Friday, March 22, 2013

! … በህወሓት መሪዎች ምርጫ የትግራይ ህዝብ ኣሳዘነ …!

ኣንድበቅድመ ጉባኤ ስብሰባቸው፣ ሁለቱም ቡድኖች ልዩነታቸውን ለማጥበብ ‘የመተካካት መርህ’ እንደሚተገብሩ ቃል ገብተው ነበር። ከሁለቱም ቡድኖች የተወሰኑ እንደሚቀነሱ (የቀሩ ደግሞ ስልጣን እንደ ሚከፋፈሉ) ስምምነት ነበር። ሸምጋዮቹ ኣዲሱ ለገሰ፣ ሃይለማርያም ደሳለኝና ቴድሮስ ኣድሓኖም (በረከት ስምዖንም እጅ ነበረው) የነ ኣባይ ወልዱ ኣደረጃጀት ስለተረዱ በነ ኣርከበ ቡድን ጫና ፈጥረዋል።
የሸምጋዮቹ ኣቋም ‘ህወሓት መከፋፈል የለበትም፤ ህወሓት ከተዳከመ ኢህኣዴግ ኣቅሙ ይዳከማል፣ ስለዚ compromise ማድረግ ኣለባቹ’ የሚል ነበር። ግዝያዊ ሽምግልናው ሰራና ወደ ጉባኤ ተገባ።
ሁለት
የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ራሱ የመለመላቸው ጉባኤተኞች (በራስ ኣለመተማመን ይመስላል) በስብሰባው 1ለ5 ኣደረጃጀት (የድርጅት ስራ) ተግባራዊ በማድረግ እነሆ የነ ኣርከበ ቡድን መምታት ችለዋል። ዕቅዱ የነ ኣርከበ ቡድን ሙሉ በሙሉ ከስራ ኣስፈፃሚነት ማስወገድ ነበር።
በጉባኤው ‘የመለስ ታሪክና ራእይ’ የኣንድ ቀን ሙሉ ኣጀንዳ ነበር። ‘የመለስ ራእይ’ ተብለው የሚነገሩ ፖሊሲና ስትራተጂዎች በቡድኖቹ ልዩነት ፈጥረው ሲያከራክሩ ውለዋል። ኣንዱ ቡድን ‘የመለስ ራእይ ሳይከለስ ሳይበረዝ መተግበር ኣለበት’ ሲል (እነ ኣባይና ኣዜብ) ሌላኛው ደግሞ ‘መለስ የራሱ ሚና ተጫውተዋል፣ ሁሉም የህወሓት ታሪክ ለመለስ መስጠት ግን የሰማእታት ሚና ማራከስ ይሆንብናል’ ተብሏል (የነ ኣርከበ ቡድን)።
ኣርከበ ‘መለስን ኣታካብዱት የራሳችሁን ታሪክ ስሩ’ (ቃል በቃል ኣይደለም) የሚል ሓሳብ ሲያንፀባርቅ፣ ስዩም መስፍን ደግሞ ‘መለስ ጥሩ ነገር ሰርተዋል ግን በዲፕሎማሲ እሱ የሰራውን ካለ ‘እስቲ የሰራቸውን ነገሮች ዘርዝሩልኝ’ ዓይነት ኣንድምታ ያለው ሓሳብ ሲሰጥ የመለስን ሚና ኣታጋንኑት ለማለት ነበር። ነገር ግን የስዩምን ሓሳብ በኢቲቪና ሬድዮ ፋና ሲቀርብ መለስን ያሞካሸበት ሓሳብ ኣስመስለው እንዳቀረቡት ስምቻለሁ።
ባጠቃላይ ልዩነታቸው ግልፅ ነበር። የነ ኣርከበ ቡድን በነ ኣባይ ወልዱ የተደራጀ 1ለ5 ታክቲክ ተረድተውታል። እንደሚሸነፉ ገብቷቸዋል። ተመካከሩ። በምርጫ ተሸንፈዋል ከሚባሉ ራሳቸው እንድያገሉ (እንዲቀነሱ) ተገደዱ። ጥሩ ማምለጫ ኣገኙ፤ ‘ተገንጥለው ወጡ’ ወይ ምርጫ ተሸነፉ ከሚባሉ ‘በፍቃደኝነት ተሰናበቱ’ ቢባሉ ይሻላል።
ከተቀነሱ ዘጠኝ ሰዎች ሰባቱ የነ ኣርከበ ናቸው። ኣንዱ የነ ኣባይ ወልዱ ሲሆን ኣንድ ደግሞ ከመሃል ሰፋሪዎች ነው። ጸጋይ በርሀ እንዲቀነስ ታስቦ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ንጉሰ ገበረ ተቀነሰ። ከተመረጡት 45 የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ዘጠኙ ሲቪል እንደሆኑ ከመንግስት ሚድያ ሰምተናል። ዘጠኝ ከኣርባ ኣምስት ትንሽ ነው። ይባስ ብሎ ደግሞ እነዚህ ሲቪሎች የኣለቆቻቸው ታማኝ ኣገልጋዮች የነበሩ ናቸው። በራሳቸው መቆም የሚችሉ ኣይደልም።
