Friday, August 2, 2013

እንደራሴ ስሚዝ አዲስ አበባ ሊሄዱ ነው




chris smith


አሜሪካና ሌሎች ለሰብአዊ መብት መከበር ዋጋ የሚሰጡ አገሮች በሙሉ በ”አዲስ አበባው” አገዛዝ ላይ ጠንካራ አቋም መያዛቸውን ያለ አንዳች ማወላወል ማሳየት እንደሚገባቸው አሳስበው የነበሩት ኮንግረንስ ማን ክሪስ ስሚዝና ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ተጠቆመ። በሰኔ (ጁን) ወር “… የአሜሪካ መንግስትም ሆነ ሌሎች የምዕራብ አገራት፣ ኢህአዴግ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየፈጸመ ያለውን ተግባር በመረዳት አቋማቸውን በግልጽ ማስቀመጥ ይገባቸዋል” የሚል ጥሪ ያስተላለፉት ክሪስ ስሚዝ አዲስ አበባ መምጣት ኢህአዴግን እንዳሳሰበው ለማወቅ ተችሏል።
ኢትዮጵያ ከመለስ በኋላ” በሚል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የነበረውን የምክክር ስብሰባ የመሩት የአሜሪካን ምክር ቤት እንደራሴ /ኮንግረንስማን/ ክሪስ ስሚዝና ሌላዋ ባልደረባቸው እንደራሴ ኬረን ባስ ኢህአዴግ እስር ቤቶችን እንዲያሳይ፣ የታሰሩትን የፖለቲካ እስረኞችንም ይሁን ከሙስሊሙ ኅብረተሰብ በግፍ ለእስር የተዳረጉትን እንዲያስጎበኝ ለሚቀርብለት ጥያቄና በጸረ ሽብርና ህጉ ዙሪያ የሚሰጠው ምላሽ በጉጉት ይጠበቃል።
ምክክሩን ሲከፍቱ አቶ መለስን “አሮጋንት /እብሪተኛ/፣ የፈለገውን ነገር በፈለገው ጊዜ የሚያደርግ ሰው እንደነበር አዲስ አበባ ሄጄ ባነጋገርኩበት ወቅት አረጋግጫለሁ” በማለት የገለጹት ክሪስ ስሚዝ፣ ከባልደረባቸው ጋር ወደ አዲስ አበባ የሚያመሩት አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታራምደውን አቋም ለመመርመር የሚያስችላትን ስራ ለመስራት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ከምክክሩ በፊትና በኋላ ክሪስ ስሚዝ በሰጡት ጠንካራ አስተያየት የተደናገጠው ኢህአዴግ አዲስ ዘመን በሚባለው ልሳኑ “አሜሪካ የኢትዮጵያ አጋርና ወዳጅ መሆንዋን አረጋገጠች” በማለት የሌሎች ተናጋሪዎችን  ወደጎን በመተው የአምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶን ብቻ አንድ ሃረግ ንግግር ቀንጭቦ ዘግቦ ነበር። በአሜሪካ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ባልተለመደ ሁኔታ የተብጠለጠለው ኢህአዴግ ወዳጆቹን ለማረጋጋት ያማሞቶን ጠቅሶ ያሰራጨው ዜና በወቅቱ በደጋፊዎቹ የፌስቡክ ገጽ ላይ በስፋት ተበትኖ ነበር።
Bass
እንደራሴ ኬረን ባስ
ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ወቅት ላይ መሆኗን ያመላክታል የተባለው የአዲስ አበባ ጉብኝት አስመልክቶ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኢህአዴግ የፖለተካውን ምህዳር በማጥበብ፣ በጸረ ሽብር ህጉ እያሳበበ የመናገርና የመሰብሰብ መብትን ማፈኑ፣ የነጻ ሚዲያና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ማነቁ፣ በተለይም በእስር ቤት የሚሰቃዩ ወገኖችን በአካል በመገኘት በማነጋገር አቋም ለመውሰድ መታቀዱን አመልክተዋል። ይህም ከፖለቲካ እስረኞች ጀምሮ፣ ጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን፣ የሙስሊሙን ኅብረተሰብ ጥያቄ ከፍ አድገው በማንሳታቸው ለእስር የተዳረጉትን ወዘተ የሚያጠቃልል ይሆናል፡፡
