Saturday, January 25, 2014
የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው አቶ በቀለ ገርባ አልተፈታም፤
የእስር ጊዜውን ያጠናቀቀው አቶ በቀለ ገርባ አልተፈታም፤ በውሸት በተቀነባበረ ሴራ በህገወጥ ፍርድ በግፍ ያለ አግባብ የታሰረውና እና አሁን የእስር ጊዜውን ጨርሶው ያልተፈታው መምህር በቀለ ገርባ። «አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው» የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች በእስር ቤት የሚገኘው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ኦፌዴን) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ በባለፈው እሁድ የእስራት ቅጣቱን አጠናቆ የነበረ እና መፈታት የነበረበት ቢሆንም እስካሁን ድረስ በእስር ቤት ነው የሚገኘው። በቅርቡ ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ቃሌቲ ሄደን አግኝተነው ነበር። አመክሮ ለማግኘት እንደ መስፈርት የሚወሰደው፤ በቆይታው ወቅት የነበረው ስነ ምግባር በበቂ ሁኔታ እንዳሟላ እንደተገለፀለት ነግሮናል። ወደ ማረሚያ ቤት ከመግባቱ በፊት ማእከላዊ ያሳለፋቸው 41 ቀናት ሲደመሩ ነው ባለፈው እሁድ መውጣት የነበረበት። ማእከላዊ በእስር የቆየባቸው ቀናት መያዝና እና አለመያዝ የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር የይሁንታ ፈቃድ ማግኘት እንደሚያስፈልግ ተነግሮታል። በህጉ መሰረት ከሆነ ግን ማንም መፍቀድ ሳይጠበቅበት ሊደመርለት ይገባ ነበር። ትላንት ይህን ጉዳይ ይዘው የማረሚያ ቤቱን ሃላፊዎች ለጠየቁ ቤተሰቦቹ «አመክሮ መስጠትም አለመስጠትም መብታችን ነው» የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። በቀለን ለመጠየቅ የሚፈልግ በስራ ቀናት ጠዋትና ከሰዓት፤ በእረፍት ቀናት ደግሞ ጠዋት ብቻ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን 2 ሄዶ ማግኘት ይችላል። ፍትህ ለበቀለ ገርባ!
Thursday, January 23, 2014
ከቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ የሚያንጸባርቁ ከዋክብት (ዳዊት ከበደ ወየሳ፣ አትላንታ)
(ይህ ጽሁፍ የርዕዮት አለሙ የልደት በአል በአዲስ አበባ በተከበረበት ወቅት; ከውጭ አገር ንግግር እንዳደርግ በተጋበዝኩበት ወቅት… የስራ ባልደረቦቼን እስክንድር, ውብሸት እና ርዕዮትን በማሰብ የተዘጋጀ ነው)
ይህ ሳምንት የታላቁ ማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በመላ አሜሪካ የሚከበርበት ነው:: በአሜሪካ ከክርስቶስ ልደት ቀጥሎ ስራ እና ትምህርት ቤት ተዘግቶ ልደቱ የሚከበርለት አንድ ሰው ቢኖር ማርቲን ሉተር ኪንግ ብቻ መሆኑን ልብ ይበሉ:: የማርቲን ሉተር ኪንግ የልደት በአል በሚከበርበት ወቅት በህይወት ዘመኑ ለጥቁር ህዝብ ነጻነት ያደረገው አስተዋፅኦ ይታወሳል:: በህይወት በነበረበት ወቅት ለሰው ልጅ እኩልነት ተሟግቷል; የነጻነት ቀንዲልን ለኩሷል:: ሆኖም እኩልነት እና ነጻነትን ሳያጣጥም በበርሚንግሃም እስር ቤት ተጥሎ ፍዳውን እንዲቆጥር ተፈርዶበት ነበር:: በመጨረሻም የሰውን ልጅ ክብር እና ነጻነት በማይደግፉ ሰዎች ህይወቱ ማለፉ ይታወቃል – መልካም ስራዎቹ ግን አላለፉም::
ዛሬም በአገራችን ስለፍትህ, ስለነጻነት የሰበኩና የደሰኮሩ; የጻፉና የመሰከሩ… ለሃቅ ቆመው፣ ግፍ የተሰራባቸው፣ ከአገር የተሰደዱና የወጡ፤ በግፍ ሰንሰለት ለጨለማ እስር የተዳረጉ ወገኖቻችን ብዙ ናቸው:: እስክንድር፣ ውብሸት፣ ርእዮት፣ አንዷለም እና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ራሳቸውን በሰብአዊነት መሰረት ላይ ስላነጹ እና ሃሳባቸውን በነጻነት ስለገለጹ መጨረሻቸው እስር እና እንግልት ሆኗል::
እንደ እውነቱ ከሆነ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ… ብሎም የህዝብ ልሳን ሆኖ ለህዝብ የቤዛነት ዋጋ መክፈል የሚያስከብር እንጂ የሚያሳስር አልነበረም:: በመሆኑም ለነጻ ፕሬስ መክፈል የሚገባቸውን ዋጋ ከመጠን አሳልፈው የከፈሉት፤ ርዕዮት አለሙ፣ እስክንድር ነጋ እና ውብሸት ታዬ… ሶስቱም ከአገራቸው አልፈው በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና አግኝተዋል:: በአለም አቀፍ ደረጃም በልዩ ልዩ አለም አቀፍ የጋዜጠኞች ማህበራትና ተቅውውማት ለሽልማት ታጭተው አሸናፊ ሆነዋል::
