Friday, June 14, 2013

በደቡብ ጎንደር ዞን መምህራን በደህንነት ሀይሎች ታፍነው ተወሰዱ


gondar_6
ሰኔ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደብረ ታቦር ከተማ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ የተባሉ መምህራን ትናንት ማታ እና ዛሬ ጠዋት በደህንነት ሐይሎች ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዳቸውን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
መምህር ታደሰ መንግስቴና መምህር ፈቃዱ ጌትነት የሚባሉ በ ፈቀደ እግዚ ኮሌጅ ውስጥ አስተማሪዎች ሲሆኑ መምህር አሸናፊ አለሙ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ መምህር ነው።
አብይ ሃይሌ እና ማስረሻ የተባሉ ወጣቶችም እንዲሁ ታፍነው ተወስደዋል።
ታፍነው ከተወሰዱት መካከል የሁለቱ የቅርብ ጓደኛ የሆነ ወጣት እንደገለጸው ቤተሰቦቻቸው የአካባቢውን ፖሊሶች ሲጠይቁ ” የት እንደተወሰዱ አናውቅም” የሚል መልስ ተሰጥቷቸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የፌደራል ፖሊስ አዛዦችን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

Thursday, June 13, 2013

የግብጽ መከላኪያ ሚንስተር በኢትዮጵያ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ ግዜው ገና ነው አሉ


Egyptian armed forces spokesperson Ahmed Mohamed Ali said Thursday that it is too early to talk about military action against Ethiopia over the Grand Renaissance Dam dispute.
Egypt has other political, economic and social means with which to tackle the matter, Ali stated, adding “military action is usually a last resort.”
The statement comes after President Mohamed Morsy warned Monday that Egypt does not want war with Ethiopia but will keep “all options open,” piling pressure on an ongoing dispute over the giant dam Addis Ababa is building across the River Nile.
In a televised speech to cheering Islamist supporters, Morsy voiced his understanding for the development needs of poorer nations upstream in the Nile basin, but still deployed emotive language to claim Egyptians would not tolerate any reduction in water supplies.
“Egypt’s water security cannot be violated in any way,” Morsy said. “As head of state, I confirm to you that all options are open.”
“We are not calling for war, but we will never permit our water security…to be threatened,” the president added.
Drawing on an old Egyptian song about the Nile, he said: “If it diminishes by one drop then our blood is the alternative.”
Source/www. egyptindependent.com

ፓርላማው የኢንተቤን የአባይ ወንዝ አጠቃቀም ውል አፀደቀ


የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብዛኛውን የአባይ ወንዝ ግብፅና ሱዳን እንዲጠቀሙ ያደርጋል የተባለ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል የሚተካ ውል ዛሬ አፅድቋል።
የአባይ ተፋሰስ - /ደቡብ ሱዳን ነፃ ከመውጣቷ በፊት የተሠራ ካርታ ስለሆነ ስሟ አልተጠቀሰም፡፡ አሥራ አንዱ የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ (ዲ.ሪ)፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ ናቸው፡፡/
የአባይ ተፋሰስ – /ደቡብ ሱዳን ነፃ ከመውጣቷ በፊት የተሠራ ካርታ ስለሆነ ስሟ አልተጠቀሰም፡፡ አሥራ አንዱ የአባይ ተፋሰስ ሃገሮች ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ (ዲ.ሪ)፣ ታንዛኒያ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራ፣ ግብፅ ናቸው፡፡/
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ33ተኛው መደበኛ ስብሰባው ከመከረባቸው አምስት ጉዳዮች አንዱ የሆነውን የአባይ ተፋሰስ የትብብር ስምምነት ረቂቅ አዋጅ እንዳፀደቀ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ስምምነቱ አባይን በጋራና በፍትሃዊ መንገድ ለመጠቀም በተፋሰሱ አባላት አገሮች ካሁን ቀደም ኢንቴቤ-ዩጋንዳ ውስጥ የተፈረመ መሆኑ ይታወቃል።
ከኢትዮጵያ በስተቀር አምስቱ አገሮች ማለትም የርዋንዳ፣ የታንዛኒያ፣ የዩጋንዳ፣ የኬንያና የቡሩንዲ ፓርላማዎች ቀደም ብለው ውሉን ያፀደቁት መሆኑን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል።
የኢንቴቤ ስምምነት እየተባለ የሚጠራው ውል ቅኝ ገዢ በነበረችው ታላቋ ብሪታኒያ በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር በ1929 ዓ.ም የተረቀቀና በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከተፋሰስ አገሮች ይልቅ ለግብፅ ሙሉ መብት የሚሰጠውን ውል የሚተካ መሆኑ ይታወቃል።
ውሉ ዛሬ በኢትዮጵያ የተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ሰሞኑን በግብፅና በኢትዮጵያ መካከል በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ ከሚካሄደው ውዝግብ ጋር ግንኙነት እንደሌለው የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
ይህ ዛሬ የጸደቀው ውል ምንድነው? አቶ አያና ይናገራሉ፡፡
ለተጨማሪና ዝርዝር ትዝታ በላቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት የሕዝብ ግንኙት ባለሙያ አቶ አያና ከበደ ጋር ያካሄደችውን ሙሉ ቃለምልልስ ያድምጡ፡፡
VOA