“የሚሆነው እስከሚሆን መጠበቅ ነው” በማለት ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ አንድ ዲፕሎማት እንዳሉት ነሐሴ 10 ወይም 11 ቀን 2005 (ኦገስት 16 ወይም 17፤ 2013) ወደ ኢትዮጵያ የሚያመሩት ሁለቱ እንደራሴዎች፤ ለኢህአዴግ የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች እጅግ መሰረታዊ እንደሆኑ ይናገራሉ።
“ጉብኝቱ የሽርሽርና እንደተለመደው አይነት የሁለትዮሽ ስብሰባና ስምምነት ለማድረግ አይደለም” የሚሉት አስተያየት ሰጪ “ኢህአዴግ በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች እስር ቤቶችን እንዳይጎበኙ እንደከለከለው ማድረግ አይችልም” ብለዋል። ሲያስረዱም “በደቡብ ሱዳን ያለው የፖለቲካ ኡደት፣ በሶማሊያ ጭብጡ ያለየለት ሁከት፣ በኤርትራ ያለው የዛለ መንግስት እጣፈንታና የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር ከፋፍሎ ጥቂቶች እንዲበለጽጉ ያደረገው ኢህአዴግ መጨረሻው አሜሪካንን በእጅጉ ሃሳብ ላይ ጥሏታል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሰፋ የሄደው ቁርሾና የጥላቻ ፖለቲካ ሳይፈነዳ ኢህአዴግን ማረቅ የአሜሪካ ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል። ይህንን አጀንዳ አሜሪካ በቀላሉ ተጭበርብራ የምትቆልፈው አይሆንም።”
“የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ህገደንብ” የሚል ስያሜ ያለው ህግ ኢትዮጵያን የሚመራው ኢህአዴግ ከአሜሪካ መንግስት ለሚፈልገው ማናቸውም ድጋፍ መሟላት የሚገባቸውን የሰብአዊና የዴሞክራሲ መብት ግብአቶችን በቅድመ ሁኔታ የሚያስቀምጥ ነበር። ይህ ህግ ኢህአዴግ በከፍተኛ ደረጃ ገንዘብ አፍስሶ በአሜሪካን ጎትጓቾች (ሎቢዪስቶች) ዘመቻ ያካሄደበትና የወቅቱ የቡሽ አስተዳደር “እንዝላልነት” ታክሎበት ሊመክን ችሏል። ይህን ህግ እንደገና ለማጸደቅ እንደሚሰሩ በግልጽ የተናገሩት ስሚዝ፣ “አሁን ፖሊሲያችንን ዳግም የመፈተሽያ ጊዜ ላይ ነን። ቁም ነገሩ ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር መቆሙ ላይ ነው። ከተጨቆኑት ወገኖች ጋር እንቆማለን” በማለት አቋማቸውን ግልጽ አድርገው ነበር።
በዚህ ይሁን በሌላ ምክንያት የመለስ ምትክ የሆኑት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የስኳር ሚኒስትሩ አቶ አባይ ጸሐዬ ሰሞኑንን “የዲሞክራሲ ማበብ የህልውና ጉዳይ ነው” በማለት ለተለያዩ መገናኛዎች በየፊናቸው የተናገሩትን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በስፋት ዘግቦታል። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታው ከመለስ እጅ በተካሄደው ርክክብ መሰረት አፈናውን አጠናክሮ የቀጠለ ስለመሆኑ ከየአቅጣጫው የሚጎርፈው መረጃ ከወትሮው በተለየ ይፋ እየሆነ ነው።
ኢትዮጵያን በነጻ አውጪ ስም እየመራ ያለው ህወሃት በራሳቸው በአሜሪካኖቹ ቋንቋ ‘አሸባሪን መዋጋት’ በሚል ሰበብ ምዕራባውያንን ሲያልባቸው ቢቆይም “ሽብርንና ሽብርተኛነትን የመታገል ትብብር ግን የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመርገጥ ፍቃድ ማግኛ አይደለም። የመብት ረገጣ ሽፋን ሊሆን አይገባም” ሲሉ በጀርመን ሬዲዮ የመረረ ንግግር ንግግር የተናገሩት እንደራሴ ስሚዝ “ዛሬ አሜሪካ አቋሟን የምትፈትሽበት ጊዜ ላይ ነች” በማለት ከሁለት ወር በፊት የተናገሩትን ከዳር ያደርሱት ይሆን የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያገኝበት ወቅት ተደርሷል፡፡

