Wednesday, January 15, 2014

የአፍሪካው ልዑል የተሰኘውን መጽኃፍ በሬዲዩ ፋና መተረኩ ተቃውሞ ገጠመው


ኢሳት ዜና :- በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በመተረክ ላይ ባለው በታጋይ መዝሙር ፈንቴ ተርጓሚኒት  በአቶ ዳንኤል ግዛው ጸኃፊነት የቀረበው መጽሀፍ  በአማራ ህዝብ  ላይ  ጥላቻ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት የብአዴን አባላት ተቃውመውታል።
አባላቱ በብር ሸለቆ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ላይ  እንደተናገሩት ሬዲዩ ፋና ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ፡፡ “የህውሃት ድብቅ አላማ እውን እየሆነ ነው” ያሉት ፤ መካከለኛ እና ታዳጊ የብአዴን አመራሮች ፤ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር ታሪክን በማሳሳት እና በማጥላላት የትውልድ ጠላትነትን አስፍቶ አሁንም የህውሃት የበላይነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያደርግ ነው በማለት በጽኑ ተቃውመውታል።
ጥያቄው የቀረበላቸው  የኢህአዴግ የስልጠና ዋና ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ “መፅሃፉ እየተተረከ መሆኑን በፍጽም አላውቅም” ያሉ ሲሆን ፣ ምላሹን አጣርተው እንደሚመጡ ተናግረዋል፡፡ የመጽሃፉ ትረካ ባሰቸኳይ እንዲቆም የጠየቁት አመራሮች ፣ ፋና ራዲዮን መስማት ማቆማቸውንም ለአቶ አዲሱ ተናግረዋል፡፡ የመለያየት ፖለቲካው  መርዛማነት እያሰቃየን ነው ሲሉም አባላቱ አክለዋል፡፡
ከቀናት በሁዋላ ወደ ተለያዩ አካላት  በመደወል መረጃ ያሰባሰቡት አቶ አዲሱ ለገሰ፣ ” ሃይለማርያም እንደፈረመበት እና  ፍቅር እስከ መቃብር ሲል እንዳወደሰው”  በማሾፍ መልክ መናገራቸውንና  ከፋና ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው ” የመጽሃፉ ትረካ ቢቋረጥ በሬዲዩ ጣቢያው ላይ የሚፈጥረው ችግር ታይቶ ቢያንስ ቢያንስ የአድማጭ አስተያየት ባለመቀበል ልናጠፋው እንሞክራለን” ሲሉ መልስ እንደሰጡዋቸውና ሰልጣኞችን ለማረጋገት እንደሞከሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ “መጽኃፉን አንብቤ እከታተለዋለሁ” ያሉት አቶ አዲሱ፣ ስህተቱ መፈፀም የለበትም ሲሉ አክለዋል፡
“ስህተቱ በኢትዮጵያ ውስጥ የሁቱና ቱትሲ አይነት ግጭት የሚፈጥር ነው” ያሉት አባላቱ፣ ከደቡብ ወንድሞቻችን ጋር የሚፈፀም ቅራኔን አንፈልገውም” ሲሉ ለአቶ አዲሱ ገልጸውላቸዋል።
ሟቹ ጠ/ሚ አቶ መለስ ዜናዊና አቶ በረከት ስምኦን መጽሀፉ እንዲታተም ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ ነበር ያሉት ምንጮች፣ ሬዲዮ ፋናም የሩዋንዳውን የራዲዮ ሚሊኮልን ስራ እየሰራ ነው ሲሉ” ተቃውመውታል።

