Monday, June 30, 2014

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ

2665272d78511e341383257989
June 30, 2014
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን ባለሥልጣናት እገታ ላይ መሆኑን በማስመልከት የወጣ መግለጫ
ሰኔ 23 ቀን 2006 ዓ.ም
የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓም ለሥራ ጉዳይ በየመኒያ አየር መንገድ አይሮፕላን ተጉዞ በትራንዚት ሰንዓ ከተማ እያለ በየመን መንግሥት ፀጥታ ኃይሎች በሕገወጥ መንገድ ታግቷል። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን የጉዞው መዳረሻ አልነበረም፤ ከየመን ጋርም የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ አልነበረውም። የየመን መንግሥት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን አግቶ ለአንድ ሰዓት እንኳን ለማቆየት ምንም ምክንያት የለውም። በዚህም ምክንያት ያለአግባብ የታገተብን የንቅናቄያችንን አመራር በአስቸኳይ እንዲፈታ በተለያዩ መንገዶች ላለፈው አንድ ሣምንት ያደረግነው ጥረት እስካሁን አልተሳካም። እንዲያውም የየመን ባለስልጣናት አምባገኑን ወያኔ ለመርዳት ባለው ፍላጎት ሳቢያ መሪያችንን አሳልፎ ሊሰጠው ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብናል።
አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ በሀገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ፣ ነፃነትና ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጊዜውን፣ እውቀቱንና ጉልበቱን ብቻ ሳይሆን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት የተዘጋጀ፤ ዝግጁነቱንም በተግባር ያሳየ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው። የየመን መንግሥት ከዘረኛውና ፋሽስታዊው ወያኔ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ታጋይ መሪያችን ላይ እየፀመ ያለውን ደባ የጉዳዩ ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቅ የንቅናቄዓችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ወስኗል።
ትግላችን መስዋትነት እንደሚያስከፍል እናውቃለን። ከዚህ በፊትም ብዙ ጓዶቻችን መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ወደፊትም ብዙ መስዋዕትነት መከፈሉ የማይቀር ጉዳይ ነው። አሁን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ላይ የደረሰውና ወደፊትም ሊደርስ የሚችለው ጉዳት ምሬታችን በማብዛት፣ ቁጣችንና ዝግጁነታችን ከማጠንከር በስተቀር ቅንጣት ታክል እንኳን ወደ ኋላ እንድናፈገፍግ እንደማያደርገን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ለአባሎቻችንና ለደጋፊዎቻችን ሁሉ መግለጽ እንወዳለን።
መንግሥታት ይመጣሉ፣ ይሄዳሉ። ኢትዮጵያና የመን ግን ጎረቤታሞች ሆነው መቆየታቸው የማይቀር ነው። የየመን መንግሥት የወያኔ እድሜ አጭር መሆኑ የተገነዘበ አይመስልም። በዚህም ምክንያት የየመን መንግሥት የሁለቱን አገሮች ሕዝቦች የቆየ ወዳጅነት የሚያደፈርስ እርምጃ ወስዷል። የየመን መንግሥት የየመንን የወደፊት የረዥም ጊዜ ጥቅም እንዲያሰላና ያገተብንን መሪ በአስቸኳይ እንዲፈታ እንመክራለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመሪያችን ላይ ጉዳት ቢደርስ ወይም ለወያኔ አሳልፎ ቢሰጥ የመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይሽር ቂም ውስጥ የምትገባ መሆኑን የየመን መንግሥት አውቆ በጥብቅ እንዲያስብበት እናስጠነቅቃለን።
በየመን መንግሥት አልሰማ ባይነት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለፋሽስቱ የወያኔ አገዛዝ ተላልፎ ቢሰጥ በአካሉና በሕይወቱ ለሚደርሰው ሁሉ የወያኔ ፋሽስቶችን ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑ ከአሁኑ እናስጠነቅቃለን። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስና ሕይወት ላይ የሚደርሰው ማንኛውም ጥቃት ለነፃነታቸው ለመሰዋት ዝግጁ የሚሆኑ እልፍ አዕላፍ ታጋዮችን እንደሚፈጥር ጥርጥር የለንም። በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ አካል፣ መንፈስ እና ሕይወት ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ሁሉ በማንኛውም መንገድ በማንኛውም ቦታ የምንበቀል መሆኑንና ብዙ የወያኔ ሹማምንት ዋጋ የሚከፍሉበት እንደሚሆን እንዲያውቁት እናስጠነቅቃለን ።
በመስዋዕትነት ድልን እንቀዳጃለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
http://www.ginbot7.org/wp-content/uploads/2014/06/Press-release-Andargachew.pdf

Sunday, June 29, 2014

ቴዎድሮስ ካሣሁንን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው?