የቃሊቲ እንግልት፤ – ከግርማ ሠይፉ ማሩ


ጎበዝ እንግዲህ እዚህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጉድ ሳይሰማ አይታደርም አይደል፡፡ ዛሬ ከአቤል አለማየሁ ጋር አንዱዓለም አራጌን እና ርዕዮት ዓለሙን እንጠይቅ ተባብለን ወደ ቃሊት ወረድን፡፡ ለዛሬው የነበረን ዕቅድ ሁለቱን ብቻ የማየት ነበር፡፡ ለዚህም እንዲሆን በቂ የሚባል ሰዓት ይዘን ልክ ከቀኑ አምሰት ሰዓት ላይ ቃሊት በር ደረሰን፡፡ በቅርቡ ቃሊት የሚገኙትን ወዳጆቻችን ለመጠየቅ የተለሳለስ ሁኔታ መኖሩን በአገኘሁት አጋጣሚ የገለፅኩ ሲሆን ይህንኑ ሃሳብ ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ለአንድነት ብሔራዊ ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ ገልፀውት ነበር፡፡ ምሰጋናችን አንድ ሳምንት ሳይሞላው እብድ ይሻለዋል እንጂ አይደንም እንደሚባለው ሆኖ አገኘነው፡፡
ዛሬ (ሐሙስ ሐምሌ 25) ቃሊት በሩ ላይ ስንደርስ አንድ አንድ ነገር እንግዛ በሚል ቆም ባልንበት አጠገባችን ያሉት ዘቦች እኔን እየተመለከቱ ሲጠቃቀሱ ተመለከትኩ፣ ውይይቱን ያስነሳው በበሩ ላይ የቆመው ባለ አንድ ኮከብ ማዕረግ ባደረገ በአሁኑ አጠራር ረዳት ኢንስፔክተር (በቀድሞ ምክትል የመቶ አለቃ) ነው፡፡ ባደረገው ማዕረግ ልክ ግን ያልሆነ ሰው ነው፡፡ በሚያደርገው ነገር እምነት እንደሌለው የሚያሳብቀው ንግግሩ ብቻም አይደለም ሰሙን ለመናገር ፈቃደኛ አይደለም፡፡ ማነኛውም የመንግሰት ሰራተኛ አገልግሎት ሰጪ ሙሉ ስሙን በግልፅ መፃፍ እንደሚጠበቅበት ግልፅ ነው፡፡ ይህ ባለ ማዕረግ ግን ይህንን አለማድረጉ ብቻ ሳይሆን ሲጠየቅ ስሙን ለመናገር ድፍረት የለውም፡፡ እንግዲህ ለዚህ ነው ኮኮብ ማዕረግ በትከሻው ላይ የተደረገለት እና ለዚህም በሚል ደሞዝ የሚቆረጥለት፡፡ በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ሁኔታ ከዚህ ከፍ ያለ ማዕረግ ያለው እሼ ግደይ (በቅፅል ስሙ ሻቢያ) የሚባል ሰሙን አልናገርም ብሎ ህዝብ በተሰበሰበበት ተሳድቦ፣ ይህ ስድብ እኔን ሳይሆን የምክር ቤቱን ክብር የነካ ነው ብዬ ከስሼው ነበር፡፡ በኋላ ላይ የምክር ቤት አባል መሆናቸውን አልተናገሩም እንዳውም ተሳድበዋል የሚል ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል በሚያስብል መልኩ መከላከል ጀምሮ ነበር፡፡ የዛሬው ረዳት ኢንስፔክተር አልተሳደቡም ሰደበኝም አላሉም በዚህ አደንቃቸዋለሁ፡፡
ወደ ዝርዝር ድራማው ከመግባቴ በፊት ግን አንድ ነገር ማለት ያለብኝ ይመስለኛል፡፡ የተገልጋዩን መታወቂያ እያገላበጡ የሚያዩ አገልጋይ ነን እያሉ የሚመፃደቁ ሁሉ በህግ አምላክ ስማችሁን ቢቻል ከነፎቶ የሚገልፅ ነገር በደረታችሁ ላይ አድርጉልን፡፡ ይህን የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ በአሰቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ያድርግልን እላለሁ፡፡ እዛው በምዝገባ ላይ ከነበረች ረዳት ሳጅን (ሰሜ አስቴር ነው ብላኛለች) እንደሰማሁት ባጁ አለ የሚል ነው፡፡ ከፍተኛ የመንግሰት ሀብት ወጥቶበት ከተዘጋጀ በኋላ ለምን እንደማይደረግ ግን መልስ እንፈልጋለን፡፡ በነገራችሁ ላይ በደርግ ጊዜ ፖሊሱ ሁሉ የመለያ ቁጥር በደረቱ ላይ ያደርግ ነበር፡፡