Tuesday, January 14, 2014

አንዱዋለም ግንቦት ሰባት ከተባለ እኔም ግንቦት ሰባት ነኝ – ግርማ ካሳ


«በሕገ መንግስቱ የመደራጀት መብታቸው የተጠበቀላቸው ፓርቲዎችን አልከሰስንም።ፓርቲዎችን ግን ሽፋን አድርገዉ ስርዓቱን ወይንም ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ ኃይሎችን ግን ዛሬም ፣ ነገም ፣ ሕጉን የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት ስላለብን ከመከሰስ አያመልጡም ማለት ነዉ።»
ኢቲቪ በቅርቡ በ«ሽብርተኝነት» ላይ፣ በቅርቡ ባቀረበዉ አሳዛኝ ዶኩሜንተሪ ላይ ፣ የፌደራል መንግስት አቃቤ ሕግ፣ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ የተናገሩት ነበር።
እኝህ የሕግ ባለሞያ እየደጋገሙ ሕግን ስለማክበርና ስለ ሕገ መንግስቱ ነግረዉናል። ስለሕገ መንግስት ካነሳን አይቀር አንድ ነገር ጣል ላድርግ። የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29 ንኡስ አንቀጽ 4 «በመንግስት ገንዘብ የሚካሄድ ወይንም በመንግስት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙሃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል» የሚል ድንጋጌ ያካትታል። ኢቲቪ በሕዝብ ገንዘብ የሚተዳደር እንደመሆኑ ይህ የሕገ መንግስት አንቀጽ ይመለከተዋል። ነገር ግን ኢቲቪ በቀጥታ፣ ሕግ መንግስቱን ሲንድ፣ ገለልተኛነት በጎደለው መልኩ የአንድ ድርጅትን የፖለቲክ ፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ ሲሆን ነው እያየን ያለነዉ። እነ አንዱዋለም አራጌ ላይ፣ ኢቲቪ የአንድ ወገንን አቋም የያዘ፣ የስም ማጥፋት ዘመቻ ሲያዥጎደጉድ፣ ቢያንስ ቢያንስ ጥቂት ሰኮንዶች፣ የአንዷለምን ጠበቃዎች፣ ወይንም ቤተሰብ፣ አሊያም የትግል አጋሮቹ የሆኑት የአንድነት አመራር አባላትን ለማነጋገር አልተሞከረም። እንግዲህ ከዚህ የምንረዳዉ፣ ሕግን በማክበር አኳያ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴጎችና ኢቲቪ፣ አንድ ጣታቸዉን ወደሌሎች ሲጠቁሙ፣ አራቱ ጣቶቻቸው ወደ እነርሱ መዞራቸውን፣ ሕገ መንግስቱን እየጣሱ ያሉ እነርሱ መሆናቸውን ነዉ።
«አንዱዋለም አራጌን በተመለከተ፣ የግንቦት ሰባትን ተእልኮ ለማስፈጸም አገር ዉስጥ በሕቡእ (ስዉር) ይንቀሳቀሳል በሰላማዊ ትግል እንታገላለን የሚሉ የፓርቲዎችን ሽፋን አድርጎ ሲንቀሳቀስ የነበረ በመሆኑ በቂ ማስረጃ አቅርበናል» ሲሉ ነበር የፌደራል አቃቤ ሕጉ ለኢቲቪ አክለው የገለጹት። ምን አይነት መረጃ እንዳቀረቡ ግን አልነገሩንም። ለምን ቢባል ምንም ስለሌለ።
አንዱዋለም ያደርጋቸው የነበሩ እንቅስቃሴዎች በሙሉ ሲያደርግ የነበረው በግልጽና በገሃድ ነዉ። ለተለያዩ ፓልቶክ ክፍሎች፣ አገር ዉስጥና በዉጭ ለሚገኙ ሜዲያዎች በርካታ ቃለ መጠይቆችን ሰጥቷል። በአገር ቤት፣ በአንድነት ፓርቲ ዉስጥ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች በተደረጉ ዉይይቶችና ስብሰባዎች ያቀረባቸው ንግግሮች በሙሉ የተደበቁ አይደሉም። ዉጭ ካሉ ኢትዮጵያዊያን ጋር (አንዱም እኔው ነበርኩ) ፣ ብዙ ጊዜ በስልክ ሃሳቦችን ተለዋዉጧል። በስልክ ያደረጋቸው ንግግሮችም፣ 24 ሰዓት የሰላማዊ ተቃዋሚ መሪዎችን ስልክ በሚጠልፈው ቴሌ ዘንድ የተሰሙ ናቸው። ቤቱና ቢሮዉ ከላይ እስከ ታች ተበርብረዉ ፣ የሚስጥራዊ የኮሚኒኬሽን መሳሪያዎች፣ ቦምቦች፣ ፈንጂዎች፣ ሚስጥራዊ ሰነዶች አልተገኙም። ኤሜሎቹ በሙሉ ተነበዋል። አንዱዋለምን ከግንቦት ሰባት ጋር የሚያገናኝ፣ በሕቡእ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሆነ የሚያመለክት አንዳች መረጃ አቃቤ ሕግ አላቀረበም። መረጃዎች ቢኖሩ ኖሮ፣ «እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ» እንደተባለ፣ ዜጎችን በማዋረድና በማሳነስ የሚታወቀዉ ኢቲቪ፣ ይሄን ጊዜ በስፋት ያወራልን ነበር።
ኢቲቪ ግን አንዱዋለምን ለመክሰስ ያቀረበው፣ አንድ የአንድነት አባል የነበሩ፣ ተስፋሁን አናጋዉ የተባሉ ሰው የተናገሩትን ነዉ። አንዱዋለም ከታሰረ በኋላ አቃቤ ሕጎች መረጃ ማቅረብ ባለመቻላቸው፣ የዉሸት መረጃዎች ማሰባሰቡ የግድ ሆነባቸው። የታሰሩ ሌሎች የአንድነት አባላትን ማግባባት ጀመሩ። «በአንዱዋለም ላይ እኛ ተናገሩ የምንላችሁን ከተናጋራችሁ እንፈታቹሃለን» ብለው እጆቻቸዉን ጠመዘዙ። ብዙዎች በአንዱዋለም ላይ የዉሸት መረጃ ማቅረቡ ሕሊናቸውን ስለከበደው ፍቃደኛ አልሆኑም። ነገር ግን እንደ ተስፋሁን አናጋው፣ የሚባሉ ደካማ ሰዎች ተገኙና የዉሸት ምስክርነት ቀረበ። እንግዲህ በአገዛዙ ካድሬዎች ተቀናብረው ከቀረቡ የዉሽት ምስክርነቶች ዉጭ፣ ቅንጣት የምታክል፣ አንዱዋለምን ሽብርተኛ ወይንም ከግንቦት ስባት ጋር የሚሰራ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ አልቀረበም።