የ’ነዚህ የስራ ባልደረቦቼ ብዕር… ህዝብን ሳይሆን የተወሰኑ ወገኖችን አሸብሮ ሊሆን ይችላል:: እነርዕዮት አለሙ በዚህ አይነት ሰበብ አስባብ በቃሊቲ እና በቂሊንጦ እስር ቤት ታግተው፤ ነጻነታቸውን አጥተውና ህክምና ተነፍገው ይታሰሩ እንጂ፤ ለእውነት የቆሙ ወገኖች ግን ለመልካም ስራቸው ሽልማትን አልነፈጓቸውም::
ማርቲን ሉተር ኪንግ በበርሚንግሃም እስር ቤት ታስሮ ቢማቅቅም የአሜሪካም ሆነ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ አልዘነጋውም:: ቆይቶም ቢሆን የአለም አቀፉ ኖቤል ተሸላሚ እስከመሆን ደርሷል:: ዛሬ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች የኖቤል ተሸላሚ ባይሆኑም አለም ግን አልረሳቸውም:: ከታሰሩበት የጨለማ ወህኒ ቤት ጀርባ፤ ከብረት ፍርግርግ እና ከግድግዳዎቹ ባሻገር በመቶዎች፣ በሺዎች እና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እነዚህን ጋዜጠኞች በመልካም ስራቸው ያስታውሷቸዋል; ይዘክሯቸዋል:: ስለሆነም የጻድቃን ሞት፤ የሰማዕትነት ጽድቅ ተደርጎ እንደሚቆጠረው ሁሉ… የነ እስክንድር፣ ውብሸትና ርዕዮት እስር፤ ከቶውኑ ዋጋ ቢስ እና ፍሬ አልባ ሊሆን አይችልም::
ኢትዮጵያ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት በፕሬስ ጉዳይ ተደጋጋሚ የሆነ እስር ደርሶብኛል:: በ’ነዚህ የእስር እና እንግልት ጊዜያት ግን… ከጨለማው እስር ቤት ማዶ ለምን እንደታሰርኩ የሚረዱ ሺዎች በመኖራቸው ሁልጊዜ እጽናና ነበር:: በተደጋጋሚ እስር ቤት እየመጣ የሚጠይቀኝ እና የዋስ መብቴን አስጠብቆ ከእስር እንድወጣ ያደርገኝ የነበረው ወላጅ አባቴ፤ “የታሰርከው ሰርቀህ ወይም ሌላ ወንጀል ሰርተህ ሳይሆን፤ እውነትን ስለተናገርክ ነው:: ስለዚህ አንገትህን ቀና ልታደርግ እንጂ ልትሸማቀቅ አይገባህም::” የሚል አጽናኝ ቃል ሁሌ ይነግረኝ ነበር:: ዛሬ አባቴ በህይወት የለም:: ቃሉ እና ምክሩ ግን አብሮኝ አለ:: በእስር ላይ ለሚገኙ የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ “አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” የሚለውን መልዕክት አጋራቸዋለሁ::
ዛሬ በጋዜጠኞቻችን ላይ የተለያዩ ክሶች ተመስርቶባቸው መታሰራቸው ሳያንስ; ከታሰሩም በኋላ በሃሰት ሊወነጅሏቸው የሚሹ ብዙ ግራ ዘመም ሰዎች መኖራቸውን ታዝበናል:: በአሜሪካ ከፍተኛ የአየር ሽፋን አግኝቶ ዲሞክራቶችን በመሳደብ የሚታወቀው ራሽ ሊምቦ የተባለ ጋዜጠኛ በቅርቡ ኔልሰን ማንዴላ በሞት ሲለዩ… “ብታምኑም ባታምኑም ኔልሰን ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ::” ብሎ ሰፊ ሙግት ፈጥሮ ነበር:: ይህ አባባሉ ለኛ እና ለሌሎች አፍሪቃውያን ሊገርመን ይችል ይሆናል:: ነገር ግን የራሳቸው አመዛዛኝ ህሊና ያልፈጠረባቸውና ይህን ሰው በጭፍን የሚከተሉት ሰዎች “አዎ ማንዴላ አሸባሪ ነበሩ” ብለው ቢሉ ሊገርመን አይገባም::
ዛሬም ባገራችን በተመሳሳይ መልኩ የነርዕዮት አለሙን መልካም ስም ጥላሸት ለመቀባት እላይ ታች የሚሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ… እኛ ግን እንላለን:: “ወንጀል አልሰራችሁምና አንገታችሁን ቀና አድርጉ!” ስማችሁ ከቃሊቲና ከቂሊንጦ እስር ቤቶች በላይ፤ በጠራው ሰማይ ላይ ያንጸባርቃል፤ ቃለ ሃቃቹህ በአየር ናኝቶ… ኢትዮጵያዊያን ባሉበት ሁሉ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቷል::
የማርቲን ሉተር ኪንግ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቹ እንደሚወደሱ ሁሉ፤ ዛሬም ሆነ ወደፊት የነርእዮት አለሙ ልደት ሲከበር መልካም ስራዎቻቸው በተደጋጋሚ ይነሳሉ ይዘከራሉ:: ዛሬ ማንዴላን አሸባሪ ብለው የሚከሱ ሰዎች እንደመኖራቸው መጠን; በተመሳሳይ መልኩ ለነርእዮት አለሙ ተመሳሳይ ስም የሰጡና ያሰጡ… ለመስጠት እና ለማሰጠት የሚጥሩ ሰዎች አሉ:: እኛ ግን የተለኮሱ ሻማዎች ይዘን ልደት ስናከብር; የብርሃናችን ጮራ፤ ሌሎች የፈጠሩትን የጨለማ ድባብ ሰንጥቆ… አንዳች ብርሃን እንደሚፈነጥቅላቸው በማመን ነው:: ዛሬ የርዕዮት አለሙን የልደት ቀን ስናከብር፤ ያለፍትህ የታሰሩትን ፍትህ የሚፈልጉትን፤ ነጻነት የተጠሙትን ነፍሶች በማሰብ ጭምር ነው::
መልካም ልደት – ርዕዮት!