ከላይ እንደገለፅኩላችሁ ሲጠቃቀሱ የነበሩት ዘቦች ጋ ጠጋ ብዬ በቀልድ ዓይነት ልክ ናችሁ በቴሌቪዥን የምታዩኝ ግርማ ነኝ ብዬ ተቀላቀልኳቸው፡፡ መዋሸት ጀመሩ እኛ ሰለአንተ አልተነጋገርንም ብለው በአድማ ዋሹ፤ ችግር የለም ብዬ መንጃ ፍቃድ ሰጠዋቸው ስሜን ተመልክተው እርግጠኛ ከሆኑ በኋላ የቀበሌ መታወቂያ አምጣ አሉኝ፤ ለምን? አልኳቸው፣ በዚህ አናስገባም፡፡ ሌላ ጊዜ በዚህ ነው የምገባው ብል የሚሰማኝ አጣው፡፡ ደግነቱ መኪናዬ ውስጥ የቀበሌም የምክር ቤትም መታወቂያ ስለያዝኩኝ ሄጄ አምጥቼ ይህው የቀበሌ መታወቂያ ብዬ ሳሳይ አማረልኝ ያለች አንዷ ገብቶሃል ቁጭ በል የሚል ትዕዛዝ ሰጠችኝ፣ አልገባኝም፣ ስላት በሚገባህ ቋንቋ ይነገርሃል ብላ ተናግራ ልታናግረኝ ዘለግ ካለም ልታስፈራራኝ ስትፈልግ፣ የምችለው ቋንቋ አማርኛ ነው ከዚህ ሌላ ካለሽ አምጭ አልኳት፡፡ አታካሮው በዚህ አበቃ ይህች ሴት በዛው ሄዳ ቀረች፡፡ ከጀርባ ሄዳ እሼ ግደይ (ሻቢያ) እንዳደረገው ልትከሰኝ ማለት ነው፡፡ ይህ አካሄድ ተቋማዊ እንደሆነ የገባኝ በኋላ ነው፡፡
እኔም በረዳት ኢንስፔክተሩ ትዕዛዝ መሰረት ሰልክ ተደውሎ እስኪፈቀድ ቆይ ተባልኩ፣ እሺ ብዬ ቁጭ ብዬ ስጠብቅ ለ45 ደቂቃ ቆየው፡፡ በዚህ ቆይታዬ አጠገቢ ካለው ኢንስፔክተር ጋር ለምን ሰሙን እንደማይነግረኝ፣ ይህ ደግሞ ተገቢ እንዳልሆነ፣ እየነገርኩት እርሱም ባይለጠፍ ችግር እንደሌለው ሲያስረዳኝ ቆይቶም ሲሰለቸው እንደሚያጣራ ሄዶ ሲጠፋ ጊዜውን ገደልነው፡፡ በመሃሉ ሌሎች ተሰተናጋጆች መጥተው ሲገቡ ሲወጡ እያየሁ አንድ ጥያቄ ጠየኩት ለምንድነው መንጃ ፍቃድ አይሆንም ያልከኝ? እዚህ ቁጭ ብዬ በመንጃ ፍቃድ ሌሎች እየገቡ አይቻለሁ አልኩት፡፡ እዚህ ድረስ መጥተው ሰዎች እንዳይጉላሉ ነው ብሎኝ አረፈው፡፡ የምክር ቤት አባል አጉላሉ ተብላችኋል ወይ? ብዬ ያልጠበቀውን ጥያቄ ዱብ ሳደርግ አጠገቤ የነበረችው መዝጋቢ ሳጅን አይደለም እኔ አላውቅህም እነርሱ ግን ስላወቁ የሚያጠሩት ነገር እስኪያጣሩ ብሎ ነው ተወው ብላኝ ቅድም ስለ አንተ አልተነጋገርንም ብለው የዋሹትን አጋለጠች፡፡ እኔም በዚሁ አበቃው፡፡ ድንገት ሌላ ሴት መጥታ በዋናው በር ይሂዱ! አይናደዱ ብላኝ ወደ ዋናው በር አመራሁ፡፡ በሩ ጋ ስደርስ፤
• ወዴት ነው? የሚል ጥያቄ በአንድ ታዛ ስር ያለች ሴት ፖሊስ አቀረበችልኝ፡፡
• እስረኛ ልጠይቅ፡፡
• በዚህ ነው የሚጠየቀው? ብላ ስትጠይቀኝ
• በመጠየቂያው በኩል በዚህ ሂድ ተብዬ ነው ብዬ መለስኩ፡፡
• ለምን?
• ለምን እንደሆነ የሚያውቁት ወደዚህ እንድሄድ የላኩኝ ናቸው፡፡ በዛ በኩል ተከለከልኩ በዚህ እንድሄድ ታዘዝኩ፡፡
• አትናደድ ከተናደድክም እዚሁ ጨርስና ትገባለህ ብላኝ እንደገና ታናድደኝ ገባች፡፡
አሁን እንግዲህ ሌላ እላፊ ቃል እንዳትናገር በሚል የምክር ቤት አባል መሆኔን የሚያሳይ መታወቂያ ሰጠኋት መታወቂያዬን ይዛ ወደ ውስጥ ገባችና ተመልሳ መጥታ ይግቡ አለችኝ፡፡ ውስጥ ስገባ ወደዚህ ወደዚህ ብለው አንድ ዘብ መድበው ከአንዱዓለም ጋር አገናኙኝ፡፡ እውነት እላችሁ አለው ከአንዱዓም ጋር ብዙ መጫወት አልቻልንም፡፡ ርዕዮትንም መጠየቅ ሰዓት ረፈደ፡፡ እንደዚህ አድርገው አዋክበው ስልችቶን እንድንቀር፣ ጠያቂ አጣው ብሎ አንዱዓለምን ተስፋ እንዲቆርጥ ነው እቅዱ፡፡ ከአንዱዓለም ጋር የምናወራውን የሚያደምጠው ዘብ መውጣት ስለምፈልግ ከመውጣቴ በፊት ግን የተቋሙን ኃላፊ ማግኘት እፈልጋለሁ፣ ዝም ብዬ ከዚህ ግቢ አልወጣም ስለው ደውሎ ሐጎስ የሚባል ስው ጠራላኝ፡፡
