽንግተን ነዋሪ ኢትዮጵያዉያን ያልተናገሩትን የደራሽ ግብረሃይል ምስጢር የሚያጋልጡበት ወቅት አሁን በመሆኑ ነዉ። ሳይቸግረዉ የነካካቸዉ ይመስለኛል፧ያዉም የሞራል ህልዉናን በሚፈታተን መልኩ፥ለዚህ ወስላታ የመልስ ምት አያስፈልገዉ ብለዉ ነዉ ሃጂ?! ነገሩ እንዲህ ነዉ በክፍል አንድና ሁለት ላይ በግልፅ እንዳሠፈርኩት የዛሬ አስር አመት አካባቢ አገራችን ኢትዮጵያ በከፍተኛ ረሀብና ድርቅ በተጠቃችበትና አላፊነት የጎደለዉ የህወሀት ዘረኛ አምባገነን አገዛዝም ሁኔታዉን ለመደበቅ በሚድበሰበስበት በዚያን ወቅት የዓለም አቀፍ የዜና ማሰራጫዎች ሁኔታዉን ገሀድ ማዉጣታቸዉ እርግጥ ነዉ። በወገኖቻችን ላይ ደርሶ የነበረዉ አስከፊ ሁኔታ ወያኔን ከመታገል ጎን ለጎን ለተጎዱት ወገኖች በአፋጣኝ መድረስ ጊዜዉ ግድ ይል ነበር። በዚህም መሰረት በዳያስፓራ የሚገኙት አገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ትልቅ ድርሻ አበርክተዋል በዋሽንግተንና አካባቢዉም በተመሳሳይ መልኩ ከተጎጂ ወገኖቻቸዉ ጎን ለመቆም መንቀሳቀሳቸዉ አልቀረም። ይህንኑ የወገን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ሲባል በተቋቋመዉ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ግብረሃይል ዉስጥ ከፍተኛ ተሳትፎ በማድረግ ከሁለት መቶ ሽህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ የተሰበሰበዉንም ገንዘብ ደራሽ ግብረሃይል የሚል ስያሜ ለተሰጠዉ ኮሚቴ በአደራ በአደራ አስረከበና ዉጤቱን መጠባበቅ ጀመረ። በጊዜዉ ከኮሚቴዉ አባላት ዉስጥ በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያዊነት ራዲዮኑ ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ፤የሀገር ፍቅር ራዲዮኑ ባንዳዉ ንጉሴ ወልደማርያም፤የፈርስቲ ኢጅራዉ ፕሬዘዳንት ሃጂ ነጂብና ሲስተር እማዋይሽ ነበሩ። ተወካዮቹ በአካል ተገኝተዉ ለተጎጂ ወገኖቻችን አስፈላጊዉን ቁሳቁስ ገዝተዉ አንዲሰጡ የሕዝብ አደራ ተቀበሉ ፧አደራዉን ግን በሉት።
እንዲህ ሆነላችሁ የተከበራችሁ ኢትዮጵያዉያን ወገኖቼ፧ የኮሚቴዉ ተወካዮች አዲስ አበባ ቦሌ አለምአቀፍ አዉሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ በወያኔ ካድሬዎችና ሰላዮች ታጅበዉ ወደተዘጋጀላቸዉ ሸራተን ሆቴል አመሩ፧ ከተለያዩ ባለስልጣኖችም የምስጋናና የእንኳን ደህና መጣችሁ ስልኮች አቃጨሉላቸዉ የኰሚቴዉ መሪ የነበረዉ ሆድ አደር ተላላኪዉ ንጉሤ ወልደማርያም ከመመሪያ ጋር በእለቱ በሆቴል ክፍሉ ዉስጥ የወያኔ አባልነት ፎርም መሙላቱን የከብት ሕክምና ባለሙያዋ ባለቤቱ ታወራለች። በተያዘላቸዉ ምርጥ ክፍል አርፈዉ ለጥቂት ቀናት በከተመዉ ዉስጥ ከተዝናኑ በኋላ ፧ከየአቅጣጫዉ ከአገር ዉስጥም ሆነ ከዉጭ አገር በተጎጂዎች ስም በሚጎርፍለት ገንዘብ የሰከረዉ ወያኔ መልእክተኞቹን በቴሌቪዥን መስታወት ለጥቂት ደቂቃዎች ከሌሎች ለጋሾች ጋር ቀርበዉ ሁለት መቶ ሽህ የኢትዮጵያ ብር በጊዜዉ የወያኔ የአደጋ መከላከል ኰሚሽን ኮሚሽነር ለነበሩት ለአቶ ስምኦን መቻሌ ያስረክቡና በሌላ የክህደት ፕሮግራም ለመገናኘት ተማምለዉ ይለያያሉ። ከመሐል አንድ እህታችን ብቻ በነገሩ ግራ በመጋባት ይህንን የህዝብ አደራ በልነትን ታወግዛለች ወደ አሜሪካ ስትመለስ ለማጋለጥም ለራሷ ቃል ትገባና ዋሽንግተን በገቡ ማግስት ጀምሮ በተለያዩ ራዲዮኖች እየቀረበች ወገኖቼ የረሀብተኛዉ የእርዳታ ገንዘብ ተበላ እያለች መጮህዋን ትቀጥላለች ፧ቀሪ የኰሚቴ አባላትን ጨምሮ በአማላጅ ሁኔታዉ ይፋ እንዲወጣ ታስጠይቃለች ነገር ግን የሚሰማት ጠፋ ። አንድ እለት ብቻ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ከሕብረተሰቡ ዛቻና ማስፈራርያ ሲበዛበት በራሱ ራዲዮ ላይ ወጥቶ ሃምሣ ሽህ ዶላር ብቻ መቅረቱንና ይህም ገንዘብ ወደፊት የሕዝብ ዉሳኔ ያገኛል ብሎ ለፈፈ፤ከዚያ ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን አስቆጠሩ እነሆ ዛሬ አስርተ አመቱ ተቆጠረ ነገሩ የተረሳ ከሀዲ ቀማኞቹም ለይቶላቸዉ ወያኔ በፍርፋሪ ከጎኑ በግልፅና በስዉር አሰልፏቸዉ በሚመፀወቱት የራዲዮን የአየር ሰአት እንደገና ይሰድቡናል ያላግጡብናል፣ ገንዘቡንና ጊዜዉን የተበላዉ ነዋሪም አፈር ብላ ብሎ ተራግሞ ወደ ቤቱ ገባ ብዙዎች ግን በተለያዩ ቦታዎች የነዚህን ከሀዲዎች ፀያፍ ተግባር ዛሬም ያስታዉሳሉ። ይህ የህዝብ ገንዘብ ነዉ ያለንበት አገር ደግሞ የህግ የበላይነት ይከበራል የተበላዉ በረሀብ ለተጎዱ ወገኖች የተዋጣ ገንዘብ ነዉ የፈለገዉ ያህል ጊዜ ቢቆይም ጉዳዩን በሕግ ፊት ማቅረብ ይቻላልና የህግ ባለሞያ ኢትዮጵያዉያንን ነገሩን እንዲመረምሩት በዚህ አጋጣሚ አሳስባለሁ!
