የህወሓቶች ዋነኛ አከራካሪ አጀንዳ የት.እ.ም.ት ጉዳይ ሁነዋል። ትእምት ማን ይምራው? እንዴት ይተዳደር? የተፈጠረ ችግር እንዴት እንፍታው? … ወዘተ የሚሉ ጉዳዮች እያከራከሩ ነው። ከስብሰባው በኋላ በትእምት የስራ አመራር ለውጥ እንደሚኖር ተገምቷል።
የህወሓቶች ስብሰባ ከተጠናቀቀ በኋላ የሌሎች የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች ስብሰባ ይከተላል። ከዛ የአጋር ድርጅቶች፤ ቀጥሎም የአምባሳደሮችና የመንግስት ተወካይ ባለስልጣናት ስብሰባ ይካሄዳል።
ኢህአዴጎች አጠቃላይ የመንግስት አደረጃጀት ለውጥና የባለስልጣናት መቀያየር ለማድረግ አቅደዋል።
ኢህአዴግና ስብሰባ የ አንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ። እኔ ደግሞ ስብሰባ ሲደብረኝ!
No comments:
Post a Comment