«ግንቦት ሰባት ፣ ግንቦት ሰባት ……» እንባላለን። ከጅምሩ በግንቦት ሰባት ላይ ጠንካራ ተቃዉሞ ያለኝ ሰው ነኝ። የግንቦት ሰባት ፖለቲካ አይመቸኝም፣ ለአገርም ይጠቅማል ብዬ አላስብም። ግንቦት ሰባቶች ከያዙት የተሳሳተ መንገድ እንዲመለሱ፣ በሻእቢያ ድጋፍ ሳይሆን፣ በሕዝብ ጉልበት በመተማመን ወደ ሰላሙ መንገድ እንዲመጡ መክሪያለሁ። በተለያዩ ጊዜያት ለአንባቢያን ያቀረብኳቸውን ጽሆፍችን መመልከት ይቻላል።
ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በአገር ዉስጥ በሰላም ለዉጥ ለማምጣት የሚሰሩ ድርጅቶችን ደግፊያለሁ። በተለይም የአንድነት ፓርቲ በጣም የሚመቸኝ ፓርቲ እንደመሆኑ፣ አንዱዋለም አራጌን ጨምሮ፣ ከፓርቲዉ አመራር አባላት ጋር ሃሳብ የተለዋወጥኩባቸው በርካታ ጊዜያት ነበሩ። አንዱዋለም አራጌ፣ እግዚአብሄርን የሚፈራ፣ የልጆች አባት፣ የሰላማዊ ትግል አርበኛ ነዉ። አንዱዋለም ስለ ትጥቅ ትግል ያለዉን አመለካከት አውቃለሁ። በየትኛዉም መድረክና ፍርድ ቤት፣ መጽህፍ ቅዱስ ላይ እጄን ጭኜ የምመሰክረዉ ነዉ። አንዱዋለም አራጌ የግንቦት ስባት አባል ወይንም ሽብርተኛ ነው የሚለውን፣ በምን መስፈርትና መልኩ ልቀበለው አልችልም። በርግጥ አንዱዋለም የግንቦት ሰባት አባል ከተባለ፣ እኔም የግንቦት ሰባት አባል ነኝ እንደ ማለት ነዉ።
በጣም ያሳዝናል። እንደ አንዱዋለም አራጌ አይነት አገር ወዳድ ዜጎች፣ አገራቸዉን በመዉደዳቸው፣ የሕዝብ መብት ይከበር በማለታቸው፣ «ሽብርተኞች» በሚል አሳዛኝ ክስ ሲታሰሩ ማየት፣ አገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች ቀና ብለው የሚራመዱባት ሳይሆን ፣ አሳፋሪ ድራማ የሚካሄድባት፣ ሕግ መቀለጃ የሆነባት አገር መሆኗ፣ በርግጥ ልብን የሚያደማ ነው።
እንግዲህ፣ ሁሌ እንደማደርገዉ፣ ጥሪ ለኢሕአዴጎች አስተላልፋለሁ። ኢሕአዴግ ዉስጥ፣ ለአገርና ለሕዝብ የሚያስቡ ካሉ፣ በድርጅታቸው ዉስጥ እየተደረገ ያለውን አፈናና ግፍ በቃ የማለት አቅምና ጉልበት ሊኖራቸው ይገባል ባይ ነኝ። ድርጅታቸው ዉስጥ ያሉ ጥቂቶች ድርጅታቸውን ይዘው ገደል እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም። እነ አንዱዋለምን በማሰር ኢሕአዴግ ምንም የሚጠቀመው ነገር የለም። እነ አንዱዋለምን በዉሸት ክስ ከሶ፣ በቴለቭዥኝ ደግሞ ስማቸውን ማጉደፍ፣ ነዉር ነዉ። ኢሕአዴግ የበለጠ እንዲጠላ የሚያደርግ ነዉ። የአረና ትግራይ አመራር አባል አብርሃ ደስታ አንዴ ሲጽፍ፣ የሕወሃት እምብርት በነበረችው የትግራይ ክልል፣ አንዱዋለም አራጌ በጣም ተወዳጅ ፖለቲከኛ እንደሆነ ገልጾ ነበር። አንዱዋለም አራጌ፣ በክልሎች ሁሉ ሕዝብ የሚያውቀዉ ጀግና መሪ ነዉ። በርሱ ላይ እየተደረገ ያለው ዘመቻ፣ የበለጠ አንዱዋለምን ከፍ የሚያደርግ፣ ኢሕአዴግን ደግሞ የሚያሳንስ ነዉ። አንዱዋለምን እና ሌሎች የሕሊና እስረኞች፣ አለመፍታት በቀጥታ ከሕዝቡ ጋር እንደመላተም ነው። አይጠቅምም። ጉዳት አለው።
ለኢሕአዴጎች ጥሪ ባቀርብም፣ የነአንዱዋለም ጉዳይ፣ የኢሕአዴጎች ጉዳይ ብቻ ግን አደለም። ኢሕአዴጎች ወደ ሕሊናቸው ተመልሰው መልካም ነገር ያደርጉ ዘንድ እነርሱን ማነጋገርና ለማሳመን መሞከር፣ ማበረታታት ተገቢ ነዉ የሚል እምነት ቢኖረኝም፣ ሁሉንም ነገር ከነርሱ ጠብቆ ቁጭ ማለቱ ግን፣ እጅግ በጣም ትልቅ ስህተት ነው። እነርሱ ቢሰሙ መልካም ነዉ፤ ካልሆነ ግን እያንዳንዳችን መብታችንን የማስከበር ሃላፊነት ያለብን ይመስለኛል። ዛሬ እነ አንዱዋለም ናቸው። ነገ እያንዳንዳችን ቤት ይንኳኳል ። ዛሬ ሊመቸን ይችላል። ነገር ግን ለሕይወታችን ምንም ዋስትና አይኖረንም። አንድ የመንግስት ባለስልጣን ፊታችንን አይቶ ከጠላን፣ በቀላሉ ወደ ወህኒ ሊወረወረን የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ ማወቅ አለብን። አለን የምንለውን ቢዝነስ አንዱ ከፈለገዉ፣ «ያለ የሌለዉን እያመጡ፣ ይሄን ያህል ግብር ክፈል» ተብለን ከጨዋታ ዉጭ በቀላሉ ልንሆን የምንችልበት አገር ነዉ ያለችን። አቤት የምንልበት የሕግ ስርዓት የለም። አብዛኞቹ ዳኞች በመመሪያ የሚፈርዱ ካድሬዎች ናቸው። በመሆኑም፣ ኢትዮጵያ፣ ሕግ የበላይ የሆነባት፣ ለሁሉ ዜጎቸ እኩል የሆነች፣ ኢትዮጵያዊያን ሳይፈሩና ሳይሸማቀቁ ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ የሚችሉባት፣ መቀባባል፣ ይቅርታ፣ ፍቅር፣ ሰላም ፣ ፍትህና ወንድማማችነት የሰፈነባት፣ የበለጸገች አገር እንድትሆን፣ እያንዳንዳችን የድርሻችንን መወጣት አለብን። ዳር ሆኖ ተቀመጦ ማውራት ይብቃ። ሌሎች ለምን እንዲህ አላደረጉም ብሎ መክሰስ ይብቃ። ሌሎች ሞተው በነርሱ አስክሬን ላይ ተረማመደን ለመሻሻል መሞከር ይብቃ። አገራችን የእስክንደር፣ ወይንም የአንዱዋለም፣ ወይንም የበቀለ ገርባ፣ ወይንም የርዮት አለሙ ብቻ ሳትሆን የሁላችንም ናት፣ ሁላችንም ተስፋ ሳንቆርጥ፣ ሌሎች ነጻ እንዲያወጡን ሳንጠብቅ፣ የድርሻችንን እንወጣ።