አሁንም በቅርቡ በዚያ በዘራፊዎቹ ንኡስ ኰሚቴ ዉስጥ የነበሩ አዛዉንትን አግኝቼ ሳነሳባቸዉ ነገሩ እንደዉስጥ እግር እሳት ያንገበግበኛል አሉ ወንጀለኞቹን እነ በትናቸዉ ስንሻዉን ዛሬም ምርር ብለዉ በፊቴ ተራገሙ በተጨማሪም እንዲህ አሉኝ በዚያን ወቅት ተጨንቄ ሃጂ ነጂብም ዘንድ ሄጄ እዉነቱን ለሕዝቡ ንገሩ ብዬ ብጠይቀዉ ዳግም አጠገቡ እንዳልደርስ አባረረኝ አሉና ሁኔታዉን ጊዜ እንዳመቻቸዉ የሚያዉቁትን ሁሉ በተገኘዉ ሚዲያ ገሃድ እንደሚያደርጉት ገለፁልኝና ተሰነባበትን።
በመጨረሻ ማሳሰብ የምወደዉ ሃጂ ነጅብ የሚያዉቁትን ይንገሩንና እርስዎም ከሕሊና ወቀሳ ይገላገሉ፣በብዙ ሀይማኖቶች ሲነገር የምንሰማዉ፦ ሌባና ሌባ ሲሰረቅ አይቶ እንዳላየ የሆነ ፧የሁለቱም ወንጀል አንድ ነዉ ይባል የለ?!እና እነዚህ ወሮበሎች ስለዘረፉት ገንዘብ የሚያውቁትን ይንገሩን እግረመንገድዎንም ከሃሜቱ ነፃ ይዉጡ እያልኩ ነዉ። ወቅቱም አሁን ነዉና!!!
የጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ ጉድ መቸም ቢጎለጎል አያልቅም እኔም አንዴ ጀምሬዋለሁና የማዉቃቸዉንና የሚደርሱኝን መረጃዎች በሙሉ እሄድባቸዋለሁ አዲስ አበባ አፍንጮ በር አካባቢ ለምትኖረዉ የድሮ ጓደኛዪ ምሥራቅ ስንሻዉ ከባለቤትዋ ከታጋይ ተክሌ አጋበዝ ጋር ሆና የወንድምዋን ጉድ እንድታየዉና ይህንን ፅሁፍ እንድትፈትሸዉ ሰሞኑን ሳልደዉልላት አልቀርም።
ይህን ማስታወሻ ስፅፍ ዶክተር ታዬ ወልደሰማያትና አቶ ብርሃነ መዋ ትዝ አይሉኝ መሰላችሁ!?በነገራችን ላይ ሁለቱንም ወንድሞቼን እጅግ አድርጌ አከብራቸዋለሁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ዉስጥ ቀላል የማይባል አስተዋፅዖ ማበርከታቸዉ እውነት ነው። ዛሬ ግን ወደ ፓለቲካዉ መድረክ ዳግም ላይመለሱ ከአንደበታቸዉ ብዙዎቻችን ሰማን። የሚገርማችሁ ደግሞ ሁለቱም በአንድ ወቅት በቅንጅት መፍረስ ማግስት መሆኑ ነዉ፧ ለዚህ ትልቁና ዋናዉ ተከሳሽ ጓድ በትናቸዉ ስንሻዉ መሆኑ አይደንቅም። የቅንጅት አመራሮች በእስር ላይ በነበሩበት ግዜ እዚህ የነበሩት የቅንጅት የድጋፍ ኮሚቴ አባላት መከፋፈል ጀመሩ የኰሚቴው ሰብሳቢ የነበሩት ሻለቃ ዮሴፍ በእስር ላይ ከሚገኙት የቅንጅት ፕሬዘዳንት ከኢንጅነር ሃይሉ ሻወል የኰሚቴ አባላቶች ሹም ሽር በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ ላኩ ተባለ አሰራሩ ማእከላዊነት ያልጠበቀ ነዉ ይሄ የንጉሣዊ ሹመት አይነት ነዉና አንቀበልም የሚል አካል ተፈጠረ የነብርሃነ መዋ ቡድን፧ ከስር ቤት ሾልኮ መጣ በተባለዉ የሹመት ዝርዝር ዉስጥ በዚያ የፓርቲ ስብስብ ዉስጥ ያልነበሩት የዶክተር ታየ ወልደሰማያት ስም የመሪነቱን ቦታ ይዞ ቀረበ ይህንን ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እንዲያራግቡት ሃላፊነቱን በበላይነት አንዲመራዉ ደጎስ ካለ የገንዘብ ጉርሻ ጋር ጓድ ምርጫዉ ስንሻዉ ተረከበ ረዳት ሆድአደር አፍራሾችም ተመደቡለት ረዳቶቹ ደግሞ ከኛ ወዲያ ትግል ላሳር የሚሉ የትግል ዘመናቸዉን ሻማ በማብራት ብቻ የሚደክሙ የዲሲ ፋኖዎችና በታኞች ተሳካላቸዉ በአጭር ጊዜ የአገሪቱን ሕዝብ አንድ አድርጎ ወያኔን ያርበደበደዉን ብዙ ዜጎች በጠራራ ፀሐይ ዉድና ተተኪ የማይገኝለትን ዉድ ሕይወታቸዉን የገበሩለትን የፓለቲካ ንቅናቄ ጠልፈዉ ጣሉት አሽመደመዱት። አዎ ምርጫዉ ስንሻዉ፧እነ ሻለቃ ዮሴፍንና ታዋቂዉን ስመ ጥር የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ማኖ አስነካቸዉ ሸወዳቸዉ በግርግርም ከፍተኛ ገንዘብ ተበላ ቅንጅትም ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከጨዋታ ዉጪ ሆነ ተበተነ የበትናቸዉ ስንሻዉ አለቆች ከበሮአቸዉን ደለቁ ከሕዝባዊዉ ማእበል ተጠራርጎ ከመጥፋት ዳኑ፧ ያን ሁሉ ወንጀል ፈፅመዉ ዛሬም እነምርጫዉ አሉ!አሁንም ኢንጅነር ሐይሉን እነ ብርሃነ መዋንም ጨምሮ ሁሉንም ባልተገራዉ ግልብ ንግግሩ ሙልጭ አድርጎ እያወረዳቸዉ ነዉ።ዛሬ በዚህ ባንዳ ምክንያት ብዙ ጠንካራ ሰዎችን አጥተናል አሁንም ዘለፋዉን ቀጥሏል።
መቸም በበትናቸዉ ስንሻዉ ዘለፋና ዝርፊያ ቆሽቱ ያልተቃጠለ አንጀቱ ያላረረ የለምና የዚህ ካድሬ ተጠቂዎች ለዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ብዙ መረጃዎች አደርሰዉታል፧ብዙዎቹ ይበሳጫሉ እንዲህ ያለ ኢትዮጵያዊ የለም ያስብላሉ ተግባራቶቹ ግን እዉነቶች ናቸዉ። እና አኔ እያልኩ ያለሁት ስም ለማጥፋት ለመጠፋፋት ሳይሆን አካሄድህ አስነዋሪ ነዉ ብሎ እሱነቱንና ወልጋዳ አካሄዱን ለራሱ እንደመስታወት አሳይቶ ወደወገኖቹ ለመመለስ ነዉ እንጂ ከተላላኪ ሆድ አደሮች ጋር ይሄን ያህል ግዜ ማባከን ባላስፈለገም ነበር ምናልባት ወደቀልቢያዉ ቢመለስ ብዬ እንጂ!!
