Tuesday, December 17, 2013

“ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፤ ኢህአዴግ ለዘለዓለም መግዛት አለብኝ የሚል ድርጅት ነው” ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ


ወ/ሮ አረጋሽ አዳነ ከህወሓት ጋር 17 ዓመታት በትግል ያሣለፉ እና ከፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ በ1993 ዓ.ም ከፓርቲው ከተሰናበቱ አባላት አንደ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት የ“አረና” ፓርቲ አባል የሆኑት ወ/ሮ አረጋሽ በአጠቃላይ ጉዳዮች ዙሪያ ከ“ሎሚ” አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ጋር ያደረጉት ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

ሎሚ፡- የኢህአዴግ ጭቆናና፣ አፈና፣ የተንሰራፈው በመላው ሀገሪቱ ነው የሚል አቋም ካላችሁ፣ ብሔር ተኮር ፓርቲ የመሰረታችሁበት ምክንያት ምንድነው;
አረጋሽ፡- ፓርቲ የሚመሰረተው በአካባቢ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት አድርጐ ነው፡፡ ተጨባጭ ሁኔታ ስል የማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ሰብዓዊ መብት፣ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመጥቀስ ፈልጌ ነው፡፡ ማንኛውም ድርጅት በዚህ መልኩ ነው የሚመሰረተው፡፡ አረናም በዚሁ መሠረት የተመሠረተ ፓርቲ ነው፡፡
ከሕወሐት ክፍፍል በኋላ አረና ሲደራጅ፣ ለአገራችን የታገልንለት ዓላማ ሙሉ በሙሉ ስላልተሣካ፣ ያልተሣካው እንዲስተካከል አለያም የተሻለ ለማድረግ የራሣችንን ጫና ማሣደር አለብን ብለን ነው አቋም የያዝነው፡፡ ስንደራጅ ሀገራዊ ፓርቲ የመመስረት ዓላማም ፍላጐትም ነበረን፡፡ ነገር ግን በነበርንበት ሁኔታ አገራዊ ድርጅት መመስረት ቀላል አልነበረም፡፡ ጠንካራ ርዕዮተ ዓለም፣ በጣም ወሣኝ አባላት ያሉት አገራዊ ድርጅት መመስረት አሁንም ቢሆን አስቸጋሪ ነው፡፡ ሀገራዊ ድርጅት የመመስረት ፍላጐት ቢኖረንም የነበርንበት ተጨባጭ ሁኔታ አልፈቀደልንም፡፡ በተግባር ስንመለከተው የብሔረሰቦች መብት ሙሉ ለሙሉ ባይከበሩም፣ ሀገራዊ ፓርቲ ለመመስረት ሁኔታዎች እስኪፈቅዱልን ድረስ ብለን አረናን መሰረትን፡፡
ይህን ካደረግን በኋላ አረናን ይዘን ቁጭ አላልንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ ካልተመሠረተ የትግራይም ይሁን የሌላው ብሔር ብሔረሰቦች ችግር ይፈታል ብለን አናምንም፡፡ ሀገራዊ ፓርቲ የሚመሠረትበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን ብለን ከሌሎቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ህጋዊ እውቅና ካላቸውና በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ ፓርቲዎች ጋር በአጭር ጊዜ ውይይት ጀመርን፡፡ መድረክ በሚባለው ድርጅትም የገባነው በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
ሎሚ፡- ከክፍፍሉ በኋላ ተዘጋጅቶ የነበረው “ሕዝባዊ” የተባለ ጋዜጣ በምርጫ 97 በጋዜጣው ርዕሰ አንቀፅ ከገዢው ፓርቲ ይልቅ ቅንጅት ላይ ጠንካራ ትችት ታቀርቡ ነበር ይባላል፤ እንዲያ ተደርጎ ከሆነ ትኩረታችሁን ወደ ተቃዋሚ ፓርቲ ያነጣጠራችሁበት ምክንያቱ ምንነበር;
አረጋሽ፡- ከኢህአዴግ ይልቅ ወደ ቅንጅት ያተኮረ ነበር የሚለው አስተያየት ለኔ ትክክል አይመስለኝም፡፡ ጋዜጣውን በትክክል አንብቦ ተረድቶ የተሰጠ አስተያየት አይመስለኝም፡፡ ያኔ ኢህአዴግን ነበር የምንታገለው፡፡ ከዴሞክራሲ አንፃር፣ ከህግ ልዕልና አንፃር፣ ከመናገርና መደራጀት አንፃር፣ ከፕሬስ ነፃነት አንፃር… እነዚህን እና ሌሎች ተጨባጭ ሁኔታዎችን መነሻ እያደረግን በጋዜጣችን ጠንከር ጠንከር ያሉ አስተያየቶችን እንሰጥ ነበር፡፡ የ97 እንቅስቃሴ ሲመጣም ኢህአዴግ “ዴሞክራሲያዊ፣ ግልፅ እና ነፃ ምርጫ ይመጣል” ብሎ ከጀመረ በኋላ ኃይሉ ሲዛባበት፣ ስልጣኑ እየተንገዳገደ መሆኑን ሲረዳ ቀድሞ የገባውን ቃል ማጠፍ ጀመረ፡፡ እንዲያውም የመሸነፍ አዝማሚያ ሲያይ ባልተጠበቀ ሁኔታ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በቴሌቪዥን በመቅረብ “ኢህአዴግ አሸንፏል” ነበር ያለው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ፀረ-ዴሞክራሲ የሆኑ አዋጆችን አውጇል፡፡
ከዚህ በመነሣት ተገቢ አለመሆኑን በሚመለከት በርካታ ነገሮች ፅፈናል፡፡ “ይሄ የዴሞክራሲውን አካሄድ ማጥበብ እንደሆነ፣ ገና ቆጠራው ሣይጠናቀቅ እኛ አሸንፈናል ብሎ መናገር ኢ-ዴሞክራሲያዊ እና አምባገነናዊነት እንደሆነ፣ ተቃዋሚዎቹም ቢሆኑ በህጉና በአግባቡ መያዝ እንዳለባቸው፣ የሕዝብ ድምፅ በአግባቡ ሊቆጠርና ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባው፣ መሸነፉን አምኖ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ መቀበል እንዳለበት በሚመለከት ደጋግመን ፅፈናል፡፡ ከዚህ አንፃር ካየነው ቅንጅትን የሚያጠቃ አቋም ነበራችሁ የሚለው አስተያየት አሳማኝ አይደለም፡፡ ቅንጅት ላይ ጫና ወይም ትኩረት ማድረግ ሳይሆን፣ ቅንጅቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የጠቆምንበት ሁኔታ ነበር፡፡
ሎሚ፡- ፓርቲያችሁ አረና በ2006 ዓ.ም. ምን ዓይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው;
አረጋሽ፡- አረና ጳጉሜ ውስጥ ሦስተኛ ጉባዔውን አካሂዷል፡፡ አንዳንድ ሕገ ደንቦቹን አስተካክሏል፤ የሚሻሻሉ ነገሮችን አሻሽሏል፡፡ አዳዲስ አመራሮችን መርጧል፤ ለምሣሌ የቀድሞው የፓርቲው ሊቀ-መንበር በአዲስ እንዲተኩ አድርገናል፡፡ ወጣቶችን ወደ አመራር አምጥተናል፡፡ ለውጥና የማሸጋሸግ ስራ ተሰርቷል፡፡ ወጣቱ ወደ ፖለቲካው መድረክ ቢመጣ የትግል ሂደቱን እየተላመደና እየተማረበት ይሔዳል በሚል ነው፡፡ እኛ የወደፊት መሪዎች አይደለንም፤ የወደፊት መሪዎቹ ወጣቶቹ ናቸው፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ የዕቅድ አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡ በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገራዊ ፓርቲ እንዲፈጠር የማድረግ ስራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል እያደረግንም ነው፡፡ በእውነቱ ይህ በእኛ ፍላጐት ብቻ የሚወሰን አይደለም፡፡ የሌሎቹም ፍላጐት ያስፈልጋል፡፡
እንዲሁም ሀገሪቱ የወጣት ምሁራን የተሻለ አመራር እንድታገኝ የማድረግ ኃላፊነት አለብን የሚሉ ግለሰቦችን የማሰባሰብ አቅም ያስፈልጋል፡፡ እኛ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠርና እንዲመቻች ካሉት ፓርቲዎች ጋር በፕሮግራሞቻችን ተስማምተን ሀገራዊ ፓርቲ እንዲመሠረት እንቅስቃሴ እያደረግን ነው፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ ንዑስ ኮሚቴ ከኛም ከሌሎችም ድርጅቶች ተውጣጥቶ እየተንቀሣቀሰ ነው፡፡ የአረና ጉባኤ አንደኛው ማጠንጠኛም ይሔ ነው፡፡ ሌላው የጉባኤው አጀንዳ ፓርቲው በተጠናከረ መልኩ ከሕዝቡ ጋር መገናኘት፣ እስከ ገጠር የዘለቀ እንቅስቃሴ ማድረግ እንዳለብን የሚያሳስብ ነው፡፡ ይሁንና እነዚህን ነገሮች እንዳናደርግ የሚያግዱን ችግሮች አሉ፡፡ አንዱ የገንዘብ አቅም ነው፡፡ ህዝቡ ከስጋትና ከፍራቻ አልወጣም፡፡ ቢሆንም ባለን አቅምና ችሎታ በትናንሽ ከተማዎች ስብሰባ በማድረግ እንቅስቃሴያችንን ጀምረናል፡፡ እንዲሁም ከመድረክ ጋር በመሆን በናዝሬት፣ ሀዋሳ፣ መቀሌ ከተማዎች ሕዝባዊ ስብሰባ ለመጥራት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡
ሎሚ- ፓርቲያችሁ ባደረገው ጉባኤ ማጠናቀቂያ ላይ ባወጣው መግለጫ “ውህድ ፓርቲ” እንደሚያስፈልግ ደጋግሞ ገልጿል፡፡ ወደዚህ አቋም የመጣችሁበትን አቋም ቢያብራሩልን;
አረጋሽ፡- ቀደም ብዬ እንደገለፅኩት ሀገራዊ ድርጅት ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በተበታተነ መንገድ በክልሎች ብቻ ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ያሉት ችግሮች ሀገራዊ መፍትሔ ካልተቀመጠላቸው በስተቀር በክልል ደረጃ ብቻ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የምንፈልገውን ለውጥ አናመጣም፡፡ ጠንካራ አመራር ያስፈልጋል፡፡ ሀገር የሚቀይር ኃይል ያስፈልጋል፡፡ ሀገር እንዲቀየር ከተፈለገ ሀገራዊ ፓርቲ መኖር አለበት፡፡ ይሕም ማለት ውህደት መፍጠር ማለቴ ነው፡፡ ውህደት ሲኖር ነው በሀገርም ሆነ በክልል ደረጃ ያለውን ችግር አብሮ መፍታት የሚቻለው፡፡ በግንባር ደረጃ ብቻ አብሮ መታገል መንግስትን ላይፈትነው ይችላል፡፡ ተገቢውን ጫና አሳድሮ መንግስት ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ እንዲያደርግ ሊያስገድደው አይችልም፡፡ ስለዚህ ሀገራዊ ፓርቲ ተፈጥሮ፣ ሀገራዊ አመራር ካልተመሠረተ ለየብቻ በሚደረግ ትግል የሚመጣ ለውጥ የትም አያደርስም በሚል ነው ለውህደት የተነሳነው፡፡
ሎሚ፡- የህወሓት መመስረቻና መቀመጫ በሆነው ትግራይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በርካታ ወጣቶች በማህበራዊ ድረ ገፆችና በሌሎች ሚዲያዎችም በገዢው ፓርቲ ላይ ተቃውሟቸውን እየገለፁ ነው፡፡ ይሔ ምንን ተከትሎ የመጣ ይመስልዎታል;… በአንፃሩ የሴቶች እንቅስቃሴ የማይንፀባረቀውስ ለምንድን ነው;