እኔ ቢሮ ውስጥ ሆኜ በስርዓቱ ነበር መነጋገር የፈለኩት፡፡ አንዱዓለም እንዲገባ ተደርጎ እዛው በቆምኩበት ለምን እንደዚህ እንደሚደረግ ቢቻል በክብር ካልተቻለ እንደ ዜጋ ለምንድነው የማልስተናገደው የሚል ጥያቄ አቀረብኩለት፡፡ በር ላይ ያሉት አሰተናጋጆች የምክር ቤት አባላት እንዴት እንደሚስተናገዱ ስለማያውቁ ነው፡፡ እኛ በስነ ስርዓት ለማስተናገድ ብለን የበላይ አካል ጠይቀን ነው የምናስገባው (ልብ በሉ የበላይ አካል ጠይቀን የሚለውን) አቶ ግርማ እርሶ ያውቃሉ ለምን እንደታሰረ፣ እርሶም ትንሽ ትዕግሰት ቢያደርጉ ጥሩ ነው በር ላይ ካሉ ሰዎች ጋር ለምን ይጨቃጨቃሉ፡፡ ይቅር ብለን ነው እንጂ ስብዕናዬን ነክቶኛል ብለው አቤት ብለዋል ብሎ አረዳኝ፡፡ እሺ (ሻቢያ ትዝ አለኝ) ሰዎቹ ይጠሩ አልኩና ተጠርተው መጡ (በር ላይ በሚገባህ ቋንቋ ብላ የተሰወረችው ዘብና መግቢያ ላይ እትናደድ እያለች የማላቀውን ጥያቄ ስትጠይቀኝ እና ስታናድደኝ የነበረች ብዙዬ የምትባል ሴት መጡ)፣ ምን እንዳደረኩ ሲጠየቁ ሲናገሩ ይቆጣሉ ወደሚል ዝቅ ብሎ እነርሱን አሰናበታቸውና ከዛሬ ጀምሮ እስረኛ ለመጠየቅ ሰመጣ ሐጎስ ብዬ በዋናው በር ብቻ እንድመጣ በዚሁ መሰረት እንደ ምክር ቤት አባል ወንበር ተዘጋጅቶልኝ እንደምስተናገድ መመሪያ ተሰጠኝ፡፡
የዛኑ ዕለት ሪፖርት ጋዜጣ ላይ ክቡር ሚኒስትር በሚል ርዕስ ስር ያነበብኩት ትዝ አለኝ፡፡ ተጠሪ ወደ አልሆኑበት ተቋም እየደወሉ የስራ መመሪያ የሚቀበሉ፣ በማያገባቸው ገብተው መመሪያ የሚሰጡ እንዳሉ በፌዝ አድርጎ ይነግረን ነበር፡፡ የቃሊቲ የበላይ አካል ማን ነው? ይህ ስው ከቃሊት ተደውሎለት የተከበሩ አቶ ግርማ ሠይፉ መጥተዋል እናስገባቸው? ወይስ አናስገባቸው? ተብሎ የሚጠየቀው ከውጤቱ እንደተረዳሁት ይህ ሰው የሰጠው መልስ አስገቧቸው ግን አጠገባቸው ሰው መድቡና ምን እንደሚያወሩ አድምጡ ነው የሚለው፡፡ ይህ ምን ያህል ውርደት እንደሆነ ለሚያዘውም ለሚታዘዘውም ግልፅ ይመስለኛል፡፡ ሌላው ሐጎስ ያለኝ በምን እንደታሰረ ታውቃለህ ነው ያለኝ፡፡ አዎ አውቃለሁ አንዱዓለም ሲሰርቅ፣ ቦንብ ሲያፈነዳ አልተያዘም ባለው የፖለቲካ አቋም እንደታሰረ እና የፖለቲካ እስረኛ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው ከአምስት ሺ እስረኛ በተለየ ሁኔታ አንዱዓለምን ልንጠይቅ የምንታገደው፡፡ ሐጎስ ግን አንዱዓለም ይህን ጥያቄ ሲጠይቀኝ ምን አስቦ ይሆን፡፡ አንዱዓለም አሽባሪ ነው ብሎ አያምንም፡፡ ለነገሩ የማረሚያ (ለእነ አንዱዓለም እስር ቤት) ስራው የመጣለትን እስረኛ መጠበቅ ብቻ ነው መሆን ያለበት እንጂ ለምን እንደመጡ ማወቅ ያለባቸው አይመስለኝም፡፡ እረ በህግ፣ መታሰራችን አንሶ መጠየቅ ስንከለከል፣ ወይም መጎላላት ሲደርስብን ወዴት ነው ልትገፉን የምትፈልጉት? ብለን ለመጠየቅ ግድ ይለናል፡፡ የኢትዮጵያ ህገ መንግሰት አንቀፅ 21 በጥበቃ ስር ስላሉ ዜጎች ግልፅ ድንጋጌ አለው፡፡ ከዚህ በተፃራሪ የተፃፈ ህግ፣ መመሪያ ደንብ፣ ወዘተ ህገ መንግሰቱን እንደመናድ ይቆጠራል፡፡ ከሳሾቻችን ህገ መንግሰቱን ስለ ማክበርና ማስከበር በህገ መንግሰቱ አንቀፅ 9 ማንበብና ተግባራዊ ማድረግ ግድ ይላችኋል፡፡
ethiopforem