ትናንት አንድ ወዳጄ አንድ አባት በዚህ አጉራ ዘለል ካድሬ የሆኑትን ልንገራችሁና የዛሬዉን ፅሁፊን ላብቃ በአንድ ወቅት ለከፈተዉ ቤተክርስትያን በደመወዝ እንዲያገለግሉት አንድ አባት ከምስጢራተ ቤተክርስትያንና ቅዱሳን መጽሐፍቶች ጋር ከአገር ቤት ያስመጣቸዋል በሚኖርበት አካባቢ ነዋሪዎች ቪላ ዉስጥ የምትገኝ አንድ ጠባብ ክፍል ይከራይላቸውና ይገባሉ ቄሱም በየወሩ ከሚሰጣቸዉ ደመወዝ ለቤቱ ኪራይ እየቀነሰ ቀሪዉን ሲሰጣቸዉ ይከርማል የሰዉየዉ ግልብ ባህርይ ባይመቻቸዉም ሌላ መጠጊያ ስለሌላቸዉ ረዘም ላለ ጊዜ እንደተቀመጡ እንባ እየተናነቃቸዉ ይናገራሉ አነጋገራቸዉ ሁኔታቸዉ በዚህ በመጦርያ እድሜያቸዉ ስደተኝነታቸዉና ሁኔታቸዉ እጅግ አሳዝኖኝ መንፈሴ እየተሸበረ ስላስቸገረኝ ንግግራቸዉን ቶሎ እንዲጨርሱ በመመኘት ከዚያ በኋላስ አልኳቸዉ ከዚያ በኋላማ ልጄ አሉ አንገታቸዉን አቀርቅረዉ መሬቱን በያዙት ረጅም ጃንጥላ ጫፍ እየቆረቆሩ ፦አንድ ቀን ትንሽ አመም አርጎኝ እቤት ዋልኩ ያለወትሮየ ቤት መዋሌን የተመለከቱት የቤቱ ባለቤቶች ሊጠይቁኝ መጡ እህል ዉሃም ሰጡኝና በደንብ ሳይሻለኝ እንዳልነሳ ሲመክሩኝ አይ እዚህ አገር ወጪዉ መች ያስተኛል አልኳቸዉ ሴትየዋም ሳቅ ብለዉ አይ አባ እርስዎ ደግሞ ምን ወጪ አለብዎት ለምግቡም ቢሆን አያስቡ አሉኝ እኔም ለሆዴ እንኳ ግድ የለኝም የቤት ኪራዩን ማን ይከፍልልኛል ስላቸዉ የምን የቤት ኪራይ ነዉ የሚያወሩት እኛ ሁኔታዎን አይተን ምርቃትዎ ይበቃናል ብለን ገንዘብ ተቀብለዉ አናዉቅም አሉኝ እኔም በየወሩ ከደመዜ ላይ እንደሚቆርጥብኝ ነገርኳቸዉና ከዚያን አለት ጀምሮ አይኑን አያሳየኝ ብዬ ለአምላኬ አልቅሼ ቀረሁ አሉኝ። አይገርምም ወገኖቼ?!
እነዚህን የመሳሰሉ አሳፋሪ ብዙ ተግባሮቹን ብዙ ትሰማላችሁ እዚህ አካባቢ ጎራ ብትሉ፤ከዚህ ነዉረኛ የወያኔ ተላላኪ የምንረዳው አንድ ነገር አለ ይኸዉም አምባገነኑና ጨካኑ የህወሀት ስርአት በዙርያው የሚኮለኩላቸዉ ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች ምንአይነት ከርሳሞችና ምግባረ ብልሹዎች እንደሆኑ ነዉ።
ክፍል ፮ ይቀጥላል

Wednesday, August 21, 2013

ደብዳቤ ከመለስ ዜናዊ (ይድረስ ለጓድ ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማርያም ደሳለኝ)

ካለሁበት ቦታ ጓዳዊ ሰላምታየ ይድረስህ። ከመጣሁ ጀምሮ ደብዳቤ ልጽፍልህ አስቤ ሳይሳካልኝ ስለቀረ እስከአሁን ቆየሁ። እዚህ ከመጣሁ ብዙ ነገር አጋጥሞኛል። በየጊዜው ብዙ ሰወች ስለሚመጡ፣ ስለናንተ ብዙ ነገር ይደርሰኛል።
እኔ ያለሁበት ቦታ በጣም የተለየ ቢሆንም፣ እዚህ ከመጣሁ በጣም ብዙ ሰው አግኝቻለሁ። ብዙወች ያውቁኛል። እኔም የማውቃቸው ብዙ ናቸው። ተሰባስበው ያነጋገሩኝ ብዙወቹ እኔ በተለያየ መንገድ ከምድር ወደዚህ የላኳቸው ናችው።
እንድሁም ታዋቂ የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞችም በቦታው ነበሩ። የኢትዮጵያዊያኖችን በይበልጥም የዘመዶቻቸውን ቁስል ላለመቀስቀስ ስል ስም አልጠራም። ዝርዝሩን ከፈለግክና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲናገር ከፈቀድክለት ይነግርሃል። የደህንነት መስሪያ ቤታችን ያረጋግጥልሃል።
በጣም ቁጥር ስፍር የሌላቸው፣ ትግራይን ለማስገንጠልና ኤርትራን ነፃ ለማውጣት ብለህ፣ ከኢትዮጵያ ጦር በኩል፣ ከህወሃት በኩል፣ ከሻብያ በኩል፣ ያስጨረስከን ነን ይሉኛል። በጣም የገረመኝ ሁሉም በአንድ ሆነውና ተስማምተው ነው
ያነጋገሩኝ። በተደጋጋሚ ያቀረቡልኝም ጥያቄ እኛን አስጨረሰህ ትግራይና ኤርትራ ምን የተሻለ ነገር አገኙ፤ ህዝቡ ከመለመን፣ ከመሰደድ፣ ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከአምባገነን አገዛዝ ነፃ ወጣ ወይ የሚል ነበር። እንድሁም በትግራይ ተራራወች የጨፈጨፍናቸው የደርግን ግድያ ሸሽተው የነበረ የኢህአፓ ወጣቶች፣ በአዲስ አበባ ጎንደርና ሌሎች ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ በማድረጋቸው በአጋዚ አነጣጣሪ ተኳሾች በኔ ትዛዝ ያስገደልኳቸው፤ በኦሮሚያ፣ በጋምቤላና በደቡብ ህዝቦች በዘር ለያይተን ያጋደልናቸውና፣ በበደኖ፣ አርባጉጉ ከነህይወታቸው ገደል ያስጨመርናቸው፣ የብሄረሰቦች መብት እስከ መገንጠል በማለት ቀስቅሰን በየጫካውና በየከተማው ኦነጎች ናችሁ እያልን የገደልናቸው የወለጋ፣ ባሌ፣ ጅማና ሃረር ወጣቶች፤ እንዲሁም ነፍጠኛ በማለት ፈርጀን እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ ያደረግናቸው ገበሬወች ነበሩ። በተጨማሪም በኤርትራ በየዋሻው ታስረው በርሃብና በግዳጅ ስራ ጠያቂ ሳይኖራቸው ያለቁ የኢትዮጵያ ወታደሮች፣ በተለያዩ ቦታወች እየተያዙ እንዲገደሉና እንዲሰወሩ ያደረግናቸው ኢትዮጵያዊያን በጣም ብዙ ነበሩ። እነዚህም ያናገሩኝ በአንድ ላይ ሆነው ነው። ሌሎቹ ቁጥራቸው የሚበዛው ከኢሳያስ ጋር በነበረን የግል አለመግባባት በባድሜ ስም ጦርነት ከፍተን ያስጨፈጨፍናቸው ነበሩ። ሁሉም እንዲወክላቸው የመረጡዋቸው፣ እቤታቸው በር ላይ በህወሃት ተኳሾቸ ያስገድልኩዋቸው መምህር አሰፋ ማሩ ነበሩ። ሁሉም ባንድ ቃልና በከፍተኛ ትዕግስት አናገሩኝ። አንተም ወደዚህ ትመጣለህን ብለው የተወሰኑት ቀለዱብኝ። ያሉበትን አለም የሚገዛው፣ እውነት፣ ሰባአዊነትና ትግስት ነው። ብዙወቹ ለአገር ሰማዕታት የሚሰጥ ልዩ የክብር ቦታ ተሰጥቷቸዋል።
