Tuesday, October 8, 2013
ታማኝ እና ቴዲ ትላንት ምሽት (ክንፉ አሰፋ)
Friday, October 4, 2013
“ኢህአዴግ፤ የምትቃወሙትንም እኔ ነኝ የምሰጣችሁ እንዳይለን” – ተቃዋሚዎች
“የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ወቀሳ ደርሶብኛል “ሥልጣን ለኢህአዴግ የምርጫ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” ውዲቷን ኢትዮጵያ ላለፉት 12 ዓመታት በርዕሰብሔርነት የመሯት (ወይስ መራቻቸው?) የ90 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ፤ ከጥቂት ቀናት
በኋላ ሥልጣናቸውን በአደራ ለሰጣቸው ኢህአዴግ አስረክበው ከቤተመንግስት በመውጣት ኢህአዴግ ወዳዘጋጀላቸው መኖርያ ቤት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። “ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል” ሲባል ሰማሁ ልበል? ወይስ ጆሮዬ ነው? (ጆሮዬ በሆነ!) ለምን መሰላችሁ? መቼም እሳቸው ከሥልጣን አልወርድም ብለው ከኢህአዴግ ጋር ሙግት ሊገጥሙ አይችሉም። ይሄማ ውለታ ቢስ መሆን ነው። እናላችሁ —- “ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር” ከሚለው ይልቅ “ሰላማዊ የሥልጣን እርክክብ” ቢባል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ወገኖች አሉ። በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሥልጣን ዘመናቸው ከህመማቸው በቀር በሌላ በሌላው እድለኛ ናቸው ማለት ይቻላል። እንዴት ብትሉ—- ስንቱ ቱባ ቱባ የኢህአዴግ ሹማምንት በጋዜጠኞች ሲሞለጩና ሲተቹ፣ በፓርቲያቸው ሲገመገሙና “ሂሳችሁን ዋጡ” ሲባሉ፤ እሳቸው ግን ለ12 ዓመት እንደተከበሩ ኖረዋል። (ከተሳሳትኩ እታረማለሁ!) የፕሬዚዳንቱ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ፤ “ውጤታማና እድለኛ ናቸው” ያሉት ለዚህ ይሆን እንዴ? በእርግጥ አልተሳሳቱም፤ሰውየው እድለኛ ናቸው። ባለቀ ሰዓት ግን ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባልሾመ አንጀታቸው የትችት መዓት አወሩዱባቸው እንጂ።
ባለፈው ሳምንት በዚሁ ጋዜጣ ላይ ስለፕሬዚዳንቱ የ12 ዓመት የሥልጣን ዘመን አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ምሁራን በአንድ ድምፅ “ውጤታማ አልነበሩም” ብለዋቸዋል። እኔ ፕሬዚዳንቱን ብሆን (ምኞት እኮ ነው!) ምን እንደምል ታውቃላችሁ? “የእኔን እድል ይስጣችሁ” (እርግማን እኮ አይደለም!) “እንደእኔ ፕሬዚዳንት ሆናችሁ እዩት” ለማለት ነው። ልክ ነዋ! ኢህአዴግ በፕሬዚዳንትነት የሾመው ሰው ያለው ሥልጣንና ሃላፊነት የቱ ድረስ እንደሆነ ሳያውቁ እኮ ነው ተመቸን ብለው የሚናገሩት። ኢህአዴግ የሾመው ከኢህአዴግ ፍላጎት ውጭ ተዓምር እንዲሰራ መጠበቅ “ፌር” አይደለም። (በኢህአዴግ ደግሞ ትግል እንጂ “ተዓምር” መስራት አይፈቀድም!) ከፓርቲው አፈንግጦ ተዓምር ለመስራት የሚወራጭ ካለም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ዓይነት እጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ከቤተመንግስት ወጥቶ ጣራው የሚያፈስ የኪራይ ቤቶች ቤት ውስጥ ይገባል።
ይሄም ታዲያ እጁን ከፖለቲካ ሰብስቦ ከተቀመጠ ብቻ ነው። ነጋሶ ግን እጃቸውን ሰብስበው አልተቀመጡም። በግላቸው በምርጫ ተወዳድረው በማሸነፍ ፓርላማ ገቡ። ራሴ ባረቀቅሁት ህገመንግስት ውስጥ የሰፈረውን ፖለቲካዊ መብቴን ከማስወስድ የሚያፈስ ቤታችሁን ውሰዱልኝ አሉ። (“የነጋሶ መንገድ” በሚለው መፅሃፋቸው እንደነገሩን) በነገራችሁ ላይ ፕሬዚዳንት ግርማ “ውጤታማ አልነበሩም” የሚለውን የተቃዋሚዎች ትችት እየተቃወምኩም ሆነ እየደገፍኩኝ አይደለም። (“አይቻልም ወይ መኖር የማንም ሳይሆኑ” ያለችው ድምፃዊት ማን ነበረች?) እኔ ግን ጥያቄ አለኝ – በፕሬዚዳንቱ ላይ በተሰነዘሩት አስተያየቶች ዙሪያ። ፕሬዚዳንቱ ይሄን ሁሉ ዘመን ኖረው ኖረው ከቤተመንግስት ሊወጡ አንድ ሐሙስ ሲቀራቸው “ውጤታማ ነበሩ? አልነበሩም?” የሚለውን የጦፈ ሙግት ምን አመጣው? ምናልባት ኢህአዴግ አዲስ ለሚሾመው ፕሬዚዳንት ይጠቅም እንደሆነ እንጂ ለተሰናባቹ እኮ የሚተርፋቸው ፀፀት ብቻ ነው። (The damage is already done! አለ ፈረንጅ) እውነቱን ለመናገር— ተቃዋሚዎች ስለፕሬዚዳንቱ የሰጡት አስተያየት የድሮ ተረት ከማስታወስ ያለፈ ፋይዳ አለው ብዬ አላስብም (“ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ” አሉ) የሚገርመው ደግሞ ከአስተያየት ሰጪዎቹ መሃል ጠንካራና ደካማ ጎኖቻቸው ወይም ስኬትና ውድቀታቸው ብሎ ከፋፍሎ ለማየት አንድ እንኳን የሞከረ የለም። ተቃዋሚዎቹ “የማርያም ጠላት” ያደረጓቸውን ያህል በፓርላማ የኢህአዴግ ደጋፊና ብቸኛው የግል ተመራጭ ዶ/ር አሸብርም እንከን የሌለባቸው ፍፁም ፕሬዚዳንት አድርገው ነው ያቀረቧቸው። (“ወልደህ ሳትጨርስ—”የሚለው ተረት ትዝ ብሏቸው ይሆን?) የፕሬዚዳንት ግርማ አማካሪ አቶ አሰፋ ከሲቶ እንኳን የቱንም ያህል መላዕክ ቢያደርጓቸው አይፈረድባቸውም (ሥራቸው ነዋ!) እኔ ተቃዋሚዎችን ብሆን ግን ትችቴን አንድም ኢህአዴግ ላይ አሊያም የፕሬዚዳንቱን ሥልጣን በገደበው ህገመንግስቱ ላይ ነበር የማነጣጥረው።