Thursday, August 1, 2013

ESAT Daliy News Amsterdam August 01 2013 Ethiopia


የሳውዲዋ ልዕልት የመብት ገፈፋ ክስና የኢትዮጵያዊቷ ጉብል አበሳ . . .

ነቢዩ ሲራክ (የማለዳ ወግ. . . )
princess


የሳውዲ ንጉሳውያን ቤተሰብ አባል የሆኑት የ42 አመት እመቤት በምድረ አሜሪካ በቤት ሰራተኛቸው መብት ገፈፋ ተከሰው ለፍርድ ቀርበዋል። ልዕልቷ ኬንያዊዋን የቤት ሰራተኛቸውን በአነስተኛ ክፍያ ከ16 ላላነሱ ሰአታት በመክፈል እና የኬንያዊቷን ሰራተኛ ፖስፖርት ለባለቤቷ ባለመስጠታቸው ተከሰው በምድረ አሜሪካ ለወህኒ ከተዳረጉበት በ5 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ቢፈቱም ዛሬም ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ሰምተናን። ይህንን ዜና ሳነብ ያን ሰሞን ” ጋዜጠኛ ነህ አሉ እርዳኝ? ” ብላ ከወደ ደማም በተንቀሳቃሽ ስልኬ እየደወለች የምታነባዋ ኢትዮጵያዊት እህት ፍዳ አስታወስኩ !
ዛሬ ረፋዱ ላይ ያነጋገርኳት ይህች እህት የሚደርስባት ግፍ ሳያንስ የተሰደደች የምትገፋበትን የወር ደመወዟን ላለፉት በርካታ ወራት እንዳልተሰጣት ገልጻልኛለች ። ዛሬ በጣሙን ከፍቷት እያለቀሰች ከገባችበት ስቃይ እታደጋት ዘንድ ተማጽናኛለች! አቅሙ ኖሮኝ ምንም ልረዳት ባልችልም አበሳዋን ግን እነግራችኋለሁ! ይህች ግፉዕ ደራሽ ያጣችው እህት በኮንትራት ከኢትዮጽያ ከመጣች አመት የደፈነችው በያዝነው ወር መሆኑን ገልጻልኛለች። ከመጣች ቀን አንስቶ ለ16 ላላነሱ ሰአታት እንድትሰራ ስትገደድ ግልምጫ እርግጫና ስድቡን ችላ እንዳሳለፈች እያሳልፈችው ቢሆንም የማትቋቋመው ፈተና ገጥሟታል! የጋብቻ ቃል ኪዳን አስራ ሰርታ ራሷን ለመለወጥ የመጣችው እህት በአሰሪዎቿ ቤተሰቦች ጥቃት ተማራለች! ሚስት በቅናት ተነሳስታ ቁም ስቅሏን የምታሳያት ሳይበቃ የአሰሪዎቿ ሁለት ጎረምሳ ልጆች በየተራ ” እንድፈርሽ !” ብለው የሚያደርሱባትን ትንኮሳ መቋቋም አለመቻሏን እንባ እያዘራች ምርር ብላ እያለቀሰች አጫውታኛለች !
ይህች እህት ወደ ፍትህ አካል የሚያቀርባት ፣ ከገባችበት የመከራ ህይዎት የሚገላግላት የመብት አስከባሪ አካላት አጥታለች ። ኤጀንሲዋን አነጋግራ ” በርረሽ ወጥተሽ እጅሺን ለፖሊስ ስጭ!” ከማለት ያለፈ መፍትሔ አልሰጧትም። አጣብቂኝ የገባችው እህት መፍትሔ ታገኝ ዘንድ የሪያድ ኢንባሲ ሃላፊዎችን ተንቀሳቃሽ ስልክ ሳይቀር ሰጥች ለማረጋጋት የሞከርኩት ቢሳካም ወደ ሃላፊዎች ስልክ ደውላ ከችግሯ ይታደጓት ዘንድ ብትማጸናቸውም ተስፋ ከመስጠት አልፈው የሰሩት ስራ አለመኖሩን እንባ እያዘራች ስታጫውተኝ አሁን አሁን የኢንባሲው ሃላፊዎች ስልክ ስትደውል እንኳ ሊመልሱላት እንዳልቻሉ አጫውታኛለች ። እኔ እስከ ዛሬ ረፋዱ ድረስ ሃላፊዎችን ደውየ ለማነጋገር ያደረግኩት ሙከራ ስልካቸውን ስለማያነሱ ጥረቴ አልተሳካም !
ይህን ግፍ የሳውዲ ህግና መንግስትም አይደግፈውም! ይህ መሰሉን ግፍ በሰራተኛ ላይ መፈጸም ከባድ ቀጣት ቢኖረውም ህግ ፊት የሚያቀርባት ቀርቶ ከገባችበት መቀመቅ የሚያወጣት የሃገሯ ተወካዮችን አጥታ ኑሮን በመከራ እየገፋች መሆኑን ባደረግነው ውይይት ተረድቻለሁ! የሚያሳዝነው ይህች እህት ከዚህ ሁሉ ጭንቀት በኋላ ምን ልትሆን እንደምትችል አላውቅም! ግፉ ከቀጠለ በሚፈጠር ግጭት ምን ሊፈጠርባት እንደሚችል መገመት ይከብዳል! ጎረምሶቹ በጉልበት እንድረፈርሽ ሲሏትም ሆን ሚስት በቅናት ተነሳስታ በምታደርገው የመልስ ጥቃት እንድትጠነቀቅ አበክሬ ከመምከር ባለፈ ምንም ማለት አልቻልኩም! የሳውዲዋ ንግስት ፈጸመችው በተባለው እኛ የአረብ ሃገር ነዋሪዎች መብት ረገጣውን ለምደነው “እዚህ ግባ የማይባል !” የምንለው ጥፋት በነጻዋ አሜሪካ መድር መብት ነክተዋልና ቁም ስቅላቸውን እያዩ ነው ፣ የእኛዋ እህት ደግሞ የግፍ ግፍ እየተፈጠረባት የሃገሯ መንግስ ተወካዮች እንኳ ድረሱልኝ ተብለው ተጠርተው ሊደርሱላት ባለመቻላቸው በሳውዲ ምድር አበሳዋን እያየች ትገኛለች ! የነገን ግን እንጃ. . .
ለሁሉም እኔ ያየሁ የሰማሁትን ተናግሬያለሁ ! ጀሮ ያለው ይስማ . . .!
ቸር ያሰማን !