Wednesday, January 22, 2014
ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ
ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው።
በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል።
ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ የሚጠራውን ቦታ አልፈዋል” በሚል ባቀረቡት አቤቱታ ላይ ተመሰርቶ ኮሚቴ መቋቋሙን ያወሱት ባለስልጣኑ፣ “ይሁን እንጅ ኮሚቴው ምንም አይነት የድንበር ማካለል ሳያደርግ እስከዛሬ ቆይቷል ።”
“አሁን በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሚደረገውን ውይይት የምትገዛው ደብዳቤ ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተለዋወጡት ደብዳቤ መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቅሰው ፣ ኮሚቴው በጊዜው ችግሩን በሰላም ለመፍታት የመፍትሄ ሃሳቦችን አቅርቦ እንደነበርም አክለዋል።
“ሱዳኖች ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያን መሬት ለመውሰድ አቅም አልነበራቸውም ” የሚሉት ባለስልጣኑ ፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ1995/96 የግብጹን መሪ አዲስ አበባ ላይ ለመግደል የተደረገውን ሙከራ ተከትሎ የኢትዮጵያ ጦር አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ የ ትግራይና የአማራ ክልሎች ለኢንቨስተሮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የሱዳን መሬት መስጠታቸውን ገልጸዋል። ሱዳኖች ቀደም ሲል ጀምሮ ግዛታችንን መልሱ የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ቢቆዩም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጥያቄያቸው እየገፋ ምጣቱን አብራርተዋል። 1965 ዓም ጀምሮ መሬት የሚባል ለሱዳን አለመሰጠቱትነ አጠንክረው የተናገሩት ባለስልጣኑ፣ በቅርቡ ግን የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት ሱዳኖች ያቋቋሙት ኮሚቴ አዲስ ሃሳብ ይዞ መቅረቡን ገልጸዋል። አዲሱም ሀሳብ ” መሬቱን እንደያዛችሁት ቆዩ፣ የዜጎቻችሁን መብቶች እናስጠብቃለን፣ ነገር ግን ቢያንስ በንደፈ ሃሳብ ደረጃ መሬቱ የእኛ መሆኑን የሚያሳየውን ካርታ ተቀብላችሁ አረጋግጡልን ” የሚል መሆኑን ባለስልጣኑ አስረድተዋል
“በረኻት የሚባል የትግራይ ከተማ ላይ ሆናችሁ ሞባይላችሁን ብታወጡ የሚያሳያችሁ ሱዳንን ነው፣ እንዲሁም አርማጭሆ ላይ ሆናችሁ ሞባይሎቻችሁን ብታዩ ያላችሁበት ኢትዮጵያ የሚባለው ቦታ ሱዳን ነው ” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ “የፈለገውን ፖለቲከኛ መሸወድ ይቻላል፣ ሳይንሱን ግን መሸወድ አይቻልም” በማለት ገልጸዋል
የአርማጭሆ መሬት ለሱዳን ተሰጠ እየተባለ የሚወራው ውሸት ነው ያሉት ባለስልጣኑ ፣ “አንዳንድ ጊዜ የሱዳን ፖሊስ ድፍረቱ ሲኖረው እየገባ ግጭት ይፈጥራል፣ የኛ ሚሊሺያዎችም የሚሰንፉ አይደሉም ፣ እንዲያውም የእኛ ሚሊሺያዎች የሱዳንን ወታደሮች እንደ ወታደር አይቆጥሩዋቸውም” በማለት በሱዳንና በኢትዮጵያ ድንበር ፖሊሶች መካከል ያለውን ልዩነት ተናግረዋል።
“አይናችን የሚያየውን ሁሉ እንይዛለን ማለት አይደለም” ያሉት ባለስጣኑ፣ በእርግጥ እንያዝ ካልን ካርቱምንም መያዝ እንችላለን ሲሉ የሱዳንን የመከላከያ ብቃት አጣጥለዋል።
አቶ መለስ በነበሩበት ጊዜ በሱዳኖች በኩል ለቀረበው ሃሳብ መልስ እንዲሰጥ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ኮሚቴ በሀሳቦች ልዩነት የተነሳ እስካሁን መልስ መስጠት አለመቻሉንም ባለስልጣኑ ገልጸዋል። አንዳንዱ የኮሚቴ አባል “ከአሁን በሁዋላ ሰዎቻችን ተነሱ ቢባሉስ እንዴት እሽ ብለው ይነሳሉ” የሚል ሀሳብ ያቀርባል ብለዋል።
“ጥያቄችን የሞራል እና የሶሻል እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም” የሚሉት ባለስልጣኑ፣ እርሳቸው አንዱ የኮሚቴው አባል ቢሆኑም መልስ ለመስጠት እንኳን እንደተቸገሩ ተናግረዋል።
“በ1965 በሞፈር ዘመት መሬት የያዙ አርሶአደሮች ከአርባ አመት በሁዋላ የያዛችሁት መሬት አገራችሁ አይደለም ሲባሉ ቢቃወሙ የሚገርም አይሆንም” የሚሉት ከፍተኛው ባለስልጣኑ፣ “የህግ ክርክሮች ቢነሱ የማንኮራባቸው ጉዳዮች ቢኖሩም ቅሉ እስካሁን ግን የድንበር ማካለል ስራ አልተጀመረም ።
ሱዳን ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ በፈረንጆች አቆጣጠር በ2007 ሰፊ መሬት ከኢትዮጵያ ለሱዳን መሰጠቱን የአካባቢውን አስተዳዳሪ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
አዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ።
የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የድርጅቱ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ከወራት በፊት ከተሾሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር አንዳንድ ወገኞች እያገናኙት መሆኑ ስህሀት ነው ይላሉ ጋዜጠኞቹ። በተለይ በቀጣዩ አንድ ዓመት በአስተዳደራዊ መልኩ ከሕትመት እንዲወጡ ለማድረግ የታሰቡ ጋዜጦችና መጽሄቶችን ጉዳይ ለማሳካት ቁርጠኝነት እንዳላቸው በመገመት አቶ ዘርአይ መሾማቸውን ይናገራሉ፡፡
አቶ ዘርዓይ በባህርያቸው ግትርና አምባገነን መሆናቸውን ያስታወሱት ጋዜጠኞች፣ ከዚህ ቀደም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዴሞክራሲ ተቋማት ጉዳይ ላይ ያደረጉት ውይይት ከዕውቅናየ ውጪ እንዲቆራረጥ ተደርጓል በሚል በአንድ የግል ጋዜጣ ተቃውሞ ያቀረበውን አንድ ጋዜጠኛ ያለምንም ማንገራገር ከድርጅቱ እንዲሰናበት ማድረጋቸው የአምባገነንነታቸው አንድ መገለጫ ነው ሲሉ ጋዜጠኞቹ ያወሳሉ።
የኢቴቪ ባልደረባ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለአዲስ አበባው ዘጋቢ እንደተናገረው አቶ ዘርዓይን እንደዋና ስራ አስኪያጅ በቀላሉአግኝቶ ማነጋገር፣ችግርን ማስረዳት ለሰራተኞች እንኩዋን የሚቻል አለመሆኑን በመጥቀስ ወደእሳቸው ቢሮ ከመግባትጠ/ሚኒስትሩ ቢሮ መግባት ይቀል ነበር ብሎአል፡፡
በእሳቸው አመራር ዘመን በድርጅቱ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ባለሙያዎች ሳይቀር የኪራይሰብሳቢነት ዝንባሌ ገዝፎ መታየቱን፣ በተለይ የእሳቸው ተከታይ የሆኑ ጋዜጠኞች ቢያጠፉ እንኩዋን አይቶ ዝም ከማለት ያለፈ እርምጃ አይወስዱም ነበር ብለዋል፡፡
አቶ በረከት ስምኦን የቦርድ ሰብሳቢ በነበሩበት ዓመታት ከአቶ ዘርዓይ ጋር መግባባት እንዳልነበራቸውና ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ አቶ ዘርዓይ ታዛዥነታቸው ከማንም ይልቅ ለህወሃት ሰዎች ብቻ በመሆኑ ነው ሲሉ ጋዜጠኞች ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት አቶ በረከት አዛዡን ማንሳትም፣ መቃወምም ተቸግረው መቆየታቸውን ጋዜጠኛው ተናግሯል።
የአቶ ደስታው ከብሮድካስት ባለስልጣን ዳሬክተርነት ሲነሱ ምናልባት በራሱ የሚተማመን ፣ሕግና ስርዓትን ብቻ አክብሮ የሚሰራ ተሹዋሚ ሊመጣ ይችላል የሚለውን ጭላንጭል ተስፋ የአቶ ዘርዓይ ሹመት እንደሻረው ጋዜጠኛው አክሎ ተናግሯል።
በቦረና ኦሮሞና በቡርጂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሰዎች እየተሰደዱ ነው
ቦረና አከባቢ የሚኖሩ ቡርጂዎች እየተሰደዱ ነው፡፡ ከአከባቢው ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የግጭቱ መንስኤ በቡርጂ መንደር ተገድሎ ተገኘ ተባለ የቦረና ብሄረሰብ አባል አስከሬን ነው፡፡ ባለፉት 70 እና 80 ዓመታት በዚያ አከባቢ ከመኖራቸውም በላይ የኦሮሚኛ ተናጋሪ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቡርጂዎች ዛሬ ለመፈናቀል ያበቃቸው ምክንያት ሴራ እንሆነ ይናገራሉ፡፡ እንደአስተያየት ሰጪዎች መረጃ ታህሳስ 25 በድሬ ወረዳ ሜጋ ከተማ የቡርጂ ተወላጅ ተማሪዎች ክፍል እንዳይገቡ ተከለከሉ፡፡ በ27/ 04 /2006 ዓ.ም በቦዳ ጫጩ ሩምሴ ቀበሌ አቶ ጃርሶ ተባለ የቦረና አባል ሁን ተብሎ በካድሬዎች የግጭት መንስኤ እንዲሆን የተቀነባበረ ሴራ ተገድሎ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ በዚሁ እለት በቦዳ ዜሮ ቀበሌ አቶ ገልገሎ ሁቃ የተባለ የበረና አባል ተገድሎ ተገኘ ፡፡ በዚሁ ግጭት ጫልሰሞ ጮልጎ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባል በኢታኔ ገልዶ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ሱማሌ ህርቦ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ ደግሞ በቦዳ ዜሮ ቀበሌ ተገደለ፡፡ አቶ ቦዴ ፊርጤ የተባለ የቡርጂ ብሄረሰብ አባልም ተገደሉ፡፡
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የቡርጂ ሰዎች
1. አቶ ጉዮ ሞሉ
2. አቶ እብቻ ሎሌ
3. አቶ ብሩ አሸቱ
የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የቡርጂ ሰዎች
1. አቶ ጉዮ ሞሉ
2. አቶ እብቻ ሎሌ
3. አቶ ብሩ አሸቱ
Monday, January 20, 2014
በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!
ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን።
ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን?
አያቶቻችንና አባቶቻችን ደማቸውን ገብረው ፣አጥንታቸውን ከስክሰው ያስረከቡንን የሀገር ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ ለመጭው ትውልድ ማስተላለፍ የእኛ የአሁኑ ትውልድ የታሪክ ግዴታ ነው። ይህን የታሪክ ግዴታችንን ሳንወጣ/ችል በማለት/ በመሰሪው የህወሃት/ ኢህአዴግ አመራር የሃገራችን ሉአላዊነት እየተሸራረፈ ለባዕድ ሀገራት ሲሰጥ በምን አገባኝ ስሜትዝም ብለን ብንመለከት በ– ዚ–ያ ዘመን ዘመናዊ መሳሪያ ከታጠቀ የውጭ ጠላትጋር የሀገሬን ሉአላዊነት አላስደፍርም በማለት በዱላ፣ በጦርና ጋሻ፣ ዘመናዊ ባልሆነ የጦር መሳሪያ ፣በባዶ እግራቸው በመዝመት ደማቸውን አፍስሰው ፣ አጥንታቸውን ከስክሰው የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ሳያስደፍሩያስረከቡን የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይወጋናል።
“የኢትዮጵያ ድንበሮች በኢትዮጵያውያን ደም የራሱ፣ በኢትዮጵያውያን አጥንት የተገነቡ ሲሆኑ ድንበሮቻችንን ለማስከበር ከሁልቆ መሣፍርት፣ ተራ ዜጐች አንስቶ እስከ አንድ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት አጼ ዮሐንስ አንገታቸው ሰጥተዋል፡፡ በዶጋሊ፣ በጉራዓ፣ በጉንዲት፣ በመተማ፣ በአድዋ፣ በወልወል በቅርብ ጊዜያት ደግሞ በሶማሊያና በኤርትራ የፈሰሰው የኢትዮጵያውያን ደም የሌላውን ግዛት በመቋመጥ ሳይሆን ድንበሬን አላስነካም በሚል ነበር፡፡ እንደዛሬው መኪና ወይንም ባቡር ባልኖረበት የቀደምት ኢትዮጵያውያን ከመሃል አገር ተነስተው በእግር ለወራት በረሃውን አቋርጠው፣ ተራራውን ወጥተው፣ ንዳዱን ተቋቁመው፣ ወባውን ደፍረው ከሙስታሂል እስከ ጋምቤላ፣ ከራስ ካሣር እስከ ሞያሌ ዘልቀው ድንበሩን ሰፍረው ኢትዮጵያን ለዚህ ትውልድ አስረክበው ሄዱ፡፡ ይህ ተረካቢ ትውልድ የተረከበውን መሬት ሳይቀነስ ለቀጣዩ ትውልድ ያስተላልፋል ይሆን—-” ከያዕቆብ ኃይለማሪያም/20 July 2008/።
ይህ ትውልድ ከአባቶቹ የወረሰውን አደራ ጠብቆ የሀገሩን ሉአላዊነት ሳይሸራረፍ በማስከበር ለመጭው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ ያለበት መሆኑን ለአፍታ መዘንጋት የለበትም ። ህወሃት/ኢህአዴግ ከኢትዮጵያ ህዝብ እውቅና ውጭ በሚስጥር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት ዳር ድንበራችንን ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የተደረገውን የውል ስምምነት የፖለቲካ ልዩነት፣ ብሄር፣ ሃይማኖት፣አመለካከት ሳይለያየን የፖለቲካፓርቲዎች ፣ ድርጅቶች፣ ሲቪክስማህበራትና ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በጋራ ተንቀሳቅሰን አሁኑኑ ማስቆም ካልቻልን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት ከማስደፈርም አልፎ እስከ ወዳኛው ትውልድ ድረስ ብጥብጥና ትርምስን የሚያወርስ ስውር ደባ ነው።
በመሆኑም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና ሉአላዊነት በመጋፋት ለም መሬታችንን ለሱዳን አሳልፎ የሚሰጠውን ስምምነት አገር ወዳድ የሆንን ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በጋራ በመንቀሳቀስ በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም! በሚል መርህ ተግባብተን ይህንን እኩይ ተግባር ለማስቆም ግዜ ሳንወስድ በያለንበት ፈጥነን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ ሀገር አሳልፎ የመስጠት ታሪክ አልወረስንም!