(“አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” አሉ!) እኔ የምለው ግን— ጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ በፕሬዚዳንት ግርማ ላይ የወረደውን የትችት ውርጅብኝ ሰምቶ ይሆን? ከሩጫ በኋላ ፕሬዚዳንት የመሆን ፍላጎት አለኝ ስላለ እኮ ነው! (ፍላጎት ነው ምኞት?) በኋላ ከሚቆጨኝ ለአትሌታችን ምክር ቢጤ ጣል ባደርግለት ደስ ይለኛል። ለፖለቲካ ዲሲፕሊንና ልምምድ ብቻ በቂ አይደሉም። (ሩጫና ፖለቲካ ለየቅል ናቸው!) እንግዲህ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ባለፉት 12 ዓመታት ሰሩም ተባለ አልሰሩ በቅርቡ ከሥልጣናቸው ይሰናበታሉ። ከወር በፊት ይመስለኛል— ፕሬዚዳንቱ ከ“ሚት ኢቲቪ” አዘጋጅ ተፈራ ገዳሙ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ ለሁለተኛ ጊዜ ሲመረጡ የፍርሃት ስሜት አድሮባቸው እንደሆነ ጠይቋቸው፣ በመጀመርያው ጊዜ እንጂ በሁለተኛው ምንም ዓይነት ፍርሃት እንዳልተሰማቸው ገልፀው፣ለሦስተኛ ዙር በፕሬዚዳንትነት መቀጠል አለመቻሉ ትንሽ እንደሚያናድድ ተናግረዋል – በቀልድ መልክ። (ከአንጀታቸውም ሊሆን ይችላል!) ግን አያችሁልኝ— የኢህአዴግን ምስጢር ወዳድነት። እስካሁን እኮ ቀጣዩ ፕሬዚዳንት ማን እንደሚሆን ፍንጭ እንኳ አልሰጠንም። (ኢህአዴግ “ሰርፕራይዝ” ማድረግም ነፍሱ ነው አሉ!) እናላችሁ— ችግር የለም፤ ቀኑ ሲደርስ አዲሱን ፕሬዚዳንት በፓርላማ አቅርቦ ሰርፕራይዝ ይለናል – እንደ ልደት ስጦታ (ስጦታውስ ለኛ ሳይሆን ለተሿሚው ነው!) ባለፈው ሳምንት “ታጋይ ደከመኝ አይልም እንጂ ኢህአዴግ ድክም ብሎታል” በሚል ርዕስ ያቀረብኩትን ፅሁፍ ያነበቡ አንድ ደንበኛ ስልክ ደውለው እንዴት እንደወቀሱኝ አልነግራችሁም። ወቀሳው ምን መሰላችሁ? “የኢህአዴግን የሥልጣን ዘመን አጭበርብረሃል” የሚል ነው። በመቆርቆር ግን አይመስልም፤ “23 ዓመት አንቀጥቅጦ ገዝቶን እንዴት 21 ዓመት ብቻ ትላለህ? ሁለቱን የት ደብቀህለት ነው?” ነበር ያሉኝ።
እኔ እንኳን መደበቄ አልነበረም። ሁለቷ ዓመት የልምምድ ጊዜ ናት ብዬ ነበር የተውኳት (ለካስ ሂሳብ ማወራረድ ተጀምሯል!) እኔ ግን 30 እና 40 ዓመት የመግዛት ራዕይ ላለው ፓርቲ ገና ወገቡ ላይ ሆነን ሂሳብ መተሳሰብ ፋይዳው አልታየኝም። ባይሆን 30ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ሲገባ የሥልጣን ዘመኑን መቆጣጠር እንጀምራለን፤ አሁንማ ምን ተነካና። በነገራችሁ ላይ — ኢህአዴግ የሥራ ብዛትና ጫና ስላደከመው ከመውደቁ በፊት የአንድ ዓመት እረፍት ይውሰድ በሚል ያቀረብኩትን ሃሳብ አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት ክፉኛ እንደተቃወሙትና እንዳወገዙት ሰምቻለሁ – “ታጋይ አይደክመውም” በማለት። ከዚህ ሃሳቤ የማልታቀብ ከሆነም በቅርቡ የተቃውሞ ሰልፍ ለመውጣት እንደዛቱብኝ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ሹክ ብለውኛል። ከሁሉም የገረመኝ ግን ምን መሰላችሁ? አንዳንድ የኢህአዴግ ካድሬዎች በእኔ ላይ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ገና ካሁኑ መፈክሮች ማዘጋጀት መጀመራቸው ነው። (የሰልፍ ፈቃድ ሳያገኙ?) እስቲ ከመፈክሮቹ ጥቂቶቹን እንያቸው – “ኢህአዴግ ደክሞታል በሚል ማደናገርያ ሥልጣን በአቋራጭ መያዝ የህልም እንጀራ ነው!” “ሥልጣን ለኢህአዴግ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው!” “ኢህአዴግ አረፍ እንዲል የሚፈልጉት የኒዮሊበራል ተላላኪዎች ናቸው!” እኔ ግን እንደነሱ አይደለሁም።
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ቀንደኛ አቀንቃኝ ስለሆንኩ በዛቻውም ሆነ በመፈክሮቻቸው ቅያሜ አላደረብኝም። እንደውም ያለውዝግብ የሰላማዊ ሰልፍ ፈቃድ ካገኙ ከእነሱ ጋር ሰልፍ ለመውጣት ሁሉ አስቤአለሁ – ተቃውሞው በእኔ ላይ ቢሆንም። ከገዢ ፓርቲ ጋር ተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ምን ዓይነት ስሜት እንደሚፈጥር ማወቅ እፈልጋለሁ (ለጠቅላላ እውቀት እኮ ነው!) በዚያ ላይ ተቃዋሚዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሚጠሩት በእያንዳንዱ ሰልፍ ከአዲስ አበባ መስተዳድር ፈቃድ ክፍልና ከፖሊስ ጋር የሚጋቡትን እልህና ውዝግብ ሰበብ ለማወቅ እፈልጋለሁ። ኢህአዴግስ ተመሳሳይ ውዝግብና እልህ ውስጥ ይገባል ወይስ ነገሩ አልጋ በአልጋ ይሆንለታል? (የባለቤቱ ልጅ መሆኑ እኮ አልጠፋኝም!) ይሄን ሁሉ የመፈተሽና የማጥናት ፍላጎት አለኝ። ስፖንሰር ተደርጌ እኮ አይደለም። (የሃገሬ ጉዳይ አያገባኝም እንዴ?) ባለፈው እሁድ ሰማያዊ ፓርቲ በመስቀል አደባባይ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ቦታው በኮንስትራክሽን ሥራ ላይ እንደሆነና “ለልማት ነው ቅድምያ የምንሰጠው” የሚል ምላሽ እንደተሰጠው ገልጿል።