አረጋሽ፡- የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ እየሄደ ነው፡፡ መሠረታዊ መነሻውም ትግራይ ውስጥ ያለው ኢ-ፍትሃዊ ስርዓት አካሄድ ነው ብዬ ነው የማምነው፡፡ ያ ሁኔታ በወጣቱ ላይ ተንፀባርቋል፡፡ ሕዝቡ ደጋግሞ የታገለ ሕዝብ ነው፡፡ ብዙ መስዋዕትነት የከፈለ ሕዝብ ነው፡፡ መስዋዕትነት የከፈለው ደግሞ የዲሞክራሲ፣ የኑሮ፣ የኢኮኖሚ ለውጥ እንዲመጣ ነው፡፡ ሕዝቡ ከዚህ በኋላ የምንበደልበት ስርዓት አይኖርም ብሎ ነው ሦስትና አራት ልጆቹን ከአንድ ቤት ልኮ ያታገለው፡፡ ያንን እምነት ይዞ የታገለ ሕዝብ፣ መልሶ ለዚህ ዓላማ ነው የታገልኩት የሚለው ድርጅት (ህወሓት) ሲጨቁነው ምሬት ሊሰማው የማይችልበት ምክንያት የለም፡፡
አስተዳደሩ ሕዝቡን ከሌሎች ክልሎች በበለጠ ተቆጣጥሮና ወጥሮ ይዞታል፡፡ በትግራይ ውስጥ ሁሉንም ሕዝብ በወጣት፣ በሴቶች፣ በተለያዩ ማህበሮች አደራጅቶ ከህወሓት ትዕዛዝ ውጭ እንዳይመራ እየተደረገ ነው፡፡ የወገንተኝነት፣ የዝምድና ሥራ፣ የሙስናም ጉዳይ አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ችግሬ እየተሰማ አይደለም የሚል ስሜትም አለ፡፡ ይህንን መሠል እሮሮዎች እየወጡ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ የተማረው ክፍል በተወሰነ መልኩም ቢሆን የነፃነት ስሜት ስላለው ያንን ማስተጋባት ጀምሯል፡፡ ተቃውሞው ከዚህ የመነጨ ይመስለኛል፡፡ ሌላኛው የሕወሓት ሥጋት ተጨማሪ ኃይል እየፈጠረ ያለው የአረና እንቅስቃሴ ነው፡፡ የአረና እንቅስቃሴ ወጣቶችን እያደራጀ ነው፤ ወጣቶችን ወደ አመራርነት እያመጣ ነው፡፡ ዓላማውን እየገለፁ ነው፤ ትግራይ ውስጥ ያለውን ችግር አብሮ እየተወያየበትና እየመከረበት ነው፡፡ ይሔ ደግሞ የበለጠ እንዲነቃቃ አድርጐታል፡፡ በተለይ እኛ የቀድሞ የህወሓት አባላት ለሕዝብ ችግር መታገል አለብን ብለን መንቀሳቀሳችን ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባቸዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር፣ የሕዝቡ ምሬት፣ የእኛ እንቅስቃሴ ተዳምሮ ወጣቱን እንዲነሳሳ እያደረገው ነው፡፡
የሴቶች ተሳትፎን በሚመለከት… አረና ከተመሰረተ ገና አምስት ዓመቱ ነው፡፡ እንቅስቃሴያችን ደግሞ ውሱን ነበር፡፡ ሴቶችን ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ በማህበር ተደራጅተዋል፤ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሳይቀር በሊግ (በአንድ ለአምስት) ተጠርንፈዋል፡፡ ይሕም ሆኖ የአረና አባላት የሆኑ ሴቶች አሉ፡፡ በአመራር ደረጃም የተወሰኑ አሉ፡፡ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴያችን እየጠነከረ ሲሄድ ሴቶቹ የመምጣታቸው ነገር ይጨምራል የሚል እምነት አለኝ፡፡ ኢህአዴግ ዋነኛ ኃይሎቹ ሴቶች ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ በልማት፣ በማህበር አደራጅቶ እንዲንቀሣቀሱ ያደረገው ሴቶችን ነው፡፡ ይህም ጥቅም ፈጥሮለታል፡፡ እኛ ይህን አዝማሚያ መስበር አለብን፡፡ ግን በሂደት ለውጦች ተፈጥረው የሴቶች እንቅስቃሴም እየጐላ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ሎሚ፡- በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴቶች እንቅስቃሴ በማይታይበት ሁኔታ እንደ ብርቱካን ሚደቅሳና፣ ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ያሉ ሴቶች እስከ መታሰር የሚከፍሉትን መስዕዋትነት እንዴት ይመለከቱታል;
አረጋሽ፡- የእነሱ ወደ እስር ቤት መሄድ በተናጠል የሚታይ ነገር አይደለም፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ስልጣኑን በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ መንገድ መልቀቅ የማይፈልግ ድርጅት ስለሆነ፣ ለይስሙላ ዴሞክራሲ አለ፣ ነጻ ምርጫ እናደርጋለን እያለ በሚዲያ ቢያስተጋባም በተግባር ግን ዜሮ ነው፡፡ በሕዝብ ድምፅ ተሸንፎ ሥልጣኑን ለማስረከብ የተዘጋጀ ድርጅት አይደለም፡፡ ከስልጣን የመውረድ ስጋትና ፍራቻ ስላለው፣ ዴሞክራቲክ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን አይፈልግም፡፡ ኃይል ያለው ሀሳብን፣ ኃይል ያለው ፅሁፍን ይፈራል፡፡
የሕዝብ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶች… እንዲጠናከሩ፣ እንዲያብቡ ወደ መድረክ እንዲመጡ አይፈልግም፡፡ ብዙኃኑን ሕዝብ ያንቀሳቅሳሉ ያላቸውን ሰዎች በአጭር ጊዜም ይሁን በረጅም ጊዜ ለይቶ ያዳክማቸዋል፡፡ ምክንያቱም ሀሣባቸው ወይም የሚያነሱት ጥያቄ የራሣቸው “የግል” አይደለም ብሎ ስለሚያስብና ሕዝብ ጋ ከደረሰ ችግር ይፈጥራል ብሎ ስለሚሰጋ በአጭሩ የመቅጨት ስራ ይሰራል፡፡
የብርቱካንም ይሁን የርዕዮት እንዲሁም የሌሎች የፖለቲካ ታሳሪዎች ሁኔታ ከኢህአዴግ ስጋት የመነጨ ነው፡፡ ምንም ዓይነት ሀሣብ እንዲስተጋባና እንዲሰማ አይፈልግም፡፡ አዲስ ሀሣብ ሕዝቡ ጋር ደርሶ ኃይል እንዲፈጥር አይፈልግም፡፡ በሽብር እና በሌሎች ምክንያቶች በማሳበብ ሊወጡበት የማይችሉበት ቦታ ውስጥ ያስገባቸዋል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ ከማሰር ጐን ለጐን የማሳቀቅና ከመንገዳቸው የማስወጣት ሥራዎችም ይሰራል፡፡ በአጠቃላይ በብዙ መንገድ ይኮረኩማል፡፡ ኢህአዴግ ነፃና ግልፅ የሆነ ምርጫ አካሂዶ ሲሸነፍ ሊወርድ፣ ካልተሸነፈ ሊቆይ የተዘጋጀ ፓርቲ አይደለም፡፡ ለዘላለም እኔ ነኝ መግዛት ያለብኝ ብሎ የሚያምን ድርጅት ነው፡፡ ይሔንን አስተሳሰቡን የሚፃረረውን ድርጅትም ይሁን ግለሰብ ማጥፋት የለመደ ፓርቲ ስለሆነ የሚወስዳቸው እርምጃዎች ከዚህ ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
ሎሚ፡- ህወሓት “የአዲስ አበባ እና የመቀሌ” በሚል ቡድን ለሁለት መከፈሉ ይነገራል፤ የኢህአዴግ “አስኳል” ነው የሚባለው ህወሓት ውስጥ መከፋፈል መከሰቱ የሚፈጥረው አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት ይኖራል;
አረጋሽ፡- በህወሓት ውስጥ ክፍፍል አለ፤ ለሁለት ተከፍሏል የሚባለውን ነገር ላውቀው አልቻልኩም፡፡ ክፍፍል አለ ብዬ ለመውሰድ ትክክለኛ መረጃ የለኝም፡፡ “ተከፋፍለዋል” የሚል እምነት የለኝም፤ አንድ ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንኳን ተከፋፍለው አንድ ሆነውም ለመዝለቅ የማይችሉበት ሁኔታ ላይ ናቸው የሚለው ጥያቄ ቢነሣ ነው የሚሻለው፡፡
በአጠቃላይ ሕወሓት ከመለስ ሞት በኋላ እየተዳከመ ያለ ድርጅት ነው፡፡ ሁልጊዜም ደጋግመው “የጠ/ሚ መለስን ራዕይ እናስተገብራለን” ነው የሚሉት፡፡ ራዕይ ለተወሰነ ጊዜ ትቶላቸው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁኔታዎች ግን በየጊዜው ነው የሚቀያየሩት፡፡ ከሁኔታውና ከጊዜው ጋር የሚሄድ “ራዕይ” ካልያዙ የያዙት እምነት የሚገድላቸው ይመስለኛል፡፡ አዳዲስ ሀሣቦችን፣ አዳዲስ አቅጣጫዎችን ከነባራዊው ሁኔታ ጋር እያስተሳሰሩ መሔድ ካልቻሉ ለውጥ ሊመጣ አይችልም፡፡ ሕዝብ የሚጠይቃቸውን ጥያቄዎች ግምት ውስጥ የሚያስገባ ራዕይ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሕዝቡ ተበደልን ሲል፣ ዴሞክራሲ የለም ሲል የህግ ልዕልና የለም ሲል፣ ፍትህ የለም ሲል፣ ጉቦና ወገንተኝነት እየተስፋፋ ነው ሲል፣ መፍትሄ አምጡልን ሲል፣ “ሀገሪቱ በእድገት ላይ ነች፤ አንዳንድ ችግሮች ብቻ ነው፤ እነሱንም በሂደት እንፈታቸዋለን” የሚል ምላሽ እየሰጡ መዝለቅ አይችሉም፡፡ ተከፋፍለዋል የሚለው ግን እኔ የተከፋፈሉበትን ሁኔታ ስላላየሁ ስለሱ አስተያየት ለመስጠት ይከብደኛል፡፡
ሎሚ፡- የትግራይ ሕዝብና የህወሓት ግንኙነትስ ምን ይመስላል;
አረጋሽ፡- ህወሓት ከትግራይ ሕዝብ ጋር የተሳሰረ ታሪክ አለው፡፡ 17 ዓመት ሙሉ ሕዝቡ ታግሏል፡፡ አመራሩ ተለወጠ እንጂ አሁንም ሕዝቡ የችግሩ ገፈት ቀማሽ ነው፡፡ ያንን ሁሉ ትግል ያደረገው ደግሞ ደህና ስርዓት ይመጣል ብሎ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ በመኖር ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ የሆነ ስርአት ይመጣል ብሎ ነው መስዕዋትነት የከፈለው፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ደግሞ ህወሓት ይሔንን እንዳይቀጥል እያጠፋ፣ ኢ-ዴሞክራሲያዊ፣ ኢ-ፍትሃዊ እየሆነ፣ አፋኝ እየሆነ ነው ያለው፡፡ ከዚህ አንፃር የትግራይ ሕዝብ በህወሓት ላይ እየተማረረ ነው፡፡ መፍትሄ ስጡን እያለ ነው፡፡ ስብሰባ በተደረገ ቁጥር ችግሩን በስፋት ይገልፃል፡፡ እንዲሰሙትም እየጠየቀ ነው፡፡ ይሁንና ተደጋግሞ ጥያቄ ቢያቀርብም መፍትሄ ግን አላገኘም፡፡ በዚህ ምክንያት ቅሬታ እየተፈጠረ ነው፡፡ ጠንካራ የሆነ ድርጅት ከተፈጠረ የትግራይ ሕዝብ አብሮ ከመታገል ወደኋላ አይልም፡፡ አሁን ግን የእኛ አቅም ነው የሚወስነው፡፡ ሀገራዊ በምንለውና ይፈጠራል በምንለው ፓርቲ ዙሪያ የሚወሰን ነው፡፡ ለትግልም ሆነ ለመብቱ በሰላማዊ መንገድ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመታገል የትግራይ ሕዝብ ዝግጁ ነው፡፡ እኛ ጋ ድረሱ፤ ከተማ ብቻ ቁጭ አትበሉ እያለ ነው፡፡ አንድ ጊዜ አለን ትላላችሁ፤ ሌላ ጊዜ ትጠፋላችሁ የሚለው ጥያቄ ተደጋግሞ እየተነሳ ነው፡፡ የህወሓትና የትግራይ ሕዝብ ሁኔታም እየሻከረ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለውጥ ፈላጊ ነው፡፡
Ze-Habesha 