በስራ ኣስፈፃሚ ኮሚቴ ኣባልነት ሙሉ በሙሉ በሚባል ሁኔታ እነ ኣባይ ወልዱ ኣሸናፊ ናቸው። ስምንት ለ ኣንድ (ቴድሮስ መሃል ሰፋሪ ቢሆንም) በሆነ ውጤት ኣሸንፈዋል። የነ ኣርከበ ቡድን ኣንድ ነጥብ (ዶ/ር ደብረፅዮን ብቻ) ኣለው። የነ ኣባይ ቡድን ኣባዲ ዘሞና ፀጋይ በርሀ (ሁለቱም የነ ኣርከበ ቡድን ነበሩ) ከስራ ኣስፈፃሚነት በማባረር ኣለም ገብረዋህድ (የኣባይ ወልዱ የቅርብ ወዳጅ)ና ገብረመስቀል ታረቀ ኣስገብተዋል። መለስ ዜናዊ ደግሞ በትርፉ ኪዳነማርያም (የኣባይ ወልዱ ሚስት የነበረች ወይ የሆነች) ተይዘዋል።
የትርፉ ኪዳነማርያም ፖሊትብሮ ኣባል መሆን የነ ኣባይ ወልዱ ቡድን ማሸነፉ ማረጋገጫ ነው የሚሉ ኣስተያየት ሰጪዎች ኣሉ። ‘ትርፉ የፖሊት ቢሮ ኣባል ሆነች’ ሲባል ማን ትዝ እንዳለኝ ታውቃላቹ??? ተወልደ ወልደማርያም። ይህንን ሲሰማ ብፃይ ተወልደ ምን ብሎ ይሆን (ኣጠገቡ በነበርኩ!)?
ሦስት
ባሰባሰብኩት የህዝብ ኣስተያየት መሰረት በህወሓት ጉባኤና ወጤቱ የትግራይ ህዝብ (ኣብዛኛው የፓርቲው ኣባል ጨምሮ) በጣም ኣዝነዋል። በተመረጡ ሰዎች ተስፋ የለውም። ህዝቡ ኣዳዲስ የህወሓት ኣመራሮች በመጠባበቅ ላይ ነበር። የፓርቲው ሊቀመንበርነቱን ይዞ የቀጠለው ኣባይ ወልዱና ምክትሉ እንደሆነ የሚቆየው ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ይቀየራሉ (በሌሎች ወጣት ሙሁራን ይተካሉ ብሎ) ሲጠባበቅ ነበር።
የትርፉ ኪዳነማርያም ፖሊት ቢሮ ኣባል መሆን ብዙ ሰው ኣስገርሟል። ኣባይ ወልዱና ኣዜብ መስፍንም ኣልተጠበቁም። ቴድሮስ ሓጎስ ስልጣኑ ይለቃል የሚል ግምት ነበር። ኣባይ ፀሃየና ኣርከበ ዕቁባይ ለፓርቲው ሊቀመንበርነት ታስበው ነበር (በህዝቡ)። ባጠቃላይ የፖሊት ቢሮ ኣባላት ማንነት ኣስጨናቂ ሁነዋል። ‘እነዚህ ሰዎች መርተው የት ያደርሱናል?’ በሚል የፓርቲው ኣባላት ግራ ተጋብተዋል። በጉባኤው የተሳተፉ ኣባላት ጭምር በድራማው ተገርመዋል።
ህዝቡን በጣም ተስፋ ያስቆረጠው ጉዳይ ‘መተካካት’ ነው። ‘የመተካካት ዕቅድ’ በህወሓቶች ከሽፈዋል ማለት ይቻላል። የመተካካት መንፈስ ፈፅሞ ኣልታየም። ከጉባኤው በፊት በነበረ የማእከላዊ ኮሚቴ ኣባላት ስብሰባ የተስማሙበት ነጥብ ዋነኛው ‘መተካካት’ እንደሚኖር ነበር። ኣሁን የታየው ግን ‘መተካካት’ ሳይሆን የተወሰኑ ሰዎች የመቀያየር ሁኔታ ብቻ ነው።
እነዚህ የተቀያየሩ ሰዎች በምን መስፈርት ነው? በዕድሜ? በስልጣን ሰኔሪቲ? በብቃት? NO. በሁሉም ኣይደለም። በፖለቲካ ልዩነትና በዝምድና ነው። ይሄን የሚያሳየን ህወሓት ተተኪ ወጣቶች ማበራታታት ኣይፈልግም። የመሪዎቻችን ዓላማ በስልጣን መቆየት መሆኑ ግልፅ ሁነዋል። በህወሓት ውስጥ ጥሩ ሓሳብ የያዘ ወጣት ተቀባይነት ኣይኖረውም። በህወሓት ውስጥ ሁነው ለለውጥ መታገል ውጤት ሊያመጣ ኣይችልም።
ደግሞ የትእምት ሃብት ለማን ትተው ስልጣን ሊለቁ??? መተካካት፣ ስልጣን መልቀቅ ኣይታሰብም። በፓርቲው ኣባላት ጥያቄ (በጉባኤ) ቀርቶ በህዝብ ጥያቄም (በምርጫ) ከስልጣን ለመውረድ ፍቃደኞች ኣይሆኑም። የሚያስገደድ ሁኔታ ካላጋጠማቸው በቀር። ዋናው መፍትሔ የሚሆነው የህዝቡ የፖለቲካ ንቃተ-ህልና ከፍ እንዲል ማድረግ ነው።
It is so!!!