በዚሁ ሰበብ ፖሊስ ከቢሮው ንብረቶች እንደወሰደበት እንዲሁም እሁድ እለት ሰልፉን ሊያካሂዱ ሲሉ መንገድ በመዝጋት ሰልፉን እንዳቋረጠባቸው ፓርቲው በሰጠው መግለጫ አስታውቋል። አንድነት ፓርቲም በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቆ፤ ሌላ አማራጭ ቦታዎች አቅርብ ከተባለ በኋላ ያቀረበው ሁሉ ውድቅ ሆኖ ሰልፉን ጃንሜዳ አድርግ እንደተባለ አስታውቋል። በዚሁ ሰሞን ሰላማዊ ሰልፍን የሚገድብ አዲስ መመሪያ ከአዲስ አበባ መስተዳድር መውጣቱን የሚናገሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፤ የተቃውሞ ሰልፉ የሚደረግበትን ቦታና ጊዜ የሚወስነው መስተዳድሩ እንደሆነ ጠቁመው፤ “አሁን የቀራቸው የምትቃወሙትንም የምንሰጣችሁ እኛ ነን” ማለት ብቻ ነው ሲሉ ክፉኛ አሽሟጠዋል። አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ አዲስ ወጣ በተባለው መመሪያ ተናዶ ምን እንዳለኝ ታውቃላችሁ? “እንደዚያ ከሆነማ ለምን ሰልፍ የሚወጣውንም ህዝብ እነሱ አይመድቡልንም?” በአሁኑ ጊዜ ኢህአዴግ የተቃዋሚዎች ሰልፍ በጣም አስፈርቶታል የሚለው ይሄው የተቃዋሚ ደጋፊ፤ “በመኪና ለመቀስቀስ፣ ፖስተር ለመለጠፍ፣ በራሪ ወረቀት ለመበተን፣ ወዘተ— ለሁሉ ነገር አስፈቅዱኝ እያለ ነው፣ ለምን መፈክሮቹንም እሱ አያዘጋጅልንም” በማለት አዲስ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ለገዢው ፓርቲ አበርክቶለታል። “እናም ኢህአዴግ በቅርቡ “ሰላማዊ ሰልፍ እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ አጀንዳዎችን እንቀርፃለን፣ ለሰልፍ የሚወጣ ህዝብ እንመለምላለን፣ በራሪ ወረቀቶችን እናዘጋጃለን፣ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ እናደርጋለን ወዘተ– የሚል ልዩ ማስታወቂያ በኢቴቪ ሲያስተላልፍ ልንሰማ እንችላለን” ብሏል – የተቃዋሚ ደጋፊው። (ግን ወዴት እየሄድን ይሆን? ለሁሉም የቀረበ ወቅታዊ ጥያቄ ነው!)
ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው "እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልሸጥነው መሬት ነው" መለስ
“መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው።
“የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … ” ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ ህሊናን የሚሰብር መረጃዎች አሉ።
(Photo: IC magazine)
አንድ የአካባቢው ነዋሪ “ሰላማዊ ህዝብ፣ በቅጡ የሚለብሰው እንኳን የሌለውን ህዝብ፣ አሮጊቶችን፣ አዛውንቶችንና ህጻናትን ሲገድሉና ሲያሰቃዩ የቆዩት ለዚህ ነው? ለዚህ ኢንቨስትመንት ነው ያ ሁሉ የተፈጥሮ ደን ወድሞ ከሰል እንዲሁን የተደረገው? ገንዘብ ሳይሆን የከሰል ጆንያ ይዘው ክልሉን እንዲቀራመቱ የሚፈቅዱት ክፍሎች ስለጊዜና ስለዘመን ለምን አያስቡም?” ሲል ይጠይቃል። በማያያዝም “70 ከመቶ የሚሆኑት ባለሃብቶች የትግራይ ሰዎች መሆናቸውን እናውቃለን። መረጃውም አለን። እባካችሁ የተጨቆናችሁ የትግራይ ወንድምና እህቶች እባካችሁን በስማችሁ እየተፈጸመብን ያለውን በደል ተቃወሙ” ሲል ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አስረድቷል።
አዛውንቱ ጸሐይ ለመሞቅ ታዛ ስር ቁጭ ባሉበት (በፎቶው የሚታዩት አይደሉም) ከሙሉ ቤተሰባቸው ጋር የጥይት ራት የተደረጉበት ኢንቨስትመንት አስቀድሞ የተገለጸ ቢሆንም መጨረሻው ሌብነት እንደሆነ ኢህአዴግና ራሱ ድርጅቱ ማመናቸው ተሰማ። አቶ መለስ ሲጀነኑበት የነበረው ኢንቨስትመንት አውላላ ሜዳ ላይ የተደፋ ስለመሆኑ የተጠየቁት አቶ ኦባንግ ሜቶ “እኛን የሚያሳስበን በሊዝ ያልተሸጠው መሬት ነው” በማለት አቶ መለስ የተናገሩትን በማስታወስ “ህዝብን የማይሰማ ድርጅት ዞሮ ዞሮ ከውርደት አይድንም” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። የሰሙት ዜና የሚጠበቅ እንደሆነ ያመለከቱት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ “ሚዲያዎች በነካ እጃቸው ስለ ሰለባዎቹም ይተንፍሱ” ሲሉ ጠይቀዋል።
ኦገስት 31/ 2013 የታተመው የጎልጉል ዜና “የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል” ሲል መዘገቡ ይታወሳል።
በዚሁ ዘገባ ላይ በቦታው ኢህአዴግና ጭፍሮቹ መካከል ሆነው የተካሄደባቸውን የመሬት ነጠቃ በመቃወምና ለሚመለከታቸው አካላት በማሳወቅ ጀብድ ለሰሩት “… በቦታው ላይ ሆናችሁ ለህይወታችሁ ሳትፈሩ ይህንን መረጃ የሰጣችሁ ሁሉ የአገር ጀግኖች ናችሁ፤ አሁን አትታወቁም። አሁን ልንገልጻችሁ አንችልም። ጊዜና ወቅት ጀግንነታችሁን እስኪገልጹት ግን አትረሱም። ልትረሱም አትችሉም። ብዙ ባይነገርላችሁና ባይዘመርላችሁም ታላቅ ስራ ሰርታችኋልና ክብር ይሁንላችሁ” ሲሉ አቶ አባንግ ያስተላለፉት መልክትም ከዜናው ጋር ተካትቶ ነበር።