የኔ መምጣት እንደተሰማ ካናገሩኝ ውስጥ ራስ አሉላ አባ ነጋ፣ አጼ ምኒሊክ፣ አጼ ዩሃንስ፣ ደጃችህ ገረሱ ዱኪ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ በላይ ዘለቀ፣ ሞገስ አስገዶም፣ አብርሃም ደቦጭ እና ሌሎችም የኢትዮጵያ አርበኞች ነበሩ። ከሁሉም ግን ራስ
አሉላ በጣም ተበሳጭተዉና ደማቸው ፈልቶ፣ ይህን ከሃዲ አምጡልኝ በማለት፣ ምን ለማድረግ ነው ስንት ህዝብ መስዋዕት ሆኖ ያቆያትን አገር ለማፍረስ ይህን ሁሉ ያደረግከው በማለት ጠየቁኝ። እኔም በፀፀትና በፍርሃት መንቀጥቀጥ ጀመርኩ። ከዚያም ከፊቴ ጥፋ ብለው አባረሩኝ። እኔም በሁለት እሳት መካከል ሆንኩ፣ አንዱ በስራዬ የተፈረደብኝ ሌላው ደግሞ የደረሰብኝ ፀፀት ነበር። ከዚያም ሃጢያቴን ለመናዘዝ አባታችን መምጣታቸውን ስለሰማሁ መፈለግ ጀመርኩ። እንደምንም አገኘኋቸው። እንደፊቱ የሚፈሩኝ መስሎኝ አባት ያሳልሙኝ ብዬ ጠጋ ስል፣ ክላ በማለት መቋሚያቸውን አንስተውና እኔንም አሳስተህ አስቀስፈኸኛል ብለው አባረሩኝ። ተስፋ ባለመቁረጥ ስፈልግ ሌላ አባት አገኘሁ። ቀረብ ብዬ አባት ሃጢያቴን መናዘዝ፣ ንስሃ መግባትና ካለሁበት እሳት መውጣት እፈልጋለሁ ስላቸው፣ ስለአንተ ቀድሜ ብዙ ሰምቻለሁ፣ መብርቅ መትቶህ በድንገት ነው እንዴ ወደዚህ የመጣህው አሉኝ። አይ አይደለም፣ ለረጂም ጊዜ ታምሜ ነበር አልኳቸው። እሳቸውም መልሰው ታዲያ የንስሃ እድሜ ተሰጥቶህ ይህን ሁሉ ጉድ ሃጥያት ተሸክመህ እንዴት ሳትናዘዝ ትመጣለህ ብለው በመገሰጽ ይቅርታ መጠየቅና ንስሃ መግባት ያለብኝ ግፍ በፈፀምኩበት በኢትዮጵያ ህዝብ ፊት መሆኑን ነገሩኝ። በዚህም የተነሳ ይህን ደብዳቤ ፃፍኩልህ።
ጓድ ሃይለማርያም፣ በቅርብ የመጡ ብዙ ሰወች አገኘሁ። ከሁሉም የሰማሁት ተመሳሳይ ነው። አንተና የህወሃት ኢህአድግ ሰወች የመለስን “ሌጋሲ” (ውርስ) ሳይበረዝ ሳይከለስ እንቀጥላለን እያላችሁ ትፎክራላችሁ አሉ። ይህ የምትሰሩት
ስራ ሃጢያቴን እያባዘው ነው። አዜብ የመለስ ህይወት ታሪክ ሲነገር ገድሉ በአግባቡ አልተገለፀም አለች አሉ። ይህ ሁሉ ለኔ ምን ይጠቅመኛል? ያለሁበት ቦታ ውሸት፣ ከንቱ ውዳሴና ማሞካሸት የሚያስፈልገው አይደለም። ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት የማይቀረው እየመጣ መሆኑን አውቄ እንኳ የሰረፀብኝን ትዕቢት ማሸነፍ፣ እውነቱን መቀበል፣ ያጠፋሁትን መናገርና ይቅርታ መጠየቅ አልፈለግኩም። እንዳውም እስከመጨረሻው ጊዜ ድረስ ከከፋፋይና ዘረኛ ስራየ አልተገታሁም።
አሁን ሌላ ሰው ነኝ፤ አልዋሽህም። ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ስክድና ሚልዮኖችን እንዳሸበርኩ ሁሉ፣ ጥላየን ስፈራ፣ ራሴን በከንቱ ስከላከል ኖሪያለሁ። እናንተም በፍርሃትና በጭንቀት ተሸፍናችሁ ማየት ያልቻላችሁትን እኔነቴን ልግለጽላችሁ። መሪ መሆን ማለት ከምንም ነገር ቅድሚያ ሃላፊነት መውሰድ ነው። ምንም እንኳ በስሬ የተሰለፉት እበላ ባዮች የተንኮል ተልዕኮየን ለማሳካት ቢረዱኝም፣ በአገሩ ጉዳይ ገለልተኛ ሁኖ፣ የተጫነውን ሁሉ ተሸክሞ የሚኖረው ብዙ ኢትዮጵያዊ ላደረግኩት በደል በዝምታው አስተዋፅዖ አድረጓል። እኔም ለማደርገው ሁሉ ሃላፊነት ሳይሰማኝ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳሰቃይና ስጨርስ ኖሪያለሁ። አንተ ደግሞ የኔን ስራ ያለምንም ለውጥ እደግማለሁ ብለህ መነሳትህ፣ ከምንም ነገር በላይ አሳሰበኝ።
እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ የተጠናወተኝን አገር የመከፋፈልና ኤርትራን የማስገንጠል አባዜ ሳነበንብ በወንጀል ላይ ወንጀል ስሰራ ወደዚህ መጣሁ። ኢትዮጵያን ነፃ ለማወጣት ሳይሆን ትግራይን ለመገንጠል፣ የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር
(ህወሃት) ብለን ተነስተን በብዙ ሺወች የሚቆጠሩ የትግራይን ወጣቶች በከንቱ አስጨረስን። ያአገር ድንበር ለማስከበር የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያንን በግፍ ጨፈጨፍን። በመሰሪና መርዝ በሆነ ቅስቀሳችን በደርግ የግፍ አገዛዝ የተማረረውን ህዝብ አታለልን። ስውር ተልእኳችንን አሳካን።
ብዙ ኢትዮጵያዊያንና በለንደኑ ጉባኤ ያደራደሩን ፈረንጆች ሳይቀሩ የመከሩኝን ባለመስማት፣ ለኢሳያስ የገባሁትን ቃል ለመጠበቅና፣ ለአንድ አገር እድገት የባህር በር አያስፈልግም በማለትና የሃሰት ታሪክ በመፍጠር፣ ኤርትራን ከናት አገሯ