Monday, March 18, 2013

Ethiopia ‘blocks’ Al Jazeera websites

Traffic to English and Arabic websites has plummeted since the network aired coverage of protests in August last year.
Al Jazeera’s English and Arabic websites are reported to have been blocked in Ethiopia, raising fresh fears that the government is continuing its efforts to silence the media.
Though the authorities in Addis Ababa have refused to comment on the reported censorship, Google Analytics data accessed by Al Jazeera shows that traffic from Ethiopia to the English website had plummeted from 50,000 hits in July 2012 to just 114 in September.
Traffic data revealed a similar drop for the Arabic website, with visits to the site dropping to 2 in September from 5,371 in July.
A blogger, who cannot be identified for his own safety, said Ethiopian censors had been targeting Al Jazeera since the Qatar-based network began airing coverage of ongoing protests against the way in which spiritual leaders are elected in the Horn of African nation.
The steep decline in web traffic began on August 2 last year, the same day that Al Jazeera Mubasher aired a forum with guests denouncing the government’s “interference” with Muslim religious affairs, and three days after Al Jazeera English published an article detailing deadly ethnic clashes between two of the country’s southern tribes.
Attempts by Al Jazeera to get an official response from authorities failed.
Poor track record
Ethiopia is ranked 137 out of 179 surveyed nations on the latest Press Freedom Index of Reporters Without Borders (RSF), an international advocacy group for press rights.
Both RSF and the Committee to Protect Journalists (CPJ) have tied Ethiopia’s deteriorating media environment, in part, to a 2009 anti-terrorism law that has been used to jail 11 journalists since its ratification.
“The usage and practice of this law is illegal. It has a clause that makes whoever writes about so-called terrorist groups, which are mostly normal opposition groups, a terrorist,” CPJ’s East Africa Consultant Thom Rhodes told Al Jazeera.
“Now it’s got to the point that the law is being used to label those in the Muslim community conducting peaceful protests to defend their right to choose their spiritual leaders as terrorists. It’s a sad state of affairs.”
CPJ says Ethiopia is the second-highest jailer of journalists in Africa after neighbouring Eritrea, were seven journalists are currently detained.
Both the RSF and CPJ have expressed concern over reports that the country has begun using much more sophisticated online censorship systems over the last year, including ones that can identify specific internet protocols and block them.
Since Ethiopia’s government owns the sole telecommunications provider in the country, Ethio Telecom, it allows authorities to tightly control internet freedom.
Image

የዮናታን ጉዳይ ፍርድቤት ሲቀርብ እኛ ሁላችን መቅረባችንን መዘንጋት የለብንም(አጭር ማስታወሻ)