“በእውቀት ላይ የተመረኮዘ፣ በእቅድ የተያዘ ትግል እያካሄድን እንደሆነ በገለጽኩበት ወቅት ካሩቱሪ በኪሳራ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚወጣ ተናግሬ ነበር። አሁን ጉዳዩ ያለው የኢትዮጵያን ድንግል መሬት በሳንቲም የቸበቸቡትና ያስቸበቸቡት የጥቅም ተጋሪዎችና ደላሎችን ለይቶ ለፍርድ የሚቀርቡበትን ስራ መስራቱ ላይ ነው። በህንድ ጥሪያችንን ሰምተው ትግላችንን የተቀላቀሉ ፍትህ ወዳድ እህትና ወንድሞች፣ ምስጋና ይገባቸዋል” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ካሩቱሪ የተሰማውን ዜና አስመልክተው ተናግረዋል።
ሰንደቅ የተሰኘው ጋዜጣ ዜና ባለስልጣኖችንና የካሩቱሪን ሃላፊ አነጋግሮ ይፋ ያደረገው ዜና ኢህአዴግን የሚያሳፍር ከመሆኑም በላይ ከዝርፊያው በስተጀርባ ያሉትን በሙሉ ያስደነገጠ ሆኗል። የጎልጉል ምንጭ እንደሚሉት የጋምቤላ ድንግል መሬት በሳንቲም ሲቸበቸብ ከጀርባ ሆነው ኮሚሽን የተቀበሉና የሚቀበሉ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ደላሎች አሉ። እነዚህ ሰዎች የአገሪቱን ሃብት በዓይነት፣ ገንዘቧን በብድር፣ ወገኖቻቸውን በጥይት እያስደበደቡ ለባዕድ በመስጠት የፈጸሙት ወንጀል መጨረሻ በራሳቸው አንደበት ይፋ ተደርጓል።
የአክሲዮን ሽያጩና የብድር ምንጩ የደረቀበት ካሩቱሪ ንብረቱ ለሃራጅ እንዲቀርብ በዝግጅት ላይ ነው። ሰንደቅ ባይገልጸውም ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ሳዑዲ ስታር በሚባለው የግብርና ተቋማቸው ሰፊ መጠን ያለው መሬት በመውሰድ ህዝብ እንዲፈናቀል ካደረጉት ጋር እንደሚደመሩ በተለያየ ጊዜ የሚጠቆም ነው።
የሰንደቅ ዜና እንዲህ ይነበባል፡-
የህንድ ካራቱሪ ኩባንያ 62 ሚሊዮን ብር የንግድ ባንክን ዕዳን መክፈል አልቻለም
ኩባንያው የሠራተኞች ግብር፣ ጡረታ እንዲሁም የክልሉን የመሬት ግብር አልከፈለም
ከቀረጥ ነጻ ያስገባቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና በመሸጥ እየተከሰሰ ነው።
ከተረከበው 300 ሺ ሔክታር ያለማው 800 ሔክታር ብቻ ነው።
መሠረቱን በጋምቤላ ክልል ያደረገው የህንድ ካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኀ/የተ/የግ/ማህበር በተሰጠው መሬት ላይ የልማት ሥራ ማከናወን አለመቻሉን እንዲሁም የባንክ ብድርና የግብር ግዴታዎቹን እየተወጣ አለመሆኑ ተገለፀ።
አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠባባቂ የቢዝነስ ዴቭሎፕመንት የስራ ሒደት ባለቤት ስለጉዳዩ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንዳስረዱት “ካራቱሪ ከባንኩ እ.ኤ.አ በዲሴምበር 2011 ወደ 62 ሚሊየን ብር ብድር መውሰዱን አስታውሰው ነገር ግን መክፈል በሚገባው ጊዜ ሊከፍል አለመቻሉን፣ ብድሩንም ለማስታመም የተደረጉ ተጨማሪ ጥረቶች ባለመሳካታቸው ጉዳዩ ወደህግ ክፍል መመራቱን አስታውቀዋል። ባንኩ በአሁኑ ወቅት ይህ ብድር የተበላሸ ወይንም መመለስ የማይችል ነው በሚል ጉዳዩን ይዞት ለማስመለስ ወደ ሕጋዊ እርምጃ መግባቱን” ተናግረዋል።
በተያያዘም በግብርናው ዘርፍ ለመሰማራት ከአራት ዓመት በፊት በጋምቤላ ክልል 300ሺ ሄክታር መሬት ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር ጋር ተዋውሎ የገባው የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ባለው ደካማ ማኔጅመንት ምክንያት ሥራውን ማከናወን ባለመቻሉ በአሁኑ ወቅት ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
አቶ አለምሰገድ አያሌው የኩባንያው የምርት መሳሪዎች ዋና ክፍል ኃላፊና የሠራተኞች ተወካይ ለሰንደቅ ጋዜጣ በስልክ እንደገለጹት ኩባንያው 300ሺ ሄክታር ለማልማት ከግብርና ሚኒስቴር መሬት ተረክቦ የነበረ ቢሆንም ባለፉት አምስት አመታት ከ800 ሄክታር በላይ ለማልማት አልቻለም።
ግብርና ሚኒስቴር ይህንኑ ደካማ አፈጻጸም በማየት ከአንድ ዓመት በፊት 200ሺ ሄክታር መሬት የነጠቃቸው መሆኑን አቶ አለምሰገድ አስታውሰው ይህንንም ማልማት ባለመቻላቸው በአሁኑ ወቅት በእጃቸው የሚገኘው መሬት 10ሺ ሄክታር ብቻ ነው ብለዋል። ይህም ሆኖ በአሁኑ ወቅት በበቆሎ ሰብል የተሸፈነው 800 ሄክታር ገደማ ብቻ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
ድርጅቱ 150 ያህል ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞች እንዳሉት ያስታወሱት አቶ አለምሰገድ የሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ እስከ 45 ቀናት እንደሚዘገይ፣ ለጡረታና ለግብር ከሰራተኛው የሚሰበሰበው ክፍያ በአግባቡ ለሚመለከተው አካል እንደማይገባ ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል።
የኩባንያው አመራሮች በውጪ ምንዛሪ የሚያስገቡዋቸውን ዘርና ማዳበሪያ በአገር ውስጥ እንደሚሸጡ፣ ከቀረጥ ነጻ ያስገቡዋቸውን ማሽነሪዎች በማከራየትና ለሶስተኛ ወገን በመሸጥ ያልተገባ ጥቅም እንደሚያጋብሱ ተናግረዋል።
ይህንኑ አቤቱታቸውን ለጋምቤላ ክልል የሚመለከታቸው መ/ቤቶች በተደጋጋሚ ማሳወቃቸውን ገልጸዋል።