Saturday, January 18, 2014
ለሕዝብ ግልፅ ያልሆነው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ
በቅርቡ ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ የተለያዩ ኀሳቦች እየተነሱ ነው። በተለይ ከሰሞኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ካርቱምን ከጎበኙ በኋላ ከሌሎች ጉዳዮች በበለጠ የድንበሩ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል።የካርቱም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃንም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው የድንበር ማካለል አለመግባባት (Demarcation disputes) በቅርቡ መፍትሄ እንደሚያገኝ ዘግበዋል። የሱዳኑ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዓሊ ከርቲ ሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል ችግራቸውን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልፀዋል። ሱዳኖቹ “ፍሻጋ” በማለት በሚጠሩት አካባቢ ያለው የድንበር ችግር ይፈታል ብለው እንደሚያስቡ እየገለፁ ነው። በሌላ ወገን aበርካታ ኢትዮጵያውያን መሬት ከኢትዮጵያ ተቆርጦ ለሱዳን ሊሰጥ ነው በሚል ቅሬታ እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ እስካሁን የሰጠው መረጃ የለም። በቅርቡ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ሁለቱም አገሮች ሰላማዊ የድንበር ቀጠና እንዲኖራቸው እየሰሩ ነው ከማለታቸው ባለፈ፤ በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ አልሰጡም። በቀጣይም በሀገር ውስጥና በውጪ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እውነታውን ይገልፃሉ ተብሎም ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይሄው ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት በመሳቡ በፓርላማው ቀርበው ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሁለቱ ሀገሮች ድንበር ችግር ያለበት መሆኑን በመጥቀስ የማካለል ስራው እንደሚከናወን መግለፃቸው አይዘነጋም። ይኼው የድንበር ማካለል ከጥቂት ወራት በኋላ ሊከናወን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ነገር ግን የማካለል ሂደቱ በምን መልኩ እንደሚፈፀም የታወቀ ነገር የለም።
በሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ግን የድንበር ማካለሉ ሂደት ግልፅነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ በመንግስት ላይ ጥያቄ አንስተዋል። ኢዴፓ፣ መኢአድ፣ አረናም ሆነ አንድነት ቅሬታቸውን ገልፀዋል።
የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አብርሃ ደስታ ጉዳዩን በተመለከተ ፓርቲው እንደ ፓርቲ መረጃ እንደሌለው ገልፀዋል። ነገር ግን በግል በሁመራ ከሚገኙ ነዋሪዎች መረጃውን ለማጣራት ጥረት ማድረጋቸውን ገልፀዋል። በሁመራ የሚኖሩ አንዳንድ ግለሰብ ነዋሪዎች “መሬቱ ለሱዳን ይሰጣል” ተብሎ እየተወራ መሆኑን ደርሰንበታል ብለዋል። በተጨማሪም የአካባቢው ባለስልጣናትን ስለጉዳዩ ለመጠየቅ ሙከራ ማድረጋቸውንም የሚገልፁት አቶ አብርሃ ባለስልጣናቱም “የምናውቀው ነገር የለም” እንዷላቸውም ነው የገለፁት።

ፓርቲው ጉዳዩ የሀገር ጉዳይ እንደመሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶት እያጣራ መሆኑን የገለፁት አቶ አብርሃ፤ ከስርዓቱ ባህሪ በመነሳት በድንበር ማካለሉ ላይ እምነት መያዙ አስቸጋሪ ነው ይላሉ። “ሥርዓቱ ለስልጣን ብሎ እንጂ የሀገር ድንበር ለመጠበቅ አይደለም። ከዚህ ጉዳይ ተነስቶ የኤርትራን ጉዳይ እንዳለ ሆኖ የሱዳንም ጉዳይ ሊያጠራጥር ይችላል። ምክንያቱም ሥርዓቱ ለኢትዮጵያ ያለው ተአማኒነት ላይ ጥርጣሬ አለን። ሥርዓቱ ዳርድንበር ከመጠበቅ ባለፈ፤ የውጪ ኃይሎችም ጋር ቢሆን በስልጣን የሚቆይበትን መንገድ ሊያፈላልግ ይችላል” በማለት ጥርጣሬአቸውን ገልፀዋል።
የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ በመደገፉ በምትኩ ከኢትዮጵያ መሬት ተቆርሶ ተሰጥቶት ሊሆን ይችላል የሚለውን ጥርጣሬም በተመለከተ አቶ አብርሃ ሲመልሱ፤ “የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩ ነው። ነገር ግን የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ ቢደግፈውም፣ ባይደግፈውም የእኛ ግድብ ነው። የሱዳን መንግስት የአባይን ግድብ መደገፉ ጥሩና የምንፈልገው ቢሆንም፤ ስለደገፈ ተብሎ የሚሰጥ መሬት ሊኖር አይገባም። ከአባት፣ አያቶቻችን የተረከብነው መሬት ለሌላ አካል ሊሰጥ አይገባም። ድርጊቱ ተፈፅሞ ከሆነ እንታገለዋለን” ሲሉ መልሰዋል።
“መንግስት በጉዳዩ ላይ ግልፅ መሆን አለበት” የሚሉት አቶ አብርሃ፤ በጉዳዩ ላይ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ግልፅ መደረግ አለበት ብለዋል። ድንበሩ ሲካለልም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፍ አለባቸው ብለዋል።
“የድንበር ጉዳይ የአንድ ፓርቲ ጉዳይ አይደለም። ኢህአዴግ በመንግስትነቱ ሳይሆን በፓርቲነቱ ስለሚሰራ ጥርጣሬ አለን” የሚሉት አቶ አብርሃ ስለሆነም ለጉዳዩ ማረጋገጫ የሚሆን ግልፅ መረጃ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ቀጠናው የተረጋጋ ባለመሆኑ የድንበር መካለል እንደሌለበት የጠቀሱት አቶ አብርሃ የድንበር ማካለሉ ሂደት ተጀምሮም ከሆነ መቆም አለበት ብለዋል። በደቡብ ሱዳንና በሰሜን ሱዳን አንዳንድ አካባቢዎች መረጋጋት በሌለበት በድብብቆሽ ወደ ድንበር መካከል መገባት የለበትም ሲሉም አሳስበዋል።
የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ጫኔ ታደሰም እንደ አቶ አብርሃ በጉዳዩ ላይ ከመንግስት ግልፅ የሆነ መረጃ ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀው፤ ነገር ግን መንግስት በውጪ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ዙሪያ ላይ ጠንከር ያለና ኢትዮጵያውያንን ለሚጠቅም ተግባር ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የድንበር ጉዳይ የሕዝብ ጉዳይ እንደመሆኑ ግልፅ አሰራርን መከተል አለበት ብለዋል። ከመንግስት ባለፈ ሚዲያውም ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።
አቶ ጫኔ በመንግስት በኩል የሀገር ድንበርን በተመለከተ የመድበስበስ አካሄድ መኖር የራሱ አደጋ እንዳለው ይገልፃሉ። ፓርቲያቸውም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊና እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ የሚያሳስበው እንደሆነና በጉዳዩም ላይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት እየጣረ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ ፓርቲም በአካባቢው ከሚገኙ አባሎቹም መረጃ የማሰባሰብ ስራም እያከናወነ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ኢዴፓ ከኢህአዴግ ጋር የውጪ ግንኙነት ፖሊሲ ልዩነት እንዳለውም ጠቅሰዋል። ከድንበር ማካለል ጋር በተያያዘም ያሉ ችግሮች የኢህአዴግ የውጪ ፖሊሲ ችግሮች የሚመነጭ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም በመንግስት በኩል የኢትዮ ሱዳንን ድንበር ማካለል ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሚጎዳ መልኩ የሚፈፀም ከሆነ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን ቆመን የማጋለጥና የመቃወም ስራ እንሰራለን ብለዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ስለሺ ፈይሳ በበኩላቸው ፓርቲያቸው በጉዳዩ ላይ አቋም መወሰዱን ይናገራሉ። ፓርቲው የወሰደው አቋም፤ ጉዳዩን የማጋለጥና ሕዝቡ እንዲያውቀው የማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
“የኢትዮጵያ መንግስት ከሕዝቡ ጀርባ ሆኖ ድንበር የማካለል ስራ እየተሰራ በመሆኑ እንቃወመዋለን። ጉዳዩን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚያውቀው አይመስለንም። ምን ያህል መሬት ለሱዳን ይሰጣል? ለምንስ ይሰጣል? ታሪካዊ ባለቤትነቱ የማነው? የሚለው መታየት አለበት የሚሉት አቶ ስለሺ፤ ድንበሩን በድብብቆሽ የማካለሉ ተግባር ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ፓርቲው ከልዩ ልዩ ምሁራንና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሰዎች እንደተረዳው የኢትዮ ሱዳን የድንበር ማካለል ባለፉት ሰርዓቶች ቢነሳም ጉዳዩ ሳያስተናግዱት መቆየታቸውን አስታውሰው ኢህአዴግ ግን መነሻው ግልፅ ባልሆነ መንገድ የድንበር ማካለል ጥያቄውን አሁን ማንሳቱን ጠቅሰዋል። ያም ሆኖ ኢህአዴግ በሱዳን ድንበር አሸባሪ የሚላቸው ወገኖች ተደራጅተው እንዳይመጡበት ገዢ መሬት ለማሳጣት ድንበሩን ለድርድር አቅርቦ እንደሚሆንም እንገምታለን ብለዋል።
ፓርቲውም ይሄንኑ ጉዳይ እንደ አጀንዳ በመያዝ የፓናል ውይይት በማዘጋጀት ከፓናል ውይይቱ በሚነሳው ኀሳብ ደግሞ ሕዝቡ አቋም እንዲይዝና እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ወደ አካባቢው በማቅናት በጎንደር ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።
“በአሁኑ ወቅት መሬቱ በእርግጥም ለሱዳን አልተሰጠም” ያሉት አቶ ስለሺ፤ ሆኖም ግን በድንበር ማካለሉ ላይ ድርድር ተካሂዶ በወረቀት ደረጃ ሁለቱ አገሮች መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መንግስትም በኀሳብ ደረጃ ተስማምቶ በመጪው መጋቢት የመሬት ርክክብ እንደሚፈፀም የሱዳን የመገናኛ ብዙሃንና ሌሎች ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች እየዘገቡት እንደሆነም ተናግረዋል።
“ጉዳዩን እየደበቀው ያለው ኢህአዴግ ብቻ ነው” የሚሉት አቶ ስለሺ፤ “ነገሩ ግመል ሰርቆ አጎንብሶ ነው” ብለውታል። የድንበር ማካለል ጉዳይ የሉአላዊነት በመሆኑ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ ሊፈፀም አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል። ኢህአዴግ ለሀገሪቱ ታሪካዊ ሉአላዊነት ደንታቢስ በመሆኑም የድንበር ማካለሉን ለስልጣኑ ብሎ ከመፈፀም ወደኋላ አይልም ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ፓርቲያቸው ሕዝቡ ጉዳዩን እንዲያውቀው ከማድረግ ባለፈ ኢህአዴግ በድርድር የተስማማባቸው ስምምነቶች በመጪው ትውልድ ተቀባይነት እንዳይኖረው ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራ ነው ጨምረው የገለፁት።