አስገንጥየ፣ ቀሪውን የኢትዮጵያን ህዝብ በጠመንጃ ሃይል አፍኘ፣ የአገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለት የተለየ ሃሳብ ያቀረቡትንና የተቃወሙትን ሁሉ ተራ በተራ አጠፋሁ። ኢትዮጵያን ያለባህር በር አስቀረሁ። ኤርትራን ከማስገንጠል አልፌ በአለም አቀፍ መድረክ የመጀመሪያውን እውቅና ለኤርትራ ሰጠሁ። በኢትዮጵያ ስም ተበድሬ ከፍተኛ ገንዘብ ለኤርትራ አስተላለፍኩ። ስራየ ሁሉ የኤርትራን ጥቅም ማስጠበቅ ሆነ።
የውጭ ጥቃት ይመጣል ተብሎ ሲሰጋ፣ አገሪቱን ከጥቃት ሊከላከል የሚችለውን የባህርና አየር ሃይል በተን። መውጫና መግቢያችን በትንሿ አገር ጂቡቲ መልካም ፈቃድ የሚወሰን ሆነ። ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላምና በአንድነቱ
እንዳይኖር፣ ጠባብ የዘር ፖለቲካ በመስበክና በህገመንግስቱ ዉስጥ የብሄረሰቦች መብት ያለገደብ እስከመገንጠል የሚለውን  በማጽደቅ፣ አገሪቱን ጣሊያኖቹ ባሳዩን መንገድ በዘር ከፋፈልን፣ የአገሪቱን አንድነትና ደህንነት ለአደጋ ተጋልጦ እንዲኖር ህጋዊ መሰረት አስቀመጥን። ኢትዮጵያዊነትና የጋራ እሴት የሆነውን ሁሉ መግደል ዋናው ስራየ ሆነ። በአጭሩ በአዲስ አበባ የሚኖር የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባርን ዓላማ አስፈፃሚና የኢሳያስ አምባሳደር ሆንኩ። በጣም የሚያስገርመው የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር የሚለውን ስማችንን እንኳ ሳንቀይር ኢትዮጵያን ይህን ያህል ዘመን መግዛታችን ነው።ይህን የማያውቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብየ ሳይሆን ነገርን ከስሩ በየ ነው። ለነገሩ እኛ መግዛት ከጀመርን የተወለዱትና የኛን ዘረኛ ቅስቀሳ እንደወተት እየጠጡ ላደጉት ወጣቶች ይህን ስራየን ባሳውቃቸው ምን ይከፋል።
የፈለግኩትን ሁሉ አፍርሸ እንደገና እገነባዋለሁ የሚል ከንቱ አመለካከት ነበረኝ። በዚህም መሰረት ያአገሪቱን ምሁራን አባርሬ ሌላ ምሁራንን በራሴ አምሳል እፈጥራለሁ በማለት፣ የተለየ ሃሳብ ያላቸውንና ይተቹኛል ብየ የፈራኋቸውን
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ችሎታ የላቸውም በማለት፣ ለአገር በሚጠቅሙበትና ብዙ ሊያስተምሩ በሚችሉበት እድሚያቸው፣ አባረርኩ። ያገሪቱን ምሁራን በማሳደድ ያለፍላጎታቸው የባዕድ አገር አገልጋይ እንዲሆኑና ብዙወችም
ተበሳጭተውና ተሰቃይተው እንዲሞቱ አደረግኩ። ለዚህ ወ/ሮ ገነት ዘውዴ ትልቅ ሚና ተጫውታልኛለች። በየመስርያ ቤቱ የኛን የዘር ፖለቲካ የማይቀበሉትን ሁሉ አባረርን። ምንም ችሎታው በሌላቸው ታጋዮች ተካን። ታማኞቻችንን በከፍተኛ ቦታ ለመመደብ ብዙው ሰው ድንጋይ መፈልፈያ እያለ በሚጠራው ሲቭል ሰርቪስ ኮሌጅ በማስገባት ዲግሪ አደልን። እንዲሁም ከአውሮጳ የተልዕኮ ዩኒቨርስቲወች “ድፕሎማ ሚልስ” በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ዲግሪ በመግዛት አደልን። ዛሬ እኔ ሳነጥስ አብረው ያነጥሱ የነበሩት በስሬ ያሰማራኋቸው አድርባዮች ሁሉ ባለ ማስተርስ ዲግሪ ተብለዋል። ለምን ያን ያህል የውጭ ምንዛሬ እንደአወጣሁና ትምህርት መርጃውን ራሴ እያተምኩ እንዳልሰጠኋቸው እስካሁን ለራሴም አልገባኝም። ታዲያ ነገሩ ሁሉ የኔን ቃላት እንደ ፀሎት መድገምና ድንቁርናን በአገሪቱ ማባዛት ሆነ።
ፈረንጆቹን ለማታለል፣ ከፍተኛ ብድር ለመበደርና ዕርዳታ ለማግኘት፣ የተጋነነና የውሸት መረጃ በመሰብሰብ፣ ለማስመሰል ያህል ህንጻ በመገተር ትምህርትን አስፋፋሁ አልኩ። ለህሊናቸው የሚገዙትንና የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ምሁራን
በስለላ ድርጅታችን ተብትበን በመያዝ አሽመደመድናቸዉ። ባጭሩ ተቋማቱ የካድሬ መፈልፈያና፣ እንደኮብል ድንጋይ ቀርጸው ካስቀመጡባቸው የማይንቀሳቀሱ፣ ሰምተውና አስበው የማይጠይቁ፣ አምባገነንን የሚያመልኩ በቀቀኖች ማምረቻ ሆኑ። በአገሪቱ እኔው ምሁር፣ እኔው ተመራማሪ፣ እኔው ህግ፣ እኔው ህግ አውጭ፣ እኔው ዳኛ፣ እኔው ፖሊስ፣ እኔው የጦር መሪ ሆኜ ኖርኩ።
በዘረኝነት መርሃችን የትግራይን ህዝብ እንዲጠላ ለማድረግና ምንጊዜም የኛ ደጋፊ ለማድረግ በሸርብነው ሴራ፣ ለሙን የጎንደርና፣ የወሎን መሬት ወደ ትግራይ ከለልን። ብዙ የዋህ ኢትዮጵያዊያን የትም ክልል ይሁን የኢትዮጵያ አካል
እስከሆነ ድረስ ብለው ተቀበሉት። የግል ደጋፊወቻችንን ሰፊና ዘመናዊ እርሻ እንዲኖራቸው በሁመራ ሰሊጥ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲያገኙ በማድረግ የዛሬ ሃብታሞች የነገ አገር መሪዎችን ፈጠርንበት። ቀሪው ኢትዮጵያን የመግዛት ዘመናችን ካለቀ ግን፣ በጠባቡ አመለካከታችን ትግራይን ገንጥሎ ወደ ኤርትራ ለመቀላቀል የሚያስፈልገንን ሁሉ አዘጋጀን። ለዚህም እርዳታ እንድናገኝና ቀደም ብሎ በጫካ እያለን የተደረገልንን ውለታ ለመመለስ የጎንደርን ሰፊ ለም መሬት፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ሳያውቅ፣ ለሱዳን አሳልፈን ሰጠን። በተወሰነ የህውሃት መሪወች በተቆጣጠርነውና ከኢትዮጵያ ተዘርፎ፣ ከመንግስት ባንኮች ተውስዶ፣ በተቋቋመው፣ በግልጽ ባለቤትነቱ በማይታወቀው፣ የሂሳብ አያያዙ በማይመረመረው፣ ግብር በማይከፍለው፣ በትግራይ ልማት ድርጅት (ኤፈርት) ስም፣ ሌላ ባለሃብቶችን በማዳከም፣ ያአገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጠርን።