Monday, December 16, 2013

ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በኖርዎይ በርገን ከተማ በደመቀ ሁኔታ ተካሔደ


በበርገን ከተማ ለመጀመርያ ግዜ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  በርገን ቅርንጫፍ አስተናጋጅነት በዲሴምበር 14፥2013 የተዘጋጀው ህዝባዊ ስብሰባ በደመቀ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ100 በላይ የሚገመት ህዝብ የተገኘ ሲሆን ከተለያዩ የኖርዎይ ከተሞች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱም ላይ ተገኝተዋል፥፥
በዝግጅቱ ላይ ተጋባዥ እንግዶች የነበሩት
1ኛ. ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ አባል
2ኛ. አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር
3ኛ. ዶ/ር ሙሉአለም አዳም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ በኖርዎይ የድርጅት አባል ናቸው፥፥
የውይይት መድረኩ ከመጀመሩ በፊት በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ፥ እየተገደሉ እንዲሁም በግፍ ኢሰብአዊ ድርጊት ለተፈፀመባቸው ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት ሰብሳቢ አቶ ሹሜ ወርቁ አጭር የመክፈቻ ንግግር ካረጉ በኋዋላ ተጋባዥ እንግዶቹ በየተራ ስለሚመሩአቸው ድርጅቶችና የወቅቱን የሃገራችንን አስከፊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተና ሁሉም የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች አብረው በስምምነት የሚሰሩበትን ሁኔታ ማምጣት እንዳለብን እንዲሁም ስለ  መደራጀት አስፈላጊነት ሰፋ ያለ ማብራርያ  ሰጥተዋል፥፥
ዶ/ር ታደሰ ብሩ ስለ ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዓላማ ራእይና ግብ እንዲሁም ስለውጭ እምቢተኝነት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ከሰጡ  በኋላ ሁሉም ኢትዮያዊ ግንቦት7ትን እንዲቀላቀልና ሃገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አዘቅት ውስጥ ተባብረን እንታደጋት በማለት  ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በተለያዩ ድርጅቶች ስር ተደራጅቶና ታቅፎ መንቀሳቀሱ ያለውን ጠቀሜታና የሐይማኖትና የሲቪክ ማህበራትን ማደራጀትና ማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን አሳስበዋል፥፥ ፥፥
 አቶ ዮሃንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዎይ  ዋና ሊቀመንበር ስለ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ አመሰራረትና የደረሰበትን ደረጃ እንዲሁም ያከናወናቸውን ተግባራት በተመለከተ በሰፊው ገለጻ  ያደረጉ ሲሆን  ከህዝቡም  ለቀረበላቸው ጥያቄም  ምላሽ ሰጥተዋል፥፥
በተጨማሪም ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም በኖርዎይ የስደተኞች አኗኗር ዙሪያ ያለውን ችግር እንዲሁም ሁሉም የተቃቃሚ ድርጅቶች አንድ ላይ ሆነው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ የበርገን ቅርንጫፍ በተቋቋመ በአጭር ግዜ ውስጥ የደረሰበት ደረጃም በእጅጉ አስደሳች እንደሆነ በመግለፅ ያላቸውን አድናቆት ገልጸው ህዝቡ ለነጻነት ለሚደረገው  ትግል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል፥፥
እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ በሐና ሰመረ ሐቅ ተሰደደ በሚል ርእስ አጭር ግጥም የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በሎሚታ ገብረሚካኤል በምስል በተደገፈ በቀረበው የኢትዮጵያ የታሪክ ጉዞ ከነገስታት ስርአት እስከ ሐገራችን በወያኔ አገዛዝ ስር ወድቃ አሁን የደረሰችበትን ሁኔታ የሚያሳይ ዘገባ ለታዳሚው ቀርቧል፥፥
በመጨረሻም ለእንግዶቹ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦ ውይይት ከተደረገ በኋላ ዝግጅቱ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሐይል መዝሙርን በመዘበር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፥፥
የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዎይ  የበርገን  ቅርንጫፍ ጽ/ት