የጋምቤላ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ ዳይሬክተር አቶ ጆን ሾል ስለጉዳዩ ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው የካራቱሪ የስራ አፈጻጸም እጅግ ደካማ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኩባንያው በተጨማሪም ለወረዳ መክፈል ያለበትን የመሬት ግብር ጭምር እንዳልከፈለ የጠቆሙት አቶ ጆን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክም የተበደረውን ባለመክፈሉ ባንኩ በመያዥነት የያዛቸውን ንብረቶች ወደማስከበር ስራ ፊቱን ማዞሩን ጠቁመዋል።
በቅርቡ ከፌዴራል መንግስት ባለሙያዎች ወደቦታው መጥተው ችግሩን አጥንተው መመለሳቸውን ጠቁመው በቅርቡ ኩባንያውን በተመለከተ የመጨረሻ መፍትሔ ሊገኝ እንደሚችል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የካራቱሪ አግሮ ፕሮዳክት ኃ.የተ.የግ.ማኅበር (ጋምቤላ ኤሊያ አካባቢ) የሥራ ኃላፊዎችን በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
የትህዴን ደጋፊዎች ግንቦት-7 እያካሄደው ባለ ስብሰባ መገኘታቸውን የትህዴን የህዝብ ግንኝነት ገለጸ
ትህዴን የትጥቅ ትግል በማካሄድ ላይ ከሚገኘው ግንበት-7 ጋር ተባብሮ ለመስራት መግባባት ላይ ከመድረሱም በላይ በተግባር በተለያየ መልኩ ሲተጋገዙ የቆዩ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ሃገራት የሚገኙ የትህዴን አ ባላት የጉንበት-7 አ መራር ከአ ባላቱ ጋር በተለያዩ ሃገራት እያካሄደው ባለ ስብሰባ በመገኘት አንድነታችንን አ ጠናክረን እጅ ለእጅ
ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ለግንበት-7 ያላቸውን ድጋፍ መግለጻቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣ በስብሰባው የተገኙ የትህዴን ተወካዮች አ ያይዘው እኛ በዚሁ ስብሰባ
ስንገኝ ለይምሰል ሳይሆን የህዝብን ድምጽ በAፈሙዝ ረግጦ ስልጣን የተቆናጠጠውን ከፋፋዩን የእህAዴግ ስርዓትን በሚገባው ቋንቋ በትጥቅ ትግል ከስሩ መንግሎ ለመጣል ገና ከመነሻው ትህዴን አ ምኖበት የተነሳለት በመሆኑ የድርጅቱን ዓላማ እግቡ ለማድረስ የሁለቱም ድርጅቶች Aባላትና ደጋፊዎች የIህአ ዴግ ስርዓት መለያ ከሆነው በዘር የመከፋፈል Aባዜ በመውጣት በሙሉ ልብ ድርጊቱን በማውገዝ ከሃገር ውስጥ ይሁን ከሃገር ውጭ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ከመቸውም ጊዜ በላይ ግንኝነታችንን አጠናክረን ተባብረን መስራት ይጠበቅብናል በማለት ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፣ የግንበት-7 አመራርናአ ባላት በቡኩላቸው የትጥቅ ትግል በማድረግ ላይ ካሉት ተቃዋሚ ድርጅቶች በመሳሪያ ፤ በሰው ሃይልና በዓላማ ሲታይ ትህዴን ንካራ መሆኑን በመግለጽ እንዲህ ካለው Aስተማማኝ ድርጅት ጋር ተባብሮ ለመስራት ከመግባባት አልፈን አ ብረን እየሰራን ነው፣ ይህ መልካም ጅምር አጠናክረን እንቀጥልበትአለን ሲሉ ገልፇል::
Source: ትህዴን
Tuesday, October 1, 2013
የአንዱዓለም አራጌ መልክት ከቃሊቲ (በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ) የአንዱዓለም አራጌ መልክት ከቃሊቲ (በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነበበ)
ከሁሉ አስቀድሜ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ሠላማዊ ሠልፍ ለተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼለእያንዳንዳችሁ በተናጠል ልባዊ የአክብሮትና የናፍቆት ሠላምታዬ በግፍ ከታሰርኩባት ጠባቧ ክፍል ይድረሳችሁ
Andualem Aragie (3)ኢትዮጵያውያን ለዘመናት እውን ያላደረግነውን የህዝባዊ ልዕልና ጥያቄና ሌሎች ከነፃነት እጦት ጋር የተቆራኙ በአገዛዙ የሚፈፀሙ አያሌ የአፈና ተግባሮችን ለመቃወም በተጠራው በዚህ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ከጎናችሁ መሠለፍ ባለመቻሌ ባዝንም፣ ከተሰለፋችሁላቸው ዓላማዎች አንዱ የእኔና የጓደኞቼን ከእስር መቀቀቅ የሚመለከትና የታሰርኩለትም ዓላማ አካል በመሆኑ በመንፈስ ከጎናችሁ እንዳለሁ አምናለሁ፡፡ በዚህም ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡
Andualem Aragie (3)ኢትዮጵያውያን ለዘመናት እውን ያላደረግነውን የህዝባዊ ልዕልና ጥያቄና ሌሎች ከነፃነት እጦት ጋር የተቆራኙ በአገዛዙ የሚፈፀሙ አያሌ የአፈና ተግባሮችን ለመቃወም በተጠራው በዚህ ሠላማዊ ሠልፍ ላይ ከጎናችሁ መሠለፍ ባለመቻሌ ባዝንም፣ ከተሰለፋችሁላቸው ዓላማዎች አንዱ የእኔና የጓደኞቼን ከእስር መቀቀቅ የሚመለከትና የታሰርኩለትም ዓላማ አካል በመሆኑ በመንፈስ ከጎናችሁ እንዳለሁ አምናለሁ፡፡ በዚህም ታላቅ ደስታ ይሰማኛል፡፡