ሌላው ወንጀሌ የኢትዮጵያን የመሬት ስሪት በማስመልከት የፈፅምኩት ነው። መሬት የመንግስት ነው ብለን ስንነሳ የረቀቀ የረጅም ጊዜ ዓላማ ይዘን የኢትዮጵያን መሬት ለመሽጥ፣ ለፈለግነው ደጋፊወቻችን ለመስጠት መሆኑን የተረዱ ብዙ
አልነበሩም። የኢትዮጵያን ህዝብ ከመመገብ አልፎ ለሌላ አገር ይተርፋል የተባለውን ቆላማ መሬት ለውጭ ባለሃብቶች ለመሽጥ በነበረን የረጅም ጊዜ ዕቅድ መሰረት፣ መጀመሪያ ያደረግነው ህዝቡን በዘር መከፋፈልና ካአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ሂዶ እንዳይሰራ ማድረግ ነበር። በዚህም ከበሽታና ከርሃብ ተርፈው የተቋቋሙትን ሰፋሪወች ከጋምቤላ፣ አሶሳ፣ ባሌና ደቡብ ህዝቦች እንዲፈናቀሉና እንዲገደሉ አደረግኩ። የብዙ ህፃናትና ደካሞች ህይወት ሳይቀር አለፈ። ብዙ የመሃል አገር ሰወች በአርባጉጉ፣ በበደኖ እና ሌሎች ቦታወች ነፍጠኛ እየተባሉ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ። ብዙ የመንግስት ሰራተኞች ክልላችሁ አይደለም እየተባለ ተባረሩ። የኢትዮጵያ ባንድራ ተወረወረ። ኢትዮጵያዊነት እዲጠፋ፣ ጎሰኝነት እንድነግስ በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘመቻ አደረግን። በዚህ ረገድ እነ ጓድ ታምራት ላይኔና አሰን አሊ በዘረኛ ቅስቀሳቸው ያደረጉት አስተዋጾዖ ከፍተኛ ነበር። ዛሬ ግን ታምራት እኔና ባለቤቴን እግዚአብሄር በተደጋጋሚ በገሃድ መጥቶ አናገረን እያለ ፈረንጆቹን ያታልላል አሉ። ድሮም ብልጣ ብልጥ ነበር። በዕውነት እግዚአብሄር ከቀረበው ቅድሚያ የኢትዮጵያን ህዝብ ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት። በዚህም መሬት ስሪትና ዘረኛ መርህ በሚስጥር በሚደረግ ስምምነት ሰፋፊ በአገር የሚተካከል መሬት ለነ ካራቱሪ፣ ሸህ አላሙዲንና ሌሎችም ሸጥን። በጋምቤላና ሌሎች ቦታዎች ብዙ ህዝብ ተገደለ፣ ተፈናቀለ፣ ሰፊና ዘላቂ የተፈጥሮ ሃብቱ ተጨፈጨፈ። መሬቱ ሃላፊነት በጎደለው መንገድ በኬሚካል እንዲበከልና የአካባቢው ህዝብ በበሽታ እንዲለከፍ ተደረገ። እንዲሁም የከተማውን ቦታ ዋጋ ጣራ በማድረስ ከመንግስት የተጠጉና መሬት በተለያየ መንገድ በእጃቸው የገባ ደጋፊወቻችንን ሚሊዮነሮች እንድሆኑ አድርገናል። እኛን ያልደገፉትን ግን ኪራይ ሰብሳቢ በማለት በማሰር አሰቃይተናል።
ጓድ ሃይለማሪያም፣ ካደረግኩት ነገር ሁሉ አንተን ወደ ስልጣን ማስጠጋቴ የተሻለ ስራ የሰራሁ መስሎኝ ነበር። ምክንያቱም ፈርሃ-እግዚአብሄር አለህ ሲባል ሰምቸ ስለነበር ነው። እንዲሁም ደግሞ አንተ እንደ እኔ የሰው ህይወት እያጠፋህ፣ በሰው አካል ላይ እየተረማመድክ የመጣህ ጨካኝ ስላልሆንክ ነው። በተጨማሪም የተማርክ በመሆንህ የምታገናዝብና በራስህ የምትተማመን ትሆናለህ በየ ስለገመትኩ ነው። ምንም እንኳ ከስሬ ያላችሁትን ሁሉ ረግጬ በመያዝ፣ በኔ አዕምሮ እንድታስቡ ባደርጋችሁና የህወሃት ሰወች አላሰራም ቢሉህም፣ በምድር ሳልኖር ግን ይህን ያክል እኔን የምትፈራበትና፣ እኔን ለመሆን የምትጥርበት ጉዳይ አልገባኝም። ይህን ስራህን ያዩ ኢትዮጵያዊያን “the cloned” መለስ
እያሉ እንደሚጠሩህ ሰማሁ። “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” ማለትህንም ሰማሁ። እንዴት ብትፈራኝ ነው? በዕውነት ይህ ለኔ ይገባልን? ደግሞ መለስ “የሚማሩበት፣ የሚመራመሩበትና በርካታ ለመጪው ትውልድ አመራር አባላት በቂ የመነሻ ሃሳብ የሚያገኙበት በጥቅሉ ለጥልቅ ጥናትና ምርምር አንጡራ ሀብት ነው” ብለህ ማለትህ አሽሙር መናገርህ ነው። ጥሩ ብልሃል። የሰራሁት ወንጀል በዕውነትና በአግባቡ ተጠንቶና በመረጃ ተደግፎ ተጠናቅሮ ይቀመጥ ማለትህ ከሆነ ጥሩ ብለሃል። በትክክል እውነቱ ከወጣና ከተጠና የኔን ወንጀል ባለመድገም ከኔ የምትማሩት ብዙ ነገር አለ። አንተ ባትነግራቸውም ግን ብዙ ኢትዮጵያዊያን መረጃቸውን ሰብስበው ቀን እየጠበቁ መሆኑን አውቃለሁ። የትም ማምለጥ
አይቻልም፤ ወዮላችሁ።
ሰው እድሜው ሲጨምር ይበልጥ ራሱን ይሆናል ይባላል። አንተ ግን በየዕለቱ እኔን ለመሆን እየጣርክ ነው። ምነው አዕምሮህን ለኔ ባሪያ የምታደርገው? አንተ እኔ በየድንጋዩ ስር ስደበቅ፣ ስትማር፣ ስትመራመርና ስታስተምር ነበር።
እኔ በኮሚንስት አመለካከቴ እግዚአብሄርን ሳልፈራ እንዴት የሰውን ህይወት እደማጠፋ ሴራ ሳውጠነጥን ብዙውችን ስረሽን ሳስረሽን፣ አንተ የእግዚአብሄርን ቃል ስታነብ ነበር። ራስህን ሁን እንጂ ጓድ ጠቅላይ ሚንስተር። እኔን ሁነህ በጠባብ ህወሃቶች ከምትወደድ፣ ራስህን ሆነህ፣ ለህሊናህ ተገዝተህ ብትጠላ አይሻልምን?