Wednesday, December 11, 2013

አንዱዓለም አራጌ ከእስር ቤት “እኔ እስሩ አልከበደኝም፤ በጣም ያሳዘነኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም” አለ


(ዘ-ሐበሻ) የ2005 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ምርጥ ተብሎ የተሰየመውና በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት የሚገኘው ወጣቱ ታጋይ አንዱዓለም አራጌ እስር ቤት ሊጠይቁት ለሄዱት የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች መልዕክት አስተላለፈ። በጣም ማዘኑንም ገለጸ። ዕድሜ ልክ እስራቱን ተቀብሎ እስር ቤት የሚገኘው አንዷለም አራጌ “ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል እስካሁን በእስር ቤት እየማቀቀ ሲሆን “በእኔ መታሰር ብዙ ልትጠቀሙበት ስትችሉ አለመጠቀማችሁ ያሳዝነኛል:: እኔ አሁን በእስር ባለሁበት ሰዓት የኢትዮጵያን ሕዝብ የነፃነት ትግሉን ወደ ፊት ለመግፋት አጋጣሚ ሊሆንላችሁ ቢችልም አልተጠቀማችሁበትም ” ሲል የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን መውቀሱን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገልጸዋል።
 
“እኔ መታሰሩና፤ በእስር ቤት እየደረሰብኝ ያለው ስቃይ አልከበደኝም። የከበደኝ ግን በኔ መታሰር ልትጠቀሙበት አለመቻላችሁ ነው። በኔ መታሰር መንግስት ብዙ ጫና ውስጥ እንዳለ ይታወቃል። በኔ መታሰር ብዙ ሥራ ልትሰሩበት፤ ትግሉን ወደፊት ልታስኬዱበት ስትሉ ይህን አላደረጋችሁም” ያለው አንዷለም አራጌ አሁንም የመንፈስ ጥንካሬው አብሮት እንዳለ በ እስር ቤት ካነጋገሩት ወገኖች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።
 
አንዷለም አራጌ የፌደራሉ ማረሚያ ቤት የሚጠይቁህን ሰዎች ስም ዝርዝር አስመዝግብ ተብሎ ተጠይቆ የነበረ ሲሆን እርሱ ግን ማንም ሰው መጥቶ ሊጠይቀኝ መብቱ ነውና ስም ዝርዝር አውጥቼ አልሰጥም ሲል ፈቃደኛ አለመሆኑን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም።

Monday, December 9, 2013

December 9, 2013
The Horn Times Newsletter
by Getahune Bekele-Qunu village, South Africa
US president Barack Obama, first lady Michelle Obama and three previous occupants of the white house will join more than 80,000 mourners at the colossal FNB stadium in Soweto-Johannesburg, to pay an impassioned and emotional tribute to the late peace icon Nelson Mandela, the man who forged a new multi-racial South Africa from the discredited remnants of the brutal apartheid rule.
Affectionately called Madiba here in Africa, the gallant freedom fighter was once labeled the instigator of disobedience and listed as terrorist
Affectionately called Madiba here in Africa, the gallant freedom fighter was once labeled the instigator of disobedience and listed as terrorist by western powers only to be showered with praises after he dismantled the white minority rule to create the new rainbow nation on the southern tip of Africa.
On Tuesday 10 December 2013, at the massive memorial service, countless A-list and marquee celebrities like Oprah Winfrey, Bono and British billionaire Richard Branson will be joined on the podium by more than 60 heads of state including Palestinian president Mahmud Abbas and Nigerian president Goodluck Jonatan. No accreditation would be needed for the public to attend the memorial.
Nonetheless, to ease congestions and overcrowding at the FNB stadium, the government of South Africa urged the public to use alternative viewpoints or simply go to the three nearby stadiums that are prepared by the city of Johannesburg to watch the historic event live on giant screens without compromising the safety of their families.
In additional news, as part of the week long serious of funeral events and global farewell, the recalled South African parliament is currently holding a special session in Cape Town to honor Madiba, the founding father of this beautiful land of contrasts. President Jacob Zuma used the somber but colorful occasion to appeal to the South African public to unite behind Madiba’s ideals of equality, freedom and justice.
Furthermore, according to the inter-ministerial task force spokesperson Collins Chabane, Mandela’s remains will lie in state for three days from Wednesday 11 December, to Friday 13 December to be viewed by the public in the amphitheater of the union buildings in Pretoria where he was sworn in as president in 1994.
“As we speak, President Mandela’s body is being prepared by the military health service of the SA National Defense Force to lie in state.” Chabane said.
“There would also be a public procession through the streets of Pretoria on each day that Mandela’s remains were transported between 1-military Hospital and the Union Buildings.” Chabane added inviting mourners to line up those routes and form a public guard of honor for the revered Madiba to ensure that the event is dignified and secured.
However, Chabane said he is not sure whether Mandela’s casket would be open or closed during the parade through the streets.
Next Saturday, Mandela’s remains would be transported to the Eastern Cape village of Qunu, his boyhood village, the final resting place of the great son of Africa.
We will post more stories about the pristine hilltop rural village of Qunu, as we prepare to say goodbye to Madiba.

የአና ጐሜዝና የኢህአዴግን “ፍቅር” እንመነው እንዴ?