ኢትዮጵያ ህዝባዊ ልዕልና የሠፈነባት የነፃነትና የዴሞክራሲ ምድር ትሆን ዘንድ የቀደሙ ትውልዶች ከፍተኛ መሰዋእትነት ከፍለዋል፡፡ ሌላውን ትተን የዛሬ 4ዐ ዓመት የተደረገውን ትግል ብቻ መጥቀስ ጥሩ ማሳያ ይሆናል፡፡ የዛሬ 4ዐ ዓመት ‹‹ሕዝባዊ መንግሥት›› ለመመስረት በሚል በተደረገ ትግል ሊለካ የማይችል መስዋዕትነት ተከፍሏል፡፡ ነገር ግን ‹‹ከጎናቸው ተሰልፈን ታገልን የሚሉን ወገኖች ዛሬ የኢትዮጵያን ህዝብ እግረ ከወርች አስረው እየረገጡት ይገኛሉ፡፡
ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሉዓላዊ ሥልጣኑ ባለቤት መሆን አልቻለም፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ ሕዝብ ከገጠር እስከ ከተማ በካድሬዎች ፈርጣማ መዳፍ እየታሸ ነው፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ ከማደናገሪያ ስልትነት ባለፈ የህዝብ የመናገርና የመፃፍ መብት አልተከበረም፡፡ ዛሬም 4ዐ ዓመት በኋላ አገዛዙን የሚቃወሙ ዜጎች በበሬ ወለደ ክስ በግፍ ይታሰራሉ፡፡
እኔና ጓደኞቼ ለዚህ ማሳያዎች ነን፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመረጠው ሳይሆን አፈ-ሙዝ ያገነነው በምርጫ ተውኔት 99.6% የህዝብ ድምጽ በመዝረፍ ሀገራችንን በዓለም ፊት የሚያኮስስና የህዝቧን ክብር የሚያዋርድ ተግባር የሚፈፀምባት ሀገር ነች፡፡ ዛሬም ከ4ዐ ዓመት በኋላ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በጥቂት የወቅቱ አምባገነኖች በገዛ ሀገሩ እስረኛ ሆኖ ይገኛል፡፡
ዛሬ እየተካሄደ ያለው ሠልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘመናት እስራት ነፃ ለመውጣት የሚያደርገው አጠቃላይ ትግል አካል ነው፡፡ ኢትዮጰያውያን የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪዎች ብንሆን፣ የየትኛውም እምነት ተከታዮች ብንሆን፣ የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባሎች ብንሆን፣ በየትኛውም የፆታና የእድሜ ክልል ብንገኝ ሁላችን አንድ የሚያደርግ ሰብአዊ ልዕልናችን ተከብሮ በነፃነት የመኖር ተቀዳሚ አጀንዳ አለን፡፡
ዛሬ እየተካሄደ ያለው ሠልፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘመናት እስራት ነፃ ለመውጣት የሚያደርገው አጠቃላይ ትግል አካል ነው፡፡ ኢትዮጰያውያን የየትኛውም ቋንቋ ተናጋሪዎች ብንሆን፣ የየትኛውም እምነት ተከታዮች ብንሆን፣ የየትኛውም ፖለቲካ ፓርቲ አባሎች ብንሆን፣ በየትኛውም የፆታና የእድሜ ክልል ብንገኝ ሁላችን አንድ የሚያደርግ ሰብአዊ ልዕልናችን ተከብሮ በነፃነት የመኖር ተቀዳሚ አጀንዳ አለን፡፡
ነፃነት ማንም በችሮታ ወይንም በአዋጅ የሚያረጋግጥልን ሳይሆን በነፃነት ለነፃነት የተፈጠርን ሉዓላዊ ፍጡራን መሆናችንን ከልብ ስናምን የምንጎናፀፈው ፀጋ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ትልቁ የነፃነት ጠላት እራስን ዝቅ አድርጎ ከማየት የሚመጣ ፍርሃት ነው፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ሕዝብ በአዋጅ ነፃ ሊወጣ አይችልም፡፡ አዋጅ መች ቸገረንና? ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ የነፃነቱ ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ፍርሃትን ያላሸነፈ ህዝብ ለልጆቹ ነፃ ሀገር ሊያወርስ አይችልም፡፡ የፍርሃትንና የግለኝነት ወረርሽኝ ማስወገድ ፈጽሞ ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አይደለም፡፡ ፍርሃትንና ለኔነትን ድልነስታችሁ ዛሬ ለነኀነት መሰለፍ በመቻላችሁ የተግሉን የመጀመሪያና ወሳኝ መዕራፍ ተሻግራችኋል፡፡
ፍርሃትን በማሸነፍ ለነፃነት መታገል ወሳኝ የመሆኑን ያህል፣ ከቀደሙ ስህተቶቻችን መማር፣ ትግሉን በተጠናና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ማካሄድም የዚያኑ ያህል አስፈላጊና ወሳኝ ነው፡፡
እስከ አሁን በዝምታችን አምባገነኖች የልብ ልብ እንዲሰማቸው ብሎም አፍነው እንዲገዙን እድል ሰጥተናቸዋል፡፡ እስከ አሁን መብቶቻችንና ሰብአዊ ክብራችን በግደለሽነት እንዲረገጡ በመፍቀዳችን ኢትዮጵያና ሕዝቧ የጥቂት ገዢዎች አንጡራ ሀብት ሆናለች፡፡ እስከ አሁን በቁርጠኝነት ባለመታገላችን ዛሬም እንደ አዲስ ከአምባገነንነት ጋር ግብግብ መግጠም ግድ ሆኖብናል፡፡ የአፈናውን የክፋት ደረጃና የአገዛዙን አሙለጭላጭ የአፈና ስልቶች ግንዛቤ ውስጥ ያስገባና ዘመኑን የሚመጥን የፀና ሠላማዊ ትግል ማድረግ ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይጠበቃል፡፡
ሠላማዊ ትግል በአንድ ወይንም በሁለት ሠልፍ የሚቋጭ ሳይሆን አያሌ ስልቶችንና ሠፊና ቀጣይነት ያለውን እንቅስቃሴ የሚያካትት ነው፡፡ የፖለቲካ ባህላችንና አስተሳሰባችንን ከማዘመን ጀምሮ ገዢዎች ነፃነትን የማይፈሩበትን ስነ-ልቦና እንዲላበሱ ማድረግና ለበርካታ ዘመናት በጭቆና ደቅድቅ ጨለማ ውስጥ ያለችውን ሀገራችን የነፃነት ብርሃን ከደር እስከዳር የሚበራባት ሀገር እስክትሆን ድረስ መታገል ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ የላቀና የከበረ ምን ቁም ነገር ይኖራል?