የወያኔ “የድህነት ቅነሳ ፓሊሲ” ለድሀው – “ላም አለኝ በሰማይ …”

ከወያኔ አሰልቺ ዲስኩሮች አንዱ “ልማት” በተለይም “ድህነት ቅነሳ” ነው። ወያኔ ስለ ፈጣን ልማትና ስለ ድህነት ቅነሳ ሲነገረን እነሆ ሁለት አስርታት አለፉ!!!
እርግጥ ነው ወያኔ የራሱን አባላት ድህነት ቀንሷል። የሌላው ኢትዮጵያዊ ድሀ ድህነት ግን እየጨመረ ነው። ያም ሆኖ ግን ወያኔ የራሱ ሹማምንት ከሕዝብ በዘረፉት ገንዘብ የገነቧቸውን ፎቆች እያሳየን “እነሆ ልማታችሁ” እያለ ይሳለቅብናል። በውሸቱ የተሞሉ የምርት መጠንና ምርታማነት መስፈርቶችን እያስነበበን እየራበን “ጠገብን”፤ እየታርዝን “ለበስን” እንድንል ያደርገናል። “ኮንዶሚኒየም አድላለሁ” እያለ እያጓጓን ያችኑ ትንሿ ጥሪታችንን ይነጥቀናል።
ወያኔ በልማት ስም ምን ያላደረገን ነገር አለ? ትምህርት ሳይኖር ዲግሪ እያሸከመ ቀልዶብን ዲግሪ ይዘን ለኮብልስቶን ማንጠፍ ሥራ ተወዳድረናል። ህክምና ሳይኖር በክሊኒኮች መብዛት ተደስታችሁ ጨፍሩ ብሎናል። በጨለማ ውስጥ ተቀምጠን ስለግድቦች መብዛትና ስለ መብራት ኃይል ምርት መትረፍረፍ መስክሩ ይለናል።
ስንቶቻችን ነን የዕለት ተዕለት ኑሮዓችን እና የወያኔ የልማት ዲስኩሮች አልጣጣም እያሉን የተቸገርነው? ፈረንጆችም እነዚያኑ የወያኔ ቁጥሮችን መልሰው ሲነግሩን ስንቶቻችን ነው ከቁጥሮች ጋር የተጣላነው? የወያኔ ልማት፤ የወያኔ ድህነት ቅነሳ ፓሊሲ “ላም አለኝ በሰማይ፤ ወተትዋን እማላይ” የሆነብን ስንቶቻችን ነን?
ወያኔ ሰጠኋቸው በሚለው ሳይሆን እኛ በበላነውና በለበስነው፣ ባገኘው የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች ኑሮዓችን ቢለካ ደረጃችን የት ይሆናል? በሚነገረን ሳይሆን በምንኖረው መጠን ትዳራችን ቢለካ ደረጃችን የት ነው?
ከድህነት መለኪያዎች ሁሉ የተሻለና የተሟላ ነው የሚባለው በእንግሊዝኛ Multidimensional Poverty Index የሚባለው ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ነው። ይህን መለኪያ ሰዎች በእርግጥ ባገኙትና በተጠቀሙት ምርትና አገልግሎት መጠን ይነሳል። ሌሎች የድህነት መለኪያዎች መንግሥት አመረትኩ ወይም ሰጠሁ በሚለው ቁጥር ነው የሚነሱት። ውሸት በማይበዛባቸው አገራት በዚህም ተለካ በዚያ እጅግም ለውጥ የለውም። እኛጋ ግን ልዩነቱ የትየለሌ ነው።
ወያኔ የሚወዳቸው መለኪያዎች መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ልንገባ መቃረባችንን ይነግሩናል። እነሱ መሠረት ያደረጉት ወያኔ አመረትኩ፣ ሰጠሁ የሚለውን ነው። ኑሮዓችን እኛ የተቀበልነው መሠረት በሚያደርገው ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ሲለካ ግን ውጤቱ ፈጽሞ ሌላ ነው።
የ2013 የአውሮፓውያን ዓመት የዓለም ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ ስታትስቲክስ ባለፈው ሣምንት ይፋ ተደርጓል። ዘገባው እንደሚያሳየው የዓለማችን የመጨረሻዎቹ አስር ድሀ አገሮች በሙሉ አፍሪቃ ውስጥ ነው ያሉት። ከእነዚህ የመጨረሻ አስር ድሀ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ አገራችን ናት።
አሳዛኙ ዜና ይህ ብቻ አይደለም።
