(በ ለምለም ሀይሌ)
ባሁኑ ግዜ በሀገራችን ያለውን ሰላማዊ ትግል አስመልክቶ የተለያዩ ነጥቦችን ማንሳት ይቻላል። ከአመት በላይ ያስቆጠረውን የድምጻችን ይሰማ ሰላማዊ ትግል፣ የሰማያዊ ፓርቲ እና የአንድነት ፓርቲ እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ይህ ነው የሚባል አይደለም። በተለይ በ 2009 ዓ ም በወጣው ANTI TERRORISM LAW በታጠረውና ምንም አይነት የመናገር ነጻነት በሌለበት ሀገር ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በሀገራችን ያለውን የመብት ረገጣ፣የዜጎች ያለአግባብ መፈናቀል ይብቃ በማለት እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ ትግል ይህ ነው የሚባል አይደለም። ይህ ነገር ለሌሎች አስተማሪና በተለይ እዚህ ነጻነት ባለበት ሀገር ለምንኖር ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የበለጠ እንድንሰራና እንድንታገል የሚያደርግ ነው።
የሰማያዊ ፓርቲ በቅርብ ግዜ እያደረገ ያለው ከፍተኛ ትግልና ሰላማዊ ሰልፍ የሚኖረውን የህዝብ ብዛት ስንመለከት፣ ለወጣለት አላማ ምን ያህል ቆርጦ የተነሳ ህዝብ እንዳለ እንረዳለን። ሆኖም ግን በዚህ ትግል ውስጥ የሚደርስባቸው እና እየደረሰባቸው ያለ ከፍተኛ የሆነ ችግር እንዳለ ግልጽ ነው።
በተለያዩ ቦታዎች የቅስቀሳ ስራቸውን እንዳያደርጉ ከመታገድ ጀምሮ እስከ ድብደባና እስር ያሉ ጉዳቶች ይደርስባቸዋል። ያልተፈቀደላችሁ ቦታ ቅስቀሳ አካሂዳችዃል፣ እንዲሁም ያልተፈቀደላችሁ ቦታ ሰላማዊ ሰልፍ ወታችዃል በሚሉ ጥቃቅንና ተልካሻ ምክንያቶች ከሚድያ ሽፋን ውጭ በመሆን በአባላቱ ላይ እየደረሰ ያለውን ድብደባና እስር፣ ይህን ሰላማዊ ትግል ለማስቆም ከተደረጉ ጥረቶች መሀከል ይጠቀሳሉ።
ነገር ግን የትግሉ መሪዎች ይህን ሁሉ በገዢው መንግስት እየደረሰባቸው ያለውን ችግር በመቋቋም የያዙትን አላማ ከግብ ለማድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ። ለ22 አመት በአንድ ጨቋኝ መንግስት ስትመራ ለቆየች ሀገር ትክክለኛና ደሞክራሲያዊ የሆነ አስተዳደር ለማምጣት ከፍተኛ የሆነ መስዋእትነትን ይጠይቃል።
ስለዚህም ይህንን በአለም ያለ የነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያውያን እና በተለይም በሀገር ውስጥ ላለው ከማንም ቀድሞ ጥቃት ለሚደርስበት ወገናችን ከጎን በመሆን ይህን ሰላማዊ ትግል ከዳር ለማድረስ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል በጋራ በመሆን በወያኔ መንጋጋ ውስት ወድቃ ያለችውን ሀገራችንን ነጻ እናውጣት።
No comments:
Post a Comment