Image
ቴዎድሮስ ካሣሁንን በአካል አላውቀውም፤  በዘፈንና በጭፈራ በእውነት ተደሳች መሆን ካቃተኝ ቆይቷል፤ ከ ኅዳር 1967 ጀምሮ ነው የቆረቆረኝ፤ ይህ ሰው እንደሰውና እንደ ኢትዮጲያዊ በየጊዜው የሚደርስበትን ወደ ግፍ የሚጠጋ በደል ስመለከት ያው የለመድነው ምቀኝነት ነው እያልሁ ሳልፈው ቆየሁ፤ ግን በደሉ አላቆም አለ፤ ማንም ሊደርስለት አለመቻሉ ይበልጥ ያሳዝናል፣ በእሱ ላይ ተከታታይ  የደረሰበት በደል የሕግ ያለህ የሚያሰኝ ነው፤ በቴዎድሮስ ካሣሁን ላይ በተቀነባበረ መንገድ የሚፈፀመው ማሰቃየት ማንንም ሰው የሚያሳስብ ነው፤ ምክንያቱ ምንድን ነው? በግልጽ የታወቀ ነገር የለም።
በቴዎድሮስ ላይ ከባድ ተንኮል ሲፈጸምበት የሰማሁት በመጀመሪያ ዛሬ በስደት ላይ ባለው « አዲስ ነገር» የሚባል ጋዜጣ ላይ ነበር፤ ጋዜጣው ቴዎድሮስ በሙያው ያገኘውን መልካም ስም በሰፊው ጥላሸት ቀብቶት ነበር፤ በጣም ሰፊ የሆነ ሀተታ በቴዎድሮስ ዘፈኖች ላይ በማቅረባቸው ምን ያህል አንገብጋቢ የአገር ጉዳይ አግኝተውበት ይሆን ብዬ አነበብሁት፣ ምንም ለአገር  የሚጠቅም ጉዳይ አላገኘሁበትም፤ በዘፈኖቹ ላይ በተደረገው ሂስም ከጋዜጠኞቹ መሀከል የሙዚቃ ሙያ ባለቤት እንዳለ ብጠይቅም ጋዜጣው ባለሙያ እንደሌለውና ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ ባለሙያ ማማከራቸውን ነገሩኝ፣  ስሙ  እንዲጠቀስ የማይፈልግ ባለሙያ፣ ባለሙያ አይባልም፣ እንኳን በሙያው በራሱም አይተማመንም ማለት ነው፤ በዚህ በራሱ በማይተማመን ሰው ምስክርነት ላይ በተመሰረተ ረጅም ነቀፌታ ቴዎድሮስን ደበደቡት፤
ሁለተኛው የቴዎድሮስ ጣጣ በመኪና ሰው ገጭቷል ተብሎ መከሰሱ ነው፤ በሌሊት፣ በጨለማ ነው፤ ቴዎድሮስ እንደሚለው  «እኔ ወደአገሬ የገባሁት ሰውዬው ሞተ በተባለበት ቀን ማግስት እንደሆነ ቪዛዬ ያረጋግጣል፣»  (ነጋድራስ መስከረም 30/2001 ዓ.ም. ) በኋላም ከዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል የተገኘው መረጃ ይህንኑ የሚያረጋግጥ እንደነበረ ተነግሮአል፤  በዚሁ በነጋድራስ ጋዜጣ ላይ የሚከተሉት መረጃዎች ተጠቅሰዋል ፦
  1. ቴዎድሮስ ከውጭ የተመለሰው በ22/2/1999 ዓ.ም መሆኑ
  2. ሰውዬው በ 22/1/1999 ሞቶ አስከሬኑ በ22/2/1999 ዓ.ም መመርመሩን የጽሑፍ ማስረጃ፣
  3. ዓቃቤ ሕግና ፖሊስ በሆስፒታሉ የተገለጸው የምርመራ ቀን እንዲለወጥ መጠየቃቸው፣
  4. ከአሥራ ሦስት ቀኖች በኋላ በተደረገ ምርመራ መኪናው ላይ ምንም ደም አለመገኘቱን፣
ይህ ሁሉ ሆኖ በቴዎድሮስ ላይ ተፈርዶበት ወህኒ ወርዶ ጊዜውን ጨርሶ ከወጣ ቆይቶአል።
ከዚያ ወዲህ ደግሞ በተቀነባበረ ሁኔታ ቴዎድሮስ ካሣሁን በዘፈኑ ያገኘውን ዝና ለማጉደፍና በሥራውም የሚያገኘውን ጥቅም ለመቀነስ ተግተው የሚሠሩ ሰዎች መኖራቸውን የሚያመለክቱ ነገሮች አሉ፣ በመጀመሪያ ቴዎድሮስ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው በደል ከአለ ግልጽ ሆኖ ቢወጣና ሁላችንም ብናውቀው ጥሩ ነው፤ አለዚያ ግን እየተደራጁ አንድ ግለሰብን ለማጥቃት የሚደረገው እርምጃ የሚወገዝና ልንቃወመው የሚገባ ጉዳይ ነው፣  አንድን ሰው በእምነቱ፣ በአስተያየቱ፣ ወይም ስኬታማነቱን በመመቅኘት ለመጉዳት ዓለም -አቀፋዊ ሴራ ማካሄድ ክፋት ነው፤ ይህንን ክፋት አምጠው የወለዱትና ለማሳደግ የሚሞክሩት ሰዎች፤ የማሰብ ችግር ያለባቸውና ክፋታቸው ተመልሶ እነሱኑ የሚያጠቃ መሆኑን የመገንዘብ ችሎታ  እንኳን የሌላቸው ናቸው።
ሦስተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የበደሌ ቢራ ፋብሪካ በቴዎድሮስ ዘፈን ለመጠቀም ሲፈልግ፣ የጨለማ ሰዎች ተሰብስበው በቴዎድሮስ ዘፈን የታጀበውን የበደሌ ቢራ እንደማይጠጡ በመዛታቸው ኩባንያው ከቴዎድሮስ ጋር የነበረውን ውል መሰረዙ ነው፤  እንደተገነዘብሁት ቴዎድሮስ ትንሽ በቁንጫ ተሰቃየ እንጂ ክፍያው አልቀረበትም፣ ነገር ግን ቴዎድሮስን አንደሰው፣ እንደኢትዮጵያዊ፣ እንደዘፋኝ የሚያውቁት ሰዎች የሉም፤ ወይም በጨለማዎቹ ሰዎች ተሸንፈዋል፤ ወይም በፍርሃት ቆፈን ደንዝዘዋል! የጨለማ ሰዎቹ ቴዎድሮስ ካለበት አንጠጣውም የተባለው ቢራ ለቴዎድሮስ ወዳጆች እንዴት ጣፈጣቸው?
አራተኛው የቴዎድሮስ ስቃይ የመጣው ሦስተኛውን ጥቃት ለመቋቋምና ለማረም ምንም ዓይነት የማረሚያ እርምጃ ስላልተወሰደ ነው፤ የበደሌ ቢራ ኩባንያ እንዳደረገው ሁሉ የኮካኮላ ኩባንያም ቴዎድሮስ ካሣሁንን ለአሻሻጭነት መረጠ፤  የጨለማዎቹም  ሰዎች እንደገና ተነሡ፤  ቴዎድሮስን ካልሻራችሁ ኮካ ኮላ አንጠጣም  ብለው የቴዎድሮስ ውል እንዲፈርስ አደረጉ፤  አሁንም ቁንጫው ትንሽ ምቾቱን ከመቀነሱ በስተቀር ቴዎድሮስ ገንዘቡን አላጣም፤ አሁንም የቴዎድሮስ ወዳጆች ነን የሚሉ ኮካ ኮላ እየጣፈጣቸው ይጠጣሉ፤ ትንሽ ቆራጦች የጨለማ ሰዎች  በአደባባይ ምላሱን እየሳለ እልል ከሚለውና ከሚጨፍረው ነፍሰ-ቢስ ስብስብ ምን ያህል እንደሚበልጡና ውጤታማ እንደሚሆኑ ያሳያል።
የቴዎድሮስ ካሣሁን ጉዳይ የአንድ ግለሰብ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ነው፤ የጨለማ ሰዎቹ ግን ወደግለሰብነት ደረጃ ገና ያልደረሱ ናቸው፤ ስለዚህም ቴዎድሮስን እንደሰው እንዳያዩት እዚያ ገና አልደረሱም፤ እንደኢትዮጲያዊ እንዳያዩት መናፍቃን ናቸው፤ እንደዘፋኝ እንዳያዩት ጆሮአቸው አይሰማም።
በአዲስ ነገር ተጀምሮ እስካሁን አልበርድ ያለው ቴዎድሮስን ነጥሎ የማጥቃት ዘመቻ ምክንያቱ ምንድን ነው? በጥሞና ሊታይና ሊመረመር የሚገባው በአዲስ ነገር ጋዜጣና በጨለማዎቹ ሰዎች መሀከል ያለ የሚመስለው ድርጅታዊ ግንኙነት ነው፤  የአንድ ግለሰብን ሰብዓዊ መብቶች እየደጋገሙ በመርገጥ አጋጣሚ እየፈለጉ ማጥቃት የሚጎዳው ተረጋጩን ብቻ ሳይሆን ረጋጮቹንና የጋን ወንድሞችንም ነው፤ አንድ ቀን ግፍ ወደተነሣበት ይመለሳል።
መስፍን ወልደ-ማርያም
ሰኔ 2006 ዓ.ም
source –   http://mesfinwoldemariam.wordpress.com/2014/06/29/%E1%8B%A8%E1%89%B4%E1%8B%8E%E1%8B%B5%E1%88%AE%E1%88%B5-%E1%8A%AB%E1%88%B3%E1%88%81%E1%8A%95-%E1%89%B4%E1%8B%B2-%E1%8A%A0%E1%8D%8D%E1%88%AE-%E1%8C%A5%E1%8D%8B%E1%89%B1-%E1%88%9D%E1%8A%95/

ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ ”ሞት ሊበየንበት ይችላል” -በሽብርተኝነት ክስ ሞት ተፈርዶባቸው ሞታቸውን የሚጠባበቁ 127 ሰዎች ኣሉ

በኖርዌይ ሃገር ውስጥ በኖርዌጂያንኛ የሚታተመው ዳግብላደት የተባለው ጋዜጣና ድረ-ገጽ ”ኢትዮጵያዊው-ኖርዌጂያን” ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላ በሚቀጥለው ሳምንት ሞት ሊበየንበት ይችላል” ሲል ኣውጥቶኣል።
”ባለፈው ሳምንት ለማወቅ እንደተቻለው ዕድሜው 52  የሆነና  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ  የተባለ ኖርዌጂያን ኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት ተከሶ በእስር ላይ ይገኛል።” tiltalt for terror በማለት የጀመረው የኖርዌዩ ዳግብላደት ሲቀጥልም…”የኢትዮጵያ መንግስት ቃለ ኣቀባይ እንደሚለው ገንዘብ ኣሰባስቦና ኣጥቂ ቡድን መልምሎ ኣደጋ ለማድረስ ሲሞክር ያዝነው በማለት መከሰሱን ያትትና በበኩላቸው የኖርዌዩ የሰብኣዊ መብት ጥበቃም ሆኑ የዓለም ኣቀፉ ሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች ድርጊቱን በጥብቅ ያወገዙት ሲሆን፣ ኣያይዘውም ለዚሁ ድረ-ገጽ ታሳሪው ግለሰብ ያለበት ሁኔታ ከወትሮው የከፋ እንደሆነም ስጋታቸውን እንደገለጹለት ያወሳል።
 ኢትዮጵያንም ሆነ የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት፣ በኣሁኑ ወቅት በማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ውስጥ የሚገኙትን  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻ ”በሚገባ ያውቃሉ” ያሉዋቸውን የሰብኣዊ መብት ተሟጋችና ኖርዌጂያን ፈሊክስ ሆርነ ን  ኣነጋግሮ ድረ-ገጹ ያገኘው መልስ ”ኖርዌጂያኑን ኦኬሎ በሚቀጥለው ሳምንት የሚሰየመው ችሎት ሞት ሊበይንበት ይችላል” በማለት የገለጹ ሲሆን ኣክለውም፣
”በሃገሪቷ ውስጥ በሽብር ወንጀል የሚከሰሱት ዜጎች የሚገጥማቸው የሞት ፍርድ ነው። ነገር ግን እነዚህ ሞት የሚፈረድባቸው ዜጎች ምንም ማስረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው። በሽብር ክስ ስለተከሰሱ ብቻ ዕድላቸው ይሄው ነው። በሞት ቀጠና የሚገኙትን ዜጎች የሚዘግበው ዓለም ኣቀፉ ድርጅት በኢትዮጵያ በእስር ቤት ውስጥ በሞት ቀጠና (ሴል) የሚሰቀሉበትን ወይም የሚገደሉበትን ጊዜ የሚጠባበቁ 127  ዜጎች  ይገኛሉ ሲል ፈሊክስ ሆርነ ለድረ- ገጹ ገልጸዋል።
 ሌላው ኣምነስቲ ኢንተርናሽናል ውስጥ የሚሰሩት ጌራልድ ካዶርድ ”የኢትዮጵያ መንግስት ኦኬሎን እንደከሰሰው በሽብር ወንጀል ጦር ሲመለምልና ሲያደራጅ ኣግኝቶት ከሆነ፣ የሞት ቅጣት ይበይኑበታል የሚለው ስጋቴ ነው።የፍርድ ሂደቱን እንደምናየው የሞት ቅጣቱ በፍርድ ቤቱ ይለወጣል የሚል ዋስትና የለንም።” ኣያይዘውም ባለፈው ዓመት 8 ጋምቤላ ውስጥ ያሉ የተቃዋሚ ድርጅት ኣባላቶች በሽብርተኝነት ከሰዋቸውና የሞት ፍርድ በይነውባቸው ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው።”
 ጭፍጨፋ
ኦቻላ ከሽብርተኛ ጋር ግንኙነት እንዳለው ኣላውቅም። ነገር ግን በጋምቤላ ውስጥ መንግስትን የሚቃወም ጠንካራ ተቃዋሚ ድርጅት የለም። መንግስትን ለመቃወም የሚነሱትንም ሽብርተኛ የሚል ስም በክልሉ መንግስት ይለጠፍባቸዋል።
 ኦቻላ የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት የነበረ ጊዜ፣ massakre 13. desember 2003. የ 1000 በላይ  የኣባወራዎች መኖሪያ ቤቶች በገዥው ስርዓት ወታደሮች ሲቃጠልና ከ400 የኣኙዋክ ንጹሃን ተወላጆች በጥይትና በስለት ሲታረዱ በስፍራው  ነበር። ይሄንንም ተከትሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ስልጣኑን በመተው መሰደዱንና ከዚያም ከቤተሰቡ ጋር  በኖርዌይ ”ትሮንዳሄም” በተባለ ቦታ  በስደተኝነት በመግባትና ፈቃድ ጠይቆ በ2009 ዓ.ም የኖርዌጂያን ዜግነት ተሰጥቶት ነበር።
  ቢሆንም  ከ 2012 ጀምሮ በጋምቤላ ውስጥ በሚከናወነው ሁኔታዎች ይረበሽ ነበር። በዚህም የተነሳ ወደዚያው ኣቅንቶኣል።ማድረግ ግን ኣልነበረበትም።በኣንድ ወቅት በክረምት ወራት የሱዳን የመረጃና ደህንነት ሰራተኞች በሱዳን ጁባ ውስጥ ያለን ኣንድ ሆቴል በድንገት ከበቡት። ከዚያም በውስጡ የነበሩትን የሱን ጓደኞች  ኣስረዋቸው ወደ ኢትዮጵያ  ልከዋቸዋል በማለት ድረ- ገጹ ኣትቶኣል።
ቶርቸር 
በኣሁኑ ሰዓት ኦኬሎ በእስር ቤት ውስጥ ባልተረጋገጠ መረጃ ውስጥ ይገኛል። ይህ ኖርዌጂያን በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ ኣይቻልም።በኢትዮጵያ ውስጥ በሽብርተኝነት በእስር ቤት ውስጥ ሆኖ  የእናትነት እንክብካቤን ማግኘት ህልም ነው።እስረኞች ለቶርቸርና ስቃይ የተጋለጡ  መሆናቸውን ፈሊክስ ሆርነ  ለድረ-ገጹ ኣስረድተዋል።
የኦኬሎን የፍርድ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው ሪፖርተር የተሰኘው  ጋዜጣ ችሎቱ  ጁላይ 1 ይውላል ብሎ ቢገልጽም፣ የእኛ Dagbaldet በሲዊድን ያለውን የኢትዮጵያ ኣምባሳደር ለማግኘት ሞክረን ያልተሳካልን ሲሆን፤ ዓለም ኣቀፉን የሰብ ኣዊ መብት ተሟጋች ድርጅትንም ሆነ በኣዲስ ኣበባ ካለውም የኖርዌይ ኤምባሲ ትክክለኛ የችሎት ጊዜውን ማረጋገጥ ኣልተቻለም።
የኖርዌይ የውጭ ጉዳይም ለኣንድ ኣዲስ ኖርዌጂያን በኣደጋ ውስጥ በሚሆንበት ጊዜ፣ ወይም ኣደጋ በገጠመው ወቅት እንዴት መከላከል  እንዳለበት ከድረ- ገጹ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ መስጠት ኣልፈለጉም።ድረ- ገጹ   ምላሽ በማጣቱም ይመስላል በኮንጎ ውስጥ ኖርዌጂያዊው Joshua French  በሞት ሲቀጣና፣  Shahid Azim  በኣስገድዶ መድፈር ወንጀል ፖኪስታን ውስጥ ተይዞ ሞት ሲፈረድበትም ኣላስጣሉትም በሚል ኣጣቅሰው ያለፉት። ቢሆንም ይላሉ የውጭ ጉዳይ ቃል ኣቀባይ ፍሮደ ኣንደርሰን፥ እስከኣሁን ከተከሳሹ ስለ ፍርድ ውሳኔውንም  ሆነ  ስለ ችሎቱ ቀን የምናውቀው የለም በማለት ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ያለው የኖርዌይ ኣምባሳደር  ኦኬሎ ኦካይ ኦቻላን በተመለከተ ተደጋጋሚ  ጥያቄዎችን ለኢትዮጵያ መንግስት ኣቅርቦኣል። ኦኬሎ ያለበትን ሁኔታ፣ የፍርድ ሂደቱን ለመከታተልና በእስር ቤት ለመጎብኘት፣ ቢሆንም  ከኢትዮጵያ መንግስት ምንም  ምላሽ  ኣልተገኘም። የኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ሁኔታውን በኣደገኛነት እንደሚያዩትም ሳይገልጹ ኣላለፉም።
ባለፈው ሳምንት 
 የኦኬሎ ባለቤት ኦባ ኦድዋ ኦመት kona Obo Adwo Omot fram i Dagbladet  ”… ባለቤቴ ሽብርተኛ ሳይሆን የፖለቲካ እስረኛ ነው” በማለት ገልጻ ነበር። ይህችው የ ኣራት ልጆች እናት የሆነችው ባለቤቱ ባለፈው ሳምንት እንደገለጸችው፣ ”…በኣሁኑ ሰዓት በዚህ ጠባብ ክፍል ከኣራት ልጆቼ ጋር እገኛለሁ። ምንም የማውቀው ነገር የለም። ባለቤቴም የሚያውቀው ነገር የለም። የኖርዌይ መንግስት የተቻለውን ሁሉ ኣድርጎ ባለቤቴን ከእስር እንዲያስወጡልኝ እማጸናለሁ በማለት ነበር የገለጸችው።
For norweigian read 
http://www.dagbladet.no/2014/06/25/nyheter/etiopia/terror/hrw/samfunn/34002701/