ሌጋሲ ሌጋሲ የምትሉትና ባስለመድኳችሁ ጥራዝነጠቅ ቃላት የምታደናግሩት፣ ህዝቡ አይገባውም ብላችሁ ይሆን? እኔ ከዚህም ከዛም የባዕዳን ቃላትና ቁንጽል ሃሳብ በመቦጨቅ አንድ ጊዜ ትራንስፎርሜሽን፣ ሌላ ጊዜ ኪራይ ሰብሳቢ
ልማታዊ ባለሃብት እያልኩ የኢትዮጵያን ህዝብ ሳደናግርና ሳሳስት ኖሪያለሁ። አሁንማ ሰዉ ሲሰክር ሁሉ የሚሰዳደበው ኪራይ ሰብሳቢ እያለ ነው አሉ። እኔ ኪራይ ሰብሳቢ (ሬንት ሲከር) የሚለውን ሃረግ ስዋስ ያደረግኩት መርሁን ላጥላላ በተቃራኒው ግን ከህወሃት የተጠጉትን የስልጣን ባለቤት ብቻ ሳይሆን፣ በኪራይ ሰብሳቢነት መርህ፣ ማለትም መንግስት የሚያደርገውን ቁጥጥር፣ እገዳና አዋጅ በመጠቀምና፣ አዲስ ምርት ወይም አዲስ ሃብት በመፍጠር ሳይሆን፣ የነበረውን በመሰብሰብ፣የመንግስት የሆነውን መሬትና ንብረት በመሸጥ፣መንግስት የሚያወጣውን ጨረታ በአቋራጭ በመውሰድ፣ እንዲበለጽጉ በማድረግ፣ ሚሊዮነሮች እንድሆኑ ነው። በዚህም፣ በቅርቡ አቦይ ስብሃት እንደገለጠላችሁ፣ የኔ ዋናው ዓላማ የአሁኑን ስልጣን መያዝ ብቻ ሳይሆን ወደፊት በሃብታቸው ተጽኖ ኢትዮጵያን ሲገዙ የሚኖሩ የአገሪቱን ሃብት የሚቆጣጠሩ፣ የህወሃት የገዢ መደብ መፍጠር ነው። ብዙ ሰው ሊረዳ ያልቻለውና የኔ ውስብስቡ አላማ ከጊዚያዊ ስልጣን መያዝ አልፎ ለመጭወቹ ምእተ ዓመታት የሚቆይ ገዥን መፍጠር ነው። ለዛም ነው የኔን ልጅ እንግሊዝ አገር ሳስተምር፣ አቦይ እንደነገራችሁ የሱን ልጆች ጣሊያንና ቻይና በመላክ፣ እንዲሁም የሌሎች ጓዶቻችንን ልጆች አሜሪካ አውሮፓ ልከን በማስተማርና ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተሻለ አዋቂ በማስመሰል ለቀጣይ ገዥነት እያዘጋጀን ያለነው። በአገር ውስጥ ግን ከመቀሌ በስተቀር ህንጻ ገተርን እንጅ ሌላውን ኢትዮጵያው ማደንቆር፣ ማዳከምና የትምህርት ጥራት እንዲወድቅ ነው ያደረግነው። በተጫማሪም ወጣቱን በዘርና በቋንቋ ከፋፍለን፣ የጋራ መግባቢያ እንዳይኖረው፣ ካንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዳይሰራ፣ ከጎሳው ውጭ ለአገር እንዳያስብ አድርገነዋል።
በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው የለም ማለትህን ሰማሁ። ታዲያ እስር ቤቱን ሁሉ ያጣበቡት የኦሮሞ ወጣቶች፣ ነፃ ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ድርጅት መሪወችና የሙያ ማህበር መሪወች ከኔ ጋር በምን ተጣልተው መሰለህ። እኛ ያገባናል ብለን
በጠመንጃ ሃይል፣ የሺዎችን ህይዎት አጥፍተን፣ ስልጣን ስንይዝ፣የፈለግነውን ሁሉ ያለገደብ ስናደርግ፣ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ግን ሰው የዘር ሃረጉ እየተቆጠረ አይገደል፣ አይፈናቀል፣ የመናገር መብቱ አይታፈን፣ መሰረታዊ ሰበአዊ መብት ይከበር፣ ስላሉና በሰላም በበዕራቸው ስለታገሉ ስንቶቹን በእስር፣ በድብደባ፣ አሰቃየን። ስንቶቹን ገደልን። ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ናት ስላሉ፣ የሰው ልጅ በቋንቋው ተለይቶ መገደል የለበትም ስላሉ አስቃይተን የገደልናቸውና የብዙ ኢትዮጵያዊን ህይወት ያተርፉ የነበሩትን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ሰምቻቸው ቢሆን ኖሮ፣ የብዙ ኑፁሃንን ህይወት ማዳንና የግፍ ግድያን ማስቆም፣ ብቻ ሳይሆን ወንጀለኞች እንኳ ፍትህ የሚያገኙባት ኢትዮጵያን በፈጠርን ነበር። ስህተታችንን ሊጠቁሙ የሚችሉትንና የህዝብ አይን፣ ጆሮና አንደበት የሆኑትን የግል ጋዜጠኞችን አሰርን፣ ብዙወች አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ አደርግን። ዛሬ የመንግስትን ሃብት የሚዘርፉትን ባለስልጣናት የሚያጋልጥ ነፃ ጋዜጠኛ በመታፈኑ፣ ትንሹን ሌባ የሚያጋልጠው፣ ትልቁ ዘራፊ ሆኗል። ስንንቃቸው፣ ስናዋርዳቸውን ስናሳድዳቸው የነበሩ ጋዜጠኞች ናቸው አሉ፣ በአገር ውስጥ እውነቱን የሚናገር ጋዜጠኛ በጠፋበት ጊዜ፣ በተሰደዱበት አገር ሁነው የኔን ዜና ዕረፍት እንኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ህዝብ ያሰሙት። ዛሬ ለህይወታቸው ሳይፈሩ የህዝብ መብት ይከበር ብለው በሰላም ስለጠየቁ፣ የኔና አገዛዝ ብልሹ አሰራር ስለተቹ፣ አስረን የምናሰቃያቸው እነ እስክንድር ነጋ፣ ብርሃኑ አራጌ፣ የኦሮሞና የኦጋዴን ወጣቶች፣ንጹሃን የፖለቲካ እስረኞች ካልሆኑ ምን ሊሆኑ ነው።
በህዝቡ መካክል ልዩነትን መፍጠርን የነበረም ልዩነት ካለ ማባባስ ዋናው የመግዣ ስልቴ ነበር። በዘር መካካል የማይታረቅ ልዩነት እንዲኖር መርዛማ የሃሰት ታሪክ በመፍጠርና የኢትዮጵያ ታሪክ የመቶ አመት ታሪክ ነው ብሎ በመቀስቀስ
ብዙዎችን ማሳሳትና በጠባብ የዘር ፖለቲካ እንዲጠመዱ አድርገናል። በሃይማኖት መካከልና ልዩነት መኖሩ የስልጣን እድሜየን ለማራዘምና የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊዎችን ያዳክምልኛል ብየ በማሰብ፣ ልዩነቱ እየሰፋ ሲሄድ ዝም ብየ
ከመመልከትም አልፌ ልዩነቱን ለማስፋት የሚረዱኝን ግለሰቦች ስልጣን ላይ እንዲወጡና ነገሩን እንዲያባብሱ አድርጊያለሁ። ይህ ሁኔታ ደግሞ በቅርብ ጊዜ የምዕራባዊያንን ቀልብ ለመሳብ ረድቶኛል። በተጨማሪም የምዕራባዊያንን ድጋፍ ለማግኘትና ተቃዋሚዎችን ለማፈን፣ እንደ ሶማሊያ ያለውንም አለመረጋጋት ተጠቅሜበታለሁ።
አኔና ህወሃት በደርግ ጊዜ የነበረዉን ጊዚያዊ ችግርን በዘላቂ በሽታ ተካን። ለመጭው ትውልድ ያተርፍንለት በቀላሉ የማይነቀል የዘረኝነት በሽታ ነው። የጎሰኝነት መጨረሻው ምን እንደሆነ ከሶማሊያ የበለጠ ሊያስተምረን የሚችል
ምን ነገር ይኖራል? በቅርብ ጊዚያት በግብፅ፣ ሶሪያ፣ቱኒሲያና ሊቢያ የተከሰተው ነገር ባግባቡ ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት ነው። ከምንም ነገር በላይ የታፈነ ህዝብ በድንገት ተነስቶ ሊያመጣ የሚችለውን ለውጥ አሳይቶናል። የአምባገነኖች
መጨረሻቸው ምን እደሆነ ታይቷል:: ዛሬ አድናቆታቸው ያልተለየህ ሃያላን ቀን ሲጥልህ ከጎንህ እንደማይቆሙ ከሆስኒ ሙባረክ ሁኔታ የተማርክ ይመስለኛል። ብዙወቻችሁ የኔ እድል ላያጋጥማችሁና ባቋራጭ ወደዚህ አትመጡ ይሆናል። ዘመኑ የመረጃ ጊዜ በመሆኑና ከህዝብ የተደበቀ ነገር ሊኖር ባለመቻሉ ለፍርድ በምትቆሙበት ጊዜ የሚከላከልላችሁ ነገር ካለ የራሳችሁ ስራ ብቻ ነው። አስተውሉ። ጥሩ መሪ ችግር ድንገተኛ አደጋ ሁኖ ከመምጣቱ በፊት ያስተውላል ሲባል
አልሰማህምን?