Women’s Rights Group Demands Release of Jailed Award-Winning Ethiopian Journalist



BY NICHOLAS IBEKWE
A global women’s rights and advocacy group, Safe World for Women, has put up an online petition for the immediate release of jailed award-winning Ethiopian journalist with breast tumour, Reeyot Alemu.
Ms. Alemu, 34, who is also a teacher, was jailed under the nebulous Ethiopian anti-terrorism law for her criticism of the intolerant government in Addis Ababa. On June 21, 2011, she was arrested from the school where she teaches and kept in an undisclosed location.
Four days earlier, she had written a critical article about the fund-raising method for a dam project by the ruling political party in her country comparing then Prime Minister of Ethiopia, Meles Zenawi, with late Libyan leader, Muammar Gaddafi. She was subsequently charged with supporting an unnamed terrorist organisation but her specific crimes were not listed. In 2009, the Ethiopian government passed a vaguely worded and far-reaching anti-terrorism law that allows it to charge anyone thought to be encouraging terrorism.
Ms. Alemu was initially sentenced to 14 years in prison and fined about $2,000 (N319, 580) but an appeal court later commuted the sentence to five years. During her trial a government prosecutor presented articles she had written criticising the prime minister and telephone conversations about peace protest as evidence against her.
Despite her failing health, she refused an offer of clemency in exchange for providing information on other journalists. She was placed in solitary confinement for two weeks as punishment.
In 2012, the International Women Media Foundation, WMF, presented the Courage in Journalism Award to Ms. Alemu in absentia for her “refusal to self-censor in a place where that practice is standard, and her unwillingness to apologize for truth-telling, even though contrition could win her freedom.”
“I believe that I must contribute something to bring a better future… Since there are a lot of injustices and oppressions in Ethiopia, I must reveal and oppose them in my articles,” she told the IWMF in an earlier interview.
She is also the 2013 winner of UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize.
She was held for three months before the trial without the opportunity of a counsel during the trial proper. Her charges were never read to her and the witnesses used by the prosecutor were anonymous. Before the trial, the government also ran a documentary on national television profiling her as a terrorist.
 
Ethiopia
Miscommunication – Telecoms Expansion Targets Quantity Not Quality
Although ethio-telecom is in the midst of an expansion to increase the number of service beneficiaries, such as mobile

Despite the tumour in her breast, she is being denied proper medical care. Her father, the only person allowed to see her said her breast is bleeding. She might lose the entire breast, even die, if she does not get prompt attention.
Amnesty International described her continued detention as an “affront to freedom of expression.”
The Ethiopian government is one of the most intolerant governments in the world.
The Committee to Protect Journalists, CPJ, said, “Ethiopia has refused to comply with a decision by the U.N. special rapporteur on torture in the case of Reeyot.”
“Woubshet Taye, Reeyot Alemu, and Elias Kifle have been sentenced solely in relation to their peaceful exercise of their right to freedom of expression, in violation of Article 19 of the International Covenant on Civil and Political Rights and Article 9 of the African Charter on Human and People’s Rights, to which Ethiopia is a signatory. We therefore protest the harsh sentences handed down to them and call for the immediate and unconditional release of Taye and Alemu,” said the PEN American Centre.
The petition will be sent to the United Nations’ UN Special Rapporteur on the promotion and protection of the right to freedom of expression, Frank William La Rue, UN Special Rapporteur on Violence against Women, its causes and consequences, Rashida Manjoo, and UN Special Rapporteur on torture and other cruel, inhuman or degrading treatment or punishment Juan Méndez. A copy will also be sent to Permanent Representative of the Ethiopia to the UN, Tekeda Alemu.
The Petitioner seeks 10,000 signatures; so far only 810 people have signed it. Interested people can sign it on http://chn.ge/1iGxvQj
Source allafrica.com

Saturday, January 11, 2014

የግል መጽሔት አዘጋጆች፤ “የፅንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳናት ሆነዋል” መባላቸውን አጣጣሉ ሪፖርቱ የአደጋ ምልክት ነው ብለዋል