Tuesday, June 24, 2014

በሀዋሳ ሰ.መ.ጉ እስረኞችን እንዳይጎበኝ ተከለከለ

ፍኖተ ነፃነት

በሃዋሳ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ወደ ሃዋሳ እስር ቤቶች ያመሩት የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ሀላፊዎች እስረኞቹን ለማግኘት እንደማይችሉና ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ትዕዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ታሳሪዎቹን ማግኘት እንዳልተቻለና የጣቢያ ሀላፊዎቹን ለማናገር የተደረገውም ጥረት እንዳልተሳካ አስረድተዋል፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2006ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ‹‹ፍትህን ተነፍገን ትግላችን አይቆምም ››በማለት ዛሬም ለ4ኛ ቀን በርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡አባላቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቅዳሜ እለት ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በኢ/ፌ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1-ሀ)32/1-ሀ/እና 257 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በሚል የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ዐ/ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ በእስር እንዲቆዩና ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለሰኔ 20 ቀን 2006 እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡

10448208_657204214364516_9050720156707149922_n
10438349_657205647697706_637993046936063852_n
10450753_657204294364508_6267425299544943631_n

ደምወዝ ጭማሪ ..የምርጫ ጉቦ …

በደምወዝ ጭማሪ የመንግስት ሰራተኛውን የፖለቲካ ባሪያ ማድረግ አይቻልም።ደምወዝ ተጨምሮልሃል የተባለው ከመጋረጃ ጀርባ አንገቱን እንዲሰብር እየተደረገ ያለው የመንግስት ሰራተኛ ማንን እንደሚመርጥ እና ድምጹንም እንደማያባክን ጠንቅቆ ያውቃል። የደሞዝ ጭማሪው የወያኔን አጣብቂን ውስጥ መዘፈቅን ያሳያል።
ውሻ ጆሮውን ቆርጠው ቢሰጡት ስጋ የሸለሙት ይመስለዋል .በሚል ወያኔያዊ የፖለቲካ ብሂል ተነስቶ ለመንግስት ሰራተኛው የደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ እንደሚፈልግ በሹመኛው አማካኝነት ተናግሯል። በኢትዮጵያ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ እና ለሃገር ዋናው ዋልት ይሆነው የመንግስት ሰራተኛው ባለፉት 23 አመታት የታላላቅ ግፎች ተሸካሚ የኢኮኖሚ በሽተኛ ሆኖ እየኖረ ያለ ሲሆን ብሄሩ እየተለየ እና የፖለቲካ እምነቱ እየተመዘነ ሲንገራተት የደረጃ እርከን እና የደምወዝ ችማሪ ሲከለከል እንዲሁም ከስራ ሲፈናቀል እና ቤተሰቡ ሲበተን ሲሰደድ የነበረ እና ያለ የሚኖር የመንግስት ሰራተኛው የፖለቲካ ባሪያ ለማድረግ በኢሕ አዴግ የማይቆፈር ጉድጓድ የለም ።
በወያኔ የሚመራው የወንበዴዎች ጁንታ ስልታኑን ከተቆጣጠር ጀምሮ የመንግስት ሰራተኛውን መሰረታዊ ማህበራት በማፍረስ ለሰራተኛው የሚከራከሩትን የመብት ተማጓቾች እና የሰራተና ማህበር መሪዎችን እንዲሰደዱ ከስራቸው እንዲፈናቀሩ በማያውቁት የፈጠራ ወንጀል እንዲታሰሩ ወዘተ ተመሳሳይ እኩይ ተግባራትን በመፈጸም በራሱ መልክ እና አምሳል ጠፍጥፎ የሰራቸውን ማህበራት እና አመራሮች በማስቀመጥ እንዲሁም በየምስሪያ ቤቱ ያልተማሩ እና ልምድ የሌላችው በፖለቲካ እምነታቸው ብቻ እንዲመደቡ እየተደረገ በየክፍሉ የደህንነት ቡድን በማደራጀት አንድ ለአምስት እየጠረንፈ ሰራተኛውን በማሰቃየት ዛሬ የምርጫ ቀን ሲደርስ የምረጡኝ ጉቦ የሆነውን የደምወዝ ጭማሪ ማድረግ ማንን ለማታለል ነው ?
በኑሮ ውድነት ናላው የዞረው የመንግስት ሰራተኛው በከፍተኛ እዳ ውስጥ እና አተዳደራዊ በደል ውስጥ ገብቶ ቤተሰቡን እየመራ ሲሆን ጥቂት ባለስልጣናትተና ዘመዶቻቸው እንዲሁም ጭፍሮቻቸው የመንግስት ሰራተኛውን ላብ እየበዘበዙ ህገሪቱን እና ሕዝቡን ለድህነት ዳርገውታል፡፤ ዛሬ ምርጫ ሲደርስ የመንግስት ሰራተኛውን ለማባበል በደምወዝ ጭማሪ መደለል ሰሚ አያገኝም ። የመንግስት ሰራተኛው የሚበጀውን እና የማይብጀውን በ1997 ምርጫ በተግባር አሳይቷል። አህንም ኢሕአዴግ ሆይ የመንግስት ሰራተኛው ማንን እንደሚመርጥ ያውቃል። #ምንሊክሳልሳዊ
http://www.abugidainfo.com/amharic/index.php/15036#more-15036

