የልደት ቃለ ምዕዳን
“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ስምረቱ ለሰብእ”
“ክብር ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ሰላምም በምድር፣ ለሰውም በጎ ፈቃድ ይሁን።” /ሉቃ 2፣14/
በቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ፣ እንዲሁም በመላው ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም በጤና አደረሳችሁ። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

ወያኔ የጫካ ዉስጥ ኑሮ በቃኝ ብሎ አዲስ አበባን ከረገጠ በኋላ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብዙ አዳዲስ ቃላት ተፈጥረዋል፤ አንዳንድ አብረናቸዉ ያደግናቸዉ ቃላትና የቦታ ስሞች ደግሞ እየፋፉ መጥተዉ የሌሎች ሰፋ ያሉ ሀሳቦች መግለጫ ሆነዋል። ለምሳሌ የዛሬ ሃያ አምስት አመት ኮሌጅ የጨረሰ ልጅ አባቱን ቃሊቲ መግባቴ ነዉ ብሎ ቢነግረዉ አባቱ . . . . ምንዉ ስራ አገኘህ እንዴ ብሎ ከመጠየቅ ዉጭ በልጁ አባባል በፍጹም አይደነግጥም። ዛሬ ግን “ዕድሜ ለወያኔ” ቃሊቲ ሲባል የማይደነግጥ ኢትዮጵያዊ የለም። በፋብሪካ ማዕከልነቷ ትታወቅ የነበረችዉ ቃሊቲ ዛሬ አጥሩ ዉስጥ ወያኔ አፍኖ የከተታቸዉ ሰላማዊ ዜጎች ከአጥሩ ዉጭ ደግሞ የእነዚሁ ሰላማዊ ዜጎች ቤተሰቦች የሚተራመሱበት የጭንቅና የመከራ አምባ ሆናለች። አዎ ቃሊቲ እንደ አልባኒያዋ ቡሪልና እንደ ሩሲያዋ ሳይቤሪያ ዜጎችን ለማፈንና በዜጎች ላይ ሰቆቃ ለመፈጸም ሆን ተብላ እንደገና የተፈጠረችና አለፍላጎቷ አስቀያሚ ገጽታ የተከናነበች ከተማ ሆናለች። ቃሊቲ ታሪክ ከክፋታቸዉና ከጭካኔያቸዉ ዉጭ በፍጹም የማያስታዉሳቸዉን የሩሲያዉን ጆሴፍ ስታሊንና የአልባኒያዉን ኤንቨር ሆዣን እኛ ኢትዮጵያዉያን አለዝምድናችን በግድ እንድናስታዉሳቸዉ የተገደድንባት የአምባገነንነት ተምሳሌት ናት። የሚገረመዉ ቃሊቲ ወያኔ ተሸክሞ ካመጠልን የጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ መንታ ትዝታዎች አንዷ ናት። ጆሴፍ ስታሊንና ኢንቨር ሆዣ የሩሲያንና የአልባኒያን ህዝብ እስር ቤት ዉስጥ ብቻ አልነበረም ያሰሩት፤ አንድ ለአምስት በሚሉት ማለቂያ በሌለዉ ሰንሰለታቸዉ በመኖሪያ ቤቱ ዉስጥ፤ በሚሰራበት ፋብሪካ ዉስጥ፤ በሚማርበት ት/ቤቶች ዉስጥና በተደራጀበት ገበሬ ማህበር ዉስጥ ጭምር ጭምድድ አድርገዉ አስረዉታል።