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪም እንደሌሎቹ የፓርቲ አመራሮች ጉዳይ የሚያሳስበው መሆኑን በመግለፅ ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩን ተናግረዋል። አጣሪ ቡድኑ በሚያመጣው መረጃ ላይ መግለጫ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ይሁን እንጂ መኢአድ እንደ ፓርቲ ድንበሩ በቅድመ አያቶቻችን አባቶቻችን የተካለለ በመሆኑ እንደገና መከለል የለበትም የሚል አቋም እንዳለው ገልፀዋል። የፓርቲው አቋም የአከላለል ሂደቱ ግልፅ ይሁን አይሁን ከማለት ባለፈ ድንበሩ እንደገና መከለል አይገባውም የሚል እንደሆነ ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ድንበር ማካለል ቀደም ሲል በነበሩ ስርዓቶች ሳይነሳ አሁን የተነሳበት ምክንያት የአማራውን ብሔር በመልከአምድር እና በቁጥር ለማሳነስ የሚደረግ ሴራ ነው የሚሉት አቶ አበባው፤ ፍትህና ዴሞክራሲ እንዲሁም በሕዝብ እኩልነት የሚያምን ሁሉ ሊቃወመው ይገባል ብለዋል።
በመንግስት በኩል የድንበር ማካለሉን ሂደት ለሕዝብ ግልፅ ማድረግ በተለይ ጎንደር አካባቢ ሱዳኖች ይገባናል ስለሚሉት መሬት ግልፅ አቋም መያዝ አለበት የሚሉት አቶ አበባው፤ “ሕዝቡ ድምፁ ሊሰማና የታሪክ አዋቂዎችና አባቶች በጉዳዩ ሊጠየቁ ይገባል። ሽፍንፍን ባለ ሁኔታ ድንበር ማካለል ተገቢ አይደለም። ይህ አካሄድ ለሱዳንም ሆነ ለኢህአዴግ አይጠቅምም” ሲሉ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን አድርጎ እና እያደረገ ከሆነም እንደገና ነገሩን እንዲያጤነው” ሲሉ አሳስበዋል።
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው በበኩላቸው የፓርቲው አዲሱ የስራ አስፈፃሚ እየተወያየባቸው ካሉ ሦስት አስቸኳይ ዋና ርዕሰ ጉዳዮች የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማከለል ጉዳይ አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።
ኢህአዴግ በሉአላዊ ግዛት ማስከበር ጉዳይ የላላ አመለካከት ያለው በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅማችንን ሊጐዳ የሚችል እርምጃ ሲወስድ በመቆየቱ አሁንም በዚህ ተግባሩ ሊቀጥል እንደሚችል የጠቀሱት አቶ ሀብታሙ ከዚህ በፊትም የሀገሪቱን ታሪካዊ ባለቤትነት በጣሰ መንገድ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ መደረጓን አቶ ሀብታሙ አስታውሰዋል። አሁንም የኢትዮ-ሱዳን ድንበር የኢትዮጵያን ጥቅም ባላስጠበቀ መንገድ ሊፈፀም ስለሚችል ከፍተኛ ሰጋት አድሮብናል ብለዋል።
“በሱዳን በኩል እየተጠየቀ ያለው መሬት የኢትዮጵያ ነው” የሚሉት አቶ ሀብታሙ፤ ይሄንን ሉአላዊ ግዛት ለሱዳን መስጠት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ግዛት ላይ እንደገና ከተደራደረበት ከሕዝብ ጋር በመሆን የምንታገለው ነው ብለዋል።
እስካሁን በመንግስት በኩል ግልፅ መረጃ እንዲሰጥ ፓርቲያቸው ደጋግሞ እያሳሰበ መሆኑን የጠቀሱት ህዝብ ግንኙነቱ የድርድሩ ውጤት ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ለህዝቡ ግልፅ መደረግ እንዳለበትም አሳስበዋል።
“ከዚህ በፊት ከ60ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የረገፉበት የባድመ ጉዳይ መፍትሄ አላገኘም። የአሰብ ወደብን በተመለከተም ኢህአዴግ ቸልተኛ አቋም በመከተሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ጎድቷል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ አሁንም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ማካለል በተመለከተ ኢህአዴግን እንድንጠራጠረው አድርጎናል ብለዋል።
ኢህአዴግ በተፈጥሮአዊ ባህሪውን እና ከቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚመነጭ አስተሳሰብ መረዳት እንደሚቻለው ግንባሩ በሉአላዊነት ላይ የተዛባ አቋም ያለው በመሆኑ አሁንም የሀገሪቱን ሉአላዊነት በመጠበቅ ላይ ስጋት አለን ሲሉ አቶ ሀብታሙ ገልፀዋል።
“ሀገር ማለት ሕዝብ ነው ነው ብለው ለኢትዮ-ኤርትራ ድንበር 60 ሺህ ሰው አስጨርሰዋል” የሚሉት አቶ ሀብታሙ ከሱዳን ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ ለማድረግና የአባይን ግድብ መደገፉን ተከትሎ መሬት ቆርጦ ለመስጠት ከታሰበ ተገቢም፣ ትክክል አይደለም ብለዋል። ድንበር እየሰጡ ግድብ መገደብ ሰጥቶ መቀበል አይደለም በማለት ተቃውመውታል። ግድብ መገደብ የሀገሪቱ መብት እንደሆነም መታወቅ አለበት ሲሉ አጠቃለዋል።
በዚሁ አወዛጋቢ ጉዳይ ላይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ለማነጋገር ጥረት አድርገናል። ነገር ግን ከጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ኦፊሴላዊ ጉብኝት ጋር በተያያዘ ስራ ስለበዛባቸው ልናገኛቸው አልቻልንም። በተመሳሳይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች በኩልም መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል። በመስሪያ ቤቱ አሰራር በቃል አቀባዩ በኩል መረጃ ስለሚሰጥ ሊሳካልን አልቻለም።
በተጨማሪም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሽመልስ ከማልን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ቴሌፎናቸው ስለማይሰራ ልናገኛቸው አልቻልንም። በጠቅላይ ሚኒስትር የሕዝብ ግንኙነት አማካሪ አቶ ደስታ ተስፋውን አነጋግረን አቶ ሽመልስን ወይም አምባሳደር ዲናን ብቻ ማነጋገር እንደምንችል ገልፀውልናል። በቀጣይ ሳምንት የመንግሥትን ምላሽ ይዘን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።

Subscribe to:
Posts (Atom)