Wednesday, June 18, 2014

‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፣ የእናንተም ነው›› እስክንድር ነጋ

በኤልያስ ገብሩ ጎዳና
‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእናንተም ነው፡፡ …››
‹‹በእስር ላይ የምትገኙ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ››
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ
‹‹አሁን ደስተኛ ነኝ››
‹‹እስክንድርን ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው››
አቶ አንዷለም አራጌ
ከትናንት በስትያ ሰኔ 03 ቀን 2006 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ከቅርብ ጓደኛዬ እና የሙያ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ጋር ወደቃሊቲ ማረሚያ ቤት [እስር ቤትም ነው] አምርተን ነበር- ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋንና የአንድነት ፓርቲ ጸሐፊ የሆኑትን አቶ አንዷለም አራጌን ለመጠየቅ፡፡ የተለመደውን የፖሊስ ፍተሻ አልፈን ወደ ውስጥ ስንዘልቅ የሰማያዊ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፈ አቶ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ፣ አቶ ሳሙኤል የተባሉ አባልና የ‹‹ነገረ ኢትዮጵያ›› ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እስክንድርን ሊጠይቁ ቀድመውን ደርሰው ነበር፡፡Ethiopian political prisoners Eskinder Nega and Andualem Arage
…እስክንድርን እና አንዷለምን አስጠራናቸው፡፡ ሁለቱም ሲያዩን ደስ አላቸው፡፡ በተለይ በተለይ የእስክንድር ፈገግታ በጣም ደማቅ ነበር፡፡ ተከፋፍለን ከሁለቱም ጋር ሃሳቦችን መለዋወጥ ጀመርን፡፡
እስክንድር በዓለም የጋዜጠኞች እና የዜና አታሚዎች ማኅበር የዓመቱ የወርቅ ብዕር የ “pen Golden of freedom 2014″ ተሸላሚ በመሆኑ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ›› አልኩት፡፡ ‹‹አመሰግናለሁ፡፡ ትናንት አንድ ልጅ ሊጠይኝ መጥቶ ነግሮኛል›› ካለን በኋላ ደግመን ስለሽልማቱ በጋራ ሃሳብ መለዋወጥ ቀጠልን፡፡ እስክንድር ሽልማቱ አዲስ መሆኑን አላወቀም ነበር፡፡
በመሆኑም ስለሽልማቱ ሁኔታ፣ ማን እንደሸለመው፣ ሽልማቱ የት እንደተደረገ፣ ሽልማቱን ማን እንደተቀበለለት [ሽልማቱን የተቀበለው በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ወንጀለኛ ተብሎ ከባልደረባው ፎቶ አንሺ ጋር 11 ዓመታት ከተፈረደበት በኋላ በይቅርታ የተለቀቀው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብዬ ነበር]፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ምን እንደሚመሰል፣ በሽልማቱ እነማን እንደተገኙ …ያወቅነውን ሁሉ ነገርነው፡፡
‹‹ይህንን አላዋኩኝም፣ ሰርካለም (ባለቤቱ) ለምን በቦታው አልተገኘችም?›› በማለት ጠየቀንና በድጋሚ ደስ ብሎት ጣቶቹን በሽቦ ውስጥ አሾልኮ ጨበጠን፡፡ ወዲያው ይህቺን መልዕክት ተናገረ፡-
‹‹ይህ ሽልማት የእኔ ብቻ አይደለም፡፡ የእናንተም ነው፡፡ የኢትዮጵያዊ ጋዜጠኞች ነው፡፡ ሁላችንንም ይመለከተናል፡፡ ለሁላንችም ይገባናል፡፡ ይሄንን ሽልማት የምመለከተው ሐሳብን በነጻነት ከመግለጽ የመብት ጥሰት አኳያ ብቻ አይደለም፡፡ ለሌሎች የዜጎች መብቶች ሲሉ ለታገሉ እና እየታገሉ ላሉ ፖለቲከኞች፣ የሕሊና እስረኞችም ጭምር ነው፡፡ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሌሎች ከተነፈጉ መብቶች ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡ ሁሉንም መብቶች እናገኛቸዋለን፣ ወይም እናጣቸዋለን፡፡ ለዚህ ደግሞ ጸንተን እንታገል፣ ትግላችን ግን ሰላማዊ ብቻ መሆን አለበት፡፡ …››
እስክንድር ደስ ብሎት ሃሳቡን መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እኔ ለተወሰኑ ቀናት በማዕከላዊ መታሰሬን ሰምቶ ስለነበረም ‹‹ማዕከላዊ እያለህ የታሰሩትን ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች ለማግኘት ችለህ ነበር?›› ብሎ ጠየቀኝ፡፡ እነሱን በአካል ማግኘት አለመቻሌን ነገር ግን ከእነሱ ጋር ታሥረው የነበሩ ሌሎች ተጠርጣሪ ዜጎችን አግኝቼ በእስር ስላሉበት ሁኔታ መጠየቄን ነገርኩት፡፡
የታሰሩት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖችን ቤተሰብ ማግኘት እችል እንደሆነና ከቻልኩም በእነሱ በኩል መልዕክቱ ይደርስለት ዘንድ በድጋሚ ጥያቄያዊ ሃሳቡን አቀረበልኝ፡፡ የተወሰኑ የእስረኛ ቤተሰቦችን ማግኘት እንደምችል አስረዳሁት፡፡
‹‹የታሰራችሁ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያኖች የእኔ ጀግኖች ናችሁ፡፡ አከብራችኋላሁ፡፡›› ብለህ ንገርልኝ አለኝ – ደጋግሞ፡፡ …
በዕለቱ ከሰዓታት በፊት ሰናይት ታከለ የምትባል ወዳጄም እስክንድርን ልጠይቀው ቃሊቲ እንደምሄድ በነገርኳት ጊዜ ‹‹እንደማከብረው እና እንደማደንቀው ንገርልኝ›› ያለችኝን መልዕክት ለእስክንድር አደረስኩላት፡፡
እሱ ግን ሳቅ እያለ ‹‹ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል! …ተሳስተሻል›› ብለህ ንገራት አለኝ፡፡ ‹‹ለምን?›› አልኩት፡፡ ‹‹ገና ምን ሰርቼ?›› በማለት በዚያ ትሁት አንደበቱ መለሰልኝ፡፡ በእውነት መልሱ አስደመመን፡፡ ዋይ እስክንድር፣ ፍጹም የተለየ ታላቅ ሰው!!!
እስክንድርን እናናግረው የነበርን ጠያቂዎች ወደ አንዷለም አራጌ ዞርን፡፡ አንዷለም ጋር የነበሩት ደግሞ ወደ እስክንድር፡፡
አንዷለም የስፖርት ቲ-ሸርት ከቁምጣ ጋር ለብሷል፡፡ ጥቁር መነጽር አድርጓል፡፡ ረጋ ብሎ ፈገግ በማለት ‹‹ምን አዲስ ነገር አለ?›› በማለት ጨዋታ ጀመረ፡፡ አንዷለም የእስክንድርን ሽልማት ሰምቶ ኖሮ፣ ‹‹አሁን ከምሳ በኋላ ጣፋጭ የለውዝ ሻይ እሱን እና ጓደኞቻችንን በመጋበዝ ‹እንኳን ደስ ያልህ!› በማለት ሰርፕራይዝ አደርገዋለሁ፡፡ ምግብ ማብሰል እያለማመድኩት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ እኔ ነኝ ሰርቼ የማበላው፡፡ በልጅነቱ በበርገር ያደገ ልጅ አሁን ሽንኩርት እና ቲማቲም መክተፍ ችሏል …›› በማለት በቀልድ ነገረን፡፡
‹እነማን ከእናንተ ጋር አሉ? በአንድ ክፍል ውስጥስ ስንት ናችሁ? ጊዜያችሁንስ እንዴት ነው የምትጠቀሙበት?›› የሚል ጥያቄ አቀረብንለት፡፡
‹‹ለረዥም ጊዜ፣ በጣም አስቸጋሪ ክፍል ውስጥ፣ መሬት ላይ ስንከባለል ነበር በእስር ያሳለፍሉት፡፡ አሁን አቶ ስዬ አብርሃ ታስሮ በነበረበት ጥሩ በሚባል ክፍል ውስጥ ለአምስት ታስረን እንገኛለን፡፡ አቶ መላኩ ተፈራ፣ አቶ መላኩ ፈንታ ና አንድ ባለሃብት አብረውን ናቸው፡፡ አሁን አልጋ ላይ መተኛት ጀምሬአለሁ፡፡ ይሄ ለእኔ እንደ አዲስ ሕይወት ነው፡፡ አሁን ደስተኛ ነኝ፡፡ …ጊዜያችንን በጥሩ ሁኔታ ከፋፍለን እየተጠቀምንበት ነው፡፡ እናነባለን፣ እንወያያለን፣ የምንፈልጋቸውን መጽሐፍት ግን በምንፈልገው ጊዜ አናገኝም፣ በዚህ በኩል መጠነኛ ችግር አለ፡፡ በተረፈ ደህና ነኝ፡፡ እኔ ተስፈኛ ነኝ፡፡ እናንተም በተሰማራችሁበት ዘርፍ የምትችሉትን ሁሉ ለሀገራችሁ ለውጥ መታገል አለባችሁ…››
ከሁለቱም ጋር የነበረንን የ30 ደቂቃ ቆይታ ሳንጠግብ ‹‹በቃችሁ›› የሚለው የፖሊስ ድምጽ ተሰማ፡፡ ‹‹እናመሰግናለን፣ በቃ ሂዱ›› ሲል አንዷለም በእርጋታ ተናግሮ በሽቦ ስር አሾልኮ እጆቻችንን ጨበጠን፡፡
እስክንድር ደግሞ ‹‹‹ሲመቻችሁ ብቻ መጥታችሁ ጠይቁን፣ ሥራ እንዳይበደል!፡፡ ሥራችሁን ሥሩ›› በማለት ለእኛም ያለውን አሳቢነት ከምክሩ ጋር ደጋግሞ ገለጸልን – ሁሉንም ሰላም በሉልኝ በማለት፡፡ እንግዲህ እስክንድርን የምትሉ ሁሉ ሰላምታውን በእኔ በኩል አድርሻለሁ፡፡
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12575/