ይህ ትውልድ ለማመን የሚከብዱ ታላላቅ ገድሎችን የሰሩ አባቶች ልጆች መሆናችንን ለአፍታ እንኳ መዘንጋት አይገባውም፡፡ በተግባርም የላቀ ገድል በመስራት ማንነቱን ሊያስመሰክር ይገባል፡፡ አባቶቻችን የሞቱላትንና የአጽማቸው ማረፊያ፣ እትብታችን የተቀበረባትንና የሁለንተናዊ ማንነታችን ማህደርና የልጆቻችን ተስፋና መኖሪያ የሆነችውን የምንወዳትን ሀገራችንን ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሰፈነባት የማይደርቅ የህዝባዊ ሉዓላዊነት ምንጭ እስክናደርጋት ድረስ እጅ ለእጅ ተያይዘን ትግላችንን በጽናት መቀጠል የጠበቅብናል፡፡ የዓላማና የህሊና ንጽህናን ተላብሰን ለወንድማማችነት፣ ዴሞክራሲና ነፃነት በምናደርገው ሠላማዊ ትግል ፈጣሪም ከእኛ ጋር እንደሚሆን አምናለሁ፡፡
በመጨረሻም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በእስራኤል አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እየከፈልኩት ላለው ዋጋ እውቅና ሰጥተው ስለዘከሩኝ፣ የኢሳት ቴሌቭዥን ተመልካቶችና የዘ-ሀበሻ ድረ-ገጽ ታዳሚዎች ‹‹የዓመቱ ሰው›› ብለው በመምረጠ ላጎናፀፉኝ ትልቅ ክብር ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ በግፍ የታሰርን ሰዎች እንድንፈታ በመጠየቁ አመሰግናለሁ፡፡ በአጠቃላይ በፀሎት ከማሰብ ጀምሮ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ከጎኔ በመቆማችሁ የላቀ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡ ይህ የመከራ የሀሩር ወቅት አልፎ ብርሃን በሞላው የፀደይ ወቅት በነፃነት ለመኖር ትግላችንን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ አጠናክረን ልነቀጥል ይገባልይገባናል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብም ሆነ ህሊናዩን የሚያሳዝን አንዳችም ነገር ፈጽሜአለሁ ብዬ አላምንም! ፍፁም ሠላም ይሠማኛል፡፡ እኔን እዚህ ያቆመኝ የነፃነት ናፍቆት ነው፡፡
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ!
የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን የሰውለሰው ድራማ በ አጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለፊልሙ ባለቤቶች አሳሰበ።
* የኢትዮጲያ ቴሌቪዥን የሰውለሰው ድራማ በ አጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለፊልሙ ባለቤቶች አሳሰበ። በ፮ ወር ጊዜ ውስጥ ሊጠናቀቅ ይችላል።
13 ያህል ስደተኞች በጀልባ ሰምጠዉ መሞታቸዉ ተሰማ
13 ያህል ስደተኞች በጀልባ ወደ ኢጣሊያ- ሲሲሊ የባህር ዳርቻ በዋና ለመድረስ ሲሞክሩ ሰምጠዉ መሞታቸዉ ተሰምቷል። ከጀልባ ወርደው በዋና ለመሰወር ሲሞክሩ ነው። የተባበሩት መንግሥትት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ UNHCR እንዳስታወቀው በኢጣሊያ በኩል የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋ ሲነፃፀር በ3 እጥፍ ጨምሯል።
ባለፈው ረቡዕ ነበር ከ700 በላይ ተገን ጠያቂ ስደተኖችን ያሳፈሩ ሶስትጀልባዎች ደቡብ ኢጣሊያ ሲሺሊ ግዛት የባህር ዳርቻ ገብተው የተገኙትየኢጣሊያ ጠረፍ ጠባቂ ዘበኖች ለኣጃንስ ፍራንስ የዜና ኣገልግሎት እንደደገለጹት ሁለቱ የመጡት በላምፔዱሳ ደሴት በኩል ነው በኢጣሊያ ደቡባዊ ጫፍ የምትገነው የላምፔዱስ ደሴት የማንነት
ማረጋገጫያልያዙ በርካታ ስደተኖች ወደ ኣውሮፓ የሚሸጋገሩባት ዋንና በር መሆንዋ ይነገርላታል ከስደተኖቹ መካከልም ገሚሶቹ የሶሪያ ዜጎች መሆናቸው ታውቀዋል በዘገባው መሰረት የመጀመሪያዋ ጀልባ ብቻ 398 የሶሪያ ስደተኖችን ይዛለች በሁለተኛው ጀልባ ላይ የነበሩት 111 ስደተኖች ማንነት ወደፊት ይጣራል ተብለዋል ። የመጨረሻዎቹ ደራሾች 350 ስደተኖችን ብቻ በምታስጠልል
የደሴቲቱ ጊዛዊ የስደተኖች ማቆያ ጣቢያ ውስጥ ተጨናንቀው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችለዋል 200 ተሳፋሪዎችን የያዘችው ሶስተናዋ ጀልባ ባለፈው ማክሰኖ ነበር በቅንት ኣውሮፕላን ታይታ በሲሺሊው የሲራውኮውስ ወደብ እንድትጠለል የተደረገችው ከ200 ዎቹ ተሳፋሪዎች መካከል 70ዎቹ ህጻናት መሆናቸው ታውቀዋል