  •   December, 09/2013
  •  
“ወሬኛም ያውራ ሃሜት ይደርድር እኛስ ሆነናል ፍቅር በፍቅር ሊያፈርስ አስቦ የሸረበውን ተክቦ ሆኗል የሚያገኘው…”
ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!
ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡ 
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!) 
ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡ 
እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡   እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)  
እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ  በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!) 
እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም – “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…) 
እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!) እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡ 
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ – ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ – “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡ 
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡ 
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም  የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!)  በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡ ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው! ኤልያስ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡ 
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!) ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡ እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡   እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)  እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ  በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!) 
እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም – “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…) 
እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!) እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡ 
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ – ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ – “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡ 
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡ 
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም  የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!)  በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡
ተቃውሞን የሚፈራ “ሰነፍ” መንግስት ብቻ ነው!
ኤልያስ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ለንባብ የበቃው The Reporter የእንግሊዝኛ ጋዜጣ፣ በፊት ለፊት ገፁ ላይ “GOMEZ In the House” ከሚል ርዕስ ሥር ያወጣው ምስል “Best picture of the year” ለመባል የሚበቃ ነው፡፡ ታሪካዊ ፎቶግራፍ እኮ ነው-ታሪክ የሚናገር! እኔማ ብዙ ነገሮችን በውስጤ አመላላስኩ፡፡ አሁን ማን ይሙት … የፓርላማ አፈጉባኤው የተከበሩ አባ ዱላ እና አና ጐሜዝ እንዲህ “ፍቅር በፍቅር” ይሆናሉ ብሎ የገመተ ነበር? የፕላኔታችን ምርጥ “አዋቂ” (ተንባይ) እንኳን ሊተነብየው የማይችለው እንግዳ ክስተት እኮ ነው፡፡ ሁለት ፈጽሞ ሊቀራረቡ ቀርቶ አንዳቸው የሌላቸውን ስም እንኳን የማያነሱ የሚመስሉን ሰዎች ድንገት እየተሳሳቁ ተጨባብጠው “ፍቅራችን ደራ!” በሚል ስሜት ሲያጓጉን ማየት ያስደነግጣልም፤ ያስገርማልም፡፡ እኔማ የሁለቱን ሰዎች ምስልና ነገረ ስራቸውን ስንት ጊዜ ትክ ብዬ እንዳስተዋልኩት አልነገራችሁም፡፡ እኔን እንዲህ ካስገረመኝ ተቃዋሚዎችን ደሞ ምን ያህል እንደሚያስገርም አስቡት! (ጐሜዝ በ9 ዓመታቸው ማሊያ ቀይረው ከች አሉ እንዴ ያስብላል!) እናላችሁ … ፎቶውን አይቼ አይቼ መጨረሻ ላይ ዓይኔን ማመን ስላቃተኝ “ከምራችሁ ነው?” አልኳቸው ድምጽ አውጥቼ፤ ምስሉ ላይ እንዳፈጠጥኩኝ፡፡ 
እንዴ … የ97 ምርጫ ጊዜ አና ጐሜዝ በኢህደዴግ ላይ የሰነዘረችው ትችትና ነቀፌታ “ዓይንሽ ላፈር” የሚያስብል ነበር እኮ! እናም ኢህአዴግ “ዓይንሽ ላፈር” ብሏት ነበር፡፡ (በዓይኑ መጣቻ!) ጊዜ ደጉ ግን ሁሉንም ገለባበጠው፡፡ በነገራችሁ ላይ በጐሜዝና በአፈጉባኤው ተቃቅፎ ፎቶ መነሳት መደንገጤ ሊገርማችሁ አይገባም፡፡ ለምን መሰላችሁ … ራሷ አና ጐሜዝም ብትሆን በአዲስ አበባ በሚካሄደው 26ኛው የአፍሪካ፣ የካሪቢያን፣ የፓስፊክ አገራትና ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ በሚያደርጉት የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ የኢትዮጵያ መንግስት “ቪዛ አይሰጠኝም” የሚል ስጋት እንደነበራት ከእንግሊዝኛው ሪፖርተር ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ ገልፃለች፡፡ 
እኔ የምለው ግን … አፈጉባኤው ከጐሜዝ ጋር ያወረዱት ሰላም በግል ነው ወይስ ፓርቲውን ወክለው? (ብዥታው ይጥራ ብዬ እኮ ነው!) በነገራችሁ ላይ እርቁና ሰላሙ ከአንገት በላይ ቢሆን እንኳን፣ ኢህአዴግ ስሙን በከባዱ ያደሰበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው፡፡   እስቲ አስቡት … በ97 ምርጫ ለተቃዋሚዎች “ተደርባ አሳቅላናለች” በሚል ኩርፊያ፣ ዛሬ በ2006 ይከናወን በነበረ ትልቅ የፓርላማ አባላት ጉባኤ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ቪዛ ቢከለክል ኖሮ እንዴት embarassing እንደሚሆን? (“ተጠቃሽ የአገር ገፅ ግንባታ” ብየዋለሁ!) እንዲያም ሆኖ ግን “ቂመኛ ነው” የሚባለው አውራው ፓርቲ፤ እንዴት ለአና ጐሜዝ “አንጀተ ቀጭን” (ርህሩህ ለማለት ነው!) ሆነላት? የሚለው ጥያቄ አሁንም ከልቤ አልወጣም። (ሴቲቱ ቆቅ ሳትሆን አትቀርም!) ይገርማል እኮ! እዚህ ኢህአዴግና ተቃዋሚዎች ከ97ቱ የፖለቲካ ውጥንቅጥ በኋላ እርቅ ሳያወርዱ እንደተፋጠጡ አሉት፡፡ (አሁንም ድመትና አይጥ ናቸው እኮ!)  እኔ የምለው … ፎቶውን ትክ ብላችሁ ስታዩት ግን “ፍቅራቸው” ወይም የወረደው ሰላም የምር ይመስላል እንዴ? (የጐሜዝና የአፈጉባኤውን ማለቴ ነው!) እኔማ “እንዳንቺ አይደለንም!”፣ “ይብላኝ ላንቺ”፣ “ነገሩ ነው እንጂ ጩቤ ሰው አይጐዳም” የሚል መልዕክት ኢህአዴግን ከወከሉት ሰውዬ ሳቅ ውስጥ የማነብ እየመሰለኝ ተቸግሬ ሰነበትኩላችሁ  በነገራችሁ ላይ … የሁለቱን የፓርላማ ሰዎች የሳቅ ትርጉም በትክክል የገመተ ይሸለማል (በአውሮፓ ህብረት ስፖንሰር አድራጊነት!) እናላችሁ … አና ጐሜዝ ከጉባኤው በኋላ በቤተመንግስት እራት ከመጋበዟም ባሻገር ከኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ መብት አያያዝ፣ በታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዙሪያ መወያየቷን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገልፃለች። እንደውም የኢህአዴግ ባለስልጣናት ሃሳቧን ለመስማት ፈቃደኛ መሆናቸው ራሱ አስደንቋታል (“ምን ደግሰውልኝ ይሆን?” አለማለቷ ይገርማል!) እንዲህ ብላ ብቻ ግን አታበቃም – “ቅመሟ ጐሜዝ”! ከ97 ምርጫ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና ዲሞክራሲው እየቀጨጨ መጥቷል ብላለች-በይፋ። በመጨረሻም በሽብርተኝነት ተፈርዶባቸው የታሰሩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞችም መፈታት አለባቸው ያለችው ጐሜዝ፤ “የፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ዲሞክራሲን ለማቀጨጭ እየዋለ ነው” በማለት በድፍረት ተናግራ ወደ አገሯ ተፈተለከች፡፡ (እኛም እኮ ሌላ አገር ቢኖረን…) እኔ የምላችሁ … የመስቀል በዓል በዩኔስኮ ስሙ መስፈሩን ሰማችሁ አይደል? የኢቴቪ “አለርጂክ” አለብን የምትሉ የዲሽ ወዳጆችም ብትሆኑ፣ ከሌሎች ሚዲያዎች ሳትሰሙት እንደማትቀሩ እገምታለሁ፡፡ “የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ” በሚል ዘርፍ ነው “መስቀል” የተመዘገበው ተብሏል፡፡ (ኩራት ቢጤ ተሰማኝ!) እንደሰማነው ከሆነ ታዲያ … መስቀል በቅርስነት መስፈሩ ወደ አገራችን የሚመጡ ቱሪስቶችንና ተመራማሪዎችን ቁጥር ያበራክታል ተብሏል፡፡ (ይሄማ ምን ያጠራጥራል!) የእኔ ጥርጣሬ ምን መሰላችሁ? እንግዶቹ የጠበቁትን መስተንግዶና አገልግሎት አግኝተው፣ ሳይቀየሙን፣ በሰላም ወደ አገራቸው ይሸኛሉ ወይ የሚለው ነው፡፡ ከምሬ ነው … ያማሩ የሆቴል ህንፃዎች እኮ መስተንግዶ አይሆኑም! (ብቁ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ ለማለት ነው!) ለመግባባት በቂ የቋንቋ ችሎታ ያላቸው፣ ከሆስፒታሊቲ ኢንደስትሪው ጋር በቅጡ የተዋወቁ የሆቴል ባለሙያዎች፣ አስጐብኚ ድርጅቶች ወዘተ … የግድ ነው፡፡ ያለዚያ የአገር ገፅ ግንባታው የአገር ገፅ እንዳያፈርስ ያሰጋል፡፡ (“አፍሶ መልቀም” አሉ!) የኢቴቪ ጋዜጠኞችም የመጣው ቱሪስት ሁሉ “Ethiopia is an amazing country; its people, its culture …፣” ወዘተ እንዲል መጠበቅ የለባቸውም፡፡ የቱሪስቶች ቁጥር የማይጨምረው ምናልባት የኢቴቪ ኢንተርቪው እያጨናነቃቸው ቢሆንስ? (ገራገር ግምት ናት!) እናላችሁ … በዩኔስኮ መዝገብ ላይ ስለሰፈረው የመስቀል በዓላችን እያብሰላሰልኩ ሳለ ድንገተኛ ሃሳብ ከአዕምሮዬ ተገፍትሮ ሲወጣ ተሰማኝ፡፡ ወዲያው ጅራቱን አንቄ ያዝኩት፡፡ ሃሳቡ እንግዳ ቢመስልም ክፋት ግን የለውም፡፡ ምን መሰላችሁ? ዲሞክራሲ ባህላችንን ለምን “ከማይዳሰስ ዘመናዊ” ቅርስነት” በዩኔስኮ አናስመዘገበው? … የሚል ነው፡፡ 
(“አና ጐሜዝ ዲሞክራሲያችሁ ቀጭጯል” የምትለውን መርሳት ነው!) በዚያ ላይ “democracy is a process” (በኢህአዴግ ቋንቋ “እየወደቅን እየተነሳን ነው”) የሚል አባባል አለ አይደል? እናላችሁ … አል ስሚዝ የተባሉ አሜሪካዊ ፖለቲከኛ ምን ይላሉ መሰላችሁ – ስለ ዲሞክራሲ፡፡ “የዲሞክራሲ ህፀፆች የሚታከሙት በበለጠ ዲሞክራሲ ነው” (የ“ተማረ ይግደለኝ” ሳይሆን “በደንብ ያስተምረኝ” አልኩኛ!) ለእኛ አገር ቀረብ የሚል የመሰለኝን ደግሞ እነሆ – “ልማት ዲሞክራሲን ይፈልጋል፤ እውነተኛው የህዝብ ማሳተፍያ!” ይህን የተናገሩት ደግሞ የበርማ የፖለቲካ መሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ናቸው፡፡ 
እናንተ … ለካስ ኢህአዴግ “ዲሞክራሲ ለእኛ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው” የሚለው ወዶ አይደለም፡፡ (ዲሞክራሲ በአንድ ጀንበር ተቦክቶ የሚጋገር ሳይሆን ሂደት መሆኑን ግን አትርሱ!) እኔ የምላችሁ … ግን ተቃውሞን አምርረው የሚጠሉ፣ ተቃዋሚዎችን እንዴት ብለን አይተን የሚሉ መንግስታትና ገዢ ፓርቲዎች እጅግ “ሰነፎች” አይመስሏችሁም?” “የለም፤ አምባገነኖች ናቸው እንጂ!” ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ እኔ ግን ምን እላለሁ መሰላችሁ? የሚቀድመው ስንፍናቸው ነው! ከዚያ ነው አምባገነንነታቸው የሚከተለው፡፡ 
የምን ስንፍና መሰላችሁ? ለህዝብ ቅሬታ በቂ ጆሮና ተገቢውን ምላሽ ያለመስጠት ስንፍና!! የህዝብን አንገብጋቢ ችግሮች በወቅቱ ያለመፍታት ስንፍና!! የስልጣን ኮርቻ ላይ ሲወጡ ለህዝብ የገቡትን ቃል ችላ የማለት ስንፍና!! የህዝብን መብትና ነፃነት በማን አለብኝነት የመደፍጠጥ ስንፍና!! ብዙ እንዲህ ያሉ … ስንፍናዎች ሲጠረቃቀሙ አምባገነንነት ይወለዳል ይላል-በልምድ ላይ የተመሰረተው ጥናቴ፡፡ በነገራችሁ ላይ … የህገመንግስት አንቀጽ ደልዞ ወይም የምርጫ ኮሮጆ ገልብጦ የስልጣን ዕድሜን ማራዘም  የ“ሰነፍ መንግስታት” መገለጫ ነው፡፡ የሥልጣን ጥመኞች እኮ “ሰነፎች” ናቸው-ከቤተመንግስት ወጥተው ተራ ህይወት መኖር ሞት የሚሆንባቸው!! (ካላመናችሁኝ ራሳቸውን ጠይቋቸው!!)  በመጨረሻ የዲሞክራሲ ዘብ ነኝ ለምትለው አና ጐሜዝና እጅ መጠምዘዝ አይቻልም ለሚሉት የፓርላማ አፈጉባኤ የንዋይ ደበበን ዘፈን ጋብዣቸው ልሰናበት፡፡ 

Thursday, December 5, 2013

‹‹መለስ ዛሬ የለም፡፡ አዲስ ጊዜ ነው፡፡ ደስ ብሎኛል፤ ቪዛዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተሰጥቶኛል፡፡››...አና ጎሜዝ

የሸፈተው የአና ጎሜዝ ልብ?!