Wednesday, June 12, 2013

ወደሶማሌ ክልል ተጉዞ የነበረው የአርቲስቶችና የጋዜጠኞች ቡድን በክልሉ አስተማማኝ ሰላም እንዳለ ምስክርነቱን በመስጠት የአንድ ሳምንት ጉዞውን ሰኞ ዕለት አጠናቀቀ

ሰኔ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ቡድኑ ከጎዴ ተነስቶ በቀብሪደህር፣ በደገሃቡር፣ በቀብሪበይህ፣ በጂጂጋ አድርጎ ወደሐረር በመግባት የሳምንት ጉዞውን በድሬዳዋ ከተማ ባለፈው እሁድ አጠናቋል፡፡
በጉዞው ወቅት በአገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገለት የተጓዘው የዚሁ ቡድን አባላት ከሆኑት መካከል፤ አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ፣ደበሽ ተመስገን፣ጥላሁን ጉግሳ፣ችሮታው ከልካይ፣አብራር አብዶ፣ አበበ ባልቻና የመሳሰሉ አርቲስቶችና ጸሐፊዎች “በሶማሌ ክልል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም አለ” በሚል   ምስክርነት የሰጡ ሲሆን  ይህም  ብዙዎችን አስገርሟል፡፡
አርቲስት ሰራዊት ፍቅሬ በአንድ መድረክ ላይ ባደረገው ንግግር “መጀመሪያ ከቤተሰቦቼ በቀን ለአምስት ጊዜያት ያህል ሰላም ነህ ወይ እየተባለ ይደወልልኝ ነበር፡፡ ቀስ እያለ በቀን ወደሶስቴ፣ ወደሁለቴ ወረደ፡፡ በአሁኑ ወቅት እኛ እንምጣ ወይ ሳይሉ አይቀሩም” በማለት  ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡
በጉዞው ወቅት የመከላከያ ሰራዊት ቡድኑን ከማጀቡም በተጨማሪ በየበረሃው ከወትሮው በተለየ መልኩ የሰራዊቱ አባላት በከፍተኛ ቁጥር ተሰማርተው መታየታቸው፤ በአካባቢው የጸጥታ ችግር መኖሩን ጠቋሚ ኧንደሆነ በቡድኑ ውስጥ የተሳተፉ ወገኖች ተናግረዋል፡፡
በአንዳንድ አካባቢዎችም ጉዞው ለደቂቃዎች እንዲቆም ኧየተደርገ ሰራዊቱ ቦታ ቦታውን ከያዘ በሃላ  እንዲቀጥል መደረጉታውቋል፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ አንዳንድ አርቲስቶች የሰጡት  ምስክርነት እውነታውን የማይገልጽ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ያስገመተ እንደሆነ ለመረዳት ተችሎአል፡፡
በግልጽ ንግግራቸው የሚታወቁት የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ ባለፈው ዓርብ ዕለት ለአርቲስቶችና ጋዜጠኞች ባደረጉት ንግግር በክልሉ በተቃዋሚነት የሚንቀሳቀሰው ኦብነግ የተባለው ቡድን ጠንካራ እንደነበር አረጋግጠዋል፡፡
ኦብነግ ታላቋ ሶማሊያን ለመገንባት በእነኳታርና ግብጽ እየተደገፈ ሲንቀሳቀስ መቆየቱን፣ በዚህ ምክንያት የክልሉ ሰላም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ወድቆ እንደነበር በንግግራቸው ያስታወሱት ፕሬዝዳንቱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሳይቀር የኦብነግን እንቅስቃሴ በመደገፍ በሁለት ቢላዋ ይበሉ እንደነበር አረጋግጠዋል፡፡