ከአስሩ የመጨረሻ ድሀ አገሮች የመጨረሻዋ ኒጀር ስትሆን ከዚያ ቀጥላ የምትመጣው ኢትዮጵያ ነች። በሌላ አነጋገር ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ የመጨረሻ ድሀ አገር ናት። በድህነት ለኢትዮጵያ የባሰች አገር ኒጀር ብቻ ነች። ጅቡቲ እና ደቡብ ሱዳን ብቻ ሳይሆን ሶማሊያ እንኳ ከእኛ በተሻለ ሁኔታ ላይ ነው ያለችው።
ይህ ምንን ይነግረናል?
በወያኔ ቴሌቪዥን የሚቀርብልን ማዕድ ምግብ አይሆነንም። ጆሮዓችን እስኪደነቁር “ልማት፤ ልማት” እየተባለ ስለተጮኸብን ማጀታችን አይሞላም። መራብና መታረዛችን ሳያንስ “ጠግባችኋል” እየተባለ የሚቀለድን መሆኑ በእጅጉ ያሳዝናል። እኛ እየተራብንና እየታረዝን ባዕዳን ቱጃሮች በመሬታችን ላይ በሀብት ላይ ሀብት የሚጨምሩ መሆኑ ያስከፋናል። እኛ በጨለማ ተውጠን የመብራት ኃይል የሚሸጥ መሆኑ ይቆጨናል።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ሳንበላ በጥጋብ እንድናገሳ፤ ደሳሳ ጎጆዓችን እየፈረሰ “ልማት መጣ” እያልን እንድንጨፍር፤ በጨለማ እየኖርን ለግድብ መዋጮ የምንገፈግፍ ምስኪኖች ሆነናል።
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በድህነታችን ላይ መጫወቱ መቆም አለበት ይላል። ግንቦት 7: “መሮናል፤ ከፍቶናል። ወያኔን ከነውሸቱ ልናወስግድ ተነስተናል። ለወያኔ የውሸት “ድህነት ቅነሳ” ጆሮዓችንን አንስጥ። ይልቁንም ወያኔን አስወግደን የመልማት እድላችንን በእጃችን እናስገባ፤ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት ሲኖር ደግሞ የውሸት ሳይሆን የእውነት እንደምንለማ ባለሙሉ ተስፋዎች ነን” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!

በጦር ሀይሎች፤ጎጃምበረንዳ እና ሌሎች አካባቢዎች ሙስሊሞች በፖሊስ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ነው፡፡

ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሙስሊሞች በፖሊስ እየታፈሱ ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ነው፡፡
በዛሬው እለት በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ቅጥራው በውል ያልታወቁ ሙስሊሞች በፖሊሶች እየታፈሱ እንደሆነ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
የረመዳንን ወር ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ በመደረጉ የተደናገጠው መንግስት የነገውን ተቃውሞ ለማኮላሸት በዛሬ ምሽት ብዛት ያላቸውን ወንድሞቻችን እያፈሰ ወደ እስር ቤት እያጎረ ይገኛል፡፡
በጦር ሀይሎች፤ጎጃምበረንዳ እና ሌሎች አካባቢዎች ወንድሞቻችን እየጣፈሱ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ሙስሊሙ ህብረተሰብ ይራሱን ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ እናሳስባለን፡፡
እስር፤ድብደባ ከሰላማዊ ተቃውሟችን ንቅንቅ አያደርገንም !!
አላህ(ሱ.ወ) ከወሰንብን ውጪ የሚደርስብን አናዳችም ነገር የለም!!!!!!
አላሁ አክበር

Breaking News Aug 01, 2013