‹‹መለስ ዛሬ የለም፡፡ አዲስ ጊዜ ነው፡፡ ደስ ብሎኛል፤ ቪዛዬም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተሰጥቶኛል፡፡››...
(… Meles has gone! This is a new timing. I am pleased I was granted visa without preconditions.)
ይህንን ያሉት በምርጫ በ1997 የአውሮፓ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ሆነው የመጡት ሚስስ አና ጎሜዝ ሰሞኑን ከአዲስ ስታንዳርድ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው፡፡
የአፍሪካ መዲና አዲስ አበባ መሰንበቻውን ካስተናግደችው ጉባኤዎች መካከል የአፍሪካ ካሪቢያን፣ የፓስፊክና አውሮፓ የጋራ የፓርላማ ስብሰባ አንዱ ነበር፡፡ ጉባኤው የመንግሥት ሚዲያ ቀልብ ይሳብ እንጂ የሕዝቡን ቀልብ የሳበው ግን ሌላ ነው፡፡ ሪፖርተርን ጨምሮ የግሉን ሚዲያና የሕዝቡን ቀልብ የሳበው የሚስስ አና ጎሜዝ ወደ አዲስ አበባ መምጣት ነው፡፡ 
ከዘጠኝ ዓመት በፊት ከመንግሥት ጋር የተወዛገቡት የአና ጎሜዝ መምጣት የበለጠ አስገራሚ ያደረገው እሳቸው በዚሁ ጉባኤ በአዲስ አበባ መገኘታቸው ብቻ አይመስልም፡፡ እሳቸው በአባልነታቸው የሚታወቁበት አውሮፓ ኅብረት ፓርላማ ለኢትዮጵያ 5.5 ቢሊዮን ብር በዕርዳታ መልክ መለገሱን ኢቲቪ ዘግቧል፡፡ በአመዛኙ የምርጫ 97ን ተከትሎ የፖለቲካ ምህዳሩ መጥበቡን ቢናገሩም፤ ከአንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ግልጽ ውይይት ማድረጋቸውና አዲስ የለውጥ ነፋስ አየሁ ማለታቸውም ሌላው አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል፡፡ 
አና ጎሜዝና ምርጫ 97
ኢትዮጵያ ከደርግ ውድቀት በኋላ ቢያንስ በመርህ ደረጃ የሕዝብ ይሁንታ የሚረጋገጥበት ሕዝባዊ ሥልጣን በምርጫ የሚያዝበት ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ታውጇል፡፡ ኢሕአዴግ አብዛኛው የፓርላማ መቀመጫውን በምርጫ ስም (ገለልተኛ ታዛቢዎች እንደሚሉት) መቆጣጠር ይዞት የመጣው ባህል፣ በሦስተኛው ዙር የ1997ቱ አገራዊ ምርጫ ተሰብሮ ነበር፡፡ በወቅቱ እንደ አሸን የፈሉ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሁለት አውራ ጥምረቶች (ኅብረትና ቅንጅት) በመፍጠር ገዥውን ፓርቲ ኢሕአዴግ በሰላማዊ መንገድ መፈታተን ችለው ነበር፡፡ ኋላ ኋላ ጉዳዩ ላይ ጥናት ያካሄዱት ምሁራን እንደሚሉት በሙያ ሥነ ምግባር ጉድለት ምክንያት፣ የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨት አደገኛነቱ የሚያመዝን ቢሆንም፣ የግል ሚዲያው በአገሪቱ ታሪክ ተጠናክሮ የመጣበት ወቅትም ነበር፡፡ መንግሥት የሰነዘራቸው ከፍተኛ ትችቶች ሳይዘነጉም የአገር በቀልና የውጭ ሲቪክ ማኅበራትም በፖለቲካው የላቀ ሚናቸውን ተጫውተዋል፡፡  
ይኸው የ97ቱ ምርጫ በአንዳንድ የኅብረተሰብ ክፍል ላይ የራሱ የሆነ የማይረሳ መጥፎ ጠባሳ ጥሎ አልፏል፡፡ በመንግሥትና በተቃዋሚዎች ግንኙነት ላይ ያስከተለው ሕመምም አሁንም ድረስ አልተፈወሰም፡፡ ምርጫውን ተከትሎ ለተፈጠረው ቀውስም፣ በዋና ተዋናዮቹ ሁለቱ ወገኖች ብቻ የተወሰነ አልነበረም፡፡ 
ኢሕአዴግ እንደሚለው፣ አንዳንድ የፖለቲካ ሰዎች የራሳቸው የፖለቲካ አጀንዳ ይዘው የተንቀሳቀሱ የ‹‹ኒዮሊበራል›› ኃይሎች በገንዘብም ሆነ በሞራል ጫና ለመፍጠር ክፍተቱን ተጠቅመው ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ይህ በማናቸውም አገሮች የሚፈጠር ቀውስ ለውጭ ኃይሎች በር መክፈቱ ግን በኢትዮጵያም በሌሎች አገሮችም እንግዳ አይደለም፡፡ በምርጫም ሽፋንም ሆነ በኃይል በመፈንቅለ መንግሥት፣ በተለይ ምዕራባውያን ኃይሎች የማይፈልጉትን አካል ለመጣልና የሚፈልጉትን ወገን ደግሞ ለማንገሥ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጣልቃ ገብነት ከማድረግ አይቦዝኑም፡፡ የሚያስከትለው ውጤት ከአገር አገር ይለይ እንጂ፣ በተለይ በድሀ አፍሪካ አገሮች የእነዚህ ኃይሎች እጅ ረዘም ያለ ነበር፡፡ ዋና አጀንዳቸው ባይሆንም ለዲሞክራሲ መስፋፋት ምንም ዓይነት ፋይዳ አይኖራቸውም ግን አይባልም፡፡ 
ከምርጫ 97 ጋር በተያያዘ ስማቸው በቀላሉ ከሕዝብ አእምሮ ከማይጠፋው ጥቂት የፖለቲካ ሰዎች እኩል የሚታየው፣ የውጭ ሰዎች ግንባር ቀደሙ ደግሞ የሚስስ አና ጎሜዝ ነው፡፡ ለዚህም ይሆናል ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተደረገው ዓለም አቀፍ ጉባኤና ከአውሮፓ ኅብረት ከፍተኛ ዕርዳታም በላይ፣ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ የሚመስለው፡፡ ወይዘሮዋ በአሁኑ ወቅት በተለይ የአዲስ አበባን ነዋሪዎች ቀልብ የሳቡት ከምርጫው ቀውስ ዘጠኝ ዓመት በኋላ ወደ ከተማይቱ ሲመጡ ለመጀመርያ ጊዜ በመሆኑ ብቻ አይመስልም፡፡ ያሳዩት የአቋም ለውጥ ጭምር እንጂ፡፡ 
የአና ጎሜዝ ልብ ዛሬ ወዴት ነው?
ከሁለት ዓመት እስር በኋላ በይቅርታ የተፈቱ የቅንጅት አመራሮች፣ የሚዲያና የሲቪክ ማኅበራት የፖለቲካ አራማጆችም፣ በምርጫው ወቅት ያሳዩትን ጉልበት ይዘው መቀጠል አልቻሉም፡፡ በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ የቆረጡት ግን የአሜሪካ መንግሥት (ቀጥሎ የመጣው የኦባማ አስተዳደር) እና የአውሮፓ ኅብረት ብቻ አልነበሩም፡፡ በምርጫ ውጤት እንደታየው፣ መራጩ ሕዝብ በተቃዋሚዎች ላይ ተስፋ መቁረጡን በግልጽ አሳይቷል፡፡ ማሳያው በ1997 ምርጫ መቶ በመቶ ቅንጅትን የመረጠው የአዲስ አበባው ሕዝብ፣ ከአንድ ወንበር በስተቀር በ2002 ዓ.ም. ኢሕአዴግን መርጧል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የፖለቲካ ቁርጠኝነት የትግል ጽናት የላቸውም ብሎ ተስፋ የቆረጠባቸው የተቃዋሚዎች አመራሮች ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰናል›› በሚል ይቅርታ መጠየቃቸው ብቻም አይመስልም፡፡ መሪዎቹ ከእስር ከወጡ በኋላ በሁለት እግሩ መቆም የሚችል ድርጅት ይዘው መቀጠል አለመቻላቸውም ጭምር ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ምትክ፣ በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት ወደተራ ድብድብ እስከመግባት የደረሱ ነበሩ፡፡ መንግሥት ይህንን ክስተት ለፕሮፖጋንዳ በስፋት ተጠቅሞት ነበር፡፡ 
በቅርቡ አዲስ አበባ የመጡት አና ጎሜዝ ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ተገናኝተው ግልጽ የሆነ ውይይት ማድረጋቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡ ከተቃዋሚዎች ጋር ምንም ንግግር አለማድረጋቸው ይነገራል፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ድንገተኛ ሕልፈት አገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር እንድታደርግ እንደ መልካም አጋጣሚ የተመለከቱት አና ጎሜዝ፣ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ መሠረታዊ የሆነ ለውጥ ለማየት የጓጉ ይመስላሉ፡፡ 
በዚሁ ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት፣ ‹‹አዲስ ነፋስ አለ›› ያሉት መንግሥት ለእሳቸው ያለምንም መንገላታትና እንቅፋት ቪዛ ስለሰጣቸው የአወንታዊው ለውጥ ምልከታቸው ቀዳሚ ነው፡፡ አሁንም ከ97 በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩን በተመለከተ ችግሮች መኖራቸው አስረግጠው የተናገሩት አና ጎሜዝ፣ በአጠቃላይ ግን አገሪቱ በተለየና አዲስ አመራር ውስጥ መሆኗን ይናገራሉ፡፡ ያዩዋቸው ለውጦች ምን ምን እንደሚያካትቱ በዝርዝር ባያስረዱም፡፡ አንድ ትልቅ ለውጥ የተመለከቱት የሶሻል ሚዲያ መስፋፋት ሲሆን፣ ያንንም ከመንግሥት ቁጥጥር በላይ በመሆኑ ነው ይላሉ፡፡ በሙሰኞች ላይ የተወሰደ ዕርምጃም አድንቀዋል፡፡ ‹‹በኢትዮጵያ ላይ እኔ ምንም የኢኮኖሚ ሆነ ምንም ግላዊ ፍላጎት የለኝም›› የሚሉት አና ጎሜዝ፣ አንዳንድ ባለሥልጣናት በግልጽ ለመነጋገር መፍቀዳቸውንም እንደ ለውጥ ሳይመለከቱት አልቀሩም፡፡ ‹‹እኔን ለመስማት መፈለጋቸው ራሱ ጥሩ ይመስለኛል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በሽብርተኝነት የታሠሩት ጋዜጠኞች እንጂ አሸባሪዎች አይደሉም›› ለሚለው ሙግታቸው ማስረጃ እንዲያቀርቡ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ጋዜጠኞች መሆናቸውን ነው የማውቀው›› ከማለት ውጪ የማቀርበው ማስረጃም የለኝም ብለዋል፡፡ 
በወቅቱ ከቅንጅት አመራሮች አንዱ የነበሩት ዶክተር ኃይሉ አርአያ፣ የአና ጎሜዝን መምጣት በበጎ ጎን አይተውታል፡፡ ‹‹መቀራረቡ በእኔ በኩል ገንቢ ነገር ነው፤››  የሚሉት ዶክተር ኃይሉ፣ ‹‹በአገሪቱ ተለውጧል ያሉትን ነገር ግን እሳቸው ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እሳቸው በወቅቱ ይዘውት ከነበረው አቋም አሁን ምንም የተለወጠ ነገር አላየሁም፡፡ አቋማቸውን የሚያስለውጥ መሠረታዊ ለውጥ አላየሁም፤›› ብለዋል፡፡ ዶክተር ኃይሉ እንደሚሉት፣ በአገሪቱ እሳቸውም የማይክዱት ልማት እየመጣ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ከዚያ ውጪ ግን በፖለቲካ መስክ ምንም የመጣ ለውጥ የለም፡፡ ቪዛ ስለተሰጣቸው ብቻ አዲስ ለውጥ አለ ማለት ግን አግባብ አይደለም፤›› ይላሉ፡፡ 
የቀድሞ አምባሳደር ተስፋዬ ሀቢሶ በበኩላቸው በ1997 ዓ.ም. በካምፓላ (ኡጋንዳ) አምባሳደር የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩን በቅርበት ይከታተሉ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ አና ጎሜዝ በወቅቱ በኢትዮጵያ ላይ የያዙት አቋም የግላቸው እንዳልነበር በአጠቃላይ የምዕራባውያን መንግሥታት አቋም እንደነበር ይናገራሉ፡፡ በተለይ ደግሞ፣ ኒዮሊበራሊዝምን አክርረው የሚቃወሙት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስን እንደ ‹‹የወገብ ቅማል›› አድርገው ነበር የሚያዩዋቸው ብለዋል፡፡ በወቅቱ ከኢትዮጵያ የተባረሩት አራት የውጭ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችም የተቃውሞ እንቅስቃሴውን በገንዘብ ሲደግፉ እንደነበር ለአብነት ይጠቅሳሉ፡፡ አና ጎሜዝ ብቻም ሳይሆኑ እነ ክርስቶፈር ክላፋም፣ ክሪስ ቦርና የኤችአር 2003 ሕግ አርቃቂ ዶናልድ ፐይን የመሳሰሉትም በተመሳሳይ ይጠቅሳሉ፡፡ እሳቸውም እንደ ዶክተር ኃይሉ ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ አቋም የሚያስለውጥ ምንም የተለወጠ ነገር የለም፤›› በሚለው ሐሳብ ይስማማሉ፡፡ 