Thursday, June 12, 2014

ወያኔ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ሆኗል።


የወያኔ ጉጅሌ ራሱ ከሳሽ፣ ፖሊስና ዳኛ ሆኖ በሚገዛት ሀገራችን ውስጥ የሚያካሂደው ግፍ አንድ ህዝብ ሊሸከመው ለሚችለው በላይ ሆኗል።
የወያኔ ሹማምንትና በዘር ለዝርፊያ የተሰማራው ድርጅታቸው በቅርቡ ደግሞ ስዘርፍ አያችሁኝ በሚል ቁጣ ከአንደበታቸው በላይ ምንም ባልታጠቁ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ከአካሄደው ጅምላ ጭፍጨፋ አልፎ ግለሰብ ተማሪዎችን በማሳደድ ሰቆቃ መፈጸሙን ቀጥሎበታል። በዚህ ሰአት በርካታ ተማሪዎች በታወቁና ባልታወቁ እስር ቤቶች ታጉረዋል። ብዙዎቹ ከትምህርት ገበታ ካላንዳች ጥያቄ ተባረዋል እየተባረሩም ይገኛሉ።
ከወያኔ ግፎች ሁሉ በእጅጉ የሚዘገንነው ሌሎችን በመወንጀል ማሰቃየትና መግደል በፈለገ ቁጥር ራሱ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ ወንጀሉን በሌሎች ላይ ለማመኻኘትና ለመቅጣት የሚጠቀሙበት የሃሳብ ዘዴ ነው።
በአለምያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተሰበሰቡበት አዳራሽ ውስጥ የደህንነት አባሎች ቦንብ አፈንድተው ጉዳት ካደረሱ በኋላ የሚፈልጓቸውን ወጣቶች ቦንብ ሲያፈነዱና ሲጠምዱ ያዝናቸው በማለት ከዚህ በፊት በዊክሊክ መረጃ እንደተለቀቀው የተለመደ በሰው ልጆች ላይ ሰቆቃ ይፈጽማሉ። ሌላው ቀርቶ ቦምብ አፈነዱ ተብለው የተከሰሱት ተማሪዎች በገዛ ጓደኞቻቸው ላይ ቦምብን የሚወረውሩበት ምክንያት የላቸውም።
ወያኔ ተማሪዎቹን አረመኔና እብድ ለማስመሰል የሰራው የራሱ ትንሽዪ ድራማ ወይም ሌላኛው አኬልዳማ መሆኑ ግልጽ ነው።
ወያኔ ደግሞ እንዲህ አይነት የወሮበላ ስራ እንደሚሰራ እንዳላዪ የሚያዩት ለጋሽ ሀገሮች ሁሉ ያጋለጡት፣ የሚያውቁት የአደባባይ ሚስጥር ከሆነ ሰንብቷል።
በዚህ መሰሪ ወንጀል ያዝናቸው ብለው ከአሰሯቸው ተማሪዎች ውስጥ የቦኮ ትቤ ተወላጅ የሆነ ኑረዲን ሃሰን የተባለ የአለመያ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በድብደባ አሰቃይተው ከገደሉት በኋላ ራሱን ገደለ ብለው አስክሬኑን ለቤተሰቦቹ ሸጠውታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ብዙ ተማሪዎች የደረሱበት እና የገቡበት ተፍጧል።
ይህ ሰቆቃ መጠኑን አልፏል! ግፍ በዚሁ እንዲቀጥል ከሆነ ደግሞ መቆም የሚችልበት ተግባር ባለመፈጸማችን ሁላችንም የዚያች ሀገር ልጆች ከታሪክ ወቀሳ እና ከህሊና ጸጸት አናመልጥም። ወያኔዎች በዘር ከፋፍለው በየተራ ስለሚያጠቁን ነው ይህ የሽብር አገዛዛቸው እድሜ ያገኘው። ይህን አደገኛ ክፍተት ካልዘጋነው መከራው ቀጥሎ ያሰቃየናል።
ግንቦት 7 የፍትህና የዴሞክራሲ ንቅናቄ አገራችን ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ማስተናገድ እንዲበቃት ልጆቿ ተባብረን እንድንነሳ ደጋግሞ ጥሪውን ያቀርባል።
ለወያኔ የተመቸነው በየተራ ለመጠቃት አንዱን ብሄረሰብ በሌላው በማስፈራራትና ጥርጣሬ በመንዛት ለመግዛት የቀየሰው ዘዴ ሰለባ መሆናችን ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ፤ የወያኔ የግፍ ቀንበር እንዲሰበር ሰፊ ህብረት ፈጥረን ከመታገል ውጪ አማራጪ የለንም ይላል።
የወያኔ ግፍ ይብቃ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ኢህአዴግ ምርጫውን አስታኮ ቤቶችን ለያከፋፍል ነው