Meshat
“በኢትዮጵያ የሚታተሙ ሰባት የግል መጽሔቶች የጽንፈኛ ፖለቲካ ልሳናት ሆነዋል፤ በሚያቀርቧቸው የተሳሳቱ መረጃዎች ህዝቡ በስርአቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ ያደርጋሉ” ሲል የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትና የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በጋራ ያሠሩት የጥናት ሰነድ አመለከተ። የመጽሔቶቹ አዘጋጆች በበኩላቸው፤ ሪፖርቱን ያጣጣሉ ሲሆን ለመጽሔቶቹ የአደጋ ምልክት መሆኑን ግን አልሸሸጉም፡፡ ተቋማቱ ያስጠኗቸው አዲስ ጉዳይ፣ ፋክት፣ ሎሚ፣ ቆንጆ፣ ጃኖ፣ ዕንቁና ሊያ መጽሔቶች ሲሆኑ ከመስከረም 1 ቀን እስከ ህዳር 30 ቀን 2006 ዓ.ም ባወጧቸው ህትመቶች ላይ በተደረገ የአዝማሚያ ትንተና መሠረት፤ መጽሔቶቹ የግል መገናኛ ብዙሃን ሳይሆኑ የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሣናት ሆነዋል ተብሏል፡፡ መጽሔቶቹ በሚያቀርቧቸው የተሳሳቱ መረጃዎች ይዘት፣ ህዝቡ በስርአቱ ላይ እምነት አጥቶ ለአመጽ እንዲነሳሳ የሚያደርጉና የቀለም አብዮት ባስተናገዱ አገሮች የታየውን ቅኝት የሚከተሉ ሆነው ይታያሉ ብሏል – የጥናት ሰነዱ፡፡ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ በረቡዕ እትሙ የጥናት ሰነዱን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ “የሁሉም ጽሑፎች ይዘት ያተኮረው አሉታዊ ጉዳዮችን በማራገብ፣ መረጃዎችን አዛብቶ በማቅረብ፣ መንግስት በልማት፣ በሰላምና በዲሞክራሲ መስኮች ያመጣቸው ለውጦች የሌሉ በማስመሰል እንዲሁም ህዝቡ ከችግር ለመውጣት የሚያደርገው ጥረት ላይ በማሾፍና በማንኳሰስ ነው” ብሏል፡፡
ሁሉም መጽሔቶች የጋራ የመረጃ ምንጮችን ይጠቀማሉ ያለው ሰነዱ፤ የኒዮሊበራል አክራሪ ሃይሎች ድርጅቶች፣ ተቋማትና ግለሰቦች፤ ለህገመንግስታዊ ስርአቱ እጅግ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው የድሮ ስርአት ናፋቂዎችና በሽብር ወንጀል የተፈረደባቸው ግለሰቦችና ቡድኖች ሲል ዘርዝሯቸዋል፡፡ “አዲስ ዘመን” ጋዜጣ ላይ የወጣውን የጥናት ሪፖርት በተመለከተ ያነጋገርናቸው የግል መጽሔቶች አዘጋጆች፤ “የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሣናት ሆነዋል” በሚል የወጣውን ትንተና ያጣጣሉት ሲሆን ጥናቱ ከዚህ ቀደም በታየው ልምድ መሠረት ለመጽሔቶቹ የአደጋ ምልክት ነው ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በሪፖርቱ ከተካተቱት መጽሔቶች መካከል የእንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ፤ “ጥናቱ የግሉን ፕሬስ ሆን ብሎ ለማሸማቀቅ እና ለመወንጀል የወጣ ነው” ሲል ተችቶታል፡፡
የጥናቱ ምንጭ የሆኑት ሁለቱ ተቋማት የመንግስት እንደመሆናቸው ገለልተኛ ናቸው ለማለት እቸገራለሁ ብሏል አዘጋጁ። “የፅንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሣናት” የሚለው አገላለጽ በየአስራ አምስት ቀኑ የምትወጣውን “ዕንቁ” መጽሔትን አይወክልም፤ እኛ ከጋዜጠኝነት መርህ አኳያ እንሠራለን እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ ልሣን አይደለንም፤ ልንሆንም አንችልም ብሏል – ዋና አዘጋጁ፡፡ “ነገር ግን መንግስት አካሄዱን እንዲያስተካክል በመረጃ ተደግፈን እንተቻለን፣ የምንሠራው ህግና ስርአቱን አክብረን ነው” ሲል ገልጿል፡፡ ሪፖርቱ ለመጽሔቶቹ የአደጋ ምልክት መሆኑን የጠቀሰው ዋና አዘጋጁ፤ በተለይ መጽሔታቸውን ከሽብርተኝነት ጋር ማያያዙና የአመጽ ጥሪ አቅራቢ እያለ መወንጀሉ በስራቸው ላይ ከባድ ስጋት እንደሚፈጥርባቸው ገልጿል፡፡ ከዚህ በፊት በመንግስት ላይ ጠንካራ ትችት ያቀርቡ የነበሩ ጋዜጦችም የዚህ መሰሉ ውንጀላ ሠለባ ከሆኑ በኋላ ነው የተዘጉት ያለው ኤልያስ፤ የአሁኑ ሪፖርትም በመጽሔቶቹ ላይ ትልቅ አደጋ እንደተደቀነ የሚያመላክት ነው ብሏል፡፡