በእዚህ ሳምንት በኖርዌይ ትልቅ ኢትዮጵያን በተመለከተ ከተዘገቡት ጉዳዮች አንዱ እና ዋናው  ሕፃን ዮናታን በኖርዌይ የመኖር ፈቃዱበፍርድቤት መወሰኑ ነበር።ሕፃን ዮናታን ከወላጆቹ ጋር በግድ ወደ ሃገሩ እንዲመለስ የኖርዌይ የኢሚግሬሽን ይግባኝ ቦርድ (The Immigration Appeals Board (UNE)) ወስኖ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።የፍርድቤቱ የእዚህ ሳምንት  ውሳኔ ብዙዎቻችንንአስደስቷል።እርግጥ ነው ይህንን ያህል አንድ ስደተኛ አለምአቀፍ ሕግን ባልተከተለ መንገድ የስደተኛ መብቱ የፍርድቤት ጉዳይ መሆንነበረበት ወይ? የሚለው እራሱን የቻለ ጥያቄ ቢሆንም።ሆኖም ግን የኖርዌይ የሕግ አሰራርን የተመለከተ ስለሆነ እና ውሳኔው ከሌሎች ሕጎችጋር የሚኖረው ተቃርኖ አና  ስምምነት ኖርወጅያኖችን ብዙ አከራክሯል።ብዙዎችም መንግስታቸውን ወቅሰውበታል።ከእዚህ ባለፈደግሞ በአለምአቀፍ ግንኙነት ላይ የሚያመጣው አንደምታ ብቻ ሳይሆን አሁን በሀገሪቱ ውስጥ እየኖሩ ላሉት አያሌ የውጭ ሀገር ሕፃናትላይ የፈጠረው የስነ-ልቦና ጉዳት በእጅጉ ተፈርቷል።ለእዚህም ነው የኖርዌይ የመገናኛ ብዙሃንም ሆኑ ዜጎች ጉዳዩን የመነጋገርያ አርስትያደረጉት።

ለእኔ የሚታየኝ ግን አንድ አሳሳቢ ጉዳይ አለ። ናታን በኖርዌይ ቴሌቭዥን ዜናው ሲቀርብ እርሱ የመጫወቻ ዕቃዎቹን ይዞ ሲጫወት ነውየሚታየው። ሰው  ምን እያወራ እንደሆነ፣በቴሌቭዥን ይቅረብ አይቅረብ የእርሱ ጉዳይ አይደለም።ጫወታ ላይ ነው። ነገ ግን ዮናታንያድጋል።ሲያድግ ወላጆቹ ያዩትን ፈተና እርሱም ምን ተብሎ እንደነበር ከእነመረጃው ይመለከታል።ያንጊዜ ናታን ጥያቄዎች ይኖሩታል።እንዲህ የሚሉ -
''በሀገሬ ለምን መኖር አልቻልኩምለምን አባት እና እናቴ ተሰደዱእኛ ኢትዮጵያውያን ሀገር አጥተን ከኢትዮጵያ በብዙ ማይሎችየምትልቅ ሀገር መኖርያ ስጭን እያልን መለመን ነበረብን? '' የመሳሰሉት ጥያቄዎች። ይህን ጉዳይ የማነሳው ወላጆቹን ለመውቀስአይደለም። በሀገራችን ያለውን ፖለቲካዊ፣ማህበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እናውቀዋለን።ወላጆቹም ከእዚህ የተለየ ማድረግ የሚችሉትነገር ሊኖር አይችልም።

የዮናታን ጥያቄ ግን አሁን ላለነው ትውልዶች ሁሉ ነው። ችግር አለብን።አዎን ሀገራችን የመናገር፣የመፃፍ ወዘተ ችግሮች ብቻ ሳይሆንየማሰብ ነፃነት እራሱ ደብዛው ጠፍቷል።የኑሮው ችግር ተባብሷል።ነገር ግን ናታንን ይህ ጉዳይ አሁን አይመለከተውም ።ሕፃንነውና።ትውልዱን ግን ይመለከታል።ባእዳን ሃገራት ለተወሰነ ጊዜ ያጠስልሉ ይሆናል።ዘለቀታነት ግን ሊኖራቸው አይችልም።አንድቀን ሀገሬየማለት ጥያቄ ይነሳል።ዛሬ ያላሰናዱት ሀገር ደግሞ ነገ ሀገር ሊሆን አይችልም። ዮናታን እና የዮናታን እኩዮች ሀገራቸውን ማየት እንዲችሉእና ትውልዱም በውጭ ሀገር ፍርድቤቶች እየተንከራተተ ’የመኖርያ ፍቃድ ስጡን’ ብሎ እንደፍልስጤማውያን ሀገር ለማኝእንዳይሆን፣ዮናታንም ነገ አድጎ እናንተስ የሀገራችሁን ችግሮች ለመፍታት ምን አደረጋችሁ?ብሎ ሳይወቅሰን ሀገራችንን ማሰናዳትችግሯንመፍታት፣ጉድፏን መጥረግ የእዚህ ትውልድ ዕዳ ነው። የዮናታን ጉዳይ ፍርድቤት ሲቀርብ እኛ ሁላችን በ አካል ባይሆን በዜግነት መቅረባችንን መዘንጋት የለብንም።
Refer Yonatan case court decisions
Click http://www.norwaypost.no/index.php/news/latest-news/28255-nathan-7-wins-against-the-immigration-appeals-board 
http://theforeigner.no/pages/news/norway-immigration-officials-lose-ethiopia-case/ 

አበቃሁ 
ጌታቸው በቀለ 
ኦስሎ 