አና ጎሜዝ ከመንግሥት ጋር መታረቅ የፈለጉበት ምክንያት ግን ‹‹ታክቲክ›› እንደሚሆን በመገመት፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ ያለው አቋም መለወጡን ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ይገምታሉ፡፡ ‹‹ከወደቀ ጋር መሆን ማን ይፈልጋል?›› በማለት፡፡ ‹‹አሁን በ60 ዲግሪ አቋማቸው ተለውጧል ያሉት አምባሳደር ተስፋዬ፣ ግለሰቦች የራሳቸው ሚና ቢኖራቸውም ያው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ የተዉት ፖሊሲና ርዕዮተ ዓለም እየተተገበረ ስለሆነ ምንም አቋም የሚያስለውጥ ነገር የለም፤›› ይላሉ፡፡ ‹‹ስህተታቸውን አምነው፣ ለውጡ ከልብ ተቀብለውት ከሆነ ግን መልካሙን እመኝላቸዋለሁ›› ብለዋል፡፡ 
በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሰላምና ልማት ተቋም ተመራማሪው አቶ አቤል አባተ በበኩላቸው፣ ‹‹የአና ጎሜዝ መለሳለስ ከአውሮፓ ውስጥ የደረሰባቸው መገለል ውጤት ነው፤›› ይላሉ፡፡ ከ1997 ምርጫ በኋላ የኢሕአዴግ መጠናከርና መንግሥት በልማት ላይ ያሳያቸው ተጨባጭ ዕድገቶች የተቺዎቹን አፍ እየዘጋለት እንደሆነ በመግለጽ፡፡ ለዚህም ከአቶ መለስ ሕልፈት በኋላ ምንም ዓይነት የፖሊሲም ሆነ የስትራቴጂ ለውጥ ባልታየበት የአና ጎሜዝ መለሳለስ ጥሩ ማሳያ ነው ብለውታል፡፡ 
‹‹ቀደም ሲል ከተቃዋሚ አመራሮች ጋር የነበራቸው መጥፎ ስም ለማደስ ፈልገው ይሆናል፡፡ ለአቋማቸው መለወጥ ዋነኛ ምክንያት ግን መገለላቸውና በአውሮፓ ኅብረት ውስጥ ምንም ዓይነት ተሰሚነትና ተአማኒነት ማጣታቸው ነው፡፡›› 
የባከኑ ስምንት ዓመታት
አና ጎሜዝ ሰሞኑን እዚሁ አዲስ አበባ እስከታዩ ድረስ፣ በተገኙ አጋጣሚዎች በሙሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሲከሱ፣ ሲወነጅሉና ሲያጣጥሉ ቆይተዋል፡፡ 
ከይቅርታ ጠያቂዎቹ መካከል ወደ አሜሪካና አውሮፓ የገቡ አንዳንድ አመራሮች ከውጭ በመሆን ከእነ ሚስስ አና ጎሜዝና ዶናልድ ፔይን (ከሦስት ዓመት በፊት ሕይወታቸው ያለፈው) ጋር በመሆን ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ መንግሥትን በኃይል ለመጣል ከዳያስፖራ ድጋፍ እያሰባሰበ የሚገኘውና በመንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው ግንቦት ሰባት ሊቀመንበሩ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ (በአገር ክህደት ክስ በሌሉበት ሞት የተፈረደባቸው) ጋር በቅርበት ሲሠሩ ከቆዩት መካከል፣ አሁን ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ‹‹ግልፅ›› ውይይት ማድረጋቸውን የሚናገሩት ሚስስ አና ጎሜዝ ናቸው፡፡ በአውሮፓ ኅብረት አስተባባሪነት ኢትዮጵያን በሚመለከቱ መድረኮች፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የተለያዩ ተቃውሞአቸውን እንዲገልጹም ከማመቻቸት ባሻገር ራሳቸው በተለያዩ ወቅቶች ኅብረቱ በኢትዮጵያ ላይ እንዲጨክን ድምፃቸውን ሲያሰሙ ኑረዋል፡፡ በኢትዮጵያ በሽብርተኝነት ክስ ተፈርዶባቸው በእስር የሚገኙት ግለሰቦች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ መንግሥት ያፀደቃቸውን ሕጎች እንዲከልስ፣ ኅብረቱ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ዕርዳታም ሆነ ብድር እንዲያቋርጥ በተለያዩ መንገዶች ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ የእሳቸው ጥረት፣ በአጠቃላይ የአውሮፓ ኅብረትና አባል አገሮች ሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት ዕውቅና እንዲነፍጉ የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚያም አልፈው ወይዘሮዋ፣ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ባለው የድንበር ግጭትም ጭምር አስተያየት የሚሰጡ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሄጉ ፍርደ ገምድል ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲያደርግ ለዚህም ኅብረቱ ጫና እንዲፈጥር ይጠይቃሉ፡፡ 
በተለይ አምና መጋቢት ወር ላይ ለኅብረቱ ባቀረቡት ስሞታ፣ የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑት ጆሴ ማኑኤል ባሮሶ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን በሚያነጋግሩዋቸው ወቅት፣ አገሪቱ ‹‹የፖለቲካ›› እስረኞቿን በአስቸኳይ እንድትፈታ የድንበር ውሳኔው በአስቸኳይ እንዲተገበርና በሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት እንድታቆም ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹በእርግጥ እሳቸው ማምጣት የሚችሉት ለውጥ እምብዛም ነው›› ያሉዋቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምንም የሥልጣን ሽግግር እንዲያደርጉ ፕሬዚዳንቱ ጫና ይፈጥሩ ዘንድ ተማጽነው ነበር፡፡ አውሮፓ ኅብረት ምርጫ 97ን ተከትሎ ያደረገው ለውጥ ካለ፣ ለአገሪቱ የሚሰጠው ዕርዳታ በመንግሥት በኩል መሆኑ ቀርቶ በፕሮጀክቶች አማካይነት በቀጥታ ለዜጎች እንዲውል ማድረጉ ነው፡፡ ከዚያ ውጪ በሶማሊያም ጉዳይ ሆነ በአካባቢው ደኅንነትና የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ዙርያ በጋራ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ ይህ ግን ለአና ጎሜዝ ፍፁም ተቀባይነት የለውም፡፡ ኅብረቱ በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለው ፖሊሲ እስካሁንም አይዋጥላቸውም፡፡
በመጀመርያ አካባቢ የአውሮፓ ኅብረት በተለይ ደግሞ የኅብረቱ ዋና አከርካሪ ከሆኑት አባል አገሮች ግንባር ቀደም ከሆኑት መካከል እንግሊዝ በኢትዮጵያ ላይ የዕርዳታና ብድር ለኢትዮጵያ መንግሥት በቀጥታ እንዳይሰጥ በመከልከል የተሳካላት ቢመስልም የኋላ ኋላ ነገሮች እየተቀየሩ መጥተዋል፡፡ የአውሮፓ ኅብረትም ሆነ የአሜሪካ መንግሥት፣ ተስፋ የጣለባቸው ተቃዋሚዎችና ‹‹አክቲቪስቶች›› ወደ እስር ቤት በመግባታቸው ተፅዕኖዋቸው እየቀጨጨ በመሄዱ የውጭ ኃይሎችም ተስፋ እየቆረጡ መጥተዋል፡፡ ወይዘሮዋም ‹‹አይዟችሁ›› ሲሉዋቸው የነበሩ አመራሮችን ከእስር አላዳኑዋቸውም፡፡ 
እንደ የፖለቲካ ተመራማሪዎች ትንተና፣ በአገሪቱ የተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስና መንግሥት የሰጠው አሉታዊ ምላሽ፣ የአገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ጉዞን ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት ቢሆንም፣ የውጭ ኃይሎች ግን ተስፋ የተጣለውን ያህል ተቃዋሚዎች የዲሞክራሲ ጉዞውንም የሚታደጉ አልነበሩም፡፡ ከውጭ ተፅዕኖ በአንጻራዊነት ነፃ መሆኑን የሚያምነው ኢሕአዴግም ሊቀመንበሩ አቶ መለስም፣ ክፍተቱን ተጠቅመው በኢትዮጵያ ላይ እጃቸውን የሰደዱ ኃይሎች በቀላሉ መቋቋም ችለዋል፡፡ 
የአና ጎሜዝ ድምዳሜና መዘዙ
የመለስ ዜናዊ አጠቃላይ ትንተና የአውሮፓ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ ላይ ሐቀኛ ሪፖርት አላቀረበም የሚል ነው፡፡ በተለይ የምርጫ ታዛቢ ቡድኑን በመሩት ፖርቱጋላዊቷ አና ጎሜዝ ላይ ጠንከር ያለ ተቃውሞን ከመሰንዘር ባሻገር ዘለፋ አከል አነጋገሮችን ተጠቅመዋል፡፡ በኢትዮጵያን ሔራልድ ጋዜጣ ለመጀመርያ ጊዜ በስማቸው ባወጡት ጽሑፍ ቡድኑ በሪፖርቱ ያካተታቸው ጥሬ ሐቆች ያሉት ቢሆንም፣ ድምዳሜው ሁሉ መሠረታዊ ችግር ያለበት መሆኑን ይጠቁማሉ፡፡ በሪፖርቱ በተካተቱ የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ተስተዋሉ የተባሉትን ችግሮች በዝርዝር በማስታወስ ለችግሮቹ መንስዔ የሆኑትንና ሪፖርቱ በውል ያላጤናቸውን ነገሮች በመዘርዘር የሪፖርቱን ኢ-ሚዛናዊነት ያስቀምጣሉ፡፡ በተለይ በቡድን መሪዋ ላይ ካነሷቸው አበይት ነጥቦች መካከል ግለሰቧ የምርጫውን ሒደት ከመታዘብና ከመዘገብ ኃላፊነት አልፈው በድህረ ምርጫው በተነሱት ያለመግባባት ጥያቄዎች የመፍትሔ ሐሳብ ጠቋሚ ሆነው ቀርበዋል የሚል ነው፡፡ አና ጎሜዝ በሪፖርታቸው ምርጫው በተቃዋሚዎች አሸናፊነት መጠናቀቁን ገልጸው የተጋረጠውን አደጋ መመለስ የሚቻለው መንግሥትና ተቃዋሚዎች ወደ ጥምር መንግሥት የሚያመራቸውን የጋራ ስምምነት ማድረግ ሲችሉ እንደሆነ የሚገልጽ ንድፈ ሐሳብ ነበራቸው፡፡ 
በእነዚህና በሌሎችም ተጨማሪ ጉዳዮች የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ‹‹በሪፖርቱ ያልተካተተ ነገር ግን የሪፖርቱ ችግር ምንጭ›› ያሉት አና ጎሜዝን የሚሸነቁጡ ንግግሮችንና ዘለፋዎችን ሰንዝረዋል፡፡ በምላሻቸው ማጠናቀቂያ ላይ የቡድን መሪዋን የመፍትሔ ሐሳብ ላቅርብ ባይነትን በነገር ሲወጉ ‹‹የተከበሩት ወይዘሮዋ ከምርጫው ጋር ተያያዥነት የለውም ብለው እንጂ ዘንድሮ ስላገኘነው ጥሩ የዝናብ መጠንም አስተያየት መስጠት ይችሉ ነበር፤›› ሲሉ መልሰዋል፡፡ 
ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ምላሽ የብዙዎችን ቀልብ የሳበው በጽሑፋቸው መጨረሻ ያሰፈሩት፣ ‹‹What’s love got to do with it›› የታዋቂዋ አፍሪካ አሜሪካዊት ዘፋኝ ቲና ተርነር ዘፈን ወይዘሮዋን ሸንቆጥ ማድረጋቸው ነበር፡፡ የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጽሑፍ እስካሁን በወይዘሮዋ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ይመስላል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ኅልፈት ያደረባቸውን ስሜት እስከመግለጽ ደርሰዋል፡፡ 
አና ጎሜዝ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ በእጅጉ መበሳጨታቸውን በመግለጽ ‹‹ከተቃዋሚዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደተደረገልኝና ሌላ ሌላ አስመስለው ነው የገለጹኝ፡፡ በጣም ምርጥ ጭንቅላት ያለው ሰው ቢሆንም የሰው ሐሳብ የማምታታት ችሎታ የነበረው መሪ ነው፤›› ሲሉ ነው የገለጿቸው፡፡ 
ቪዛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ማግኘታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሞት ያገናኙት አና ጎሜዝ የብሔር ጉዳይም ማንሳታቸው በኢትየጵያ ስላዩት መሻሻል እንዲነግሩት ለጠየቃቸው አዲስ ስታንዳርድ መጽሔት፣ በሰጡት ምላሽ ‹‹አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሚናውን ለመጫወት ቀላል አይሆንም፡፡ በውስጣቸው የሥልጣን ሽኩቻ እንደነበርም አውቃለሁ፤ እሱ ከትግራይ አይደለማ፡፡ የተሰጠኝን ቪዛ ትልቅ ትርጉም እሰጠዋለሁ፤›› ብለዋል፡፡ 

ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን


ሰበር አስዛኝ ዜና !!! ከወደ ደቡብ አፍሪካ !! ታላቁ አፍሪካዊ መሪ ክቡር ኒሰን ማዴላ ከዚህ አለም በሞት ተለዩን ! BBC – South Africa’s Nelson Mandela dies
Mr Mandela, 95, led South Africa’s transition from white-minority rule in the 1990s, after 27 years in prison.
He had been receiving intense home-based medical care for a lung infection after three months in hospital.
In a statement on South African national TV, Mr Zuma said Mr Mandela had “departed” and was at peace.
“our nation has lost its greatest son,” Mr Zuma said.
The Nobel Peace Prize laureate was one of the world’s most revered statesmen after preaching reconciliation despite being imprisoned for 27 years.
He had rarely been seen in public since officially retiring in 2004.
“What made Nelson Mandela great was precisely what made him human. We saw in him what we seek in ourselves,” Mr Zuma said.
“Fellow South Africans, Nelson Mandela brought us together and it is together that we will bid him farewell.”
Earlier, the BBC’s Mike Wooldridge, outside Mr Mandela’s home in the Johannesburg suburb of Houghton, said there appeared to have been an unusually large family gathering.
Among those attending was family elder Bantu Holomisa,
A number of government vehicles were there during the evening as well, our correspondent says.
Since he was released from hospital, the South African presidency repeatedly described Mr Mandela’s condition as critical but stable.
He was awarded the Nobel Peace Prize in 1993 and was elected South Africa’s first black president in 1994. He stepped down after five years in office.
source : BBC  NWES