ሰኔ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ መራሹ መንግሥት በቀጣይ ዓመት የሚጠናቀቀው የእድገትን የትራንስፎርሜሽን እቅድ በአብዛኛው ዘርፎች ባያሳካም የመጪውን ዓመት ምርጫ ተከትሎ በጊዜያዊነት የሕዝቡን ድጋፍ የሚያስገኙለትን ሥራዎች ለማከናውን አቅዶ መንቀሳቀስ መጀመሩን የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል
በዚሁዕቅድመሠረትየመኖሪያቤትለማግኘትወደ 800ሺሕዝብየተመዘገበበትበአዲስ አበባከተማበያዝነውወርእናበነሐሴወር 40 ሺኮንዶምኒየምቤቶችንእጣለማውጣትናበዚህምድጋፍለማግኘትታቅዶአል፡፡
በተመሳሳይሁኔታእስከ ታህሳስወር 2007 ባሉት ጊዜያት እንዲሁ ወደ 40ሺ የሚሆኑ ተጨማሪ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ምንጮቻችን ጠቁመዋል፡፡
ከዚህቀደምየቤቶቹግንባታ 50 በመቶ እንኩዋን ሳይጠናቀቅ በአየር ላይ ዕጣ እንዲወጣ በማድረግ ዕድለኞች ቤታቸውን እስኪረከቡ እስከ ሁለት ዓመታት ጊዜ ይፈጅ የነበረው ጊዜ አሁን ከምርጫው ጋር በተገናኘ ዕጣው በወጣ ሰሞን ዕድለኞች ቤቱን እንዲረከቡ በከተማዋ አስተዳደር በኩል ጥንቃቄ እንዲደረግ በተሰጠው ማሳሰቢያ መሰረት ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞች እጣው በወጣበት ሰሞን ቤታቸውን ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በአዲስ አበባ ያለው መኖሪያ ቤት ችግር የኢህአዴግ አባላትም ጭምር በየጊዜው ቅሬታ የሚያቀርቡበትና የሚጋሩት በመሆኑ ገዥው ፓርቲ በጊዜያዊነት በሚወስዳቸው እርምጃዎች ጥገናዊ ለውጥ አገኝበታለሁ ብሎ ማመኑ ተጠቁሞአል፡፡
በተለይ በአስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ዜጎች ችግሮቻቸውን ማለትም የብድር፣የመስሪያ ቦታና የመሳሰሉት በአፋጣኝ ተፈትቶላቸው ይህን ኃይል የምርጫ ሠራዊት ለማድረግ መታሰቡም ታውቋል፡፡
ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እጅግ የተለጠጠ የአምስት ዓመት ዕቅዱ በቀጣይ ዓመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ሲሆን በዚህ ዕቅድ መሠረት ይደረስበታል ተብሎ የታሰቡ ስራዎች በአብዛኛው ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡
በተለይባለፉትሁለትዓመታትበቡናላይየተመሰረተውኤክስፖርትመቀዛቀዙ መንግስትን ከፍተኛገቢአሳጥቶታል፡፡
የሰለጠነየሰውሃይልእጥረት፣የፋይናንስአቅምውስንነትእንዲሁምዕቅዱሁሉንምወገንአሳታፊባለመሆኑምክንያትከግብርናወደኢንዱስትሪይደረጋልየተባለውሽግግርበአየር ላይ መቅረቱን ምንጮች ይገልጻሉ፡፡
የግልባለሃብቱንበማሳተፍረገድየታየውዳተኝነትናበኢኮኖሚውስጥየመንግስትናበገዥውፓርቲስርያሉየንግድተቋማትጣልቃገብነትመጠናከርዕቅዱእንዳይሳካትልቅአስተዋጽኦማድረጋቸው ታውቋል፡፡
ኢህአዴግ በምርጫ የማሸነፊያ ስትራቴጂው መሰረት ለከተማ ነዋሪዎች መሬት በአነስተኛ ገንዘብ ያከፋፍላል። ለአርሶአደሮች ደግሞ የማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር እዳ እፎይታ ይሰጣል።
ኢህአዴግ ይፋዊ ያልሆነ የምርጫ ቅስቀሳውን አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ፣ በተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ  በአምስት አመቱ ተገኙ ያላቸውን ድሎች በራሱ ካድሬዎች አማካኝነት ህዝቡ እንዲያውቃቸው እየጣረ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ህዝቡ ኢህአዴግ ካሰበው በተቀራኒ እየተናገረ ሲሆን በቅርቡ በሳምንቱ መግቢያ በደብረብርሃን ከተማ ተካሂዶ በነበረው ውይይት ላይ ህዝቡ በልማቱ ተጠቃሚ አለመሆኑን መናገሩ ታውቋል።
በደብረብርሃን የነበረውን ስብሰባ ዜና እና የህዝቡን አስተያየት በነገው ዜና የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