በአንድ ወቅት በውጪ አገር ለኦብነግ ድጋፍ አልሰጥም ያለ የክልሉ ተወላጅ ወደሶማሌ ክልል ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ በሄደበት ጊዜ በክልሉ ፖሊስ ተይዞ ያለአንዳች ምክንያት እንዲታሰር መደረጉን ያወሱት ፕሬዝዳንቱ   ኦብነግን ለምንድነው የማትደግፈው ተብሎ ሲጠየቅም፤ ሰውየው ጥፋተኛ መሆኑን፣ ከእንግዲህ ለመደገፍና ያለፈውንም ለመካስ ቃል በመግባቱ ከእስር መለቀቁን በመግለፅ ግንባሩ የቱን ያህል የመንግስት መዋቅርን ጭምር ተቆጣጥሮት እንደነበር ተናግረዋል፡፡
አቶ አብዲ በአሁኑ ሰዓት_ ኦብነግን ጨምሮ የሌሎች የጠላት ሃይሎች እንቅስቃሴ በመከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ ልዩ ሃይልና በሕዝቡ ትብብር ተረጋግጦአል ቢሉም አንዳንድ በጅጅጋ ያነጋገርናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ግን ዋና ከተማዋ ጅጅጋ እንኩዋን በከፍተኛ ጥበቃ ስር በመሆንዋ እንደልብ ወጥቶ ለመግባት እንደማይቻል ተናግረዋል:: አክለውም  ይህ የሰላም ምልክት እንዴት ሊሆን ይችላል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
ለ አርቲስቶችና ለጋዜጠኞች ቡድን በሶማሌ እና በሐረሪ ክልሎች ከፍተኛ አቀባበልና የጫት ግብዣ ተደርጎላቸዋል:: በቆይታቸው ደረጃውን ለጠበቀ የጫት ግብዝ ብቻ   ከ100ሺ ብር በላይ እንደወጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ወገኖች አረጋግጠዋል፡፡
ጉዞውን የፌዴሬሽን ም/ቤት ከክልሎቹ ጋር በመቀናጀት ያዘጋጀው ነበር፡፡

ESAT Daily News - Amsterdam June 12, 2013 Ethiopia


ወያኔ በሁመራ ከአርበኞች ጋር መዋጋቱን አመነ

Ethiopian People Patriotic Front Fighters in Action
CADF – ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር “ነበልባል” በመባል የሚታወቀው ባብዛኛው በወጣቶች የተገነባው ተዋጊ ሀይል በሁመራ አካባቢ 35ኛውን የወያኔ ክፍለጦርና ሚሊሻዎችን ገጥሞ አንጸባራቂ ድል እንደተቀናጀ አስታውቆ ነበር። ዜናውን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ።
ቁስለኞቹን እና የተገደሉ ወታደሮቹን ሲያሸሽ የከረመው ወያኔ ከሶስት ሳምንታት በሗላ አርበኞችን ገደልኩ… ብሎ ዜና ሰርቶ ለቋል።
በሁመራ አካባቢ የተደረገውን የአርበኞቹን የውጊያ ውሎ የግንባሩ ሬድዮ በበኩሉ እንደሚከተለው ዘግቦታል፣
“35ኛው የወያኔ ክፍለጦር አባላት አዳዲስ ኦራል መኪና በመንዳትና አዳዲስ ዩኒፎርም በመልበስ አስፈሪ የጦር ሀይል ይመስሉ ነበር… ይሁንና ያን ሁሉ ኩራት እና መመጻደቅ ግንቦት 24 ቀን ነበልባሉ አርበኛ ውሀ ቸልሶበታል.. አዳዲሶቹ ኦራል መኪኖችም የወያኔዎቹን ቁስለኛና ሟች ወታደሮች ሲያጓጉዙ ሰንብተዋል።”
እንደ ሬድዮው ዘገባ የጎንደር ነዋሪዎች በአርበኞቹ የወጊያ ብቃትና ጀግንነት እጅግ ተደንቀዋል።
የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር ሬድዮ ዘገባን ያዳምጡ።
Ethiopian People Patriotic Front fighters