ከሰላሳ በላይ ገፆች ያሉትን የጥናት ሪፖርት እንዳነበበ የገለፀው የ “ቆንጆ” መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ካሣ በበኩሉ፤ መንግስት በቀጣዩ ምርጫ መጽሔቶች ስጋት ይሆኑብኛል ብሎ በመፍራቱ ነው እንዲህ ያለ ሪፖርት ያወጣው ሲል ተናግሯል፡፡ መጽሔታችን ሚዛናዊነትን ጠብቆ የጋዜጠኝነት ሚናውን እየተወጣ እንጂ የየትኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ልሣን አይደለም ያለው ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤ መንግስት የግሉ ፕሬስ ስላልተመቸው በርግገው ከሃገር ይሰደዳሉ በሚል እምነት ነው ይሄን ያደረገው ብሏል፡፡ በተለይም የአጥኝዎችን ማንነት ስንመለከት ዋና ስራቸው ዜናዎችን መቀበልና ማሠራጨት እንጂ ጥናት እያጠኑና እያስጠኑ፣ ደረጃ እንዲመድቡ ወይም እገሌ መጽሔት ይሄን ያህል በመቶ ሽብርተኝነትን ቀስቅሷል፣ ይሄን ያህል በመቶ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገቱን ክዷል በሚል መፈረጅ አይደለም ሲል ተችቷል፡፡ ከዚህ ቀደም የነበሩት ጋዜጦች የከሰሙበትን መንገድ ሲያስታውስም፤ “ብዙውን ጊዜ በአዲስ ዘመን ላይ ትችቶች በተከታታይ ይቀርባሉ፣ በቴሌቪዥን ዶክመንተሪ ይሰራበታል፤ ከዚያም የህዝብ አስተያየት ተብሎ ይሰበስብና ይወገዛል፤ በሂደትም መጽሔቶቹንና ጋዜጦቹን በተለያዩ ክሶች በማዳከም እንዲከስሙ ይደረጋል” ያለው ቴዎድሮስ፤ ይህ መሰሉ ልምድ ባለበት ሁኔታ የዚህ ሪፖርት መውጣት ከፍተኛ ስጋት ይፈጥርብናል ብሏል፡፡
“ጥናቱን ያደረጉት የመንግስት ተቋማት ምን ለማለት እንደፈለጉ ይገባናል፤ እዚህች ሃገር ላይ የፕሬስ ነፃነት እንዲኖር አይፈልግም” ያለው የሳምንታዊው ሎሚ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር፤ የጥናቱ ሪፖርት በግል መጽሔቶቹ ላይ እርምጃ ሊወሰድ መታሰቡን የሚጠቁም ነው ብሏል። “መጽሔቶች የጽንፈኛ ፖለቲካ ልሣናት ናቸው የተባለው እንደልብ የምናገኛቸውን የመረጃ ምንጮች ስለምንጠቀም ነው” ያለው ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤ የመንግስት ባለስልጣናትን ቃለ መጠይቅ ለመስራት ስንሞክር አናገኛቸውም ብሏል፡፡ ጥናቱን የሠሩት ተቋማት እኛን ከመፈረጅ ይልቅ በማተሚያ ቤቶች ያለብንን ችግርና ወረቀት ከውጭ ሀገር ለማስመጣት ያለውን ፈተና ለምን አያጠኑም ሲልም ጠይቋል – ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፡፡ የሊያ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር መላኩ አማረ በበኩሉ፤ በጥናቱ የተገለፀው ፍረጃ የመጽሔታቸውን ባህሪ እንደማያንፀባርቅ ገልፆ፤ ከሪፖርቱ በተቃራኒው የህብረተሰቡ ልሣን በመሆን እየሠሩ መሆኑን ተናግሯል፡፡
ጥናቱ ሚዛናዊነት የጐደለው ነው ያለው መላኩ፤ ጥናቱ ተደረገ የተባለባቸውን ያለፉትን ሶስት ወራት የመጽሔቶች ህትመት እንዳየና ከተወነጀሉበት “የፅንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሣናት” አስተሳሰብ የራቁ ጉዳዮችን ሲያነሱ እንደነበር ማረጋገጡን ገልጿል። የፕሬስ ትልቁ አላማው የፖለቲካ አስተሳሰብና የህዝቡን ሃሳብ በነፃነት ማንሸራሸርና ማስተላለፍ ነው ያለው ማኔጂንግ ዳይሬክተሩ፤ ሪፖርቱ ምናልባትም የመጽሔቶቹ ቀጣይ ህልውና ላይ ቀይ ምልክት የሚያበራ በመሆኑ አዘጋጆችን የበለጠ የሚያሸማቅቅና ሥጋት ላይ የሚጥል ነው ብሏል። “መንግስት ፕሬሶችን ለማጥፋት ሲፈልግ ቀይ መብራት የሚያሳየው አዲስ ዘመን ላይ በሚወጡ ትችቶች ነው” ያለው መላኩ፤ የረቡዕ እለቱን የጋዜጣውን እትም ለየት የሚያደርገው ርዕሰ አንቀፁም ጭምር የኛ ጉዳይ ላይ ማተኮሩ ነው ብሏል፡፡ የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ዮሐንስ ካሣሁን ስለጉዳዩ በሰጠው አስተያየት፤ “የጽንፈኛ ፖለቲካ ፓርቲ ልሣን” የሚለው ፍረጃ ለእኛም አዲስና ያልጠበቅነው ስለሆነ ተገርመናል፤ እኛ የምንሠራው የጋዜጠኝነትን ሙያ እንጂ ሌላ አይደለም ብሏል። “ቀደም ባሉት የአዲስ ዘመን እትሞች ላይ ‘አዲስ ጉዳይ’ን የሚያብጠለጥሉ ጽሑፎች ሲስተናገዱ ተመልክተናል፡፡ እኛም ለትችቶቹ መልስ ስንሰጥ ከርመናል፡፡ ይሄኛውም ከዚያ የተለየ አይሆንም” ሲል አስተያየቱን ሰንዝሯል፡፡ በመጽሔቶቹ ላይ የተደረገው ጥናት ያተኮረው “የመንግስት ኀላፊዎችን የግል ስብዕና የሚነኩ፣ የአመጽ ጥሪዎችን የሚያስተላልፉ፣ ሽብርተኝነትን የሚያበረታቱ፣ የፖለቲካ ስርአቱን የሚያጨልሙ፣ የኢኮኖሚ እድገቱን የሚክዱና ህገመንግስቱን የሚያጣጥሉ” በሚሉ ነጥቦች ላይ ሲሆን በተከታታይ ህትመቶች የተነሳበት ድግግሞሽም ሆነ በአንድ ህትመት የተለያዩ አምዶች የተነሳበት ብዛት በቁጥር መተንተኑ ተገልጿል፡፡
Source-www.addisadmas.com

