Tuesday, June 24, 2014

ደምወዝ ጭማሪ ..የምርጫ ጉቦ …

በደምወዝ ጭማሪ የመንግስት ሰራተኛውን የፖለቲካ ባሪያ ማድረግ አይቻልም።ደምወዝ ተጨምሮልሃል የተባለው ከመጋረጃ ጀርባ አንገቱን እንዲሰብር እየተደረገ ያለው የመንግስት ሰራተኛ ማንን እንደሚመርጥ እና ድምጹንም እንደማያባክን ጠንቅቆ ያውቃል። የደሞዝ ጭማሪው የወያኔን አጣብቂን ውስጥ መዘፈቅን ያሳያል።
ውሻ ጆሮውን ቆርጠው ቢሰጡት ስጋ የሸለሙት ይመስለዋል .በሚል ወያኔያዊ የፖለቲካ ብሂል ተነስቶ ለመንግስት ሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚፈልግ በሹመኛው አማካኝነት ተናግሯል። በኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ እና ለሃገር ዋናው ዋልት ይሆነው የመንግስት ሰራተኛው ባለፉት 23 አመታት የታላላቅ ግፎች ተሸካሚ የኢኮኖሚ በሽተኛ ሆኖ እየኖረ ያለ ሲሆን ብሄሩ እየተለየ እና የፖለቲካ እምነቱ እየተመዘነ ሲንገራተት የደረጃ እርከን እና የደምወዝ ችማሪ ሲከለከል እንዲሁም ከስራ ሲፈናቀል እና ቤተሰቡ ሲበተን ሲሰደድ የነበረ እና ያለ የሚኖር የመንግስት ሰራተኛው የፖለቲካ ባሪያ ለማድረግ በኢሕ አዴግ የማይቆፈር ጉድጓድ የለም ።
በወያኔ የሚመራው የወንበዴዎች ጁንታ ስልታኑን ከተቆጣጠር ጀምሮ የመንግስት ሰራተኛውን መሰረታዊ ማህበራት በማፍረስ ለሰራተኛው የሚከራከሩትን የመብት ተማጓቾች እና የሰራተና ማህበር መሪዎችን እንዲሰደዱ ከስራቸው እንዲፈናቀሩ በማያውቁት የፈጠራ ወንጀል እንዲታሰሩ ወዘተ ተመሳሳይ እኩይ ተግባራትን በመፈጸም በራሱ መልክ እና አምሳል ጠፍጥፎ የሰራቸውን ማህበራት እና አመራሮች በማስቀመጥ እንዲሁም በየምስሪያ ቤቱ ያልተማሩ እና ልምድ የሌላችው በፖለቲካ እምነታቸው ብቻ እንዲመደቡ እየተደረገ በየክፍሉ የደህንነት ቡድን በማደራጀት አንድ ለአምስት እየጠረንፈ ሰራተኛውን በማሰቃየት ዛሬ የምርጫ ቀን ሲደርስ የምረጡኝ ጉቦ የሆነውን የደምወዝ ጭማሪ ማድረግ ማንን ለማታለል ነው ?
በኑሮ ውድነት ናላው የዞረው የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ እዳ ውስጥ እና አተዳደራዊ በደል ውስጥ ገብቶ ቤተሰቡን እየመራ ሲሆን ጥቂት ባለስልጣናትተና ዘመዶቻቸው እንዲሁም ጭፍሮቻቸው የመንግስት ሰራተኛውን ላብ እየበዘበዙ ህገሪቱን እና ሕዝቡን ለድህነት ዳርገውታል፡፤ ዛሬ ምርጫ ሲደርስ የመንግስት ሰራተኛውን ለማባበል በደምወዝ ጭማሪ መደለል ሰሚ አያገኝም ። የመንግስት ሰራተኛው የሚበጀውን እና የማይብጀውን በ1997 ምርጫ በተግባር አሳይቷል። አህንም ኢሕአዴግ ሆይ የመንግስት ሰራተኛው ማንን እንደሚመርጥ ያውቃል። #ምንሊክሳልሳዊ
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15036#more-15036

No comments:

Post a Comment