ኢትዮጵያ በግብፅ ላይ ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ ይበቃታል

በፋኑኤል ክንፉ
የግብፅ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ የሕዳሴውን ሃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በተመለከተ ሁሉም አማራጮች በጠረጴዛ ላይ ናቸው ማለታቸውን ተከትሎ፣ አንድ የቀድሞ መንግስት ከፍተኛ ወታደራዊ ኤክስፐርት የግብፅ መንግስት ላይ ተመጣጣኝ እርምጃ ለመውሰድ 1ሺ 500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል መታጠቅ ብቻ በቂ ነው ሲሉ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።
ኤክስፐርቱ እንደገለፁት “ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግንባታ ግድብ በጦር መሣሪያ ለመምታት ካስቀመጠቻቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን በመጠቆም ግብፅ የሕዳሴውን ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመታ ለኢትዮጵያ መንግስት ደግሞ በአፀፋው የአስዋን ግድብን እንዲመታ ሕጋዊ ፍቃድ መስጠቷን ልታውቅ ይገባል” ብለዋል።
አያይዘውም፤ “ግብፅ በወታደራዊ እቅዷ ከገፋችበት በኢትዮጵያ በኩል አማራጭ መንገዶችን መመልከት ተገቢ ነው። ለምሳሌ፤ ከሰሜን ኢትዮጵያ መነሻ አድርገህ ላቲቲውዱን በ14.3000 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን በ36.6167 ዲግሪ ብትወስደው እንዲሁም አስዋን የሚገኝበት ላቲቲውድ 23.9706 ዲግሪ እና ሎንግቲውዱን 32.8779 ዲግሪን አቀናጅተህ ብታሰላው በአየር ላይ ያለው ርቀት ከ1100 እስከ 1500 ኪሎ ሜትር የአየር ርቀት ነው ያለው። በዚህ ውጤት መነሻ የኢትዮጵያ መንግስት ከ1500 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ የስከድ ሚሳኤሎችን መታጠቅ ብቻ በግብፅ አሰዋን ግድብ ላይ ተመጣጣኝ ሃይል ሊፈጥር ይችላል።”  ብለዋል።
ወታደራዊ የአየር ርቀቱን ለመለካት የተሄደበትን አሰራር ቢያብራሩት ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፤ “ይህ ሮኬት ሳይንስ አይደለም። http://www.movable-type.co.uk/scripts/latlong-gridref.html በሚለው ድረ ገጽ ዲግሪውን በመጠቀም ማስላት ይቻላል። ቁም ነገሩ ግን ወታደራዊ አማራጭ ሁለቱንም ወገኖች ተጠቃሚ አያደርግም። ብቸኛው አማራጭ በዲፕሎማሲ ደረጃ ለመፍታት መሞከር ነው” ሲሉ ኤክስፐርቱ አሳስበዋል።
በአሁን ሰዓት በዓለማችን ላይ ከ1ሺ 500 ኪሎ ሜትር እስከ 15ሺ ኪሎ ሜትር የሚወነጨፍ ሚሳኤል የታጠቁ ሀገሮች አሉ። ከእነዚህ ውስጥ ፈረንሳይ፣ ሕንድ፣ ኢራን፣ እስራኤል፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ቻይና፣ ፓኪስታን፣ ሩሲያ፣ ሳዑዲአረቢያ እና አሜሪካ ይገኙበታል።