ጨካኝ መሪን ባያሳድገውም ብዙ ጊዜ የሚወልደው አምባገነን መሪ ነው። የኔ ትልቁ ፍራቻ፣ ከኔ የባሰ ጨካኝ መሪ ኢትዮጵያን እንዳይቆጣጠራት ነው። ደርግ አገሪቱን ለኛ እንዳስረከበው፣ እኔና እኔ የፈጠርኩት አምባገነን ስርዓት ደግሞ አገር ሊመሩና ለኢትዮጵያ ሊያስቡ የሚችሉትን ሁሉ ተራ በተራ በማጥፋት፣ የአገሪቱን አንድነት አደጋ ላይ ሊጥሉ ለሚችሉና በድንገት ስልጣን ላይ ለሚወጡ ክፉ አምባገነኖች ኢትዮጵያን አመቻቸናት። ላንተ ያወርስኩህ ኢትዮጵያ ይህች ናት። ስለዚህ የኔ ዋናው መለዕክት የመለስ ሌጋሲ፣ የመለስ ሌጋሲ የምትለውን ትተህ ራስህን ሁን። እኔም ልረፍበት። የአጠቃላይ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን መሪ ሁን። ከኔ መጥፎና ዘረኛ አገዛዝ ተማር። ዛሬ በመካድ የነገን ተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም። እኔ የፈጸምኩትን ስህተታት አትድገም። ይህን መልዕክት ደግሞ በስርህ ለተሰለፉት ባለስጣኖችህና ኢትይጵያዊያን አስተላልፍልኝ። ለኢትዮጵያ መልካም ነገር ታደርግ ዘንድ እግዚአብሄር ብርታቱን፣ ጥበቡንና ድፍረቱን
ይስጥህ።
ሰላም ለኢትዮጵያ ይሁን
መለስ ዜናዊ
ከላይኛው ቤት

Letter from prison / Reeyot Alemu, Ethiopia

2012 Courage in Journalism Award winner Reeyot Alemuwas arrested on June 21, 2011.
Today is her 793th day in prison.by Reeyot Alemu, Ethiopia
Many questions cross my mind when I look at the "'Anti-Terrorism Decree" and its application. Why does this decree have paragraphs that violate human rights? Why does it prosecute innocent citizens who have no ties to terrorism or terrorist organizations? I ask myself. In order to answer these questions one needs to look at the reasons behind the creation of such a decree, and so I did.
Why was the anti-terrorism decree written? One needn't look too far to realize that the ruling party, EPRDF, didn't create these anti-terrorism laws because it faced a real threat. You only need to look at the individuals who are either facing such charges, or have already been found guilty under this decree. Members of the opposition party who have denounced human rights violations and have peacefully called for the replacement of the current regime by a more democratic one, freethinkers who dared ask stern questions to officials at locally organized discussion forums, leaders of the Muslim community who refused to dilute and redraft their religious beliefs to appease the government's stance on religion, and ourselves, members of the free press who performed their duty as voices of the people have been the main victims of this anti-terrorist decree. 
This proves that the real purpose of this decree is to enable the current regime to comfortably rule without any criticism, opposition, or competition. These actions are not creations of the EPRDF, instead they are old tried and true methods copied from other brutal regimes. It is very well known that colonial regimes of the past found it convenient to label the freedom fighters that refused to kneel as "terrorists." And today, the EPRDF travels this same colonial path by stuffing its prisons with its own citizens and punishing those of us who have refused to give up our human and citizenship dignity. 
What is to be done? Stopping the gross human rights violations that the EPRDF is committing under the guise of the anti-terrorism decree requires a lot of work. The current anti-terrorism decree will have to be replaced by a more appropriate one. Even with such changes, as long as the judicial system leans in favor of the EPRDF such arrests will continue. For, those of us who are currently imprisoned would have been found "not guilty" had we been judged fairly, even under the current anti-terrorism decree. As such, demonstrations and movements aimed at this decree, and more importantly at the ruling EPRDF who seeks to illegally use it, shall be strengthened and continued.
The reason I strongly believe that these protests should primarily be aimed at the ruling party is because it is the source of the wrongful application of this law and other innumerable Ethiopian problems. We have observed with disgust the length this regime will travel to protect its grip on power, and its rule. In other words, the actions of the EPRDF are based on motives that are tied to ethnicity, power hunger, and unjust prosperity among others. In Arthur Gordon's words “If one's motives are wrong, nothing can be right.” Because of this, nothing good can be expected from the EPRDF. 
Therefore our only option for change remains a modern and peaceful struggle wherein we should be prepared to provide the needed sacrifices. As we embark on this journey to transform the system, there are many related issues that we should consider. We should deeply consider all the challenges set forth by the ruling party whether they are the ethnic, religious, ideological, or the interest based divisive elements it nourishes. We shall learn how to unite our many fronts of struggle into one. 
Looking forward, it is the role of any responsible citizen, and especially that of the opposition parties and related groups, to think of and discuss  the nature of the system that shall proceed the current one. For as long as we accomplish these required duties, and stay  firm in our convictions, a Bright Day will not be too far.

The author, a columnist for the now-defunct Ethiopian newspaper Feteh, is currently serving a 5-year prison sentence in Addis Ababa on bogus terrorism charges. The International Women's Media Foundation honored Alemu with its 2012 Courage in Journalism Award last year, and in May 2013, the UNESCO recognized her "commitment to freedom of expression" with its Guillermo Cano World Press Freedom Prize.
The article has been translated from the Amharic original exclusively for the IWMF.
Source The Global Network for Women in the News Media.