Tuesday, June 10, 2014

Teddy Afro’s response to Coca-Cola statement

We issued a press release on May 31,2014 regarding our position on the unwarranted prevention of the release of the Ethiopian Version of the World Cup Anthem.
So far, Coca Cola or its Agent, Manadala TV, have not given us any response although we have brought the issue to their attention before we decided to publish the press release on our website. No surprise, this pattern of conduct has been consistent over the past several months.
Much to our surprise, we now have come across a statement issued by Coca Cola on June 7, 2014, posted on “Tadias Megazine,” and although we have not yet received the statement directly, in the interest of our esteemed fans, we deemed it appropriate to clarify and expose issues in the statement that have no contractual, factual or legal basis. The statement begins by explaining how and for what goal Teddy Afro came in contact with Coca Cola. “Teddy Afro was brought into our Coke Studio in Africa to record a version of the Coca-Cola FIFA World Cup song, ‘The World is Ours’ with the goal of capturing the unique genre of Ethiopian music,” the statement reads.
Teddy Afro, Coca-Cola and the World cup 2014

The statement however, does not indicate or reveal who “brought” him and made the selection. As we explained in our press release, Mr. Misikir Mulugeta approached us and took the initiative to make the selection for the Coke project and further “brought” us in touch with Coke Studio, signed the contract with Mandala TV, the agent for Coca Cola, Central, East and West Africa Limited.Notwithstanding the employment and agent-principal legal relationship between Coca Cola, Mr. Misikir and Mandala TV respectively, the statement categorically denied any relationship whatsoever and even went much further as to dissociate the link by emphasizing that “the contract with Teddy Afro was executed by a 3rd party, Mandala Limited, a production House based Nairobi.” (Italic ours.)
A 3rd party is one who is not a party to…agreement or other transactions… and sometimes termed as outside party. This means that according to the statement, Mr. Misikir Mulugeta, Brand Manager for Ethiopia and Eritrea, and Manadala TV, the agent that provides various services for the production and launch of a music property called COKE STUDIO, are strangers that have nothing to do with the agreement or any transaction with Coca Cola as well as what has been plainly described in the statement as “Our Coke Studio.”
Mr. Misikir as an employee and Manadala TV as the agent who have been contracted to carry out various musical property services and acted for and on behalf of Coca Cola Central, East and West Africa, in the same legal capacity and effect as the representative of Coca Cola, headquartered in Atlanta that issued the statement.
This factual and legal nexus between the employee and the agent with Coca Cola has been entirely rejected by replacing the relationship, in the statement issued, with an entirely irrelevant term of “third party” in an attempt to distance any attachment with Coca Cola. It is quite reminiscent of Pilate’s biblical quote: “I wash my hands off!”
This is a degrading and disrespectful statement that challenges and defies the wisdom, mind and understanding of humanity, all of our fans and even Coca Cola’s Customers. It is also an act against the supposed corporate ethical principles of integrity, honesty, public trust and confidence.
If Coca Cola does not have any relationship with Teddy Afro, then why did it feel the need to issue the statement in general and its emphasis and confirmation, among others, on Teddy’s compensation “in full for his efforts,” and that “the produced track become the property of Coca-Cola CEWA?”
Regrettably, over the past months we have been receiving similar reactions and sustaining gruesome damages in most verbal and written correspondences with Coca Cola and Manadala TV. We do not believe such acts to be the result of good faith or lack of knowledge, but rather acts of utter and wanton disregard or corporate arrogance at best.
With patience, humility and honour befitting all self-respecting Ethiopians, we nevertheless await the highly anticipated release of the anthem or the disclosure of the reason for its non-release until the last second of the opening ceremony of the World Cup.
http://ecadforum.com/2014/06/10/teddy-afros-response-to-coca-cola-statement/

ሰማዕታትን እንዘክር፤ እራሳችንንም እንጠይቅ! (ግንቦት7)

ሰኔ 1997 በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የተለከፉ የትግራይ ገዢ ጉጅሌ አባላት ጭካኔ በይፋ የታየበት ወቅት ነው። ለዓመታት በማስመሰያ ጭንብል ተሸፋፍኖ የቆየው የህወሓት እውነተኛ ባህርይ የዛሬ ዘጠኝ ዓመት በወርሃ ሰኔ አደባባይ ወጣ። በሀውዜን ላይ የደረሰውን የግፍ ጭፍጨፋ ሲያወግዝ የቆየው ቡድን ሌላ ሀውዜን አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ፈጠረ። ይኸኛው ሀውዜን ግን በአንድ ቦታ ተወስኖ የቀረ አልነበረም። ጭፍጨፋው በአዲስ አበባ ተጀምሮ ወደ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ አዋሳ፣ ሃረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች ከተሞችና ገጠሮች ተዛመተ። “አግዓዚ” የተሰኘው ገዳይ ሠራዊት በሰላማዊ እናቶችና አባቶች፤ ወጣቶችና ህፃናት ላይ ዘመተ። ደብተርና እርሳሶቻቸውን እንደያዙ ከትምህርት ቤት የሚመለሱ እምቦቃቅላ ህፃናትን ሳይቀር በጥይት ግንባርና ደረታቸውን እየመታ ጣለ።Ginbot 7 Ethiopian opposition party
በ1997ቱ ሚያዝያ መጨረሻና ግንቦት መጀመሪያ ላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በደስታና ተስፋ ተሞልቶ ነበር። የሚያዝያ 30 ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ እና የግንቦት 7 ጨዋነት የተላበለው ምርጫ የፈጠሩት ተስፋ ቃላት ሊገልጹት በሚችሉት በላይ ነበር። ሆኖም በህወሓት የተመራው የሰኔው ጭፍጨፋ ያንን ሠናይ ስሜት አደፈረሰው፤ አጨለመው።
በዘረኝነት፣ በአፍቅሮተ ንዋይና አፍቅሮተ ሥልጣን የታወረው ወያኔ ከራሱ አባላት ሌላ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው መኖሩ አይታየውም። በህወሓት ጎጠኞች እሳቤ መሠረት ወጣት ሽብሬ፣ ህፃን ነቢዩ፣ ወ/ሮ እቴነሽ፣ ሌሎች እናቶችና አባቶች ሰዎች አይደሉም። ስለሆነም ያለአንዳች ምክንያት ተገደሉ። እስከዛሬ ድረስም ከገዳዮች መካከል አንዱ እንኳን ተጠያቂ አልሆነም። በግልባጩ ገዳዮች በመግደላቸው ተሾሙ፤ ተሸለሙ። ይህ ሁሉ ያሳምማል።
የሰኔ 1997 ሰማዕታትን የምናስባቸው በጥልቅ ሃዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትና እልህ ጭምርም ነው። ወገኖቻችን እንደሰው ባለመቆጠራቸው ተገደሉ። አሁንም እንደሰው የማይቆጠሩ በመሆኑ ሙት ዓመታቸውን መዘከር ወንጀል ነው። መቸ ነው ይህ ውርደት የሚያበቃው?
ሰማዕታት ወገኖቻችን የሕይወት ዋጋ ከፍለው ዘረኝነትን የማስወገድ ሸክም እኛ ላይ ጥለዋል። እኛስ ይህንን ኃላፊነት ለመሸከም ብቁዎች ነንን? እያንዳንዳችን የገዛ ራሳችንን እንጠይቅ።
ዘላለማዊ ክብር ለሰማዕቶቻችን !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!
http://ecadforum.com/Amharic/archives/12501/