ማረጋገጫያልያዙ በርካታ ስደተኖች ወደ ኣውሮፓ የሚሸጋገሩባት ዋንና በር መሆንዋ ይነገርላታል ከስደተኖቹ መካከልም ገሚሶቹ የሶሪያ ዜጎች መሆናቸው ታውቀዋል በዘገባው መሰረት የመጀመሪያዋ ጀልባ ብቻ 398 የሶሪያ ስደተኖችን ይዛለች በሁለተኛው ጀልባ ላይ የነበሩት 111 ስደተኖች ማንነት ወደፊት ይጣራል ተብለዋል ። የመጨረሻዎቹ ደራሾች 350 ስደተኖችን ብቻ በምታስጠልል
የደሴቲቱ ጊዛዊ የስደተኖች ማቆያ ጣቢያ ውስጥ ተጨናንቀው እንደሚገኙም ለማወቅ ተችለዋል 200 ተሳፋሪዎችን የያዘችው ሶስተናዋ ጀልባ ባለፈው ማክሰኖ ነበር በቅንት ኣውሮፕላን ታይታ በሲሺሊው የሲራውኮውስ ወደብ እንድትጠለል የተደረገችው ከ200 ዎቹ ተሳፋሪዎች መካከል 70ዎቹ ህጻናት መሆናቸው ታውቀዋል
የእነዚህ ጀልባዎች ኣመጣጥ የግጭት ቀጠና ከሆኑት የሜዲትራኒያን ባህር እና የኣፍሪቃ ቀንድ አካባቢዎች የሚመጡ ጀልባዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ መምጣቱን ያመለክታል ተብለዋል የ ተ መ ድ የስደተኖች ተቁዋም ባሳለፍነው ወር መጀመሪያ ላይ እንዳስታወቀው
ከ20000 በላይ ተገን ጠያቂ ስደተኖች ኢጣሊያ መድረሳቸው ሲታይ ይህ አኃዝ በ2012 እ ኣ,ኣ ማለት ነው በዓመቱ ከገቡት ስደተኖች በሶስት እጥፍ ማሻቀቡን ያመለክታልአብዛኖቹ የሚመጡት ደግሞ ከኤርትራ ሶማሊያ እና ሶሪያ መሆኑ ታውቀዋል ። የእነዚህ ጀልባዎች ጉዞ በራሱ ፈታን መሆኑን ብዙዎች በምሬት ይናገራሉ
በትላንትናው ዕለትም 13 ስደተኖች እጣሊያ ጠረፍ ከደረሱ በኃላ ከጀልባ ወርደው በዋና ለመሰወር ሲሞክሩ መሞታቸውን የአካባቢው ከንቲባ አስታውቀዋል አንዳንዶቹም ለጥቂት ተርፈው በኣካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ 339 ስደተኞችን አሳፍራ ሲሲሊ እጣሊያ በደረሰች ጀልባ ላይም ኣንዲት የ 22 ዓመት የሲሪያ ዜጋ ሞታ መገነትዋ ተዘግበዋል ኣንዳንዴም ኢጣሊያ ጠረፍ ሲደርሱ ስደተኖች በባለጀልባዎቹ አማካኝነት ወደ ባህር የሚወረወሩበት ኣጋጣሚም እንዳለ ተወስተዋል

ከ20000 በላይ ተገን ጠያቂ ስደተኖች ኢጣሊያ መድረሳቸው ሲታይ ይህ አኃዝ በ2012 እ ኣ,ኣ ማለት ነው በዓመቱ ከገቡት ስደተኖች በሶስት እጥፍ ማሻቀቡን ያመለክታልአብዛኖቹ የሚመጡት ደግሞ ከኤርትራ ሶማሊያ እና ሶሪያ መሆኑ ታውቀዋል ። የእነዚህ ጀልባዎች ጉዞ በራሱ ፈታን መሆኑን ብዙዎች በምሬት ይናገራሉ
በትላንትናው ዕለትም 13 ስደተኖች እጣሊያ ጠረፍ ከደረሱ በኃላ ከጀልባ ወርደው በዋና ለመሰወር ሲሞክሩ መሞታቸውን የአካባቢው ከንቲባ አስታውቀዋል አንዳንዶቹም ለጥቂት ተርፈው በኣካባቢው ወደሚገኝ ሆስፒታል የተላኩ ሲሆን ባለፈው ቅዳሜ 339 ስደተኞችን አሳፍራ ሲሲሊ እጣሊያ በደረሰች ጀልባ ላይም ኣንዲት የ 22 ዓመት የሲሪያ ዜጋ ሞታ መገነትዋ ተዘግበዋል ኣንዳንዴም ኢጣሊያ ጠረፍ ሲደርሱ ስደተኖች በባለጀልባዎቹ አማካኝነት ወደ ባህር የሚወረወሩበት ኣጋጣሚም እንዳለ ተወስተዋል
የካቶሊክ ቄስ የሆኑት አባ ሙሴ ዘርዓይ THE AGENCY ABESHA የተባለ ግብረ ሰናይ ተቋዋ መሪ ናቸው ድርጅታቸው ከሊቢያ ተሳፍረው በኢጣሊያ በኩል የሚገቡ ስደተኖችን በማማከር እና በመርዳት ይታወቃልችግሩ ከስደተኖቹ አንጻር ሌላ ኣማራጭ አለመኖሩ ሲሆን የኣውሮጳ መንግስታትም በዚህ ረገድ ከልብ አላሰቡበትም ይላሉ አባ ሙሴ ። አባ ሙሴ እንደሚሉት በዚህ ዓመት ብቻ 100 ያህል ስደተኖች በተመሳሳይ ሁኔታ ህይወታቸውን ኣተዋል
ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ 1800 ያህል ስደተኖች በባህር መምጣታቸውን የጠቀሱት አባ ሙሴ በኣሁኑ ጊዜ 1500 ያህሉ በተለያዩ ካምፖች ይገኛሉ ብለዋል ይህንኑ ሁኔታ ለማስቆምም የኣውሮፓ ህብረት ኢጣሊያን ጨምሮ ከሊቢያ እና ቱኒዚያ መንግስታት ጋር በመሆን ሰብዓዊ የሆነ መፍትሄ መሻትይኖርበታል ሲሉ መክረዋል ።
ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ
ባለፉት ሶስት ሳምንታት ብቻ 1800 ያህል ስደተኖች በባህር መምጣታቸውን የጠቀሱት አባ ሙሴ በኣሁኑ ጊዜ 1500 ያህሉ በተለያዩ ካምፖች ይገኛሉ ብለዋል ይህንኑ ሁኔታ ለማስቆምም የኣውሮፓ ህብረት ኢጣሊያን ጨምሮ ከሊቢያ እና ቱኒዚያ መንግስታት ጋር በመሆን ሰብዓዊ የሆነ መፍትሄ መሻትይኖርበታል ሲሉ መክረዋል ።
ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ
ሊንኩን በመንካት ዝርዝር ዘገባውን ያዳምቱ
Subscribe to:
Posts (Atom)