Thursday, January 9, 2014

ሰማያዊ ፓርቲ ሀሳቡን በኢሳት ላይ ለመግለጽ የማንንም ይሁንታ እንደማይጠይቅ አስታወቀ

ፓርቲው "የምንናገርበትን የመገናኛ ብዙሃን ማንም እንዲመርጥልን ወይም እንዲወስንልን አንፈቅድም" በሚል ርእስ ባወጣው የአቋም መግለጫ፣ " ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም እንዲወስንለት የማይፈልግ መሆኑን ግልፅ " አድርጓል።
"በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠውን ማንም ሰው በመረጠው መንገድ ሃሳቡን የማስተላለፍ መብቱን በመጠቀም በኢሳትም ሆነ እድሉን ካገኘ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቋሙንና እምነቱን ማስተላለፍ የሚቀጥል መሆኑን ማረጋገጥ ይወዳል" በማለት ፓርቲው በኢሳት ላይ ቀርቦ አቋሙን ከመግለጽ እንደማይገታ ግልጽ አድርጓል።

ሰማያዊ ፓርቲ ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓም በኢቲቪ የተላላፈውን ዶክመንታሪ ፊልም "የእብሪት መልዕክት" ያዘለና እና "ከተራ ርካሽ ፕሮፓጋንዳነት የማያልፍ የሕግና የዲሞክራሲያዊ መብት ገደብን ካለማወቅ የሚመነጭ አስተሳሰብ ነው" ሲል አጣጥሎታል።

"የብሔራዊ ደህንነት መረጃ እና የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል በተደጋጋሚ ጊዜ በሽብር ወንጀል ጠርጥሬአቸዋለሁ የሚላቸውን ሁሉ በመክሰስ ወደ እስር ቤት እንዲወርዱ እያደረገ ጉዳያቸው የፍርድ ቤት ውሳኔ ሳያገኝ እንደፈለገ በሚቆጣጠረው ወይም በሚያዘው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንና ሬዲዮ ድርጅት አማካኝነት የፈለገውን ዓይነት ፍረጃና ሥም ማጥፋት ሲያካሒድባቸው" መቆየቱን ያስታወሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ይህ ራሱን ከሕግ በላይ የሰቀለ አካል ያለምንም ገደብ ከሚሰራቸው ተግባራት እንዲታቀብ በሕግ የሚያስቆመው በመጥፋቱ እስካሁን የፈፀማቸውን የማንአለብኝነት ተግባራት እንደጥፋት ሳይሆን እንደ መልካም ሥራ ቆጥሯቸው በተመሳሳይ የሥም ማጥፋትና የፍረጃ ተግባሩ እንዲገፋበት አድርጎታል" ብሎአል።
“ኢሳት” የተባለ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ መንግስት በሽብርተኝነት ከተፈረጀ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገለትና በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በተለይም ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እንዳይጠቀም የማስጠንቀቂያ ዛቻ ተላልፎለታል" ሲል ያስታወሰው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ይህ አስፈራሪ አካል ራሱን ሕግ አውጭና ሕግ ተርጓሚ በማድረግ የዚህች ሐገር ዜጎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትንና የማይገልጹበትን የመገናኛ ብዙሃን እየወሰነላቸውና እየመረጠላቸው ይገኛል፣ ብሎአል ።

የገዥው ቡድን ሰዎች ሀሳብን በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይችሉ ስለሚያውቁት የቀራቸው አማራጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ሃሳባቸውን የሚያሰራጩባቸውን መንገዶች መዝጋት ብቻ መሆኑን ፓርቲያችን ይገነዘባል ያለው ሰማያዊ ፓርቲ፣ ማንም አካል በሕግም ሆነ በሞራል ተጠያቂ የሚሆነው የሚያስተላልፈው መልዕክት ይዘት የሌሎችን ዲሞክራሲያዊና ሞራላዊ መብት የሚጋፋ መሆን አለመሆኑ እንጂ ገዥው ቡድን በጠላው ወይም በወደደው የመገናኛ ብዙሃን መልዕክቱን ማስተላለፉ አይደለም" ሲል አቋሙን ግልጽ አድርጓል፡፡ መልዕክትን የገዥው ቡድን ሰዎች በጠሉት የመገናኛ ብዙሃን ማስተላለፍ በራሱ ወንጀለኛ ወይም ሽብርተኛ ለማድረግ የሚያበቃ ምንም ዓይነት የሕግ መሰረት እንደሌለውም ገልጿል፡፡
ፓርቲው በመጨረሻም " ሰማያዊ ፓርቲ መልዕክቱን የሚያስተላልፍበትን መገናኛ ብዙሃን ማንም አካል እንዲመርጥለት ወይም በዚሁ አጋጣሚም የፓርቲያችንን መልካም ስም በሃሰት ለማጉደፍ የተሰነዘሩ ቃላትን በቀላሉ የማንመለከታቸው መሆኑን ሕግ ባለበት ሐገር ራስን ከሕግ በላይ በማስቀመጥ ማንንም አካል መፈረጅና ስም ማጉደፍ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑን የዘጋቢ ፊልሙ ባለቤቶች እንዲያውቁትና ወደፊትም ተመሳሳይ ድርጊት ከመፈፀም እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡" ብሎአል።

በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ሰማያዊ ፓርቲ እና አንድነት ፓርቲ በኢሳት ላይ ቀርበው አቋማቸውን እንዳይገልጹ መንግስት ሰሞኑን ምክር አዘል ማስጠንቀቂያና ማስፈራሪያ በኢቲቪ አማካኝነት መስጠቱ ይታወሳል።
ከመጪው ምርጫ ጋር ተያይዞ ኢሳት ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ፕሮግራሞቻቸውንና መልእክቶቻቸውን በነጻ እና ያለገደብ የሚያስተላልፉበትን አሰራር በመቀየስ ላይ ነው።
ESAT

ከመር የሱፍ የተባለው የኦሮመኛ ዘፋኝ ሚኒሊክን የአፍሪካ ሂትለር በማለት አዲስ ዜማ አወጣ

ከመር የሱፍ በሚኒሊክ ዙሪያ ዜማ እንደሚያወጣ በቅርቡ ዜናችን ማስነብባችን ይታወሳል::በዚህ ሳምንት ብቻ ከአዲስ አበባ ጸረ ሚኒሊክና ቴዲ አፍሮ መልእክት ያላቸው ዜማዎች ተለቀዋል  :: የከመር የሱፍን  ethiotube.net  የሙዚቃ ክሉቡን በድህረገጹ Kemer yesuf is back   በማለት አውጥቶታል:: ethiotube ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቴዲና ሚኒሊክ  ላይ በሚካሄደው ዘመቻ ላይ ከኦሮሞ ፈርስት ከሚባለው ዘረኛ ድርጅት ጋር መቆሙን በተደጋጋሚ አስመስክርዋል::ጃዋር መሀመድ ኢትዮቱዩብ አምስተኛ አመቱን ሲያከብር የክብር እንግዳ እንደነበር የሚታወስ ነው::
ethiotube-anti-teddy-afro 
ባለፈው በአብዲ ፈቲ የተባለ የኦሮሞ ፈርስት አባል የተሰራውን  የቴዲን ስም እንዲሁም  በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች   አይን ያወጣ ስድብና ዘለፋን ያካተተን video   “ቴዲን አጋለጠው “በሚል አጋነው ምስሉን ድህረገጻቸው ላይ ፖስት ማድረጋቸው ሚታወስ ነው::

Wednesday, January 8, 2014

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት ወታደራዊ ጥቃት ፈፀመ


በሀገራችን ላይ የተንሠራፋውን አምባገነናዊ ሥርዓት ገርስሶ ለመጣል የመጨረሻ አማራጭ የሆነውን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ የሚወስዳቸውን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃዎች አጠናክሮ በመቀጠል በታህሳስ 23 ቀን 2006 ዓ/ም በሰሜን ጎንደር በላይ አርማጭሆ ወረዳ ልዩ ስሙ ገራርዋ ባምብላ ወንዝ በተባለው ቦታ መሽጎ የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያሰቃይና ሲያንገላታ ከነበረው የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር እና ከፀረ-ሽምቅ ታጣቂ ኃይሎች ጋር ባደረገው ውጊያ 24 የጠላት ወታደሮችን ገድሎ 11 በማቁሰል የግንባሩ ሠራዊት አንፀባራቂ ድል አስመዝግቧል፡፡ በዚሁ ዕለትም በተደረገው እልህ አስጨራሸ ውጊያ የወያኔ 24ኛ ቴዎድሮስ ክ/ጦር ከኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የሚደርስበትን የተኩስ ናዳ መቋቋም ተስኖት ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ እግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጡን ታውቋል::
ይህ በእንዲሀ እንዳለ የአካባቢው ነዋሪዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት በጠላት ላይ ባስመዘገበው ከፍተኛ ወታደራዊ ድል መደሰታቸውና ወደፊትም ሀገራዊና ሕዝባዊ አላማን አንግቦ የህብረተሰቡን እምባ በማበስ ግንባር ቀደም በመሆን ለሀገርና ለወገን ደራሽነቱን እያስመሰከረ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊትን በመደገፍ የቆመለትን አላማ ከግብ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀው ግንባሩ በተከታታይ ጊዜያቶች የሚወስዳቸው ወታደራዊ ጥቃቶችና የሚያስመዘግባቸው አንፀባራዊ ድሎች የወገንን አንጀት በማራስ በአንፃሩ ደግሞ የጠላትን አንገት በማስደፋቱ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የአካባቢው ህብረተሰብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሠራዊት የጀግና አቀባበል ያደረጉለት ሲሆን ወታደራዊ የማጥቃት እርምጃው ተጠናክሮ እንዲቀጥል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ከግንባሩ ሠራዊት ጎን በመሰለፍ ሀገራዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ቆርጠው መነሳታቸውን አስታውቀዋል፡፡